cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ድን መመካከር ነው الدين النصيحة

ድን መመካከር ነው الدين النصيحة ቁርአንና ሀዲስ በሰለፎች ግንዛቤ እንዲሁም የሰለፎች ንግግር ላይ ያተኮሩ አጫጭር ፅሁፎች እና የድምፅ ትምህርቶች የሚተላለፉበት፤ ኢስላማዊ ግንዛቤዎን ከፍ ለማድረግ የሚተጋ ቻናል ነው። ሼር እንድሁም ጆይን ያድርጉ! 👇 👇 👇 👇 👇 https://telegram.me/dinmemekaker

Show more
Advertising posts
201
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
+430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Show all...
የፎቶ ጉዳይ.mp33.95 KB
Show all...
አስለቃሽ እና አስተማሪ ትእግስት.m4a25.08 MB
👉 ሰዎች ወደ አብሬት ለምን ይጓዛሉ ? የኢስላም ጠላቶች የእስልምና ጮራ ከፈነጠቀበት ጊዜ አንስተው ብርሀኑን ለመግታት ከቻሉም ለማጥፋት ብዙ ሞክረዋል ። በተለይ የመጀመሪያው ትውልድ የኢስላምን አድማስ እያሰፋ በነበረበት ጊዜ በዐለም ላይ የነበሩ ሀያላን የሚባሉ ሀገራት ከኢስላሙ ብርሀን ፊት ለመቆም ብዙ ዋጋ ከፍለዋል ። ግን ልፋታቸው ያ ትውልድ ከአላህ ጋር በነበረው ጥብቅ ትስስር ምክንያት መክኖ እንዲቀር አድርጎታል ። ተስፋ የማይቆርጠው የሸይጣን ሰራዊት አንዱ ሜዳ ላይ ሲሸነፍ ሌላ ሜዳ ፊቱን እያዞረ ከአራሕማን ሰራዊት ጋር ሲፋጠጥ ምኞቱ ከስሞ ቅስሙ ተሰብሮ መመለስ እንጂ ወደ ፊት መቀጠል አልቻለም ። የዚህ አይነቱ ሽንፈት ሚስጢር ሳይገባቸው በማያውቁት ነገር የኪሳራ ካባ ሲደራርቡ ሚስጢሩን ማወቅ አለብን አሉ ። በዚህም ቆም ብለው ያሳለፉትን በህሊናቸው መስኮት እያማተሩ ሲያዩ ብዙ ሰራዊት በቁጥርም በትጥቅም የማይገናኝ ከጥቂቶች ፊት መቆም እንዲያቅተው ያደረገው በአራሕማን ሰራዊት ልብ ውስጥ የነበረው የኢማን ሀይል መሆኑን አወቁ ። እየተሸነፉ ያሉት በመሳሪያና በሰራዊት ብዛት እንዳልሆነ ይልቁንም ትንሹ ሰራዊት ከአላህ ጋር ባለው የጠበቀ ትስስር በአላህ እርዳታ መሆኑን ገባቸው ። እያሸነፋቸው ያለው የተውሒድ አቅም እንጂ የሰራዊት አቅም አለመሆኑን አመኑ ። የዚህን ጊዜ እስትራቴጂ መቀየር አስፈላጊ ሆነ ። ጦርነቱ ከኢማን ጋር ከተውሒድ ጋር ሆነ ለዚህም ሰራዊት መመልመል ጀመሩ ። የአሁኑ መሳሪያ በጀርባ አዝለውት በትከሻ ተሸክመውት የሚሄዱት አይደለም ። ቀላል ሆኖ በጣም አጥፊ መሳሪያ ነው ። በሙስሊሞች ልቦና ውስጥ ያለውን ተውሒድ የሚያጨልም ኢማናቸውን የሚያቀልጥ የሹብሃ መሳሪያ የስሜት መከተል መሳሪያ መታኮስ መሳየፍ የማያስፈልገው በጥቂት ቃላቶች የሚገለፅ ቶሎ ልብ ላይ የሚሰርፅ መሳሪያ መጠቀም ጀመሩ ። የጦርነቱ ሜዳ ከበረሀ ወደ ሽርክና ቢዳዓ ፋብሪካ ተዛወረ ። ከሙስሊሙ ውስጥ ለዚህ ፋብሪካ ሰራዊት መለመሉ ከበላይ የሚመራው የዐብዱላሂ ኢብኑ ሰበእ አልየሁድይ ሀላፊነቱ የተወሰነ የኩፍር ማህበር ሆነ ። የሺዓ ፋብሪካ ተከፈተ በወልይ ስም ሙታኖች ይጠቅማሉ ፣ ይሰማሉ ፣ ይረዳሉ ፣ አላህ ስልጣን ሰጥቷቸዋል በሚል አላህን ትቶ እነርሱን መጥራት ተንሰራፋ ። ጎን ለጎን የተለያዩ የቢዳዓ ፋብሪካዎች እየተከፈቱ የሙታን መንፈስ ማምለኩ አድማሱ እያሰፋ ቅርንጫፉ እየበዛ ለዓለም ተዳረሰ ። የሱፍያው እህት ኩባንያ ይህን ሽርክ የማስፋፋቱ ስራ በሰፊው ተያያዘው ። በዚህም በቀላሉ ከሙስሊሙ ማህበረሰብ አላህ ያዘነለት ሲቀር ከውስጡ በአላህ ማመን የሚባለውን ማውጣት ቻሉ ። በዚህም አብዛኛውን ሙስሊም ኮፍያ ጥምጣምና ጀለብያ የለበሰ ቆሞ የሚሄድ ውስጡ ባዶ የሆነ እስከሌተን አደረጉት ። የኢስላም ጠላቶች ሀገራችን ላይ ሙስሊሙን ከኢማኑ ለማራቆት ከከፈትዋቸው የሽርክ ፋብሪካዎች አንዱ አብሬት ያለው ሀድራ ነው ። ቅርንጫፉ ጠቅላይ ቢሮ የሚባለው አ/አ ነው ። ሰዎች በየአመቱ ወደ አብሬት የሚገርፉት በአላህ ላይ ለማጋራት ውስጣቸውን አላህ ይጠቅማል ከሚለው ኢማን ባዶ አድርገው ያብሬት ሸይኾች ይጠቅማሉ በሚል ቀይረው ለሳቸው ችግራቸውን ለመንገር ነው ። ‼ አው አብሬት የሚሄድ ሙሪድ ኮፍያ ያደረገ ፣ ጀለብያ የለበሰ ፣ ጥምጣም የጠመጠመ ወይም ስሙ ሙሐመድ ፣ አሕመድ ፣ ከማል ፣ ሰፋ ፣ ጀማል የሆነ የሙታን መንፈስ አምላኪ ነው ። ሀድራውን የሚመሩት ጫት ናላቸውን ያዞራቸው ጠንቋዮች ናቸው ። ህዝቡን ቁርኣንና ሐዲስ ሳይሆን ያብሬትዬ የሚሉት ሸይጣን ወሕይ የሚያደርግላቸው ገድል ነው ። አብዛኛው አብሬትዬ ይመጣሉ በሚል ከሀገሩ የወጣ ነው ። ዱዓእ ሲያደርጉ በሀድራቸው አላህ ያስገባቸው የሚል ነው ።‼ ይህ ተራውን ህዝብ የሚያስተኙበት እንጂ ገስግስ እንደገደላቸው ያውቃሉ ። የራሳቸው ልጆች አንዱ ሌላውን አባታችንን አስገድለዋል በሚል ክስ ላይ ናቸው ። ይህ ከመሆኑ ጋር ወደ አብሬት የሚጎርፈው ህዝብ ችግሩን ለአብሬትዬ ይናገራል ። ዘር ስጡኝ ፣ ከጭንቅ አውጡኝ ፣ ድረሱልኝ ፣ ለማን ተውኝ ይላል ። መከራውን ፣ ችግሩን ፣ ሐዘኑን ፣ ማጣቱን ፣ መጎዳቱን ፣ ፍርሀቱን ለሳቸው ይናገራል ። እርዱኝ ፣ አክብሩኝ ፣ እጄን ያዙኝ ይላል ። ኧናገራ ያለውን የአባታቸው ቀብር ( ኧቁባይ ) ሄዶ አፈር ይበላል ። በእንብርክኩ ወደ ቀብሩ ይደርሳል ። ስልኩን አጥፍቶ ጫማውን ከሐረሙ ( ከጊቢ ) ውጪ አስቀምጦ በእንብርክክ ሄዶ ቀብሩ ጋር ስጁድ አድርጎ በጠዋፍ ዞሮ ለአላህ እንጂ የማይገባ አምልኮ ያደርጋል ። ጉዱ በዚህ አይቆምም በየአመቱ የሚሄዱ አንድ ላምስት ተደራጅተው ወደዚህ ቀብር አምልኮ ለመጣራት ተስማምተው ይመጣሉ ። አሕባሽና ሱፍዮች የዚህ አይነቱን የሽርክና የኩፍር ተግባር በገንዘብ በመርዳት አድማሱ እንዲሰፋና ሙስሊሞች ቀብር አምላኪ እንዲሆኑ ቀንና ለሊት ይሰራሉ ። ይህ ከእስልምና የሚያወጣ ሽርክ ነው ተብሎ ስፍር ቁጥር የሌላቸው የቁርኣን አንቀፆች ሲነገራቸው ለከሀዲያን የወረዱ የቁርኣን አንቀፆች ለሙስሊሞች ያደርጋሉ ይላሉ ። ‼ እነዚያ አላህ ሙሽሪክ ያላቸው ከሀዲ ያላቸው ሰዎች ጥቁር ፣ቀይ ፣ ዐረብ ፣ ዐጀም ፣ አጭር ፣ ረዥም ፣ ስለነበሩ ነው ወይስ የሚሰሩት የነበረው ተግባር የኩፍርና የሽርክ ተግባር ስለነበረ ነው ? በእነዚ አባባል ስለ ሶላት ፆምና ዘካ የሚናገሩ አንቀፆች ለእነዛ በዛ ዘመን ለነበሩት ብቻ ነበር አሁን አይሰራባቸውም ማለት ነው ። ‼ ሁሉም በየትኛውም ጉዳይ የመጡ የቁርኣንና የሐዲስ መረጃዎች በየትኛውም ዘመን የትም ቦታ ይሰራሉ ። ሙሽሪኮቹ ሲሰሩት የነበረውን ሺርክ የሚሰራ ሙሽሪክ ይባላል ። ከሀዲያን የሚሰሩትን የኩፍር ተግባር የሚሰራ ካፊር ይባላል ። በግለሰብ ላይ ብይኑን ለመስጠት የሚያስችሉ መስፈርቶች ተሟልተው ከልካዮች ሲወገዱ መረጃው ሲደርስ ያግለሰብ ካፍር ነው ይባላል ። የቁርኣን ህጎች በወረዱበት ምክንያት የተገደቡ አይደሉም ። ቃሉ በያዘው ብይን እስከቂያማ ይሰራሉ ። በመሆኑም እናትና አባቶቻችንን ከአሕባሽና ሱፍዮች እጅ ለማውጣትና ወደ ተውሒድና ትክክለኛ እስልምና ለማምጣት የምንችለውን ማድረግ ይጠበቅብናል ። አላህ ይወፍቀን ። https://t.me/bahruteka
Show all...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

بسم الله الرحمن الرحيم ድሮ ስእል በመሳል ላይ የሚሰማሩት ጥቂቶች ነበሩ፡፡ ዛሬ ግን ከድሮው በተሻለ ምስልን ለማስገኘት ያን ያክል ብቃትም አይጠይቅም፡፡ ዘመናዊ መሳሪያዎችን በመጠቀም ከህፃን እስከ አዋቂ፣ ከገጠሬ እስከ ከተሜው ሁሉም በቀላሉ ምስሎችን ማምረት ይችላል፡፡ የሰራውንም በቀላሉ በማህበራዊ ድረ-ገፆች መልቀቅ ይችላል፡፡ ስእል መሳል በዲናችን የተወገዘ ምግባር ነው፡፡ ኧረ እንዳውም ከከባባድ ወንጀሎች ውስጥ የሚመደብ ነው፡፡ ይህን ከሚያመላክቱ ማስረጃዎች ውስጥ ጥቂቶቹን ለማየት እንሞክር፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፡- 1. “ከሰው ሁሉ ቅጣት የሚበረታባቸው ሰዎች ሰአሊዎች ናቸው፡፡” (ቡኻሪና ሙስሊም) 2. “የቂያማ ቀን የሚያዩ ሁለት አይኖች፣ የሚሰሙ ሁለት ጆሮዎች እና የሚናገር ምላስ ያለው አንገት ከእሳት ውስት ይወጣና እንዲህ ይላል፡ እኔ በሶስት ሰዎች ላይ ተወክያለሁ፡፡ በእያንዳንዱ አረመኔ አንባገነን ላይ፤ በእያንዳንዱ ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ በተጣራ እና በሰአሊዎች ላይ!!” (ቲርሚዚ) 3. ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሰኣሊን ተራግመዋል፡፡ (ቡኻሪ) ሱብሓነላህ! እነዚህ ሐዲሦች ምንኛ አስፈሪ መልእክት ነው የያዙት!! ጌታዬ ሆይ ከአሳማሚውና አስፈሪው ቅጣትህ እና ከነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እርግማን አንተው ጠብቀን፡፡ ምስል ያለበት ቤት መላእክት አይገባም!! ይህን አስመልክተው ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፡- 1. “ምስሎች ካሉበት ቤት ውስጥ መላእክት አይገቡም፡፡” (ቡኻሪና ሙስሊም) 2. “ውሻና ምስል ካለበት ቤት ውስጥ መላእክት አይገቡም፡፡” (ቡኻሪና ሙስሊም) ልብ ይበሉ፡-1 የተከለከለው የምስል አይነት አንዳንዶች እንደሚያስቡት የሚዳሰስ የሚጨበጥ ጥላ ያለው ብቻ አይደለም፡፡ የቅብ ወይም የቀለም ስእሎችም ከዚሁ ውስጥ ይገባሉ፡፡ ለዚህም ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ስእል ያለበት መጋረጃ ሲያዩ ተቆጥተው ማስወገዳቸው ዋቢ መሆን ይችላል፡፡ ልብ ይበሉ፡- 2 ምስል በየትኛውም መንገድ ቢሰራ ምስል ነው፡፡ በየትኛውም መንገድ ቢገኝም ውግዝ ነው፡፡ “ሰአሊ ሁሉ የእሳት ነው” የሚለው የነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ንግግር ጠቅላይ መልእክት ነው፡፡ ጥቅል ህግ ደግሞ ያለ ማስረጃ አይገደብም፡፡ “አይ በዚህ ጠቅላይ ህግ ውስጥ የማይካተቱ ነገሮች አሉ” የሚል ካለ ጠንካራና የማያሻማ ቁርኣናዊ ወይም ሐዲሣዊ ማስረጃ ሊጠቅስ የግድ ይለዋል፡፡ ልብ ይበሉ፡- 3 ግልፅና የማያሻሙ አስፈሪ የነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሐዲሶች እየተጠቀሱ ሳለ በተቃራኒው ፍፁም ያልሆኑ ሰዎችን አባባል መጥቀስ አደብ አይደለም፡፡ ሐቅ ፈላጊ የሆነ ሰው ወሕይን በረእይ አይዳፈርም፡፡ ሰማያዊ መልእክትን በግለሰባዊ ንግግር ወይም ተግባር አያፈርስም፡፡ ሌላው ቀርቶ ለምን ተናጋሪው ሶሐባ አይሆንም!! ኢብኑ ዐባስ ረዲየላሁ ዐንሁ፡ “ከሰማይ ድንጋይ ሊዘንብባችሁ ይቀርባል!! የአላህ መልእክተኛ እንዲህ አሉ እላችኋለሁ እናንተ አቡ በክር እንዲህ ብሎ ዑመር እንዲህ ብሎ ትላላችሁ” በማለት አስፈሪ ነገር ይናገራሉ፡፡ አስተውሉ! ሐዲሥ እየተጠቀሰ አቡ በክርንና ዑመርን በተቃራኒው ማጣቀስ እንዲህ ካስባለ ከነሱ እጅግ ያነሱ አካላትን ማጣቀስስ ምን ሊባል ነው? ስለዚህ ለማንም ንግግር ብለን የነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሐዲሥ ልንጥል አይገባም፡፡ “የአላህ መልእክተኛን ሐዲሥ የመለሰ እሱ የጥፋት አፋፍ ላይ ነው” ይላሉ አልኢማም አሕመድ፡፡ ልብ ይበሉ፡- 4 - ፎቶን የሚፈቅዱ ዑለማዎች እራሳቸው የሚከለክሉባቸውም ብዙ ፈትዋዎች ስላሏቸው ሚዛን የሚደፋውን ሳንፈትሽ ከስሜታችን ጋር የሚሄደውን ብቻ እየመረጥን አንውሰድ፡፡ - የሚፈቅዱት እራሳቸው ለማስታወሻና ለመዝናኛ መጠቀምን፣ ማስቀመጥን አልፈቀዱም፡፡ የማወራው ስለሱና ዑለማዎች ብቻ ነው፡፡ - በዚያ ላይ ደግሞ የዑለማ ንግግር ማስረጃ የሚፈልግ እንጂ በራሱ ማስረጃ አይደለም፡፡ ማስረጃ ያለው በቁርኣንና በሐዲሥ ላይ ነው፡፡ ያሉት ማስረጃዎች ደግሞ አስፈሪና የማያሻሙ ናቸው፡፡ ልብ ይበሉ ፡- 5 ምስል መሳል የተከለከለበት አንዱ ምክኒያት ለባእድ አምልኮ ስለሚያሸጋግር ነው፡፡ ይህን ምክኒያት ብቻ ነጥሎ በማውጣት “የኛ ከዚህ ጋር የሚገናኝ ስላልሆነ ችግር የለውም” የሚሉ አሉ፡፡ ነገር ግን ምስል የተከለከለበት ምክኒያት ይሄ ብቻ አይደለም፡፡ ለምሳሌ ፈጣሪ እንደሚፈጥረው ማመሳሰል መኖሩ አንድ ምክኒያት ነው፡፡ ለዚህም የሚከተሉት ሐዲሦች ማስረጃ ይሆናሉ፡- 1. “አሸናፊና የላቀው አላህ እንዲህ ብላል፡ እንደኔ መፍጠር ሊፈጥር እንደሞከረ ሰው ማን በዳይ አለ?! (ከቻሉ) ቅንጣትን ይፍጠሩ፡፡ የገብስ ፍሬን ይፍጠሩ፡፡” (ቡኻሪና ሙስሊም) 2. “እነዚያ ምስሎችን የሚሰሩ ሰዎች በቂያማ ቀን ይቀጣሉ፡፡ የፈጠራችሁትን ህይወት ዝሩበት! ይባላሉ፡፡” (ቡኻሪና ሙስሊም) 3. “ዱንያ ላይ ምስልን የሰራ የቂያማ ቀን ሩሕ እንዲነፋበት ይገደዳል፡፡ የሚነፋ ደግሞ አይደለም፡፡” (ቡኻሪና ሙስሊም) 4. “ሰአሊ ሁሉ የእሳት ነው፡፡ በእያንዳንዱ በሳላት ምስል ነፍስ ይደረግና ጀሀነም ውስጥ ትቀጣዋለች፡፡” (ቡኻሪና ሙስሊም) ስለዚህ “እኔ ማመሳሰልን አስቤበት አይደለም” ማለት አያዋጣም፡፡ ምስሉን ማስገኘቱ በራሱ ማመሳሰል ነውና፡፡ ፎቶ የሚፈቅዱ ሰዎች ከማይጨበጡ ፍልስፍናዎቻቸው በተጨማሪ በዋናነት የሚያጣቅሱት ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚንን ነው ረሒመሁላህ፡፡ ሸይኹ ግን “ማመሳሰል ነው ለማለት ያን አስቦ መስራቱ መስፈርት አይደለም፡፡ እናም ማመሳሰሉ እስከተገኘ ድረስ ብይኑም ተከትሎት ይረጋገጣል” ይላሉ፡፡ ልብ ይበሉ፡-6 አንገብጋቢ ለሆኑ ጉዳዮች ምስልን መጠቀም እንደሚቻል ዑለማዎች ይናገራሉ፡፡ ይሄ ደግሞ “ችግሮች የተከለከሉ ነገሮች ያስፈቅዳሉ” ከሚለው ሸሪዐዊ መርህ የተወሰደና ቁርኣናዊም ሐዲሣዊም መነሻ ያለው ህግ ነው፡፡ ልክ አማራጭ ያጣ ሰው በክት መብላት እንደሚችለው ማለት ነው፡፡ በዚህም መሰረት ለተለያዩ አንገብጋቢ ማስረጃዎች ለምሳሌ፡- መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ መንጃ ፍቃድ፣ የመኖሪያ ፍቃድ፣ የአፋልጉኝ ማስታወቂያ፣ አጥፊዎችን ለማደን፣ ለማስተማርና ለመሳሰሉት መጠቀም ይቻላል ማለት ነው፡፡ እዚህ ላይ ግን ለችግሩ የሚያስፈልገውን ያክል ብቻ ነው እንድንጠቀም የሚፈቀደው፡፡ ልብ ይበሉ፡- 7 ወንዶች ሆይ! ክልከላው እኮ ወንዱንም ይመለከታል፡፡ ከሴቶች ፎቶ ስር እየተከተልን “አላህን ፍሩ” የምንል ወንዶች ማስታወሳችን ጥሩ ሆኖ ሳለ ነገር ግን እራሳችንንም ልንረሳ አይገባንም፡፡ እህቶቻችንን እንደምናስታውሰው እራሳችንንም ወንድሞቻችንንም እናስታውስ፡፡ እርግጥ ነው ተያያዥ መዘዝ ከመከተሉ አንፃር ካየነው የጥፋቱ መጠን ሊለያይ ይችላል፡፡ ቢሆንም ግን ወንዱ ይቅር የተባለ እስከሚመስል ዝምታን ባንመርጥ መልካም ነው፡፡ ማህበራዊ ድረ-ገፆች ላይ “አላህን ፍሩ” በማለት ፋንታ “ዋው” “ዊው” እያሉ ለጥፋት ሞራል የምንሰጥ ሁሉ የጥፋቱ ተጋሪዎች እንደምንሆን አንርሳ፡፡ ልብ ይበሉ፡- 8 ምስል አይተን ሳናበላሽ እንዳናልፍ ነብያዊ አደራ ተጥሎብናል፡፡ (አሕካሙል ጀናኢዝ፡ 207) ስለዚህ የቻለ ሰው ፊትና በማይፈጥር መልኩ ምስሎችን የማስወገድ አሃላፊነት አለበት፡፡ ይህ ካልሆነ ግን በምላስ ማስጠንቀቅ፡፡ ይህም ካልሆነ በልብ መጥላት ይጠበቅብናል፡፡ ይህን ድንበር አልፈን ከጥፋቱ ከወደቅን ለጥፋት ልንሟገት፣ ለአጥፊዎች ጠበቃ ልንሆን፣ ለጥፋታችን ሸሪአዊ ሽፋን ልንፈልግ አይገባም፡፡ ይልቁንም ጥፋታችንን ማመን የተሻለ ምርጫ ነው፡፡ አላህ እሱን በመፍራት ላይ ያግዘን፡፡
Show all...
ድን መመካከር ነው الدين النصيحة

ድን መመካከር ነው الدين النصيحة ቁርአንና ሀዲስ በሰለፎች ግንዛቤ እንዲሁም የሰለፎች ንግግር ላይ ያተኮሩ አጫጭር ፅሁፎች እና የድምፅ ትምህርቶች የሚተላለፉበት፤ ኢስላማዊ ግንዛቤዎን ከፍ ለማድረግ የሚተጋ ቻናል ነው። ሼር እንድሁም ጆይን ያድርጉ! 👇 👇 👇 👇 👇

https://telegram.me/dinmemekaker

** ስለዚህ በማህበራዊ ድረ-ገፆች ፎቷችሁን እየለቀቃችሁ የፊትና ሰበብ የምትሆኑ ወገኖች ሆይ! ፎቶ በመፅሄት የምታወጡ የኮሌጅና የዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች ሆይ አላህን ፍሩ፡፡ እዚህ ግባ ለማይባል የማይጨበጥ ቅፅበታዊ ደስታ ብላችሁ ከአላህ ጋር አትጣሉ፡፡ ወወላሂ ለመፅሄት የተሰበሰቡ ፎቶዎችን መፅሄቱ ላይ አውጥተው ሲመለሱ ቆንጆ ቆንጆ የሚሏቸውን ሴቶች ፎቶ ለማስቀረት ሲመርጡ የነበሩ ወንዶችን በአይኔ አይቻለሁ፡፡ ፌስቡክም ላይ የሴቶችን ፎቶ ግራፍ ለእኩይ ምግባር የሚያውሉ ወንዶችን እየተመለከትን ነው፡፡ አላህ የመልእክተኛውን ትእዛዝ የምናከብር፣ ክልከላቸውንመ የምንርቅ ያድርገን፡፡ وصلى الله على نبينا محمد وعلى آله وصحبه وسلم https://t.me/dinmemekaker
Show all...
ድን መመካከር ነው الدين النصيحة

ድን መመካከር ነው الدين النصيحة ቁርአንና ሀዲስ በሰለፎች ግንዛቤ እንዲሁም የሰለፎች ንግግር ላይ ያተኮሩ አጫጭር ፅሁፎች እና የድምፅ ትምህርቶች የሚተላለፉበት፤ ኢስላማዊ ግንዛቤዎን ከፍ ለማድረግ የሚተጋ ቻናል ነው። ሼር እንድሁም ጆይን ያድርጉ! 👇 👇 👇 👇 👇

https://telegram.me/dinmemekaker

እህታችን በከበደ ሁኔታ ውስጥ ነች ፣ ለአላህ ብለን እንርዳት !! አሰላሙ  ዓለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካቱህ:—እህታችን ዘህራ ሰዒድ የአ አ ነዋሪና የሁለት ሴት ልጆት እናት ስትሆን በአሁኑ ሰዓት በከፍተኛ የኩላሊት ችግር እንዲሁም ከኩላሊት ችግሩ ጋር ተያይዞ የቫይታሚን ዲ እጥረት ፣ የአጥንት መሳሳት ችግር የወለደው የዳሌ አጥንት ስብራት እና ከፍተኛ የሆነ የደም ማነስ  አስከትሎባታል ለአጥንት ስብራቱ በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በወንድሞች ትብብር ከመቶ ሺህ ባላነሰ ወጭ የታከመች ሲሆን አሁን ላይ ሆስፒታሉ  የኩላሊት እጥበት እንደሚያስፈልጋት ቢወስንም ትጥበቱን ማግኘት የምትችለው በግል ሆስፒታል ሲሆን ለመጀመር ደግሞ  80000 ብር ተጠይቃለች ለቀጣይ ስንት እንደሚያስፈልጋት ባይታወቅም ሰለሆነም ይህች ሚስኪን እህታችን እነኚኅ  ተደራራቢ የሆኑ የጤና ችግሮች የገጠሟት ስለሆነ በዱዓም እጆቻችንንም በመዘርጋት እንተባበራት ። አሏህ ኸይር  ጀዛችሁን ይክፈላችሁ ። ከጤና መታወክም ሁላችንንም ይጠብቀን። እሷንም አሏህ ጤናዋን ይመልስላት። 1000539386917 Sofia Yimam endris CBE
Show all...
Show all...
ድን መመካከር ነው الدين النصيحة

ድን መመካከር ነው الدين النصيحة ቁርአንና ሀዲስ በሰለፎች ግንዛቤ እንዲሁም የሰለፎች ንግግር ላይ ያተኮሩ አጫጭር ፅሁፎች እና የድምፅ ትምህርቶች የሚተላለፉበት፤ ኢስላማዊ ግንዛቤዎን ከፍ ለማድረግ የሚተጋ ቻናል ነው። ሼር እንድሁም ጆይን ያድርጉ! 👇 👇 👇 👇 👇

https://telegram.me/dinmemekaker

Photo unavailableShow in Telegram
የዚክር ትሩፋት! ከአቢ ደርዳ (رضي ﷲ عنه) ተይዞ: ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿أَلَا أُنَبِّئُكُمْ بِخَيْرِ أَعْمَالِكُمْ، وَأَزْكَاهَا عِنْدَ مَلِيكِكُمْ، وَأَرْفَعِهَا فِي دَرَجَاتِكُمْ، وَخَيْرٌ لَكُمْ مِنْ إِنْفَاقِ الذَّهَبِ وَالْوَرِقِ، وَخَيْرٌ لَكُمْ مِنْ أَنْ تَلْقَوْا عَدُوَّكُمْ، فَتَضْرِبُوا أَعْنَاقَهُمْ، وَيَضْرِبُوا أَعْنَاقَكُمْ ". قَالُوا : بَلَى. قَالَ : " ذِكْرُ اللَّهِ تَعَالَى﴾ فَقَالَ مُعَاذُ بْنُ جَبَلٍ: مَا شَيْءٌ أَنْجَى مِنْ عَذَابِ اللَّهِ مِنْ ذِكْرِ اللَّهِ “ከመልካም ስራዎቻችሁ በላጭ፣ ከንጉሳችሁ ዘንድ የጠራ፣ ደረጃዎቻችሁን ከፍ የሚያደርግ፣ ወርቅና ብር ከመለገስ የሚሻላችሁ፣ ጠላቶቻችሁን አግኝታችሁ አንገቶቻቸውን ከምትመቱና አንገቶቻችሁን ከሚመቱ (ከጂሃድ) የሚበልጥባችሁን አልነግራችሁምን? ሶሐቦች እንዴታ! ይንገሩን የአላህ መልእክተኛ ሆይ! አሉ። ‘አሸናፊና የላቀውን አላህ ማውሳት’ አሉ።” ሙዐዝ ቢን ጀበል እንዲህ ይላል፦ “ከአላህ ቅጣት ነፃ የሚያወጣ አንድም ነገር የለም ዚክር ‘አላህን ማውሳት’ ቢሆን እንጂ።” 📚 ቲርሚዚ ሶሂህ ብለውታል: 3377 በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦ Telegeram፦ https://bit.ly/4ayf0xJ Whatsup፦ https://bit.ly/486xnrS Facebook፦ https://bit.ly/41zEZkk Instagram፦ https://bit.ly/4arMbTx X፦ https://bit.ly/41tIUPv Youtube፦ https://bit.ly/41yPkNg
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.