ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

የስንኝ ቋጠሮ

የስንኝ ቋጠሮ

الذهاب إلى القناة على Telegram

የዚህ ቻናል ዋና አላማ የተለያዩ ወጣቶች የግጥም ችሎታቸውን የሚዳብሩበት እና የሚያወጡበት ቻናል ነው። ግጥሞችን ለመላክ @mogea ይጠቀሙ መልሰን ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል!!

إظهار المزيد
2 046
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام
أرشيف المشاركات
ተወዳዳሪዎችን ሸልመናል!!

sticker.webp0.16 KB

አንደኛ እና ሁለተኛ የወጡትን እንሸልማለን አንደኛ ሃሊድ ሁለተኛ ጎሳዬ ፍቄ ናቸው ሶስተኛ የወጣ የለም ስንጠብቅ ነበር ግን መድረስ አልቻሉም ስለሆነም አሁን ያሸነፋችሁ በውስጥ መስመር ስልካችሁን ላኩልን @gitmv @gitmv

አንደኛ

ሁለተኛ 🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆

አሁን ሁለተኛውን እና ሶስተኛውን እንጠብቃለን

አንደኛ 🏆🏆🏆🏆🏆🏆😁🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆

#ግጥመ -ቸርነት ⌚️⌚️⌚️"ጊዜ"⌚️⌚️⌚️ ጊዜ ሴኮንድ ነው ጊዜ ሚሊንየም፣ ባንዴ የሰራውን ሲያፈርስ አይዘገይም፣ ወይም በሌላ ጎን ሲገነባ አይፈጥንም። ጊዜ ስልጣን አለው፤ሹማምንቱን ሽሯል፣ ያላለፈ የለም ፤ሁሉም ተፈራርቋል። ግና ምን ያደርጋል ከንቱ እንጅ ነው ሁሉ ለጊዜም ጊዜ አለው፤ቦ ጊዜ ለኩሉ፣ እ'ግዜ'ሩ ሲመጣ አዝማናት ያልፋሉ። ስለዚህ ወገኔ ዘምን በዘመንህ፣ አኅትክን አትድፈር እዘን ለወንድምህ፣ ኋላ ፀሀይ ገብታ፤ ለዘለአለም ጠፍታ፣ መሽቶ እንዳይጨልምህ። 📝በቸርነት ሰኔ 2013 ዓ.ም @gitmv Code #6

#ግጥመ -ቸርነት ⌚️⌚️⌚️"ጊዜ"⌚️⌚️⌚️ ጊዜ ሴኮንድ ነው ጊዜ ሚሊንየም፣ ባንዴ የሰራውን ሲያፈርስ አይዘገይም፣ ወይም በሌላ ጎን ሲገነባ አይፈጥንም። ጊዜ ስልጣን አለው፤ሹማምንቱን ሽሯል፣ ያላለፈ የለም ፤ሁሉም ተፈራርቋል። ግና ምን ያደርጋል ከንቱ እንጅ ነው ሁሉ ለጊዜም ጊዜ አለው፤ቦ ጊዜ ለኩሉ፣ እ'ግዜ'ሩ ሲመጣ አዝማናት ያልፋሉ። ስለዚህ ወገኔ ዘምን በዘመንህ፣ አኅትክን አትድፈር እዘን ለወንድምህ፣ ኋላ ፀሀይ ገብታ፤ ለዘለአለም ጠፍታ፣ መሽቶ እንዳይጨልምህ። 📝በቸርነት ሰኔ 2013 ዓ.ም @gitmv Code #6

አይ የግዜ አይ የቀኑ መግፋት ፣አይ የግፉ መብዛት ፣ ግዜም እንደቀልድ ግፉም እንደ ልማድ ፣ ነጎደ በረረ ሁሉም እንደ ቀልድ ፣ ፡ ሳናስበዉ መሸ ጸሃዮዋም ጠለቀች ፣ እሷም ርቃኝ ሄደች ቆየች ከመጠቀች ፣ ፡ እኔም እያሰብኩሽ አንች ያለሽበት ፣ የኑሮ አቀበት የተራረን ግዝፈት ፣ እጅጉን ከብዶኛል አለቻልኩትም መዉጣት ፣ ፡ አይ የግዜ ክፋት አይ የግዜ ቅናት ፣ እሷ እኔጋ ሳለች ይሮጣል ለመመሸት ፣ አይቼ ሳልጠግባት አቅፌ ሳልስማት ፣ ፡ ንጋቱን በአንድ ላይ በዉብ ሳሰልፋት ፣ ግዜዉ ቀንቶብን ይሮጣል ለመንጋት ፣ አይ የግፉ መብዛት አይ የግዜዉ ቅናት። በ ጎሣዬ ፊቄ✍ @gitmv Code #5

"ጊዜ" """""""""""""""""""""""""""""""""""""""" ነገ ስል፤ ዛራ ስል.. ዛሬ ስል፤ ነገ ስል.. ዛሬ ላይ ቁጭ ብየ፤ ነገ ይሆናል ስል ነገን እያሰብኩኝ፤ ዛሬ ላይ ቁጭ ስል ነገ ያልኩት ጊዜ፤ ዛሬ ሆኖ ያልፋል ዛሬ ነው ያልኩት ቀን፤ ትላንት ሆኖ ያርፋል... የማይመለሰው፤ እድሜየ ይጎርፋል ብቻ በቀጠሮ፤ ጊዜ እያሳለፍኩኝ 'ቆይ ነገ፤ ቆይ ዛሬ'፤ ይሆናል እያልኩኝ ጊዜም እድሜው አልቆ፤ ነገ ራሱ ቀርቶ ጊዜም ጊዜው ደርሶ፤ ዛሬ መባል ትቶ ዛሬና ነጋችን፤ ትላንት ሆኖ ቀርቶ በቃ~ጊዜ አርጅቶ በቃ~ጊዜ ቀርቶ ጊዜ እሚባል~ጠፍቶ... የዛሬ ሀሳቤ... ለነገ እንዳይሰፋ የነገ ተስፋየ ደብዛው እንዳይጠፋ ጊዜም ሰነፍ ይሁን፤ እሱም ጊዜ ያጥፋ """""""""""""""""""""""""""""""""""""" Halidoo ✍ @gitmv Code #4

⌚⌚⌚ ጊዜ ⌚⌚⌚ በዚህ ፈጣን ዘመን ፣ ጉልበቴ ባልቻለው ፣ ለመስራት ለማግኘት ፣ ቀኔን የማረዝመው ፣ ነገር ግን ሳይሰሩ ቢበሉም ፣ እንጀራው ያለቅሳል ፣ የሚባል አባባል ፣ ጫንቃችን ላይ ወቷል ፣ ለመኖር በአለም ላይ ፣ አቅም ይላልና ፣ ለፍተህ ጥረህ ግረህ ፣ ሀብት አዳብርና ፣ ጊዜህን ተጠቀም ፣ ዞሮ አይመጣምና ፣ ✍✍በቃለአብ መስፍን @gitmv Code #3

ጊዜ መሰላል ነው ያነሳል ይጥላል፣ ፊተኘዉን ከኋላ ኋለኘዉን ከፊት ያሽቅደመድመዋል። እረ ጊዜ ጊዜ የት ትመለሽ አለሽ፣ አንዴ ካመለጥሽኝ ፊትሽን አላገኝሽ። (አቢ) @gitmv Code #2

ጊዜ ማንም አይቻለው ጊዜን ሊለውጥ ተፈጥሮ ነውና ከላይ የሚሰጥ። በሰማይ በመሬት ስራ ለመስራት ፤ ጊዜ ያስፈልጋል በእቅድ መመራት ። እንደ ጊዜ ጀግና ከቶ የት ይገኛል፤ ግጥምም ለመጻፍ ጊዜ ያስፈልጋል ፤ ለሰራበት ሰጥቶ ላልሰራበት ያልፋል። JUNE 12-2021 Fisiha @gitmv code #1

ጀመረ

1⃣

2⃣

3⃣

ሊጀምር ነው

ልክ 3:00 ላይ ውድድሩን እንጀምራለን