አርምሞ🧘🏽♂
📈 Analytical overview of Telegram channel አርምሞ🧘🏽♂
Channel አርምሞ🧘🏽♂ (@armemo_offical) in the Amharic language segment is an active participant. Currently, the community unites 12 005 subscribers, ranking 7 493 in the Religion & Spirituality category and 2 917 in the Ethiopia region.
📊 Audience metrics and dynamics
Since its creation on невідомо, the project has demonstrated rapid growth, gathering an audience of 12 005 subscribers.
According to the latest data from 28 October, 2026, the channel demonstrates stable activity. Although there has been a change in the number of participants by 269 over the last 30 days and by 9 over the last 24 hours, overall reach remains high.
- Verification status: Not verified
- Engagement rate (ER): The average audience engagement rate is 19.59%. Within the first 24 hours after publication, content typically collects 7.61% reactions from the total number of subscribers.
- Post reach: On average, each post receives 2 352 views. Within the first day, a publication typically gains 913 views.
- Reactions and interaction: The audience actively supports content: the average number of reactions per post is 34.
📝 Description and content policy
The author describes the resource as a platform for expressing subjective opinions:
“ጥ ቂ ት ም ና ኔ. .🧘🏽♂️”
Thanks to the high frequency of updates (latest data received on 29 October, 2026), the channel maintains relevance and a high level of publication reach. Analytics show that the audience actively interacts with content, making it an important point of influence in the Religion & Spirituality category.
«ጭካኔን ላስተማሯችሁ ሰዎች አጨብጭቡላቸው። ከዚያ ግን ጠንከር ያለ ጥፊ ምቷቸው፤ እነሱ በከንቱ እንዳለፉ፤ እናንተም ጎበዝ ተማሪ እንደሆናችሁ ለማሳወቅ!።» 🤗
―ሙሐሙድ ዳርዊሽ
@Imagination_officiallyየጫካ እንስሳቶች አንድ ሀሳብ አመጡ። አሳቡም በጫካ ውስጥ ያለው ስፍራ ንጹህ ደን እንዲኖረው የእንስሳት መጸዳጃ ለመገንባት የተወሰነ እቅድ ነው። ታድያ ተገንብቶ እንዳለቀ ለአንድ ሳምንት ያህል ሁሉም ነገር እንዳመረበት ደህንነቱን ጠብቆ ነበር።
ነገር ግን የሆነ ቀን ላይ እንዲህ ሆነ። የመጸዳጃ ቤቱ በር ላይ ትንሽዬ ቀዳዳ ተፈጠረ። የጫካው ኮሚቴ ተደርጎ የተሾመው ተኩላ ሁሉንም እንስሳ ሰብስቦ ጠየቃቸው፦«እዚህ ምን እንደተፈጠረ የሚነግረኝ አለ?»
ከእንስሳት መካከል ጥንቸሏ «አዎ አንድ ነገር አውቃለሁ» አለች። ቀጥላም «አየህ ዝሆኑ ሽንት ቤት ለመጠቀም ገብቶ ነበር። ቢሆንም የሽንት ቤቱ ወረቀት በጠቅላላ አልቋል። እኔ ደግሞ ውጪ ነበርኩ። እና ዝሆኑ ሲያየኝ ያዘኝና ቂጡን ተጠራርጎ ወደ በሩ አሽቀናጥሮ ወረወረኝ። ቀዳዳው በዛ ምክንያት ነው የተሰነጠቀው።»
ዝሆንም ይህንን ሲሰማ በኩራት፦«የተናገረችው ነገር በጠቅላላ እውነት ነው!» ብሎ መለሰ። አቶ ዝሆን ግዙፍና ጠንካራ ስለሆነ ተኩላው ከእሱ ጋር ለመጣላት አልደፈርም ብቻ እንዳቀረቀረ «ችግር የለውም በሩን እናስተካክለዋለን። ይህ የሚደገም አይመስለኝም።» በማለት አለፈው።
ሌላ ሳምንት መጣ። ዛሬ ደግሞ ካለፈው ሳምንት በባሰ መልኩ የሽንት ቤቱ በር ሙሉ ለሙሉ ተነቅሎ መሬት ላይ ወድቋል። ተኩላው እንደገና እንስሳቱን ሰብስቦ ጠየቀ፦«እዚህ ምን እንደተፈጠረ የሚነግረኝ አለ?»
ከእንስሳቱም መካከል ቀበሮ እጁን እያወጣ «አዎ አንድ ነገር አውቃለሁ» አለ። «አዎ አንድ ነገር አውቃለሁ፤ አቶ ዝሆን ሽንት ቤት ለመጠቀም ገብቶ ነበር። ግን የሽንት ቤት ወረቀት አልነበረም። እኔ ደግሞ በዛ በኩል እያለፍኩ ነበር። እና ዝሆኑ ሲያየኝ ያዘኝና ቂጡን ተጠራርጎ በኃይል ወረወረኝ ለዛ ነው ሙሉ ለሙሉ በሩ የተገነጠለው» አለ። ሁሉም እንስሳት ስለዝሆኑ ጭካኔ በጥልቀት አሰቡ። እንደዚህ ያለ ግዙፍ እንስሳን ተደባድበው ማሳመን እንደማይችሉ ተረድተዋል። ስለዚህ እንደገና በዝምታ በሩን አስተካክለው ምንም ሳይናገሩ ተበታተኑ።
ነገር ግን ከአንድ ሳምንት በኋላ ያልታሰበ ነገር ተከሰተ። የሽንት ቤቱ አጠቃላይ ሕንፃ ሙሉ በሙሉ ተደረማምሷል። ግድግዳዎቹ በጠቅላላ ወደ ፍርስራሽነት ተቀይረዋል። አብዛኞችሁ ዛፎች ተገነዳድሰዋል። ይሄን የተመለከተው ኮሚቴ ተኩላ ድንጋጤ እንደዋጠው፦«ይህ በጣም በዛ!። ማን እንደፈጸመው ግልጽ ነው። የአቶ ዝሆን ድርጊት ነው!። ቢሆንም እንደሌላ ግዜ በመካከላችን ተገኝቶ ጥፋቱን አላመነም። የት እንደሄደ እንጃ እዚህ እያየውት አይደለም። በሌለበት ደግሞ ስሙን ማጥፋት የለብንም። ፕሮቶኮሉን ለመጠበቅ ብቻ እዚህ ምን እንደተፈጠረ ማንስ ይህንን ድርጊት እንደፈጸመ የሚነገርኝ አለ?»
ከእንስሳት መካከል «አዎ አንድ ነገር አውቃለሁ..» የሚል ድምፅ ተሰማ። ሁሉም ድምፁን ወደሰሙት እንስሳ ዞር አሉ። ጃርት ነበረች 🦔😁
(ስለዝሆኑ የቂጥ ጤንነት አይወራ 😓)
@Armemo_offical እንደቀልድ አልተደረሰም። ያለምንም ማስታወቂያ በእራሳቸው ፈቅደው የገነቡት ቦታ ነውና አመሰግናለሁ። በዚህ ቻናል በፖለቲካው ጎን ባለመስማማትና በመበሳጨት የወጡ ሰዎች እጅግ በጣም ብዙ ቢሆኑም በዛው ልክ የእውነትን መራር ጎን የሚቀበሉ አሳብያን ደግሞ እስከዛሬ አብረውኝ ዘልቀዋል። ምን ልላችሁ ገና ነን°°🫡
https://t.me/Armemo_offical ለትዳር አላማ «ዊንታ »ከምትባል ቆንጆ ኤርትራዊት ልጅ ጋር ተገናኘው። ያንን የትዳር አላማ ለማሟላት የህክምና ሙያዬ በቂ ነው ብዬ አስቤ ነበር። ነገር ግን ዊንታ ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎች ነበራት።
በጥያቄ ታጣድፈኝ ጀመር፦«በትርፍ ግዜ የምታሳልፋቸው ሆቢዎች አሉህ?»
-አይ
«ፊልሞችን ትመለከታለህ?»
-አይ
«ሌሎች ቦታዎች ጉዞ አድርገህ ታውቃለህ?»
-አይ
«መፅሃፍት ታነባለህ?»
-አይ
«ተራራዎችን ወጥተ ታውቃለህ?»
-አይ
«ታድያ በትርፍ ጊዜህ ምንድነው የምታደርገው?»
-ትርፍ ጊዜ የለኝም በስራ ነው የማሳልፈው።
ለአፍታ ዝም ካለች በኋላ እንዲህ አለች፦«አየህ አንተ ተራ ሰው ነህ!። ተራ ባትሆን ባንተ ላይ ፍላጎት ይኖረኝ ነበር።»
እነዚያ ቃላት ጭንቅላቴን እንደ ነጎድጓድ መታው።15 አመታትን ብዙ የህክምና መጽሃፍቶች ሳገላብጥ አሳልፌ በመጨረሻም «ተራ» የሚባል ማዕረግ አገኘሁ!።
ወደ ቤት ተመለስኩ እና በዚያ ምሽት እንቅልፍ እንዳልተኛሁ አስታውሳለሁ። በጠዋቱ ወደ አውሮፓ ለመሄድ ትኬቴን ቆርጬ በፕሌን ተጓዝኩ። በተለያዩ ሀገራት የተለያዩ ነገሮችን አድርጌ ወደ አገር ቤት ተመለስኩ። ስመለስ አዕምሮዬ ላይ የመጣው ቀጥታ ዊንታን ማግኘት ነበር። ነገር ግን ይህ ሁኔታ ብቻ በቂ እንዳልሆነ ገባኝ። ብዙ መፅሃፍቶችን ማንበብ አለብኝ። ቤት ውስጥ ራሴን አግልዬ በደርዘን የሚቆጠሩ የፍልስፍና፣ የታሪክ እና የሶሺዮሎጂ መጽሃፎችን በማንበብ ግዜዬን አሳለፍኩኝ።
ከጨረስኩ በኋላ «ይህ በቂ አይደለም» አልኩና ለአንድ ወር ያህል በጣም አስፈላጊ የሆኑ ፊልሞች መርጬ አየሁ። ስጨርስ «ይህ በቂ አይደለም» አልኩና ፈረስ ግልቢያ፣ ሙዚቃን፣ ዲዛይንን፣ ፎቶግራፍን ተማርኩ እና ብዙ አስደናቂ የትርፍ ጊዜ ማሳለፊያዎችን እስከሚዋሃደኝ ድረስ ተለማመድኩ።
ስጨርስ ይህ በቂ አይደለም አልኩኝና ወደ ተራራ ጫፍ መውጣት እንዲለብኝ ወሰንኩኝ። ከሁለት ሳምንት አድካሚ ጉዞ በኋላ ወደ ተራራው ጫፍ ደረስኩና እጆቼን ዘርግቼ ጭንቅላቴን ቀና አደረኩኝ። በርግጥ ይህ በቂ እንደሆነ ተሰማኝ፤ ነገር ግን በድንገት ወደ ዊንታ የመመለስ አምሮቴ እሬት እሬት አለኝ።
ምክንያቱም እኔ ባለብዙ ሆቢዎች ባለቤት ሆንኩ ዊንታ ደግሞ ተራ ሴት ሆነችብኝ።
አመሰግናለሁ ዊንታ..🚶🏼🙏😌
@Armemo_officalየሆነ ገበሬ በመንደር እየሄደ ሳለ ከሰዎች አንዱ ተመለከተውና፦«እንዴ አንተ ሰው! አህያህን ባላያት ኖሮ ሌላ ሰው ነው የምትመስለኝ የምር አላወቅኩህም ነበር» አለው።
ይሄኔ ገበሬው ተረጋግተቶ መለሰ፡-«ልክ ነህ አህዮች እርስ በእርሳቸው ይተዋወቃሉ» 🙂
@Armemo_officalከብዙ የሙያ ዘርፎች መካከል በጭንቅላታቸው የማደንቃቸው ጠበቃዎች ናቸው። የጠበቃ እና የደላላ ቴክኒክ ብዙ የሚያመሳስለው ነገሮች አሉት። ቢሆንም ደላላ ብዙም እውቀት የሌላቸው ሰዎችን አዕምሮ ሲሸጥ፤ ጠበቃ ግን እንደሱ ያሉና ከእሱም በላይ የሆኑ ሙያተኞችን የማሳመን ብቃት ያለው ጂንየስ ነው።
በነገራችን ላይ የጠበቃን ብቃት የሚወስነው ሕጉን ማወቁ ብቻ አይደለም፤ የሰውን ስነልቦና፣ የዳኛው የአስተሳሰብ ብሎም ማስረጃ በሰው አእምሮ ውስጥ የሚፈጥረውን ተጽዕኖ ጠንቅቆ የሚያውቅ ግለሰብ ነው። የሰው ልጅ ሁልግዜም ቢሆን የሚያምነው እውነትን ስላገኘ ሳይሆን፤ እውነት መስሎ በቀረበለት ነገር ስለሚማረክ ነው። ብልህ ጠበቃ ደግሞ ይህንን የሰው ባህሪ ከማንም በላይ ይረዳዋል። ከማስረጃ በፊት የሚመጣውን ግምት፣ ከእውነት በፊት የሚቀድመውን ጥርጣሬና ከፍርድ በፊት የሚፈጠረውን የአእምሮ ውሳኔ ያውቃል። ምክንያቱም አንድ ነገር እውነት መሆኑና እውነት መሆኑን ማስረዳት ሁለት የተለያዩ ችሎታዎች ናቸው።
አሜሪካኖች አንዲት አባባል አለቻቸው፦«A good lawyer knows the law; a clever lawyer knows the judge.» ምን ማለታቸው መሰላችሁ፦«ጎበዝ ጠበቃ ሕጉን ያውቃል፤ ብልህ ጠበቃ ግን ዳኛውን ያውቀዋል።»
ሁሌም በፍርድ ቤት ውስጥ የሚነገረው ቃል እውነት ነው ለማለት አያስደፍርም፤ የሌላውን ሰው አስተሳሰብ ሊቀይር የሚችል መሣሪያም ጭምር ነው። ጠበቃው አንድን ማስረጃ በተለያየ መንገድ በማቅረብ የዳኛውን ትኩረት ሊሰርቅ ይችላል። ለዛም ነው የጠበቃ ሙያ ከሕግ ባሻገር ወደ ፍልስፍናዊ ጥያቄዎች የሚገባ ሰንሰለት ነው የምላችሁ። «እውነት ምንድን ናት?» እና «ሰው በማስረጃ ነው የሚያምነው ወይስ ማስረጃው በተፈጠረበት ስሜት?» የሚለውን ሳይኮሎጂ በደንብ አድርገው በልተውታል። ዳኛው ሰው ነው፤ ጠበቃውም ሰው ነው። ሁለቱም የሰውን የማሰብ ገደብ የተሸከሙ ፍጡሮች ናቸው። ስለዚህ እዚህ ጋር ከተፈጠረው እውነት ይልቅ በማስረጃ የቀረበው ውሸት ሚዛን ይደፋል።
ጠበቃ እውነትን ሳይሆን እውነት የሚመስለውን ነገር በመፈለግ የተጠመደ ሙያተኛ ነው። ፍትሕ ለንጹህ የሚበየን ፍርድ ሳይሆን መረጃው ላለው የሚቀርብ ቁስ አካላዊ ቲዎሪ ነው። አብዛኛው ጠበቆች ደንበኛቸውን ለማንፃት አፋቸውን በተመረጡ ቃላት ይቀባባሉ፣ የማይመቻቸውን ማስረጃ ያደበዝዛሉ፣ ጥርጣሬን ወደ እርግጠኝነት ይቀይራሉ። እውነትን ለማሳመን ከሚጠቀሙበት ቃል በበለጠ ብዙ ውሸቶችን ይፈጥራሉ። ያኔ ነው ቃላት የፍትሕ መሣሪያ መሆኑን ትቶ ለማሳመን የምንገለገልበት የሐሰት መሣሪያ የሚሆነው።
በርግጥ ግን በጅምላ ጠበቃን መዝለፍ ተገቢ አይደለም። ሁሉም ጠበቃዎች ክርክሩን ለማሸነፍ ማንኛውንም ነገር ያደርጋሉ፤ አንዳንዴ እውነት እስከመናገር እራሱ ይደርሳሉ 🤭 የውሸት አባቷ ዲያቢሎስ ነው ይበላል፤ የዲያቢሎስን ልጅ ግን ያገባው ደላላ እና ጠበቃ ነው 😃
@Armemo_officalፈጣሪም በመጨረሻ እንዲህ ያለ ይመስለኛል፦«አንድ ዕፀ በለስ በአንድነት ተስማምታችሁ በልታችሁ የጀመራችሁትን ጉዳይ እንኳን በጋራ ችግሩን መፍታት አልቻላችሁም!። አዳምን ከአፈር ሠራሁት፤ ሔዋንን ከጎድን አጥንቱ ፈጠርኳት፤ እባቡንም በምድር ላይ አስቀመጥኩ። ሁሉም ግን ጥፋቱን ከእራሱ እያሸሸ ወደሌላኛው ፍጥረት ያዘዋውራል። የዝውውሩም መጨረሻ ሴት መሆኗ ደግሞ ጨክኜ እንዳልፈርድ ከሴት ማህፀን የማተርፈውን ጻድቃን ያሳጣኛል። ስለዚህ ሴት ትኑር ወንድም የሴት እራስ ሆኖ ይግዛት፤ እሱም እሷን ለመግዛት ባሰበው ልክ የእርሷ ባርያ ፍትወታም ይሁን!። 🤙🏽
@Armemo_offical ጠየቀ፦«አዳም ሆይ አታድርግ ያልኩህን ለምን አደረግህ?»
አዳምም መለሰ፦«ሔዋን አሳስታኝ ነው»
እግዝአብሔር ጠየቀ፦«ሔዋን ሆይ ለምን አዳምን አሳሳትሽው»
ሔዋንም መለሰች፦«እባብ ነው የመከረኝ»
እግዘብሔርም ጠየቀ፦«እባብ ሆይ ለምን የሰውን ልጅን አሳሳትኽ?»
እባብም መለሰ፦«ሴቷ እባብ አሳስታኝ ነው» 😑
@Armemo_officalሙላ ነስሩዲን በባስ እየተጓዘ ሳለ አንድ እንግዳ ሰውዬ ቀልድ አዘል ረጅም ታሪክ ታክሲ ውስጥ ላሉ ተሳፈሪዎች በሙላ እየተናገረ ሌሎችም በትኩረት እያዳመጡ ነበር። ነገር ግን ሰውዬው በጣም ግልጽ ባልሆነ መንገድ ንግግሩን ክፉኛ በማርዘሙ ቀልዱ ምንም አያስቅም። ታድያ ሰውዬው ቀልዶ ሲጨርስ ታክሲ ውስጥ ያሉት ሰዎች በጠቅላላ ፊታቸውን ጥለው ዝም አሉ። ሙላ ግን ሁለቱንም እግሩን አንስቶ ፊቱ እስከሚያልበው ሳቀ።
ይሄኔ ሰውዬው ነስሩዲንን ጠየቀው፦«ነስሩዲን ለምን ሳቅክ?»
ነስሩዲን፦«ሁሌም የምጠቀመው ቴክኒክ ነው። ለምን መሠለህ ለአንድ ሰው ቀልድ ነግሮኝ ካልሳቅኩለት ሁል ጊዜ ቀልዱን ደግሞ የመናገር ብቻ ሳይሆን ቀልዱ ምን እንደሆነ የማብራራት እኔም ደግሞ ደጋግሞ የመስማት አደጋ ውስጥ እገባለሁ።» 🙂
አያችሁ ሰዎች የራሳቸው ምክንያት አላቸው። ሳቅ እንኳን ንግድና ኢኮኖሚያዊ ፖለቲካ ሆኗል። መሳሳቅ አለቅጥ ተበርዞ በሌሎች መዳፍ ስር ንጽህናው አድፏል። ሳቅ በራሱ ሳቅ መሆን አቅቶታል!። በንጹህ መንገድ፣ በቀላል መንገድ፣ ልጅን በመምሰል እንኳን መሳቅ አትችሉም። ታድያ በንጹህ መንገድ መሳቅ ካቃታችሁ እጅግም ጠቃሚ የሆነ ነገር ጎድላችኋል። ድንግልናችሁን፣ ንጽህናችሁን፣ ውበታችሁን እያጣችሁ ነው።
እስቲ አንድ ትንሽ ህፃን ልጅ ተመልከቱ። ሳቁን አስተውሉ በጣም ጥልቅና ከውስጥ የሚመነጭ ነው። አንድ ልጅ ሲወለድ ህጻኑ የሚማረው የመጀመሪያው ማህበራዊ እንቅስቃሴው ያልተበረዘ ነው። ይሄ ከየትም ሳይሆን ከራሱ የሚመነጭ ንጽህና ስለሆነ ሳቁም ለሌሎች ሳቆች ምክንያት ይሆናል። አስተውላችሁ አታውቁም? አንድ ህፃን ልጅ ስታጫውቱና ህፃኑ ሲስቅ እኛም ሳናስበው ፈገግ እንላለን። በዚህ አዲስ ፈገግታ የህብረተሰቡ አካል ሆኖ ይቀላቀላል። በጣም ተፈጥሯዊና ድንገተኛ ይመስላል። ሌሎች ነገሮች ከዛ በኋላ የሚመጡ ነገሮች ናቸው። ህፃኑ ፈገግ ባለ ጊዜም በአለም ውስጥ የመሆኑ የመጀመሪያ ብልጭታ እያሳየ ነው።
አንዲት እናት የልጇን ፈገግታ ስትመለከት በጣም ደስተኛ ትሆናለች። ምክንያቱም ያ ፈገግታ ጤናን ያሳያል፤ ያ ፈገግታ ብልህነትን ያሳያል፤ ያ ፈገግታ የውበት መገለጫ ነው፤ ያ ፈገግታ የልጁን ንጽሁነት፣ የተወደደና ደስተኛ እንደሆነ ያመላክታል።
እናትየው በዚህ ተግባር በቀላሉ ፈገግታ ይሞላታል፤ ደስተኛ ትሆናለች። ይህ የመጀመሪያው ማህበራዊ እንቅስቃሴ ነው። አንድ ሰው መላ ህይወቱን እየሳቀ መሄድ አለበት። በሁሉም ዓይነት ሁኔታዎች ውስጥ መሳቅ ከቻላችሁ እራሳችሁን ብሎም የሌሎችን ትክክለኛ ጎን የምታገኙ ትሆናላችሁ፤ እናም ያ ገጠመኝ 'ማቹሪቲ' ብስለትን ያመጣላችዋል።
ከዛሬ ጀምሮ በፈገግታ ዙርያችሁን ዘውሩ። ሳቃችሁን ለተፈጥሮ አስተጋቡና የሳቅን ተአምራዊ በረከት ተካፈሉ። በማልቀስ ውስጥ እንባ ህመምና እውነት ይወጣል፤ መሳቅ ግን መለኮታዊ አምልኮ እስንፋሳዊ እውነትም ነው።
እኔ አታልቅሱ እያልኩ አይደለም። እንደውም መሳቅ ያቃተው ማልቀስ ፈጽሞ አይቻለውም። ሁለቱ አብረው ይሄዳሉ እነሱ የአንድ ክስተት አካል ናቸው፤ ትኩስ አዲስና እና እውነተኛ መሆን ይገለጥባቸዋል። ነገር ግን መሳቅ ስናቆም እንዴት ማልቀስ እንዳለብን እራሱ አናውቅም። የንጽህና ባዶነት ከለመድነው ባዶነት ፈጽሞ የተለየ ነው። የተለመደው ባዶነት ደስታን ካለማማጣም ሀዘንን ከመልመድ የመጣ ስሜት የለሽ በድንነት ነው። የንጽህና ባዶነት ግን ልክ እንደ ህፃን ልጅ በአንድ የቲቪ ፕሮግራም ቁጭ ብሎ መዝናና ነው።
―The Secret of Secret 📖
@Armemo_officalአንድ ሙስሊም ጓደኛ አለኝ። እና ከጀማው ቀድሞ ያገባው እሱ ነው። በዛ ላይ ቤታቸው ስንሄድ ያላቸው ፍቅርና ሰላም ያስቀናል። ነገር ግን የሆነ ዋጨታ አጫወተኝ። ዋጨታውም ሌላ ተጨማሪ ሴት ለማግባት ማሰቡ ነው። እኔ አልተስማማውም ግን ነፃ ፈቃዱና ከእምነቱ አንፃር ስለሚፈቀድ ጣልቃ ለመግባት አላሰብኩም። ታድያ የዛሬ ሳምንት ይህን ሃሳቡን ለሚስቱ ማሳወቅና ምላሽዋ ምን እንደሆነ ለማወቅ ቀርቦ እንዲህ አላት፦«ሁለተኛ ሚስት ማግባት እፈልጋለሁ?»
ታድያ ከዚህ ጥያቄ በኋላ የመጀመሪያው ቀን አለፈ እናም ምንም የቁጣ መልስ ከሚስቱ አላየም::
ቀጥሎ ሁለተኛው ቀን አለፈ አሁንም ምንም ምላሽ ከእሷ አላየም::
በሶስተኛው ቀን ግን በቀኝ አይኑ ትንሽ ትንሽ ማየት ጀመረ 😓
@Armemo_officalአንድ ሙስሊም ጓደኛ አለኝ። እና ከጀማው ቀድሞ ያገባው እሱ ነው። በዛ ላይ ቤታቸው ስንሄድ ያላቸው ፍቅርና ሰላም ያስቀናል። ነገር ግን የሆነ ዋጨታ አጫወተኝ። ዋጨታውም ሌላ ተጨማሪ ሴት ለማግባት ማሰቡ ነው። እኔ አልተስማማውም ግን ነፃ ፈቃዱና ከእምነቱ አንፃር ስለሚፈቀድ ጣልቃ ለመግባት አላሰብኩም። ታድያ የዛሬ ሳምንት ይህን ሃሳቡን ለሚስቱ ማሳወቅና ምላሽዋ ምን እንደሆነ ለማወቅ ቀርቦ እንዲህ አላት፦«ሁለተኛ ሚስት ማግባት እፈልጋለሁ?»
ታድያ ከዚህ ጥያቄ በኋላ የመጀመሪያው ቀን አለፈ እናም ምንም የቁጣ መልስ ከሚስቱ አላየም::
ቀጥሎ ሁለተኛው ቀን አለፈ አሁንም ምንም ምላሽ ከእሷ አላየም::
በሶስተኛው ቀን ግን በቀኝ አይኑ ትንሽ ትንሽ ማየት ጀመረ 😓
@Armemo_offical