cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ፈለገ ሰላም ሰ/ት/ቤት

ይህ የቤላ ፈለገ ሰላም መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን ፤ፈለገ ሰላም ሰ/ት/ቤት ገፅ ነው ። በዚህ ገፅ ፦ 👉 መንፈሳዊ ትምህርቶች ፣ መልዕክቶች ፣ ምክሮች 👉 መዝሙሮች ፣ ኪነጥበባዊ ዝግጅቶች 👉 ወቅታዊ የቤተክርስቲያን እና የሰ/ት/ቤት ጉዳዮች 👉የሰ/ት/ቤት መልዕክቶች ፣ ማስታወቂያዎች ይቀርቡበታል። ቤተ መጻሕፍትና ሚዲያ ክፍል ለመቀላቀል ➠ @felegeselam1

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
595
المشتركون
+324 ساعات
+77 أيام
+1830 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿 ሥርዓተ ማኅሌት ዘትንሣኤ ✨ቶራ ሚድያ✨ 🏁 follow our sunday school media 📱 Youtube   ⬅️click here 📱 Tiktok 📱 Instagram ©መዝሙረ ማኅሌት    ✨አብርሂ ፈለገ ሰላም✨  ✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈•✥
إظهار الكل...
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት 2016 ዓ.ም በዓለ ትንሣኤን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ። ሚያዝያ 26 / 2016 ዓ.ም (ፍ.እ.ሚ./አዲስ አበባ)
إظهار الكل...
እናደርግ ዘንድ መንፈሳዊ ጥሪያችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፤ በድጋሚ በዓሉን የሰላም የዕርቅ የይቅርታ የትንሣኤ ኀሊና ወልቡና ያድርግልን! እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!! ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!! ኣሜን። አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ሚያዝያ ፳፯ ቀን ፳፻፲ወ፮ ዓ.ም አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
إظهار الكل...
ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ትንሣኤሁ ለእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘዕሥራ ምእት ዐሠርቱ ወስድስቱ ዓመተ ምሕረት፡፡ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን • በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ • ከህገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ በሕመም ምክንያት በየፀበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፤ እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ሁሉ- የትንሣኤ ሙታን በኵር በመሆን ቀድሞ የተነሣው አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለሁለት ሺሕ ዐሥራ ስድስት ዓመተ ምሕረት በዓለ ትንሣኤ በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ “ወይእዜኒ ክርስቶስ ቀደመ ተንሥኦ እምኵሎሙ ሰብእ ሙታን፡ አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት ሁሉ በኵር ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል” (፩ ቆሮ ፲፭፥፳) በዛሬው ዕለት በከፍተኛ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት የሚከበረው የጌታችን ትንሣኤ ለስው ልጅ ያለው መንፈሳዊ ትርጉም አጅግ የላቀ ነው፤ እግዚአብሔር ፍጥረታትን በሙሉ በተለይም የሰው ልጅን ሲፈጥር በፍጹም ፍቅር ነው፡፡ ለዚህም የሰው በአርአያ እግዚአብሔር መፈጠር በቂ ማስረጃ ነው : ሰው በበደሉ ምክንያት ለሞት ቢዳረግም የእግዚአብሔር ፍጹም ፍቅር ጨርሶ አልተለየውም፣ እግዚአብሔር አንድ ቀን ሞትን ከሰው ጫንቃ አሽቀንጥሮ እንደሚጥል በየጊዜው ይገልጽ ነበረ፣ ያም በራሱ ልዩ ጥበብ እንደሚከናወን አረጋግጦ ለሰው ልጅ ተስፋውን አሳውቆ ነበር) ያም ልዩ ጥበብ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ዕውቀትና ጥበብ ድንበር የለውምና ከፍጥረተ ዓለም በፊት ሳይቀር የሰው ድኅነት በኢየሱስ ክርስቶስ ደም እንደሚፈጸም በእግዚአብሔር ዘንድ የተቈረጠ ነገር ነበረ፤ ጊዜው ሲደርስም በህላዌና በክዋኔ ከእርሱ ጋር አንድ የሆነ እግዚአብሐር ወልድ የሰውን ሰውነት ተዋሕዶ ሰውን የማዳን ስራውን አንድ ብሎ ጀመረ፡፡ ሰዎች በኃጢአትና በዲያብሎስ በደዌና በሞት ላይ ሥልጣን ያለው አዳኝ እሱ እንደሆነ ያውቁ ዘንድ የማዳን ስራውን በመዋዕለ ሥጋዌው በስፋት አከናወነ፡፡ ልዩ ልዩ ደዌና በሽታ የሚያሠቃያቸውን ፈወሰ፤ ኃጢአተኞችን በይቅርታ ተቀበለ፤ ኃጢአታቸውንም ደመሰሰ፤ አጋንንትንም በትእዛዝ አስወጣ፣ ወደ ጥልቁም አስመጣቸው: ዲያብሎስንም ድል ነሥቶ አባረረ፣ ሙታንንም አነሣ፤ በባሕር ላይ በእግሩ ተራመደ፣ ነፋሳትን ገሠጸ፣ በአምስት እንጀራ ከአምስት ሺሕ ሕዝብ በላይ መገበ ፣ ውሀውንም ወደ ጠጅ ለወጠ። ሰውን ሁሉ በፍቅርና በይቅርታ ይቀበልና ያገለግል ነበር እንጂ በአንዱ ስንኳ የመጨከንና የማግለል መንፈስ አላሳየም፤ ይህ ሁሉ ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔር ፍቅር ማሳያ ነበረ። በፍጥረት ሁሉ ላይ መለኮታዊ ሥልጣን እንዳለውም ማረጋገጫ ነበረ፣ መልእክቱም ዓለም መዳኛዋና አዳኝዋ እሱ መሆኑን አውቃ በአእምሮ እንድትከተለውና የድኅነቱ ተቋዳሽ እንድትሆን ማስቻል ነው፡፡ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት! በእግዚአብሔር አሠራር ኃጢአት ያለ ቤዛነት አይሰረይም፣ በመሆኑም ስው በእግዚአብሔር ፊት ፍጹም ኃጢአተኛ ሆኖ ስለተገኘ ቤዛ ሆኖ የሚያድነው ያስፈልገው ነበር፣ ቤዛ መሆን የሚችለው አካል ደግሞ ራሱ ፍጹም ንጹህ መሆን ነበረበት፡፡ ከዚህም አንጻር በእግዚአብሔር ፊት ለሱ የሚመጥን ንጹህ ኣካል ከፍጡራን ወገን አልተገኘምና እሱ ራሱ ሰው ሆኖ የሰው ቤዛ ለመሆን በሥጋ ተገለጠ፤ በዚህም መሠረት የሰው ቤዛ ሆኖ በመስቀል ላይ በመስቀል ንጹህ ደሙን አፈስስ፣ በዚህ ደም ምክንያት የሰው ኃጢአት በሥርየት ተዘጋ፡ ለዚህም ነው ቅዱስ መጽሐፍ “ያለ ደም ሥርየት ወይም ይቅርታ የለም" ብሎ የሚነግረን። ከዚህ ደም መፍሰስ በኋላ ወደ ሲኦል ወርዶ በዚያ የነበሩ የኃጢአት ግዞተኞችን በሙሉ ፈትቶ ወደ ቀደመ ስፍራቸው ወደ ገነት መለስ፤ ከስቅለተ ክርስቶስ ጀምሮ እስከ መጨረሻ ያለው የሰው ኃጢአት በሙሉ በክርስቶስ ደም ይደመሰሳል።ሆኖም ይህ ሥርየት የሚገኘው በእምነት መሆኑን ቅዱስ መጽሐፍ አበክሮ ይነግረናል፤ በክርስቶስ አምኖ በደሙ የነጻ ሁሉ ክርስቶስ በተነሣው ዓይነት ትንሣኤ ይነሣል፡፡ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት! የጌታችንን ትንሣኤ ስናከብር የኛንም ትንሣኤ በማስብ ሊሆን ይገባል! ትልቁ ነገርም የኛን ትንሣኤ ማሰቡ ላይ ነው፤ ምክንያቱም የክርስቶስ ትንሣኤ ለኛ ተብሎ የተደረገ በመሆኑ ነው። የሱ ትንሣኤ ለኛ ትንሣኤ በኵር ነው: ማሳያና ማረጋገጫም ነው፤ እግዚአብሔር በየዕለቱ የሚፈልገው የኛን ትንሣኤ ማየት ነው፤ የኛ ትንሣኤ በአንድ ቀን በቅዕበት የሚሆን አይደለም: ትንሣኤያችን አምነን ስንጠመቅ ተጀምሮ ከመቃብር ስንነሣ የሚጠናቀቅ ነው፡፡ እግዚአብሔር ዛሬም እያንዳንዱ ሰው በትንሣኤ ሕይወት እንዲመላለስ ይጠራል፤ ምክንያቱም የኋለኛው ትንሣኤ የሚገኘው በፊተኛው ትንሣኤ እንደሆነ እግዚአብሔር በመጽሓፉ ነግሮናልና ነው፤ በፊተኛው ትንሣኤ ዕድል ያለው ብፁዕ ነው፤ በሱ ላይ ሞት ሥልጣን የለውምና ነው፤ ለሰው ልጆች ተጠብቆልን ያለው ተስፋ ይህ ነው፡፡ ተስፋውን እውን ማድረግ የሚቻለውም በኛ ሃይማኖታዊና ተግባራዊ ተሳትፎ እንደዚሁም በኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛዊ ደም ነው፡ የነገውን ትንሣኤ ተሳታፊ ለመሆን ዛሬ መነሣት ግድ ይላል) ይሀም የሚቻል እንጂ የማይቻል አይደለም፡፡ በእምነት ትንሣኤ፣ በአምልኮተ እግዚአብሔር ትንሣኤ፣ ለእግዚአብሔር በመታዘዝ ትንሣኤ፣ በፍቅር ትንሣኤ፣ በሰላም ትንሣኤ፣ በይቅርታ ትንሣኤ፣ በመከባበር ትንሣኤ፣ በአንድነት ትንሣኤ፣ በመተሳሰብ ትንሣኤ ወዘተ በመሳስሉ ሃይማኖታዊና ግብረ ገባዊነት ጸንተን መኖር ከቻልን የፊተኛው ትንሣኤ ማለት እሱ ነው፡፡ ዛሬ እግዚእብሔር እያንዳንዳችን ይህንን ትንሣኤ እውን አድርገን ስንኖርና ስንመላለስ ማየት ይፈልጋል፡፡ በአንጻሩም ክሕደትን፣ ከሕገ ተፈጥሮ ያፈነገጠ ጸያፍ ተግባርን፣ ጥላቻን፣ ጦርነትን፣ መለያየትን፣ ራስን ብቻ መውደድን፣ መጨካከንን፣ ግብረ ኃጢአትን፣ ፈሪሐ እግዚአብሔር ገንዘብ አለማድረግን፣ ፈጣሪን አለማመንን የተጸየፈ ምእመንን ማየት ይፈልጋል፡፡ ምክንያቱም ሁሉም ኃጣውእ አፅራረ ትንሣኤ ናቸውና ነው፤ ኃጣውእ በምድርም በሰማይም የሰው ጠላቶች ናቸው፤ በምድር ለሥጋዊና መንፈሳዊ በሽታ ይዳርጉናል፡፡ በተለይም በእግዚአብሔር ፊት እጅግ አስጸያፊ የሆነው የነውረ ኃጢአት ርኵሰትና በጋብቻ ያልታሰረ ሩካቤ ሥጋ ትውልድን እንደ ቅጠል አያረገፈው እንደሆነ፣ ምንም ዓይነት ፈውስ ላልተገኘለት የኤች አይ ቪ ኤድስ በሽታ ዋነኛ መተላፊያም ይህ ነውረ ኃጢአት እንደሆነ ተደጋግሞ ተነግሮአል፡፡ ይሁንና አሁንም ጥንቃቄ በጎደለው ድርጊት ስሕተቱ በመቀጠሰ በጦርነት ከሚያልቀው ሕዝብ ባልተናነሰ በዚህ ገዳይ በሽታ ብዙ ወገን እያለቀ ነውና እባካችሁ ሕዝበ እግዚአብሔር አንድ ለአንድ በመተሣሰርና በተቀደስ የጋብቻ ሕይወት በመወሰን ትንሣኤያችንን እናብስር፡፡ በመጨረሻም በዓለ ትንሣኤ የእግዚብሔር ፍቅር መገለጫና የተስፋችን ማሳያ መሆኑን በመገንዘብ ለእግዚአብሔር ክብርና ለሰው ልጆች ደኅንነት በአንድነት በመቆም ለተራቡት፤ ለተጠሙት፣ ለታረዙት፣ ለታመሙትና ስታሰሩትም ሁሉ ካለን ከፍለን በመስጠት ከኛ ጋራ በመንፈስና በሞራል በዓለ ትንሣኤውን እንዲያሳልፉ
إظهار الكل...
የ"ገብረ ሰላመ" በዓል ቅዱስ ፓትርያርኩ በተገኙበት በደማቅ ሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓት ተከበረ። ሚያዝያ 26/2016 ዓ.ም ( ፍ.እ.ሚ./አዲስ አበባ) በየዓመቱ በበዓለ ትንሣኤ ዋዜማ "በቀዳም ስዑር" የሚከበረው የገብረ ሰላመ በዓል ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአከኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በተገኙበት ዛሬ ሚያዝያ ፳፮ ቀን ፳፻፲ወ፮ ዓ/ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በደማቅ ሃይማኖታዊ ሥርዓተ አምልኮ ተከበረ። በዓሉ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ሥራውን መፈጸሙ የሚዘከርበት፣ በመስቀል ላይም በፈጸመው የማዳን ሥራ ለዓለም ድኅነትን መስጠቱ የሚታወጅበት ታላቅ ሃይማኖታዊ በዓል ነው። በኖኅ ዘመን መጥቶ የነበረው ጥፋት ማብቃቱ ርግቧ ይዛ በመጣችው የወይራ ቅጠል እንደታወቀ ሁሉ በአዳም በደል ምክንያት በሰው ልጆች የውድቀት ዘመን ማብቃቱ የሚታወጅበት ቄጤማም በቅዱስ ፓትርያርኩ ለበዓሉ ታዳሚዎች ሁሉ ከመልካም ምኞት ጋር ታድሏል። በቅዱስ ያሬድ ለዕለቱ የተዘጋጀው "ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃደ..." የሚለው ቃለ እግዚአብሔርም ለዕለቱ በተመደቡት በመርካቶ ደብረ አሚን ዳግሚት ደብረ ሊባኖስ ገዳም ሊቃውንት ደርሷል። በዐሉ ላይም በቅዱስነታቸው መሪነት ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል፣ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ፣ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ፣ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት እና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሥራ ኃላፊዎች፣ የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ካህናትና ምእመናን ተገኝተዋል። ©ኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
إظهار الكل...
✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿 ቀዳም ሥዑር (የተሻረች ቅዳሜ) ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተሰቀለበት ዕለት ማግሥት ያለው ቅዳሜ በተለያዩ ስያሜዎች ይጠራል:- 🔖ቀዳም ሥዑር፡- በዚች ዕለች ከድሮው በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረችው ቅዳሜ ትባላለች፡፡ የማትጾመዋ ቅዳሜ ስለምትጾም ሥዑር /የተሻረች/ ተብላለች በዓል መሻርን አይመለከትም በቀዳም ሥዑር ሌሊት ሥርዓቱ የሚጀመረው በመኀልየ ሰሎሞን ምንባብ ነው፡፡ ማኀሌቱም እዝሉ እየተቃኘ እየተመጠነ፣ እየተዘመመ እየተመረገደ እየተጸፋ ያድራል፡፡ ጥዋት አቡን መዋሥዕት ውዳሴ ማርያም ዜማ ተደርሶ ወለመልአከ ሕይወትሰ ሰቀልዎ በሚለው ሰላም ይጠናቀቃል፡፡በዚህ ዕለት ልብሰ ተክህኖ የለበሱ ካህናትና ዲያቆናት ቄጤማ ተሸክመው ቃጭል ሲያቃጨሉ መታየታቸው ዕለተ ትንሣኤውን ለሚናፍቅ ምእመን ትልቅ ብስራት ነው፡፡ 🌿ለምለም ቅዳሜ፡- ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት ስለሆነ በዚህ ተሰይሟል፡፡ ቀጤማውንም ምእመናን እስከ ትንሣኤ ሌሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል፡፡ በቀዳም ሥዑር ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ቃጭል /ቃለዓዋዲ/ እየመቱ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃደ የሚለውን ያሬዳዊ ዜማ በመዘመር፤ ጌታ በመስቀሉ ሰላምን እንደሰጠን እና ትንሣኤውንም እንደገለጠልን በማብሰር፤ ቄጤማውን ለምእመናን ይሰጣሉ፡፡ ምእመናኑም በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውል ገጸ በረከት ያቀርባሉ፡፡ ቄጤማውንም በራሳቸው ያስራሉ፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን እያሰቃዩ ሊሰቅሉት ባሉ ጊዜ የእሾህ አክሊል ጭንቅላቱ ላይ ያሠሩበትን ድርጊት የሚያስታውስ ነው፡፡ (የቀጤማው አመጣጥና ምስጢርም ከአባታችን ከኖኅ ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ምድር በማየ አይኅ /በጥፋት ውኃ/ በጠፋችበት ወቅት የኖኅ ታማኝ መልእክተኛ ርግብ የውኃውን መጉደል ያበሰረችው ቀጤማ ይዛ በመግባት ነው፡፡ ዛሬም ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች የኃጢአት ውኃ ጐደለ፣ የኃጢአት ውኃ ጠፋ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነጻነት ተሰበከ ታወጀ በማለት ካህናት ቄጠማ ይዘው ምእመናንን ያበሥሩበታል፡፡) 🙏ቅዱስ ቅዳሜ፡- ቅዱስ ቅዳሜ መባሉ ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ከፈጠረ በኋላ በዚህ ቀን ከሥራው ሁሉ ያረፈበት ነው፡፡ በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ፣ በነፍሱ ሲዖልን በርብሮ ባዶዋን አስቀርቷታል፡፡ በዚያ ለነበሩት ነፍሳትም የዘለዓለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ከሌሎቹ ዕለታት የተለየ ዕለት ለማለት ቅዱስ ቅዳሜ ተብሏል፡፡ (ስምዐ ተዋሕዶ የስምዐ ጽድቅ ልዩ እትም ዘሰሙነ ሕማማት ሚያዝያ 2004 ዓም) ©ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት ✨🌞✨አብርሂ ፈለገ ሰላም✨🌞✨ 🏁 follow our sunday school media 📱 Youtube   ⬅️ click here 📱 Tiktok 📱 Instagram    ✨🌞✨አብርሂ ፈለገ ሰላም✨🌞✨       ✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈•✥
إظهار الكل...
tora media on TikTok

@tora.media 984 Followers, 1 Following, 5325 Likes - Watch awesome short videos created by tora media

👍 5
✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿✨🌿✨ ቀዳም ሥዑር (የተሻረች ቅዳሜ) ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተሰቀለበት ዕለት ማግሥት ያለው ቅዳሜ በተለያዩ ስያሜዎች ይጠራል:- 🔖ቀዳም ሥዑር፡- በዚች ዕለች ከድሮው በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረችው ቅዳሜ ትባላለች፡፡ የማትጾመዋ ቅዳሜ ስለምትጾም ሥዑር /የተሻረች/ ተብላለች በዓል መሻርን አይመለከትም በቀዳም ሥዑር ሌሊት ሥርዓቱ የሚጀመረው በመኀልየ ሰሎሞን ምንባብ ነው፡፡ ማኀሌቱም እዝሉ እየተቃኘ እየተመጠነ፣ እየተዘመመ እየተመረገደ እየተጸፋ ያድራል፡፡ ጥዋት አቡን መዋሥዕት ውዳሴ ማርያም ዜማ ተደርሶ ወለመልአከ ሕይወትሰ ሰቀልዎ በሚለው ሰላም ይጠናቀቃል፡፡በዚህ ዕለት ልብሰ ተክህኖ የለበሱ ካህናትና ዲያቆናት ቄጤማ ተሸክመው ቃጭል ሲያቃጨሉ መታየታቸው ዕለተ ትንሣኤውን ለሚናፍቅ ምእመን ትልቅ ብስራት ነው፡፡ 🌿ለምለም ቅዳሜ፡- ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት ስለሆነ በዚህ ተሰይሟል፡፡ ቀጤማውንም ምእመናን እስከ ትንሣኤ ሌሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል፡፡ በቀዳም ሥዑር ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ቃጭል /ቃለዓዋዲ/ እየመቱ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃደ የሚለውን ያሬዳዊ ዜማ በመዘመር፤ ጌታ በመስቀሉ ሰላምን እንደሰጠን እና ትንሣኤውንም እንደገለጠልን በማብሰር፤ ቄጤማውን ለምእመናን ይሰጣሉ፡፡ ምእመናኑም በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውል ገጸ በረከት ያቀርባሉ፡፡ ቄጤማውንም በራሳቸው ያስራሉ፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን እያሰቃዩ ሊሰቅሉት ባሉ ጊዜ የእሾህ አክሊል ጭንቅላቱ ላይ ያሠሩበትን ድርጊት የሚያስታውስ ነው፡፡ (የቀጤማው አመጣጥና ምስጢርም ከአባታችን ከኖኅ ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ምድር በማየ አይኅ /በጥፋት ውኃ/ በጠፋችበት ወቅት የኖኅ ታማኝ መልእክተኛ ርግብ የውኃውን መጉደል ያበሰረችው ቀጤማ ይዛ በመግባት ነው፡፡ ዛሬም ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች የኃጢአት ውኃ ጐደለ፣ የኃጢአት ውኃ ጠፋ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነጻነት ተሰበከ ታወጀ በማለት ካህናት ቄጠማ ይዘው ምእመናንን ያበሥሩበታል፡፡) 🙏ቅዱስ ቅዳሜ፡- ቅዱስ ቅዳሜ መባሉ ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ከፈጠረ በኋላ በዚህ ቀን ከሥራው ሁሉ ያረፈበት ነው፡፡ በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ፣ በነፍሱ ሲዖልን በርብሮ ባዶዋን አስቀርቷታል፡፡ በዚያ ለነበሩት ነፍሳትም የዘለዓለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ከሌሎቹ ዕለታት የተለየ ዕለት ለማለት ቅዱስ ቅዳሜ ተብሏል፡፡ (ስምዐ ተዋሕዶ የስምዐ ጽድቅ ልዩ እትም ዘሰሙነ ሕማማት ሚያዝያ 2004 ዓም) ©ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት ✨🌞✨አብርሂ ፈለገ ሰላም✨🌞✨ 🏁 follow our sunday school media 📱 Youtube   ⬅️ click here 📱 Tiktok 📱 Instagram    ✨🌞✨አብርሂ ፈለገ ሰላም✨🌞✨       ✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈•✥
إظهار الكل...
7🙏 2
🔖የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ስቅለት በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያን በልዩ ሥርዓተ ጸሎትና ስግደት እየተከናወነ ይገኛል። በመንበረ ፓትርያክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም እየተከናወነ ባለው ሥርዓተ ጸሎት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በርካታ ካህናትና ምዕመናን ተገኝተዋል። ምንጭ፦eotc.tv ✨🌞✨አብርሂ ፈለገ ሰላም✨🌞✨ 🏁 follow our sunday school media 📱 Youtube   ⬅️ click here 📱 Tiktok 📱 Instagram    ✨🌞✨አብርሂ ፈለገ ሰላም✨🌞✨       ✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈•✥
إظهار الكل...