cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

በዚህ ቻናል የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርቶች እና የአበው ቀደምት የተናገሯቸው መንፈሳዊ ንግግሮች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች ይተላለፉበታል፡፡

Show more
Advertising posts
28 787Subscribers
+3624 hours
+2157 days
+49630 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የቀሲስ በላይ ጉዳይ ከቤተክርስቲያኗ ጋር የሚያገናኘው ነገር እንደሌለ አስታወቀች‼️ ከሰሞኑ ቀሲስ በላይ መኮንን በሀተኛ ሰነድ 6 ሚሊዮን 50 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ገንዘብ ለማዘዋወር ሞክረዋል በሚል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉበት ጉዳይ ከቤተክርትያኗ ጋር የሚያገናኘው ምንም ነገር እንደሌለ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ማስታወቋን ዶቸቬለ ዘግቧል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ግለሰቡ በቤተክርስቲያኗ በከፍተኛ ኃላፊነት የሚያገለግሉ ቢሆንም፤ ተጭበርብሯል ከተባለው ሰነድ ጋር ግን ቤተክርስቲያኗን የሚያገናኛት ምንም ነገር እንደሌለ አስታውቃለች፡፡ መምህር ዶ/ር አካለወልድ ተሰማ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የመንበረ ፓትሪያርክ ህዝብ ግንኙነት የሚዲያ ክፍል ዋና ኃላፊ “ሊቀ አዕላፍ በላይ መኮንን በህግ ጥላ ስር በዋሉበት ጉዳይ ላይ ቤተክርስቲያን ጉዳዩን የመከታተል ጥረት ላይ ትገኛለች ማለታቸውን  ሸገር ታይምስ ሚዲያ ከዜና ምንጩ ዘገባ ለመመልከት ችሏል። ኃላፊው “እስካሁን በተደረገው ክትትል “ሊቀ አዕላፍ በላይ መኮንን በህግ ጥላ ስር የዋሉበት ጉዳይ ከቤተክርስቲያናችን ጋር የሚያገናኘው ምንም ጉዳይ እንደሌለና በግል ህይወታቸው ውስጥ የገጠማቸው ነገር እንደሆነ ነው የተረዳነው” ብለዋል። መምህር ዶ/ር አካለወልድ አክለውም በቀጣይ ጉዳዩ ቤተክርስቲያንን የሚጎዳ ነገር አለው ወይ? የሚለው በህግ ክፍል በኩል ማጣራት እንዲደረግ ትዕዛዝ መተላለፉንም አመልክተዋል፡፡
Show all...
👍 19🙏 2 1
"እግዚአብሔር የሚወዳችሁ እናንተም የምትወዱት ልጆቼ ሆይ! ወርሐ ጾሙ ሲያልቅ ባዶ እጃችንን እንዳንገኝ በኹሉም ረገድ እንበርታ ብዬ እማልዳችኋለሁ፡፡ በጾም እየደከሙ ሳለ የጾምን ዋጋ ሳያገኙ መቅረት አለና፡፡ "ይህስ እንደምን ነው?" ያላችሁኝ እንደኾነም "ከምግበ ሥጋ እየጾምን ሳለ የኃጢአትን መብል ስንመገብ፣ ሥጋን ከመብላት ተከልክለን ሳለ የድኻውን ቤት ስንበረብር፣ ወይንን ከመጠጣት ታቅበን ሳለ በክፉ መሻቶች ስንሰክር፣ ቀን ሙሉ ምግብ ሳንበላ ውለን ሳለ ዓይናችን ግን ክፉ ነገሮችን ሲመለከት ነዋ" ብዬ እመልስላችኋለሁ፡፡" #ቅዱስ_ዮሃንስ_አፈወርቅ
Show all...
65🙏 12👍 1🏆 1
በቤትህ ያለው ዳቦ ለተራበው ሰው የሚውል(ንብረቱ) ነው፥ በልብስ ማስቀመጫህ ውስጥ ያለው የማትጠቀመው ኮት የችግረኛው ገንዘቡ ነው፥ በጫማ ማስቀመጫህ ውስጥ አልፈልገውም ብለህ ሊበላሽብህ የሆነው ጫማ የደሃው ጫማ (ጫማ ለሌለው ገንዘቡ) ነው ፥ ያከማቸኸው ገንዘብ ለድሃው የሚገባው ነው.... ዛፍ በፍሬው ይታወቃል፥ ሰውም በድርጊቱ፡፡ መልካም ስራ መቼም አይጠፋም፡፡ መልካም እርዳታን የሚዘራ፥ ወዳጅነትን ያጭዳል፡፡ ደግነትን የሚተክል ፍቅርን ይሰበስባል፡፡ "ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ ብቻ የለብንም፥ ነገር ግን ካነበብነው ተምረን ማደግ አለብን፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ምንም የማይጠቅም ነገር እንዳልተጻፈ ተገንዘብ፡፡ አሁንም ለጥንካሬ፣ ለመታገስ፣ ለመዳን፣ ለመለወጥ ጊዜ አለህ! ተኝተሃልን? ንቃ! ኃጢአት ሰርተሃልን? እንግዲያውስ  መስራቱን አቁም፡፡ #ቅዱስ_ባስልዮስ_ዘቂሳርያ @beteafework    @beteafework @beteafework    @beteafework @beteafework    @beteafework
Show all...
54👍 6🙏 2
እሺ ብትሉ… ልጆቼ! እስኪ ምላሴን ላሰናብትባችሁና እናንተም በትዕግሥት አድምጡኝ! የቤት ሠራተኛ አላችሁ እንበል፡፡ ይህቺ የቤት ሠራተኛችሁ የለበሰችውንና በወጥ፣ በአመድ እንዲሁም በሌላ ቆሻሻ እድፍ ያለ ልብሷን ትለብሱ ዘንድ ትፈቅዳላችሁን? በእርግጠኝነት አትፈቅዱም፡፡ ግን የብዙዎቻችን ሰውነት ከዚህ ልብስ በላይ መቆሸሽዋስ ታውቃላችሁን? ልጆቼ! ንግግሬ በጣም እንደሚያሳምም አውቃለሁ፤ ግን ምን ላድርግ? የተስተካከለ ሕይወት ቢኖረን እንዲህ የምናገር ይመስላችኋልን? በፍጹም! አንድ የቆሰለ የሰውነት ክፍል ቢኖራችሁ ሐኪሙ ይህን ቁስላችሁ በጣቱ ሳይነካካ ማከም ይችላልን? አይችልም! እኔም እንዲህ ቁስላችሁን ካልነካካሁት በስተቀር ማከም አልችልም፡፡ ለነገሩ ሰው ሰውነትህን አትንካ ማለት ይቻላልን አይቻልም! ታድያ እኔና እንናተ እኮ አንድ አካል ነን፡፡ በክርስቶስ አንድ ኾነን የለምን? እንግዲያውስ ንግግሬን አትጥሉት፤ ክፉ ግብራችሁን እንጂ፡፡ ችግሩ ከማን ነው ከእኛው ወይስ ከቆሻሻው? አንድ ወደ ትዕይንት (ቲያትር) ቤት የሄደ ወጣት ገላዋን ገላልጣ የምትተውን ተዋናይትን አይቶ ዝሙትን መፈጸም የማያስብ ማን ነው? ደጋግሞ የዝሙት ዘፈንን የሚሰማ ሰው ዝሙትን ከመፈጸም መቋቋም እችላለሁ የሚል ማን ነው? ቀኑን ሙሉ የዝሙት ጽሑፎችን ሲያነብ የሚውል ሰው ዝሙትን ከመፈጸም መጠበቅ እችላለሁ የሚል ማን ነው? ልጆቼ! ትዕይንቱን እያየነው፣ ዘፈኑን እየዘፈንነው፣ መጽሐፉንም እያነበብነው ኾኖም ግን መፍትሔ ካላገኘንበት ችግሩ እየባሰ የሚሄድ አይደለምን? እኛ ፈቃደኞች ከኾንን ግን መፍትሔው በሥጋችን ላይ ካለው ደዌ በላይ በጣም ቀላል ነው፡፡ ምክንያቱም የሥጋችን ቁስል ሐኪም፣ መድኃኒት፣ ጊዜ ያስፈልጓል፡፡ የነፍሳችንን ቁስል ግን ፈቃድ በቂ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔርን የማያውቁ አሕዛብ ከእኛ በላይ በንጽሕና ሲኖሩ ሳይ በጣም አፍራለሁ፡፡ እንግዲያውስ ልጆቼ እንመለስ፡፡ ያቆሸሹንን ነገሮች እንጣላቸው፤ እንቁረጣቸው፤ እናስወግዳቸው፡፡ ሰነፎች አንሁን፡፡ ውሳኔው የእኛው ነው፡፡ መጽሐፍ ሲናገር “እሺ ብትሉ ለእኔም ብትታዘዙ የምድርን በረከት ትበላላችሁ፤ እምቢ ብትሉ ግን ብታምፁም ሰይፍ ይበላችኋል” ይላል /ኢሳ.1፡19-20/፡፡ ስለዚህ ሁሉም ነገር በእኛ እሺታና እምቢታ የተወሰነ ነው ማለት ነው፡፡ የምንኮነነውም የምንመሰገነውም በዚሁ መሠረት ነው ማለት ነው፡፡ መድኃኒዓለም በመንግሥቱ በመጣ ጊዜ ኑ እናንተ የአባቴ ብሩካን ከሚላቸው ጋር በቸርነቱ ይደምረን አሜን፡፡ ምንጭ፦ ሰማዕትነት አያምልጣችሁ መጽሐፍ በ ገብረ እግዚአብሔር ኪደ
Show all...
67👍 11🏆 2💯 1
"ድኃ በቤትኽ ደጃፍ ይጮኻልን? ተነስተህ በደስታ የቤትህን ደጅ ክፈትለት የድኃውን ልመና ቸል አትበል፡፡ በነፍሱ የመረረው ነውና ቢረግምህ እግዚአብሔር አቤቱታውን ይሰማዋል፡፡ ስለዚህ ይረግምህ ዘንድ ምክንያት አትሁነው አዝኖ ከሆነ በመልካም መስተንግዶ ደስ አሰኘው፡፡ በኀዘን የከበደው ልቡ በአንተ ይረፍ፤ በሕይወት ዘመንህ ማጣት የሚያመጣቸውን ስቃዮች ታውቃቸዋለህና ችግረኛውን ከቤትህ ደጅ አትመልሰው፡፡" #ቅዱስ_ኤፍሬም_ሶሪያዊ
Show all...
138👍 9
በፍቅር ላዚምህ ፍቅር ነህ ጌታዬ በደም የገዛኸኝ ባለውለታዬ (ሰብስክራይብ እና ሼር እያደረጋችሁ) https://youtu.be/-oXwx5Tv3Q8?si=tN33BoOfnwOIsezT https://youtu.be/-oXwx5Tv3Q8?si=tN33BoOfnwOIsezT https://youtu.be/-oXwx5Tv3Q8?si=tN33BoOfnwOIsezT
Show all...
በፍቅር ላዚምህ - በዲያቆን ዘአማኑኤል #eotc #mahiberekidusan #ሄኖክ_ኃይሌ #ማኅበረ_ቅዱሳን

14👍 3💯 2
የሌሊቱ ተማሪ ኒቆዲሞስ ኒቆዲሞስ ፈሪሳዊ፥ ከአይሁድ አለቆችና መምህራና አንዱ ነው። በዮሐ. 3÷1 ከፈሪሳውያን ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የተባለ አንድ ሰው እንደነበረና እርሱም በሌሊት ወደ ጌታችን መጥቶ እንደተማረ ተጠቅሷል። (ዮሐ 1÷2) በአይሁድ አለቆች ፊትም ”ሕጋችን አስቀድሞ ሳይሰማ የሠራውንም ሳያውቅ በሰው ይፈርዳልን?” በማለት ስለ መድኃኔዓለም ክርስቶስ የተናገረ እሱ ነው ኒቆዲሞስ “መምህር ሆይ ልታስተምር ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደመጣህ እናውቃለን እግዚአብሔር ከርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርገውን ይህን ተአምር ሊያደርገ የሚችል የለምና።" በማለት ተናገረ።(ዮሐ3፥2) በዚህ ጊዜ ጌታችን የገነት በር ስለሆነው ስለ ምስጢረ ጥምቀት አስፍቶና አምልቶ በምሳሌ ጭምር አስረዳው። "እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ዳግመኛ ያልተወለደ ሰው የእግዚአብሔርን መንግሥት ለማየት አይችልም” (ዮሐ 3፥3) በማለት መንፈሳዊ እውቀት የጎደለው መሆኑን አሳይቶ ዳግመኛ ያልተወለደ ሰው ከእግዚአብሔር መንግሥት ውጪ እንደሚሆን አስርግጦ ነገረው። በዚህም ታላቅ ምስጢርን ሊገልጥለት ወደደ። ይህ አነጋገር ከአይሁድ አለቆች አንዱ ለሆነው ፈሪሳዊ ሰው ከባድ ነበር። ምሥጢሩም ቢጸናበት ጊዜ ጌታን እንዲህ በማለት ጠየቀው “ሰው ከሸመገለ በኋላ እንደምን ሊወለድ ይችላል? ዳግመኛ ይወለድ ዘንድ ወደ እናቱ ማሕጸን ተመልሶ ሊገባ ይችላልን?“። (ዮሐ 3፥4) ጌታችንም ለኒቆዲሞስ መልሶ የአዳም ልጆች ሁሉ ከውሃና ከመንፈስ ዳግም ካልተወለዱ (በመንፈስ ቅዱስ መታደስን በሚያሰጥ ጥምቀት ካልተጠመቁ) መንግሥተ ሰማያትን መውረስ እንደማይችሉ ነገረው። ወስብሀት ለእግዚአብሔር!!! @beteafework    @beteafework @beteafework    @beteafework
Show all...
43👍 18
29👍 5💔 1
#ኒቆዲሞስ (የዐቢይ ጾም ሰባተኛ ሳምንት) ከፈሪሳውያን ወገን የአይሁድ አለቃ በነበረው በኒቆዲሞስ የተሰየመ ሰንበት ነው፡፡ የአይሁድ አለቆች አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን “ምልክት አሳየን” እያሉ ይፈታተኑት ነበር፡፡ ስለሞቱና ትንሣኤው በምሳሌ ቢነግራቸው አልገባቸውም፡፡ ሲያስተምር ብዙዎች ያምኑ ነበር፡፡ ለአይሁድ አለቆች ግን ጭንቅ ነበር፤ የታመሙ ሲፈወሱ ሕጋችን ተሻረ ይሉ ነበር፡፡ በዚህ ሁሉ ተአምራትና ትምህርት የአይሁድ አለቆች ክርስቶስን ለመክሰስ በሚፈልጉበት ወቅት ከአይሁድ አለቆች አንዱ ኒቆዲሞስ በቀን እንዳያደርገው አይሁድን ፈርቶ አንድም ጊዜ አላደርሰው ብሎ እንደ አይሁድ አለቆች ኢየሱስን መቃወሙን ትቶ በሌሊት ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ሄደ፡፡ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በነፍስ የታመሙትን በቃሉ በሥጋ የታመሙትን በተአምራቱ ሲፈውስ፤ ኒቆዲሞስ ሰምቶና ተመልክቶ “መምህር ነኝ” ብሎ በመምህርነቱ ሳይኮራ አለቅነቱን መመኪያ ሳያደርግ፡፡ በልቦናው የተሳለውን እውነትን የመፈለግ ስሜት አንግቦ ጌታው መምህሩ ዘንድ በሌሊት ገሠገሠ ዮሐ.3÷1ደርሶም ምስክርነቱን እንዲህ ሲል መስጠት ጀመረ “መምህር ልታስተምር ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደመጣህ እናውቃለን፡፡ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርገውን ተአምራት ሊያደርግ የሚችል የለምና” ዮሐ.9÷24፣ የሐዋ.ሥራ 10÷38 በማለት መመስከር ሲጀምር ጎዶሎን የሚሞላ፡፡ አላዋቂነት በአዋቂነት የሚለውጥ፡፡ ከምድራዊ እውቀት ወደ ሰማያዊ ምስጢር የሚያሸጋግር አምላክ፡፡ “ዳግመኛ ያልተወለደ የእግዚአብሔርን መንግሥት ለማየት አይችልም” ዮሐ.3÷6 ,1ጴጥ.1÷23 በማለት የአይሁድ መምህር ለሆነው ኒቆዲሞስ ቢያስተምረው ስለዳግመኛ መወለድ ከመጽሐፍ ቢያገኘውም ምስጢሩ አልተገለጠለትምና “ሰው ከሸመገለ በኋላ ዳግመኛ መወለድ እንደምን ይቻላል? ዳግመኛ ይወለድ ዘንድ ወደ እናቱ ማኅፀን ተመልሶ መግባት ይችላልን?” በማለት ጥያቄ አቅርቧል፡፡ “እውነት እውነት እልሃለሁ ዳግመኛ ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ ያልተወለደ ወደ እግዝአበሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም፡፡ ኤፌ.5÷26 ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፡፡ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነውና፡፡ በማለት አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቢያስረዳው ምስጢሩ ከአቅሙ በላይ የሆነበት ኒቆዲሞስ እንደምን ይቻላል? በማለት ጠይቋል፡፡ አበ ብዙኀን አብርሃም ከአምላኩ ሞገስን አግኝቶ፤ የሰዶምና ገሞራ ጥፋት እንዳይደርስ እያማለደ ከእግዚአብሔር ጋር ሲነጋገር እንደ ነበረ፤ ኒቆዲሞስም አላዋቂነቱን አምኖ ያልገባውን ምስጢር አምላኩን የመጠየቅ ዕድል በማግኘቱ ሲጠይቅ፣ ኢየሱስ ክርስቶስም “አንተ የእስራኤል መምህራቸው ነህ ግን ይህን ነገር አታውቅምን? በምድር ያለውን ስንነግራቸው ካላመናችሁ በሰማይ ያለውን ብንነግራችሁ እንደምን ታምናላችሁ? ከሰማይ ከወረደው ከሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም፡፡ ሙሴ ምድረ በዳ እባቡን እንደ ሰቀለ የሰው ልጅ እንዲሁ ይሰቀላል፡፡ ያመኑበት ሁሉ ለዘለዓለም ሕያው ሆኖ እንዲኖር እንጂ እንዲጠፉ አይደለም…..” ዮሐ.3÷14፡፡ እያለ ለድኅነተ ዓለም እንደ መጣ ሰው በመብል፣ አምላኩን ከድቶ ልጅነቱን ትቶ ከእግዚአብሔር ቢለይም የሰው ልጅ ያጣውን ልጅነት ለመመለስ ስመ ግብርና ሀብተ ወልድን ለመስጠት መምጣቱን አስረዳው። “ሐወጽከኒ ሌሊተ ወፈተንኮ ለልብየ፡፡ አመከርከኒ ወኢተረከ በዓመፃ በላዕሌየ፡፡ ከመ ኢይንብብ አፉየ ግብረ እጓለ እመሕያው፡፡ ልቤን ፈተንከው በሌሊትም ጎበኘኸኝ ፈተንከኝም ምንም አላገኘህብኝም፡፡ የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር ፈቃዴ ነው” መዝ.16÷3 እንዳለ ቅዱስ ዳዊት ምስጢረ ሥጋዌን የድኅነት ምስጢር ገልጾለታል፡፡ በሌሊት ከአምላኩ ተምሮ ምስጢሩ የተገለጸለት ኒቆዲሞስ ፍርሃት ርቆለት ቀድሞ በአደባባይ ሄዶ መማርን የፈራ ምስጢሩ ሲገለጽለት አይሁድ በሰቀሉት ዕለት ሳይፈራ ከአርማትያሱ ዮሴፍ ጋር ቅዱስ ሥጋውን ገንዞ ለመቅበር በቃ “ወአልቦ ፍርሃት ውስተ ተፋቅሮትነ፡፡ ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል ማቴ.27÷58፣ 1ዮሐ.4÷18 እንዲል፡፡ ያመነ የተጠመቀ ይድናል፡፡ ያላመነ ያልተጠመቀ ይፈረድበታል ማር.16÷16፡፡ ባለው አማናዊ ቃል ኪዳን መሠረት አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ አምላክነቱ አምነን ለመንግሥቱ ዜጋ እንድንሆን ለኒቆዲሞስ ምስጢሩን ጥበቡን የገለጸ አምላክ ለኛም ይግለጽልን፡፡ #የዕለቱ_የሰንበት_መዝሙር_እና_ግጻዌ #መዝሙር፦ ሖረ ኀቤሁ ዘስሙ ኒቆዲሞስ ወይቤሎ ለኢየሱስ ረቢ ሊቅ ንሕነ ነአምን ብከ ከመ እምኃበ አብ መጻእከ ከመ ትኩን መምህረ፤ ዕጓለ አንበሳ ሰከብከ ወኖምከ አንሥአኒ በትንሣኤከ፡፡ (ስሙ ኒቆዲሞስ የተባለው ሰው ወደ ጌታችን ኢየሱስ ሄደ፤ መምህር ሆይ ልታስተምር ከእግዚአብሔር አብ ዘንድ እንደመጣህ እናምንብሃለን አለው። የአንበሳ ደቦል ተኛህ፣ አንቀላፋህም፤ በትንሣኤህ አንሣኝ።) #መልዕክታት፦ ሮሜ 7÷1-12 "ወንድሞች ሆይ፥ ሕግን ለሚያውቁ እናገራለሁና ሰው ባለበት ዘመን ሁሉ ሕግ እንዲገዛው አታውቁምን? ያገባች ሴት ባልዋ በሕይወት ሲኖር ከእርሱ ጋር በሕግ ታስራለችና፤ ባልዋ ቢሞት ግን ስለ ባል ከሆነው ሕግ ተፈትታለች።... 1ኛ ዮሐ. 4 ÷18 - ፍጻሜ ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም፥ ፍርሃት ቅጣት አለውና፤ የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም። ..... የሐዋ.ሥራ 5÷34 - ፍጻሜ በሕዝብ ሁሉ ዘንድ የከበረ የሕግ መምህር ገማልያል የሚሉት አንድ ፈሪሳዊ በሸንጎ ተነሥቶ ሐዋርያትን ጥቂት ፈቀቅ እንዲያደርጉአቸው አዘዘ...... #ምስባክ፦ መዝ.16፥3 ሐወጽከኒ ሌሊተ ወፈተንኮ ለልብየ፡፡ አመከርከኒ ወኢተረክበ ዓመፃ በላዕሌየ፡፡ ከመ ኢይንብብ አፉየ ግብረ እጓለ እመ ሕያው፡፡ ትርጉም፦ በሌሊትም ጐበኘኸኝ፤ ልቤንም ፈተንኸው÷ ፈተንኸኝ÷ ዐመፅም አልተገኘብኝም፡፡ የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር #ወንጌል፦ ዮሐንስ 3፥1-12 "ከፈሪሳውያንም ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤ እርሱም በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ። መምህር ሆይ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርጋቸውን እነዚህን ምልክቶች ሊያደርግ የሚችል የለምና መምህር ሆነህ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ መጣህ እናውቃለን አለው።.... #ቅዳሴ - ዘእግዝእትነ ማርያም [ጎሥዐ] (#ማኅበረ_ቅዱሳን_ድረ_ገጽ እና #ግጻዌ)
Show all...
👍 28 17🙏 1