en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe 👈

Gondar City Education Department

Gondar City Education Department

Open in Telegram

ይህ የጎንደር ከተማ አስ/ትምህርት መምሪያ የቴሌ ግራም ቻናል ነው። የፌስቡክ ገጻችንንም ይከተሉ፦ https://www.facebook.com/GondarEdu ወቅታዊና ጠቃሚ ትምህርት ነክ መረጃዎችን ያገኙበታል።

Show more
3 682
Subscribers
No data24 hours
+137 days
+2930 days
Posts Archive
📢 የማስታወቂያ በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር ለተመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፤ ትምህርት ሚኒስቴር በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ባሉ ክፍት ቦታዎች ተ
📢 የማስታወቂያ በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር ለተመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፤ ትምህርት ሚኒስቴር በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ባሉ ክፍት ቦታዎች ተማሪዎችን ለመቀበል ባወጣው ማስታወቂያ መሠረት ለተመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን፣ ሰዓት እና ቦታ መወሰኑን እንገልጻለን። 📝 የፈተናው ዝርዝር መረጃ 📅 የፈተናው ቀን፦ መጪው ቅዳሜ፣ ጥቅምት 7 ቀን 2019 ዓ.ም ⏰ የመግቢያ ሰዓት፦ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት 📍 የፈተና ቦታ፦ በአቅራቢያችሁ በሚገኙ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በኦንላይን (Online) በተሰጠባቸው የፈተና ማዕከላት ⚠️ ማሳሰቢያ፦ ተማሪዎች ፈተናውን አልፈው በሚመደቡባቸው የትምህርት ቤቶች ለመማር ፈቃደኛ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

መመሪያ ቁጥር 51-2018ዓ.ም (2).pdf94.23 MB

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የዕውቅናና ሽልማት መመሪያ

የመምህርነት ምልመላ
+8
የመምህርነት ምልመላ

የቅጥር #ማስታወቂያ 📢 የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ትምህርት ቤት 🏫
+2
የቅጥር #ማስታወቂያ 📢 የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ትምህርት ቤት 🏫

መምህራን ለደረጃ እድገት ውድድር ብቁ ለመሆን ማሟላት ከሚገባቸው የጋራ መስፈርቶች መካከል በመምህርነት ሙያ ዕውቅና ካለው ተቋም የተመረቁ መሆን፣ የሙያ ፈቃድ ምስክር ወረቀት መያዝ፣ እንዲሁም ለጀማሪ መምህራን የመውጫ ምዘና ማለፍ በዋናነት ተቀምጠዋል። ከዚህ በተጨማሪም አንድ መምህር ለደረጃ እድገት ለመብቃት ከሚያስተምራቸው ተማሪዎች ውስጥ ቢያንስ 75 በመቶ የሚሆኑት 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸው በገለልተኛ አካል መረጋገጥ እንዳለበት ሰነዱ ያትታል። በተጨማሪም ጀማሪ መምህራን ቢያንስ የ40 ሰዓታት፣ ከመለስተኛ መምህር ጀምሮ ያሉት ደግሞ የ60 ሰዓታት ሙያ ተኮር አጫጭር ሥልጠናዎችን መከታተልና የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ (CPD) ዕቅዳቸውን በአግባቡ መፈጸም ይጠበቅባቸዋል። ወደ ከፍተኛ የእድገት እርከኖች ለመሸጋገር የተቀመጡት መመዘኛዎች የማስተማር ብቃትን ብቻ ሳይሆን የምርምርና የማኅበረሰብ አገልግሎት ተሳትፎንም ያካተቱ ናቸው። በዚህም መሠረት መምህራን ከደረጃ ወደ ደረጃ ሲሸጋገሩ ከ70 እስከ 90 በመቶ የሚደርስ የሥራ አፈጻጸም ውጤት ማስመዝገብ፣ የተደራጀ ማኅደረ-ተግባር (Portfolio) መያዝ፣ ጀማሪ መምህራንን በአማካሪነት መደገፍ እንዲሁም ልዩ ፍላጎት ያላቸውንና ተጋላጭ ተማሪዎችን መርዳት ግዴታ ተጥሎባቸዋል። በተለይም ከመካከለኛ ደረጃ ጀምሮ ባሉት ከፍተኛ እርከኖች ለመወዳደር የመማሪያና የመምሪያ መጻሕፍትን መገምገም፣ አጋዥ የትምህርት ጽሑፎችን ማዘጋጀት እና በመማር ማስተማር ችግሮች ዙሪያ ተግባራዊ ጥናትና ምርምሮችን (Action Research) ማካሄድ የግድ እንደሚል ሰነዱ በዝርዝር አስቀምጧል። አዲሱ መመሪያ የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ መምህራን የተፋጠነ የደረጃ እድገት የሚሰጥበትን አሠራርም አስተዋውቋል። በዚህም መሠረት ከመምህርነት እስከ መሪ መምህርነት ባለው እርከን የሚገኝ ማንኛውም መምህር የሚያስተምራቸው ተማሪዎች በሙሉ 85 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት በተከታታይ ሁለት ዓመታት እንዲያስመዘግቡ ካደረገ እና ይህም በገለልተኛ አካል ሲረጋገጥ፣ የሦስት ዓመት የቆይታ ጊዜውን ሳይጠብቅ በሁለት ዓመት ውስጥ እንዲያድግ ይደረጋል። በተመሳሳይም የተማሪዎቹን ውጤት 90 በመቶ እና ከዚያ በላይ ለተከታታይ ሦስት ዓመታት ያደረሰ መምህር አንድ የደረጃ መሰላል ዘሎ እንዲያድግ የሚፈቀድ ሲሆን፤ በከፍተኛ መሪ መምህርነት ደረጃ ላሉት ደግሞ የሁለት እርከን ደመወዝ ጭማሪ እንደሚሰጥ ተመላክቷል። በሌላ በኩል መመሪያው የወሊድ ፈቃድ ላይ ያሉ መምህራንን፣ በጤና እክል ምክንያት በቦርድ ውሳኔ ከክፍል የተገለሉ ባለሙያዎችን እና በመምህራን ማኅበራት በአመራርነት የሚያገለግሉ አባላትን የደረጃ እድገት አፈጻጸም በልዩ ሁኔታ አካቷል። የደረጃ እድገቱ በየዓመቱ በሁለት ዙር ማለትም በጥር አንድ እና በሐምሌ አንድ ቀን ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን፣ ሂደቱም በትምህርት ቤት ቴክኒክ ኮሚቴና በደረጃ እድገት ኮሚቴ ተጣርቶ በወረዳ ትምህርት ጽሕፈት ቤት አማካይነት ይጸድቃል። አሠራሩ ፍትሐዊና ገለልተኛ እንዲሆን የጥቅም ግጭትን የሚከላከሉ ድንጋጌዎች የተካተቱበት ሲሆን፣ በውሳኔው ላይ ቅሬታ ያላቸው መምህራንም ደብዳቤው በደረሳቸው በ10 የሥራ ቀናት ውስጥ አቤቱታ ማቅረብ እንደሚችሉ ተደንግጓል።

1148_የአጠቃላይ_ትምህርት_መምህራን_የደረጃ_እድገት_አፈጻጸም_1.pdf3.32 KB

የትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት መምህራን የደረጃ እድገት አፈጻጸም መመሪያን ይፋ አደረገ። የትምህርት ሚኒስቴር በመንግሥት ትምህርት ቤቶች ከቅድመ አንደኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ በሚያስተምሩ መምህራን ላይ ተፈጻሚ የሚሆን "የአጠቃላይ ትምህርት መምህራን የደረጃ እድገት አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 1148/2018" አውጥቷል። ሚኒስቴሩ በአጠቃላይ ትምህርት አዋጅ ቁጥር 1368/2017 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ያዘጋጀው ይህ መመሪያ፣ በማስተማር ሥራቸው የላቀ ውጤት የሚያስመዘግቡ መምህራንን ለማበረታታት፣ የሥራ ተነሳሽነታቸውን ለማሳደግ እንዲሁም አጠቃላይ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑ ተገልጿል። በመመሪያው ድንጋጌ መሠረት የአጠቃላይ ትምህርት መምህራን የእድገት መሰላል በሰባት ደረጃዎች የተከፋፈለ ሲሆን፤ እነሱም ፦ - ጀማሪ መምህር፣ - መለስተኛ መምህር፣ - መምህር፣ - ከፍተኛ መምህር፣ - ተባባሪ መሪ መምህር፣ - መሪ መምህር እና ከፍተኛ መሪ መምህር ናቸው። በመመሪያው የተቀመጠው የቆይታ ጊዜም ከጀማሪ ወደ መለስተኛ መምህርነት ለመሸጋገር 2 ዓመት፣ በቀጣዮቹ ደረጃዎች ደግሞ በእያንዳንዱ እርከን የ3 ዓመታት ቆይታ የሚጠይቅ ነው። ይሁን እንጂ አንድ መምህር በተከታታይ ወይም በተለያየ ጊዜ በውድድር ሁለት ጊዜ እድገት ማግኘት ካልቻለ ለሦስተኛ ጊዜ የመወዳደር ዕድል እንደማይኖረው በመመሪያው ተደንግጓል። መምህራን ለደረጃ እድገት ውድድር ብቁ ለመሆን ማሟላት ከሚገባቸው የጋራ መስፈርቶች መካከል በመምህርነት ሙያ ዕውቅና ካለው ተቋም የተመረቁ መሆን፣ የሙያ ፈቃድ ምስክር ወረቀት መያዝ፣ እንዲሁም ለጀማሪ መምህራን የመውጫ ምዘና ማለፍ በዋናነት ተቀምጠዋል። ከዚህ በተጨማሪም አንድ መምህር ለደረጃ እድገት ለመብቃት ከሚያስተምራቸው ተማሪዎች ውስጥ ቢያንስ 75 በመቶ የሚሆኑት 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸው በገለልተኛ አካል መረጋገጥ እንዳለበት ሰነዱ ያትታል። በተጨማሪም ጀማሪ መምህራን ቢያንስ የ40 ሰዓታት፣ ከመለስተኛ መምህር ጀምሮ ያሉት ደግሞ የ60 ሰዓታት ሙያ ተኮር አጫጭር ሥልጠናዎችን መከታተልና የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ (CPD) ዕቅዳቸውን በአግባቡ መፈጸም ይጠበቅባቸዋል። ወደ ከፍተኛ የእድገት እርከኖች ለመሸጋገር የተቀመጡት መመዘኛዎች የማስተማር ብቃትን ብቻ ሳይሆን የምርምርና የማኅበረሰብ አገልግሎት ተሳትፎንም ያካተቱ ናቸው። በዚህም መሠረት መምህራን ከደረጃ ወደ ደረጃ ሲሸጋገሩ ከ70 እስከ 90 በመቶ የሚደርስ የሥራ አፈጻጸም ውጤት ማስመዝገብ፣ የተደራጀ ማኅደረ-ተግባር (Portfolio) መያዝ፣ ጀማሪ መምህራንን በአማካሪነት መደገፍ እንዲሁም ልዩ ፍላጎት ያላቸውንና ተጋላጭ ተማሪዎችን መርዳት ግዴታ ተጥሎባቸዋል። በተለይም ከመካከለኛ ደረጃ ጀምሮ ባሉት ከፍተኛ እርከኖች ለመወዳደር የመማሪያና የመምሪያ መጻሕፍትን መገምገም፣ አጋዥ የትምህርት ጽሑፎችን ማዘጋጀት እና በመማር ማስተማር ችግሮች ዙሪያ ተግባራዊ ጥናትና ምርምሮችን (Action Research) ማካሄድ የግድ እንደሚል ሰነዱ በዝርዝር አስቀምጧል። አዲሱ መመሪያ የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ መምህራን የተፋጠነ የደረጃ እድገት የሚሰጥበትን አሠራርም አስተዋውቋል። በዚህም መሠረት ከመምህርነት እስከ መሪ መምህርነት ባለው እርከን የሚገኝ ማንኛውም መምህር የሚያስተምራቸው ተማሪዎች በሙሉ 85 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት በተከታታይ ሁለት ዓመታት እንዲያስመዘግቡ ካደረገ እና ይህም በገለልተኛ አካል ሲረጋገጥ፣ የሦስት ዓመት የቆይታ ጊዜውን ሳይጠብቅ በሁለት ዓመት ውስጥ እንዲያድግ ይደረጋል። በተመሳሳይም የተማሪዎቹን ውጤት 90 በመቶ እና ከዚያ በላይ ለተከታታይ ሦስት ዓመታት ያደረሰ መምህር አንድ የደረጃ መሰላል ዘሎ እንዲያድግ የሚፈቀድ ሲሆን፤ በከፍተኛ መሪ መምህርነት ደረጃ ላሉት ደግሞ የሁለት እርከን ደመወዝ ጭማሪ እንደሚሰጥ ተመላክቷል። በሌላ በኩል መመሪያው የወሊድ ፈቃድ ላይ ያሉ መምህራንን፣ በጤና እክል ምክንያት በቦርድ ውሳኔ ከክፍል የተገለሉ ባለሙያዎችን እና በመምህራን ማኅበራት በአመራርነት የሚያገለግሉ አባላትን የደረጃ እድገት አፈጻጸም በልዩ ሁኔታ አካቷል። የደረጃ እድገቱ በየዓመቱ በሁለት ዙር ማለትም በጥር አንድ እና በሐምሌ አንድ ቀን ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን፣ ሂደቱም በትምህርት ቤት ቴክኒክ ኮሚቴና በደረጃ እድገት ኮሚቴ ተጣርቶ በወረዳ ትምህርት ጽሕፈት ቤት አማካይነት ይጸድቃል። አሠራሩ ፍትሐዊና ገለልተኛ እንዲሆን የጥቅም ግጭትን የሚከላከሉ ድንጋጌዎች የተካተቱበት ሲሆን፣ በውሳኔው ላይ ቅሬታ ያላቸው መምህራንም ደብዳቤው በደረሳቸው በ10 የሥራ ቀናት ውስጥ አቤቱታ ማቅረብ እንደሚችሉ ተደንግጓል።

በአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የፀደቁና በፍትህ ቢሮ የተመዘገቡ መመሪያዎች ለማግኘት ይፈልጋሉ። ንግዲያውስ ከታች 👇 በሃሳብ መስጫ ሳጥን ላይ የተጠቀሱትን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ማህበራዊ ሚዲያ
በአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የፀደቁና በፍትህ ቢሮ የተመዘገቡ መመሪያዎች ለማግኘት ይፈልጋሉ። ንግዲያውስ ከታች 👇 በሃሳብ መስጫ ሳጥን ላይ የተጠቀሱትን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገፆች ይከተሉ/ይወዳጁ። ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ወቅታዊ እና ጠቃሚ የትምህርት መረጃዎችን ያግኙ! 📚✨ Facebook: https://www.facebook.com/share/1EozHfa3kB/ WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029VbBFbyrGZNCxP1X9ZI3w X: https://x.com/AmharaEducation

የሪሚዲያል እና በትግራይ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ/ሲማሩ የነበሩ ተማሪዎች ምደባ ይፋ ሆነ። በ2018 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና ወስደው በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ ግብር የመግ
የሪሚዲያል እና በትግራይ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ/ሲማሩ የነበሩ ተማሪዎች ምደባ ይፋ ሆነ።   በ2018 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና ወስደው በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ ግብር የመግቢያ ውጤት ላስመዘገቡ እና በ2019 ዓ.ም በትግራይ ክልል በሚገኙ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ለተመደቡ ተማሪዎች ምደባ ይፋ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋቃ።   በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ ግብር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ (Link) በመግባት መመልከት ይችላሉ። 👉 https://student.ethernet.edu.et/view-placement ቅሬታ ለማቅረብ፡ https://student.ethernet.edu.et/complaints ተጠቀሙ ተብሏል።   በሌላ በኩል፤ በዝውውር በጊዜያዊነት ከትግራይ ክልል ውጪ ወደሚገኙ ሌሎች የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡ አዲስ ገቢ ተማሪዎች የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ (Link) በመግባት መመልከት እንደሚችሉ ተገልጿል።   👉 https://student.ethernet.edu.et/view-placement   እንዲሁም በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ሲማሩ የነበሩ ነባር ተማሪዎች በጊዜያዊነት የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ በ https://student.ethernet.edu.et/university-transfer/ ማስፈንጠሪያ በመግባት የራሳችሀውን ፋይዳ (የመለያ ቁጥር) በመጠቀም መመልከት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

"ከአንድ ዩኒቨርሲቲ ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪ ዝውውር የሚፈፀመው የላኪው እና የተቀባዩ ዩኒቨርሲቲ ስምምነት ሲኖር ብቻ ነው፡፡ ዝውውሩ ሲፈፀም ትምህርት ሚኒስቴር በደብዳቤ እንዲያውቀው መደረግ አለ
+1
"ከአንድ ዩኒቨርሲቲ ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪ ዝውውር የሚፈፀመው የላኪው እና የተቀባዩ ዩኒቨርሲቲ ስምምነት ሲኖር ብቻ ነው፡፡ ዝውውሩ ሲፈፀም ትምህርት ሚኒስቴር በደብዳቤ እንዲያውቀው መደረግ አለበት"፡፡ - ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ሚኒስቴር "የተማሪዎች ቅበላ፣ የትምህርት መስክ ምደባ እና የተማሪዎች ዝውውር አፈጻጸምን" አስመልክቶ በቀን 07/01/2019 ዓ.ም ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የተፈረመ ሰርኩላር ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ልኳል፡፡ ሰርኩላሩ፤ ዩኒቨርሲቲዎቹ ከተማሪዎች ቅበላ፣ የትምህርት መስክ ምደባ እና የተማሪዎች ዝውውር ጋር በተያያዘ ሊከተሏቸው የሚገቡ አሠራሮችን አስቀምጧል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎች በሚኒስቴሩ ከተላለፈ የምደባ ውጤት ውጭ ተማሪን በራሳቸው ተነሳሽነት መቀበል፣ የተመደበበትን ተቋም መቀየር ወይም በሌላ ተቋም የተመደበን ተማሪ ያለአግባብ መመዝገብ እንደማይችሉ ተገልጿል፡፡ ተቋማቱ ከተቀመጠው የምደባ መስፈርት ውጭ በግለሰብ ጥያቄ፣ በልዩ ትዕዛዝ ወይም ለአንድ ተማሪ ብቻ በሚደረግ ልዩ አሠራር የትምህርት መስክ ምደባ መቀየር አይችሉም። ከአንድ ዩኒቨርሲቲ ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪ ዝውውር የሚፈፀመው የላኪው እና የተቀባዩ ዩኒቨርሲቲ ስምምነት ሲኖር ብቻ ሲሆን፣ ዝውውሩ ሲፈፀም ትምህርት ሚኒስቴር በደብዳቤ እንዲያውቀው መደረግ አለበት ተብሏል። የዝውውር ጥያቄ የሚስተናገደው ተማሪው በተመደበበት ተቋም ቢያንስ አንድ ሴሚስቴር የተማረ እና ከፕሮግራሙ 50 በመቶ በላይ ያላጠናቀቀ ከሆነ ብቻ እንደሆነ ተመላክቷል፡፡ በሌላ በኩል ከመንግሥት ወደ ግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ዝውውር ሊፈፀም የሚችል ሲሆን፣ ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ወደ መንግሥት ዩኒቨርሲቲ ዝውውር ማድረግ እንደማይቻል ተገልጿል፡፡ (ሰርኩላሩ ከላይ ተያይዟል፡፡) @tikvahuniversity

📢 ለፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አዲስ ገቢ ተማሪዎች በሙሉ የተላለፈ ጥሪ! ​በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር የመግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ያለፋችሁ የ9ኛ
📢 ለፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አዲስ ገቢ ተማሪዎች በሙሉ የተላለፈ ጥሪ! ​በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር የመግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ያለፋችሁ የ9ኛ እና 10ኛ ክፍል አዲስ ገቢ ተማሪዎች ወደ ተመደባችሁባቸው ትምህርት ቤቶች የመግቢያ ቀን መስከረም 18 እና 19/2019 ዓ.ም መሆኑን ተገልጿል። ​✨ ተማሪዎች ሲመጡ ይዘዋቸው ሊመጡ የሚገቡ አስፈላጊ ቁሳቁሶች፦ ​1️⃣ የትምህርት መሣሪያዎች፦ • ደብተር፣ እስክሪብቶ፣ ቦርሳ፣ የስፖርት ትጥቅ እና ሌሎች ለትምህርት የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች። ​2️⃣ የመኝታ ቁሳቁስ፦ • ለመኝታ አገልግሎት የሚሆኑ አንሶላ እና ብርድ ልብስ። ​3️⃣ ሕጋዊ ሰነዶች፦ • እስካሁን ሲማሩበት ከነበረው ትምህርት ቤት የተሰጠ መሸኛ እና የትምህርት ውጤትን የሚገልጽ ትራንስክሪፕት። ​⚠️ ማሳሰቢያ፦ ተማሪዎች ወደ ተመደቡባቸው ትምህርት ቤቶች ከደረሱ በኋላ የሚያስፈልጋቸውን የትምህርት ቤት ዩኒፎርም በራሳቸው ወጪ የሚያስዘጋጁ በመሆኑ፣ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት እንድታደርጉ እንሳስባለን።

*ቁልፍ የትምህርት መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ!* 📚 ​የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ትክክለኛ፣ ወቅታዊ እና ጠቃሚ መረጃዎችን ለማግኘት የማህበራዊ ትስስር ገጾችንን ይከተሉ/ይወዳጁ! ​🔗 ፌስቡክ ገፅ፡https://www.facebook.com/share/1EozHfa3kB/ 🔗 ዋትሳፕ ቻናል፡https://whatsapp.com/channel/0029VbBFbyrGZNCxP1X9ZI3w 🔗 X (ትዊተር) አካውንት፡ https://x.com/AmharaEducation

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በ2019 የትምህርት ዘመን በተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት መስኮች በሪሚዲያል መርሐግብር ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማሰልጠን ተዘጋጅቷል፡፡ 🎓 ከላይ በምስሉ ላይ የተገለፀው
+2
የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በ2019 የትምህርት ዘመን በተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት መስኮች በሪሚዲያል መርሐግብር ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማሰልጠን ተዘጋጅቷል፡፡ 🎓 ከላይ በምስሉ ላይ የተገለፀውን የመቁረጫ ነጥብ ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች ለሪሚዲያል መርሐግብር የዩኒቨርሲቲ ቅበላ ብቁ መሆናቸውን ትምህርት ሚኒስቴር ያሳወቀ በመሆኑ፤ በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት መመዝገብ እንደምትችሉ ተገልጿል፡፡ ✅ በኢንስቲትዩቱ በሪሚዲያል መርሐግብር የሚታቀፉ ከአዲስ አበባ ውጪ የሚመጡ ተማሪዎች የምግብ እና የመኝታ አገልግሎት የሚያገኙ ሲሆን፣ ከአዲስ አበባ የሚመጡ ተማሪዎች የምግብ አገልግት ብቻ ያገኛሉ፡፡ 🍽️🏠 የማመልከቻ ጊዜ 👇 እስከ መስከረም 15/2019 ዓ.ም 📅 የማመልከቻ ቦታ 👇 በአዲስ አበባ ዋና ካምፓስ፣ ከላምበረት መናኸሪያ 500 ሜትር አለፍ ብሎ ወደወሰን መስመር 📍 አስፈላጊ ሰነዶች፡- ➻ የ11ኛ እና 12ኛ ከፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው 📄 ➻ የ12ኛ ከፍል ብሔራዊ ፈተና ሰርተፊኬት 📜 ➻ የፋይዳ መታወቂያ ዋናውና ኮፒ 🆔 (የመቁረጫ ነጥብ  እና  የትምህርት መስኮች  ዝርዝር  ከላይ በምስሉ ተያይዟል፡፡)

የሪሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምርጫ አድርጉ ተብሏል፡፡ በ2018 ዓ.ም የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ
የሪሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምርጫ አድርጉ ተብሏል፡፡   በ2018 ዓ.ም የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምደባ ምርጫችሁን ከመስከረም 7-11/2019 ዓ.ም ድረስ እንድታደርጉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡   የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለመምረጥ 👇 https://student.ethernet.edu.et/preferences

የሪሚዲያል መርሃ ግብር የዩኒቨርሲቲ ቅበላ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ። ለ2019 ዓ/ም የሪሚዲያል መርሃ ግብር ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የሚያስችላቸው የመቁረጫ ነጥብ በተማሪዎች ውጤት፣ በዩኒቨ
የሪሚዲያል መርሃ ግብር የዩኒቨርሲቲ ቅበላ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ። ለ2019 ዓ/ም የሪሚዲያል መርሃ ግብር ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የሚያስችላቸው የመቁረጫ ነጥብ በተማሪዎች ውጤት፣ በዩኒቨርሲቲዎች የቅበላ አቅም፣ እና በሀገራዊ የትምህርት ፍትሃዊነት መርህ ላይ ተመስርቶ መወሰኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። በዚህም መሰረት ከታችን የተገለጸውን ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ለሪሚዲያል መርሃ ግብርየዩኒቨርሲቲ ቅበላ ብቁ መሆናቸውን ሚኒስቴሩ አሳውቋል። 1. የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 👉 ከ600 ውስጥ 240 እና ከዚያ በላይ (40%) 2. የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 👉 ከ600 ውስጥ 228 እና ከዚያ በላይ (38%)

​🚀 የሳይንስ እና ፈጠራ አቅማችሁን ለዓለም የምታዩበት ወርቃማ ዕድል! 🔬💡 ​የጎንደር ዩኒቨርሲቲ STEM ማዕከል በበጀት ዓመቱ በመንግስትና በግል ትምህርት ቤቶች የሚገኙ ከ9ኛ - 12ኛ ክፍል
​🚀 የሳይንስ እና ፈጠራ አቅማችሁን ለዓለም የምታዩበት ወርቃማ ዕድል! 🔬💡 ​የጎንደር ዩኒቨርሲቲ STEM ማዕከል በበጀት ዓመቱ በመንግስትና በግል ትምህርት ቤቶች የሚገኙ ከ9ኛ - 12ኛ ክፍል ያሉ የፈጠራ አቅም ያላቸውን ተማሪዎች አወዳድሮ በሀገር አቀፍ የሳይንስ ፈጠራ ውድድር ላይ ለማሳተፍ የአካባቢያዊ የሳይንስ ፈጠራ (Local Science Fair) ውድድር አዘጋጅቷል። ​በመሆኑም በፈጠራ ሥራዎቻችሁ መወዳደር የምትፈልጉ ተማሪዎች እስከ መስከረም 15/2019 ዓ.ም ድረስ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን። ​የውድድር ዘርፎች (Categories)፦ 1️⃣ የጤና፣ ግብርና እና አካባቢ ችግሮች መፍትሔ (Health Tech, Agriculture & Environmental Solutions) 2️⃣ የማምረቻና ኢንዱስትሪ (Manufacturing & Industrial Solution) 3️⃣ ዲጂታል ቴክኖሎጂ እና የሶፍትዌር ልማት (Digital Technology & Software Dev't) 4️⃣ ሮቦቲክስ እና ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች (Robotics & Emerging Technology) ​📝 የአመዘጋገብ እና የፈጠራ ሥራ ማስረከቢያ መንገድ፡ ተወዳዳሪዎች ሙሉ ስም፣ ዕድሜ፣ ጾታ፣ የክፍል ደረጃ፣ የመጡበት ትምህርት ቤት እና የፈጠራ ሥራችሁን ዝርዝር መግለጫ (Proposal) በመያዝ፦ ​📧 በኢሜይል፡ ceil@uog.edu.et በመላክ ወይም ​🏢 በአካል፡ በዩኒቨርሲቲው ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ማዕከል አስተባባሪ ቢሮ በመገኘት መመዝገብ ትችላላችሁ። ​📅 ማስታወሻ፦ ​የምዝገባ ማብቂያ ቀን፡ እስከ መስከረም 15/2019 ዓ.ም ​ውድድሩ የሚካሄድበት ቀን፡ ጥቅምት 11 - 12/2019 ዓ.ም ​📍 ዒላማ የተደረጉት፡ በጎንደር ከተማ አስተዳደር ስር በሚገኙ ሁሉም ትምህርት ቤቶች የሚገኙ የ9ኛ - 12ኛ ክፍል ተማሪዎች።

እንኳን ደስ አለን! እንኳን ደስ አላችሁ! 🎉 የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሞዴል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያስፈተኗቸው ተማሪዎች 100% ሙሉ በ
እንኳን ደስ አለን! እንኳን ደስ አላችሁ! 🎉 የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሞዴል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያስፈተኗቸው ተማሪዎች 100% ሙሉ በሙሉ 50% እና ከዚያ በላይ አስመዝግበዋል 📈📚 በአማራ ክልል ይህንን ድንቅ ውጤት ካስመዘገቡ 8 ትምህርት ቤቶች መካከል 2ቱ በከተማችን የሚገኙ በመሆናቸው ታላቅ ኩራት ይሰማናል 👏🏫

🚨 ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች እና ወላጆች በሙሉ! ​"የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከዛሬ ምሽት 1፡00 ሰዓት ጀምረው ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ" — የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ​የ2018 ትምህር
🚨 ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች እና ወላጆች በሙሉ! ​"የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከዛሬ ምሽት 1፡00 ሰዓት ጀምረው ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ" — የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ​የ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና ውጤት የሚገለጽባቸው አማራጭ አድራሻዎች ይፋ ሆነዋል። ​ተፈታኞች ዛሬ ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ ከታች በተቀመጡት ሊንኮች (Links) በመግባት ውጤታችሁን ማየት ትችላላችሁ። ​📌 የቅሬታ ማቅረቢያ ጊዜን በተመለከተ፦ ቅሬታ ያለው ማንኛውም ተፈታኝ በአካል መምጣት ሳያስፈልገው ከነሐሴ 19 እስከ 26 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው ማስፈንጠሪያ ቅሬታውን ማቅረብ እና ምላሹንም በዚያው መከታተል የሚችል መሆኑን አገልግሎቱ አሳውቋል። ​👇 ውጤት ለማየት እና ቅሬታ ማቅረቢያ ሊንኮች:- ውጤት ለማየት፡- - በድረ ገጽ ፡ https://result.eaes.et - ቴሌግራም፡ https://result.eaes.et/telegram - አጭር የጽሑፍ መልዕክት፡ https://result.eaes.et/sms ቅሬታ ለማቅረብ፦ https://result.eaes.et/complaint

🚨 ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች እና ወላጆች በሙሉ! ​"የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከዛሬ ምሽት 1፡00 ሰዓት ጀምረው ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ" — የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ​የ2018 ትምህር
🚨 ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች እና ወላጆች በሙሉ! ​"የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከዛሬ ምሽት 1፡00 ሰዓት ጀምረው ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ" — የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ​የ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና ውጤት የሚገለጽባቸው አማራጭ አድራሻዎች ይፋ ሆነዋል። ​ተፈታኞች ዛሬ ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ ከታች በተቀመጡት ሊንኮች (Links) በመግባት ውጤታችሁን ማየት ትችላላችሁ። ​📌 የቅሬታ ማቅረቢያ ጊዜን በተመለከተ፦ ቅሬታ ያለው ማንኛውም ተፈታኝ በአካል መምጣት ሳያስፈልገው ከነሐሴ 19 እስከ 26 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው ማስፈንጠሪያ ቅሬታውን ማቅረብ እና ምላሹንም በዚያው መከታተል የሚችል መሆኑን አገልግሎቱ አሳውቋል። ​👇 ውጤት ለማየት እና ቅሬታ ማቅረቢያ ሊንኮች:- ውጤት ለማየት፡- - በድረ ገጽ ፡ https://result.eaes.et - ቴሌግራም፡ https://result.eaes.et/telegram - አጭር የጽሑፍ መልዕክት፡ https://result.eaes.et/sms ቅሬታ ለማቅረብ፦ https://result.eaes.et/complaint