en
Feedback
EEP Communication

EEP Communication

Open in Telegram

📈 Analytical overview of Telegram channel EEP Communication

Channel EEP Communication (@eepcommuication) in the Amharic language segment is an active participant. Currently, the community unites 15 676 subscribers, ranking 8 043 in the Technologies & Applications category and 2 176 in the Ethiopia region.

📊 Audience metrics and dynamics

Since its creation on невідомо, the project has demonstrated rapid growth, gathering an audience of 15 676 subscribers.

According to the latest data from 06 September, 2026, the channel demonstrates stable activity. Although there has been a change in the number of participants by 111 over the last 30 days and by -1 over the last 24 hours, overall reach remains high.

  • Verification status: Not verified
  • Engagement rate (ER): The average audience engagement rate is 25.35%. Within the first 24 hours after publication, content typically collects 15.94% reactions from the total number of subscribers.
  • Post reach: On average, each post receives 3 974 views. Within the first day, a publication typically gains 2 500 views.
  • Reactions and interaction: The audience actively supports content: the average number of reactions per post is 10.

📝 Description and content policy

The author describes the resource as a platform for expressing subjective opinions:
EEP Communication

Thanks to the high frequency of updates (latest data received on 07 September, 2026), the channel maintains relevance and a high level of publication reach. Analytics show that the audience actively interacts with content, making it an important point of influence in the Technologies & Applications category.

15 676
Subscribers
-124 hours
-157 days
+11130 days
Posts Archive
ኢትዮ-ኤሌክትሪክ አቻ ተለያይቷል .........///....... ድሬዳዋ ከተማ እየተካሄደ ባለው የኢትዮጵያ የወንዶች ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ከድሬዳዋ ከነማ ጋር ነጥብ ተጋርቷል። ትናንት ምሽት አንድ ሰዓት የተከናወነው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ያለምንም ግብ ተጠናቋል። ግብ የሚሆኑ ኳሶችን በተደጋጋሚ ሙከራ በማድረግ ድሬዳዋ ከነማ የተሻለ ሲሆን ኢትዮ-ኤሌክትሪክ በአንፃሩ በመልሶ ማጥቃት ጎል ለማግኘት ጥረት ሲያደርግ ተስተውሏል። የኢትዮ-ኤሌክትሪክ ግብ ጠባቂ ኢድሪሱ አብዱላሂ በርካታ ጎል ሊሆኑ የሚችሉ ኳሶችን በማዳን ክለቡን ታድጓል። ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ በ14 ነጥብ መቻልን ተከትሎ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ በጊዜያዊነት በሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። በ10ኛ ሳምንት መርሃግብር ኢትዮ-ኤሌክትሪክ በመጪው ህዳር 27 ቀን 2017 ዓ.ም ከስሁል ሽረ ጋር የሚጫወት ይሆናል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ህዳር 20 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+6

የተቋረጠው ኃይል መልሶ ተገናኝቷል …….///……. ለሦስት ዞኖችና ለጋምቤላ ክልል ኃይል መቋረጥ ምክንያት የሆነውን የበደሌ መቱ ባለ 230 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር የመጠገን ሥራ በስኬት ተጠናቋል። በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ዘርፍ የደቡብ ምዕራብ ሪጅን ዳይሬክተር አቶ ጌታሁን ሲሳይ እንደገለፁት ዛሬ ከረፋዱ 4፡50 ጀምሮ ለሦስት ሰዓት ከ30 ደቂቃ ተቋርጦ የነበረውን መስመር ከበደሌ ከተማ የተንቀሳቀሰው የጥገና ባለሙያዎች ቡድን ወደነበረበት እንዲመለስ አድርጓል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ህዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም

በሦስት ዞኖችና ጋምቤላ ክልል ኃይል ተቋርጧል …….///……. ከበደሌ መቱ የተዘረጋው ባለ 230 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር በመበጠሱ ኃይል መቋረጡን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ዘርፍ የደቡብ ምዕራብ ሪጅን አስታወቀ፡፡ የሪጅኑ ዳይሬክተር አቶ ጌታሁን ሲሳይ እንደገለፁት ዛሬ ከረፋዱ 4፡50 ጀምሮ በኢሉባቦር ዞን ያዩ በተባለ አካባቢ ኮንዳክተር ተበጥሷል፡፡ በዚህ የተነሳ በኢሉ አባቦር ዞን፣ በሸካ ዞን እና በቄለም ወለጋ ዞን እንዲሁም በጋምቤላ ክልል ኃይል መቋረጡን ገልፀዋል፡፡ የተበጠሰውን መስመር ለመጠገን ከበደሌ ከተማ የጥገኛ ባለሙያዎች ወደ ሥፍራው መንቀሳቀሳቸውን ዳይሬክተሩ ጠቁመው ችግሩ እስኪፈታ ድረስ ደንበኞች በትዕግስት እንዲጠብቁ ጠይቀዋል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ህዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content

በክልሉ የመሰረተ ልማት ስርቆትን ለማስቆም ሁሉም በቅንጅት እንዲሰራ ተጠየቀ ........///........ በአፋር ክልል እየተፈፀመ ያለውን የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ስርቆት ለማስቆም ሁሉም በቅንጅት ሊሰራ እንደሚገባ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአፋር ክልል የመልካም አስተዳደር ክላስተር አስተባባሪ አሳሰቡ። በክልሉ እየተፈፀመ ያለውን የኃይል መሰረተ ስርቆት ለመከላከል ከክልሉ፣ ከአውሲ ረሱ ዞን፣ ከዱብቲ፣ ሚሌና አዳአር ወረዳዎች፣ ከሰመራና ሎጊያ ከተማ አስተዳደር ከተውጣጡ አመራሮችና የፀጥታ አካላት እንዲሁም ከጎሳ መሪዎች ጋር ውይይት ተካሂዷል። በውይይቱ ላይ የተገኙት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአፋር ክልል የመልካም አስተዳደር ክላስተር  አስተባባሪ አቶ አህመድ ሁሴን እንደተናገሩት የኤሌክትሪክ ኃይል ለክልሉ ማህበረሰብ ለልማት ብቻ ሳይሆን ለእስትንፋሱም ፋይዳው የጎላ ነው። ይሁንና ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየተፈፀመ ያለው ስርቆት በማህበረሰቡ የአኗኗር ዘይቤ ላይ ተፅዕኖ እያሳደረ መጥቷል ብለዋል። በኤሌክትሪክ ኃይል መሰረተ ልማቶች ላይ የሚፈፀሙ የስርቆት ወንጀሎችን ለመከላከል በየደረጃው ያለው የክልሉ አመራር፣ የፀጥታ አካላት እና ማህበረሰቡ በቅንጅት በመስራት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡም አሳስበዋል። የአፋር ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ ቤት ኃላፊ አቶ መሀመድ ሁሴን በበኩላቸው ኤሌክትሪክ ለክልሉ ማህበረሰብ የመኖርና ያለመኖር ጉዳይ በመሆኑ አመራሩ በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚፈፀሙ ስርቆቶችን ለመከላከል ትኩረት ሠጥቶ እየሠራ ነው ብለዋል። በክልሉ ማህበረሰብ እንደ መጤ ባህል የሚቆጠረው የስርቆት  ድርጊት እንዳይስፋፋ ሁሉም ችግሩ ከመከሰቱ በፊት ሊታገለው እንደሚገባ ተናግረዋል። የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ሙሳ አብዶ እንደገለፁት የስርቆት ወንጀሎችን ለመከላከል በአቀባይና ተቀባይ መካከል ያለውን ሰንሰለት መበጠስ ያስፈልጋል። ለዚሁ ደግሞ የሁሉምን ተሳትፎ እንደሚጠይቅ ነው ያስረዱት። በስርቆት የተጠረጠሩ አካላትን ተጠያቂ ለማድረግ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ከዋሉበት ቀን ጀምሮ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ጉዳዩን በቅርበት በመከታተል ከሚመለከተው አካላት ጋር በቅንጅት መስራት እንዳለበትም አስገንዝበዋል። የአውሲ ረሱ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ናስር ሃመዱ መድረኩ ችግሩን በተናበበ መልኩ ለመከላከል ዕድል እንደሚፈጥር ጠቅሰው እየተፈፀመ ያለውን ስርቆት ለመከላከል በዞን ደረጃ አመራር ተሰጥቶበት እየተሰራ ነው ብለዋል። በኢትዮጵያ  ኤሌክትሪክ ኃይል የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን ዘርፍ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሀብታሙ ውቤ እንደገለፁት ተቋሙ በክልሉ ያለውን የኃይል ተደራሽነት ለማስፋፋት ትኩረት ሠጥቶ እየሠራ ነው። ይሁን እንጂ በሀገር አቀፍ ደረጃ በመሠረተ ልማቶቹ ላይ እየተፈፀሙ ያሉ ስርቆቶች ተቋሙ የኃይል መሠረተ ልማቱን ለማስፋፋት በሚያከናውነው ሥራ ላይ ተፅዕኖ እያሳደረ ይገኛል ብለዋል። ተቋሙ በሀገር አቀፍ ደረጃ ያለውን የኃይል መሰረተ ልማት ስርቆትን ለማስቀረት የተለያዩ ሥራዎችን ቢያከናውንም መፍትሔ እንዳልመጣ ነው የተናገሩት። በዚህም ተቋሙ በክልል በየደረጃው ከሚገኙ አመራርሮች ጋር ተቀራርቦ በመስራት ችግሩን ቀድሞ ለመከላከል በሁሉም አካባቢዎች ውይይቶችን እያካሄደ እንደሆነ እና መሠረተ ልማቱን የሚከታተልና ከክልሎች ጋር ተቀናጅቶ የሚሰራ ክፍል ማዋቀሩንም አስታውቀዋል። በክልሉ የሚስተዋሉ የስርቆት ወንጀሎችን ለመከላከል በውይይቱ ላይ የተሳተፉ አመራሮች ለህብረተሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጫዎችን በመስጠት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል። በተቋሙ የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ክትትልና ቁጥጥር ቢሮ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዋለ ታምሬ በበኩላቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ በሀገሪቱ እየተስፋፋ የመጣውን የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች ስርቆትን ለመከላከል በየደረጃው ያለው አመራር  መሰረተ ልማቶችን የመጠበቅ ግዴታ እንዳለበት ተገንዝቦ መስራት ይኖርበታል ብለዋል። ከቅድመ መከላከል ሥራው ጎን ለጎን የፍትህና የፀጥታ አካላት በመሠረተ ልማት ስርቆት የተሳተፉ ወንጀለኞች ላይ አስተማሪ ቅጣት እንዲወስዱም አሳስበዋል። በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ሥራ አስኪያጅ አቶ ፍስሃ ጌታቸው እንደተናገሩት የአፋር ክልል የኃይል መሠረተ ልማቱን ለመጠበቅ እየተከተለ ያለው አሰራርና እየወሰደ ያለው እርምጃ የሚበረታታና ለሌሎችም ተሞክሮ የሚሆን ነው። ሁሉም ለመሠረተ ልማቱ ደህንነት ዋስትና ሆኖ እንዲሰራ የእኔነት ስሜት ያለው ማህበረሰብ መፍጠር እንደሚጠይቅ እና የዳጉ ባህላዊ የመረጃ ልውውጥ ስርዓትን ማጠናከር እንደሚገባ አሳስበዋል። በተቋሙ የሰሜን ምስራቅ 2 ሪጅን የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽንና ጥገና መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ሀሰን መሀመድ ስለ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አጠቃላይ ገፅታና ባለፈው አንድ አመት በሪጅኑ ስለተፈፀሙ የማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ሞሰሶዎች ስርቆት መጠንና ስርቆቱ በየትኞቹ አካባቢዎች እንደሚስተዋል በውይይቱ ወቅት ገለፃ አድርገዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ህዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+6

photo content
+9

የውጤት ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ መጋቢት 02 ቀን 2015 ዓ.ም በኮሙዩኒኬሽን ኦፊሰር 2ኛ የስራ መደብ በቋሚነት ለመቅጠር ማስታወቂያ ማውጣታችን ይታወቃል፡፡ ስለሆነም መስፈርቱን አሟልታችሁ ከ
የውጤት ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ መጋቢት 02 ቀን 2015 ዓ.ም በኮሙዩኒኬሽን ኦፊሰር 2ኛ የስራ መደብ በቋሚነት ለመቅጠር ማስታወቂያ ማውጣታችን ይታወቃል፡፡ ስለሆነም መስፈርቱን አሟልታችሁ ከተመዘገባችሁት ተወዳዳሪዎች መካከል በተ.ቁ 1 እና 2 ላይ የተገለጻችሁ በተሰጠው የጽሁፍ ፈተና አብላጫ ውጤት ያመጣችሁ በመሆኑ ከህዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 5 (አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በዋናው መ/ቤት ኮተቤ ብረታብረት በሚገኘው የሰራተኛ ምደባ ቢሮ የትምህርት ማስረጃችሁን ዋናውን እና ኮፒ በመያዝ እየቀረባችሁ የቅጥር ፎርም እንድትሞሉ እናሳውቃለን፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ህዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም

የማከፋፈያ ጣቢያውን አቅም በአግባቡ ለመጠቀም ደንበኞቹን መሳብ ያስፈልጋል ……..///…….. የዲቼቶ ማከፋፈያ ጣቢያን በሙሉ አቅም ለመጠቀም ደንበኞችን መሳብ እንደሚገባ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን ዘርፍ አስታወቀ። የዘርፉ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሀብታሙ ውቤን ጨምሮ ሌሎች የተቋሙ የሥራ ኃላፊዎች የዲቼቶ ባለ 230 /33 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያን የኦፕሬሽን ሥራ ጎብኝተዋል። የጣቢያው ኃላፊ አቶ ብሩክ አንዳርጋቸው በጉብኝቱ ወቅት እንደተናገሩት የማከፋፈያ ጣቢያው ካሉት ወጪ መስመሮች በሁለቱ ብቻ ለዲቼቶ፣ ጋላፊ፣ ኤሊዳር፣ ውሃ ልማት፣ ሠርዶ እና ስልሳ ለተሰኙ ወረዳዎችና አካባቢዎች ኃይል እያቀረበ ነው። በማከፋፈያ ጣቢያው ላይ ያለው ትራንስፎርመር 25 ሜጋ ዋት የመሸከም አቅም ቢኖረውም በአካባቢው ያለው የኃይል ተጠቃሚ አነስተኛ በመሆኑ በአሁኑ ወቅት ለደንበኞቹ እየቀረበ ያለው ኃይል 3 ሜጋ ዋት የማይደርስ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የጣቢያው የመቆጣጠሪያ ክፍል እና የሠራተኛ መኖሪያ ቤት ላይ በተፈጥሮ ምክንያት የተስተዋለው ችግር እና በጣቢያው ያለው የውሃ ችግር እንዲፈታላቸውም ጠይቀዋል። በዘርፉ የአቅም ማሳደግ፣ ማሻሻልና ማዘመን መምሪያ ዳይሬክተር አቶ የማነ ኢሳይያስ በበኩላቸው በማከፋፈያ ጣቢያው የመቆጣጠሪያ እና የሠራተኞች መኖሪያ ቤት ላይ ያጋጠመውን ጉዳት በመጠገን ችግሩን ለመፍታት ይሰራል ብለዋል። የጣቢያውን የፓወር ትራንስፎርመር ደህንነት ለመጠበቅ የሚያስችሉ ዕቃዎች መግባታቸውንና የገጠማ ሥራው በቅርቡ እንደሚከናወንም አቶ የማነ አንስተዋል። የማከፋፈያ ጣቢያው በአካባቢው የሚኖረውን ደንበኛ ታሳቢ በማድረግ ባለመገንባቱ እና ደንበኞችም በሚፈለገው መጠን ባለመምጣታቸው የጣቢያውን አቅም በአግባቡ ጥቅም ላይ ማዋል አልተቻለም ብለዋል። እንደ ዲቼቶ ሁሉ ከአፍዴራ ማከፋፈያ ጣቢያ ኃይል የሚያገኙ ደንበኞች አነስተኛ በመሆኑ የጣቢያዎቹን የመጫን አቅም በአግባቡ ለመጠቀም የሚመለከተው አካል በአካባቢው ላይ ኢንቨስትመንቶችን በማስፋፋት ደንበኞችን መሳብ እንደሚጠበቅበት አቶ የማነ አሳስበዋል። የዘርፉ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሀብታሙ ውቤ የጣቢያው ሠራተኞች ለተቋሙ ቅድሚያ በመስጠት ንብረቶቹን በአግባቡ መጠቀም እንደሚኖርባቸው አሳስበው እያጋጠሙ ያሉ ችግሮች በሚፈቱበት ሁኔታ ላይም አቅጣጫ አስቀምጠዋል። የዲቼቶ ማከፋፈያ ጣቢያ ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ህዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+9

የክልሉ የሥራ ኃላፊዎች የሰመራ ማከፋፈያ ጣቢያን ጎበኙ ………///……… ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና ከአፋር ክልል የተውጣጡ የሥራ ኃላፊዎች የሠመራ ባለ 230/33 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያን ጎብኝተዋል። በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን ዘርፍ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሀብታሙ ውቤ፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የአፋር ክልል የመልካም አስተዳደር ክላስተር አስተባባሪ አቶ አህመድ ሁሴን፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ መሀመድ ሁሴን እና ሌሎች የክልሉና የተቋሙ የሥራ ኃላፊዎች የጣቢያውን የኦፕሬሽን ሥራዎች እና በጣቢያው እየተከናወነ ያለውን ተጨማሪ የሸንት ሪአክተር ተከላ ሥራ ተመልክተዋል። የሠመራ ማከፋፈያ ጣቢያ ኃላፊ አቶ ኢንድሪስ አህመድ ለሥራ ኃላፊዎቹ ገለፃ ባደረጉበት ወቅት እንደተናገሩት ጣቢያው አንድ ባለ 230 ኪሎ ቮልት ገቢ፣ ስድስት ባለ 33 እና ሁለት ባለ 230 ኪሎ ቮልት ወጪ መስመሮች አሉት። ጣቢያው ከኮምቦልቻ ማከፋፈያ ጣቢያ ኃይል ተቀብሎ ለሠመራ፣ ሎጊያ፣ ሚሌ፣ ዱብቲ ፣ አሳይታ ከተሞችና ለሠመራ ኢንዱስትሪ ፓርክ በ33 ኪሎ ቮልት እንዲሁም ለዲቼቶ እና አፍዴራ ማከፋፈያ ጣቢያዎች በባለ 230 ኪሎ ቮልት ወጪ መስመሮች ኃይል እያቀረበ እንደሆነ አስረድተዋል። በማከፋፈያ ጣቢያው የተተከለው 25 ሜጋ ቮልት አምፔር አቅም ያለው አንድ ትራንስፎርመር እስከ 20 ሜጋ ዋት ኃይል እየጫነ እንደሆነም ተናግረዋል። በአፍዴራ ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ ያለውን የኃይል መዋዠቅ ለማመጣጠን በሠመራ ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ ተጨማሪ የሸንት ሪአክተር ተከላ ሥራ እየተከናወነ ስለመሆኑም ገልፀዋል። በጉብኝቱ ላይ የተሳተፉት በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የአፋር ክልል የመልካም አስተዳደር ክላስተር አስተባባሪ አቶ አህመድ ሁሴን ተቋሙ በክልሉ ያለውን የኃይል ተደራሽነት ለማስፋፋት እያደረገ ያለውን ጥረት አመስግነዋል። በቀጣይ የህብረተሰቡን የኃይል ጥያቄ በዘላቂነት ለመመለስና የክልሉን ኢንቨስትመንት ለማስፋፋት ተቋሙ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን በወቅቱ አጠናቆ ወደ ሥራ ለማስገባት ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራም አሳስበዋል። በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሠሜን ምስራቅ 2 ሪጅን የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽንና ጥገና መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ሀሰን መሀመድ በበኩላቸው በክልሉ አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት እንዲኖር ለማድረግ የተለያዩ ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል። በአፍዴራ ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ ባለው የኃይል ተጠቃሚ ማነስ ምክነያት የኃይል መዋዠቅ እንደሚስተዋል ያነሱት ዳይሬክተሩ ይህም ከጣቢያው ኃይል የሚያገኙ አካባቢዎች አስተማማኝ ኃይል እንዳያገኙ እያደረገ እንደሆነ አስታውቀዋል። እንደ አቶ ሀሰን ገለፃ በሠመራ ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ እየተከናወነ ያለው ተጨማሪ የሸንት ሪያክተር ተከላ ሥራ ከአፍደራ ማከፋፈያ ጣቢያ ኃይል የሚያገኙት ኢሬፕቲ፣ አፍዴራ፣ ቢዱ እና ኩሪ የተሰኙ ወረዳዎች የ24 ሠዓት የኃይል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከማድረጉም ባለፈ በሰመራ ማከፋፈያ ጣቢያ፣ በግሪዱና በብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከሉ ላይ የተረጋጋ ኃይል እንድኖር ለማድረግ ያግዛል። በአሁኑ ወቅት 10 የክልሉ ተወላጆች በሪጅኑ በሚገኙ ማከፋፈያ ጣቢያዎች ላይ በማከፋፈያ ጣቢያ ኦፕሬተርነት በልዩ ሁኔታ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ መደረጉንና በቀጣይ ይህ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል። በተቋሙ የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን ዘርፍ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሀብታሙ ውቤ በበኩላቸው በክልሉ የሚነሱ የኃይል ጥያቄዎችን በዘላቂነት ለመመለስ ተቋሙ የተለያዩ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል ብለዋል። በአሁኑ ወቅት በሠመራ ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ እየተከናወነ ያለው የሸንት ሪያክተር ተከላ ሥራ የክልሉን ጥያቄ ለመመለስ እየተከናወነ ላለው ሥራ አንዱ አካል እንደሆነም ጠቁመዋል። በቀጣይ የሠመራ ማከፋፈያ ጣቢያን አቅም በማሳደግ እና የመቆጣጠሪያ ብሬከሮችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመቀየር የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነም ሥራ አስፈፃሚው ተናግረዋል። በክልሉ የሰሜኑ ክፍል የሚነሱ የኃይል ጥያቄዎች በቀጣይ ሊከናወኑ ከታሰቡ ትላልቅ ፕሮጀክቶች ጎን ለጎን የተቋሙን የፋይናንስ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ እንደሚመለሱና ተቋሙም ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ አቶ ሀብታሙ አረጋግጠዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ህዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+2

photo content
+9

ከተንቀሳቃሽ የማከፋፈያ ጣቢያው ኃይል ሲያገኙ ለነበሩ አካባቢዎች ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት እየተሰራ ነው ……...///………. ከቦሌ ለሚ ቁጥር አንድ ባለ 132/33/15 ኪሎ ቮልት ተንቀሳቃሽ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ኤሌክትሪክ ሲያገኙ ለነበሩ አካባቢዎች ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት እየተሰራ መሆኑን የማዕከላዊ ሁለት ሪጅን የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን መምሪያ ገለፀ። የመምሪያው ዳይሬክተር አቶ አለማየሁ ዘበርጋ እንደገለፁት በጊዜያዊነት ታስቦ የተቀመጠው የተንቀሳቃሽ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ከ9 ዓመት በላይ አስቆጥሯል። 50 ሜጋ ቮልት አምፒር አቅም ያለው ትራንፎርመር የተገጠመለት የተንቀሳቃሽ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያው የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ዞን መገንባቱን ተከትሎ ኃይል መስጠት መጀመሩን አስታውሰዋል። ጣቢያው በአሁኑ ወቅት ለቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ዞን፣ አራብሳ፣ ሰሚት፣ ክሬሸር፣ ጎሮ እና አካባቢው ከ34 ሜጋ ዋት በላይ ኃይል እያቀረበ እንደሚገኝም ነው ዳይሬክተሩ የጠቀሱት። እንደ አቶ አለማየሁ ገለፃ በቦሌ ለሚ ቁጥር ሁለት ባለ 230/33/15 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ የተከናወነው የማስፋፊያ ሥራ ለኢንዱስትሪ ዞኑና ለአካባቢዎቹ በቂና አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ ያስችላል። ቀደም ሲል የቦሌ ለሚ ቁጥር አንድ ተንቀሳቃሽ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያን ይጠቀሙ የነበሩ አካባቢዎችን መስመር በመቀየር ከቦሌ ለሚ ቁጥር ሁለት የማከፋፈያ ጣቢያ ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ ለማድረግ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነውም ብለዋል። የቦሌ ለሚ ቁጥር አንድ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ተወካይ ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ማህሌት ታዬ እንደተናገሩት ጣቢያው አንድ ባለ 132 ኪሎ ቮልት ገቢ እንዲሁም በ33 ኪሎ ቮልት ሁለት እና በ15 ኪሎ ቮልት አራት ወጪ መስመሮች አሉት። እንደ ወ/ሮ ማህሌት ገለፃ በአሁኑ ወቅት ከተንቀሳቃሽ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያው ኃይል ሲያገኙ የቆዩ አካባቢዎች በቦሌ ለሚ ቁጥር ሁለት የኃይል ማከፋፈያ ስር እንዲጠቃለሉ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን ጠቁመዋል። የተንቀሳቃሽ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያው ድንገተኛ አደጋዎችን ለመከላከልና ፈጣን ምላሽ ለመስጠት በማያመች ቦታ ላይ እንደተቀመጠ የገለፁት ሥራ አስኪያጇ የሠራተኞችን እና የጣቢያውን ደህንነት በማስጠበቅ በኩል ትኩረት እንዲሰጠውም አሳስበዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ህዳር 17 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+3

በፕሪሚየር ሊጉ የሴቶች ቡድን ሲያሸንፍ ወንዶች ነጥብ ተጋርተዋል ………///………. በኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ባህርዳር ከነማን አንድ ለባዶ ሲረታ በወንዶች ፕሪሚየር ሊግ ደግሞ ነጥብ ተጋርቶ ወጥቷል፡፡ የኢትዮ-ኤሌክትሪክ እንስቶች ሙሉ የጨዋታ የበላይነት ባሳዩበት የ5ኛ ሳምንት ጨዋታ ባህርዳር ከነማ መከላከል ላይ የተመሠረተ የአጨዋወት ስልት ተግባራዊ አድርጓል። በሁለተኛው አጋማሽ ተቀይራ ወደ ሜዳ የገባችው ሀና ሲሳይ በ90ኛው ደቂቃ ብቸኛዋን የማሸነፊያ ጎል ከመረብ ማሳረፍ ችላለች። የኢትዮ-ኤሌክትሪኳ ሃና ሲሳይ የጨዋታው ኮከብ በመሆን ተሸላሚ ሆናለች። ይህ በእንዲህ እንዳለ ትናንት ምሽት በድሬዳዋ ስቴዲየም በተከናወነው የኢትዮጵያ የወንዶች ፕሪሚየር ሊግ 8ኛ ሳምንት ጨዋታ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ከመቻል ጋር አቻ ተለያይቷል። ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ናትናኤል ገ/ጊዮርጊስ በ57ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ጎል አንድ ለባዶ ሲመራ ቢቆይም በ92ኛው ደቂቃ በተሰጠበት የፍፁም ቅጣት ምት ነጥብ ሊጋራ ችሏል። ሁለቱ ክለቦች በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ አንደኛ እና ሶስተኛ ደረጃ የሚገኙ በመሆናቸው ጠንካራ ፉክክር የታየበት ጨዋታ ያሳዩ ሲሆን መቻሎች መሀል ሜዳውን ተቆጣጥረው በመጫወት ጫና ለማድረግ ሲሞክሩ በአንፃሩ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ የመስመር ኳስ ለመጠቀም ጥረት አድርገዋል። ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ በ13 ነጥብ በሊጉ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። በመጪው ህዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም በሚካሄደው 9ኛ ሳምንት የወንዶች ፕሪሚየር ሊግ መርሃግብር ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ከድሬዳዋ ከተማ ጋር ይጫወታል። ህዳር 20 ቀን 2017 ዓ.ም በሚካሄደው 6ኛ ሳምንት የሴቶች የጨዋታ መርሃግብር ደግሞ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚገጥም ይሆናል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ህዳር 17 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+1

photo content
+9

የተቋሙ የሥራ ኃላፊዎች የቦሌ ለሚ የኃይል ማከፋፈያ  ጣቢያን ጎበኙ …...///.....… የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ ኃላፊዎች የቦሌ ለሚ ባለ 230/33/15 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያን ጎብኝተዋል። ጉብኝቱ የተካሔደው በኃይል ማከፋፈያ ጣቢያው የተከናወነው የማስፋፊያ ግንባታ ሥራ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ተከትሎ ነው። በጉብኝቱ ወቅት ለሥራ ኃላፊዎቹ ገለፃ ያደረጉት በማዕከላዊ ሁለት ሪጅን የማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽንና ጥገና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዮሐንስ ተስፋዬ እንዳስታወቁት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአካባቢው በ15 ኪሎ ቮልት የኃይል ተጠቃሚ ደንበኞች ቁጥር መጨመር ለማስፋፊያ ግንባታው ዋና ምክንያት ነው። የማስፋፊያ ሥራው የተለያዩ የሲቪልና የኤሌክትሮ ሜካኒካል ግንባታዎችን ጨምሮ አንድ ባለ 50 ሜጋ ቮልት አምፒር አቅም ያለው ትራንፎርመር የማስቀመጥ፣ የኃይል መቆጣጠሪያ ቤት ግንባታ፣ የጂ.አይ.ኤስ ስዊች ጊር ገጠማና በ230 ኪሎ ቮልት በኩል የቤይ ዕቃዎችን የመትከል እንዲሁም የፍተሻና የሙከራ ሥራዎችን እንደሚያጠቃልል ነው በጉብኝቱ ወቅት የገለፁት። አንድ ዓመት ከስድስት ወር በወሰደው የማስፋፊያ  ሥራ ስድስት ባለ 15 ኪሎ ቮልት ወጪ መስመሮች እንደተገነቡ የገለፁት ሥራ አስኪያጁ ይህም ለቦሌ አራብሳ፣ በሻሌና አካባቢው አስተማማኝ ኃይል ለማቅረብ እንደሚያስችል ተናግረዋል። የማዕከላዊ ሁለት ሪጅን የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን መምሪያ ዳይሬክተር አቶ አለማየሁ ዘበርጋ እንደገለፁት በሪጅኑ አቅም በጣቢያው የተከናወነው የማስፋፊያ ሥራ እንደ ተቋም የመጀመሪያ ሊባል የሚችል ነው። በኃይል ማከፋፈያ ጣቢያው በተከናወነው የማስፋፊያ ግንባታ አዳዲስ መሐንዲሶች እና የቴክኒክ ባለሙያዎች የልምድና የዕውቀት ሽግግር እንዲያገኙ በር የከፈተ ነውም ብለዋል። የማስፋፊያ ሥራው 15 ሚሊየን ብር ወጪ እንደተደረገበት የገለፁት አቶ አለማየሁ ግንባታው በሪጅኑ አቅም በመከናወኑ ተቋሙን ከተጨማሪ ወጪ ማዳን መቻሉን ጠቅሰዋል። በተቋሙ የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን ዘርፍ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሀብታሙ ውቤ በበኩላቸው የተከናወነው የማስፋፊያ ሥራ አዲስ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ከመገንባት ጋር እኩል ነው። በኃይል ማከፋፈያ ጣቢያው የተከናወነው የማስፋፊያ ሥራ በአካባቢው ለረጅም ዓመታት ተገንብተው የኃይል አቅርቦት ሳያገኙ ለቆዩ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እፎይታን የሚሰጥ እንደሆነም ነው የገለፁት። በጣቢያው ዝግጁ የተደረጉት አዳዲስ ወጪ መስመሮች ለህብረተሰቡ ኃይል መስጠት እንዲችሉ ለማድረግ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በኩል የማሰራጫ መስመሮች ዝርጋታ መጀመሩንም ነው ያስታወቁት። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ህዳር 16 ቀን 2017 ዓ.ም