የስንኝ ቋጠሮ
Open in Telegram
የዚህ ቻናል ዋና አላማ የተለያዩ ወጣቶች የግጥም ችሎታቸውን የሚዳብሩበት እና የሚያወጡበት ቻናል ነው። ግጥሞችን ለመላክ @mogea ይጠቀሙ መልሰን ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል!!
Show more2 046
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
2 046
#ግጥመ -ቸርነት
⌚️⌚️⌚️"ጊዜ"⌚️⌚️⌚️
ጊዜ ሴኮንድ ነው ጊዜ ሚሊንየም፣
ባንዴ የሰራውን ሲያፈርስ አይዘገይም፣
ወይም በሌላ ጎን ሲገነባ አይፈጥንም።
ጊዜ ስልጣን አለው፤ሹማምንቱን ሽሯል፣
ያላለፈ የለም ፤ሁሉም ተፈራርቋል።
ግና ምን ያደርጋል ከንቱ እንጅ ነው ሁሉ
ለጊዜም ጊዜ አለው፤ቦ ጊዜ ለኩሉ፣
እ'ግዜ'ሩ ሲመጣ አዝማናት ያልፋሉ።
ስለዚህ ወገኔ ዘምን በዘመንህ፣
አኅትክን አትድፈር እዘን ለወንድምህ፣
ኋላ ፀሀይ ገብታ፤
ለዘለአለም ጠፍታ፣
መሽቶ እንዳይጨልምህ።
📝በቸርነት ሰኔ 2013 ዓ.ም
@gitmv
Code #6
2 046
#ግጥመ -ቸርነት
⌚️⌚️⌚️"ጊዜ"⌚️⌚️⌚️
ጊዜ ሴኮንድ ነው ጊዜ ሚሊንየም፣
ባንዴ የሰራውን ሲያፈርስ አይዘገይም፣
ወይም በሌላ ጎን ሲገነባ አይፈጥንም።
ጊዜ ስልጣን አለው፤ሹማምንቱን ሽሯል፣
ያላለፈ የለም ፤ሁሉም ተፈራርቋል።
ግና ምን ያደርጋል ከንቱ እንጅ ነው ሁሉ
ለጊዜም ጊዜ አለው፤ቦ ጊዜ ለኩሉ፣
እ'ግዜ'ሩ ሲመጣ አዝማናት ያልፋሉ።
ስለዚህ ወገኔ ዘምን በዘመንህ፣
አኅትክን አትድፈር እዘን ለወንድምህ፣
ኋላ ፀሀይ ገብታ፤
ለዘለአለም ጠፍታ፣
መሽቶ እንዳይጨልምህ።
📝በቸርነት ሰኔ 2013 ዓ.ም
@gitmv
Code #6
2 046
አይ የግዜ
አይ የቀኑ መግፋት ፣አይ የግፉ መብዛት ፣
ግዜም እንደቀልድ ግፉም እንደ ልማድ ፣
ነጎደ በረረ ሁሉም እንደ ቀልድ ፣
፡
ሳናስበዉ መሸ ጸሃዮዋም ጠለቀች ፣
እሷም ርቃኝ ሄደች ቆየች ከመጠቀች ፣
፡
እኔም እያሰብኩሽ አንች ያለሽበት ፣
የኑሮ አቀበት የተራረን ግዝፈት ፣
እጅጉን ከብዶኛል አለቻልኩትም መዉጣት ፣
፡
አይ የግዜ ክፋት አይ የግዜ ቅናት ፣
እሷ እኔጋ ሳለች ይሮጣል ለመመሸት ፣
አይቼ ሳልጠግባት አቅፌ ሳልስማት ፣
፡
ንጋቱን በአንድ ላይ በዉብ ሳሰልፋት ፣
ግዜዉ ቀንቶብን ይሮጣል ለመንጋት ፣
አይ የግፉ መብዛት አይ የግዜዉ ቅናት።
በ ጎሣዬ ፊቄ✍
@gitmv
Code #5
2 046
"ጊዜ"
""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""
ነገ ስል፤ ዛራ ስል..
ዛሬ ስል፤ ነገ ስል..
ዛሬ ላይ ቁጭ ብየ፤ ነገ ይሆናል ስል
ነገን እያሰብኩኝ፤ ዛሬ ላይ ቁጭ ስል
ነገ ያልኩት ጊዜ፤ ዛሬ ሆኖ ያልፋል
ዛሬ ነው ያልኩት ቀን፤ ትላንት ሆኖ ያርፋል...
የማይመለሰው፤ እድሜየ ይጎርፋል
ብቻ በቀጠሮ፤ ጊዜ እያሳለፍኩኝ
'ቆይ ነገ፤ ቆይ ዛሬ'፤ ይሆናል እያልኩኝ
ጊዜም እድሜው አልቆ፤ ነገ ራሱ ቀርቶ
ጊዜም ጊዜው ደርሶ፤ ዛሬ መባል ትቶ
ዛሬና ነጋችን፤ ትላንት ሆኖ ቀርቶ
በቃ~ጊዜ አርጅቶ
በቃ~ጊዜ ቀርቶ
ጊዜ እሚባል~ጠፍቶ...
የዛሬ ሀሳቤ... ለነገ እንዳይሰፋ
የነገ ተስፋየ ደብዛው እንዳይጠፋ
ጊዜም ሰነፍ ይሁን፤ እሱም ጊዜ ያጥፋ
""""""""""""""""""""""""""""""""""""""
Halidoo ✍
@gitmv
Code #4
