cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

"ቃለ እግዚአብሔር "

"ጥበብን ማግኘት ምንኛ ከወርቅ ይሻላል! ማስተዋልንም ማግኘት ከብር ይልቅ የሚመረጥ ነው።" ምሳ 16 "ሥጋችን ምግብ ሲያጣ እንደሚደክም ሁሉ ነፍስም ምግቧን የእግዚአብሔርን ቃል ስታጣ ትደክማለች።" - ብጹዕ አቡነ ሽኖዳ በመንፈሳዊ ህይወት ዙሪያ ጥያቄ ካላችሁ ለመምህራችን በ @henokasrat3 መላክ ትችላላቹ።

Show more
Advertising posts
8 312
Subscribers
+1124 hours
+137 days
-230 days
Posts Archive
ጥር12 እንኳን  ቃና ዘገሊላ  ታላቅ ክብር በዓል በሰላም አደርሳችሁ አደርሰን አሜን #ቃና ዘገሊላ ምንድነው? ቃና ዘገሊላ በቀጥታ ትርጉም የገሊላዋ ቃና ማለት ነው፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን አስተምህሮ በጥምቀት በዓል ማግስት(ጥር 12) ቀን የቃና ዘገሊላ በዓል ይከበራል፡፡ ይህ በዓል ከጌታ ጥምቀት በዓል ጋር ተያይዞ በድምቀት የሚከበር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዳራ ያለው በዓል ነው፡፡ በዓሉ ቃና ዘገሊላ የሚል ስያሜ ያገኘው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የገሊላ ሀገር ክፍል በምትሆን ቃና በተባለችው ቦታ በፈፀመው ተአምር መነሻነት ነው፡፡ የቃና ዘገሊላ ጥንተ ነገሩ ወይም ታሪኩ የተፈፀመው የካቲት 23 ቀን ነው፡፡ ነገር ግን አባቶቻችን የውኃን በዓል ከውኃ በዓል ጋር ለማክበር ብለው የየካቲቱን በዓል ወደ ጥር 12 አምጥተውታል፡፡ ይህም ውኃ ወደ ወይን የተለወጠበትን በዓል ከጌታ ጥምቀት በዓል ጋር ለማስተሣሠር ለማስኬድ ነው፡፡ በመሆኑም የቃና ዘገሊላ በዓል ጥር 12 ቀን ይከበራል፡፡ በቃና ዘገሊላ ምን ተፈፀመ? ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የገሊላ ክፍል በምትሆን በቃና በተደረገ ሠርግ ላይ ከእናቱ ከድንግል ማርያም ጋር ተገኝቶ ነበር፡፡ ‹‹ወሀለወት ህየ እሙ ለእግዚእ ኢየሱስ›› ‹‹የጌታ የኢየሱስ እናትም በዚያ ነበረች›› እንዳለ ቅዱስ ዮሐንስ በወንጌሉ (ዮሐ 2÷1) እመቤታችን ለሠርገኞቹ ዘመድ ነበረችና ከልጇ ከወዳጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ በሰርጉ ላይ ታድማ ነበር፡፡ እናትን ጠርቶ ልጅን መተው ሥርዓት ስላልሆነ፤ በተጨማሪ ደግሞ ደቀ መዛሙርቱ ከጌታ ጋር በሰርጉ ታድመዋል፡፡ ይህም መምህርን ጠርቶ ደቀ መዛሙርቱን መተው ሥርዓት ስላልሆነ (ተገቢ ስላልሆነ) ነው፡፡ የሠርጉ ሥነ-ሥርዓት በሠመረ ባማረ ሁኔታ እየተከናወነ ሳለ ድንገት የወይን ጠጅ አለቀ፡፡ አስተናባሪዎቹ በጭንቀት ባሕር ሰጥመው ምን እንደሚያደርጉ ግራ በገባቸው በጠበባቸው ጊዜ የችግር ጊዜ ደራሽ የኃዘን ጊዜ አፅናኝ የሆነችው የአምላክ እናት ድንግል ማርያም ቅዱስ ገብርኤል እንደተናገረ በፀጋ የተሞላች ናትና (ሉቃ 1÷28) ማንም ሳይነግራት የልቦናቸውን ጭንቀት አይታ፣ ጎዶሎአቸውን ተመልክታ ወደ ልጃ_ ወደ ወዳጃ_ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘወር ብላ ‹‹ወይንኬ አልቦሙ›› ‹‹ወይን ጠጅ እኮ አልቆባቸዋል›› አለችው፡፡ እርሱም መልሶ ‹‹አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?›› ‹‹ጊዜዬ ገና አልደረሰም›› አላት፡፡ እመቤታችንም ለአገልጋዮቹ ‹‹የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ›› አለቻቸው፡፡ ጌታም በቦታው የነበሩ ስድስት ጋኖች ውኃ ሞልተው እንዲያመጡ አዘዛቸው፡፡ ውኃውንም ወደ ወይን ለውጦ ለሊቀ ምርፋቅ (ለአሳዳሪው) እንዲሠጡት አዘዘ፡፡ አሳዳሪውም ወደ ወይን የተለወጠውን ውኃ በቀመሰ ጊዜ አደነቀ፡፡ ከወዴት እንደመጣ ስላላወቀ ሙሽራውን ‹‹ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል ከሰከሩም በኋላ መናኛውን ያቀርባል አንተ ግን መልካሙን እስከ አሁን አቆይተሃል›› አለው፡፡ ወይኑም በሰው እጅ ያይደለ በሠማያዊው አባት የተዘጋጀ ስለነበር ጣፋጭ እና ልብን የሚያስደስት ነበር፡፡ ‹‹አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?›› ይህንን የጌታችንን ንግግር ብዙዎች በዘመናችን ሲሣሣቱበት ይታያል ፡፡ ክብር ይግባውና አምላካችን ይህንን የተናገረው እናቱን ሊያቃልል ሽቶ አይደለም፡፡ ስለሆነም ከመጽሐፍ ቅዱስ አንፃር ይህን አረፍተ ነገር መመልከቱ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ በተናጠል ስንመለከት ‹‹አንቺ ሴት›› ሴት የሚል ቃል የፆታ መጠሪያ ነውና በፆታዋ አክብሮ ሲጠራት ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሔዋን ከአዳም በተፈጠረች ጊዜ አዳም እንዲህ ሲል ተናግሮ ነበር ‹‹ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት ሥጋም ከሥጋዬ ናት እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል›› (ዘፍ 2÷23) በመሆኑም ጌታ አንቺ ሴት ማለቱ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍስዋ ነፍስ መንሣቱን ለማጠየቅ ነው፡፡ ‹‹ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?›› የሚለውን ዐረፍተ ነገር የንቀት ስለመሰለን ብቻ ‘ የዳቦ መልክ የያዘ ድንጋይ፤ ዳቦ ነው እንደማይባል’ የንቀት ንግግር ነው ልንል አይገባም፡፡ ጌታም እንዲህ ሲል ውኃውን ወይን አድርግላቸው ብትይኝ አላደርግም እልሽ ዘንድ ከአንቺ ጋር ምን ፀብ አለኝ ማለቱ ነው፡፡ ይህ ንግግር በመጽሐፍ ቅዱስ በብዙ ቦታ ተጽፎ እንደሚገኘው በዕብራውያን ዘንድ የተለመደ የአነጋገር ዘይቤ ነው፡፡ አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር  በእናቱ በቅድስት ድንግል አማላጅነት ወኃውን ወደ ወይን እንደ ቀየር ዛሬም የተመሰቃለብን  ህይወታችን  በእናቱ አማላጅነት  በመልካም ጎዳና ይቀርልን  ። ከወላዲት አምላክ ረድኤት በረከት ያሳትፈን አሜን
Show all...
👍 12
06:20
Video unavailableShow in Telegram
👍 3
👉የሆነው ከአእምሮ በላይ ነው ከማመስገን በቀር አንደበት የለንም እግዚአብሔር ይህንን ዓለም ከፈጠረበት ጥበቡ ይልቅ ይህንን ዓለም ያዳነበት ጥበቡ ደግሞ እጅግ ድንቅ ነው። ………….ትንቢተ ኢሳይያስ 9:6……… ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።" በዙፋኑ ሆኖ ማዳን እየቻለ ለሰው ልጆች ያለውን ፍቅር ለመግለጽ ተነግሮ በማያልቅ እና ልዩ በሆነ ልደት ተወልዶ፣ በፈጠረው ፍጥረት መከራ ተቀብሎ፣ በሞቱ ዓለምን ያዳነበት ጥበቡ እጅግ ድንቅ ነው። ቅዱስ ኤፍሬምም ይህንን መግለጫ የሌለውን የጌታችንን ልደት በተናገረበት አንቀጹ «ልዩ ከሆነች ድንግል ማርያም ይህ የአምላክ መወለድ ምን ይደንቅ» ብሎ አድንቆ ጽፏል። በአጠቃላይ እንዳሰበ የሚሠራ እንደፈቀደም የሚያከናውን፣ በሰማይም ሆነ በምድር ከምድርም በታች በሁሉ የሚሠራ፣ በሁሉ የሚያዝ፣በሁሉ ላይ የሠለጠነ፣ የሚሳነው ነገር የሌለ አምላካችን ፣ለሥራው ረዳት አጋዥ አማካሪ የማይሻ፣ ሁሉን ከባሕርይ የሚያከናውን አምላክ ከላይ ሳይጎድል በከብቶች ግርግም መወለዱ፣ ሰማያውያን መላእክት ከምድራውያን እረኞች ጋር ማመስገናቸው የሚያስደንቅ ነው። ቅዱሳት መላእክት «ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ሥምረቱ ለሰብእ» ብለው እንዳመሰገኑት እኛም ዝም ብለን ከማድነቅና ከማመስገን በቀር ምንም አንደበት የለንም። ..............የሉስ ወንጌል 02........... 10 መልአኩም እንዲህ አላቸው፡— እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤ 11 ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና። 👉ለጌታችን እና ለመድሀኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ ልደት በአል እንኳን አደረሳችሁ ዛሬ የደስታ እና የምስጋና ቀናችን ነው በምስጋና ዋሉ🙏 @KaleEgziabeher
Show all...
👍 9
🙏
ቀዳማዊ ልደቱ ጥንትና ፍጻሜ የሌለው የማይመረመር ስለሆነ ቀዳማዊ ልደቱን ለመግለፅ ቅድመ ዓለም ያለ እናት ከአብ እንደ ተወለደ ድኅረ ዓለምም ከእመቤታችን /እንበለ ዘርዓ ብዕሲ/ ያለ አባት ተወለደ፡፡ እሱም እመቤታችን ያለ አባት የወለደችው ፤ እግዚአብሔርም ያለ እናት የወለደው ወልድ ዋሕድ ኢየሱስ ክርስቶስ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ሰባቱ መስተጻርራን /ተቃራኒ ነገሮች አንድ ሆነዋል ሕዝብና አሕዛብ ፤ በጠብና በክርክር ይፈላለጉ የነበሩ ሕዝብና አሕዛብ በጌታችን ልደት ታርቀዋል ፡፡ ይኸውም ሊታወቅ ከዚህ አስቀድሞ ቤተ መቅደሱን ለማፍረስ ንዋየ ቅድሳቱን ለመዝረፍ ሕዝቡን ለመማረክ ምታ ነገሪት ብለው ይመጡ የነበሩ የሩቅ ምስራቅ /የፋርስ የባቢሎን ሰዎች በጌታችን ልደት ምክንያት ወርቅ፣ ዕጣን፣ ከርቤ "አይቴ ሃሎ ዘተወልደ ንጉሠ አይሁድ የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው" (ማቴ.2፥4) እያሉ መጥተው ወርቅ፣ እጣን፣ ከርቤ ገብረውለታል፡፡ ✔  ነፍስና ሥጋ፡- በሲዖልና በመቃብር ተለያይተው የነበሩ ነፍስና ሥጋ ከእመቤታችን ከነፍሷ ነፍስ ከሥጋዋ ሥጋ ነሥቶ በተዋሕዶ ሰው በሆነ ጊዜ ነፍስና ሥጋን አስታርቋል፡፡ ሰውና እግዚአብሔር፡- አባታችን አዳም አትብላ የተባለውን ዕፀ በለስ በልቶ የሰውና የእግዚአብሔር የፍቅር ግንኙነት ለአምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን ተቋርጦ ነበርና ጌታችን የሰውን ሥጋ ተዋሕዶ በተወለደ ጊዜ እርቀ ሰላም ተገኝቷል፡፡ ✔ ሰውና መላእክት፡- አባታችን አዳም ከእግዚአብሔር ጋር በተጣላ ጊዜ ቅዱሳን መላእክትም ስለተጣሉት በምትገለባበጥ ሰይፈ እሳት አስፈራርተው ከገነት ካስወጡት በኋላ ወደ ገነትም እንዳይገባ ገነትን ይጠብቁ ነበር፡፡ ጌታችን በተወለደ ጊዜ አንድ ሆነው ዝማሬ አቅርበዋል፡፡ ይኸውም ዮም አሐደ መርኤተ ኮኑ መላእክት ወሰብእ ከመ ይሰብህዎ ለክርስቶስ እንዲል፡፡ ሰውና መላእክት ክርስቶስን ለማመስገን አንድ ሆኑ እንዳለ ሊቁ፡፡ ✔  ቤተ ክርስቲያን ፤ ጌታችን የተወለደባት እና ሰባቱ መስተጻርራን አንድ የሆኑባት፤ ሰውና መላእክት የዘመሩባት የብርሃን ጎርፍ የጎረፈባት እንስሳት እስትንፋሳቸውን የገበሩባት ቤተልሔም በቤተ ክርስቲያን ትመሰላለች፡፡ ✔  ቤተልሔም፡- ተለያይተው የነበሩ ሕዝብና አሕዛብ ፤ ሰውና እግዚአብሔር ፤ ነፍስና ሥጋ ፤ ሰውና መላእክት አንድ ሆነው በቤተልሔም እንደዘመሩ ዛሬም የፍቅር ተምሳሌትና የአማኞች ሁሉ እናት በሆነችው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በዘር፣ በጎሣ፣ በጥቅም፣ በሥልጣን ሳንከፋፈል አንዲት ቤተ ክርስቲያንን በፍቅር እንድናገለግል በቤተልሔም የተደረገው የልደቱ ምሥጢር ይህን ያስተምረናል፡፡ ክርስቲያኖች የጌታን መወለድ የምናስበው በዚህ መንፈስ ነው፡፡ መልካም የልደት በዓል ይሁንልን አሜን !!!       ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖❖ ❖ ❖   💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫            ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ የልደት በዓል ማኅሌት  ❖ ❖ ❖            ❖ ❖ ❖ ዚቅ ❖ ❖ ❖ ርእይዎ ኖሎት አእኮትዎ መላእክት ፤ ለዘተወልደ እማርያም እምቅድስት ድንግል፤ ዮም ሰማያዊ በጎል ሰከበ፡፡ ትርጉም፦ ቅድስት ድንግል ከሆነች ማርያም የተወለደውን እረኞች አዩት መላእክትም አመሰገኑት፤ እነሆ ዛሬ ሰማያዊው በበረት ተኛ፡፡           ❖ ❖ ❖ ንግሥ ❖ ❖ ❖ ሰላም ለልደትከ ኦ አማኑኤል፤ ዘቀዳሚ ወዘደኃሪ ብሉየ መዋዕል፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘአብ ቃል፤ እፎ እፎ አግመረተከ ድንግል፤ ወእፎ እንዘ አምላክ ሰከብከ በጎል፡፡ ትርጉም፦ በዘመናት የሸመገልክ መጀመርያና መጨረሻ የሆንክ አማኑኤል ሆይ ለልደት ሰላም እላለሁ የአብ ቃል የሆንክ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ድንግል እንዴት ተሸከመችህ? አምላክስ ስትሆን እንዴት በበረት ተኛህ?           ❖ ❖ ❖ ዚቅ ❖ ❖ ❖ በጎል ሰከበ በአፅርቅት ተጠብለለ፤ ውስተ ማኅፀነ ድንግል ኀደረ፤ እፎ ተሴሰየ ሐሊብ ከመ ሕፃናት፡፡ ትርጉም፦ በበረት ተኛ በጨርቅም ተጠቀለለ፤ በድንግል ማኅፀንም አደረ፤ እንደ ሕፃናት ወተትን እንዴት ተመገበ?         ❖ ❖ ❖ መልክአ ኢየሱስ ❖ ❖ ❖ ሰላም ለአፅፋረ እዴከ ዘሕበሪሆን ጸዓዳ... ትርጉም፦ቀለማቸው ነጭ ለሆኑት የእጆችህ ጥፍሮች ሰላም እላለሁ.....          ❖ ❖ ❖ ዚቅ ❖ ❖ ❖ አንፈርዓፁ ሰብአ ሰገል ፤ አምኃሆሙ አምፅኡ መድምመ ፤ ረኪቦሙ ሕፃነ ዘተወልደ ለነ፡፡ ትርጉም፦ሰብአ ሰገል የተወለደልንን ሕፃን አገኙ በደስታም ዘለሉ ስጦታቸውንም አመጡ፡፡         ❖ ❖ ❖ ምስባክ ❖ ❖ ❖ ዲያቆኑ በቅኔ ማኅሌቱ  "መዝ 71:10" ይሰብካል። “ነገሥተ ተርሴስ ወደሴያት አምኃ ያበውዑ ፤ ነገስተ ሳባ ወዓረብ ጋዳ ያመፅኡ ፤ ወይሰግዱ ሎቱ ኩሎሙ ነገሥተ ምድር ፡፡ ትርጉም፦ የተርሴስና የደሴቶች ነገሥታት ስጦታን ያመጣሉ የዓረብና የሳባ ነገሥታት እጅ መንሻን ያቀርባሉ! ነገሥታት ኹሉ ይሰግዱለታል። አሕዛብም ኹሉ ይገዙለታል፡፡         ❖ ❖ ❖ ምልጣን ❖ ❖ ❖ መዘምራን (መሪጌቶች) መሪና ተመሪ ኾነው የሚዘምሩት ሲኾን በመቀጠልም ኹሉም በኅብረት እየደጋገመ የሚዘምረው ነው! እንዲህ ይላል..... ዮም ፍስሐ ኮነ በእንተ ልደቱ ለክርስቶስ ፤ እም ቅድስት ድንግል ውእቱ ኢየሱስ ክርስቶስ፤ ዘሎቱ ሰብአ ሰገል ሰገዱ ሎቱ፤ አማን መንክር ስብሐተ ልደቱ፡፡ ትርጉም፦ እነሆ ዛሬ በክርስቶስ ልደት ምክንያት ደስታ ኾነ ከቅድስት ድንግል የተወለደው እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ለእርሱ ሰብአ ሰገል ሰገዱለት! በእውነት የልደቱ ምስጋና ድንቅ ነው፡፡           ❖ ❖ ❖ እስመ ለዓለም ❖ ❖ ❖ ተወልደ ኢየሱስ በቤተልሔም ዘይሁዳ፤ አዋልደ ጢሮስ አሜሃ ይሰግዳ፤ ሰብአ ሰገል አምፅኡ ሎቱ ጋዳ፤ ወይትኃሠያ አዋልደ ይሁዳ ፡፡ ትርጉም፦ኢየሱስ በይሁዳ ቤተልሔም ተወለደ፤ የጢሮስ ሴቶች ልጆችም በዚያ ይሰግዱለታል፤ ሰብአ ሰገል እጅ መንሻን አመጡለት፤ የይሁዳ ሴቶች ልጆችም ደስ ይላቸዋል፡፡          ❖ ❖ ❖ ዑደት ❖ ❖ ❖ “ኹላችንም በልደቱን ብርሃን በማሰብና ጧፍ በማብራት "ሥዕለ አድኅኖ" ይዘው ከሚዞሩት ካህናት በስተኋላ ተሰልፈን እንዲኽ ይኼንን ዝማሬ እናቀርባለን! “አማን በአማን አማን በአማን፤ መንክር ስብሐተ ልደቱ ፡፡ ትርጉም፦እውነት በእውነት እውነት በእውነት፤ የልደቱ ምስጋና ድንቅ ነው፡፡          ❖ ❖ ❖ ዕዝል ❖ ❖ ❖ በጎል ሰከበ በአፅርቅት ተጠብለለ፤ ውስተ ማኅፀነ ድንግል ኃደረ፤ ዮም ተወልደ እግዚእ ወመድኅን ቤዛ ኩሉ ዓለም፡፡ ትርጉም፦ በበረት ተኛ በጨርቅም ተጠቀለለ ፤ በድንግል ማኅፀን አደረ፤ የዓለም ኹሉ ቤዛ የኾነው ጌታና አዳኝ ዛሬ ተወለደ፡፡         ❖ ❖ ❖ ሰላም ❖ ❖ ❖ ተስሃልከ እግዚኦ ምድረከ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ ንሰብክ ወልደ እም ዘርዓ ዳዊት ዘመፅአ ወተወልደ በስጋ፤ ሰብእ እንዘ ኢየአርቅ እመንበረ ስብሐቲሁ፤ ውስተ ማኅፀነ ድንግል ኃደረ ስጋ ኮነ ወተወልደ፡፡ ትርጉም፦ ጌታ ሆይ ምድርህን ይቅር አልክ ሃሌ ሉያ ከዳዊት ዘር የመጣውንና በሥጋ የተወለደውን ወልድን እንሰብካለን ከምስጋናው ዙፋን የማይራቆት ሰው ነው! በድንግል ማኅፀን አደረ ሥጋ ኾኖም ተወለደ፡፡ የሚቀደሰው ቅዳሴ   ☞    "ቅዳሴ ጎርጎርዮስ ካልእ" የቅዳሴው ምስባክ   ☞ መዝ 71:15 ፤ የሚነበበው ወንጌል  ☞ ሉቃ2:1-21     💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
Show all...
👍 5
ወንድም እህቶቼ እንኳን አደረሳችሁ 🙏🙏🙏🙏ይህንን ያውቃሉ🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 ❖ ❖ ❖እነሆ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኀኒት ተወልዶላችኋል ሉቃ.2፥11   ❖ ❖ ❖      ❖ ❖ ❖ እንኳን ለጌታችን ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡  ❖ ❖ ❖ 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹        ❖ ❖ ❖ " ጌና" ❖ ❖ ❖ ጌና እና ልደት {ዋዜማና ክብረ በዓል } /የተለያዩ ቀናት/ ቢኾኑም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን ጌና ልደትን እየተካ እንጠቀምበታለን ፤ ነገር ግን ይህ ሊስተካከል ይገባዋል፡፡ ልዩነት ስላለውም የኢትዮጵያ ብርሃን የተባለው አፈ ጳዝዮን አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ለጌናና ለልደት ለ2ቱም በዓላት ለየብቻቸው በመጽሐፈ ምሥጢር ድርሰት ደርሶላቸዋል፡፡ #ጌና ፤ የልደት በዓል ዋዜማ ቀን ሲኾን በዚህ ቀን ‹‹በገና ጨዋታ አይቆጡም ጌታ›› የተባለለትን ‹‹የገና ጨዋታ›› እንጫወታለን፤ የምንጫወትበት የኳሱ ስያሜ ‹‹ሩር›› ሲባል ስያሜውን ያገኘው፤ ሰብዓ ሰገል እልፍ እልፍ ሠራዊት አስከትለው የተወለደውን የአይሁድ ንጉሥ ፍለጋ ወደ ንጉሡ ሔሮድስ ደርሰው ነበርና ፤ ሔሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ፈልጎና በውስጡ ሸሽጎ ለሰብዓ ሰገል ሂዱ ሕፃኑን ፈልጉ ስታገኙትም ንገሩኝ ብሎ ሰድዷቸዋል ፤ ነገር ግን በዚያው ሳይነግሩኝ እንዳይሄዱ በማለት እነርሱ ሳያውቁ  ‹‹ሩር›› የተባለ ሰላይ በመሃላቸው አስገብቶ ነበርና ሰብዓ ሰገልን ይመራቸው የነበረው ኰከብ ተሠውሮባቸዋል ፤ ሰብዓ ሰገል ሠራዊታቸውን ቢያጣሩ ከመሃከላቸው የተቀላቀለ ሩር የተባለ የሔሮድስን ሰላይ አገኙ ይህንንም ሰላይ የሰብዓ ሰገል ሠራዊት አንገቱን በሰይፍ ቀልተውታልና ያን ለማስታወስ ዛሬ በገና ጨዋታ ላይ ሩር የተባለው ኳስ የሔሮድስ ሰላይን ‹‹ሩር›› እንዲያስታውስ አባቶች ሥርዐትን ሠሩ፡፡      ❖ ❖ ❖ የጌታችን የመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ❖ ❖ ❖ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውኃ ፈሳሽ አይደለም፡፡ ከጥንት ከመሠረት ጀምሮ በመላእክት ፤ በነቢያት ሲነገር ፤ ሲሰበክ የመጣ ነው እንጂ፡፡ ማቴ.1፥18፡፡ ሰው የመሆኑን ምሥጢር ለመጀመሪያ ጊዜ በማዕከለ ገነት የተናገረ እርሱ እግዚአብሔር ነው፡፡ አባታችን አዳም ከእግዚአብሔር ትዕዛዝ ወጥቶ ዕፀ በለስን በልቶ ከጸጋ እግዚአብሔር በተራቆተ ጊዜ /አዳም ኮነ ከመ አሐዱ እምኔነ/ አዳም ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ ዘፍ.3፥22 ብሎ ከሦስቱ ቅዱስ አንዱ ቅዱስ እግዚአብሔር ወልድ በተለየ አካሉ ከእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው እንደሚሆን ተናግሯል፡፡ በዚህ ቃል መሠረት /መሪነት/ ቅዱሳን መላእክት ምሥጢረ ትንቢት ተገልጾላቸዋል፡፡ እነሱም የተገለጸላቸውን ምሥጢረ ትንቢት ኀላፍያትንና መጻእያትን ለሚናገሩ ነቢያት ነግረዋቸዋል፡፡ ቅዱሳን ነቢያትም ከእግዚአብሔር ያገኙትን ከመላእክት የሰሙትን መነሻ አድርገው በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ ምሳሌያት በተለያዩ ዘመናት የወልደ እግዚአብሔርን ሥጋዌ ሰብከዋል /ገልጸዋል/ ዕብ.1፥1፡፡ ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ ፥ ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን፡፡     ✔ የጌታችን ልደት በትንቢተ ነቢያት ፦ 👉 ከዓበይት ነቢያት መካከል አንዱ የሆነው ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ የሚከተለውን ትንቢት ተናግሯል፡፡ "እነሆ ድንግል በድንግልና ፀንሳ በድንግልና ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች ( ኢሳ.7፥14፣ ሕዝ.44፥1) ፡፡ በኅቱም ድንግልና ተፀንሶ በኅቱም ድንግልና የተወልደው አማኑኤል ጌታ ነው፡፡ ትርጉሙም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ ማለት ነው፡፡ነቢዩ በጎላና በተረዳ ነገር “ሕፃን ተወልዶልናል ወልድ ልጅም ተሰጥቶናል አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፡ ስሙም ድንቅ መካር ኀያል አምላክ የዘለዓለም አባት የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል“ በማለት የሚወለደው ሕፃን የባሕርይ አምላክ የዘለዓለም አባት የሰላም አለቃ ሥልጣን የባሕርይ ገንዘቡ እንደሆነ እና ለሥልጣኑም ወሰን ድንበር እንደሌለው ተናግሯል፡፡ 👉 ከደቂቀ ነቢያት መካከል አንዱ ሚልክያስም በቤተልሔም ስለመወለዱ፡- "የኤፍራታ ምድር አንቺ ቤተልሔም ከይሁዳ አለቆች ከቶ አታንሽም ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ ንጉሥ ከአንቺ ይወጣልና" (ሚክ.5፥2፣ ማቴ.2፥6) ብሏል፡፡ 👉• ነቢየ እግዚብሔር ቅዱስ ዳዊትም "እነሆ በኤፍራታ ሰማነው ዛፍ በበዛበትም ቦታ አገኘነው እንግዲህስ ወደ እግዚአብሔር ማደሪዎች እንገባለን ብሎ የወመለዱን ምሥጢር ተናግሯል" (መዝ.131፥6) 👉• ነቢዩ ዕንባቆምም "አቤቱ ድምፅህን ሰምቼ ፈራሁ ሥራህንም ዐይቼ አደነቅሁ በሁለት እንስሶች መካከል አየሁህ ዘመኑ እንደደረሰ አድርጌ አውቅህአለሁ ዘመኑም በደረሰ ጊዜ ተገለጥክ" ብሎ በቤተልሔም በረት በተወለደ ጊዜ አድግና ላኅም እስትንፋሳቸውን እንደሚገብሩለት (ዕንባቆም 3፥1) ተናግሯል፡፡ ከዚህ በኋላ የዘመኑ ፍጻሜ ሲደርስ እግዚአብሔር መልአኩን ቅዱስ ገብርኤልን ወደ ድንግል ማርያም በመላክ አብሥሯታል፡፡ “ማርያም ሆይ፥ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋ አግኝተሻልና አትፍሪ። እነሆም፥ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ።እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፥ ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል" በማለት፡፡ ሉቃ. 1፡32 እመቤታችንም በብዙ ኅብረ አምሳል ትንቢት ሲነገርለት፤ ምሳሌ ሲመሰልለት፤ ሱባኤ ሲቆጠርለት የነበረውን ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በቤተልሔም ግርግም  ወለደችው፡፡ ይህንንም ብስራት በቤተልሔም ዋሻ መንጋቸውን ነቅተውና ተግተው ይጠብቁ ለነበሩ እረኞች መጋቤ ሐዲስ አብሣሬ ትስብዕት ቅዱስ ገብርኤል ፤ እነሆ ዛሬ መድኀኒት በዳዊት ከተማ ተወልዶላችኋል ይኸውም ቡሩክ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ የሚያርቅ በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስ የሚያድል ከዓለም በፊት ንጉሥ የነበረ ዛሬም ከዳዊት ባሕርይ /ዘር/ በቤተልሔም ዋሻ ዓለምን ለማዳን የተወለደ የዳዊት ልጅ ንጉሠ ነገሥት ኢየሱስ ክርስቶስ ተወለደ ሲል አበሰራቸው፡፡ (መዝ.73፥12) 💥 የጌታችንን ልደት ስናነሣ ሁለት ልደታት እንዳሉት እናምናለን፡፡ እኒሁም ልደታት /ልደት ቀደማዊና/ /ልደት ደኃራዊ/ ናቸው፡፡ ✔ ልደት ቀዳማዊ ፦ ቅድመ ዓለም ከአብ አካል ዘእም አካል ባሕርይ ዘእም ባሕርይ ከእግዚአብሔር አብ ያለ እናት የተወለደው ልደት ሲሆን /ነቢዩ ዳዊት እንዲህ ይገልጸዋል፡፡ "ወለድኩከ እምከርሥ እምቅድመ ኮከበ ጽ ባህ መዝ.109፥3 ከአጥቢያ ኮከብ አስቀድሞ ወለድኩህ ፤አንተ ልጄ ነህ እኔም ዛሬ ወለድኩህ" (መዝ.2፥7)   ✔ ልደት ደኃራዊ ፦ አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን ሲፈፀም በዕለት ሐሙስ ወበመንፈቃ ለዕለት እትወለድ እምወለተ ወለትከ እንዲል ቃሉ፡፡ ቅድስት ድንግል ከምትሆን ከእመቤታችን እንበለ ዘርዓ ብዕሲ ያለ አባት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሔም የተወለደው ልደት ነው፡፡
Show all...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
👍 12
Show all...
👍 2
+++ የአንድ ኃጢአተኛ ሰው ጸሎት ++ ( ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ ) አቤቱ “በጎውን ነገር ማን ያሳየናል?” የምንልበት ዘመን አይደለም፤ እንኳን በእኛ ዘንድ ይቅርና ወንጌል በአሕዛብ ዘንድ ሳይቀር የተሰበከበት ዘመን ነውና። ነገር ግን የተሰበከውን ቃል በልቤ አኑሬ ሕይወቴን ሳልለውጥበት ብዙ ዘመናትና ዓመታት አለፉ። ቃልህን ሰምቶ አለማድረግ በአንተ መዘባበት መሆኑን አውቃለሁ፤ ቃልህን የምሰማ እንጅ የምፈጽም ባለመሆኔም ምክንያት በድቡሽት ላይ እንደተሠራ ቤት ሆኛለሁ። ጥልቀት በሌለው አኗኗር ላይ የተገነባው መንፈሳዊነቴ ጎርፍ በጎረፈ፣ ነፋስ ባለፈ ጊዜ የሚናወጥ ደካማ ሆኖብኛል። ዓለምን ለማሳለፍ ዳግመኛ መምጣትህን ባሰብሁ ጊዜ እደነግጣለሁ። ጻድቃን “አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ቶሎ ና” እያሉ የምትመጣበትን ቀን ሙሽራዋን እንደምትጠብቅ ሴት በተስፋ ይጠባበቃሉ፤ እኔ ግን አሁንም ለንስሐ ዕድሜ እንድትጨምርልኝ እለምናለሁ። ለንስሐ ብየ የለመንሁትን ዕድሜ አሁንም ማለቂያ ለሌለው ፍላጎቴ ባውለውም አንተ ግን የለመንሁትን ዕድሜ ሰጥተህ አጠገብኸኝ። ሰው ምን ቢቸግረው ነው የሠርጉን ቀን የሚያራዝመው? የደስታ ቀኑ እንዳትደርስ የሚከላከል ሰው ማለት እኔ ነኝ። አንተ የምትመጣበት ቀን ከዓለም አስቀድሞ ያጨኻትን የጻድቃንን ነፍስ እንደ ሴት ሙሽራ በአፍህ መሳም ስመህ መኃ 1፥2 የምትቀበልበት ቀን ነው። ፀሐይና ጨረቃ በማያስፈልጓት ከተማ ለመኖር ጻድቃን ራሳቸው እንደ ፀሐይና ጨረቃ የሚያበሩበትን ያንን ቀን በቶሎ እንዲመጣ አለመለመን እንዴት ያለ ሞኝነት ነው? ያንጊዜ ታላቅ ደስታ ይደረጋል፤ ሙታንን የሚያነቃቸው ታላቁ ዝማሬ በሰማያውያን መላእክት ይጀመራል፤ መላእክት “ቅዱስ እግዚአብሔር” ሲሉ ምድራውያን ጻድቃንም “ቅዱስ ኃያል.......” እያሉ ያንን ዝማሬ ሊቀበሉ ከመቃብራቸው ይወጣሉ። ሞት ያንን ምስጋና ሰምቶ ይደነግጣል። ዲያብሎስ ይገሠጻል። በእውነት የዚያን ቀን የሚደረገው ተድላ ደስታ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ እስካሁን አልተደረገም። እመቤታችን “ተፈሥሒ” የሚለውን የምስጋና ቃል በሰማች ጊዜ ያገኘችውን ደስታ ጻድቃን ያንጊዜ ያገኙታል። ያችን የደስታ ቀን ባለመዘጋጀቴ መድረሷን እየቸኮሉ ከሚጠባበቁት ውስጥ አይደለሁምና አዝናለሁ። ጌታዬና አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! ያንን ቀን በደስታ እንድጠብቅ እንጅ ባሰብሁት ጊዜ ከመደንገጥ አውጣኝ። አውቃለሁ ጌታዬ ዛሬ ቃልህን ሰምተው ደስ የማይላቸው ሰዎች ያንጌዜ “ንዑ ኀቤዬ” የሚለውን ቃልህን ሰምተው ደስ አይላቸውም። ያንጊዜም ደስታን የሚሰጠን ዛሬ የምንሰማው ቃልህ ነው። ይህንንማ በመካከላችን ስብከትን በጀመርህባት ቀን “መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ” ባልኸን ጊዜ ገልጠህልን ነበር። መንግሥተ ሰማያት ብለህ የጠራሃት ቃልህን መሆኑን መምህራኖቻችን፥ “መንግሥተ ሰማያት፡− ሕገ ወንጌል፣ ሕገ ወንጌል፡− ተስፋ፣ ተስፋ፡− እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው” ብለው ተርጉመው ነግረውን ተረድተን ነበር። መንግሥተ ሰማያትን በመካከላችን ያኖርህልን ሆይ! ቃልህን በሰሙ ጊዜ የማር ወለላ እንዳቀረቡላቸው ሕጻናት ሳስተው እንደሚሰሙህ ወዳጆችህ እንድሆን እርዳኝ። ደፍሬ ስምህን መጥራቴን ሳስብ አንዳንድ ጊዜ ፍርሃት ይይዘኛል፤ ደግሞ “ሰውን የምትወድ ሆይ” ብለው ካህኑ በቅዳሴ ጊዜ ሲጠሩህ ስሰማ ፍርሀቴን ያርቅልኛል። አንተ በምትከብርበት መቅደስ ውስጥ ገብቼ መቆሜንም ሳስብ በቅዱሳን ጉባኤ መካከል የአንድ ኃጢአተኛ የእኔ መገኘት ያስጨንቀኛል፤ ነገር ግን ካህኑ በቅዳሴው መካከል “ወንጌል” ብለው ወጥተው “ኃጥአንን ለንስሐ እንጅ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም” የሚለውን ቃልህን ሲያነቡ በሰማሁ ጊዜ በሰጠኸኝ ዕድል ድምጼን ከፍ አድርጌ አመሰገንሁህ። ሰዎች እስኪገርማቸው ድረስ በእኔ በቀራጩ ቤት መዋልህ ለምንድነው? በፊትህ በድለው ከማያውቁ መላእክት ይልቅ የእኔን ምስጋና ለመስማት መምጣትህ ለምንድነው? ሰውን መውደድህ ያስደንቃል! ከተግሣጽህ ይልቅ ፍቅርህ ማርኮኝ መጥቻለሁ። ደዌ ከጸናበት ሰው በቀር ሀኪሙን በብርቱ ፍለጋ ማን ይፈልገዋል? እኔም ደዌ ነፍስ ቢጸናብኝ ኃጢአት ቢያስጨንቀኝ መጥቻለሁና ፈውሰኝ። ላገለግልህ ብወድም እንደ ሐማተ ጴጥሮስ ሳልፈወስ ላገለግልህ አልፈቀድሁም። ለአንተ ምን ይሳንሃል? ከለምጼ ልታነጻኝ ብትወድ ይቻልሃል። ከአልጋዬ ልታነሣኝ ብትወድስ ማን ይከለክልሃል? ፈውሰኝና ዕድሜዬን በሙሉ አገልጋይህ አድርገኝ። ሳልፈወስ ባገለግል ደዌዬ ወደ ሌሎችም እየተዛመተ ብዙዎችን ይበክላል። ይሁዳ ባዛመተው ገንዘብ መውደድ፣ አፍኒንና ፊንሐስ በጀመሩት የመቅደስ ውስጥ ድፍረት፣ ዳታንና አቤሮን ባቀጣጠሉት ዘረኝነት፣ ሲሞናውያን ባሳዩት ጉቦኛነት ተይዘው ያልተፈወሱ ብዙ ናቸው፤ የእኔም ተጨምሮ የፈውስ ጊዜአችንን እንዳያርቅብን ስለምፈራ ፈውሰኝና አገልጋይህ ልሁን። እኔ ሥጋህንና ደምህን የምቀበለው ዝቅ ብለህ አጥበህ እንዳነጻሓቸው እንደ ሐዋርያት ንጹሕ ሆኜ አይደለም፤ እንዲያውም ስቆርብ ያዩኝ ሰዎች ገርሟቸው “ይሄ ኃጢአተኛ ሰው ቆራቢ ለመባል ብሎ ነው እንጅ አምኖበት ነው?” ብለው ተሳለቁብኝ። በሽታ የጸናበት ሰው መድኃኒቱን የሚወስደው ደዌው እንዲለቀው እንጅ ደዌው ከለቀቀው በኋላ ነውን? እኔስ ይህ ቍርባን ፈራጅ እንደሆነ ባውቅም ማኅየዊ እንደሆነም አምናለሁ። ሐዋርያት “የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል” 1ዮሐ 1፥7 ብለው ያስተማሩት ትዝ ይለኛል። የምትፈርድብኝ ፍርድ ሳይሆን “እንካችሁ ብሉ ሥጋዬን፣ እንካችሁ ጠጡ ደሜን” ብለህ ወደ እኔ የዘረጋሃት እጅህን አያታለሁ። ስለዚህም አፌን ከፍቼ እቀበልሃለሁ። ዛሬ “በምሕረትህ ብዛት ወደ ቤትህ እገባለሁ አንተን በመፍራትም ወደ ቅድስናህ መቅደስ እሰግዳለሁ” ዳግመኛ በምትመጣ ጊዜም በምሕረትህ ብዛት በሚያስፈራና በሚያስደነግጥ ዙፋንህ ፊት እቆማለሁ። ጭብጥ አፈር ወደ ባሕሩ ቢወረወር ባሕሩን ያደፈርሰዋልን? የእኔ የኃጢአተኛው ወደ መቅደስህ መግባትስ ያንተን ባሕርይ ያሳድፈዋልን? በእውነት በስምዖን ቤት መዋልህ ስምዖንን ያነጻዋል እንጅ አንተን አያረክስህም። ማርያም ኃጥዕት እግርህን ያጠበችበት እንባ እሷን አነጻት እንጅ አንተን አላረከሰህም። ደም የሚፈሳት ሴት ልብስህን በመንካቷ ካንተ የወጣው ኃይል እሷን ጎበኛት እንጅ አንተን አልለወጠኸም። እኔም ወደ ቤትህ የምገባው ይህንን እያሰብሁ ነው። በተራራው ስብከት ጊዜ ተገኝቼ ስታስተምር ባልሰማህም፤ በደብረ ታቦር በተገለጥህ ጊዜ ክብርህን ካዩት መካከል ባልሆንም፤ በደብረ ዘይት እጅህን ጭነህ ከሾምኻቸው ውስጥ ባልመደብም አንተ ግን ለእኔ ምሕረት ማድረግን አትሰለችም። ወደ አንተ ባልመጣ እንኳን በተኛሁበት መጥተህ “ልትድን ትወዳለህ?” ማለትህ አይቀርም። ከሰማይ የወረድህልኝ ሆይ! ኢያሱ ለእስራኤል ርስታቸውን እስኪያወርሳቸው ፀሐይን እንዳቆምህለት በምድር ላይ ያለን ኃጥአን ልጆችህ ሰማያዊት ርስትህን ሳንወርሳት ፀሐይ አትጥለቅብን፤ ዕድሜአችን አይለቅብን። አሜን! @ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ
Show all...
👍 23
በጣም ልብን የሚነካ ነው እባካችሁ አንብቡት።
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
👍 14
🍂 + #ቅድስት_አርሴማ_ሰማዕት + 🍀 ታህሳስ 6 ቅዳሴ ቤቷ 🍂 የቤተክርስቲያኗም ቅዳሴ ቤት በአርማንያ ሀገር ፣ በኪልቂያ ፣ በሶርያ ፣ በአንጾኪያና በግብጽ አውራጃዎች ሁሉ በታኅሳስ ወር በ6ኛው ቀን ሆነ ። አባቷ 🍂 ቴዎድሮስ እናቷ 🍂 አትናስያ ይባላሉ በስዕለት የተገኘች እነደሆነች ቤተሰቦቿ በ3 ዓመቷ ወደ ቤተ እግዚአብሔር ዘንድ ወስደዋታል በዚያም የሐይማኖትን ትምህርት መጻሕፍተ ሐዲሳትንም እየተማረች በጾም በጸሎት በስግደት ተወስና ፣በቤተ ክርስቲያን አድጋለች ። ዕድሜዋም ሲደርስ ቤተሰቦቿም ቢድሯትም የዚህን ዓለም ከንቱነት ስለተረዳች ራሷን ለክርስቶስ ሙሽራ አድርጋ ወደኋላ ምናኔው ሕይወት ገብታለች። በመስከረም 29 ቀን አንገቷን ተሰይፋ የሰማዕትነት አክሊልን ተቀዳጅታለች። ከእርሷም ጋር በሐይማኖት በገድል ጸንተው የሚኖሩ ሃያ ሰባቱ ቅዱሳን አብረዋት ሰማዕት ሆነዋል። 🍂 የቤተክርስቲያኗም ቅዳሴ ቤት በአርማንያ ሀገር ፣ በኪልቂያ ፣ በሶርያ ፣ በአንጾኪያና በግብጽ አውራጃዎች ሁሉ በታኅሳስ ወር በ6ኛው ቀን ሆኗል። ጌታችን ከገባላት ብዙ ቃልኪዳን ውስጥ አንደኛው " #ልጁን_በአንቺ_ስም_የጠራውን_በመንግስተ_ሰማያት_የበለጠና_የከበረ_ስምን_እኔ_እሰጠዋለው ።" የሚል ነው ። ✨ የሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ረድኤት ከሁላችን ጋር ይሁን✨ በቃልኪዳኗ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ትሰውረን 🙏🏾 🙏🏾 🙏🏾
Show all...
👍 14
ታህሳስ ፫ በታዕካ ነገስ በዓታ ማርያም ታላቋ ገዳም እንገና           ።።።።   እንኳን አደረሳሽሁ።፡።።።። ✝️እንኳን ለእናታችን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ዕለት (በዓታ ማርያም ውስተ ቤተ መቅደስ) ዓመታዊ መታሰቢያ ታላቅ የንግሥ ክብረ በዓል በሰላም በጤና አደረሰን፤ አደረሳችሁ። ✝️ታህሳስ ፫ በአታ ለእግዝእትነ ማርያም ውስተ ቤተመቅደስ “እበውዕ ቤተከ ምስለ መባእየ” ፤ “ከመባዬ ጋራ ወደ ቤትህ እገባለሁ።” መዝ. ፷፭(፷፮)፥፲፫ እመቤታችን አባቷ ኢያቄም እናቷ ሐና ይባላሉ። በፈቃደ እግዚአብሔር በብስራተ መልአክ ወልደዋታል። የብፅዓት ልጅ ናትና ሶስት ዓመት ሲሆናት ይህች ልጅ አንድ ነገር ብትሆን ከእግዚአብሔርም ከልጃችንም ሳንሆን እንዳንቀር ሆዷ ዘመድ ሳይወድ አፏ እህል ሳይለምድ ወስደን እንስጥ ብለው መባዕ ጨምረው ወደ ቤተመቅደስ ይዘዋት ሄዱ። ሊቀ ካህናቱ ዘካርያስ መጥቅዕ መጥቶ ሕዝቡን ሰብስቦ የምግቧ ነገር ይያዝልኝ አለ። ወዲያው ሊቀ መላእክት ቅዱስ ፋኑኤል ኅብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ሰማያዊ ይዞ ረቦ ታየ። ዘካርያስ ለእርሱ የመጣ መስሎት ዛሬስ ክብሬን በሰው ፊት ሊገልጸው ነው ብሎ ሊቀበል ተነሣ። መልአኩ ወደ ላይ ራቀበት። የእርሱ ተወራጅ ስምዖንም እንኪያስ ለእኔ የመጣ ይሆናል ብሎ ቀረበ። ራቀበት። ካህናቱም ሕዝቡም በተራ ቢቀርቡ ራቀባቸው። ምናልባት ጥበበ እግዚአብሔር አይመረመርም ለዚህች ብላቴና የመጣ እንደሆነ እንይ ሐና ትተሻት እልፍ በይ አሏት። ትታት እልፍ አለች። ድክ ድክ እያለች እናቷን ስትከተል መልአኩ ፈጥኖ ወርዶ አንድ ክንፉን አንጽፎ አንድ ክንፉን ጋርዶ በሰው ቁመት ልክ ከመሬት ከፍ አድርጎ መግቧት ዐረገ። የምግቧ ነገር ከተያዘልንማ ትግባ እንጁ ብለው ከመካነ ደናግል አስገቧት። “ከመዝ ነበርኪ ውስተ ቤተ መቅደስ ወመላእክት ያመጽኡ ወትረ ሲሳየኪ ከመዝ ነበርኪ ዐሠርተ ወክልዔተ ዓመተ እንዘ ትትናዘዚ እምኀበ መላእክት” ይላል። ኅብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ሰማያዊ እየተመገበች መላእክት  እየጎበኟት ፲፪ ዓመት በቤተ መቅደስ ኖራለች። የእናታችን ምልጃና ጸሎት አይለየን፤ ረድኤት በረከቷን ያሳድርብን፤ ከበዓሏ በረከትም ያሳትፈን። የዓመት ሰው ይበለን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር። ታህሳስ 3 ቀን 2016 ዓ.ም
Show all...
👍 8
ይህ መርሐ ተዋህዶ ቻናል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መንፈሳዊ ትምህርቶች የመፅሀፍ ቅዱስ ታሪኮች በቪድዬ እና በጣም ውብ በሆነ ገለፃ የሚቀርቡበት ቻናል ነው። እባካችሁ ለሌሎችም ሼር አድርጉ እናንተም ተከታተሉት። ብዙ እውቀት ታገኙበታላችሁ።
Show all...
#ሆድ_አምላክ_ይሆናልን? የሰው ልጅ ወደድኳቸው በሚላቸው ነገሮች ሕይወቱ ይወሰናል። ሰይጣንም በምንወዳቸው ነገሮች ቀዳዳ በኩል ገብቶ ነው በውንብድና የጸጋችንን መዝገብ የሚበረብር። ለእግዚአብሔርም ያለንን ፍቅር የምንገልጠው በምንወዳቸው ነገሮች ነው። እርሱ አንድ ልጁን በመስጠት ፍቅሩን እንደገለጠልን እኛም የምንወዳቸውን ለእግዚአብሔር ብለን ይቅርብን ብለን በመተው በዚህ ፍቅራችንን እንገልጣለን። የምንወዳቸው ሁሉ በእግዚአብሔር ፍቅር ፋንታ ከገቡብን፥ እነዚያ በእርግጥ የምንወዳቸው ነገር ግን በፍቅረ እግዚአብሔር የተካናቸው የወዳጅ ጠላት የሆኑበትን ጠዖታት ናቸው። ከእነዚህም ሳይገባን ጣዖታት አደርገን ከምናመልካቸው መካከል አንዱ ሆድ ነው። እግዚአብሔር አትብሉ ብሎ የከለከለንን ነገርና አትብሉ ባለን ሰአት የምንበላ ከሆነ በእርግጥ ከእግዚአብሔር ይልቅ ሆዳችንን እየወደድን ስለሆነ ሆዳችንን አመለክን ማለት ነው። ይህ ብቻ አይደለም፤ እግዚአብሔር እውነት ነው እቸገራለሁ ብሎ አስቦ መዋሸትም ጣዖት ማምለክ ነው። ለሆዱ ብሎ የሚዋሽ ሰው ከእግዚአብሔር ባሕርይ ጋር ይቃረናልና። የእግዚአብሔር ባሕርይው እውነት ነው። ድኻ እየተቸገረ እያዩ ለነገ በማሰብ የማይመጸውቱ ሰዎችም በሁለት መንገድ ጣዖት አምልከዋል፦ #አንደኛ አስቀድመን እንደ ገለጥነው ከፍቅር ይልቅ ገንዘብን በማስቀደም፤ #ሁለተኛ ደግሞ እግዚአብሔር ያኖረኛል ከማለት ይልቅ ራሳቸውን ለራሳቸው ጠባቂ መጋቢ አድርጎ በመሾም መግቦተ እግዚአብሔርን በመካድ ነው። እንግዲህ እናስተውል ሆድ በሦስት መሠረታዊ ምክንያቶች ጣዖት ሊሆንብን እንደሚችል፦ #መጀመሪያ እግዚአብሔር የከለከለንን በመመገብ ጊዜ ከእግዚአብሔር ይልቅ መብልን በመውደድ፤ #ሁለተኛ ለቅዳሴ መላእክት የተፈጠርን ክቡራን አገልጋዮቹ ስንሆን መላ ዘመናችን ሆዳችንን በማገልገል ራሳችንን የራሳችን ባርያዎች በማድረግ፤ #ሦስተኛ እግዚአብሔር እንደፈጠረኝ ያኖረኛል ከማለት ይልቅ ለነገ በመስገብገብ ለድኾች አለመራራት ናቸው። ጾም ፍቅር እንጅ ቀመር አይደለም። የምንጾመው ከምንወደው መብል መጠጥ በመከልከል ለእግዚአብሔር ያለንን ፍቅር ለመግለጥ እንጅ ሰባት ጾም የጾምን ሰዎች ነን የሚል መስፈርት ለማሟላት አይደለም። የሰው ልጆች ሁሉ እናትና አባት የመጀመሪያዎቹ ሰዎች አንዲት የእንጨት ፍሬ የተከለከሉት ያችን በመተው ፍቅረ እግዚአብሔርን እንዲገልጡ እንጅ ለአንዲት እንጨት ፍሬ ነፍጓቸው አይደለም። እርሱማ እንኳን የበለስ ፍሬ ሊነፍገን ሥጋውን ደሙን በለጋሥነት የሰጠ የባሕርይ ቸር አይደለምን? ክርስትና የፍቅር ሃይማኖት ነው። እግዚአብሔር ፍቅር ነውና ስለ ፍቅር ትጾማለህ፤ ስለ ፍቅር ትጸልያለህ፤ ሰለ ፍቅር ትሰደዳለህ፤ ስለ ፍቅር ትታሰራለህ፤ ስለ ፍቅር ትናቃለህ፤ ስለ ፍቅር ግፍን ሁሉ ተቀብለህ ትሞታለህ፤ በፍቅር ብርሃን ደምቀህ ትነሣለህ። ፍቅር ደግሞ ስለ ፍቅር በመማር የምታውቃት አይደለችም ስለ ፍቅር በመኖር እንጂ። ፍቅር በልቡናህ ዛፍ ሆኖ የተተከለ እንደሆነ ሥሩ እስከ ተረከዝህ ይወርዳል፤ ቅርንጫፎቹ ወደ ራስህ ያድጋሉ፤ አበባቸው በአንደበትህ ይፈነድቃሉ፤ የፍቅር ፍሬዎችም እነ ጾምና ጸሎት ምጽዋት ከአንተ በመላእክት እጅ እየተለቀሙ በሰማይ ጎተራ ይከማቻሉ፤ የፍቅርን ፍሬ እየበላህም ለዘለዓለም ትኖራለህ። እግዚአብሔርን የምትወደው ከሆነ እንኳን ሰባቱን አጽዋማትን ሁሉንም ቀን ትጾማለህ። ፍቅረ እግዚአብሔር ያነሰህ ፍቅረ መብልዕ የበዛልህ ስትሆን ደግሞ ጾም ይቀነስልኝ ብለህ ክተት ሠራዊት ትወጣለህ፤ ነጋሪት ትጎስማለህ። እንዳትጾም የሚረዱህ የሚመስልህን ጥቅሶችም በመብራት እየፈለግህ ትለኩሳለህ። በጅብ ቆዳ የተለጎመ ከበሮ ሲመቱት 'እንብላው' ብሎ ይጮኻል እንዲሉ አበው፤ የሆድ ጠበቃ የሆኑ የጅብ ስብከት የሚያመሰጥሩ የእንብላው መጽሐፍ ሊቃውንትንም አታጣም። እናም ወዳጄ ሆይ "እለ ከርሦሙ ያመልኩ" "ሆዳቸው አምላካቸው ነው" እንደለ ቅዱስ ጳውሎስ (ፊልጵ. ፫፥፲፰ )የምትወደው ሆድህ ጠላት ሆኖ በግራ እንዳያቆምህ በእግዚአብሔር ፍቅር ሰይፍነት የስስትን ገመድ ቆርጠህ ጥለህ ከምጽዋትና ከተገራ ሰውነት ጋር ጹም! #መጋቤ_ብሉይ_ወሐዲስ_አባ_ገብረ_ኪዳን (ከአባ ገብረ ኪዳን ትምህርት በቴሌግራም)
Show all...
👍 14
አስታውስ ደካማነትህን አስታውስ፦ ያን ጊዜ በጣም ጠንቃቃ ትሆናለህ፣ ሊጎዱህ በሚችሉ በትምክህትና በውዳሴ ከንቱም አትሸነፍም። የተሰጠህን በፍቅር የተሞላ የእግዚአብሔርን ቸርነት አስታውስ፦ ይህም በምስጋና የተሞላ ሕይወት እንድትመራ ያደርግሃል። በእግዚአብሔር ፍቅርና ሥራ ላይ ስትታመን ፍጹም የሆነ እምነት በልብህ እያደገ ይመጣል። ከእግዚአብሔር ጋር ያሳለፍከው ጊዜ ደግሞ በእምነት እንድትኖር ያበረታታሃል። የሰዎችን ፍቅርና ካንተ ጋር ያሳለፉትን መልካም ጊዜ አስታውስ፦ የሰዎችን ቀናነት ትጠራጠር ዘንድ ወይም ያደረጉብህን ክፉ ነገር ታስብ ዘንድ ይገባሃልን? የቀደመ ፍቅራቸው ስለ እነርሱ ይማልዳል ያንተንም ቁጣ ያበርዳል። ሞት እንዳለ አስታውስ፦ እንዲሁ በዓለም ያለ ፈተናም እንደሚያልፍ። “ከፀሐይ በታች የተሠራውን ሥራ ሁሉ አየሁ፤ እነሆም፥ ሁሉ ከንቱ ነው፥ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።” መክብብ 1፡14 ማለትን ትረዳለህ። በእግዚአብሔር ፊት መቆምህንና እርሱም እንደሚመለከትህ አስታውስ፦ ያኔ ኃጢአት አትሰራም እግዚአብሔርን ታየዋለህና። ስለ አንተ የፈሰሰውን የክርስቶስን ክቡር ደም አስታውስ፦ በዚህም ሕይወትህ ያለውን ዋጋ በእርግጥ ታውቃለህ፤ በዓይኖችህ ፊት የከበረ ይሆናል፣ ስለዚህም በከንቱ በመኖር አታጠፋውም “በዋጋ ተገዝታችኋልና” 1ኛ ቆሮ. 6፥20 እንዲል ቅዱስ ጳውሎስ። በወላጆችህ እምነት በተጠመቅህባት ቦታ ለእግዚአብሔር የገባኸውን ቃል አስታውስ፦ ዲያብሎስን፣ ሥራዎቹን ሁሉ፣ ሐሳቦቹንና ጥበቡን፣ ኃይሉንም ትክድ ዘንድ ኃይል ታገኛለሕና። በዚህ ዓለም እንግዳ መሆንህንና ወደ ሰማያዊው ቤትህ እንደምትመለስ ዘወትር አስታውስ፦ ያን ጊዜ በዚህ ዓለምና በደስታው ተስፋ ማድረግን ትተዋለህ። በጠባቡ በር መጓዝ ወደ መንግስተ ሰማያት እንደሚያደርስህ አስታውስ፦ ሰፊው ደጅ ፊት ለፊትህ ተከፍቶ ብታየው፣ አልፈኸው ሂድ ከእሱም ራቅ፣ በእርሱ የሄዱ እንዳሉ አልቀዋልና። ዘላለማዊውን ሕይወትህን አስታውስ፦ ሁልጊዜም ስለዚህ ትጋ። የእግዚአብሔር ልጅ መሆንህንና እርሱን መምሰል እንዳለብህ አስታውስ፦ እውነተኞች ከሆኑት ከእግዚአብሔር ልጆች ጋር አካሄድህን አስተካክል። የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ መሆንህን አስታውስ፦ በውስጥህ ያለውንም ቅዱሱን የእግዚአብሔር መንፈስ አታሳዝን። ዘወትርም ቅዱስ የእግዚአብሔር ማደሪያ ሁን። ብፁዕ አቡነ ሽኖዳ      🌿 @father_advice 🌿
Show all...
👍 21
Photo unavailableShow in Telegram
👍 21
❤ህዳር 21 ታቦተ ጽዮን የምትከብርበት ዕለት ሰው ሁሉ እናታችን ጽዮን ይላል መዝ 86+5 ጽዮንን የሚጠሉ ሁሉ  ይፈሩ መዝ 128+5 እግዚአብሔር ጽዮንን መርጧታልና ይላል መዝሙረኛው እግዚአብሔር የመረጣትን መጥላት ከእግዚአብሔር ጋር መጣላት ነው ❤በተለየ መልኩ የምናከብርበት ምክንያት፦ 1 ታቦተ ጽዮን በምርኮ በሄደችበት በሀገረ ፍልስጤም ዳጎን የተባለ የአህዛብን ጣኦት አድቅቃ በድል የተመለሰችበትን ዕለት ነው 2 ታቦተ ጽዮን ንጉሥ ሰሎሞን ወደ ሠራላት ቤተመቅደስ በክብር የገባችበትን ዕለት ነው 3 አበው  ነቢያት ስለእመቤታችን በተለያየ አምሳል ያዩበት ለምሳሌ፦ ነቢዩ ዕዝራ በሃገር መንፈሳዊት፣ ነቢዩ ሕዝቅኤል በተዘጋች ቤተ መቅደስ፣ ነቢዩ ዘካርያስ በተቅዋመ ወርቅ ያዩበትን ዕለትነው 4 ቀዳማዊ ምኒሊክ ከዐሥራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል የበኩር ልጅ ጋር ሊቀ ካህናቱን አዛሪያስንና ታቦተ ጽዮንን ይዞ አክሱም የደረሰበትን ዕለት ነው 5  በአብርሃ ወአፅብሃ ዘመነ መንግሥት ክርስትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት ሆኖ አዋጅ የታወጀበትን ዕለት ነው 6 ለታቦተ ጽዮን ማደሪያ አብርሃ ወአጽብሃ በወርቅና በዕንቁ ያሠሩት ባለ አሥራ ሁለት ክፍል ቤተ መቅደስ ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት ዕለት በመሆኑ ነው 7 በዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዮዲት ጉዲት አብያተ ክርስቲያንን ስታቃጥል ታቦተ ጽዮንን ይዘው ወደ ዝዋይ ሀይቅ ከተሰደዱ በኋላ ዘመነ ሰላም ሲጀመር አክሱም በነበሩ ካህናት አስታዋሽነት ከዝዋይ ወደ አክሱም የገባችበት ዕለት በመሆኑ ነው መልካም በዓል
Show all...
👍 17
18/3/2016ማታ 3 ሰዓት የሚጸለይ ጸሎት     ውዳሴ ማርያም የለቱ     መዝሙረ ዳዊት 76ስከ82      ቆሮንጦስ  ምዕራፍ 4 እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ 24 በእንተ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ24 የግል ጸሎት ከፈጣሪ ጋር መመካከር የልብን ማውራት ፍቃዱን መጠየቅ ማዳመጥ እስኪፈጸም መጠበቅ አጥብቆ መለመን አባታችን ሆይ በማለት ጸሎቱን መጨረስ መልካም የጸሎት ጊዜ አምላክ ጸሎታችንን ይቀበል ልመናችንን ይስማ 19/3/2016ማታ 3 ሰዓት የሚጸለይ ጸሎት     ውዳሴ ማርያም የለቱ     መዝሙረ ዳዊት 83ስከ 88      2ቆሮንጦስ ም 3 እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ 24 በእንተ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ24 የግል ጸሎት ከፈጣሪ ጋር መመካከር የልብን ማውራት ፍቃዱን መጠየቅ ማዳመጥ እስኪፈጸም መጠበቅ አጥብቆ መለመን አባታችን ሆይ በማለት ጸሎቱን መጨረስ መልካም የጸሎት ጊዜ አምላክ ጸሎታችንን ይቀበል ልመናችንን ይስማ 20/3/2016 ማታ 3 ሰዓት የሚጸለይ ጸሎት     ውዳሴ ማርያም የለቱ     መዝሙረ ዳዊት 89ስከ 94      እብራውራን ም 3 እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ 24 በእንተ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ24 የግል ጸሎት ከፈጣሪ ጋር መመካከር የልብን ማውራት ፍቃዱን መጠየቅ ማዳመጥ እስኪፈጸም መጠበቅ አጥብቆ መለመን አባታችን ሆይ በማለት ጸሎቱን መጨረስ መልካም የጸሎት ጊዜ አምላክ ጸሎታችንን ይቀበል ልመናችንን ይስማ 21/3/2016ማታ 4 ሰዓት የሚጸለይ ጸሎት     ውዳሴ ማርያም የለቱ     መዝሙረ ዳዊት 89ስከ 95      2ቆሮንጦስ ም 4 እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ 24 በእንተ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ24 የግል ጸሎት ከፈጣሪ ጋር መመካከር የልብን ማውራት ፍቃዱን መጠየቅ ማዳመጥ እስኪፈጸም  አጥብቆ መለመን አባታችን ሆይ በማለት ጸሎቱን መጨረስ መልካም የጸሎት ጊዜ አምላክ ጸሎታችንን ይቀበል መጠበቅልመናችንን ይስማ ለጸሎት ተነሱ 🧚‍♀🧚‍♀🧚‍♀🧚🧚🧚🧚🧚🧚🧚🧚🧚🧚🧚 22/3/2016 ማታ 3 ሰዓት የሚጸለይ ጸሎት     ውዳሴ ማርያም የለቱ     መዝሙረ ዳዊት 96እስከ103      ገላቲያ ምዕራፍ 4 እግዚኦ መሀረነ ክርስቶስ12 በእንተ ማርያም መሀረነ ክርስቶ12 የግል ጥያቄያችንን ጠይቀን አመስግነን በአባታችንሆይ ጸሎት እንዘጋለን መልካም የጸሎት ጊዜ አምላክ ጸሎታችንን ይቀበል ልመናችንን ይስማ 🙏🙏🙏ለጸሎት ተነሱ🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏          ""ጾምህና ምጽዋትህ ሁለት ዋጋ አላቸው፡፡ ከሰው ክብርን ሽተህ የምትጦም ከሆነ ኃጢአት በአንተ ላይ እንድትበረታ ደንቁርናህም እጅግ ጽኑ እንዲሆን እወቅ፡፡ ነገር ግን እጆችህን ለተቸገረ ሰው የምትዘረጋ ሕሊናህን ግን ወደ አምላክ የምታነሣ ከሆነ፣ እንዲሁም ስትጦም ጦምህን በእግዚአብሔር ፊት ያደረግህ እንደሆነ ከፈጣሪህ ዘንድ መልካምን ዋጋ ትቀበላለህ፡፡ ይህ ኃይለ ቃል “ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና፡፡”(ማቴ.6፡21) ብሎ ጌታችን ካስተማረው ትምህርት ጋር አንድ  ዓይነት ትርጉም ያለው ነው፡፡ ጦምና ምጽዋታችን በከንቱ ፈቃዳችን ምክንያት ለኃጢአት አሳልፎ እንዳይሰጠንና በደላችንንም እጥፍ ድርብ እንዳያደርግብን አምላካችን ይህን ማስተዋል ዘወትር ይሰጠን ዘንድ በዚህ የጦም ወር እንለምነው፡፡ ለወደደንና በእኛ ጥቂት ድካም ዘለዓለማዊ ዋጋን ለሚሰጠን ለእርሱ ምስጋና ይሁን ዛሬም ዘወትርም  ለዘለዓለሙ አሜን፡፡ (ቅዱስ ኤፍሬም) 23/3/2016ማታ 3 ሰዓት የሚጸለይ ጸሎት     ውዳሴ ማርያም የለቱ     መዝሙረ ዳዊት 96ስከ 102      ሮሜ ም 4 እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ 24 በእንተ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ24 የግል ጸሎት ከፈጣሪ ጋር መመካከር የልብን ማውራት ፍቃዱን መጠየቅ ማዳመጥ እስኪፈጸም መጠበቅ አጥብቆ መለመን አባታችን ሆይ በማለት ጸሎቱን መጨረስ መልካም የጸሎት ጊዜ አምላክ ጸሎታችንን ይቀበል ልመናችንን ይስማ 24/3/2016ማታ 3 ሰዓት የሚጸለይ ጸሎት     ውዳሴ ማርያም የለቱ     መዝሙረ ዳዊት 103ስከ 109     1ቆሮንጦስ ም 3 እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ 24 በእንተ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ24 የግል ጸሎት ከፈጣሪ ጋር መመካከር የልብን ማውራት ፍቃዱን መጠየቅ ማዳመጥ እስኪፈጸም መጠበቅ አጥብቆ መለመን አባታችን ሆይ በማለት ጸሎቱን መጨረስ መልካም የጸሎት ጊዜ አምላክ ጸሎታችንን ይቀበል ልመናችንን ይስማ 25/3/201ት6ማታ 3 ሰዓት የሚጸለይ ጸሎት     ውዳሴ ማርያም የለቱ     መዝሙረ ዳዊት 116ስከ 121      ያዕቆብ  ም 2 እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ 24 በእንተ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ24 የግል ጸሎት ከፈጣሪ ጋር መመካከር የልብን ማውራት ፍቃዱን መጠየቅ ማዳመጥ እስኪፈጸም መጠበቅ አጥብቆ መለመን አባታችን ሆይ በማለት ጸሎቱን መጨረስ መልካም የጸሎት ጊዜ አምላክ ጸሎታችንን ይቀበል ልመናችንን ይስማ 26/3/2016ማታ 3 ሰዓት የሚጸለይ ጸሎት     ውዳሴ ማርያም የለቱ     መዝሙረ ዳዊት 122ስከ 127      ዕብራውያን   ም 3 እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ 24 በእንተ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ24 የግል ጸሎት ከፈጣሪ ጋር መመካከር የልብን ማውራት ፍቃዱን መጠየቅ ማዳመጥ እስኪፈጸም መጠበቅ አጥብቆ መለመን አባታችን ሆይ በማለት ጸሎቱን መጨረስ መልካም የጸሎት ጊዜ አምላክ ጸሎታችንን ይቀበል ልመናችንን ይስማ ለጸሎት ተነሱ 🧚‍♀🧚‍♀🧚‍♀🧚🧚🧚🧚🧚🧚🧚🧚🧚🧚🧚 27/3/2016 ማታ 3 ሰዓት የሚጸለይ ጸሎት     ውዳሴ ማርያም የለቱ     መዝሙረ ዳዊት 128እስከ133      ዮሐንስ ወንጌል  6 እግዚኦ መሀረነ ክርስቶስ12 በእንተ ማርያም መሀረነ ክርስቶ12 የግል ጥያቄያችንን ጠይቀን አመስግነን በአባታችንሆይ ጸሎት እንዘጋለን የጸሎት ጊዜ አምላክ ጸሎታችንን ይቀበል ልመናችንን ይስማ መልካም🙏🙏🙏ለጸሎት ተነሱ🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏          ""ጾምህና ምጽዋትህ ሁለት ዋጋ አላቸው፡፡ ከሰው ክብርን ሽተህ የምትጦም ከሆነ ኃጢአት በአንተ ላይ እንድትበረታ ደንቁርናህም እጅግ ጽኑ እንዲሆን እወቅ፡፡ ነገር ግን እጆችህን ለተቸገረ ሰው የምትዘረጋ ሕሊናህን ግን ወደ አምላክ  ከሆነ፣ እንዲሁም ስትጦም ጦምህን በእግዚአብሔር ፊት ያደረግህ እንደሆነ ከፈጣሪህ የምታነሣዘንድ መልካምን ዋጋ ትቀበላለህ፡፡ ይህ ኃይለ ቃል “ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና፡፡”(ማቴ.6፡21) ብሎ ጌታችን ካስተማረው ትምህርት ጋር አንድ  ዓይነት ትርጉም ያለው ነው፡፡ ጦምና ምጽዋታችን በከንቱ ፈቃዳችን ምክንያት ለኃጢአት አሳልፎ እንዳይሰጠንና በደላችንንም እጥፍ ድርብ እንዳያደርግብን አምላካችን ይህን ማስተዋል ዘወትር ይሰጠን ዘንድ በዚህ የጦም ወር እንለምነው፡፡ ለወደደንና በእኛ ጥቂት ድካም ዘለዓለማዊ ዋጋን ለሚሰጠን ለእርሱ ምስጋና ይሁን ዛሬም ዘወትርም  ለዘለዓለሙ አሜን፡፡ (ቅዱስ ኤፍሬም)
Show all...
👍 18
ነቢያት ጌታ "ይወርዳል ይወለዳል" ብለው የተናገሩት ትንቢት እንዲፈጸም ተመኝተው ጾሙ ጸለዩ:: እኛ ስለምን እንጾማለን? ክርስቶስ ተወልዶ ፣ ተጠምቆ ፣ አስተምሮ ፣ ተሰቅሎ ፣ ሞቶ ፣ ተነሥቶ ፣ ዐርጎ ፣ በአባቱ ቀኝ አይደለምን? አሁን ለምን እንጾማለን? ብለን እናስባለን:: ጌታ በእኔና አንተ ልብ ውስጥ እውነት ተወልዶአልን? እውነት የእኛ ልብ እንደ ቤተልሔም ግርግም ለክርስቶስ ማደሪያ ሆኖአል? ማደሪያ አሳጥተን ከእናቱ ጋር አልመለስነውም? የጥምቀቱ ትሕትና በእኛ ልብ መቼ ደረሰ? የስቅለቱ ሕማም መች በእኛ ሕሊና ተጻፈ? የትንሣኤው ተስፋ የዕርገቱ ልዕልና በእኛ ልቡና መቼ ዐረፈ? ስለዚህ ነቢያት "ውረድ ተወለድ" ብለው የጾሙትን ጾም እንጾማለን:: ጌታ ሆይ በእኔ ሕይወትም ውስጥ ውረድ ተወለድ የእኔን ሰውነት ማደሪያህ አድርገው:: ሕዋሳቶቼ ከኃጢአት አርፈው እንደ ቤተልሔም ግርግም ማደሪያህ ይሁኑ:: የቤተልሔም እንስሳት ትንፋሽ ገበሩልህ ፣ የቢታንያ ድንጋዮች ዘማሪ ቢጠፋ ሊዘምሩ ዝግጁ ነበሩ ፣ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ለክብርህ ተቀደደ ፣ ጨረቃ ላንተ ደም ለበሰች ፣ ፀሐይ ስላንተ ጨለመች ፣ ከዋክብት ለስምህ ረገፉ ፣ ዓለቶች ለፍቅርህ ተሰነጠቁ:: ከቤተልሔም እንስሳት ፣ ከቢታንያ ድንጋዮች ፣ ከቤተ መቅደስ መጋረጃ እኔ እንዴት አንሼ ልገኝ? የቢታንያ ድንጋይ ያወቀህን ያህል ሳላውቅህ ፣ የቤተ መቅደስ መጋረጃ የተረዳህን ያህል ሳልረዳህ እንዴት ልኑር? ዓለት ላንተ ሲሰነጠቅ የኔ ልብ ለምን ከዓለት ደነደነ? ጨረቃ ደም ስታለቅስ እኔ መከራህ ለምን አልተሰማኝም? ሙታን በሞትህ ሲነሡ እኔ ምነው ከኃጢአት ሞት መነሣት ተሳነኝ? ለዚህ ነው በእኔ ሕይወት ገና አልተወለድክም የምለው:: ስለዚህ ጌታ ሆይ የነቢያትህን ጾም ጸሎት ሰምተህ የወረድህ የተወለድህ ጌታ ሆይ በእኔም ሕይወት ውረድ ተወለድና እኔም ከመላእክት ጋር አብሬ ልዘምር ፣ ከሰብአ ሰገል ጋር ሥጦታህን ልቁጠር ፣ ከእረኞች ጋራ ልደነቅ:: ልደትህ ሳይገባኝ ምጽዓትህ እንዳይደርስብኝ እርዳኝ:: ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ጾመ ነቢያት 2015 ዓ.ም. የተጻፈ
Show all...
👍 12
ልጆቼ፦ እግዚአብሔርን በእምነት በፀሎት እንሻው ከእኛ የጠፋ ገንዘባችንን ነቅተን ተግተን በብዙ ድካም እንድንሻው እንዲሁ ሃሳባችንን ወደ እግዚአብሔር ልናቀርብ ይገባናል፤ ልጃችን ቢጠፋብን ፈልገን በቅርብ ያላገኘነው እንደሆነ ሃይላችንን በድካም ድካማችንን በሃይል የምንለውጥ አይደለንምን? የጠፋውን ልጃችንን ስለመፈለግስ እናገኘው ዘንድ የብሱን በእግር ባህሩን በመርከብ የምንዞር አይደለንምን? ፈልገንም ያገኘነው እንደሆነ ዳግመኛ እንዳይጠፋብን ለመጠበቅ እንተጋ የለምን? እንዲህ ከሆነ መሓሪ እግዚአብሔርን በእምነትና በፀሎት እንሻው ዘንድ ምን ያህል ይገባን ይሆን? እግዚአብሔርን ፈልጉት ነጋዴ ወርቅ ቢጠፋበት ወርቁን ያገኘው እንደሆነ ሁሉን ቦታ እንደሚፈልግ እንዲሁ እግዚአብሔርን ፈልጉት እናት ልጇ ቢጠፋባት እስክታገኘው ድረስ አርፋ እንደማትቀመጥ እንዲሁ እግዚአብሔርን ፈልጉት እግዚአብሔርን እሹት ፈልጉት እስክታገኙት ድረስ በእምነት በፀሎት እሹት፡፡” ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
Show all...
👍 24
ገልጦልን እናገኛለን፡- ቅ ዱስ ገብርኤል በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ቅዱስ ሚካኤል ስለመሾሙ ሲመሰክር “በእውነት በመጽሐፍ የተጻፈውን እነግርሃለሁ፤ በዚህም ነገር ከአለቃችሁ ከሚካኤል በቀር የሚረዳኝ ማንም የለም”(ዳን.10፡21)ብሎአል፡፡ ስለዚህም ለኢያሱ የተገለጠውና እስራኤላውያንንም የመራው መልአክ ቅዱስ ሚካኤል መሆኑን እንረዳለን፡፡ የቅዱስ ሚካኤል አለቅነት በሐዲስ ኪዳንም አንደሚቀጥል ይህ ነቢይ በትንቢቱ “በዚያ ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ ሚካኤል ይነሣል..” (ዳን.12፡1) በማለት ተናግሮለታል፡፡ ስለዚህም ቅዱስ ሚካኤል እኛን ከሰይጣን አሽክላና ወጥመድ ይጠብቀንና በጸሎቱ በእግዚአብሔር ፊት ይቆምልን ዘንድ በእኛም ላይ ሹም ነው፡፡ ምክንያቱም እኛ የእግዚአብሔር ሕዝቦችና የርስቱ ወራሾች ነንና፡፡ እግዚአብሔር ነቢዩ ሙሴን የሕዝቡ መሪ አድርጎ መሾሙ እጅግ ትሑትና ስለመንጎቹ ነፍሱን እንኳ አሳልፎ እስከመስጠት ደርሶ ስለሚወዳቸው ነበር፡፡(ዘኁል.12፡3፤ዘጸአ.32፡32) በሕዝቡም ላይ እርሱን መሾሙ እንዲሠለጥንባቸው ወይም እንዲገዛቸው ሳይሆን በትምህርቱና በጸሎቱ እነርሱን እንዲቤዣቸው ነው፡፡ እንዲህም ስለሆነ ቅዱስ እስጢፋኖስ ስለሙሴ ሲመሰክር “እግዚአብሔር ሹምና ቤዛ አድርጎ ላከው”አለ፡፡ (የሐዋ.7፡35) እንዲሁ ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡ ቅዱስ ሚካኤል እጅግ ትሑትና ለሠራዊቱ ተቆርቋሪ የሆነ መልአክ በመሆኑ በመላእክትና በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ተሾመ፡፡ በመላእክትና በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ መሾሙ ልክ እንደ ሙሴ በእነርሱ ላይ ሊሠለጥንባቸው ወይም ሊገዛቸው ሳይሆን መላእክትን ሊመራ ፣ እኛን ደግሞ ከሰይጣን ጥቃት ሊጠብቀንና በጸሎቱ ሊራዳን ነው (ይሁዳ.12) ፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ቅዱሳን መላእክት እኛን እንደሚጠብቁና እንደሚራዱ እንዲሁም ስለእኛ በፊቱ አንደሚቆሙ ሲያስተምረን“ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን ስንኳ እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው በሰማያት ሁል ጊዜ በሰማይ ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ እላችኋለሁ” (ማቴ.18፡10) ብሎናል፡፡ እኛን ይጠብቁ ዘንድ የተሰጡን ቅዱሳን መላእክት ስለእኛ እንዲህ የሚቆረቆሩና ስለመዳናችን የሚተጉ ከሆነ በቅድስናው ልቆ የመላእክት አለቃ ሆኖ የተሾመው ቅዱስ ሚካኤል እንዴት ስለእኛ በእግዚአብሔር ፊት ይበልጥ አይቆም? (ሉቃ.13፡6-9) እንዴትስ በተሰጠው ሥልጣንና ኃይል አይረዳን? (መዝ.33፡7) እርሱ “ስለሕዝብህ ልጆች የሚቆመው” መባሉም እኛን በጸሎቱና በተራዳኢነቱ የጽድቅ ሕይወታችንን በሚገባ እንድናከናውን እንደሚራዳን የሚያሳይ ኃይለ ቃል ነው፡፡ የመልአኩ የቅዱስ ሚካኤል ጸሎቱና በረከቱ በእኛ ላይ ለዘለዓለሙ ይደርብን አሜን!!! ⚜💫🌺⚜💫🌺⚜💫🌺💫⚜🌺⚜ ለእልፍ አእላፋት ቅዱሳን መላእክት ክብረ በዓል እንኳን አደረሳችሁ {ሕዳር 13} ⚜💫🌺⚜💫🌺⚜💫🌺💫⚜🌺⚜        ✥ እልፍ አእላፋት መላእክት ✥ እግዚአብሔር ቅዱሳን መላእክትን ሲፈጥራቸው በነገድ መቶ (100) በክፍለ ነገድ አሥር (10) አድርጓቸዋል። አቀማመጣቸውንም በ3 ሰማያትና በ10 ከተሞች (ዓለማት) አድርጎል። መላእክት ያሉባቸው ከተሞች ከታች ወደ ላይ "ኤረር ፥ ራማና ኢዮር" ይባላሉ። አሥሩ ክፍለ ነገድ ደግሞ ከነ አለቆቻቸው ይህንን ይመስላሉ:- 1.አጋእዝት (የቀድሞ አለቃቸው ሳጥናኤል አሁን የተረፉት በቅዱስ ሚካኤል ሥር ናቸው) 2.ኪሩቤል (አለቃቸው ኪሩብ) 3.ሱራፌል (አለቃቸው ሱራፊ) 4.ኃይላት   (አለቃቸው ሚካኤል) 5.አርባብ   (አለቃቸው ገብርኤል) 6.መናብርት(አለቃቸው ሩፋኤል) 7.ስልጣናት (አለቃቸው ሱርያል) 8.መኳንንት  (አለቃቸው ሰዳካኤል) 9.ሊቃናት    (አለቃቸው ሰላታኤል) 10.መላእክት(አለቃቸው አናንኤል) ናቸው። ከእነዚህም ፣ አጋእዝት ፣ ኪሩቤል ፣ ሱራፌልና ኃይላት መኖሪያቸው በኢዮር (በ3ኛው ሰማይ) ነው። አርባብ ፤ መናብርትና ስልጣናት ቤታቸው ራማ (2ኛው ሰማይ) ነው። መኳንንት፣ ሊቃናትና፣ መላእክት ደግሞ የሚኖሩት በኤረር (በ1ኛው) ሰማይ ነው። መላእክት ተፈጥሯቸው እምኀበ አልቦ ኀበቦ ነው። አይራቡም ፥ አይጠሙም ፥ አይዋለዱም ፥ አይሞቱም። ተፈጥሯቸውም ረቂቅ ነው። ተግባራቸውም ዘወትር "ቅዱስ ቅዱስ  ቅዱስ" እያሉ ፈጣሪያቸውን ማመስገን ነው። ምግባቸውም ይሄው ነው። ዕረፍት ብሎ ነገርን አያውቁም። "አኮቴቶሙ ዕረፍቶሙ ፥ ወዕረፍቶሙ አኮቴቶሙ" እንዲል። በተጨማሪም መልአክ ማለት ተላላኪ (አገልጋይ) ነውና ከፈጣሪ ወደ ሰው ልጆች ለምሕረትም ለመዓትም ይላካሉ። ምሕረትን ያወርዳሉ ልመናን ያሳርጋሉ  ቅጡ ሲባሉም ይቀጣሉ ስነ ፍጥረት (አራቱ ወቅቶች) እንዳይዛቡ ይጠብቃሉ። ዘወትርም ስለ ሰው ልጆች ያማልዳሉ (ዘካ. 1:12) ምሥጢርን ይገልጣሉ (ዳን. 9:21)ይረዳሉ (ኢያ. 5:13) እንዳንሰናከል ይጠብቃሉ (መዝ. 90:11) ያድናሉ (መዝ. 33:7)ስግደት ይገባቸዋል (መሳ. 13:20, ኢያ. 5:13, ራዕ. 22:8) በፍርድ ቀንም ኃጥአንን ከጻድቃን ይለያሉ (ማቴ. 25:31) በአጠቃላይ ለሰው ልጆች ሕይወትና ድኅነት ሲባል ከፈጣሪያቸው የተሰጣቸውን ትዕዛዝ ሲጠብቁና ፈቃዱን ሲፈጽሙ ይኖራሉ።         ✥  እልፍ አእላፋት ✥ ይህ ዕለት በሊቃውንት አንደበት "እልፍ አእላፋት" እየተባለ ይጠራል። በሃይማኖት ፥ በተልእኮትና በምስጋና የሚኖሩ 99ኙ ነገደ መላእክት በአንድ ላይ የሚከብሩበት ቀን ነው። ሕዳር 13 ቀን ዓመታዊ በዓላቸው ነው በየወሩ ደግሞ በ13 ወርሐዊ በዓላቸው መሆኑን ያሳያልና ዘወትር ልናስባቸው ይገባል። ቅዱስ መጽሐፍ ቅዱሳን መላእክትን በስምና በማዕረግ እንደሚነግረን ሁሉ በማኅበር (በትዕይንት) አገልግሎታቸውም ይነግረናል:: ለምሳሌ:-ያዕቆብ በረዥም መሰላል ሲወጡና ሲወርዱ ተመልክቷል (ዘፍ. 28:12)። ኤልሳዕ ለግያዝ አሳይቶታል (2ነገ. 6:17)።ዳንኤል ተመልክቷል (ዳን. 7:10)።በልደት ጊዜ በዝማሬ መገለጣቸውን ቅዱስ ሉቃስ ጽፏል(ሉቃ. 2:13) ዮሐንስ በራዕዩ አይቷቸዋል (ራዕይ. 5:11)ከዚህም በላይ በብዙ የመጻሕፍት ክፍል ተጠቅሰዋል። ቅዱሳን መላእክተ ብርሃን  መንፈሳውያን ፥ ሰባሕያን ፥ መዘምራን ፥ መተንብላን (አማላጆች) ተብለውም ይጠራሉና ያስቡን ዘንድ ልናስባቸው ይገባል::   ✥ የዕለቱ የሥርዓተ ቅዳሴ  ምንባባት እና ምስባክ ✥ ዕብ. ፲፪ ፥ ፳፪ - ፳፭ የይሁዳ መል.  ፲፬ ፥ ፲፭ - ፲፯ የሐዋ. ፲፪ ፥ ፮ - ፲፪ መዝ.ዳዊት ፻፫ ፥ ፲፱ - ፳ "ጽኑዓን ወኃያላን እለ ትገብሩ ቃሎ ወእለ ትሰምኡ ቃለ ነገሩ።" (እግዚአብሔር ዙፋኑን በሰማይ አዘጋጀ፥ መንግሥቱም ሁሉን ትገዛለች። ቃሉን የምትፈጽሙ፥ ብርቱዎችና ኃያላን፥ የቃሉንም ድምፅ የምትሰሙ መላእክቱ ሁሉ፥ እግዚአብሔርን ባርኩ።) ወንጌል = ማቴ. ፳፭ ፥ ፴፩ - ፵፮ ⚜💫🌺⚜💫🌺⚜💫🌺💫⚜🌺⚜
Show all...
👍 9
መንፈሳዊ ጉባኤ: ⚜💫🌺⚜💫🌺⚜💫🌺💫⚜🌺⚜ ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል በዓለ ሲመቱ እንኳን አደረሳችሁ !!! {ሕዳር 12 } ⚜💫🌺⚜💫🌺⚜💫🌺💫⚜🌺⚜ የሰው ልጅ በገነት እንደ ቅዱሳን መላእክት በቅድስና አምላኩን በማመስገን በደስታ ይኖር ነበር፡፡ ነገር ግን “ክፉና ደጉን ከምታሳውቀው ዕፀ በለስ እንዳትበላ” ተብሎ የተሰጠውን ትእዛዝ በመተላለፉ ምክንያት ከአምላኩ ተለየ(ዘፍ.3፡6)፡፡እግዚአብሔር በአርአያውና በአምሳሉ የፈጠረው ሰው ክብሩን አጣ፣ ጸጋው ተገፈፈ፣ ፈጣሪውንም አሳዘነ፡፡ ቅዱሳን መላእክትም በእግዚአብሔር መልክና ምሳሌ የተፈጠረው ሰው ከክብሩ ተዋርዶ ሲመለከቱ ተከዙ፡፡ የሰው ልጅ ጠፍቶ እንዲቀር ያልወደደው እግዚአብሔር ወልድ ሰውን ለማዳን ራሱን ዝቅ አድርጎ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሱዋ ነፍስ ነስቶ ተወለደ፡፡ቅዱሳን መላእክትም ከላይ ከአርያም ከአባቱ ሳይለይ እግዚአብሔር ወልድ ሰውን ለማዳን ሲል በግዕዘ ሕፃናት ተወልዶ፣ በእናቱም እቅፍ ሆኖ፤ እንስሳት እስትንፋሳቸውን እያሟሟቁት በማየታቸው ተደነቁ፡፡ ሰውን ለማዳን ሲል ራሱን ዝቅ በማድረግ የባርያውን አርአያ እንደነሣ አስተውለው “ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት፣ ወሰላም በምድር ሥምረቱ ለሰብእ” (ሉቃ.2፡14) ብለው አመሰገኑት፡፡ ጌታችንም በመስቀሉ የማዳን ሥራውን ሲፈጽም ተጎሳቁሎ የነበረውን የሰው ባሕርይ ወደ ቀድሞ ክብሩ መለሰው፡፡ ስለዚህም እንደ ቅዱሳን መላእክት አምላኩን ለማመስገን እድሉን አገኘ፡፡ (ዮሐ.4፡23) ነገር ግን ከእነርሱ ጋር በመሆን ሙሉ ለሙሉ በምስጋና የሚሳተፈው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ሙታንስ በሚነሡበት ጊዜ በሰማያት እንደ እግዚአብሔር መልአክት ሆነው ይኖራሉ…….” (ማቴ.22፡30) እንዳለው በትንሣኤ ዘጉባኤ ነው፡፡ እስከዚያ ድረስ ግን በዚህ ምድር ሳለን ከእኛ የሚጠበቅብንን ፣ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቃል ያስተማረንን፣ በሥራም ያሳየንን ተግባር ተግብረን፣ እንደ ቅዱሳን መላእክት ለአምላካችን በመንፈስና በእውነት በመሆን አምልኮታችንን እንድንፈጽም የእነርሱ ተራዳኢነት በእጅጉ ያስፈልገናል፡፡ ስለዚህም ነው ቅዱስ ጳውሎስ “መላእክት ሁሉ መናፍስት አይደሉም? የዘለዓለም ሕይወትን ይወርሱ ዘንድ ስለ አላቸው ሰዎችስ ለአገልግሎት ይላኩ የለምን?” (ዕብ.1፡14) ማለቱ፡፡ “የዘለዓለም ሕይወትን ይወርሱ ዘንድ” የተባልነው ጌታችን መድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌሉ “እነርሱ በእውነት ቅዱሳን ይሆኑ ዘንድ ስለእነርሱ ራሴን እቀድሳለሁ፡፡ የምለምንህም ስለ እነዚህ ብቻ አይደለም፤ በቃላቸው ስለሚያምኑብኝ ሁሉ ነው እንጂ” (ዮሐ.17፡19-20)እንዳለው በክርስቶስ አምነን ለተጠመቅነው ክርስቲያኖች ነው፡፡ እናት ልጁዋን እንድትንከባከብና እንድታገለግል ሁሉ ቅዱሳን መላእክትም የዘለዓለም ሕይወትን እንድንወርስ ይራዱናል፡፡ (ሉቃ.13፡6-9) ያለ እነርሱ እርዳታና ድጋፍ በቅድስና ሕይወት አድገን የመንግሥቱ ወራሾች መሆን አይቻለንም፡፡ እንዲህም በመሆኑ በመንፈስ ቅዱስ የልጅነት ጸጋን ከማግኘታችን በተጨማሪ ቅዱሳን መላእክት እኛን ይራዱን ዘንድ ጠባቂ ተደርገው ተሰጥተውናል፡፡ (ማቴ.18፡10) ቅዱስ ጳውሎስ “እናንተ ግን የሕያው እግዚአብሔር ከተማ ወደምትሆን ወደ ጽዮን ተራራ በሰማያት ወደ አለችው ኢየሩሳሌም ደስ ብሎአቸው ወደሚኖሩ አእላፍ መላእክትም ደርሳችኋል” (ዕብ.12፡22) በማለት እንደተናገረው በክርስቶስ የማዳን ሥራ ከቅዱሳን መላእክት ጋር አንድ ቤተሰብ መሆንን አግኝተናል፡፡ ስለዚህም ጉዞአችንን ጨርሰን ገድላችንን ፈጸመን ለክብር እንድንበቃ ይራዱናል፡፡ በመሆኑም የእኛ ሕይወት በኃጢአት ውስጥ መገኘት ሲያሳዝናቸው፣ በንስሐ ወደ አባታችን መመለሳችን ደግሞ በእጅጉ ያስደስታቸዋል፡፡ (ሉቃ.15፡7) ስለዚህ ስለእኛ በቅድስና ሕይወት ይተጋሉ፡፡ቅዱስ ጳውሎስ "ለራሱ ስለ ሆኑት፥ ይልቁንም ስለ ቤተ ሰዎቹ የማያስብ፥ ማንም ቢሆን ሃይማኖቱን የካደ፥ ከማያምንም ይልቅ የከፋ ነው" ይላል፡፡ (1ጢሞ.5፡8) ስለዚህ እኛ የእነርሱ ቤተሰብ ሆነናልና ቤተሰባዊ ግዴታቸውን ለመወጣት ሲሉ፣ ደካማው ብርቱን እንዲረዳ ቅዱሳን መላእክትም እኛን ለመርዳት ይተጋሉ፡፡ ነገር ግን የእነርሱ እርዳታ ለእኛ የሚፈጸምልን ተራዳኢነታቸውንና ምክራቸውን የተቀበልን እንደሆን ብቻ ነው፡፡ ምክንያቱም እነርሱም እንደ አምላካቸው በእኛ ነጻ ፈቃድ ውስጥ ጣልቃ አይገቡምና፡፡ እንዲህም ስለሆነ የሎጥ ሚስት ምንም እንኳ በመልአኩ እጅ ብትያዝም ለመልአኩ ቃል ባለመታዘዙዋና ለመዳን ባለመፍቀዱዋ የጨው ሐውልት ሆና ቀርታለች (ዘፍ.19፡26)፡፡ በእርግጥ ቅዱስ ጳውሎስ “በመላእክት የተነገረው ቃል ጽኑ ከሆነ መተላለፍና አለመታዘዝ የጽድቅን ብድራት ከተቀበለ..” (ዕብ.2፡2) በማለት እንደገለጠልን እግዚአብሔር ለላከው መልአክ አለመታዘዝ ታላቅ የሆነ ቅጣትን ማምጣቱ የማይቀር ነው፡፡ ስለዚህም ቤተ ክርስቲያን ልጆቹዋ የመላእክትን ተራዳኢነት አውቀው እንዲጠቀሙና የመንግሥቱ ወራሾች ለመሆን እንዲበቁ ስትል ለቅዱሳን መላእክት የመታሰቢያ ቀን በመስጠት በእነርሱ የምናገኛቸውን እርዳታዎች እንዲታወሱ ታደርጋለች፡፡ በዚህም መሠረት በህዳር ወር በዐሥራ ሁለተኛው ቀን ቤተ ክርስቲያናችን የታላቁ መልአክ የቅዱስ ሚካኤልን በዓለ ሲመት በታላቅ ድምቀት ታከብረዋለች፡፡ እንደ ቅዱሳን አባቶቻችን አስተምህሮ ህዳር 12 ቀን ታላቁ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል በኢዮር ባለችው በአራተኛይቷ ከተማ በሚኖሩት ኃይላት እና በአሥሩ ነገደ መላእክት ላይ አለቃ ሆኖ የተሾመበት ቀን ነው፡፡እግዚአብሔር ሳጥናኤልን በትዕቢቱ ምክንያት ከሥልጣኑ ገፍፎ ወደ ምድር ሲጥለው ቅዱስ ሚካኤል በእርሱ ቦታ በዐሥሩ ከተማ በመቶውም ነገደ መላእክት ላይ ተሹሟል፡፡(ይህን ሁለተኛውን ሹመት ያገኘው በሚያዚያ 2 እንደሆነ አክሲማሮስ በሚባለው የቤተክርስቲያናችን መጽሐፍ ላይ ሰፍሮ አናገኛለን፡፡) የቅዱስ ሚካኤል ሹመት በነገደ መላእክት ላይ ብቻ ግን አይደለም ፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ሕዝብ በሆኑት ላይም ጭምር ነው ፡፡ ይህም እንደሆነ እንድንረዳ በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር ሕዝብ የተባለውን እስራኤል ዘሥጋን ሲራዳና ሲጠብቅ እንደነበረ ተጽፎልን እናገኛለን፡፡ ለምሳሌ መጽሐፍ ቅዱስ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ለኢያሱ በኢያሪኮ ምድረ በዳ እንደተገለጠለት “… ዐይኑን አንሥቶ ተመለከተ እነሆም የተመዘዘ ሰይፍ የያዘ ሰው በፊቱ ቆመ፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ “ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ? አለው፡፡ እርሱም “እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁንም ወደ አንተ መጥቼአለሁ” (ኢያ.5፡13) ይለናል፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ሕዝበ እስራኤልን ከግብጽ ባርነት ነፃ ሲያወጣቸው ይመራቸው የነበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነበር፡፡ ሹመቱ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይም በመሆኑ ስለ እነርሱ ዲያብሎስ ይዋጋው፣ በጸሎትም ይራዳቸው ነበር፡፡ ነገር ግን ኃጢአት ሠርተው ሲያገኛቸው ለእግዚአብሔር አድልቶ ኃጢአተኞችን ስለሚቀጣ እግዚአብሔር ሕዝቡን “በፊቱ ተጠንቀቁ ቃሉንም አድምጡ ስሜም በእርሱ ስለሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት” (ዘጸ.23፡21)ብሎ አስጠንቅቋቸው ነበር፡፡ ይህም ቅዱስ ሚካኤል በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ መሾሙን ያስረዳናል፡፡ ነገር ግን ከላይ የተጠቀሱት ጥቅሶች ሕዝበ እስራኤልን ይራዳቸው የነበረው ቅዱስ ሚካኤል ስለመሆኑ አያረጋግጥም የሚል ካለ “መልአክ” የተባለው ቅዱስ ሚካኤል ስለመሆኑ ቅዱስ ገብርኤል ወደ ነቢዩ ዳንኤል በተላከ ጊዜ
Show all...
👍 3