en
Feedback
ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

Open in Telegram

ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።

Show more
611
Subscribers
No data24 hours
+17 days
-1030 days
Posts Archive
❤ በአንዲት ዕለት የሶርያው ንጉሥ ሚስት ቅዱስ አውሳብዮስን አይታው እጅግ ወደደችው፡፡ ከባሮቿም ውስጥ ሁለቱን ልካ ካስመጣችው በኋላ በወርቅ አጊጣ በሐር በተነጠፈ አልጋ ላይ ሆና ጠበቀችው፡፡ከእርሷም ጋር እንዲተኛ ስትጠይቀው "እኔስ ሚስቴንም እንኳን በግብር ያላወኩ ነኝና ተይኝ ንጉሡ ባልሽ በቤት ባይኖር ሰውም ባያየን እግዚአብሔር ግን ያየናልና እንዴት በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአት እሠራለሁ? "በማለት ትቷት ሊወጣ ሲል ልብሱን ያዘችው፡፡ እርሱም ሮጦ በማምለጥ ቤተ ክርስቲያን ሲገባ እርሷ ግን በመጮህ ባሮቿ ሲመጡላት" ክፉ ነገርን አድርጎብኝ ሄደ" ብላ በሐሰት ተናገረች፡፡ ጭፍሮቿም ቅዱስ አውሳብዮስን ከቤተ ክርስቲያን አውጥተው እየደበደቡ ወደ ንግሥቲቱ አመጡት፡፡ እጆቹንና እግሮቹንም አሥረው ከከተማ ውጭ በአራት ዕንጨቶች ላይ አሰቀለችው፡፡ ከባሮቿም ውስጥ አንዲቱ በንግሥቲቱ ተልካ ሄዳ አውሳብዮስን "ከተሰቀልክበት እንዲታወርድህ ለእመቤቴ ያለችህን እሺ በላት" አለችው፡፡ እርሱም "የአመንዝራን ቃል አልሰማም" አላት፡፡ ንግሥቲቱም እሺ እንዳላላት ስታውቅ አንገቱን በገመድ አሳንቃ 160 ፍላጻዎችን በሰውነቱ ውስጥ እንዲጭምሩበት አደረገች፡፡ጌታችንም ቅዱስ ሚካኤልንና ቅዱስ ገብርኤልን ልኮለት ፍላጻዎቹን ከሰውነቱ ውስጥ አወጡለትና ፍጹም ጤነኛ ሆነ፡፡ ንጉሡም ከሄደበት ሲመለስ ንግሥት ሚስቱን አውሳብዮስን ለስቅላትና ለሞት ያበቃችው በምን ምክንያት እንደሆነ ሲጠይቃት አንተ በሌለህበት ወደ መኝታ ቤቴ ገብቶ ሊናገሩት የማይገባ ነገር ጠየቀኝ በከለከልኩትም ጊዜ በሥራዩ አሳመመኝ" አለችው፡፡ንጉሡም ተቆጥቶ ቅዱስ አውሳብዮስን ከተሰቀለበት አስወርዶ ካስመጣው በኋላ ለምን ይህን እንዳደረገ ጠየቀው፡፡ አውሳብዮስም እውነቱን በነገረው ጊዜ ጭፍሮቹን ምስክር ይሆኑ ዘንድ ሲጠይቃቸው ንግሥቲቱ ስትጮህ ወደ ውስጥ ሲገቡ ያጋጠማቸውን መሰከሩ፡፡ ንጉሡም የሚስቱን ነገር አምኖ በመቀበል በንዴት የቅዱስ አውሳብዮስን ሰውነቱን በሰይፍ አስቆርጦ ሥጋውን እንደ ላም ሥጋ ቆራርጦ በምንቸት አድርጎ በእሳት እንዲበስል አደረገው፡፡ ነገር ግን አሁንም ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል ከምቸቱ አውጥተው ከሞትም አድነው በማስነሣት ፍጹም ጤነኛ አደርገው አቆሙት፡፡ ❤ ከሞት ከተነሣም በኋላ በአገሩ ውስጥ ሲሄድ ሰዎች አይተውት ለንጉሡ ስለነገሩት ንጉሡ ድጋሚ ካስመጣው በኋላ አራት ዛንጅሮች በአካላቶቹ ውስጥ በማስገባት እጅና እግሩን አሳስሮ በእሳት ውስጥ ጨመረው፡፡ የከበሩ ሁለቱ ቅዱሳን መላእክት አሁንም መጥተው ፈወሱት፡፡ መልአኩ ቅዱስ ዑራኤልም ነጥቆ ወደ ሰማይ አሳርጎት በዚያው በሰማይ 14ዓመት ኖረ፡፡ ከዚያም ወደ ምድር ተመልሶ መጥቶ ወንጌልን እያስተማረ 40 ዓመት ኖረ፡፡ በእርሱም ትምህርት 85ሺህ አረማውያን አምነው ተጠምቀዋል፡፡ ቅዱስ አውሳብዮስ በመጨረሻ ሰማዕትነቱንና ተጋድሎውን ፈጽሞ የካቲት13 ቀን በክብር ዐርፏል፡፡ጌታችንን፡ኢየሱስም ስሙ ለሚጠራ መታሰቢያውንም ለሚያደርግ እስከ ሰባት ትውልድ ሊምርለት ቃል ኪዳን ሰጠው፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ አውሳብዮስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                                ✝ ✝ ✝ ❤ #ቅዱስ_ሰርግዮስ፦ የዚህ ቅዱስ አባቱና እናቱ ደጎች ናቸው። የአባቱ ስም ቴዎድሮስ የእናቱም ስም ማርያም ነው። ዕድሜውም ሃያ ዓመት ሲሆነው በክብር ባለቤት በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይሞት ዘንድ አሰበ ወደ መኰንኑ ቆጵርያኖስም ቀርቦ በክብር ባለቤት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ታመነ መኰንኑም ጽኑ ሥቃይን ያሠቃዩት ዘንድ ያሥሩትም ዘንድ አዘዘ ጌታችንም ነፍሱን ወደ ሰማይ አምጥቀው የቅዱሳን ሰማዕታትን መኖርያ ያሳዩዋት ዘንድ አዘዘ አይታም ተጽናናች ከሥቃይ ከሕማሙም ፈወሰው። ❤ ቀሲስ አባ መጹንና ሁለት ዲያቆናትም ተጋድሎውን ሰሙ ያን ጊዜም ተነሥተው ወደ አትሪብ አገር ገዥ ቀርበው በክብር ባለቤት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ የጸና ግርፈትም ይገርፋቸው ዘንድ አዘዘ እንዲሁም አደረጉባቸው። ሕዝቡም ሁሉ በዙርያቸው ሁነው ይመለከቷቸው ነበር ስለ ቄሱና ከእርሱ ጋር ስላሉትም አዘኑ ቄሱ ግን ፊቱን ወጀርሳቸው መልሶ ገሠጻቸው አስተማራቸውም "በክብር ባለቤት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ፡፡ በቀናች ሃይማኖት እንዲህ ጽኑ" አላቸው ከዚህም በኋላ በውኋ ላይ ጸልዮ በላያቸው ረጨ በዚያንም ጊዜ በላያቸው ወርዶአልና የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ ተቀበለው በክብር ባለቤት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ ራሶቻቸውንም በሰይፍ ቆረጧቸው የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ። ከዚያም በኋላ ቄሱን ከውሽባ ቤት ማንደጃ ውስጥ ይጨምሩት ዘንድ መኰንኑ አዘዘ እግዚአብሔርም ከእሳት አዳነው። ከእግዚአብሔርም የታዘዘ መልአክ ተገለጠለትና እርሱ ስለ ክብር ባለቤት ክርስቶስ ስም ሦስት ጊዜ ምስክር እንደሚሆን አሰረዳው ከእሳት ማንደጃው ውስጥም አወጣው። መኰንኑም ወደ እስክድርያ አገር ላከው ተጋድሎውንና ምስክርነቱን በዚያ ፈጸመ የምስክርኘቱን አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ። ❤ ከዚያም በኋላ መኰንኑ ቆጵርያኖስ የከበረ ሰርግዮስን ያቀርቡት ዘንድ አዘዘ ታላቅ ሥቃይንም አሠቃየው የነሐስ መንኰራኵሮችንም አምጥተው ከውስጣቸው አስገብተው አበራዩት ሕዋሳቱም አራት ክፍል ሁኖ ሥጋው ሁሉ ተቆራረጠ ጌታችንም አድኖ ያለ ጉዳት በጤና አስነሣው። ዳግመኛም እንዲሰግድለት ጣዖትን አመጡ ቅዱሱ ግን ሲረግጠው ወድቆ ተቀጥቅጦ ደቀቀ መኰንን ቆጵርያኖስም አይቶ በክብር ባለቤት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመነ "አምላክ ቢሆን ራሱን ማዳን በቻለ ነበር" አለ። ❤ ከዚህም በኋላ የጭፍራ አለቃ ስሙ አውህዮስ የሚባል የከበረ ሰርግዮስን ፈልጎ ያዘው ቆዳውንም ገፈው በተቀላቀለ ኮምጣጤና ጨው ቊስሉን ያሹት ዘንድ አዘዘ ጌታችን ግን በሥቃዮች ላይ ያጸናውና ያበረታው፡ ነበር። እናቱና እኅቱም ሰምተው ወደርሱ መጡ በአዩትም ጊዜ በላዩ አለቀሱ ከኀዘንም ብዛት እኅቱ ነፍሷን አሳለፈች የከበረ ሰርግዮስም ስለ እኅቱ ወደ ጌታችን ጸለየ ከሞትም ድና በሕይወት ተነሣች። ያን ጊዜ የሰማዕታትን ገድል የሚጽፍ የአቅፋስ፡አገር ሰው የከበረ ዮልዮስ መጣ ገድሉንም ሁሉ ከእርሱ ተረዳ ለሥጋውም እንደሚያስብ ቃል ገባለት። ❤ ከዚህም በኋላ ደግሞ የከበረ ሰርግዮስን በመንኰራኵር ውስጥ ያሠቃዮት ዘንድ በጆሮዎቹ የእሳት መብራቶችን እንዲጨምሩ የእጆቹንና የእግሮቹን ጥፍሮች እንዲነቅሉ በአንገቱም ከባድ ደንጊያ አንጠልጥለው ከብረት ዐልጋ ላይ አስተኝተው ከበታቹ እሳትን እንዲያነዱ አውህዮስ አዘዘ እንዳዘዘውም አደረጉበት ጌታችን ኢየሱስ ያጸናውና ያለ ጥፋት በጤና ያስነሣው ነበር። የሠራዊት አለቃ አውህዮስም ማሠቃየቱን በደከመ ጊዜ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ፡አዘዘ የከበረ ሰርግዮስ ሰምቶ እጅግ ደስ አለው ወደ አባቱና ወደ እናቱ ወደ ወንድሞቹም ላከ ዘመዶቹ ሁሉም የእርሱ የሆኑ ሰዎችም መጡ በአፋም ልጓም ለጒመው ቸብቸቦውን ወደሚቆርጡበት ሲስቡት አገኙትና መኰንኑን የረከሱ ጣዖታቱንም ረገሙ መኰንኑም ከከበረ ሰርግዮስ ጋር ሁሉንም ቸብቸቧቸውን እንዲቆርጡ አዘዘ በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበሉ።

❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ  አሜን"። ❤              ❤ #የካቲት ፲፫ (13) ቀን። ❤ እንኳን #መልካም_ስም_አጠራርና ጣፋጭ ዜና ላለው ለሶርያ መስፍን ልጁ ለሆነ በሰማዕትነት ካረፈ በኋላ #ቅዱስ_ሚካኤልና_ቅዱስ_ገብርኤል ከሞት አስነሥተውት፤ #ቅዱስ_ዑራኤልም ነጥቆ ወደ ሰማይ አሳርጎት በዚያው በሰማይ 14 ዓመት ለኖረ፤ ተመልሶ ወደ ምድር መጥቶ 40 ዓመት ለኖረ በተአምራቱና በትምህርቱ 85ሺህ አረማውያንን አሳምኖ ላጠመቀ #ለተመሰገነ_ለሁለተኛው_ለቅዱስ_አውሳብዮስ ለምስክርነቱና ለዕረፍቱ በዓል፣ ለከበረ #ለቅዱስ_ሰርግዮስ ከአባቱና እናቱ ከወድሞቹም ከሌሎችም ብዙ ሰዎች ጋር ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓልና ለኅርማኖስ ልጅ ለታላቁ ሰማዕት #ለቅዱስ_ፊቅጦር ለልደቱ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከከበረ አባት ከእስክድርያ አገር ሠላሳ ሁለተኛ ሊቀ ጳጳስ #ከአባ_ጢሞቴዎስ ዕረፍት፣ #ከቅዱስ_ፋሲለደስ ልጅ #ከቅዱስ_ቴዎድሮስ ከምስክርነቱ መታሰቢያ፣ #ከአባ_ክፍላና_ከአባ_ኅብስት ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                    ✝ ✝ ✝ ❤ #ሰማዕቱ_ቅዱስ_ፊቅጦር፦ ለዚህ ቅዱስ የአባቱ ስም ኅርማኖስ ነው እርሱም ለዲዮቅልጥያኖስ የአማካሪዎቹና የሠራዊቱ አለቃ ነው ስለ አምልኮ ጣዖት ሥራ ምክሩና ንግግሩ ሁሉ ከእርሱ ጋራ ነበር የእናቱም ስም ማርታ ይባላል በክርስትናዋ የጸናች ብፅዕት ናት። ❤ ቅዱስ ፊቅጦርም በአደገ ጊዜ አባቱ ወደ ንጉሥ አቀረበው ንጉሡም በመንግሥቱ ውስጥ ሦስተኛ ማዕርግ አድርጎ ሾመው በዚያን ጊዜ ዕድሜው ሃያ ዓመት ነበረ። እርሱም የዚህን ዓለም ክብር ናቀ ሥጋ አይባላም ወይን አይጠጣም ዘወትርም ይጾማል ጸሎትንም ባለማቋረጥ በቀንና በሌሊት ይጸልያል። በክብር ባለቤት ክርስቶስ ስም የታሠሩትን ይጐበኛቸዋል ለድኆችና ለምስኪኖችም ይመጸውታል። ❤ የቅዱስ ቆዝሞስና ድምያኖስ እናት ቅድስት ቴዎዳዳን በገደሉዋት ጊዜ ንጉሡም ስለ መፍራት ሊቀብራት ማንም አልደፈረም። ይህ ቅዱስ ፊቅጦርም መጥቶ ሥጋዋን ወሰደ ከንጉሥ ስለሚመጣው ቅጣት ሳይፈራ ቀበራት። ጣዖት ስለ ማምለኩ አባቱን ዘወትር የሚገሥጸውና ብዙ ጊዜም የሚመክረው ሆነ አባቱም ወደ ንጉሥ ከሰሰው እንጂ አልሰማውም። ተከሶም ወደ ንጉሥ በአቀረቡት ጊዜ "አማልክት ያልሆኑ ርኲሳን ጣዖታትን ለሚያመልክ ሰነፍ ዝንጉ ልብ የለሽ ለሆነ ንጉሥ አላገለግልም። ከዛሬ ጀምሮ ለሕያው ንጉሥ ክርስቶስ እገዛለሁ የሰጠኸኝንም ገንዘብህን ንሣ" ብሎ በፊቱ ትጥቁን ፈትቶ ጣለለት። ❤ አባቱ ኅርማኖስም ወደ እስክንድርያ እንዲልከውና በኄርሜኔዎስ መኰንን ዘንድ በዚያ ፊቅጦር እንዲቀጣ ንጉሡን መከረው። በዚያን ጊዜም ከአደባባይ አወጡት እናቱም በብዙ ልቅሶ ልትሸኘው መጣች። እርሱም ሲመግባቸው ስለ ነበረ የታሠሩ ምዕመናን ስለ ድኆችና ምስኪኖች ስለ ሙት ልጆችና ስለ ባልቴቶች የሚሹትን በመስጠት እንድትጐበኛቸው አዘዛት ከዚያም አፉን ለጉመው ወሰዱት። ❤ በእስክንድርያ አገር ወደ መኰንኑ ኄርሜኔዎስ ዘንድ በደረሰ ጊዜ ታላቅ ሥቃይን አሠቃዩት የእግዚአብሔርም መልአክ ወደ ሰማያት አውጥቶ ስለ ክብራቸው ለመናገር የሚያስጨንቁ የብርሃን ማደሪያዎችን አሳይቶ ወደ መኖሪያው መለሰው። መኰንኑም በእሳት በአፈሉት በዝፍት፣ በዲን ደግሞ አሠቃየው ከዚያም በብረት አልጋ ላይ አስተኝተው ከበታቹ እሳትን አነደዱ። ደግመው ከውሽባ ማንደጃ ውስጥ ጨመሩት በየአይነቱ በሆነ ሥቃይም አሠቃዩት የክብር ባለቤት ጌታችንም ያጸናውና ከሥቃዩ ያስታግሠው መልአኩንም ልኮ ከቊስሉ ይፈውሰው ነበር። ❤ ከዚህም በኋላ ወደ እንዴናው ከተማ ላከው በዚያም ታላቅ ሥቃይን አሠቃዩት ምላሱን ቆረጡ። በእሳት ያጋሉዋቸውን ችንካሮች በጐኖቹ ውስጥ ጨመሩ እግዚአብሔር ግን አጽንቶ አስታግሦ ያለ ጉዳት በደኅና ያነሣዋል። ከዚህም በኋላ በዚያ በረኃብ እንዲሞት ከዱር ባለ ግምብ ውስጥ አሠሩት። እርሱ ግን መጥረብ የሚያውቅ ስለሆነ ላይዳዎችን በመጥረብና በመሸጥ በየጥቂቱ እየተመገበ የቀረውን ለድኆች እየሰጠ ኖረ። አንድ መኰንንም መጥቶ በዚያ ግምብ አቅራቢያ አደረ ስለ ቅዱስ ፊቅጦርም እርሱ የንጉሥ የሠራዊት አለቃ የሆነ የኅርማኖስ ልጅ እንደሆነ ነገሩት። መኰንኑም ወደርሱ አቅርቦ ብዙ ሸነገለው ባልሰማውም ጊዜ ያሠቃዩት ዘንድ አዘዘ ጅማቶቹን መዘዙ አፋን መቱት ቊልቊል ሰቀሉት በእጆቹ ላይ ከባድ ደንጊያ አንጠልጠሉ። ከዚያም ከሚነድ እሳት ውስጥ ጨመሩት ሙጫ፣ አደሮ፣ ማርና ዘይትን አፍልተው በላዩ ደፉበት በማበራያም አበራዩት አፉንም በአሞትና በእሬት አመረሩት ዐይኖቹንም አወለቁት ደግመውም ዘቅዝቀው ሰቀሉት። የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጾለት አጸናው አረጋጋው። ሥሮቹንም ሕዋሳቶቹን በቦታቸው መለሰለትና አዳነው። ❤ አንዲት ዓሥራ አምስት ዓመት የሆናት ብላቴና ነበረች ቅዱስ ፊቅጦርን ሲአሠቃዩት በቤቷ መስኮት ታየው ነበር። መላእክትም በእጆቻቸው አክሊሎችን ይዘው እነርሱም በቅዱስ ፊቅጦር ራስ ላይ ሲያኖሩአቸው አይታ እንዴት እንዳየች ለአሕዛብ ነገረቻቸው እጅግም አደነቁ ከእርሳቸውም ብዙዎች በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምነው በሰማዕትነት ዐረፉ። ያቺም ብላቴና በጌታችን አመነች መኰንኑም ራሷን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ። የሕይወት አክሊልንም ተቀበለች ሁለተኛም የአመኑትን ሁሉ ራሳቸውን እንዲቆርጡአቸው አዘዘ የሕይወትንም አክሊል ተቀበሉ። ❤ ከዚህም በኋላ የከበረች የቅዱስ ፊቅጦርን ራስ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ ተጋድሎውንም ሚያዝያ 27 ፈጽሞ የሕይወትና የድል አክሊል ተቀበለ። ምዕመናን ሰዎችም ሥጋውን ወስደው በከበሩ ልብሶች በድርብ በፍታ ገነዙት። እናቱ ማርታም ከአንጾኪያ እስክትመጣ በንጹሕ ቦታ አኖሩት በመጣችም ጊዜ ከዚያ ወሰደችው። ውብ ቤተ ክርስቲያንም ሠርታ ሥጋውን በውስጥዋ አኖረች ከእርሱም ታላላቅ ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን የቅዱስ ፊቅጦር በረከቱም ከእኛ ጋራ ለዘላለም ትኑር አሜን። ምንጭ፦ የሚያዝያ 27 ስንክሳር።                                              ✝ ✝ ✝ ❤ #ሰማዕቱ_ቅዱስ_አውሳብዮስ_ዘሀገረ_ሶርያ፦ ይኽም ቅዱስ የሶርያው መስፍን ልጅ ነው፡፡ ለርሱም መንፈስ ቅዱስን የተመላች ስሟ አውሎፊያ የምትባ እኅት አለችው ይህንንም በተግሣጽና በጥበብ በማስተማር ካሳደጉት በኋላ የሮሜውን ንጉሥ ልጅ በታላቅ ክብር አጋቡት፡፡ በሠርጉም ዕለት ወደ ቅድስት ወደሆነችው ወደ እኅቱ ዘንድ ገብቶ "እስቲ ምከሪኝ ልቤ ይህን ጋብቻ አይሻውም ዓለምን ንቆ መተውን እንጂ" አላት፡፡እኅቱም "የዚህ የኃላፊው ዓለም ጣዕም ምን ይጠቅምሃል?እንደ ሊቀጳጳሳት ድሜጥሮስ በድንግልና መኖር ይሻልሃል" አለችው፡፡ ምሽትም በሆነ ወደ ሙሽራይቱ ጫጉላ ቤት ገብቶ የእነርሱ ውበትና ደምግባት እንደሚጠፋ ከዚህም ይበልጥ የሚጠቅማቸውን የጽድቅ ሥራ በመሥራት ድንግልናቸውን መጠበቅ እንዳለባቸው ሙሽራይቱን አዋያት፡፡ ሙሽራይቱም በሀሳቡ ተስማምታ ድንግልናቸውን በመጠበቅ በጾም በጸሎት እየዋሉ ሌሊትም ከባሕር ውስጥ፡ገብተው፡ቆመው ሲጸልዩ ያድሩ ጀመር፡፡ አትራ ወደምትባል ቤተ ክርስቲያን ሄደው አራት እልፍ ይሰግዳሉ፡፡

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤            ❤ #የካቲት ፲፪ (12) ቀን። ❤ እንኳን #ለኢትዮያዊው_ጻድቅ አጽፋቸውን አንጥፈው ዓባይ ወንዝ ለተሻገሩት፣ የንጉሡ ልጅ ሞቶ ሊቀበር ሲሂድ ጥላቸው ሲያርፍበት ከሞት ላስነሱት ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ሠርጸ_ጴጥሮስ ለዕረፍታቸው በዓል፣ ለኢትዮጵያኑ ሰማዕታት (#በ1929ዓ.ም #የካቲት_12_ቀን_ከ30,000 በላይ ኢትዮጵያውያን አባቶች፣ እናቶች፣ ወጣቶችና ሕፃናት በሮማዊው የፋሽስት ጦር ሰማዕትነት ለተቀበሉበት) በዓል በሰላም አደረሰን።                             ✝ ✝ ✝ ❤ #አቡነ_ሠርጸ_ጴጥሮስ፦ የትውልድ አገራቸው ሸዋ ደብረ ጽላልሽ ሲሆን በሕፃንነታቸው ወደ ወሎ ሄደው ሐይቅ እስጢፋኖስ ገብተው ብዙ ተጋድለዋል፡፡ከተጋድሎአቸውም በኋላ በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ እጅ መነኰሱ፡፡ በገዳሙ ብዙ ካገለገሉ በኋላ በመልአክ ትእዛዝ ወደ ጎጃም ሲሄዱ ዓባይን የተሻገሩት አጽፋቸውን አንጥፈው እርሱን እንደ ጀልባ ተጠቅመው ነው፡፡ ጻድቁ ታላቋን ተድባበ ማርያምን ለ41ዓመት አጥነዋል፡፡ ❤ የንጉሡ ልጅ ሞቶ ሊቀብሩት ሲወስዱት የአቡነ ሠርጸ፡ጴጥሮስ ጥላቸው ቢያርፍበት ከሞት አፈፍ ብሎ ተነሥቶ ድኖ "አምላከ አቡነ ሠርጸ ጴጥሮስ" ብሎ ፈጣሪውን አመስግኗል፡፡ ጻድቁ ሲያርፉም መቋሚያቸው አፍ አውጥታ ተናግራለች፤ ርዕደተ መቃብራቸው ሲፈጸምም እንባ አፍስሳ አልቅሳላቸዋልች፡፡ ይህቺ ተአምረኛ መቋሚያቸው ዛሬም ጎጃም ውስጥ መካነ መቃብራቸው ባለበት በደብረ ወርቅ ገዳም ትገኛለች፡፡ ጻድቁ ደብረ ወርቅ ገዳምን እንደ መሶብ አንሥተው አስባርከዋታል፡፡ አቡነ ሠርፀ ጴጥሮስ የካቲት12 ቀን ያረፉ ሲሆን ዐፅማቸውም በታላቋ ደብረ ወርቅ ይገኛል፡፡ ከሰማይ የወረደላቸው የወርቅ መስቀላቸውም በዚያው ይገኛል፡፡ጸበላቸው እጅግ ፈዋሽና ኃይለኛ ከመሆኑም በላይ በሰውነት ውስጥ የሚገኝ በሽታንና አጋንንትን የሚያስወጣበት መንገድ ለየት ያለው፡፡ ከአቡነ ሠርጸ ጴጥሮስ ረድኤት በረከትን ያሳትፈን። በጸሎታቸውም ይማረን!። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን።                

❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤            ❤ #የካቲት ፲፪ (12) ቀን። ❤ እንኳን #ለመላእክት_አለቃ ለከበረ #ለቅዱስ_ሚካኤል ወደ ረዓይታዊ ወደ ሶምሶን ተልኮ ኃይልን ሰጥቶት ጠላቶቹን ድል እንዲያደርግ ለረዳበት ወራዊ መታሰቢያ በዓል፣ ተጋዳይ ፍጹም የዋሕና ትሑት ለሆነው ለከበረ አባት #ለአባ_ገላስዮስ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ #ከዶርቃስ ከመታሰቢያው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                               ✝ ✝ ✝ ❤ #የከበረ_ቅዱስ_ሚካኤልን በዚች ዕለት እግዚአብሔር ወደ ረዓይታዊ ወደ ሶምሶን ላከው የፍልስዔም ሰዎች ሊገድሉት በጠላትነት በተነሡበት ጊዜ ድል እስከ አደረጋቸውና እስከ ገደላቸው ድረስ ረዳው ኃይልንም ሰጥቶ በአህያ መንጋጋ ከእርሳቸው አንድ ሺህ ሰዎችን ገደለ። ተጠምቶም ለሞት በተቃረበ ጊዜ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ተገለጠለትና አጸናው እግዚአብሔር ከአህያ መንጋጋ አጥንት ውኃን አፈለቀለትና ጠጥቶ ዳነ። ❤ ዳግመኛም ከሚስቱ ጋር ተስማምተው ዐይኖቹን አሳውሩ የራሱንም ጠጒር ላጩ አሠሩትም ከዚያም በኋላ ለጣዖቶቻቸው በዓልን በአዘጋጁ ጊዜ ሶምሶንን ወደ ጣዖቶቻቸው ቤት ወሰዱት በዚያም ሦስት ሽህ ያህል ሰዎች ተሰብስበው ነበር የከበረ ቅዱስ ሚካኤልም ተገለጠለትና ኃይልን መላው የዚያንም ቤት ምሰሶዎች ነቀላቸው ቤቱም በላያቸው ወድቆ ከእርሱ ጋር ሁሉንም ገደላቸው። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                                                         ✝ ✝ ✝ ❤ #አባ_ገላስዮስ፦ የዚህ ቅዱስ ወላጆቹ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ምዕመናን ናቸው በጥበብንና የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት አስተማሩትና ዲቁና ተሾመ። ከታናሽነቱም ጀምሮ ይህን ዓለም ንቆ ተወ የክብር ባለቤት የሆነ የክርስቶስንም ቀንበር በመሸከም በምንኵስና ሁኖ በትጋት እየጾመ እየጸለየና እየሰገደ ታላቅ ተጋድሎን ተጋደለ እግዚአብሔር መርጦት በአስቄጥስ ገዳም ባሉ መነኰሳት ላይ ቅስና ተሾመ። ተጋድሎውንና አገልግሎቱን እየፈጸመ ሳለ ለአባ ጳኵሚስ እንደ ተገለጠ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጠለትና መነኰሳትን ሰብስቦ ፈሪሀ እግዚአብሔርን የምንኵስናንም ሕግ ያስተምራቸው ዘንድ አዘዘው በዚያንም ጊዜ ብዙዎች መነኰሳትን ሰበሰበ መንፈሳዊ የሆ የአድነት ማኅበርራዊ ኑሮንም ሠራላቸው እርሱ በመካከላቸው እንደ መምህር አልሆነም ከእርሳቸው እንደሚያንስ አገልጋይ እንጂ። ❤ ይህ አባት የዚህ ዓለም ጥሪት ሁሉ ንቆ የተወ ሆነ እጅግም የዋህና ቸር ሆነ ከብሉይና ከሐዲስ መጻሕፍቶችም የተሰበሰበ አንድ ታላቅ መጽሐፍን አጻፈ ለማጻፊያውም ዋጋ ዐሥራ ስምንት የወርቅ ዲናር አወጣ ከርሱ ሊጠቀሙ በሚፈልጉ ጊዜ መነኰሳቱ እንዲያነቡት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በአትሮንስ ላይ አኖረው። አንድ መጻተኛ ሰውም አረጋዊ አባ ገላስዮስን ሊጎበኝ በገባ ጊዜ ያንን መጽሐፍ አየውና አማረው በጭልታም ከዚያ ሰርቆ ወጣ ወደ ከተማ ውስጥም በገባ ጊዜ ሊሸጠው ወደደ አንድ ሰውም ዋጋው "ምን ያህል ነው" አለው እርሱም "ዐሥራ ሰባት የወርቅ ዲናር ስጠኝ" አለው። ያ የሚገዛውም ሰው "ያልከውን እሰጥሃለሁ ነገር ግን ለወዳጄ እስካሳየው ታገሰኝ" አለው ያሳየውም ዘንድ ወደ አባ ገላስዮስ ወሰደውና "ተመልከትልኝ መልካም ከሆነ እገዛዋለሁ" አለው አባ ላስዮስም "ያመጣውን ሰው ከአንተ ምን ያህል ፈለገ" አለው "ዐሥራ ሰባት የወርቅ ዲናር" አለው ቅዱስ ገላስዮስም "መጽሐፉ መልካም ነው ዋጋውም ቀላል ነው ግዛው" ብሎ መለሰለት። ወደ ሌባውም በተመለሰ ጊዜ አባ ገላስዮስ የነገረውን ሠውሮ "ለአባ ገላስዮስ አሳየሁት እርሱም ዋጋው በዝቷል አለኝ" አለው፡ሌባውም "ያ ሽማግሌ ሌላ የተናገረህ ነገር የለምን" አለው "አዎን የለም" አለው። ሌባውም "እንግዲህ እኔ አልሸጠውም" ብሎ ወደ አባ ገላስዮስ ሒዶ ከእግሩ በታች ወድቆ ለመነው "ሰይጣን አስቶኛልና ይቅር በለኝ መጽሐፍህንም ውሰድ" አለው የከበረ ገላስዮስም "እኔ መጽሐፉን መውሰድ አልሻም" አለው። ሌባውም በፊቱ እያለቀሰና እየሰገደ ብዙ ለመነው በብዙ ድካምም መጽሐፉን ተቀበለው ማንም ያወቀ የለም። እግዚአብሔር ትንቢት የመናገርን ሀብት ሰጥቶት ድንቆች ተአምራቶችን አደረገ። ❤ በአንዲትም ዕለት ለገዳሙ መነኰሳት ዓሣ አመጡ ባለ ወጡ ዓሣን አብስሎ በቤት ውስጥ አኑሮ አንዱን ብላቴና ጠባቂ አድርጎ ወደ ሥራው ሔደ ብላቴናውም ከዚያ ዓሣ በላ። ባለ ወጡ በመጣ ጊዜ ተበልቶ አገኘውና በብላቴናው ላይ ተቆጥቶ "አረጋዊ አባቶች፡ ሳይባርኩት እንዴት ደፍረህ በላህ" አለው የቊጣ መንፈስም በልቡ አደረና ብላቴናውን ረገጠው ወዲያውኑ ሞተ እንደሞተም አይቶ ደነገጠ ታላቅ ፍርሀትንም ፈራ ሒዶ ለአባ ገላስዮስ የሆነው ሁሉ ነገረው እርሱም "ወስደህ ከቤተ መቅደሱ ፊት አስተኛው" አለው ሰውየውም እንዳዘዘው አደረገ ወደ ማታ ጊዜም አረጋውያን መነኰሳት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተሰብስበው የማታውን ጸሎት አድርሰው ወጡ አረጋዊ አባ ገላስዮስም በወጣ ጊዜ የሞተው ብላቴና ተነሥቶ በኋላው ተከተለው ከመነኰሳትም ማንም አላወቀም እርሱም የገደለውን ባለ ወጥ ለማንም እንዳይናገር አዘዘው። ❤ የተመሰገነ አባ ገላስዮስም ያማረ ትሩፋቱንና ተጋድሎውን ፈጽሞ አድርሶ እግዚአብሔርንም አገልግሎ ይህንንም በጎ መታሰቢያን ትቶ ከዚህ ከኃላፊው ዓለም የሚለይበት ሲደርስ የካቲት12 በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ገላስዮስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ለዘላለሙ ትኑር አሜን። ምንጭ፦የየካቲት12 ስንክሳር።                             ✝ ✝ ✝ ❤#የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ይትዐየን መልአከ እግዚአብሔር ዐውዶሙ። ለእለ ይፈርህዎ ወያድኅኖሙ። ጠዐሙ ወታእምሩ ከመ ኄር እግዚአብሔር"። መዝ 33፥7-8። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 25፥31-ፍ.ም።                              ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ወበኀቤየሰ ፈድፋደ ክቡራን አዕርክቲከ እግዝኦ። ወፈድፋደ ፀንዑ እምቀደምቶሙ። እምኌቆሙ እምኆፃ ይበዝኁ"።  መዝ 138፥17-18። የሚበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 5፥6-ፍ.ም፣ ይሁ 1፥9-19 እና የሐዋ ሥራ 28፥30-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 20፥24-29። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ ሚካኤል በዓል፣ የአቡነ ሠርጸ ጴጥሮስ የዕረፍት በዓልና የጾም ወራት ለሁላችንም ይሁንልን።                  

                           ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "እስመ ዚአየ ውእቱ ኵሉ አራዊተ ዘገዳም። እንስሳ ገዳምኒ ወአልሕምት። ወአአምር ኵሎ አዕዋፈ ሰማይ"። መዝ 49፥10-11። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ጢሞ 4፥14-19፣ ያዕ 3፥5-11 እና የሐዋ ሥራ 14፥19-ፍ.ም የሚነበበው ወንጌል ማር 1፥12-16። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ባስልዮስ ቅዳሴ ነው። መልካም በዓልና የጾም ወራት ለሁላችን ይሁንልን።               

❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤            ❤ #የካቲት ፲፩ (11) ቀን። ❤ እንኳን #ለተጋዳይ_ለታላቁ አባት በቀንና በሌሊት ሰባት መቶ ጊዜ አቡነ ዘበሰማያትን ከስግደት ጋር እየጸለ ለአርባ ዓመት በገዳም ለኖረውና በኋላም ወደ በረሃ ከአንዲት ታናሽ ዋሻ ውስጥም ገብቶ እየተጋደለ ብቻውን ለኃምሳ ዓመት ለኖረ፤ ሁለት አንበሶች እንደሰው ለሚላኩለት #ለባለ_አንበሳው_ለአባ_አውሎግ ለዕረፍት በዓል፣ ለሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ለከበረ ለአባት #ለአባ_በላትያኖስ በንጉሥ ዳኬዎስ እጅ ለአንድ ዓመት ያህል ተሰቃይቶ ኋላም አንገቱን በመሰየፍ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓልና #ለአባ_ስልዋኖስ ረድእ #ለአባ_በትራ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከኤጲስቆጶስ #ከአባ_አብርሃም_ከመነኰስ_ከአባ_መቃቢስና #ከኮንቲ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ  ረድኤትና በረከት ያሳትፈን።                               ✝ ✝ ✝ ❤ #ባለ_አንበሳው_አባ_አውሎግ፦ የዚህ ቅዱስ ወላጆች ፍጹም በወርቅና በብርም የበለጸጉ ናቸው። በአንዲትም ዕለት "አውሎግ ያለህን ገንዘብህን ሁሉ ሽጠህ ለድኆች ሰጥተህ መከራ መስቀሉን ተሸክመህ ና ተከተለኝ" የሚለውን የከበረ የወንጌልን ቃል አሰበና ወዲያውኑ ገንዘቡን ሁሉ ለድኆችና ለችግረኞች በትኖ ወደ አባ አውሎጊን ሔደ እርሱም በደስታ ተቀበለው። ስለ እርሱ እንዲህ የሚለውን ራእይ አይቶ ነበር "እነሆ ወዳንተ ጐልማሳ ይመጣል ተቀበለውና ከሚያገለግሉ መነኰሳት ጋር ቀላቅለው"። እየፈተነውም ሦስት ዓመት ያህል ኖረ ፍጹም የሆነ ቅድስናውንም በአየ ጊዜ የምንኵስናን ልብስ የመላእክትንም አስኬማ አለበሰው። ከሰንበትም እስከ ሰንበት እየጾመ በብዙ ተጋድሎ ኖረ ምግቡም እንጀራና ጨው ነበረ በቀንና በሌሊትም ሰባት መቶ ጊዜ አቡነ ዘበሰማያትን ስግደት ጋር ይጸልያል በዚህም ተጋድሎ አርባ ዓመት ኖረ። ❤ ከዚያም በኋላ ያሰናብተው ዘንድ መምህሩ አባ አውሎጊንን ማለደውና ወደ በረሀ ሔደ ከአንዲት ታናሽ ዋሻ ውስጥም ገብቶ እየተጋደለ ኃምሳ ዓመት ኖረ። ለፍላጎቱም የሚያገለግሉት ሁለት አንበሶችን እግዚአብሔር ሰጠው በአንዲትም ዕለት ታመመ አንሶቹንም "እጠጣ ዘንድ የሞቀ ውኃ እሻለሁ" አላቸው። አንዱ አንበሳም ወደ ተራራ ሒዶ እረኛ አግኝት ወደ አባ አውሎግ አመጣው በአየውም ጊዜ ሰገደለትና "አባቴ ሆይ ምን ትሻለህ" አለው እርሱም "የሞቀ ውኃ ታጠጣኝ ዘንድ እሻለሁ" አለው እንዳለውም አደረገለት ከዚህም በኋላ አንበሳው እረኛውን ወደ ቦታው መለሰው። ያም እረኛ "ለእግሩ ተረከዝ ዓለሙ ሁሉ መጠኑ የማይሆን ጻድቅ ሰው አገኘሁ" ብሎ ለሰው ሁሉ ተናገረ በሰሙ ጊዜም ሰዎች ሁሉ ወደርሱ ተሰበሰቡ፡ በሽተኞችንም ሁሉ አመጡለትና ፈወሳቸው። ❤ በዚያም ወራትም መምህሩ አባ አውሎጊን ጣዖትን የሚያመልኩ የፋርስ ሰዎችን ወደ ቀናች ሃይማኖት ለመመለስ ወደ ፋርስ አገር ሊሔድ ፈለገ ዳግመኛም ልጁ አውሎግን ከእርሱ ጋር ሊወስደው ወደርሱ መልክተኛ ሊልክ ሽቶ ሳለ መንፈስ ቅዱስ አንበሳውን አስገነዘበውና አጽፉንና ወንጌሉን አንሥቶ ተሸከመ። አባ አውሎግንም ጒዞን አመለከተው ተነሥቶም አንበሳውን ተከትሎ ወደ መምህር አውሎጊን ደረሰ እርሱም በደስታ ተቀበለው። ሲጓዝም ከጤግሮስ ወንዝ ደረሱ ውኃውም ተከፍሎላቸው ተሻገሩ ወደ አገሩም ውስጥ በደረሱ ጊዜ አስተማሩአቸው ወደ ቀናች ሃይማኖትም መለሷቸውና በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቋቸው። ❤ በአንዲትም ዕለት ደግሞ ቅዱሳን በተራቡ ጊዜ ምግባቸውን ይፈልጉላቸው ዘንድ አባ አውሎግ አንበሶችን አዘዘ ሒደውም እንጀራ በአህያ ላይ ጭኖ የሚጓዝ ሽማግሌ አገኙ ሕፃንም ከእንጀራው ጋር አለ። አህያውንም ወደ ቅዱሳን አመጡት ከድንጋጤም የተነሳ ብላቴናው ሞተ ቅዱሳንም ጸልየው ሕፃኑ ድኖ ተነሣ ቅዱሳንም ተመገቡ አንቦሶችም አህያውን ከእንጀራውና ከሕፃኑ ጋር ወደ ሽማግሌው መለሱት። ❤ ከዚህም በኋላ አባ አውሎግ ወደ በዓቱ ተመለሰና ጥቂት ታሞ የካቲት11 በሰላም ዐረፈ። በታላቅ ክብርም ተቀበረ እነዚያ አንበሶችም መቃብሩን እየጠበቁ ዐሥራ ሁለት ዓመት ኖሩ ከዚያም በኋላ ወደ ዱር ገቡ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ አውሎግ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ለዘላለሙ ትኑር አሜን።                               ✝ ✝ ✝ ❤ #አባ_በላትያኖስ፦ ይህም ቅዱስ ብልህና አዋቂ የሆነ ታላቅ ተጋድሎን የሚጋደል ነው በሮሜ አገርም ሊቀ ጵጵስና ተሹሞ በቅዱስ ጴጥሮስ ወንበር ላይ ዐሥራ ሁለት ዓመት በሰላም ኖረ ሕዝቡን የቀናች ሃይማኖትን እያስተማራቸው ሳለ መኰንኑ ፊልጶስ በንጉሥ ቀላውዴዎስ ላይ ተነስቶ በገደለው ጊዜ በርሱ ፈንታ ነገሠ በምእመናን ላይ ታላቅ መከራን አመጣ በዚህ በንጉሥ በዳኬዎስ እጅ ብዙዎች በሰማዕትነት ሞቱ። በዘመኑም ሰባቱ ደቂቅ ከእርሱ ሸሹ ሦስት መቶ ሰባ ሁለት ዓመት ተኝተው ነቁ እርሱም በኤፌሶን ከተማ መስጊድ ሠርቶ በውስጡ ጣዖታትን አኖረ ሰዎችን ሁሉ ለጣዖታት እንዲሠዉ አስገደዳቸው ለጣዖታት ያልሠዉትንም ገደላቸው። ❤ ይህ የከበረ በላትያኖስም የጣዖታት አምልኮን እንደሚቃወም ሕዝቡም በክብር ባለቤት በክርስቶስ ሃይማኖት ይጸኑ ዘንድ እንደሚያስተምር ንጉሥ በሰማ ጊዜ ወደ ሮሜ አገር ልኮ ወደ ኤፊሶን ከተማ አስመጣውና ለጣዖታት እንዲሠዋ ለመነው። እርሱም ግን ቃሉን አልሰማም ተሣለቀበት አማልክቶቹንም ረገመ እንጂ ንጉሥም ተቆጣ አንዲት ዓመት ያህልም ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃየው ማሠቃየቱንም በሰለቸ ጊዜ የካቲት11 ቀን በሰይፍ ራሱን ቆረጠው የምስክርነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም  በአባ በላትያኖስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ለዘላለሙ ትኑር አሜን።                             + + + ❤ የአባ ስልዋኖስ ረድእ አባ በትራ፦ ይህም ቅዱስ በደብረ ሲና ካለች በዓቱ በነበረ ጊዜ ትርኅምትን ይጠብቅ ነበር በራትም ጊዜ ለሥጋው የሚያሻውን ይመገባል። ፈርኑ በሚባል አገር ላይ ኤጲስቆጶስ በአደረጉት ጊዜ ትርኅምትን በማብዛት ሰውነቱን እጅግ አደከመ ደቀ መዛሙርቱ "አባታችን ሆይ በገዳም በበአትህ በነበርክ ጊዜ ትርኅምትን እንዲህ አላበዛህም ነበር" አሉት ይህም አባት እንዲህ አላቸው "ያን ጊዜ በገዳም በችግር ውስጥ ነበርኩ ዛሬ ግን ከብዙዎች መካከል በአንድነት አለሁ የምሻውም ሁሉ ብዙ አለኝ ነገር ግን ሥጋዬን ቀጥቼ ብገዛው ይሻላል" እንዲህም እየተጋደለ ኖረ ከዚህም በኋላ የካቲት10 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ በትራ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የየካቲት 11 ስንክሳር።                            ✝ ✝ ✝ ❤ "#ሰላም_ለበትራ_ረድአ_ስልዋኖስ_ወምእኑ። ኤጲስቆጶሰ ዘኮነ በሀገረ ፈርኑ። ከመ እንግር ጽድቆ ወኂሩቶ እዜኑ። ለአፉየ ወልሳንየ በመጠኑ። ዘይረድአኒ መንፈሰ ይፈኑ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የካቲት_11።

ሊቃነ ጳጳሳትና ኤጲስቆጶሳት የተላኩ መልክቶች ናቸው ወደ ምእመናንም ወንዞች ውኃዎችን እንደሚያፈልቁ እርሱ በመንፈስ ቅዱስ የሚያፈልቃቸው ሆኗልና። ❤ ይህንንም በጎ ሥራውን ሲፈጽም መልካም ጉዞውንም አከናውኖ ወደ በጎ ሽምግልና ደርሶ እግዚአብሔርንም አገልግሎ የካቲት10 በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም  በቅዱስ ኤስድሮስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ለዘላለሙ ትኑር አሜን።                               ✝ ✝ ✝ ❤ #የፋርስ_አገር_ኤጲስቆጶስ_አባ_ፊሎ፦ ይህንንም ቅዱስ ለእሳት እንዲሠዋ ለፀሐይም እንዲሰግድ የፋርስ ንጉሥ አዘዘው እምቢ በአለውም ጊዜ ታላቅ ሥቃይን አሠቃይቶ የካቲት10 ቀን ራሱን በሰይፍ ቆረጠው በመንግሥተ ሰማያት የሰማዕትነት አክሊል ተቀበለ። በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይገባል አሜን። ምንጭ፦ የየካቲት10 ስንክሳር።                            ✝ ✝ ✝ ❤ "#ሰላም_እብል_ዕረፍተ_ስሙ_ጽዑጠ። እምብዝኀ ገድሉ እንዘ እንግር ኅዳጠ። ዐሠረ ክርስቶስ ይትሉ #ሶበ_ዮስጦሳ_ተፈልጠ። መንገለ ወልዱ ወብእሲቱ ገጾ ኢሜጠ። ወአፍቅሮ ዘመድ ካዕበ በልቡ ኤሦጠ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የየካቲት_10።                           ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "አስተጋብዑ ሎቱ ጻድቃን። እለ ይገብሩ መሥዋዕተ ዘበሕጉ። ይነግራ ሰማያት ጽድቀ ዚአሁ"። መዝ 49፥5-6። የሚነበበው ወንጌል ማር 6፥30_34።                             ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦"አልቦ ነገር ወአልቦ ነቢብ ዘኢተሰምዐ ቃሎሙ። ውስተ ኵሉ ምድር ወፅአ ነገሮሙ። ወእስከ አጽናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ"። መዝ 18፥3-4። የሚነበቡት መዕልክታት 1ኛ ቆሮ 12፥4-28፣ ይሁ 1፥17-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 1፥12-15። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 10፥1-9። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱሳን ሐዋርያት ቅዳሴ ነው። መልካም የሐዋርያም የቅዱስ ያዕቆብ የዕረፍት በዓልና የጾም ወራት ለሁላችንም ይሁንልን።              

❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤            ❤ #የካቲት ፲ (10) ቀን። ❤ እንኳን #ከዐሥራ_ሁለቱ_ሐዋርያት ለአንዱ ለእልፍዮስ ልጅ #ለከበረ_ሐዋርያ_ለቅዱስ_ያዕቆብ በንጉሥ ቀላውዴዎስ ዘመን በአይሁድ እጅ በድንጋይ ተወግሮ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል፣ #ለኢትዮያዊያኑ_ጻድቅ_ለአቡነ_እንድርያስ ኤርትራ አገር የሚገኘው ታላቁ ገዳም ደብረ ጽጌ ሰፍኣ ለመሰረቱ #ለዘጠኝ_መቶ_ዘጠና_ዘጠኝ_ደቀ_መዛሙርቶች በአረማውያን እጅ ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓል (ታሪካቸውን የካቲት1 ይመልከቱ)፣ ለንጉሥ ኑማርያኖስ ልጅ ለከበረ #ለቅዱስ_ዮስጦስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል፣ ፈርማ ከሚባል አገር በገድል ለተጠመደ ምሁር ለሆነ ዐሥራ ስምንት ሺህ መጽሐፍቶችን ተግሣጻትና ድርሳናት ለጻፈ ለዓለሙ ሁሉ #መምህር_ለአባ_ኤስድሮስ ለዕረፍት በዓልና ለፋርስ አገር ኤጲስቆጶስ #ለአባ_ፌሎ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከከበሩ #ቅዱሳን_ከኒቅላዎስና_ከስምዖን ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                             ✝ ✝ ✝ ❤ #ሐዋርያው_ቅዱስ_ያዕቆብ_ወልደ_እልፍዮስ፦ ያስተምር ዘንድ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ እንዲህ ሆነ። ከእርሱ ለሚሰሙትም ሁሉ ብዙ ተአምራትን አደረገ። ንጹሕ በሆነ ልቡናም በእግዚአብሔር አመኑ። ራሳቸውንም አጸኑ። ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብም በልቡናው አሰበ። እንዲህም አለ። ሕዝቡ ከእርሱ ሰምተው እንዴት ያምናሉ አለ። እርሱም ሕዝቡ ወደተሰበሰቡበት ወደ ምኩራብ ገባ። ከአይሁድም የተቀመጡ የተሰበሰቡ ብዙ ሰዎችን አገኘ። በፍጹም ታላቅ ደስታ ያስምራቸው ዘንድም በመካከላቸውም ገባ። ለሁሉም በቃሉ ማስተማሩን አበዛ። ያለመፍራትም ሃይማኖቱን ገለጠ። አንድ ለሆነው ለእግዚአብሔር ልጅ ምስክር ሆነ። "የሕይወት ቃል ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም ሁሉ አምላክ ነው። በእውነትም የእግዚአብሔር ልጅ ነው። እርሱ ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ ከአብ ጋር ነበርና። እርሱ በአብ አለ፤ አብም በእርሱ አለ። እርሱ የአብ ቃል ነው። እርሱ ሰውን በአርአያችንና በምሳሌያችን እንፍጠር አለ። እርሱ በሰማይ አለ። እርሱ ከአባቱ ጋር አለ። እርሱ በኪሩቤል ሰረገላ ይቀመጣል። ሱራፌልም ያመሰግኑታል። እርሱ በድንግል ማርያም ማሕፀን የተወሰነ በልዕልና በገናንነቱ ሥልጣን ነው። እርሱ ድንግል ማርያም የወለደችው ጌታችን እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ሰው የሆነ አምላክ ነው"። አንድ ሰው ስንኳን ሳይፈራ በተሰበሰቡት መካከል የሐዋርያው ምስክርነት ይህ ነበር። በእውነት አንድ ለሆነው ለእግዚአብሔር ልጅ ልደትም ምስክር ሆነ። እርሱ ነበርና። በሞቱም፣ በትንሣኤውም፣ ወደ አባቱ ወደ ሰማይ ስለማረጉም ምስክ ሆነ። ለተሰበሰቡትም በክርስቶስ ስለማመን አስተማራቸው። ❤ የተሰበሰቡትም የሐዋርያውን ትምህርት በሰሙ ጊዜ ከእርሱ ጋር ካለው ከአባታቸው ከሰይጣን የተነሳ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ላይ ፈጽመው ተቆጡ። ሁሉም ተሰብስበው ተቀመጡ። የተሰበሰቡት ሁሉ ደሙን ፈለጉ። ነገሩን የሰሙትም የተባረከ ሐዋርያን ያዙት። ከንጉሥ ከቀላውዴዎስም ወሰዱት። የሐሰት ምስክሮችንም በእርሱ ላይ አስነሡ። ለንጉሡም "ይህን ጥፋተኛ ሰው በሀገሩ በአውራጃው ይዘናል" አሉት፤ "እኔ የእግዚአብሔር የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ነኝ ይላቸዋል። ለንጉሡ እንዳይገዙም ይከለክላል" አሉት። ስለተባረከው ሐዋርያ ይህን ነገር በሰማ ጊዜም እስከሚሞት ድረስ በድንጋይ ይወግሩት ዘንድ አዘዘ። አይሁድንም እግዚአብሔር ረገማቸው። ንጉሡ አይሁድን እንዳዘዛቸውም በድንጋይ ወገሩት። ከዚህ በኋላ ቡሩክ የሚሆን የእልፍዮስ ልጅ የሐዋርያው የቅዱስ የያዕቆብ ምስክርነት የካቲት ዐሥር ቀን ሆነ። በኢየሩሳሬም ቤተ መቅደስ ተቀበረ። ለአብ ለወልድና ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይገባል። ከሐዋርያው ከቅዱስ ያዕቆብ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። ምንጭ፦ ገድለ ሐዋርያት።                                                       ✝ ✝ ✝ ❤ #የንጉሥ_ኑማርያኖስ_ልጅ_ሰማዕቱ_ቅዱስ_ዮስጦስ፦ ይህም ቅዱስ በጦር ሜዳ እያለ እኅቱ ከሀዲ ዲዮቅልጥያኖስን አግብታ ንጉሥም አደረገችው ከጦርነትም በተመለሰ ጊዜ የክብር ባለቤት ክርስቶስን ዲዮቅልጥያኖስ ክዶ አገኘውና እጅግ አዘነ። የአገሩም ሰዎች በአዩት ጊዜ ወደርሱ ተሰብስበው ዲዮቅልጥያኖስን "እኛ እንገድለዋለን አንተም ጌታችን በመንግሥትህ ዙፋን ላይ ትቀመጣለህ" አሉት እርሱ ግን ይህን ስለአልፈለገ እንዳይገድሉት ከለከላቸው ከምድራዊት መንግሥት ሰማያዊት መንግሥትን መርጧልና። ❤ ከዚህም በኋላ ወደ ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ ቀርቦ በክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ ንጉሡም ፈርቶታልና "ጌታዬ ዮስጦስ ሆይ ይህን ታደርግ ዘንድ ያስገደደህ ማነው?" አለው የከበረ ዮስጦስም "በምስክርነቴ ደሜን እንዳፈስ ካልጻፍክ ሕዝቡን በአንተ ላይ አስነሥቼ ከመንግሥትህ እንደማስወጣህ የክብር ባለቤት ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሕያው ነው" ብሎ ማለ። በዚያንም ጊዜ ንጉሡ ፈርቶ ከሚስቱ ከታውክልያ ከልጁ ከአቦሊ ጋር ወደ ግብጽ አገር እንዲወስዱአቸው አዘዘ የእስክንድርያንም ገዥ አብዝቶ እንዲሸነግላቸው ምናልባት ልባቸው ቢመለስ እንዳያሳዝናቸውም አለዚያ እያንዳንዱን እንዲለያያቸው አዘዘው። ❤ ወደ ግብጽ አገርም በደረሱ ጊዜ ከእርሳቸው ጋር የንጉሥ ደብዳቤ አገልጋዮችም አሉ። የእስክንድርያም ገዥ በአያቸው ጊዜ እጅግ ፈራ ሊሸነግለውም ጀምሮ ቅዱስ ዮስጦስን "ጌታዬ እንዲህ አታድርግ ክብርህ ይሻልሃል" አለው የከበረ ዮስጦስም "ነገር አታብዛ" አለው መኰንኑም ፈርቶ ቅዱስ ዮስጦስን ወደ ላይኛው ግብጽ ወደ እንዴናው ከተማ ሰደደው ልጁ አቦሊን ወደ አገረ ብስጣ ሚስቱ ታውክልያን ወደ አገረ ፃ ላካቸው ከአገልጋዮቹም የሚአገለግሏቸው አንዳንድ ሰጣቸው የከበረ ዮስጦስንም በእንዴናው ከተማ ብዙ ከአሠቃዩት በኋላ የካቲት10 ቀን ራሱን ቆረጡት የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበለ ከሥጋውም ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ ለበሽተኞችም ታላቅ ፈውስ ሆነ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕትነት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                            ✝ ✝ ✝ ❤ #አባ_ኤስድሮስ_ዘአገረ_ፈርማ፦ የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ በምስር አገር የከበሩ ባለጸጎች ናቸው ለእስክንድርያ ሊቀነ ጳጳሳትም አባ ቴዎድሮስና አባ፡ ቄርሎስ ዘመዶች ናቸው ከእርሱም በቀር ልጅ የላቸውም መንፈሳዊ ትምህርትን ሁሉ የቤተ ክርስቲያንንም መጻሕፍት ሁሉ አስተማሩት ግልጽ አድርጎ አጠናቸው ጠበቃቸውም ዳግመኛም የዮናናውያንን የፍልስፍና ትምህርት የከዋክብትን አካሔድና ዓለምን መዞራቸውን ተማረ በእውቀቱና በጥበቡም ከብዙዎች ከፍ ከፍ አለ በገድልም የተጠመደ ትሑትና የሚተጋ ሆነ። ❤ በአገሮችም ያሉ ሰዎች ስርሱ በሰሙ ጊዜ በእስክንድርያ አገር ላይ ሊቀ ጵጵስና ይሾሙት ዘንድ ተማክረው ከኤጲስቆጶሳቱ ጋር ተስማሙ። በሌሊትም ወጥቶ ሸሸ ወደ ፈርማ ገዳም ደርሶ በዚያ መነኰሰ ከዚያም ወጥቶ ወደ አንዲት አነስተኛ ወሻ ገብቶ ብቻውን በውስጧ ብዙ ዘመናት ኖረ ብዙ ድርሳናትንና ተግሣጻትንም ደረሰ ከእርሳቸውም ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንት የደረሳቸው አሉ የቤተ ክርስቲያንን መጻሕፍቶችን ብሉያትና ሐዲሳትን ተረጐመ። የመጻሕፍትም ቊጥራቸው ዐሥራ ስምንት ሺህ ነው እሊህም ድርሳናት ተግሣጻት ጥያቄዎችና መልሶች ወደ

መልአኩን ሱርያን ላከ እርሱም በክብር ባለቤት ክርስቶስ ስም የሚደርስበትን ሥቃይ ሁሉ ነገረው "እነሆ ከአንተ ጋር እንድኖር እንዳጸናህም እግዚአብሔር አዞኛልና አትፍራ" አለው። ❤ በዚያንም ጊዜ ተነሥቶ ወደ እንዴናው ከተማ ሔደ በመኰንኑም ፊት ቁሞ በክብር ባለቤት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ መኰንኑም ልብሱን አራቁተው ይገርፋት ዘንድ አዘዘ። ይህንንም አደረጉበት ከዚህም በኋላ በጐኖቹ ውስጥ መብራቶችን አስገብተው ለበለቡት እሳት ግን አልነካችውም መኰንኑም ለጣዖት እንዲሰግድ ብዙ ገንዘብ አመጣት የተመሰገነ ጳውሎስም "ወላጆቼ ሲሞቱ ዐሥራ ሰባት የወርቅ መክሊት ትተውልኝ ነበር። ስለ ክብር ባለቤት ክርስቶስ ፍቅር ትቼ ለድኆች መጸወትኩት ወደዚህ ወደተናቀ ገንዘብህ እንዴት እመለሳለሁ" አለው። ❤ መኰንኑም ሰምቶ ብረቶችን በእሳት አግለው በአፉና በጆሮዎቹ እንዲጨምሩ አዘዘ ይህንንም አደረጉበት ሱርያል መልአክም ወርዶ ዳሠሠውና አዳነው ሁለተኛም እባቦችን በላዩ ሰደዱ አልነኩም ምላሱንም ቆረጡ ጌታችንም አዳነው። መኰንኑም ወደ እስክንድርያ ከተማ በሚሔድ ጊዜ ከእርሱ ጋር ወሰደው የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በመርከብ ውስጥ ተገለጠለትና አጽናናው የዚህም ቅዱስ ኤሲም የሚባል ወዳጅ አለው እኅቱ ቴክላም። በጌታችንም ሥጋው ከሥጋቸው ነፍሱ ከነፍሱሳቸው ጋር እንደሚሆን ነገረው ያን ጊዜ እሊህ ቅዱሳን በእስክንድርያ ከተማ በእስር ቤት ነበሩ የከበረ ጳውሎስም ወደርሳቸው በደረሰ ጊዜ እርስበርሳቸው  ተሳሳሙ በመገናኘታቸውም ነፍሳቸው ደስ ብሏት እግዚአብሔርን አመሰገኑት። ❤ መኰንኑም ወደ እንዴናው ከተማ በሚመለስ ጊዜ የቅዱስ ጳውሎስን ራስ ቆርጠው ሥጋውን ከጥልቅ ባሕር ወረወሩ የሰማዕትነትንም አክሊል በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ ምእመናንም ሥጋውን በሥውር ወስደው በአማሩ ልብሶች ገነዙት በእርሱም ዘንድ አኖሩት ከእርሱም ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕቱ በቅዱስ ጳውሎስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የየካቲት 9 ስንክሳር።                              ✝ ✝ ✝ ❤ "#ሰላም_ለጳውሎስ ቅሡፈ ዘባን በተጠብጥቦ። ወበመኃትወ ነድ ውዑየ ገቦ። #ሱርያል_መልአክ እንዘ ይሜግቦ። በድሮ ፈጺሞ ወሃይማኖቶ ዐቂቦ። ዘምስለ ኤሲ ወቴክላ ተወፈየ ዐስቦ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የየካቲት_ 9።                                    

❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤             ❤ #የካቲት ፱ (9) ቀን። ❤ እንኳን #ለከበረ_በሶርያ_አገር ላሉ መነኰሳት አባት ለሆነ እንደ ኢያሱ ፀሓይን ገዝቶ ላቆመ፣ ዝናብንም በጸሎቱ ላዘነበ፤ ሳይቀመጥ ሃምሣ አራት ዓመት ቁሞ ለኖረ #ለታላቁ_አባት_ለአባ_በርሱማ ለዕረፍት በዓልና ለከበረ ለሶሪያዊ ከሃድያን ይዘው ምላሱን በመቁረጥ፣ በእሳት በማቃጠል፣ የብረት ችንካሮችን በእሳት አግለው በአፉና በጆሮዎቹ ለቸነከሩበትና በመጨረሻውም አንገቱን ለሰየፉት #ለቅዱስ_ጳውሎስ ለዕረፍቱ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ #ከከበረ_ሰማዕት_ከቅዱስ_ጴጥሮስ ከመታሰቢያው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                ✝ ✝ ✝ ❤ #አባ_በርሱማ_ዘሶርያ፦ የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ ሳሚሳጥ ከሚባል አገር ሰዎች ውስጥ ናቸው አንድ በዋሻ ውስጥ የሚኖር ሰው በእርሱ ላይ ትንቢትን ተናገረ ከመወለዱ አስቀድሞ ለአባቱ እንዲህ አለው "የትሩፋቱ ዜና በሶርያ አገር ሁሉ የሚሰማ ጣዕም ያለው ፍሬ ከአንተ ይወጣል ከእርሱ የሚሆነውንም አሰረዳው"። ተወልዶም አድጎ እግዚአብሔርን ወደ ማወቅ በደረሰ ጊዜ ወላጆቹን ሸሽቶ ወደ ኤፍራጥስ ወንዝ ደርሶ በዚያ ስሙ አብርሃም ከሚባል ሰው ዘንድ ተቀመጠ እርሱም ወላጆቹን ስለፈራ ኪዚያ ገዳም ሰደደውና ሒዶ በአለት ውስጥ ኖረ በዚያም ታላቅ ተጋድሎን ተጋደለ ወሬውም በሶርያ አገሮች ሁሉ በተሰማ ጊዜ ብዙዎች ደቀ መዛሙርት ወደርሱ ተሰበሰቡ የዚያ ቦታ ውኃ ግን እጅግ መራራ ነበር በላዩ በጸለየ ጊዜ ተለውጦ ጣፋጭ ሆነ። እግዚአብሔርም በእጆቹ ድንቅች ተአምራቶችን አደረገ ከእርሳቸውም በአንዲት ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ከበአቱ ርቆ ሳለ የፀሓይ መግቢያ ሰዓት ተቃረበ የክብር ባለቤት ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመነው ወደ በአቱም እስቲደርስ ያን ጊዜ ፀሓይን አቆመለት። ❤ በሌላም ጊዜም እንዲህ ሆነ ረዓም የምትባል አገር ነበረች ሰዎቿም ከሀዲዎች ናቸው በላያቸውም ዝናብ ተከለከለ በተጨነቁም ጊዜ ወደ ከበረ አባ በርሱማ መጥተው ለመኑት እርሱም ገሠጻቸው እንዲህም አላቸው "ከክህደታቸሁ ተመልሳችሁ በእግዚአብሔር ብታምኑ እርሱ ብዙ ዝናብን ያወንብላችኋል" እነርሱም "እናምንበታለን አሉት"። በዚያን ጊዜ ጌታችንን ለመነውና ብዙ ዝናብ ዘነበላቸው የአገሩ ሰዎችም ሁሉ በጌታችን አመኑ። እዲሁም ሰዎቿ ከሀድያን የሆኑ ሌላ አገር ነበረች እነርሱንም ገሥጾ መክሮ አስተምሮ እግዚአብሔርን ወደ ማወቅ መለሳቸው የጣዖቶቻቸውንም ቤቶች አፈረሰ። ❤ ይህም ቅዱስ ለራሱ ቦታ አዘጋጅቶ በዚያ ሳይቀመጥ ሃምሣ አራት ዓመት ቁሞ ኖረ ከመትጋት የተነሣ ሲደክመው ከናሱ ግድግዳ ላይ ተደግፎ ያሸልባል በየሰባት ቀንም ይጾማል። የከበረ አባ ስምዖን ዘዓምድ ሊያየው ወዶ ወደርሱ ላከ የትሩፋቱንና የቅድስናውን ዜና ከብዙዎች ሰዎች ሰምቶ ነበርና እርሱም ወደ አባ ስምዖን መጥቶ እርስበርሳቸው በረከትን ተቀባበሉ ከዚያም በኋላ ወደ ገዳሙ ተመለሰ። በሶርያም አገርም አስተማረ በፊታቸው ተአምራትን በአደረገ ጊዜ በትምህርቱ ብዙዎች አመኑ። ዳግመኛም ወደ ታናሹ ቴዎዶስዮስ ንጉሥ ሒዶ በቀናች ሃይማኖት አጸናው ንጉሡም ብዙ ገንዘብን ሰጠው እርሱ ምንም ምን አልወሰደም በአንጾኪያም አገር በኤጲስቆጶሳቱ ሁሉ ላይ ሥልጣን እንዲኖረው ንጉሥ ጻፈለትና ኀቲም ቀለበትን ሰጠው። ❤ በከሀዲው ንስጥሮስ ምክንያት ሁለት መቶ ኤጲስቆጶሳት በኤፊሶን ከተማ በተሰበሰቡ ጊዜ ከእሳቸው ጋር ይህ ቅዱስ አለ። ከእርሳቸውም ጋር ንስጡርን አወገዘው ዳግመኛም በአንጾኪያ አገር ያሉ መኳንንት መሳፍንትን ሹማምንት ሁሉም ይታዘዙለት ዘንድ ንጉሥ ደብዳቤን ጻፈለት እርሱም በጎ ሥራ እንዲሠሩ በሃይማኖት እንዲጸኑ የሚያዝዝ ደብዳቤ በመጻፍ በንጉሥ ኀቲም ቀለበት እያተመ ለአገሮች ሁሉ የሚልክ ሆነ። ክፋዎች ሰዎችም ጠሉት በንጉሥም ዘንድ ነገር ሠሩበት እንዲህም አሉት" እሆ አባ በርሱማ እንደ ዓለም ሰው ሁኖ ይበላል ይጠጣል መልካም ልብስንም ይለብሳል" ንጉሥም ስለ አባ በርሱማ የተነገረውን ያረጋግጥ ዘንድ ከባለሟሎቹ አንዱን ላከ። የንጉሡም ባለሟል ወደ አባ በርሱማ በደረሰ ጊዜ በእርሱ ላይ ከተነገረው ምንም ምን ያገኘው የለም ከዚህም በኋላ ወደ ንጉሥ ወሰደው ንጉሥም ቀድሞ ከሚያውቀው ከመንፈሳዊ ሥራው ልውጥ ሁኖ ያገኘው ነገር የለም ንጉሡም ታላቅ ክብርን አከበረው ወደ ቦታውም መለሰው። ❤ መናፍቁ ንጉሥ መርቅያንም የኬልቄዶንን ጉባኤ በሰበሰበ ጊዜ የንጉሥ አማካሪዎች አባ በርሱማን እንዳያስመጣ ንጉሡን መከሩት እንደማይፈራና እንደ ማያፍር በሰው ፊትም እንደማያዳላ ተከራክሮ ረትቶ እንደሚሳፍራቸውም ስለሚያውቁ ነው። አንዱ ክርስቶስ ወደ ሁለት የከፋፈሉበት ይህ ጉባኤ በተፈጸመ ጊዜ የከበረ አባ በርሱማ ተጣላቸው ነቀፋቸው ቃላቸውንም በመሻር አወገዛቸው እርሱም ወደ ንጉሥ ወንጅለው በጽሑፍ ከሰሱት ንጉሡም ልኮ ወደርሱ አስቀረበው ግን በላዩ ስለ አደረ መንፈስ ቅዱስ ጸጋ ሊቃወመው አልቻለም በሊቁ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ላይ ስለ አደረገው ክፋት ንግሥቲቱን ረገማት ከጥቃት ቀንም በቀር አልኖረችም በክፉ አሟሟትም ሞተች። ከዚህም በኋላ መናፍቃን የሚቃወሙት ሆነ ምእመናን እንዳይታዘዙለት ወደ ሀገሮች ሁሉ ጽፈው የሚልኩ ሆኑ እነርሱ ግን አልተቀበሏቸውም እርሱ መታዘዛቸውንም አልተዉም። ዳግመኛም በጐዳና ሸምቀው ይገድሉት ዘንድ ሁለት መቶ መናፍቃን ሰዎች ከመናፍቃን ኤጲስቆጶሳት ጋር ተስማምተው ወደ እርሳቸው እንዲመጣና በአንድነት ወደ ቤተ ክርስቲያን እንደ ሚሔዱ ሁነው ላኩበት መጥቶም አብሮ በተጓዘ ጊዜ ደንጊያዎችን አንሥተው ጣሉበት ደንጊያዎታቸውም ወደ ራሳቸው የሚመለሱ ሆኑ በፍርሃትም ከእርሱ ሸሹ። ❤ እግዚአብሔርም ከዚህ ዓለም እሥረኛነት ሊአወጣው በወደደ ጊዜ መልአኩን ወደርሱ ልኮ ከአራት ቀን በኋላ ከዓለም እንሚፈልስ ነገረው በዚያንም ጊዜ በዙሪያው ወዳሉ አገሮች ምእመናንን ያጽናናቸው ዘንድ ረድኡን ላከው እርሱም ሲዞር የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ራስ ወደምትኖርበት ቦታ ደረሰና የከበረች የቅዱስ ዮሐንስን ራስ እጅ ነሣት ስለ ከሀዲው ስለ ንጉሥ መርቅያን በማልቀስ ለመነ። እንዲህ የሚልም ቃል ከመጥምቁ ዮሐንስ ራስ ወጣ " አባ በርሱማ ወደ እግዚአብሔር ስለ ከሰሰው ያ መርቅያን ሙቷልና አትፍራ"። የከበረ አባ በርሱማ ረድኡን ባረከው የካቲት9 በሰላ አረፈ። ከበአቱም ደጃፍ ከምድር እስከ ሰማይ የሚደርስ የብርሃን ምሰሶ ተተክሎ ታየ። ምእመናንም ሁሉ ከሩቅ አይተው ወደርሱ መጡ አርፎም አገኙት። ከሥጋውም ተባረኩ በላዩም አለቀሱ ከእርሱም ስለመለየታቸው እጅግ አዘኑ እደሚገባውም እየዘመሩና እያመሰገኑ ገንዘው በመቃብር አኖሩት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ በርሱማ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ለዘላለሙ ትኑር አሜን። ምንጭ፦ የየካቲት9 ስንክሳር።                             ✝ ✝ ✝ ❤ #ሶርያዊው_ሰማዕቱ_ቅዱስ_ጳውሎስ፦ የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ የሶርያ ሰዎችና በእስክንድርያ ከተማ የሚኖሩ ነጋዴዎች ናቸው ከዚህም በኋላ በእስሙናይን ከተማ የሚኖሩ ሆኑ። ወላጆቹም ሲሞቱ ብዙ ገንዘብ ተውለት ከዚህም በኋላ ከሀድያን ነገሥታትና መኳንንት በክርስቶስ የሚያምኑ ምእመናንን እንደሚያሠቃዩአቸውና እንደሚገድሏቸው ሰማ በዚያንም ጊዜ ተነሥቶ ገንዘቡን ሁሉ ለድኆችና ለችግረኞች በተነ። ከዚያም በኋላ የወደደውን መንገድ ይመራው ዘንድ ወደ ክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጸለየ ጌታችንም

❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ  አሜን"። ❤                          ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_አንገርጋሪ_ግእዝ_ዜማ፦ ሃሌ ሉያ "#ስምዖን_ተወክፎ_ዳዊት_ዘመሮ_ነቢያት ቀደሙ አእምሮ ሐዋርያት ተራው አሠሮ ሰብአ ሰገል ሰገድ ሎቱ እሙነ ኮነ ልደቱ"። ትርጉም፦ #ስምዖን_ተቀበለው #ዳዊት_ዘመረለት_ነቢያት አስቀድመው አወቁት ሐዋርያት ፍለጋውን ተከተሉ የጥበብ ሰዎች (ሰብአሰገል) ሰገዱለት ልደቱ በእርግጥ ሆነ።                           ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_እግ_ነግ_ዓራራይ_ዜማ፦ "#በቤተ_ልሔም_ተወልደ ወበናዝሬት ተሐፅነ #ወስምዖን_ተወክፎ ውስተ ሕፅኑ #ዳዊት_ዘመሮ #ወዮሐንስ_ለንጸሮ_ለሙሴ_ገሃደ_ተናገሮ"። ትርጉም፦ #በቤተ_ልሔም_ተወለደ በናዝሬትም ሰገደ #ስምዖን_ተቀበለ (ሰብአ ሰገል) ሰገዱለት ልደቱ በእርግጥ ሆነ #ዳዊት_ዘመረለት_ዮሐንስ_ተመለከተው_ለሙሴ_በግልጥ_ተናገረው። #ሊቁ_ቅዱስ_ያሬድ_በድጓው_ላይ።                 

❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ እንኳን #ለዐቢይ_ጾም_ለመጀመርያ_ሳምንት #ለዘወረደ (ለጾመ ሕርቃል)ና #ለቅበላ እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                            ✝ ✝ ✝ ❤ #የዚህ_ሳምንት_የዘወረደ_መዝሙር፦ ሃሌ ሉያ  "#ተቀነዩ_ለእግዚአብሔር_በፍርሃት_ወተሐሠዩ_ሎቱ በረዓድ እስመ ለዓለም ምሕረቱ ለትውልደ ትውልድ ጽድቁ ንሕነሰ ሕዝቡ ባኡ ቅድሜሁ በተጋንዮ ወውስተ አዕፃዲሁ በስብሐት እመንዎ፤ እ፣ #ንጹም_ጾም_ወናፍቅር_ቢጸነ_ወንትፋቀር_በበይናቲነ፤ እ፣ አክብሩ ሰንበተ ተገበሩ ጽድቀ እስመ ሰንበትሰ በእንተ ሰብእ ተፈጥረት፤ እ፣ ምሕረተ ወፍትሐ አሐሊ ለከ እዜምር ወእሌቡ ፍኖተ ንጹሐ እስመ ለዓለም ምሕረቱ ለትውልደ ትውልድ ጽድቁ ንሕነሰ ሕዝቡ አባግዐ መርዔቱ። ትርጉም፦ #ለእግዚአብሔር_በፍርሃት_ተገዙ፣ ለእርሱም መገዛት ደስ ይበላችሁ። #እግዚአብሔር ቸር ምሕረቱም ለዘላለም፣ እውነቱም ለልጅ  ልጅ ነውና። እኛስ ሕዝቡ የማሰማሪያው በጎች  ነን፤ ወደ ደጁ በመገዛት፣ ወደ አደባባዮችም በምስጋና ግቡ፤ #ጾምን _እንጹም፤ #ጓደኞቻችንን_እናፍቅር_እርስ_በርሳችንም_እንፋቀር። ሰንበት ስለሰው ተሠርታለችና ሰንበትን እናክብር። እውነትንም እንሥራ፤ አቤቱ ምሕረትንና ፍርድን እቀኝልሃለሁ፤ እዘምራለሁ፤ ንጹሕ መንገድንም አስተውላለሁ። #ሊቁ_ቅዱስ_ያሬድ_በጾመ_ድጓው ላይ።                             ✝ ✝ ✝ ❤ #ዘወረደ፦ የ0ቢይ ጾም የመጀመሪያው እሁድ (ሳምንት) ዘወረደ ይባላል። ❤ ጌታችን እኛን ለማዳን ከሰማይ መውረዱን የሚነገርበት ሳምንት በመሆኑ ዘወረደ ተብሏል። ❤ ከሰማይ ወረደ ማለት እርሱ የሌለበት ኖሮ ካለበት ወደዚህ መጣ ማለት አይደለም እርሱስ ጽርሐ አርያም ምጥቀቱ በርባኖስ ጥልቀቱ ፥ አድማስ ናጌብ ስፋቱ ተብሎ የማይነገርበት በዓለም ሙሉዕ ነውና ዓለማትን ቢወስን እንጂ ዓለማት እርሱን አይወስኑትም ።   ❤ የፀሐይ ብርሃን ከክበቡ ሳይለይ ከ0ይናችን ብሌን ጋር እንደሚዋሓድ ወልደም ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ሳይለይ በምልዓቱ መወሰን ሳይኖርበት በሥጋ ማርያም መገለጹን ሰው መሆኑን ያስረዳል :: ❤ ከሰማይ ወረደ ሲባል ስንሰማ "ሰማይ" ያለው ዕበዩን፣ ክብሩን ፣ ልዕልናውን ፣ ጌትነቱን፣ መንግሥቱን ፣ ርቀቱን .... ነው :: ስለዚህ ከሰማይ ወረደ ማለት የባሪያውን መልክ ይዞ ሰው መሆኑን ለመግለጽ ነው። ፊል 2፥6-8 ❤  ሰው ሆኖ መፈጠር ታላቅ ክብር ነው ለአምላክ ግን ሰው መሆኑ ተዋርዶ ነውና ይልቁንም እኛን ለማዳን በለበሰው ሥጋ መራብ መጠማቱ ፣ መገረፍ መታመሙ ... እንኳን ከአብ እና ከመንፈስ ቅዱስ ይቅርና ከመላእክት እንኳን ያነሰበት ነው መላእክት በባህሪያቸው መራብ መጠማት፣ መታመም የለባቸውምና " ከመላእክት እንኳን አሳነስከው" ያለውም ስለዚህ ነው ። መዝ 8፥5፣ ዕብ 2፥7 ❤ ይህ ማለት ግን ወልድ ሰው መሆኑ አምላክነቱን አጥቶ በዚህም ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ አነሰ ማለት አይደለም ጌታችንም "አብ ይበልጠኛል" ያለው በለበሰው ሥጋ ባገኘው መራብ መጠማት አነሰ ለማለት ነው አብ እና መንፈስ ቅዱስ ሰው ሆነው መራብ መጠማት ... ያላገኛቸው መሆኑን ለመግለጽ ነው። ዮሐ.14፥28 ❤ ቅዱስ ያሬድ ጾመ ድጓውን ሲጀምር  ሃሌ ሃሌ ሉያ "ዘወረደ እም ላዕሉ አይሁድ ሰቀሉ ወሚመ ኢያእመሩ እግዚአ ኩሉ ዘየሃዩ በቃሉ"። ትርጉም፦ ከሰማየ ሰማያት የወረደ አይሁድ የሰቀሉት ሁሉን በቃሉ እንደሚያድን አይሁድ ያላወቁት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።  በማለት ሰው ሆኖ በአይሁድ ተዋርዶ ያገኘው መሆኑን የዚህን ሳምንት ጠቅላላ ሀሣብ ይገልጻል። ምንጭ፦ ከአምኃ ሥላሴ (መኩሪያ ተስፋዬ) ፔጅ የተወሰደ።                             ✝ ✝ ✝ ❤ #የዐቢይ_ጾም የመጀመሪያው ሌላ ስሙ #ጾመ_ሕርቃል፦ ሕርቃል ማን ነው? ለምንስ በስሙ ተሰየመ? በ614 ዓ.ም ኪርዮስ የተባለ የፋርስ ንጉሥ ኢየሩሳሌምን በመውረር ጥቃት አደረሰ፡፡ በዚህ ወቅት በኢየሩሳሌም ንግሥት ዕሌኒ በሠራችው ቤተመቅደስ ውስጥ ሲገባ ንግሥቷ በክብር አስቀምጣው የነበረው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል እንደ ፀሐይ ሲያበራ አገኘው፡፡ ❤ ቢነካው አቃጠለው ዲያቆናቱን አሸክሞ ሌላውን ንዋየ ቅድሳት ዘርፎ 60ሺ የሚደርሱትን አቁስሎ ገድሎ 3ሺ የሚሆኑትን ማርኮ ከተማዋንም አቃጥሎ ወደ ፋርስ ባቢሎን ይመለሳል፡፡ በዚህ ጊዜ ከጦርነቱ ያመለጡ በየዋሻው በየጉራንጉሩ ገብተው የተሸሸጉ ተሰብስበው ከ14 ዓመት በኋላ በ628 ጩኸታቸውንና የደረሰባቸውን በደል ለክርስቲየኑ የሮም ንጉሥ ሕርቃል ይነግሩታል፡፡ ❤ እርሱም "ሐዋርያት ሰውን የገደለ  ዕድሜውን በሙሉ ይጹም ስላሉ እንዴት ላድርገው?" አላቸው እኛ "የአንተን ዕድሜ ተከፋፍለን እንጾማለን" ብለው አንድ አንድ ሳምንት ደርሷቸው ጾሙን በሚገባ ጾመውታል፡፡ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀልና የተማረኩ ክርስቲያኖችን ለመመለስ ሕርቃል ጦር መዝዞ በኪርዮስ ላይ ተነሳበት ድል ለሕርቃል ሆነና መስቀሉን ያለበትን አጥቶ ሲቸገር መስቀሉን ሲቀብርና ዲያቆናቱን ሲያስገድል በመስኮት ሆና ያየችው ከኢየሩሳሌም የተማረከች አንዲት ብላቴና አሳይታው አውጥቶ በልብሰ መንግሥቱ ጠቅልሎ ወደ ቊስጥንጥንያ ተመለሰ፡፡ ❤ የተማረኩት በሙሉ ነጻ ወጡ ይህን ለማሰብ ለማስታወስ በተጨማሪም በኃጢአት ላይ ድል እንድናገኝ መንፈሳዊ ጦር በውስጣችን እንዲበዛልን መስቀልህ ከምርኮ እንደተመለሰ እኛንም ከኃጢአት ምርኮ መልሰን ለሕርቃል ድል መንሳትንና በጠላቶቹ ላይ ኃይልን እንደሰጠኸው ለእኛም በኃጢአት ላይ ድል መንሳት መንፈሳዊ ኃይልን ስጠን እያልን እንጾመዋለን፡፡ ❤ በጌታ ጾም ላይ እንዲጾም የሆነበት ምክንያት ጾሙ የጌታ ጾም በሚጾምበት ወቅት ላይ ስለተጾመ ቤተክርስቲያናችን አብራ ደንግጋዋለች፡፡ እዚህ ላይ በዚያን ጊዜ ለሕርቃል ሕዝቡ ሱባኤ ይዞለታል፡፡ ❤ ዛሬም እኛ ለቤተክርስቲያን ያደረግነውን በማሰብ እግዚአብሔር አምላክ ለሕርቃል የሰጠውን በጠላቶቹ ላይ ድል መንሳትን ለእኛም እንዲሰጠን የምንጠይቅበት ስለሆነ የመጀመሪያውን ሳምንት በሕርቃል ሰይመን ጾሙን እንጾማለን፡፡ ❤ የእኛ ጠላት የጨለማ ገዥ የሆነው ዲያቢሎስ ነውና እሱን ደግሞ በጾም እንደምናሸንፈው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሮናል፡፡ ምንጭ፦ የመጋቢት 10 ስንክሳር እና ከፌስቡክ ከማኅበረ ጎዶልያስ ዘ ዑራኤል የተወሰደ።                                 ✝ ✝ ✝ ❤ #የዘወረደ_አራራይ_ዜማ፦ ሃሌሉያ "#መሐረነ ንጉሠ ስብሐት #ተሣሀለነ_እግዚአ_ለሰንበት አቡሃ ለምሕረት #ወሀበነ_ጾመ ለንስሐ በዘይሰረይ ኃጢአት። ትርጉም፦ #የምስጋና_አምላክ ማረን የምሕረት አባት #የሰንበት_ጌታ_ይቅር_በለን #ጾምን_ለንስሐ_ስጠን  ኃጢአታችን ይሰረይ ዘንድ፡፡ #ሊቁ_ቅዱስ_ያሬድ_በጾመ_ድጓው_ላይ።                               ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሃት። ወተኀሠዩ ሎቱ በረዓድ። አጽንዕዋ ለጥበብ ከመ ኢይትመዐዕ እግዚአብሔር"። መዝ 2፥11-12። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 13፥7-16፣ ያዕ 4፥6-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 25፥13-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 3፥10-25። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ እግዚእነ ነው። መልካም የቅበላ በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።                 

                            ✝ ✝ ✝ ❤ #አባ_ቴዎድሮስ፦ የእስክድርያ ሊቀ ጳጳሳት ቁጥሩም እርሱም ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት አርባ አምስተኛ ነው። ይህ አባት መርዩጥ በሚባል አገር በአንድ ገዳም ውስጥ መነኰሰ የዚያም ገዳም ስም ጠንቡራ ነው። ለአንድ ፍጹም ጻድቅ የሆነ ሽማግሌ ሰው ደቀ መዝሙሩ ሆነ። እርሱም ልጁ ቴዎድሮስ በእስክድርያ አገር ላይ ሊቀ ጵጵስና እንደሚሾም በመንፈስ ቅዱስ አይቶ ይህንን ለመነኰሳቱ ነገራቸው። ❤ ይህም አባት ቴዎድሮስ በገድል የተጠመደ ሆነ መልኩም የሚያምር ነው በሰውነቱም ላይ ከውስጥ ማቅ በመልበስ በላዩ የብረት ልብስ መንቈር ይለብስ ነበር በቅንነቱና በትሕትናው ፍጹም ሆነ። በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ተመርጦ በእስክንድርያ አገር ላይ ሊቀ ጵጵስና ተሾመ የክርስቶስንም መንጋዎች በበጎ አጠባበቅ ጠበቀ ሁልጊዜ መጻሕፍትን በማንበብ ያስተምራቸው ነበር ይልቁንም በሰንበትና በበዓላት ቀን። የሹመቱም ዘመን ጸጥታና ሰላም ነበር ቤተ ክርስቲያንም በሰላም ኖረች በወንጌላዊው ማርቆስ ወንበር ላይ ዐሥራ አንድ ዓመት ተኩል ከኖረ በኋላ፡ በሰላም ዐረፈ። ምንጭ፦ የየካቲት 7 ስንክሳር።                                ✝ ✝ ✝ ❤ "#ሰላም_እብል_ለገዳማዊ_ብሑት። ዘኢርእዮ እምሰብእ መጠነ ሰብዓ ዓመት። ከመ አዘዞ አሐዱ እምላእክት። ድኅረ ወሀባ፡ ኑዛዜ ለነፍሰ ዕብሎይ ኃጥእት። ዘአዕረፈ ዮም በሠሉስ ዕለት"። #ሊቀ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የየካቲት_7።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦"ብከ ንወግዖሙ ለኵሎሙ ፀርነ። ወበስምከ ናኀሥሮሙ ለዕለ ቆሙ ላዕሌነ። ዘአኮ በቀስትየ እትአመን"።መዝ 43፥5-6። የሚነበብት መልዕክታ ኤፌ 6፥10-19፣ ራዕ 13፥11-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 20፥28-31። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 19፥11-28። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ባስልዮስ ቅዳሴ ነው። መልካም በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።