ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

Guzo Adwa updates

Guzo Adwa updates

前往频道在 Telegram
5 337
订阅者
-424 小时
-97 天
-1430 天
帖子存档
የጉዞ ዓድዋ ሃይኪንግ ያለፈው ዓመት ( 2018 ዓ.ም ) የዓመቱ ምርጥ ተጓዦች (Hikers of the Year) ሆነው ለተመረጡት ቢንያም እና እየሩሳሌም ትልቅ ደስታችንን እንገልጻለን! ( ለጥቂት ሳምንታት የዘገየ ፖስት 🙂) በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ! 🏆 ጉዞ ዓድዋ ሃይኪንግ ላለፉት 6 ተከታታይ ዓመታት የዓመቱን ምርጥ ተጓዦች ሲሸልም የቆየ ሲሆን፣ ዘንድሮም ለሁለቱ አሸናፊዎች የ 120,000 የኢትዮጵያ ብር የሽልማት ፓኬጅ በጋራ ተበርክቶላቸዋል! 💰🎁 ሽልማቱ ባለፈው ዓመት ከእኛ ጋር ባደረጉት በርካታ የጉዞ ብዛት እና በሌሎች ተጨማሪ የኮሚቴ መመዘኛ መስፈርቶች የተሰጠ ነው። ሁሌም ከእኛ ጋር ስለምትጓዙ እጅግ ደስ ይለናል! 👉 2019 የእርስዎ ተራ ሊሆን ይችላል! ዛሬውኑ ከጉዞ ዓድዋ ሃይኪንግ ጋር መጓዝ ይጀምሩ! 🥾 #ethiopia #landoforigins #guzoadwahiking #hik

photo content
+3

በ @guzoadwahiking የአንድ ወር የእግር ጉዞ (Hiking) መርሃ ግብር መሠረት : ላለፉት አራት ተከታታይ ሳምንታት ፍጹም ደስ የሚልና ስኬታማ ጊዜያትን አብረን አሳልፈናል። ከአዲስ ዓመት መስቀልን በጉራጌ የመጀመሪያ ጉዟችን ጀምሮ የእያንዳንዱ ሳምንት የእረፍት ቀናት ድንቅ ትዝታን ጥሎብን አልፏል። የመስከረም ተፈጥሯዊ ውበት አዲስ ዓመትን በአዲስ መንፈስና በሙሉ ሀይል እንድንጀምር አድርጎናል። ለመሆኑ ያለፈው የአንድ ወር የጉዞ ዕቅዳችን ለእርስዎ እንዴት ነበር? ከሄድንባቸው ቦታዎች ይበልጥ የወደዱት የትኛውን ነው? ያመለጣችሁና ያልተካፈላችሁበት ጉዞስ የትኛው ነው? በቅርቡ በድጋሚ ለመድገም የምትመኙት የትኛውን ነው? አስተያየታችሁን ኮመንት ላይ አካፍሉን! አሁን ደግሞ የአንድ ወር መርሃ ግብራችን ማጠቃለያ የሆነውን የመጨረሻውን 5ኛ ሳምንት ጉዞ ልንጀምር ነው! “ጉዞ ወደ የም ብሔረሰብ : ቦር ተራራ” ጥቅምት 16-17 ( ሰኞ እና ማክሰኞ) ያሉን ቦታዎች ውስን ስለሆኑ አሁኑኑ ቦታዎን ይያዙ/ይመዝገቡ። ለሚቀጥለው ወር የሚሆን አዲስና አስደሳች የጉዞ መርሃ ግብር እያዘጋጀን ስለሆነ በጉጉት ጠብቁን! 📲 ለቀጣዩ ጉዞ ቦታ ለማስያዝ እንዲሁም ለተጨማሪ የጉዞ መረጃዎች በ+251942545470 , +251929176542 ያገኙናል! @guzoad @guzoadwahiking

photo content
+4

ምዝገባው ተጀምሯል!! Guzo Adwa Hiking ጥቅምት 16-17 - የሳሞ ኤታ በዓል - በየም ምድር ፤ ቦር ተራራ ላይ 🏔️ ደረሰ ! ደረሰ! ደረሰ! ከእኛ ጋር ለመጓዝ ዝግጅ ናችሁ? ጥቅምት 16 እና 17 (ሰኞ እና ማክሰኞ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኘው የየም ብሔረሰብ ለጥቅምት ወር ልዩ ሥፍራን ይሰጣል፡፡ ማህበረሰቡ የጥቅምት ወር አጋማሽ እንዳለፈ ቦር ተራራ ላይ፣ የባህላዊ መድኃኒት ለቀማን ከልሂቅ እስከ ደቂቅ የሚሳተፍበትን ኩነት ያደርጋል ፡፡ ‹‹”ሳሞ ኤታ”›› ”ሳሞ ኤታ” በየዓመቱ ጥቅምት 17 ቀን “ቦር”በሚባል ተራራ ላይ የባህላዊ መድኃኒቶች ለቀማ ይካሄዳል፡፡ ”ሳሞ ኤታ” ፍቺው የከረመ መድኃኒት ማለት ነው:: በቦር ተራራ የሚገኙ ዕፅዋት ለሰው ብቻ ሳይሆኑ ለእንሰሳትም እንደሚያገለግሉ በኅብረተሰቡ ይታመናል፡፡ የዓመት የመድኃኒት አስቤዛ ጥቅምት 17 ይሰበሰባል፡፡ “የም” በዕፅዋት ጥበብ አስቀድሞ በሽታን ይከላከላል፡፡ ቀጥሎም ሕመምን ያስወግዳል፡፡ ፈውስን ከምድር ገጸ በረከት የሚያገኝ ጥበበኛ ሕዝብ ነው፡: በዚህ ዕለት የአካባቢው ነዋሪዎች በተራራው ላይ ካሉ በርካታ የእፅዋት አይነቶች ቅጠላቸውን፣ ስሮቻቸውን እና ቅርፊታቸውን በመሰብሰብ ቤታቸው ወስደው በአግባቡ በማዘጋጀት ለሰውና ለእንስሳት የሚሆን መድሃኒትነት ይቀምሙበታል፡፡ እኛ አስደናቂውን የየም ህዝብ ባህል ፣ ታሪክ ፣ ቋንቋ እና ቅርስ እንዲሁም በአካባቢው የሚገኙ ተፈጥሯዊ የቱሪዝም መስህቦችን ዘንድሮም ለመጎብኘት ተዘጋጅተናል! ለምዝገባና ተጨማሪ መረጃዎች በተከታዮቹ አድራሻዎች ብቻ ያግኙን! @guzoad @guzoadwahiking +251942545470 , +251929176542

photo content
+9

ትናንት (ጥቅምት 08 2019 ዓ.ም) ከ @guzoadwahiking ቤተሰቦች ጋር ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት በምትገኘው የደብረዘይት /ቢሾፍቱ ኪሎሌ ሐይቅ (Lake Kilole) ያደረግነው የእግር ጉዞ በታላቅ ስኬት አጠናቀናል። በጉዟችን ወቅት በሐይቁ ዙሪያ 10 ኪሎ ሜትር ያህል በእግር በመጓዝ፣ ከባህር ጠለል በላይ 2,100 ሜትር ከፍታ ያለውን የአካባቢውን ከፍተኛ ተራራ ወጥተናል። የሂዲ ተራራ 🏔️ ከተራራው ጫፍ የሚታየው ውብ ተፈጥሯዊ እይታ እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች ያሳዩን ሞቅ ያለ እንግዳ ተቀባይነት ጉዟችንን ልዩ ያደረገው ሲሆን ፤ ጠዋት ላይ ከመደበኛ የቡና እረፍታችን በኃላ ውብ ቀናችንን የሂዲን ተራራ በመውጣት ጀምረናል። በሀይቁ ዙሪያ በነበረን የግማሽ ቀን ውሎ ከዚህ ቀደም የኦሮሞ ህዝብ የኢሬቻ የምስጋና በዓል መጀመሪያ ይከበርበት የነበረው በዚሁ በኪሎሌ ሐይቅ እንደነበርና በኋላም ቦታው ከቢሾፍቱ ከተማ ማዕከል ወጣ ብሎ ስለሚገኝ ወደ ሆራ አርሰዲ እንደተዛወረ ተረድተናል። ትናንት ከ25-30 ከሚሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች ጋር በመሆን ጥንታዊውንና የመጀመሪያውን የኢሬቻ አከባበር በቅርብ ርቀት መታደማችን ለተጓዥ ቤተሰቦቻችን ትልቅ ባህላዊና ታሪካዊ እውቀትን ጨምሮልናል። በኪሎሌ ሀይቅ የነበረንን የግማሽ ቀን ቆይታ ካጠናቀቅን በኋላ ፤ እንዲሁም ከምሳ ሰዓት እረፍት በኋላ በከተማው አቅራቢያ በሚገኘው ታዋቂው ሆራ አርሰዲ ሐይቅ ዙሪያ (Hora Arsedi) ተጨማሪ 5 ኪሎ ሜትር በእግር በመጓዝ ፤ አዳዲሶቹን የእግር ጉዞ መንገዶችና ማራኪ የተፈጥሮ ድባብ ተደስተን ቀናችንን አጠናቅቀናል። ይህ ተፈጥሮን፣ ስፖርትን እና ባህልን ያጣመረ ጉዞ ለሁላችንም የማይረሳ ትዝታን ጥሎልን አልፏል :: Guzo Adwa hiking በተከታታይ ጊዜያት በሚዘጋጀው የHiking እና camping ፕሮግራሞቻችን ላይ እየተቀላቀላችሁ ተፈጥሮንና ባህልን አብራችሁን እንድታከብሩ ጥሪያችንን እናቀርባለን። ቀጣዩ ጉዞ በቀጣዩ ሳምንት ሰኞ እና ማክሰኞ (ጥቅምት 16-17) ቀን ላይ ይካሄዳል :: ጉዞ ወደ የም ብሔረሰብ (ቦር ተራራ ) በየዓመቱ ጥቅምት 17 የሚከበረውን የሳሞ ኤታ በዓልን ለመታደም ወደ ማዕከላዊ ኢትዮዽያ ክልል የም ዞን ቦር ተራራ (የፈውስ ተራራ) እናንተን ይዘን ዘንድሮም ልናቀና ነው :: ለምዝገባ እና ተጨማሪ መረጃዎች በተከታዮቹ የስልክ አድራሻዎች ያግኙናል:: 📞 +251 942 545 470 📞 +251 929 176 542 @guzoad @guzoadwahiking #ethiopia #guzoadwahiking #lakekilole #borMountain #yem

photo content
+9

photo content
+9

photo content
+9

Hora Arsadee / ሆራ ሀይቅ ሌላኛው የቀጣዩ ጉዞ (ጥቅምት 08 2019 ዓ.ም) ተጨማሪ መዳረሻችን:: ደብረዘይት/ቢሾፍቱ ከተማ ከያዘቻቸው ሰባት የካልዴራ/የእሳተ ገሞራ ሐይቆች መካከል አንዱ የሆነው ሆራ አርሰዲ፣ ከባህር ጠለል በላይ በ1,920 ሜትር ገደማ ከፍታ ላይ የሚገኝ ሲሆን እስከ 37 ሜትር የሚደርስ ጥልቀት አለው። ሐይቁ በዙሪያው ባሉ ግዙፍ የግራርና የፅድ ዛፎች የተከበበ በመሆኑ ለአካባቢው የተረጋጋና ፍፁም ማራኪ የተፈጥሮ ድባብን ሰጥቶታል። በቅርብ ጊዜ በተገነቡት አዳዲስ የእግር ጉዞ መንገዶች (New Walking Trails) አማካኝነት ተጓዦች ሐይቁን በምቾትና በደህንነት እየዞሩ እንዲጎበኙ ያስችላል። ተጓዦች እንደምርጫቸው በሐይቁ ላይ በጀልባ/ታንኳ እየተንሳፈፉ የተፈጥሮን ነፋስ የመቀበልና የሐይቁን ውብ ማዕዘናት የመቃኘት ዕድል ያገኛሉ። ይህ ውብ ስፍራ በቀን ውስጥ ከሚኖረው ማራኪ ገጽታ በተጨማሪ፣ በምሽት ሰማይ ስር ፈጽሞ የሚገርምና አስደናቂ እይታን አለው ። ከሁሉ በላይ ይህ ሐይቀ የኦሮሞ ህዝብ ዓመታዊ የኢሬቻ (የምስጋና በዓል ) የሚከበርበት ታላቅ ስፍራ ነው። Guzo Adwa Hiking Tours በመጪው እሁድ ከኪሎሌ ሐይቅና ከሂዲ ተራራ ጉዞ እንዲሁም ከምሳ ሰዓት እረፍት በኋላ ይህ ስፍራ ላይ የመንሸራሸር እቅድ ይዟል:: የእናንተስ የመጪዎቹ የእረፍት ቀናት (ቅዳሜ እና እሁድ) የጉዞ ዕቅድ ምን ይመስላል? ሀሳባችሁን አካፍሉን! ለማንኛውም አይነት ተጨማሪ የጉዞ ምዝገባ እና መረጃዎች +251942545470 , +251929176542 መደወል ይቻላል:: @guzoadwahiking @guzoad #ethiopia #landoforigins #guzoadwahiking #lakearsede #lakekilole

photo content
+4

photo content
+9

photo content
+4

ከ 50% በላይ የሚሆነው ቦታ አስቀድመው በተመዘገቡ ተጓዥ ቤተሰቦቻችን ተይዟል። ለዚህም እጅግ አድርገን እናመሰግናለን:: አሁንም በቀሩን ውስን ቦታዎች ላይ ተመዝግቦ በመጪው እሁድ ከእኛ ጋር ለመጓዝ
ከ 50% በላይ የሚሆነው ቦታ አስቀድመው  በተመዘገቡ ተጓዥ ቤተሰቦቻችን ተይዟል። ለዚህም እጅግ አድርገን እናመሰግናለን:: አሁንም በቀሩን ውስን ቦታዎች ላይ ተመዝግቦ በመጪው እሁድ ከእኛ ጋር ለመጓዝ በተከታዮቹ አድራሻዎች ብቻ ያገኙናል:: 📞+251942545470 , +251929176542 @guzoadwahiking ,@guzoad

ትናንት (ጥቅምት 01 2019 ዓ.ም) በሁሉቆ ፏፏቴና ዋሻ (Huluqo Waterfall and Cave) ያደረግነው የ 9 ኪሎ ሜትር የእግር ጉዞ እጅግ በጣም ደስ የሚል ነበር:: መንገዳችን በሙሉ አረንጓዴ እና ወርቃማ ቀለም በለበሱ የስንዴ ፣ ገብስ እና ጤፍ ሰብሎች በተሸፈኑ ውብ እርሻዎች መካከል የነበረ በመሆኑ የአካባቢው መልክዓምድር ለአይን እጅግ ይማርክ ነበር። ምንም እንኳን የፏፏቴው ውሃ መጠን ከክረምቱ አንፃር ዝቅተኛ ቢሆንም ፤ ውሃው በጣም ንጹህና እጅግ ውብ በመሆኑ ፏፏቴው ውስጥ ገብተው የተደሰቱ የጉዞ ቤተሰቦቻችና ነበሩ። ከሁሉም በላይ ግን የአካባቢው ማህበረሰብ ያሳየን አቀባበልና እንግዶችን የማክበር ባህል ወደር የለውም ፤ በራቸውን ከፍተው በጣፋጭ ባህላዊ ምግብ እና መጠጥ ያለምንም ስስት አስተናግደውናል። ይህንን አረንጓዴና ማራኪ ወቅት ከእኛ ጋር ለማሳለፍ ከፈለጉ እንዲሁም ማህበረሰብ ተኮር ቱሪዝምን የሚያጠናክር እና ትርጉም ያለው ጉዞ ለማድረግ ከፈለጉ አሁኑኑ ጉዞ ዓድዋ ሃይኪንግ ቡድንን (Guzo Adwa Hiking) ይቀላቀሉ። የጉዞ ዓድዋ ሃይኪንግ ቀጣይ የውሎ ገብ ጉዞ ወደ ኪሎሌ ሀይቅ ይደረጋል:: በያዝነው ሳምንት እሁድ ጥቅምት 8 ቀን 2019 ዓ.ም. (October 18) ከዕለታዊ የከተማ ውካታና ድካም ወጥተን በተፈጥሮ ለመተንፈስና ለመዝናናት ወደ ደብረዘይት(ቢሾፍቱ)ውብ ተፈጥሮ እናመራለን! መዳረሻችን ደግሞ ከተማዋ 18 ኪሎ ሜትር ወጣ ብሎ የሚገኘውና ሰላማዊ ድባብ ያለው ውቡ የኪሎሌ ሐይቅ (Lake Kilole) ነው። 🥾 የጉዞ ደረጃ፡ ከጀማሪ እስከ መካከለኛ ለሆኑ ተጓዦች የሚሆን (Beginners to Intermediate) ለጉዞ ምዝገባ እና ተጨማሪ መረጃዎች በተከታዮቹ አድራሻዎች ያግኙን +251942545470 +251929176542 @guzoadwahiking @guzoad

photo content
+9

photo content
+9

ጉዞ ወደ ኪሎሌ ሀይቅ ! በቀጣዩ ሳምንት እሁድ ጥቅምት 8 ቀን 2019 ዓ.ም. (October 18) ከዕለታዊ የከተማ ውካታና ድካም ወጥተን በተፈጥሮ ለመተንፈስና ለመዝናናት ወደ ደብረዘይት(ቢሾፍቱ)ውብ ተፈጥሮ እናመራለን! መዳረሻችን ደግሞ ከተማዋ 18 ኪሎ ሜትር ወጣ ብሎ የሚገኘውና ሰላማዊ ድባብ ያለው ውቡ የኪሎሌ ሐይቅ (Lake Kilole) ነው። በስተሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ የሚገኘው ኪሎሌ ሐይቅ በአካባቢው በሚገኙ ጥንታዊ የእሳተ ገሞራ ኮረብታዎች የተከበበ ድንቅ መልክዓ ምድር ነው። ከባህር ጠለል በላይ በ2,000-2100 ሜትር ገደማ ከፍታ ላይ የሚገኘው ይህ አካባቢ : በዙሪያው ባሉ ለምለም ተራራማ እና ሜዳማ መንገዶች የተከበበ በመሆኑ ለጀማሪዎችና ለመካከለኛ ደረጃ ተጓዦች በጣም ምቹ የሆነ የእግር ጉዞ ይደረግበታል። በተጨማሪም በሐይቁ ዙሪያ ከሚገኙት ተራሮች ሁሉ ከፍተኛ በሆነው የሂዲ ተራራ (Hidi Hills) አቅራቢያ የሚገኘው ታሪካዊውና መንፈሳዊው የፃድቁ መልከጼዴቅ ገዳም የአካባቢውን ተፈጥሮአዊና መንፈሳዊ ውበት ይበለጠ ያጎላዋል። በአማካኝ ከ2 ኪሎሜትር በላይ የዲያሜትር ስፋት ያለውና በአንጻራዊነት ጥልቀቱ መካከለኛ የሆነው የኪሎሌ ሐይቅ ውሃ፣ በርካታ የአእዋፋት ዝርያዎች (እንደ African Fish Eagle, Ducks, Egyptian geese, ducks, plovers etc..) የሚገኙበት የተፈጥሮ ገነት ነው። ይህ ስፍራ ከመደበኛ የቱሪስት መዳረሻዎች ወጣ ያለ በመሆኑ፣ ጉዞው በተፈጥሯዊ ጸጥታ ውስጥ እየተንሸራሸሩ ውብ ፎቶዎችን ለማንሳትና የአእዋፋት ምልከታ (Bird Watching) ለማድረግ ፍጹም ተስማሚ ያደርገዋል። 🗓️ የጉዞ ቀን፡ እሁድ ጥቅምት 8 ቀን 2019 ዓ.ም. October 18) 🥾 የጉዞ ደረጃ፡ ከጀማሪ እስከ መካከለኛ (Beginners to Intermediate) ስለጉዞው ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እንዲሁም ቦታ ለማስያዝ፡: 📞 +251942545470 , +251929176542 @guzoadwahiking @guzoad #ethiopia #guzoadwahiking #lakekilole #ethiopianhiking #traveltoethiopia

photo content
+9

Guzo Adwa updates - Telegram 频道 @adwav 的统计与分析