cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Addis Ababa Education Bureau

ይህ ቻናል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቴሌግራም ቻናል ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የተከናወኑ እንዲሁም ሀገራዊ ፣ አህጉራዊ እና አለማቀፋዊ የትምህርት መረጃዎች ተደራሽ የሚደረጉበት ነው፡፡

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
106 498
مشترکین
+3424 ساعت
+2797 روز
+37630 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

የሀሞስ ማለዳ የተማሪዎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በመዝገበ ብርሃን ቅድመ አንደኛ ፣ መካከለኛና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት (ቀን ሚያዚያ 24/ 2016 ዓ.ም) የሀሞስ ማለዳ የተማሪዎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በመዝገበ ብርሃን ቅድመ አንደኛ ፣ መካከለኛና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ፣መምህራንና እና አስተዳደር ሰራተኞች በተገኙበት ተካሄዳል፡፡ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ! What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D flickr :- https://www.flickr.com/photos/197652854@N04/ You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728 TikTok፡- https://www.tiktok.com/@aaeducationbureau Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/ Website: - aaceb.gov.et Email;- [email protected] Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
نمایش همه...
👍 4
የተማሪዎች ትምህርታዊ ጉብኝት በአንድነት ፓርክ (ቀን ሚያዚያ 23/ 2016 ዓ.ም) የዛሬ ተማሪዎች ነገ የሃገር ተረካቢዎች በመሆናቸው ስለሃገራቸው በቂ እውቀት እንዲኖራቸው እና ሀገር ወዳድ ዜጎች ሆነው እንዲያድጉ ይረዳቸው ዘንድ አንድነት ፓርክ በት/ት ቤት በኩል ለትምህርታዊ ጉብኚት ወደ ፓርኩ ለሚመጡ ተማሪዎች በ50% የመግቢያ ትኬት ዋጋ ቅናሽ አድርጓል። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ! What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728 TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/ Website: - aaceb.gov.et Email;- [email protected] Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
نمایش همه...
👍 1
ለ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተማሪዎች እንዲዘጋጁ የትሞህርት ሚኒስቴር አሳሰበ። የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ አየለች እሸቴ በጉዳዩ ዙሪያ በተዘጋጀ የአሰልጣኞች ስልጠና ማጠቃለያ ላይ እንደገለጹት የ2016 የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናና ኦላይን ለመስጠት ከሁሉም ክልሎች በተመረጡ 25 ከተሞች ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው። በወረቀት ከሚሰጠው አገር አቀፍ ፈተና ጎን ለጎን በቴክኖሎጁ ተደግፎ የሚሰጠው የኦንላይን ፈተና ተማሪዎች ከቦታ ቦታ ሳይጓጓዙ በየአካባቢያቸው ቤተሰቦቻቸው ጋር እያደሩ ፈተናውን እንዲወስዱ እንደሚያስችላቸው ሚኒስትር ዴኤታዋ ተናግረዋል። በመሆኑም ፈተናው እንዲሰጥባቸው በተመረጡ ከተሞች ፈተናውን በኦንላይን የሚወስዱ የዚህ ዓመት የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከወዲሁ እንዲዘጋጁ ወ/ሮ አየለች አሳስበዋል። በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላትም ከወዲሁ በቅንጅት በመስራት ሃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባም ጠቁመዋል። ወላጆች ስለፈተናው የተሻለ አረዳድና ግንዛቤ እንዲኖራቸው ልጆቻቸውን እንዲደግፉና በራስ መተማመን ወደፈተናው ሊገቡ የሚችሉበትን ዕድል ሊፈጥሩ እንደሚገባም አመላክተዋል። ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮም በኦን ላይን የሚሰጠውን ፈተና በተሻለ ደረጃ ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ሚኒስትር ዴኤታዋ ጠቁመዋል። የአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) በበኩላቸው ፈተናን ለተማሪዎች በኦንላይን መስጠት ምቹና ቀላል መሆኑን በዚሁ ጊዜ ጠቅሰው የኦንላይን ተፈታኞች ፈተናውን ከመውሰዳቸው በፊት ደጋግመው እንዲለማመዱ የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያሳያል።
نمایش همه...
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከሱፐርቪዝን ስራ ጋር በተገናኘ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን መሰረት በማድረግ በየደረጃው ለሚገኙ ሱፐርቫይዘሮች የሚሰጠውን የአቅም ግንባታ ስልጠና አጠናክሮ እንደሚቀጥል የቢሮው የአጠቃላይ ትምህርት ሱፐር ቪዥን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጸጋዬ አሰፋ ገልጸዋል፡፡ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ! What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D flickr :- https://www.flickr.com/photos/197652854@N04/ You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728 TikTok፡- https://www.tiktok.com/@aaeducationbureau Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/ Website: - aaceb.gov.et Email;- [email protected] Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
نمایش همه...
👍 18 4🥰 1
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ሱፐር ቪዥን ዳይሬክቶሬት ለክፍለከተማና ክላስተር ሱፐርቫይዘሮች ለሁለት ቀን የሰጠው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡ (ቀን ሚያዚያ 22/ 2016 ዓ.ም) ስልጠናው በዋናነት ከአዲሱ ስርአተ ትምህርት አተገባበር ጋር በተገናኘ የመምህራን እለታዊና አመታዊ እቅድ አዘገጃጀት ፤ በሱፐርቪዥን ጽንሰ ሀሳብና በአፈጻጸም ስለሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች እንዲሁም የተከታታይ ምዘና ሂደት እና(continus assessment) እና ተግባራዊ ጥናትን (action research) መሰረት አድርጎ በቢሮው የስርአተ ትምህርት ባለሙያዎችና ሱፐርቫይዘሮች ነው የተሰጠው፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በስልጠናው ማጠቃለያ ባስተላለፉት መልዕክት በከተማ አስተዳደሩ በየደረጃው የሚገኙ ሱፐርቫይዘሮች የመምህራንንም ሆነ ርዕሳነ መምህራንን አቅም እየገነቡ የተማሪዎች ውጤትና ስነ-ምግባር እንዲሻሻል የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው ሱፐርቫይዘሮቹ በስልጠናው ያገኙትን ግንዛቤ መሰረት በማድረግ እውቀትና ብቃትን ታሳቢ ያደረገ የድጋፍና ክትትል ስራ በመስራት የትምህርት ጥራት እንዲረጋገጥ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ በበኩላቸው የክፍለከታ እና ክላስተር ሱፐርቫይዘሮች በትምህርትቤቶች ድጋፍና ክትትል በሚያደርጉበት ወቅት የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችና መፍትሄዎች ዙሪያ በቡድን እና በጋራ ባደረጉት ውይይት በቂ ግንዛቤ ማግኘታቸውን ጠቁመው በቀጣይ በትምህርት ቤቶች ከእቅድ ዝግጅት ጀምሮ በአፈጻጸም የሚታዩ ልዩነቶችን በማቀራረብ የትምህርት ልማት ስራውን ውጤታማ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አስታውቀዋል፡፡
نمایش همه...
የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በበይነ መረብ ኦን ላይን ለመስጠት እየተከናወኑ በሚገኙ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት ዙሪያ ውይይት ተካሄደ ። (ቀን ሚያዚያ 22/ 2016 ዓ.ም) በውውይይቱ የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎችን ጨምሮ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን የተሳተፉ ሲሆን ውይይቱ ፈተናውን በበይነ መረብ ኦን ላይን ለመስጠት ከወዲሁ መከናወን በሚገባቸው የቅድመ ዝግጅት ተግባራት ዙሪያ ነው የተካሄደው። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በውይይቱ እንደገለጹት የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በከተማ አስተዳደሩ በበይነ መረብ ለመስጠት ከወዲሁ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት በመከናወን ላይ እንደሚገኙ ጠቁመው ፈተናው ኦን ላይን እንደመሰጠቱ ኮምፒውተሮች ፣ ላፕቶፖች እና ታብሌቶችን ጨምሮ ሎሎች አስፈላጊ ግብአቶችን የማሟላት ስራ መጀመሩን አስታውቀዋል። ኃላፊው አክለውም የግል ትምህርት ቤቶች ለፈተናው አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን የማዘጋጀት ተግባራቸውን ከወዲሁ በመጀመር ፈተናው በታቀደለት መርሀ ግብር እንዲሰጥ የበኩላቸውን ኃላፊነት ሊወጡ እንደሚገባም አስገንዝበዋል። የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሀምሌ 3 እስከ 5 የማህበራዊ ሳይንስ እንዲሁም ከሀምሌ 9 እስከ 11/2016 ዓ.ም የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ በትላንትናው እለት መግለጹ ይታወቃል።
نمایش همه...
በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በመደረግ ላይ የሚገኘው የመስክ ምልከታ ዛሬም ቀጥሎ ተካሄደ። (ቀን ሚያዚያ 22/ 2016 ዓ.ም) በምልከታው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ፣ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ኡመር ፣የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም አስተባባሪ ዶክተር ታቦር ገብረ መድህን እንዲሁም ለቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም ድጋፍ ከሚያደርገው ቢግ ዊን ድርጅት የመጡ እንግዶችና ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት የተሳተፉ ሲሆን ጉብኝቱ በደጃዝማች ውንድይራድ እና መሪ ህዳሴ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ነው የተካሄደው። በከተማ አስተዳደሩ የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም ውጤታማ እንዲሆን ትኩረት ከተደረገባቸው ዘርፎች መካከል የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንደሚገኙበት እና ዛሬ ጉብኝት የተካሄደባቸው ተቋማት ፕሮግራሙ ውጤታማ እንዲሆን በልዩ ትኩረት ድጋፍ እየተደረገባቸው የሚገኙ መሆናቸው በምልከታው ተገልጿል። ጉብኝቱ የተካሄደባቸው የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራምን ውጤታማ በማድረግ ሞዴል ሆነው ሌሎች ተቋማት ልምድ የሚቀስሙባቸው እንዲሆኑ በከፍተኛ ትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ገልጸው ቢሮው በተቋማቱ እየተገነቡ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ጨምሮ መማሪያ ክፍሎችና አጠቃላይ ምድረ ግቢያቸው በስርአተ ትምህርቱ የተቀመጠውን ጫወታን መሰረት ያደረገ የማስተማር ስነ ዘዴ በአግባቡ ተግባራዊ እንዲያደርጉ ድጋፍና ክትትሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
نمایش همه...
👍 7 2
የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላት የተጣራ የአንድ ወር ደምወዛቸውን ለ"ፅዱ ጎዳና ኑሮ በጤና" ንቅናቄ በማበርከት ንቅናቄውን ተቀላቅለዋል። መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ! What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728 TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/ Website: - aaceb.gov.et Email;- [email protected] Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
نمایش همه...