en
Feedback
Guzo Adwa updates

Guzo Adwa updates

Open in Telegram
5 345
Subscribers
-124 hours
-77 days
-2430 days
Posts Archive
ይህ ቀጣዩ የጉዞ መዳረሻችን ነው:: የውሎ ገብ ጉዞ ወደ ማሩ ፏፏቴ:: መስከረም 24/october 04 ዝናቡ አልፏል ፤ ተፈጥሮ በአረንጓዴ ውበቷ እየፈካች ነው! 💚🌼 አደይ አበባ በሜዳው፣ ንጹህ ውሃ በፏፏቴው ፣ ጭጋግ በተራራው… ኢትዮጵያ በዚህ ወቅት ሌላ ውበት አላት። ⛰️ ይህ ከከተማ የመውጣት፣ የመጓዝ፣ የመሳቅ እና ከጓደኞች ጋር ትዝታ የምንፈጥርበት ወቅት ነው። ከ @guzoad ጋር በዚህ ወር ይጓዙ። አረንጓዴዋን ኢትዮጵያ፣ ንጹህ ፏፏቴዎቿን እና የተፈጥሮ ምስጢሮቿን አብረን እንፈልግ። 🥾 ወቅቱ አልፎ እንዳይቆጩ … ቦታዎን አሁኑኑ ያስይዙ! 👉ሁሌም እንደምንለው አስቀድሞ ቦታ በመያዝ የክፍያ ቅናሽ ዕድሉን ይጠቀሙ! Get 10% OFF when you book early! ለምዝገባ እና ተጨማሪ መረጃዎች በተከታዮቹ የስልክ አድራሻዎች ያግኙናል:: 📞 +251 942 545 470 📞 +251 929 176 542 ወይንም በ @guzoadwahiking @guzoad

photo content
+4

photo content
+9

የዚህ ወር የጉዞ እቅዳችሁ ከእኛ ጋር ይሁን ! MESERETE WEGERAM VILLAGE, GURAGE ⛺ 3 Days / 2 Nights Camping 📅 መስከረም 15-17 / September 25–27 የዘንድሮው መስቀልን-በጉራጌ ጉዟችን በዚህ ስፍራ በልዩ ሁኔታ ተሰናድቷል:: Culture • Nature • Adventure. 2. MARU WATERFALL / ALELTU 🥾 Day Hike 📅 መስከረም 24/ October 4 ከአለልቱ ከተማ በቅርብ ርቀት የሚገኘው ተወዳጁ የውሎ ገብ ጉዞ መዳረሻችን:: 💦 Waterfall • Nature • Adventure 3.HULUKO WATERFALL & CAVE 🥾 Day Hike 📅 ጥቅምት 01/ October 11 በቅርቡ በጉዞ ዓድዋ ሃይኪንግ ፈር ቀዳጅነት የመጀመሪያ ዙር ጉዞ ተዘጋጅቶ በብዙዎች ዘንድ የተወደደው አዲሱ የሁልቆ ፏፏቴ እና ዋሻ :: ከ አዲስ አበባ 65 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ:: 4.LAKE KILOLE (ኪሎሌ ሀይቅ) 🥾 Day Hike 📅 ጥቅምት08/ October 18 ከአዲስ አበባ 70 ኪሎ ሜትር ብቻ በመጓዝ : ከደብረዘይት ወይንም ቢሾፍቱ ከተማ 18 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምናገኘው አዲሱ የውሎ ገብ ጉዞ መዳረሻችን:: 🌊 Lake • Landscape • Hiking 5.YEM — BOR MOUNTAIN ⛺ 1 Night Camping 📅 ጥቅምት 16-17/October 26–27 (Monday-teusday የዘንድሮ የሳሞኤታ በዓል ጉዟችን ( በየዓመቱ ጥቅምት 17 በቦር ተራራ ላይ የሚከወን የመድሃኒት ለቀማ) ሰኞ እና ማክሰኞ ይውላል:: ስለዚህ ከእኛ ጋር ለመጓዝ ከወዲሁ ፕሮግራማችሁን አስተካክሉ ⛰️ Bor Mountain • Camping • Mountain Adventure. Festival ለምዝገባ እና ተጨማሪ መረጃዎች በተከታዮቹ የስልክ አድራሻዎች ያገኙናል:: 📞 +251 942 545 470 📞 +251 929 176 542 @guzoadwahiking @guzoad

የመሠረተ ወገራም መንደር ያልተነካካ የተፈጥሮና የማህበረሰብ ተኮር ቱሪዝም ሀብት:: ከክትፎ ባሻገር ያለው የቱሪዝም ሀብት 😍 የዘንድሮውን የመስቀል በዓል ለማክበር መዳረሻችንን ወደ ጉራጌ ዞን ፣ መሠረተ ወገራም መንደር አድርገናል። ባለፉት ሁለት ዓመታት በዚህ ስፍራ ላይ የተራራ ላይ የእግር ጉዞ (hiking) በማድረግ ያሳለፍናቸው ጊዜያት የማይረሱ ስለነበሩ ፣ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ከአርብ - እሁድ ከአዲስ አበባ 235 ኪሎ ሜትሮችን (በሞጆ-ሀዋሳ highway መንገድ) ተጉዘን ወደዚህ ድንቅ ቦታ ዳግመኛ ለማቅናት ዝግጅታችንን አጠናቀናል። ይህንን ቦታ በተደጋጋሚ እንድንጎበኘው ያደረገን ዙሪያውን በከበቡት ግርማ ሞገስ ባላቸው ተራራዎች፣ ድንቅ ፏፏቴዎች፣ የበለጸገ ባህል እና ወሰን በሌለው የአካባቢው ህዝብ እንግዳ ተቀባይነት በመማረካችን ነው። መሠረተ ወገራም መንደር ለአካባቢ ተኮር (Ecotourism) እና በማህበረሰብ ላይ ለተመሰረተ ቱሪዝም (Community Based Tourism) ከፍተኛ አቅም ያለው ቦታ ነው። በተራሮች መካከል የእግር ጉዞ ለማድረግ እና የህብረተሰቡን እውነተኛ ባህልና የአኗኗር ዘይቤ ለመለማመድ (experience ለማድረግ) ለሚፈልጉ ተጓዦች ተመራጭ መዳረሻ ነው። ይህ ትልቅ እምቅ አቅም ወደ ተጨባጭ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ተቀይሮ የአካባቢው ማህበረሰብ በቀጥታ ተጠቃሚ እንዲሆን ግን በርካታ ስራዎች ሊሰሩ ይገባል፡: ይህንን ያልተነካካ ውበት ለዓለም ለማስተዋወቅና የመሠረተ ወገራም ማህበረሰብ ከቱሪዝም ዘላቂ ጥቅም እንዲያገኝ የበኩላችንን እንወጣ። ይህን የፎቶ ምስሎችን በማጋራት (Share በማድረግ) ቦታውን አብረን እናስተዋውቅ! @guzoadwahiking @guzoad #Ethiopia #guzoadwahiking #MesereteWegeram #Ecotourism #CommunityBasedTourism

photo content
+4

photo content
+9

ደረሰ : ደረሰ : ደረሰ ! የመስቀልን በዓል በጉራጌ ምድር ልናከብር የአንድ ሳምንት ዕድሜ ብቻ ቀርቶናል ! ከመስከረም 15-17 (አርብ-እሁድ) ዘንድሮ መሠረተ ወገራም ነን! ለማንኛውም አይነት ተጨማሪ መረጃዎች ይደውሉልን ! +251942545470 +251929176542 ወይን በ @guzoadwahiking @guzoad #ethiopia #guzoadwahiking #meseretewegeram #meskelcelebration #guarge

photo content
+4

photo content
+9

ዝናቡ አልፏል ፤ ተፈጥሮ በአረንጓዴ ውበቷ እየፈካች ነው! 💚🌼 አደይ አበባ በሜዳው ፣ ንጹህ ውሃ በፏፏቴው ፣ ጭጋግ በተራራው… ኢትዮጵያ በዚህ ወቅት ሌላ ውበት አላት። ይህ ከከተማ የመውጣት፣ የመጓዝ፣ የመሳቅ እና ከጓደኞች ጋር ትዝታ የምንፈጥርበት ወቅት ነው። ከ @guzoadwahiking ጋር በዚህ ወር ይጓዙ። አረንጓዴዋን ኢትዮጵያ፣ ንጹህ ፏፏቴዎቿን እና የተፈጥሮ ምስጢሮቿን አብረን እንፈልግ። 🥾 ወቅቱ አልፎ እንዳይቆጩ … ቦታዎን አሁኑኑ ያስይዙ! 👉ሁሌም እንደምንለው አስቀድሞ ቦታ በመያዝ የክፍያ ቅናሽ ዕድሉን ይጠቀሙ! Get 10% OFF when you book early! ለምዝገባ እና ተጨማሪ መረጃዎች በተከታዮቹ የስልክ አድራሻዎች ያግኙናል:: 📞 +251 942 545 470 📞 +251 929 176 542 መሠረተ-ወገራም መንደር (ጉራጌ) MESERETE WEGERAM VILLAGE, GURAGE ⛺ 3 Days / 2 Nights Camping 📅 መስከረም 15-17 / September 25–27 የዘንድሮው መስቀልን-በጉራጌ ጉዟችን በዚህ ስፍራ በልዩ ሁኔታ ተሰናድቷል:: Culture • Nature • Adventure ማሩ ፏፏቴ -አሌልቱ MARU WATERFALL / ALELTU 🥾 Day Hike 📅 መስከረም 24/ October 4 ከአለልቱ ከተማ በቅርብ ርቀት የሚገኘው ተወዳጁ የውሎ ገብ ጉዞ መዳረሻችን:: 💦 Waterfall • Nature • Adventure ሁልቆ ፏፏቴ እና ዋሻ /HULUKO WATERFALL & CAVE 🥾 Day Hike 📅 ጥቅምት 01/ October 11 በቅርቡ በጉዞ ዓድዋ ሃይኪንግ ፈር ቀዳጅነት የመጀመሪያ ዙር ጉዞ ተዘጋጅቶ በብዙዎች ዘንድ የተወደደው አዲሱ የሁልቆ ፏፏቴ እና ዋሻ :: ከ አዲስ አበባ 65 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ:: LAKE KILOLE (ኪሎሌ ሀይቅ) 🥾 Day Hike 📅 ጥቅምት08/ October 18 ከአዲስ አበባ 70 ኪሎ ሜትር ብቻ በመጓዝ : ከደብረዘይት ወይንም ቢሾፍቱ ከተማ 18 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምናገኘው አዲሱ የውሎ ገብ ጉዞ መዳረሻችን:: የም ቦር ተራራ /YEM — BOR MOUNTAIN ⛺ 1 Night Camping 📅 ጥቅምት 16-17/October 26–27 (Monday-teusday የዘንድሮ የሳሞኤታ በዓል ጉዟችን ( በየዓመቱ ጥቅምት 17 በቦር ተራራ ላይ የሚከወን የመድሃኒት ለቀማ) ሰኞ እና ማክሰኞ ይውላል:: ስለዚህ ከእኛ ጋር ለመጓዝ ከወዲሁ ፕሮግራማችሁን አስተካክሉ ! #ethiopia #landoforigins #guzoadwahiking #ethiopianhiking #ExploreEthiopia

photo content

የዓመቱ የመጀመሪያ ጉዟችን ከመስከረም 15 -17 ለሶስት ቀናት ወደ መሠረተ-ወገራም መንደር (ጉራጌ) ይካሄዳል። 🌼መስቀልን በጉራጌ🌼 📌የመሠረተ ወገራም መንደር በማዕከላዊ ኢትዮዽያ ክልል : ጉራ
የዓመቱ የመጀመሪያ ጉዟችን ከመስከረም 15 -17 ለሶስት ቀናት ወደ መሠረተ-ወገራም መንደር (ጉራጌ) ይካሄዳል። 🌼መስቀልን በጉራጌ🌼 📌የመሠረተ ወገራም መንደር በማዕከላዊ ኢትዮዽያ ክልል : ጉራጌ ዞን : የዘቢዳር ሰንሰለታማ ተራሮች ምስራቃዊ ክፍል ላይ ይገኛል:: የ 3 ቀናት ጉዞ / የ 2ቀናት አዳር ጉዞ 🏕️ የጉዞ መነሻ ቀን :-  መስከረም 15 2019 ዓ.ም (አርብ) ስለጉዞው በቂ መረጃ ለማግኘት በ+251942545470 , +251929176542 ይደውሉልን ወይንም በ @guzoadwahiking , @guzoad ያግኙን:: በድጋሚ መልካም አዲስ ዓመት! #ethiopia #guzoadwahiking #መስቀልን_በጉራጌ #MesereteWegeram #gurage

በአደይ አበባ ፍካት አዲስ ዘመንን ከተፈጥሮ ጋር እንቀበል! 🥾🌼 ያለፉትን የክረምት ወራት ከ @guzoadwahiking ቤተሰቦቻችን ጋር በዝናብ እና በጭጋግ ውስጥ እየተጓዝን ፣ ድንቅ ድንቅ ተፈጥሯዊ ቦታዎችን ፣ ተራሮቻችንን እና ፏፏቴዎች በደስታ ስናደንቅ አሳልፈናል። የክረምቱ ቅዝቃዜ ተገፎ ፣ ሰማዩ ሲጠራ እና ምድር በልምላሜ ስትሸፈን ግን ተፈጥሮ ለሌላ ድንቅ ምዕራፍ መዘጋጀቷን ያበስረናል። አሁን ደግሞ የእግር ጉዞ መንገዶቻችን በወርቃማው የአደይ አበባ መስክ በመተካት፣ አዲሱን ዓመታችንን በአበባማ መንገዶች መካከል ሆነን አንድ ብለን ለመጀመር ተዘጋጅተናል። በኢትዮጵያ የክረምቱ ማብቃት እና የአዲስ ዓመት መባቻ ለየት ያለ ውበት እና ትርጉም አለው። ከነሐሴ ማጠቃለያ ጀምሮ እስከ ጥቅምት ወር ምድር በቢጫው አደይ አበባ ትሸፈናለች ፤ የመስቀል ወፍ በሐር ላባዋ ደምቃ ትታያለች፤ የልጃገረዶች የአበባዮሽ ዜማ እና የወጣቶች የሆያ ሆዬ ድምፅ አየሩን ይሞላዋል። እንደ አሜሪካው የኳስ መጣል (Ball Drop)፣ እንደ ብራዚላውያን የምስር ተረት ወይም እንደ ዴንማርካውያን ሳህን የመስበር ባህል ሁሉ እኛ ኢትዮጵያውያን ከሌሎች ለየት ባለ መልኩ አዲስ ዘመንን የምንቀበለው በቄጠማ ልምላሜ፣ በአደይ አበባ ፍካት እና በተፈጥሮ አየር መታደስ ነው። ይህ የአደይ አበባ ፍካት እና የነጻነት አየር ለአጭር ጊዜ (ለጥቂት ወራት) ብቻ የሚቆይ የተፈጥሮ ስጦታ ነው። ተራሮቻችን ፣ ሜዳዎቻችን እና ሸንተረሮቻችን በወርቃማ ምንጣፍ በተሸፈኑበት በዚህ ድንቅ ወቅት፣ ከከተማው ውካታ ወጣ ብሎ አዲሱን ዓመት በመልካም ምኞት፣ በፍቅር እና በተፈጥሮ ውበት መጀመር ለሰውነታችንም ሆነ ለመንፈሳችን ትልቅ መታደስ ነው። ስለዚህም የዚህ አዲስ ዘመን መባቻ አካል እንድትሆኑ እና በመጪዎቹ የአደይ አበባ የሃይኪንግ ጉዞዎቻችን አብራችሁን እንድትጓዙ ጥሪያችንን እናቀርባለን! አዲሱን ዓመት በተፈጥሮ መካከል አብረን እንቀበል። የዓመቱ የመጀመሪያ ጉዟችን ከመስከረም 15-17 (አርብ:ቅዳሜ:እሁድ) ወደ ተናፋቂው መሰረተ ወገራም መንደር (ጉራጌ) ይካሄዳል :: የ 3 ቀናት/2 ምሽቶች ጉዞ ይህ ስፍራ ከጥቂት ወራት በፊት ተጉዘንበት ብዙዎቻቹ ከልብ እንደወደዳችሁት ተረድተናል:: እንዲሁም በበርካታ የጉዞ ቤተሰቦቻችን ጥያቄ መሰረት የዘንድሮውን የመስቀል በዓል እዚህ ስፍራ ላይ ለማክበር ዳግመኛ ልናቀና ነው:: ማነው ለዚህ አጓጊ ጉዞ ከወዲሁ ዝግጁ የሆነው? ስለጉዞው በቂ መረጃ ለማግኘት በ+251942545470 , +251929176542 ይደውሉልን እንዲሁም በውስጥ መስመር (DM) ያድርጉልን ! @guzoad @guzoadwahiking በድጋሚ መልካም አዲስ ዓመት! ⁠ #AdeyAbeba #NewYearHike #GuzoAdwahiking #ethiopia #መስቀልን_በጉራጌ

photo content
+4

photo content
+9

እንኳን አደረሳችሁ!
እንኳን አደረሳችሁ!

ስለነበረን ድንቅ ዓመት አሁንም ደግመን እናመሰግናለን! 🙏🙏 ዻጉሜ 01 2018 ዓ.ም የዓመቱ ማሳረጊያ ጉዟችን ወደ ሁልቆ ዋሻና ፏፏቴ (Huluko Cave and Waterfall) ያደረግነው ጉዞ በከፊል ይህን ይመስል ነበር:: አዲሱ ዓመት የሰላም ፣ የጤናና ታላላቅ አዳዲስ የጉዞ መዳረሻዎችን በጋራ የምንረግጥበት ይሁንልን! @guzoadwahiking #ethiopia #landoforigins #guzoadwahiking #hulukowaterfallandcave #habeshatravel

photo content
+4

photo content
+9