5 373
مشترکین
+424 ساعت
+47 روز
+530 روز
آرشیو پست ها
5 373
ለዓመቱ የመጨረሻ ጉዟችን ዝግጁ ናችሁ?
የበያዝነው ሳምንት መጨረሻ እሁድ (ዻጉሜ 01) ይካሄዳል::
የክረምቱ ዝናብ መጠናቀቂያ ላይ ደርሰናል። ሁለት ሳምንት ብቻ ቀርቶናል::
የዚህን ዓመት ምርጥ የጉዞ ትዝታዎቻችንን በታላቅ/አዲስ የውሎ ገብ ጉዞ (day hike) ልንዘጋው አቅደናል!
👉ሁሌም እንደምንለው
አስቀድሞ ቦታ በመያዝ የክፍያ ቅናሽ ዕድሉን ይጠቀሙ!
የጉዞ ምዝገባው በማንኛውም ሰዓት በቂ ተጓዦች ክፍያ ፈፅመው ከተገኘ ወድያሁኑ ሊዘጋ ይችላል:: ‼️
ለጉዞ ምዝገባ እና ተጨማሪ መረጃዎች አሁኑኑ
በ +251 942545470, +251929176542
ይደውሉልን:: ወይንም በ @guzoadwahiking , @guzoad አጭር የፅሁፍ መልዕክት ይላኩልን::
5 373
ዛሬ (ነሐሴ 24 2018 ዓ.ም) በጉለሌ እፅዋት ማዕከል ከ Plogging-Ethiopiaፕሎጊንግ ኢትዮዽያ ጋር በመተባበር ያደረግነው የ ሃይኪንግ እና ፕሎጊንግ የጥምረት መርሃ ግብር በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።
በማዕከሉ በነበረን ቆይታ በተፈጥሮ ውበት እየተደሰትን ፣ በቸልተኛ ሰዎች የተጣሉ የፕላስቲክ ኮዳዎችን እና ሌሎች ቆሻሻዎችን ያፀዳንበትና በተጨማሪም የወደፊቱን አረንጓዴ ተስፋ (የዛፍ ችግኞች) የተከልንበት ደስ የሚል ውሎ ነበር።
በዛሬው ዕለት
👥 26 በጎ ፈቃደኞች ተገኝተዋል
🚶♂️ 11.3 ኪሎ ሜትር የእግር ጉዞ ተደረገ (Hiking)
🗑️ 33 ኪሎ ግራም የሚመዝን የፕላስቲክ ጠርሙሶች ተሰብስቧል (Plogging)
🌳 ከ50 በላይ የተመረጡ ሀገር በቀል ችግኞች ተተክለዋል (Endigenous)
በጉዟችን ወቅት በርካታ ሰዎች የፕላስቲክ ጠርሙሶችን ለዓይን በሚያሳሱ ውብ ቦታዎች ላይ በዘፈቀደ ጥለው ማየታችን እንደሁልጊዜ ያሳዘነን ፤ያበሳጨናልም ቢሆንም። ነገር ግን አሁንም ተስፋ አንቆርጥም!
ይበልጥ ይህን እና መሰል ውብ ተፈጥሯዊ ቦታዎችን ለማጽዳትና ተፈጥሯዊ ውበቱን ለመጠበቅ ወደዚሁ እና መሰል ቦታዎች ደጋግመን ከመመላለስ በፍጹም ወደ ኋላ አንልም።
በሌላ በኩል የጉለሌ እፅዋት ማዕከል የአካባቢውን ንጽህና ለመጠበቅ በርካታ የቆሻሻ መጣያ ቢኖች (Garbage Bins) በአዳዲስ ቦታዎች ላይ ማዘጋጀቱን በማየታችን ትልቅ ደስታ ተሰምቶናል።
ችግኝ የመትከሉን ሂደት ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ሙሉ በሙሉ በማመቻቸትና በማስተባበር ላደረጉልንም ታላቅ ድጋፍ ለጉለሌ እፅዋት ማዕከል ሰራተኞችና አመራሮች ከልብ የመነጨ ምስጋናችንን እናቀርባለን።
በመጨረሻም ዛሬ ተገኝታችሁ ጉልበታችሁን፣ ጊዜያችሁንና እውቀታችሁን ለተፈጥሮ የለገሳችሁ 26ቱንም በጎ ፈቃደኞች አጅግ አድርገን እንመሰግናለን!
በጉዞ ዓድዋ ሃይኪንግ መደበኛ ሳምንታዊ ጉዞዎች ደግመን እንደምንገናኝ ተስፋ እናደርጋለን።
"አካባቢያችንን እንጠብቅ፤ ተፈጥሮን እንከባከብ"
➡️የጉዞ ዓድዋ ሃይኪንግ የዓመቱ የመጨረሻ የውሎ ገብ ጉዞ ጳጉሜ 01 2018 ዓ.ም/sept 06 2026 ይካሄዳል::
ጉዞ ወደ ሁልቆ ፏፏቴ እና ዋሻ ( ከ አዲስ አበባ 65 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ)
ለጉዞ ምዝገባ እና ተጨማሪ መረጃዎች
በ +251942545470, +251929176542
ይደውሉልን:: ወይንም አጭር የፅሁፍ መልዕክት ይላኩልን:: @guzoAD @guzoadwahiking
#ethiopia #ploggingethiopia #plogging #hiking #guzoadwahiking
5 373
ዻጉሜን 01 2018 ዓ.ም (እሁድ) ለምናካሂደው የዓመቱ የመጨረሻ የውሎ ገብ ጉዟችን ምዝገባ ተጀምሯል::
👉ሁሌም እንደምንለው
አስቀድሞ ቦታ በመያዝ የክፍያ ቅናሽ ዕድሉን ይጠቀሙ!
የጉዞ ምዝገባው በማንኛውም ሰዓት በቂ ተጓዦች ክፍያ ፈፅመው ከተገኘ ወድያሁኑ ሊዘጋ ይችላል:: ‼️
ለጉዞ ምዝገባ እና ተጨማሪ መረጃዎች
በ +251 942545470, +251929176542
ይደውሉልን::
ወይንም በ @guzoadwahiking , @guzoad አጭር የፅሁፍ መልዕክት ይላኩልን::
መልካም የዕረፍት ቀናት እንዲሆንላቹሁ ተመኘን!
@guzoadwahiking
5 373
ይህ አጆራ ፣ እንሳሮ ፣ ደርባ ወይንም ማሩ ፏፏቴ አይደለም::
ይህ ከአዲስ አበባ 65 ኪሎ ሜትር ብቻ በመኪና ተጉዘው የተደበቀውን ድንቅ ተፈጥሯዊ ውበት የሚያገኙት "የሁልቆ ዋሻ እና ፏፏቴ" ነው::
የበኬን ከተማ አቋርጦ የሚመጣው ባለ ግርማ ሞገሱ ገርማሞ ወንዝ በታሪካዊው ሁልቆ ዋሻ አናት ላይ ተፈጥሮአዊ ውበቱን ጠብቆ ሲፈስ የሚፈጥረው አካባቢን የሚያነቃቃ ረጅሙ ፏፏቴ ይህን ይመስላል::
የክረምቱ ጭጋጋማ እና ንጹህ አየር ደግሞ እዚህ አካባቢ ላይ ይለያል:: ይህ ስፍራ የጥንታዊው የገርማሞ አቦ ቤተክርስቲያን መገኛም ጭምር ነው::
የጉዞ ዓድዋ ሃይኪንግ የዓመቱ የመጨረሻ የውሎ ገብ ጉዞ ጥሪ ይህን ይመስላል::
➡️ ይህ የዓመቱ የመጨረሻ ጉዞ በፍፁም እንዳያመልጣችሁ!
ጉዟችን ከጀማሪ ተጓዦች እስከ ልምድ ላላቸው እንዲሆን ተደርጎ ተሰናድቷል::
ቀን፦ ጳጉሜን 01 2018 ዓ.ም/sept 06
ለጉዞ ምዝገባ እና ተጨማሪ መረጃዎች ፦
+251942545470, +251929176542
ይደውሉልን:: ወይንም አጭር የፅሁፍ መልዕክት ይላኩልን:: @guzoadwahiking @guzoad
👉ሁሌም እንደምንለው
አስቀድሞ ቦታ በመያዝ የክፍያ ቅናሽ ዕድሉን ይጠቀሙ!
የጉዞ ምዝገባው በማንኛውም ሰዓት በቂ ተጓዦች ክፍያ ፈፅመው ከተገኘ ወድያውኑ ሊዘጋ ይችላል:: ‼️
#ethiopia #landoforigins #guzoadwahiking #hulukocaveandwaterfall #Hiking
5 373
2 ቀን ብቻ ቀርቶናል!
የፊታችን እሁድ! (ነሀሴ 24)
ከልጆችዎ ጋር ይምጡ!
ሃይኪንግና ፕሎጊንግ የሚጣመሩበትን የዓመቱ የመጨረሻ ፕሮግራም በጉለሌ እፅዋት ማዕከል ከ Plogging-Ethiopia - ፕሎጊንግ ኢትዮጵያ ጋር በትብብር አዘጋጅተናል።
ዉቡ የእፅዋት ማዕከል በዚህ ወቅት በክረምቱ በአረንጓዴ እና እርጥበታማ ውበት ይበልጥ የሚዋብበት ነው። ለነሀሴ 24 (የፊታችን እሁድ) ቀጠሯችሁን ከእኛ ጋር አድርጉ 🙏
መገናኛ ቦታ
በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል በር ላይ ከጠዋቱ 1:30።
Gullele botanic Garden Main Gate
https://maps.app.goo.gl/v6xRhyLEKuzjYdgb9
ማስታወሻ
📍ጉዞው የተዘጋጀው በነፃ ሲሆን፣ ከጉዞ በፊት የሚጠየቅ ምንም አይነት ቅድመ ክፍያ አይኖርም። ሆኖም ግን በዕለቱ የፓርክ መግቢያ እና የአስጎብኚ ክፍያዎችን ለመሸፈን በአንድ ተጓዥ ከአንድ መቶ ብር ያልበለጠ መዋጮ ብቻ ይጠየቃል ።
📍 ተጓዦች ለግማሽ ቀን ውሏቸው የሚሆን ውሃ በኮዳ እንዲሁም ቀለል ያለ እና ሃይል ሰጪ ምግብ (snacks) በትንሿ የጉዞ ቦርሳቸው እንዲይዙ እንመክራለን። እንዲሁም ለእግር ጉዞ ምቹ የሆነ ጫማ ፣ የማያንሸራትት ( ከዚህ ቀደም በእግር ጉዞ የተሞከረ ቢሆን ይመረጣል )
👉 ጉዟችን በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ደቡባዊ በር ጀምረን ከ -10 ኪሎ ሜትር የሚጠጋ የግማሽ ቀን ሃይኪንግ እና ፕሎጊንግ በኋላ ጉዟችንን የምናጠናቅቅ ይሆናል።
👉 ይህ ጉዞ ሁሉም ተጓዥ የራሱን የትራንስፖርት አማራጭ በመጠቀም የሚገናኝበት ልዩ ፕሮግራም ነው::
📞 ለተጨማሪ መረጃዎች
+251 91 320 9880 , +251942545470 ይደውሉ!
#ethiopia #plasticfree #plogging #ploggingethiopia
#guzoadwahiking #gullelebotanicgarden
5 373
Plogging Ethiopia እና Guzo adwa hiking በጋራ የሚያዘጋጁት የ hiking እና plogging እንቅስቃሴ በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል (Gullele Botanical Garden) የፊታችን እሁድ ይደረጋል::
📅 ቀን፡ ነሀሴ 24 / እሁድ
⏰ የመገናኛ ሰዓት፡ ከጠዋቱ 1:30
📍 ቦታ፡ ጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል
Gullele botanic Garden Main Gate
https://maps.app.goo.gl/v6xRhyLEKuzjYdgb9
ማስታወሻ
📍ጉዞው የተዘጋጀው በነፃ ሲሆን፣ ከጉዞ በፊት የሚጠየቅ ምንም አይነት ቅድመ ክፍያ አይኖርም። ሆኖም ግን በዕለቱ የፓርክ መግቢያ እና የአስጎብኚ ክፍያዎችን ለመሸፈን በአንድ ተጓዥ ከአንድ መቶ ብር ያልበለጠ መዋጮ ብቻ ይጠየቃል ።
📍 ተጓዦች ለግማሽ ቀን ውሏቸው የሚሆን ውሃ በኮዳ እንዲሁም ቀለል ያለ እና ሃይል ሰጪ ምግብ (snacks) በትንሿ የጉዞ ቦርሳቸው እንዲይዙ እንመክራለን። እንዲሁም ለእግር ጉዞ ምቹ የሆነ ጫማ ፣ የማያንሸራትት ( ከዚህ ቀደም በእግር ጉዞ የተሞከረ ቢሆን ይመረጣል ) በተጨማሪም የዝናብ ልብስ::
👉 ጉዟችን በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ደቡባዊ በር በመጀመር ከ 8-12 ኪሎ ሜትር የሚጠጋ የግማሽ ቀን ሃይኪንግ እና ፕሎጊንግ በኋላ ጉዟችንን የምናጠናቅቅ ይሆናል።
👉 ይህ ጉዞ ሁሉም ተጓዥ የራሱን የትራንስፖርት አማራጭ በመጠቀም የሚገናኝበት ልዩ ፕሮግራም ነው::
👉 ፕሎጊንግ የእግር ጉዞ እያደረጉ ወይም ዱብዱብ እያሉ (jogging ) እግረ መንገድ ለአካባቢ ብክለት የሆኑ ቆሻሻዎችን የማንሳት አስደሳች ልምምድ ነው።
📞 ስለ ጉዞው ተጨማሪ መረጃዎች ለማግኘት በ +251 91 320 9880 , +251942545470 ይደውሉ! ወይንም በ @guzoadwahiking @guzoad
5 373
እሁዳችን በአረንጓዴው ሀይቅ!
ነሀሴ 17 201 8 ዓ.ም
ይህ ስፍራ በተለምዶ አረንጓዴው ሀይቅ ተብሎ ይጠራ እንጂ የአካባቢው ማህበረሰብ ሆራ አዶ በተጨማሪም ሃሮ ማጋሪሳ ብሎ ይጠራዋል።
ከቢሾፍቱ /ደብረዘይት ከተማ በቅርብ ርቀት (9 ኪሎ ሜትር ላይ ) የሚገኝ እጅግ ውብ ስፍራ::
ሆራ አዶ : ቢሾፍቱ/ደብረዘይት ውስጥ እና ዙሪያ ገባው ላይ ከሚገኙ ከዘመናት በፊት ተከታታይነት በነበረው የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ምክንያት ከተፈጠሩ በቁጥር ከ 7-15 የሚደርሱ ሀይቆች መሀከል የሚገኝ ሲሆን ዙሪያውም በተራራ የተከበበ እጅግ አስደናቂ እና ልዩ ተፈጥሮን የታደለ ሀይቅ ነው።
በዚህ ጉዞ ለተሳተፋችሁ የጉዞ ቤተሰቦቻችን ሁሉ ዛሬም ከልብ ለማመስገን እንወዳለን። 🙏🙏
👉የጉዞ ዓድዋ ሃይኪንግ ቡድን የክረምቱ የውሎ ገብ ጉዞዎች አሁንም ይቀጥላሉ::
ለጉዞ ምዝገባ እና ማንኛውም አይነት መረጃዎችን ለማግኘት በ +251942545470 , +251929176542 ይደውሉልን ! ወይንም በ @guzoadwahiking @guzoad
መልካም ቀን ይሁንልን!
#ethiopia #LandOfOrigins #greenlake #ethiopianhiking #bishoftu
5 373
የሳምንቱ መጨረሻ ተጠባቂ ጉዞ ሊካሄድ 2 ቀናት እና 5 ቦታዎች ብቻ ቀርተውናል !
ነሀሴ (17 እሁድ) 🏔️
ጉዞ ወደ Green Lake
👉 ለተጨማሪ መረጃዎች ፈጥነው በተከታዮቹ አድራሻዎች ያግኙን 📞@guzoadwahiking @guzoad +251942545470
መልካም ቀን ተመኘን!
5 373
Green Lake (አረንጓዴው ሀይቅ ) የ @guzoadwahiking ቀጣይ የውሎ ገብ ጉዞ መዳረሻ:: ነሀሴ 17 (እሁድ)
ለተጨማሪ መረጃዎች በ +251942545470 +251929176542 ያግኙን :: @guzoad
#ethiopia #guzoadwahiking #greenlake #bishoftu
5 373
የዚህ ሳምንት የጉዞ መዳረሻችን Green lake /አረንጓዴው ሀይቅ ይባላል።
ነሀሴ 17/August 23 (እሁድ)
Green lake/ አረንጓዴው ሀይቅ
ከቢሾፍቱ /ደብረዘይት ከተማ በቅርብ ርቀት (9 ኪሎ ሜትር) የሚገኝ ሌላኛው አስደማሚ የውሎ ገብ ጉዞ መዳረሻችን ነው።
ይህ ሀይቅ ቢሾፍቱ/ደብረዘይት ውስጥ እና ዙሪያ ገባው ላይ ከሚገኙ ከዘመናት በፊት ተከታታይነት በነበረው የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ምክንያት ከተፈጠሩ በቁጥር ከ 7-15 የሚደርሱ ሀይቆች መሀከል የሚገኝ ሲሆን ዙሪያውም በተራራ የተከበበ አስደናቂ እና ልዩ ተፈጥሮን የታደለ ሀይቅ ነው።
የጉዞው ዓይነት :- ከጀማሪ ተጓዦች እስከ ከፍተኛ ልምድ ተጓዦች መሳተፍ የሚችሉበት ነው።
✅በዚህ የጉዞ ፕሮግራም ላይ
🔹የእግር ጉዞ በተራሮች እና በሀይቁ ዙሪያ ይደረጋል ( ከ8-13 ኪሎ ሜትር የሚደርስ )
🔹በአረንጓዴ ሀይቅ ዳርቻ ሰፊ የመዝናኛ ጊዜ ይኖራል
🔹የሻይ / ቡና ዕረፍት በደብረ ዘይት / ቢሾፍቱ ከተማ ይኖራል::
በዚህ አስደሳች ጉዞ ከእኛ ጋር መጓዝ ለሚፈልግ ማንኛውም ሰው ዕድሉ ክፍት ሲሆን ውስን ቦታዎች ብቻ ስለቀሩን ፈጥነው ቦታዎን ያስይዙ !!
የጉዞ ፓኬጁ - ከአዲስ አበባ ከተማ ደርሶ መልስ የ ትራንስፖርት ወጪ ፣ ቀለል ያለ ቁርስ እና ሻይ ቡና ፣ ምሳ ፣ ውሃ በተጨማሪም የ መግቢያ እና የጋይድ ክፍያን ጨምሮ ።
👉ሁሌም እንደምንለው
አስቀድሞ ቦታ በመያዝ የክፍያ ቅናሽ ዕድሉን ይጠቀሙ!
የጉዞ ምዝገባው በማንኛውም ሰዓት በቂ ተጓዦች ክፍያ ፈፅመው ከተገኘ ወድያሁኑ ሊዘጋ ይችላል:: ‼️
ለምዝገባ እና ተጨማሪ መረጃዎች በ +251942545470 , +251929176542 ወይንም በውስጥ መስመር አጭር የፅሁፍ መልዕክት ይላኩልን:: @guzoadwahiking @guzoad
መልካም ጊዜ !
#ethiopia #guzoadwahiking #ethiopianhiking #greenlake
5 373
ባሳለፍነው እሁድ (ነሀሴ 10 2018) በማሩ ፏፏቴ (አለልቱ) ድንቅ ቀን አሳልፈን ተመለስን::
የጉዞ ዓድዋ ሃይኪንግ ተከታታይ የክረምት ጉዞዎች አሁንም እንደቀጠሉ ናቸው:: ቀጣይ የውሎ ገብ ጉዞ መዳረሻችን አረንጓዴው ሀይቅ ነው
በያዝነው ሳምንት መጨረሻ እሁድ ነሀሴ 17
ከቢሾፍቱ /ደብረዘይት ከተማ በቅርብ ርቀት (9 ኪሎ ሜትር) የሚገኝ ሌላኛው አስደማሚ የአንድ ቀን ጉዞ መዳረሻችን ነው።
ይህ ሀይቅ ቢሾፍቱ/ደብረዘይት ውስጥ እና ዙሪያ ገባው ላይ ከሚገኙ ከዘመናት በፊት ተከታታይነት በነበረው የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ምክንያት ከተፈጠሩ በቁጥር ከ 7-15 የሚደርሱ ሀይቆች መሀከል የሚገኝ ሲሆን ዙሪያውም በተራራ የተከበበ አስደናቂ እና ልዩ ተፈጥሮን የታደለ ሀይቅ ነው።
የጉዞው ዓይነት :- ከጀማሪ ተጓዦች እስከ ከፍተኛ ልምድ ተጓዦች መሳተፍ የሚችሉበት ነው።
👉ሁሌም እንደምንለው
አስቀድሞ ቦታ በመያዝ የክፍያ ቅናሽ ዕድሉን ይጠቀሙ!
የጉዞ ምዝገባው በማንኛውም ሰዓት በቂ ተጓዦች ክፍያ ፈፅመው ከተገኘ ወድያሁኑ ሊዘጋ ይችላል::
ለምዝገባ እና ተጨማሪ መረጃዎች በ +251942545470 , +251929176542 ወይንም ወይንም በውስጥ መስመር @guzoadwahiking @guzoad አጭር የፅሁፍ መልዕክት ይላኩልን::
መልካም ቀን!
#ethiopia #guzoadwahiking #hikingadventures #ethiopianhiking
