cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ፈለገ ሰላም ሰ/ት/ቤት

ይህ የቤላ ፈለገ ሰላም መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን ፤ፈለገ ሰላም ሰ/ት/ቤት ገፅ ነው ። በዚህ ገፅ ፦ 👉 መንፈሳዊ ትምህርቶች ፣ መልዕክቶች ፣ ምክሮች 👉 መዝሙሮች ፣ ኪነጥበባዊ ዝግጅቶች 👉 ወቅታዊ የቤተክርስቲያን እና የሰ/ት/ቤት ጉዳዮች 👉የሰ/ት/ቤት መልዕክቶች ፣ ማስታወቂያዎች ይቀርቡበታል። ቤተ መጻሕፍትና ሚዲያ ክፍል ለመቀላቀል ➠ @felegeselam1

Show more
Advertising posts
591
Subscribers
-124 hours
-27 days
-430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿 #ሰው_እንደ_ዘር_ነው 🔖አባቶቻችን ሊቃውንት ሰው እንደ ዘር ነው ይላሉ። ሰው እንደ ዘር ነው ማለት ዘር ተዘርቶ የሚያድገው በሁለት መሠረታዊ ነገር ነው። በብርድ እና በጸሐይ። ዘር ዝናምና ጸሐይ ያስፈልገዋል። ዝናም ብቻ ከሆነ ሽባ ይሆናል ጸሐይ ብቻም ከሆነ ይደርቃል። 🔖ሰውም እንደ ዝናሙ የእግዚአብሔር ቸርነት ያስፈልገዋል፤ እንደ ጸሐዩም መከራ ያስፈልገዋል። ዘር በዝናሙ እየለዘበ፣ በጸሐዩ እየበሰለ እንደሚያድገው ሁሉ ሰውም በመከራ እየጠነከረ በተስፋና በእግዚአብሔር ቸርነት እየተጽናና ያድጋል። 🔖ሁልጊዜ የእግዚአብሔርን ቸርነት ብቻ ከሆነ የሚያስበው ሽባ ይሆናል። መከራ ባገኘው ጊዜ ወዲያው ተስፋ ይቆርጣል። ሃይማኖትን ሊክድ ይችላል። መከራ ብቻ ከሆነበት ደግሞ ወዲያው ደግሞ እንደዚሁ ተስፋ ቆርጦ ሊሠበር ይችላል። 🔖ስለዚህ ዘር ዝናምና ጸሐይ እንደሚያስፈልገው ሁሉ ሰውም መከራና የእግዚአብሔር ቸርነት ያስፈልገዋል። (#ርዕሰ_ሊቃውንት_አባ_ገብረ_ኪዳን) ✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿         ✨🌞ቶራ ሚድያ✨🌞 🏁 follow our sunday school media 📱 Youtube   ⬅️ click here 📱 Tiktok 📱 Instagram              አብርሂ ፈለገ ሰላም  ✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥
Show all...
👍 1
✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿
✨"የፕሌቶን እና የሲሴሮን እጅግ ውብ ጥበብ የተሞሉ የፍልስፍና አባባሎችን አንብቤያለሁ፥ ግን ከጽሑፎቻቸው በአንዱ ስንኳ “እናንት ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ ወደ እኔ ኑ” የሚል ቃል አላነበብኩም።"     ቅዱስ አውግስጢኖስ
✨መንፈስ ቅዱስ በእኛ አድሮ የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ አድርጎን እውነተኛ አምልኮን ለእግዚአብሔር ማቅረብ እንድንችልየሚያደርገን፣ በእርሱም ከጥፋት ክልል ወደ በረከት ክልል እንለወጣለን። መንፈስ ቅዱስ ከክርስቶስ ጋር እንድንተባበርና ከመለኮታዊ ባሕርይ በጸጋ ተካፋዮች እንድንኾን ያደርገናል፣ በቅድስናና በእውነት መንገድ እንድንመላለስ ያስችለናል። ታላቁ ቅዱስ ቄርሎስ

✨መንፈስ ቅዱስ በክርስቶስ ውስጥ ለመኖር እንድንችል ኀይልን የሚሰጠንና ሕይወትን የሚሰጥ የእግዚአብሔር መንፈስ ነው። ያለ እርሱ ክርስቶስን መረዳትና በትክክል በእርሱ መኖር አይቻልም። እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን የላከልን እንዲያጽናናን፣ እንዲያበረታን እንዲኹም የክርስቶስ ትምህርቶችን መማር፣ መረዳትና መጠበቅ እንድንችል ነው። መንፈስ ቅዱስ የጌታችን የኢየሱስን ክርስቶስ ሕይወት በእኛ እንዲኖር ያስችለናል። ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ

✨“ዘወትር በዐይንህ ፊት ፈሪሃ እግዚአብሔር ይኑር፤ ሕይወትና ሞት የሚሰጠውን አዘክረው፡፡ ዓለምንና በዓለም ያለውን ሁሉ ጥላው፤ ከሥጋ የሚመጣውን ደስታና ሰላም አትሻ፤ ለዚህኛው ኑሮ ሙትና ለእግዚአብሔር ሕያው ሁን፤ ለእግዚአብሔር ቃል የገባኸውን አትርሳ፤ ያም በፍርድ ቀን ካንተ ይፈለግብሃል፡፡ ረኀብን በጸጋ ተቀበለው፤ ተጠማ፥ ተራቆት፥ ንቁና በሐዘን የምትኖር ሁን፡፡ በልቡናህ አልቅስና ጩኽ፤ ለእግዚአብሔር የምትመች መሆን አለመሆንህን ፈትን፤ ሥጋህን ቀጥተህ ነፍስህን ታድናት ዘንድ፡፡”     አባ እንጦንስ
✨"ያልተቀደሰ ጾም  የአጋንንት ጾም ይመስላል እነርሱ ከምግብ የተለዩ በክፋት ሥራ ግን የተጠመዱ ናቸው።" ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿         ✨🌞ቶራ ሚድያ✨🌞 🏁 follow our sunday school media 📱 Youtube   ⬅️ click here 📱 Tiktok 📱 Instagram                 አብርሂ ፈለገ ሰላም  ✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥           
Show all...
3
Photo unavailableShow in Telegram
✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿 ተከታታይ ትምህርት እንዳያመልጦ            ✨🌞ቶራ ሚድያ✨🌞 🏁 follow our sunday school media 📱 Youtube   ⬅️ click here 📱 Tiktok 📱 Instagram                 አብርሂ ፈለገ ሰላም  ✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥           
Show all...
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን!                       ሰላም ለእናንተ ይሁን! የተወደዳችሁ የዘንድሮው 12 ክፍል ተፈታኞች  እግዚአብሔር አምላክ ይርዳችው  እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም  ትግለጥላችው በርቱ ዮሐንስ አባታቸው ያገለገላችውት ይርዳችው በርቱ  እህት፤ ወንድሞቼ ፡፡ አምላካችን እግዚአብሔር  ከፊት ሆኖ ይምራችው ከፈተና በፊት ጸሎት አድርጉ ቅዱስ ዮሐንስ አባታችን ተክለሃይማኖት ያገዛች ከጥሩ ውጤት ጋር ተመለሱልን ሰንበት ትምህርት ቤታችን ፈለገ ሰላምን እግዚአብሔር ይጠብቅልን። የሰንበት ት/ቤቱ ጽ/ቤት!!
Show all...
🙏 9
Photo unavailableShow in Telegram
✨🌿ታላቅ የንግስ በዓል ጥሪ✨🌿         ✨ኑ በአብሮነት እናክብር✨
✍"ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ ደስታና ተድላም ይሆንልሃል በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል።" ሉቃ1÷4
        ✨🌞ቶራ ሚድያ✨🌞 🏁 follow our sunday school media 📱 Youtube   ⬅️ click here 📱 Tiktok 📱 Instagram                 አብርሂ ፈለገ ሰላም  ✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥           
Show all...
2
✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿 ✨እንኳን ለታላቁ "ነቢየና ሰማዕት ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ " በዓል በሰላም አደረሳችሁ✨✨ቅዱስ ዮሐንስ መጥመቅ✨✨ 🔖ቅዱስ ወንጌል ላይ ከእመቤታችን ቀጥሎ የነዘካሪያስን ቤተሰብ ክብሩ የተገለጠለት ፍጡር ይኖራል ብሎ መናገር ይከብዳል ቅዱስ ሉቃስ ወንጌሉን የጀመረው በዚህ ቅዱስ ቤተሰብ ነውና መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ሲል አጽፎታል " ሁለቱም በጌታ ትእዛዝና ህግጋት ሁሉ ያለ ነቀፋ እየሄዱ በእግዙአብሔር ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል። ሉቃስ1፥6 🔖የሰውን እንተውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ መኖር ምን ይረቅ?ለዚህ አንክሮ ምስጋና ይገባል እኚህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን ልጅ ሳይወልዱ እድሜአቸው አልፎ ነበር ቅድስት ኤልሳቤጥ እና ካህኑ ዘካሪያስ እንደ ቤተክርስቲያን ትውፊት ኤልሳቤጥ 90 ዘካሪያስ 100 ደርሶ ነበር እድሜቸው ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ በስተ እርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ ትንቢት ለብቻው የተነገረለት (ኢሳ 40፥3) የዐዋጅ ነጋሪ ቃል የእግዚአብሔርን መንገድ በምድረ በዳ ጥረጉ ለአምላካችንም ጎዳና በበረሐ አስተካክሉ የተባለለትን ታላቅ ነብይ ይሰጣቸውም ዘንድ መልአከ ብስራት ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው ቅዱስ ዘካሪያስ ሰው ነውና ከደስታ ብዛት ብዙ ከመከራከር ድዳ ሆነ ቅድስት ኤልሳቤጥም መስከረም 26 ቀን ታላቁን ነብይ ጸንሳ 6 ወራት እራሷን ሸሸገች በ 6ኛው ወር የፍጥረታት ሁሉ ጌታ በተጸነሰ ጊዜ የአርያም ሁሉ ንግስት እመቤታችን ወደ ቅድስት ኤልሳቤጥ ዘንድ መጣች እመቤታችን ወደ ዘመዷ ኤልሳቤጥ ደርሳ ሰላም ስትላቸው በእናትና ልጅ መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው ቅድስት ኤልሳቤጥ በምስጋና መጥመቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ደግሞ ገና በማሕጸን ሳለ በደስታ ዘለለ አምላኩንም በማህጸን ሳለ አመሰገነ ከዚህ በኃላ በዚህች ቀን ሰኔ 30 ተወልዶ አባቱ ካህኑ ዘካሪያስ "ዮሐንስ ሲለው አንደበቱ ተፈቶለታል። መጥመቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ✨የቅድስት ኤልሳቤጥና የካህኑ ዘካሪያስ ልጅ ✨በማሕፀን ሳለ መንፈስ ቅዱስ የሞላበት ✨በበረሐ ያደገ በገዳማዊ ቅድስና ያጌጠ ✨እስራኤልን ለንሰሀ ያጠመቀ ✨የጌታችንን መንገድ የጠረገ ✨ጌታውን ያጠመቀና ✨ስለ እውነት አንገቱን የተቆረጠ ታላቅ ቅዱስ ካህን፣ሐዋርያ ፣ሰማዕት ወንጌላዊ፣ባህታዊ፣ነብይ ነው የመጥመቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ረድኤት በረከት ምልጃ ፈውስ ከህዝበ ክርስቲያኑን ጋር ለዘለዓለም ጸንቶ ይኑር አሜን!            ✨🌞ቶራ ሚድያ✨🌞 🏁 follow our sunday school media 📱 Youtube   ⬅️ click here 📱 Tiktok 📱 Instagram                 አብርሂ ፈለገ ሰላም  ✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥           
Show all...
tora media on TikTok

@tora.media 1027 Followers, 0 Following, 6456 Likes - Watch awesome short videos created by tora media

✨🌿ታላቅ የንግስ በዓል ጥሪ✨🌿       ✨ኑ በአብሮነት እናክብር✨
✍"ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ ደስታና ተድላም ይሆንልሃል በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል።" ሉቃ1÷4
🔖የፊታችን  ቅዳሜና እሁድ (ሰኔ 29/30) የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ዓመታዊ ክብረ በዓል በደመቀ መልኩ ከዋዜማው ጀምሮ በደብራችን ቤላ ፈለገ ሰላም መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቤ/ክ ይከብራል። እርሶም በመገኘት የበረከቱ ተሳታፊ ይሁኑ!!!!            ✨🌞ቶራ ሚድያ✨🌞 🏁 follow our sunday school media 📱 Youtube   ⬅️ click here 📱 Tiktok 📱 Instagram                 አብርሂ ፈለገ ሰላም  ✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥           
Show all...
7
Show all...
ስንክሳር ዘወርኀ ሰኔ ፳፮

✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ       አሜን

Photo unavailableShow in Telegram
ሊቀ ማእምራን ብርሃኑ ተክለ ያሬድ ከዕሥር ተፈቱ! የደቡብና ምዕራብ አፍሪካ አህጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን ብርሃኑ ተክለ ያሬድ ከሁለት ወራት የዕሥር ቆይታ በኋላ በዕሥር በዛሬው ዕለት ተፈተዋል። ሊቃ ማእምራን ብርሃኑ ተክለ ያሬድ ሚያዝያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም ጠዋት 12:00 በፌዴራል ፖሊስ ለጥያቄ ይፈለጋሉ በሚል ከቤታቸው ተወስደው መታሠራቸውን መዘገባችን ይታወሳል። ©ሰኔ 25 ቀን 2016 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)
Show all...
Show all...
ስንክሳር ዘወርኀ ሰኔ ፳፭

✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ       አሜን

Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.