cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ሊያና ኬር Liyana Care 7755

➮ የጤና ምክሮች 👨‍⚕️ ➮ ሀኪምዎን ያማክሩ7755 ➮ ቴሌሜዲስን 💉 ➮ በአይነቱ ለየት ያለ ሀክምና📱📲

Show more
Advertising posts
11 013Subscribers
-424 hours
-387 days
-14030 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የሚዋጠውን የወሊድ መከላኪያ(combined contraceptive/CHOICE) ብረሳ ምን ማድረግ ይኖርብኛል? 🤔አንድ ኪኒን ብቻ ከተረሳ-ቀጣዩ ቀን ላይ የተረሳውን፤ እንዲሁም የዛን ቀን የሚዋጠውን ኪኒን መውሰድ ነው። እናም እርግዝና የመፈጠር እድሉ በጣም ዝቅተኛ ነው። 👉ሦስት ወይም ከዛ በላይ ከተረሳ 1.የተረሳው የመጀመሪያ ወይም ሁለተኛ ሳምንት ላይ ከሆነ ያስታወሱት ቀን ጀምሮ መድሀኒቱን መውሰድ ነገር ግን ለቀጣይ ሰባት ቀናት ግንኙነት ከተደረገ እርግዝና የመፈጠር እድል ስላለ ሌላ ተጫማሪ መከላከያ(እንደ ኮንዶም) መጠቀም። 2.የተረሳው ሦስተኛ ሳምንት ላይ ከሆነ ያስታወሱት ቀን ጀምሮ መድሀኒቱን መውሰድ ነገር ግን ለቀጣይ ሰባት ቀናት ግንኙነት ከተደረገ እርግዝና መፈጠር እድል ስላለ ሌላ ተጫማሪ መከላከያ(እንደ ኮንዶም) መጠቀም። እንዲሁም ቀዩን በመተው የቀጣዩ ሆርሞናል (ነጩን ኪኒን) መውሰድ። 📌ቡኒው ወይም ቀዩን (iron) ኪኒን ከተረሳ የተረሱትን ኪኒኖች በማስወገድ ቀጣዩን መውሰድ ( የእርግዝና መፈጠር እድል አይጨምርም) ------------------------------------------------ 📞ለተጨማሪ መረጃ ወደ 7755 ይደውሉ:: ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare https://apps.apple.com/us/app/liyana-care/id1572231448
Show all...
Liyana Care - Apps on Google Play

Bringing Healthcare wherever you are!

ለምፅ ከአንድ ሰው ወደ ሌላ ሰው ሊተላለፍ ይችላል? 🔸ለምፅ( vitiligo) የቆዳ ቀለምን የሚያመርቱ ህዋሶች(melanocytes) በተለያዩ ምክንያቶች እንከን ሲኖራቸው የሚከሰት ህመም ነው፡፡ 📎ይህ ህመም 1% ያህል የሚሆነውን የዓለም ህዝብ እንደሚያጠቃ ሲታሰብ በብዛት የሚከሰተው ቡናማ ወይም ጥቁር የቆዳ ቀለም ያላቸው ሰዎች ላይ ነው፡፡ 👉ለምፅ ከታመመ ሰው ወደ ሌላ ሰው በንክኪ አይተላለፍም፡፡ ⚠️አምጪ ምክንያቶች 📎የለምፅን አምጪ ምክንያቶች በእርግጠኝነት መዘርዘር ባይቻልም ብዙ ጥናቶች ግን የሚከተሉት ነገሮች እንደ አምጪ ምክንያቶች ይጠቅሳሉ፡፡ ❗️አውቶኢሚዩን ዲስኦርደርስ( Autoimmune disorders)- እነዚህ ህመሞች ያሉባቸው ሰዎች የሰውነታቸው የበሽታ መከላከል ስርዓት የራሳቸውን ህዋሶች በማጥቃት ለህመም ይዳርጋቸዋል፡፡ ይህ የተዛባ በሽታ የመከላከል ስርዓት የቆዳ ቀለምን የሚያመርቱ ህዋሶችን (melanocytes) በሚያጠቃበት ጊዜ ለምፅ ሊከሰት ይችላል፡፡ ❗️በቤተሰብ ውስጥ በለምፅ የተያዘ ሰው መኖር ❗️በኬሚካሎች ወይም በፀሀይ ቃጠሎ ምክንያት የሚደርስ የቆዳ ጉዳት 👳ምልክቶች 🔸የቆዳ ቀለም መጥፋት 🔹ያለጊዜው የሚከሰት የሽፋሽፍት߹ የቅንድብ߹ የፂም እንዲሁም የፀጉር መንጣት 🔍ምርመራ 📎አብዛኛውን ጊዜ ለምጽ የሚታወቀው ታማሚው ለሀኪሙ በሚነግረው የህክምና ታሪክ እና ሀኪሙ በሚያደርገው አካላዊ ምርመራ ነው፡፡ 🩺ህክምና ✅አብዛኛውን ጊዜ በለምፅ ምክንያት የሚፈጠር የቆዳ ቀለም ችግር ሙሉ በሙሉ ማስተካከል አይቻልም፡፡ ነገር ግን ከ 10 እስከ 20 % የሚሆኑት የለምጽ ታማሚዎች በህክምና ታግዘው የሰውነት ቀለማቸውን ሙሉ በሙሉ ሊያገኙ ይችላሉ፡፡ 📌የለምፅ ታማሚዎች በለምፅ የተጠቃው ቆዳቸውን ከሌላው ቆዳቸው ጋር ለማመሳሰል ሜካፕ መጠቀም ይችላሉ፡፡ የፀጉር ቀለም መቀየር ያጋጠማቸው ታማሚዎች ደግሞ የፀጉር ቀለም መቀባት ይችላሉ፡፡ 👩‍⚕️በለምፅ የተጠቃ ሰው ቆዳ ወደ ተፈጥሯዊ ቀለሙ እንዲመለስ ለማድረግ ከሚረዱ ህክምናዎች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡ 💊የበሽታ መከላከል አቅምን የሚቀንሱ መድሀኒቶች 👉የብርሀን ህክምና ✂️የቆዳ ንቅለተከላ ህክምና 💊ትክክለኛ የቆዳ ቀለም ያለውን የሰውነት ክፍል በማንጣት በለምፅ የተጠቃውን ቆዳ የሚያስመስሉ መድሀኒቶች 👉ቆዳን ቀለም የሚሰጡ ሴሎች(melanocytes ) ከቆዳ በተጨማሪ በአይን ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ስለዚህም የለምፅ ታማሚዎች ለአይን ህመም ተጋላጭ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ስለሆነም የለምፅ ታማሚዎች መደበኛ የሆነ የአይን ክትትል ሊያደርጉ ይገባል፡፡ 🔸በለምፅ የተጠቃው ቆዳ በፀሀይ እንዳይጎዳ ሰንስክሪን (sunscreen) መጠቀም ይመከራል፡፡ ------------------------------------------------ ለተጨማሪ መረጃ 7755 ይደውሉ፡፡ ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare https://apps.apple.com/us/app/liyana-care/id1572231448
Show all...
Liyana Care - Apps on Google Play

Bringing Healthcare wherever you are!

📞ዶክተር split የተባለው ፊልም ላይ ያለው የስነ አዕምሮ ህመም ነው?📞 👍በትክክል 🎞split በተሠኘው 2016g.c የተሠራው ፊልም ላይ የተገለፀው የስነ አእምሮ ህመም "dissociative identity disorder" ሲሆን ዋና ገፀ ባህሪው 23 ልዩ ልዩ ስብዕናዎች አሉት። 🙇‍♂️👼በልጅነት ጊዜው በደል የደረሰበት ኬቨን ዌንዴል ክረምብ 21ቱ ስብዕናዎች ወንዶች ሲሆኑ 1ድ ሴት እና 1ድ የ9 አመት ወንድ ህፃን ልጅ ስብዕናን ይዞ እንመለከታለን። 👨‍⚕️ዲሶሺየቲቭ አይደንቲቲ ዲስኦርደር የስነ አእምሮ ህመም ነው። 👱‍♂️👱👩‍🦳በ "DID" ህመም የተጠቁ ሰዎች ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የተለዩ ማንነቶች አሏቸው። 👨‍👧‍👦 እነዚህ ስብዕናዎች በተለያየ ጊዜ ባህሪያቸውን ይቆጣጠራሉ። 🧍‍♂️🧍🚶‍♂️እያንዳንዱ ማንነት፣ የራሱ የግል ታሪክ ፣ ባሕርያት ፣ የሚወዳቸው/የምትወዳቸው/ እና የሚጠላው ነገሮች ይኖሩታል። 🩺Dissociative identity disorder (DID) ከዚ ቀደም "split personality disorder" ወይም "multiple personality disorder" ተብሎ ይጠራ ነበር። 🔴ዲ.አይ.ዲ የሚያስከትላቸው ችግሮች አንድ ሰው ከእውነታው ጋር የመገናኘት ችሎታ ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉ። 🧮 ሕመሙ ከ 0.01 እስከ 1% ባለው ሕዝብ ላይ በማንኛውም ዕድሜ ላይ ሊከሰት ይችላል። 🙍‍♀️ሴቶች ከወንዶች ይልቅ በDID የመያዝ ዕድላቸው ከፍተኛ ነው። 🟢የዲ.አይ.ዲ መከሰት ምክንያቶች ምንድን ናቸው? 👧👦DID አብዛኛውን ጊዜ በልጅነት ጊዜ የሚደርስ የወሲብ ወይም የአካል ጥቃት ውጤት ነው። 💨🔥🌪አንዳንድ ጊዜ ለተፈጥሮ አደጋ ወይም ለሌሎች እንደ አሰቃቂ ክስተቶች ምላሽ በመስጠት ያድጋል። 🕴ዲአይዲ ያለበት ሰው ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ማንነቶች ቢኖሩትም “ዋናው” ማንነት የግለሰቡ የተለመደው ስብዕና ነው። 🧍‍♂️🧍 “ተለዋዋጮች” የግለሰቡ ተለዋጭ ስብዕናዎች ናቸው። አንዳንድ ዲ.አይ.ዲ ያላቸው ሰዎች እስከ 100 የሚጠጉ ማንነቶች አሏቸው። 🔵ተለዋዋጮች እያንዳንዳቸው በጣም የተለያዩ ይሆናሉ። ይህም ማለት 🔹የተለያዩ ጾታዎች 🔹ስሞች 🔹ባህሪያቶች 🔹ፍላጎቶች እና ከአካባቢያቸው ጋር የሚገናኙባቸው መንገዶች ሊኖራቸው ይችላል። 🥼ሌሎች የተለመዱ የ DID ምልክቶች የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ- 🤦‍♂️የመንፈስ ጭንቀት. 🤷‍♂️ግራ መጋባት። 🥃🚬አደንዛዥ ዕፅ ወይም አልኮልን መጠቀም 🤷‍♀️🤷የማስታወስ ችሎታ ማጣት 🪦ራስን የማጥፋት ሀሳቦች ወይም ራስን መጉዳት 🩺ለተነጣጠለ የማንነት መታወክ (ዲ.አይ.ዲ) ሕክምናው ምንድነው? 💊አንዳንድ ለድብርት እና ጭንቀት የሚሠጡ መድሃኒቶች ለተመሣሣይ የ DID ምልክቶች ሊረዱ ይችላሉ። 🥼በጣም ውጤታማው ሕክምና የስነ -ልቦና ሕክምና ነው። በአእምሮ ጤና መታወክ ላይ ልዩ ሥልጠና ያለው የጤና እንክብካቤ አቅራቢ ፣ እንደ ሳይኮሎጂስት ወይም ሳይካትሪስት ፣ ወደ ትክክለኛው ሕክምና ሊመራዎት ይችላል። 👩‍⚕️🧑‍⚕️ከግለሰብ ፣ ከቡድን ወይም ከቤተሰብ ሕክምና ተጠቃሚ ሊሆኑ ይችላሉ። Saron Mesfin (Psychiatry professional ) ------------------------------------------------ ለተጨማሪ መረጃ 7755 ይደውሉ ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare
Show all...
Liyana Care - Apps on Google Play

Bringing Healthcare wherever you are!

The world is moving towards digitization. Our center, Liyana Digital Healthcare Solutions, as the first licensed telemedicine company in Ethiopia, is working tirelessly towards realization of digital healthcare service delivery. We would love to thank Safaricom Telecommunications Ethiopia in becoming part of this journey. We had such a great session with the employees after presentation of a webinar by our experienced psychiatrist Dr.Selam. We look forward to a fruitful partnership.
Show all...
Sign in and get access to detailed information

We will reveal these treasures to you after authorization. We promise, it's fast!