ተንሥኡ ሳይኮ ቢዝነስ - Tensiu Psycho Business
Open in Telegram
ስለ እኛ ተንሥኡ ሳይኮ ቢዝነስ (Tensiu Psycho Business) በጥናትና ምርምር ላይ በመመሥረት፣ በሰው ልጅ ሥነ-ልቦናዊ ዕድገት እና በዘመናዊ የቢዝነስ ስኬት መካከል ያለውን ቁርኝት የሚያጠናክር ቀዳሚ ተቋም ነው። እንደ ሀገር ያሉብንን የኢኮኖሚ እና የሥነ-ልቦና ፈተናዎች በዘላቂነት ለመፍታት ቴክኖሎጂን ማዕከል ያደረጉ መፍትሔዎችን ይዞ ብቅ ብሏል። ያግኙን 📞 ስልክ፦ +251 91 269 1
Show more1 385
Subscribers
-124 hours
-107 days
-2130 days
Data loading in progress...
Similar Channels
Tags Cloud
No data
Any problems? Please refresh the page or contact our support manager.
Incoming and Outgoing Mentions
---
---
---
---
---
---
Attracting Subscribers
September '26
September '26
+1
in 0 channels
August '26
+22
in 0 channels
Get PRO
July '26
+6
in 0 channels
Get PRO
June '26
+11
in 0 channels
Get PRO
May '26
+8
in 0 channels
Get PRO
April '26
+3
in 0 channels
Get PRO
March '26
+1
in 0 channels
Get PRO
February '26
+1
in 0 channels
Get PRO
January '26
+3
in 0 channels
Get PRO
December '250
in 0 channels
Get PRO
November '25
+2
in 0 channels
Get PRO
October '25
+6
in 0 channels
Get PRO
September '25
+3
in 0 channels
Get PRO
August '25
+2
in 0 channels
Get PRO
July '25
+5
in 1 channels
Get PRO
June '25
+4
in 0 channels
Get PRO
May '25
+8
in 2 channels
Get PRO
April '25
+15
in 0 channels
Get PRO
March '25
+11
in 0 channels
Get PRO
February '25
+4
in 0 channels
Get PRO
January '25
+12
in 0 channels
Get PRO
December '24
+7
in 0 channels
Get PRO
November '24
+9
in 0 channels
Get PRO
October '24
+7
in 1 channels
Get PRO
September '24
+57
in 3 channels
Get PRO
August '24
+11
in 0 channels
Get PRO
July '24
+3
in 0 channels
Get PRO
June '24
+8
in 0 channels
Get PRO
May '24
+34
in 1 channels
Get PRO
April '24
+23
in 1 channels
Get PRO
March '24
+15
in 0 channels
Get PRO
February '24
+13
in 0 channels
Get PRO
January '24
+17
in 2 channels
Get PRO
December '23
+12
in 0 channels
Get PRO
November '23
+9
in 0 channels
Get PRO
October '23
+17
in 1 channels
Get PRO
September '23
+9
in 0 channels
Get PRO
August '23
+12
in 0 channels
Get PRO
July '23
+15
in 0 channels
Get PRO
June '23
+23
in 0 channels
Get PRO
May '23
+17
in 0 channels
Get PRO
April '23
+14
in 0 channels
Get PRO
March '23
+24
in 0 channels
Get PRO
February '23
+48
in 0 channels
Get PRO
January '23
+20
in 0 channels
Get PRO
December '22
+17
in 0 channels
Get PRO
November '22
+18
in 0 channels
Get PRO
October '22
+15
in 0 channels
Get PRO
September '22
+22
in 0 channels
Get PRO
August '22
+11
in 0 channels
Get PRO
July '22
+40
in 0 channels
Get PRO
June '22
+39
in 0 channels
Get PRO
May '22
+38
in 0 channels
Get PRO
April '22
+64
in 0 channels
Get PRO
March '22
+36
in 0 channels
Get PRO
February '22
+120
in 0 channels
Get PRO
January '22
+27
in 0 channels
Get PRO
December '21
+62
in 0 channels
Get PRO
November '21
+62
in 0 channels
Get PRO
October '21
+36
in 0 channels
Get PRO
September '21
+250
in 0 channels
Get PRO
August '21
+34
in 0 channels
Get PRO
July '21
+52
in 0 channels
Get PRO
June '21
+88
in 0 channels
Get PRO
May '21
+57
in 0 channels
Get PRO
April '21
+18
in 0 channels
Get PRO
March '21
+16
in 0 channels
Get PRO
February '21
+29
in 0 channels
Get PRO
January '21
+22
in 0 channels
Get PRO
December '20
+5 139
in 0 channels
| Date | Subscriber Growth | Mentions | Channels | |
| 08 September | 0 | |||
| 07 September | 0 | |||
| 06 September | 0 | |||
| 05 September | +1 | |||
| 04 September | 0 | |||
| 03 September | 0 | |||
| 02 September | 0 | |||
| 01 September | 0 |
Channel Posts
| 2 | 40 ዓመት ቢያልፍህ እኖኳን፤ 13 ጊዜ ዩኒቨርሲቲ መግባት እንዳቃተው የጃክ ማ ስኬት ላይ መድረስ ትችላለህ!
የጃክ ማ የሕይወት ታሪክ ተስፋ አለመቁረጥ ለስኬት ያለውን ወሳኝ ሚና በግልጽ የሚያሳይ ነው። ጃክ ማ በታሪኩ እንደገለጸው 13 ጊዜ ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት ባደረገው ሙከራ መውደቁ እና ከ KFC የሥራ ቅጥር ኢንተርቪው ከ24 አመልካቾች መካከል እሱ ብቻ ተመርጦ ውድቅ መደረጉ፤ ውድቀት የአንድ ሰው መጨረሻ ሳይሆን ለበለጠ ውጤት መዘጋጃ መሆኑን ያረጋገጠበት አጋጣሚ ነው። በተጨማሪም በማኅበረሰቡ ዘንድ በውጫዊ መልኩ ምክንያት የማግለልና የማሳነስ ፈተና ቢገጥመውም፤ በራሱ ላይ ጥርጣሬ ሳያድርበት በቁርጠኝነት መሥራቱ አሊባባ የተባለውን የዓለም አቀፍ የኤሌክትሮኒክስ ንግድ ግዙፍ ኩባንያ እንዲመሠርት አድርጎታል። ይህም የሰዎች ክብርና አመለካከት በአንድ ሰው ውጫዊ ገጽታ ሳይሆን በሚፈጥረው እውነተኛ ለውጥና በሚያስመዘግበው ስኬት ላይ የሚመሠረት መሆኑን ማሳያ ነው።
በሌላ በኩል ሕይወት በከፍታና በዝቅታ የታጀበች መሆኗን ተረድቶ ውጣ ውረዶችን እየሳቀ የማለፍ ፍልስፍናው፤ የአእምሮ ጥንካሬን የመገንባትን አስፈላጊነት ያሳያል። ብዙ ጊዜ ሰዎች በወጣትነት ዕድሜያቸው ፈጣን ስኬት ካላገኙ ተስፋ የመቁረጥ አዝማሚያ ይታይባቸዋል፤ ሆኖም ግን እንደ ጃክ ማ፣ ኬነል ሳንደርስ (የ KFC መሥራች) እና ራይ ክሮክ (የማክዶናልድ መሥራች) ያሉ የዓለም ታላላቅ ስኬታማ ሰዎች ሕይወት እንደሚያሳየው፤ አብዛኞቹ ቁልፍ የዕድገት እርምጃቸውን ያረጋገጡት ከ40 ዓመት ዕድሜያቸው በኋላ ነው። ይህም ብስለት፣ የሕይወት ልምድ እና በተደጋጋሚ ውድቀቶች ውስጥ ያገኟቸው ትምህርቶች ለትልቅ ስኬት መሠረት እንደሚሆኑ ማረጋገጫ ነው። ስለዚህ ማንኛውም ሰው የሚያጋጥሙትን ፈተናዎች እንደ መሰናክል ሳይሆን እንደ ትምህርት በመቁጠር፤ ጊዜው እስኪደርስ ድረስ ሳይሰለችና ተስፋ ሳይቆርጥ በትዕግስት መጓዝ እንዳለበት ይህ የጃክ ማ ሕይወት ያስተምረናል። | 100 |
| 3 | No text... | 87 |
| 4 | ስለሆነም ስኬት ማለት መሸጥ ብቻ ሳይሆን አደጋዎችን መቆጣጠርና የገንዘብ እንቅስቃሴን በትክክል መምራት ጭምር ነው።
ለጀማሪዎች ተግባራዊ የንግድ ጅማሮ ደረጃዎች (Step-by-Step Guide)
ደረጃ 1፦ የገበያ ችግርን ይለዩ — ሰዎች ምን ይፈልጋሉ? ምን ማግኘት አቅቷቸዋል?
ደረጃ 2፦ የደንበኛ ፍላጎትን ያጠናሉ — በግምት ሳይሆን ሰዎች የሚፈልጉትን መረጃ በመፈለግ ያረጋግጡ።
ደረጃ 3፦ ታማኝ አቅራቢዎችን ይፈልጉ — በአንድ አቅራቢ ላይ ብቻ ሳይደገፉ 2 ወይም 3 አማራጮችን ይያዙ።
ደረጃ 4፦ በትንሹ ይጀምሩ — ሁሉንም ለማቅረብ ከመሞከር በ1 ወይም 2 ምርቶች ይጀምሩ።
ደረጃ 5፦ ጥሩ ይዘት (Content) ያዘጋጁ — ግልጽ ፎቶዎች፣ ቪዲዮዎችና መግለጫዎችን ያዘጋጁ።
ደረጃ 6፦ ማኅበራዊ ሚዲያዎችን ይጠቀሙ — ደንበኞችዎ ባሉበት (Telegram, TikTok, FB, WhatsApp) ያስተዋውቁ።
ደረጃ 7፦ የደንበኞችን ጥያቄ ያደምጡ — የሚጠይቋቸው ጥያቄዎች ለገበያ ጥናትዎ ትልቅ ግብዓት ናቸው።
ደረጃ 8፦ ውጤቱን ይገምግሙ** — የትኛው ምርት እንደሚሸጥና የትኛው እንደማይሄድ ይለዩ።
ደረጃ 9፦ ትርፍዎን መልሰው ኢንቨስት ያድርጉ — ያገኙትን ትርፍ ወዲያውኑ ከመጠቀም ይልቅ ቢዝነሱን ለማሳደግ ይጠቀሙበት።
ደረጃ 10፦ ይማሩ፣ ያሻሽሉ፣ ያሳድጉ — ከመጀመሪያው ፍጹምነትን አይጠብቁ፤ እየሠሩ ያሻሽሉ።
ከዚህ ሁሉ በስተጀርባ መታወቅ ያለበት ግን፤ ሁሉ ነገር እስኪሟላልዎ አትጠብቁ። ባላችሁ ነገር ጀምሩ፣ ከምታደርጉት ነገር ተማሩ፣ የሚሠራውን አሻሽሉ፣ ደረጃ በደረጃ አድጉ።
ብዙ ሰዎች "ገንዘብ ሲኖረኝ..."፣ "ምቹ ጊዜ ሲመጣ..." እያሉ ህልማቸውን ያዘገዩታል፤ ነገር ግን ፍጹም ሁኔታዎች መቼም ላይመጡ ይችላሉ። የስኬታማ ነጋዴዎች ምሥጢር ባላቸው ነገር መጀመራቸው ነው።
🌐 ለበለጠ መረጃ ተከተሉን፦
🔴 YouTube -
-https://tensiu.openinapp.co/psychobusiness
🔵 Facebook -
- https://www.facebook.com/share/1Dd7eJrkgj/
🟦 LinkedIn
https://lnkd.in/ejVyVbc2
✈️ Telegram
- https://t.me/tensiupsychobusiness
🎵Tiktalk
- tiktok.com/@tensiupsychobusiness
#OnlineReselling #Entrepreneurship #EthiopiaBusiness #BusinessOpportunity #OnlineBusiness #DigitalBusiness #StartupEthiopia #BusinessMindset #SmallBusiness #Entrepreneur #BusinessGrowth #StartSmallThinkBig | 124 |
| 5 | የኦንላይን ሥራ ምንድነው? በስንት ብር መጀመር ይቻላል? ወቅታዊው እውነታ!
ከዚህ ትምህርት የምንወስደው ዋናውና ትልቁ መልዕክት፤ ቢዝነስ ለመጀመር፣ ለመማርና ለማደግ ሁልጊዜ ብዙ ካፒታል አያስፈልግም። አነስተኛ ገንዘብ የንግድ ክህሎትን ለማዳበር፣ ገበያውን ለመፈተሽና ተግባራዊ ልምድ ለማግኘት በቂ ነው።
ለምሳሌ በ500 ብር ወይም አሁን እጃችን ላይ ያለንን ዕውቀት፣ ዕሴት፣ ሰው፣ ወዘተ… ተጠቅመን ነገ ባለሀብት መሆን ይቻላል። ከፍተኛ የሥራ መጀመሪያ ካፒታል ስላለን ብቻ ሃብታም አንሆንም። የንግድ ዓለም እንዲህ አይሠራም። ካፒታል ብቻውን ስኬታማ ቢዝነስ አይፈጥርም። የገበያ ዕውቀት፣ የደንበኛ እምነት፣ የሽያጭ ክህሎት፣ ትክክለኛ መረጃ፣ ዲሲፕሊንና ጥሩ አፈጻጸም ናቸው አነስተኛ ገንዘብን ወደ እውነተኛ የንግድ ዕድል የሚቀይሩት።
1. የኦንላይን መልሶ ሽያጭ (Online Reselling) ሥራ ምንድነው?
ኦንላይን ሪሴሊንግ ማለት የግድ የራስን ምርት ማምረት ማለት አይደለም። ሂደቱ በጣም ቀላል ነው። አንድ አካል ምርት አለው። ሌላው ደግሞ ያንን ምርት ይፈልጋል። የእርስዎ ሚና ምርቱን ከፈላጊው (ከደንበኛው) ጋር ማገናኘት ነው።
በዚህ ሂደት ውስጥ፤
* ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸውን ምርቶች ይለያሉ፤
* ዕቃ ወይም አገልጎሎት አቅራቢዎችን ያገኛሉ፤
* በፎቶ፣ በቪዲዮና በጽሑፍ ምርቱን ያስተዋውቃሉ፤
* ደንበኞችን ስበው ትዕዛዝ ይቀበላሉ፤
* ከእያንዳንዱ ሽያጭ የትርፍ ድርሻ (Profit Margin) ወይም ኮሚሽን ያገኛሉ።
ስለሆነም የኦንላይን ሪሴሊንግ እውነተኛ ዕሴት ምርት ባለቤት መሆን ሳይሆን፤ አቅርቦትና ፍላጎትን ማገናኘት ላይ መሥራት ነው። ይህ ደግሞ ለወጣቶች፣ ለተማሪዎች፣ ሥራ ፈላጊዎችና ተጨማሪ ገቢ ለሚፈልጉ ሁሉ በዚህ ወቅት ትርፋማ የሚያደርግና ትልቅ ኢንቨስትመንት ለመጀመር ጥሩ ዕድል ነው።
በትንሽ ብር መጀመር” ማለት ምን ማለት ነው?
"በትንሽ ብር ቢዝነስ ጀምር" ሲባል በአስማት ሃብታም የሚያደርግ ምሥጢር አድርገው የሚያስቡ አሉ። እውነታው ግን 500 ብር የሚከተሉትን ነገሮች ለማድረግ የሚያገለግል የመማሪያና የመፈተሻ ካፒታል ነው፦
* የትራንስፖርትና የኮሙኒኬሽን ወጪዎችን ለመሸፈን፤
* የመጀመሪያ ማስታወቂያ (Ads) ለመሞከር፤
* አነስተኛ ምርት ገዝቶ ጥራቱን ለመፈተሽ፤
* አዳዲስ የቢዝነስ ሀሳቦችን ለመሞከር።
በዚህ አነስተኛ ገንዘብ ምርት መምረጥን፣ የደንበኛ ፍላጎት መለየትን፣ ከደንበኞችና አቅራቢዎች ጋር መነጋገርን፣ ማኅበራዊ ሚዲያዎችን (Telegram, Facebook, TikTok, WhatsApp) ለቢዝነስ መጠቀምን፣ ወጪና ትርፍ ማሰላሰልን፣ እና ከስህተት መማርን ይለማመዱበታል። ስለዚህ ትንሹን ብር እንደ የመጨረሻ ካፒታል ሳይሆን እንደ መማሪያና መፈተሻ ካፒታልማየት ያስፈልጋል።
ስለዚህ በኦንላይን ሪሴሊንግ ትልቁ ካፒታል ገንዘብ አይደለም። በብዙ ቢዝነሶች ውስጥ ዋናው ሃብት ገንዘብ ሳይሆን መረጃ ነው። ጥራት ያለው ምርት በምርጥ ዋጋ የት እንደሚገኝ ካወቁ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ያንን ምርት የሚፈልጉ ነገር ግን የት እንደሚገኝ ያላወቁ ብዙ ሰዎች ካሉ፤ ይህ መረጃ ብቻውን ትልቅ የቢዝነስ ዕድል ይፈጥራል። በአንድ በኩል ምርት አለ፣ በሌላ በኩል ፍላጎት አለ፤ የእርስዎ ቢዝነስ ሁለቱን የሚያገናኝ ድልድይ ይሆናል።
የቢዝነስ ዕድል የሚጀምረው ሌሎች ያላዩትን የገበያ ክፍተት (Market Gap) ሲያዩ ነው። ስለዚህ "ምን ቢዝነስ ልጀምር?" ብለን ከመጠየቅ ይልቅ "ሰዎች በተደጋጋሚ የሚያጋጥማቸው ችግር ምንድን ነው?" ብለን መጠየቅ አለብን። ከብዙ ችግሮች ጀርባ የቢዝነስ ዕድል አለ።
ምርት ከመምረጥዎ በፊት እነዚህን ጥያቄዎች ይመልሱ፦
1. ሰዎች በእርግጥ ይህን ምርት ይፈልጉታል?
2. ምን ዓይነት ችግር ይፈታል?
3. ደንበኞች ለምን ከእኔ ይገዛሉ?
4. ምርቱን በማይቋረጥ መልኩ ማግኘት እችላለሁ?
5. ከሁሉም ወጪዎች በኋላ በቂ ትርፍ ያስገኛል?
6. አቅራቢው ታማኝ ነው?
7. የውድድር ሁኔታው እንዴት ነው?
8. ደንበኞች ደግመው ሊገዙት ይችላሉ?
9. ለማድረስና ለማስተዳደር ቀላል ነው?
10. የእውነት ፍላጎት እንዳለ ማረጋገጫ አለኝ?
ጥሩ ምርት ማለት ውድ ወይም ዘመናዊ የሆነው ሳይሆን ገበያው ሊከፍልበት ፈቃደኛ የሆነው ምርት ነው።
ይህንን ካደረጉ በኋላ የመጀመሪያ ሱቅዎን ስልክዎን ማድረግ!
ድሮ ቢዝነስ ለመጀመር ሱቅ መከራየት፣ ዕቃ ማሟላትና ትልቅ ገንዘብ ማውጣት ግድ ነበር። ዛሬ ግን ማህበራዊ ሚዲያዎች (Facebook, Telegram, TikTok, WhatsApp Business) የመጀመሪያ ሱቅዎ ናቸው።
ነገር ግን ሶሻል ሚዲያ አካውንት መክፈት ብቻውን ቢዝነስ አይሆንም። ሰዎች ምርት ብቻ ሳይሆን እምነትንም ይገዛሉ። ስለዚህ፦
* ግልጽና እውነተኛ የሆኑ የምርት ፎቶዎችን ይጠቀሙ፤
* ትክክለኛ መግለጫና የዋጋ ግልጽነት ይኑርዎት፤
* የማድረሻ (Delivery) ሁኔታዎችን ግልጽ ያድርጉ፤
* ለጥያቄዎች በፍጥነት ምላሽ ይስጡ፤
* ሐሰተኛ ቃል አትግቡ፣ ጥራቱንም አታጋንኑ።
በኦንላይን ቢዝነስ ስምዎና ሥምግባርዎ ትልቁ ሃብትዎ ነው። ብዙ ተከታይ አግኝቶ እምነት ከማጣት፣ ጥቂት ነገር ግን ታማኝ ደንበኞችን ማፍራት ለረጅም ጊዜ ዕድገት ይረዳል።
ማርኬቲንግ ማለት ሰዎችን "ግዙኝ" ብሎ መለመን አይደለም። ብዙ ሰዎች ማርኬቲንግ ላይ ይሳሳታሉ። ማርኬቲንግ "ይህን ዕቃ ግዙ፣ በጣም አሪፍ ነው!" ብሎ መለፈፍ አይደለም። ጥሩ ማርኬቲንግ የሚጀምረው የደንበኛውን ችግር በመረዳት ነው፦
❌ ትክክል ያልሆነ፦ "ይህን ምርት ግዙ፣ ጥራቱ ከፍተኛ ነው!"
✅ ትክክለኛ አቀራረብ፦ "ይህ ችግር አጋጥሞዎታል? እነሆ ይህን ችግር ሊቀርፍልዎ የሚችል መፍትሔ!"
ሰዎች ምርቱን ብቻ ሳይሆን መፍትሔውን፣ ምቾቱን፣ ጥቅሙንና ውጤቱን ነው የሚገዙት። ስለዚህ ከማስተዋወቅዎ በፊት ደንበኛዎ ማን እንደሆነ፣ ምን ችግር እንዳለበትና የእርስዎ ምርት እንዴት ያንን ችግር እንደሚፈታው በደንብ ይረዱ።
ሌላው መታሰብ ያለበት ሽያጭና ትርፍ አንድ አለመሆናቸውን ነው። በገቢ (Revenue) እና በትክክለኛ ትርፍ (Profit) መካከል ያለውን ልዩነት መረዳት ያስፈልጋል። ብዙ መሸጥ ማለት የግድ ብዙ ማተርፍ ማለት አይደለም።
ለአብነት፦
* የምርት ግዢ ዋጋ = 800 ብር
* ትራንስፖርት = 50 ብር
* ማስታወቂያ = 50 ብር
* ሌሎች ወጪዎች = 30 ብር
* ጠቅላላ ወጪ = 930 ብር
ምርቱን በ 1,100 ብር ቢሸጡት፦
ትክክለኛ ትርፍ = 1,100 – 930 = 170 ብር ነው።
ስለሆነም፦ ትርፍ = የሽያጭ ዋጋ – ጠቅላላ ወጪ ነው።
በትናንሽ ወጪዎች (ማደርሻ፣ ማሸጊያ፣ ስልክ፣ የታላላቅ ፕላትፎርሞች ክፍያ፣ የጉዳት ወጪዎች) ምክንያት ብዙ ቢዝነሶች ትክክለኛ ትርፋቸውን ሳይረዱ ይከስራሉ።
የኦንላይን ሪሴሊንግ ስጋቶችና ተደራሽ አደጋዎች
ኦንላይን ሪሴሊንግ ዕድል እንዳለው ሁሉ ስጋቶችም አሉት፦
1. አስተማማኝ ያልሆኑ አቅራቢዎች፦ በፎቶና በአካል የሚመጣው ዕቃ ሊለያይና ስምዎን ሊያጠፋ ይችላል።
2. የዋጋ መዋዠቅ፦ የአቅራቢዎች ዋጋ ድንገት ሲጨምር ትርፍዎን ይቀንሰዋል።
3. የደንበኛ እምነት ማጣት፦ ያልተጠበቀ ጥራት ሙሉ ስምዎን ያበላሻል።
4. የውድድር መብዛት፦ አንድ ምርት ሲያድግ ሲታይ ሌሎችም ገብተው የዋጋ ጦርነት ሊፈጥሩ ይችላሉ።
5. የካሽ ፍሎ (Cash Flow) ችግር፦ በወረቀት ላይ ያተረፉ ቢመስልም ገንዘብዎ በዕቃ ወይም ባልተሰበሰበ ዕዳ ውስጥ ሊታሰር ይችላል። | 68 |
| 6 | No text... | 56 |
| 7 | የፋይናንስ ነፃነትን ለማረጋገጥና ሕይወትን ለመቀየር የሚያስፈልጉ 3 የሕይወት ወርቃማ መርሆች!
ብዙዎቻችን በየቀኑ እንደክማለን፣ እንለፋለን፤ ነገር ግን አሁንም ከገንዘብ ጨዋታው በስተጀርባ ሆነን እንቀራለን። ችግሩ ግን የሥራችን ብዛት ሳይሆን የሚመራን አስተሳሰብ ነው።
የፋይናንስ ነፃነትን ለማግኘትና ስኬታማ ለመሆን እያንዳንዳችን ልንተገብራቸው የሚገቡ 3 ዋና ዋና የፋይናንስና የአስተሳሰብ መርሆች እነዚህ ናቸው፦
📌 1. ለውጥን በጸጋ መቀበልና በፍጥነት መላመድ
ዓለም በየቀኑ እየተቀየረች ነው። ትላንትና ያሠራን የሥራ ወይም የንግድ መንገድ ዛሬ ላይሠራ ይችላል። መርሁ በለመድነው ምቹ ሁኔታ (Comfort Zone) ውስጥ ብቻ ተሸጉጠን መኖር ውድቀትን ይጋብዛል የሚል ነው። የኢኮኖሚ ወይም የሥራ ሁኔታዎች ሲቀየሩ ከማጉረምረም ይልቅ በፍጥነት ከአዲሱ ሁኔታ ጋር መላመድ፣ አዳዲስ ክህሎቶችን ማዳበርና አዳዲስ ዕድሎችን መፈለግ ያስፈልጋል። ለውጥን ቀድሞ መገመትና አብሮ መንቀሳቀስ የስኬት የመጀመሪያው መሠረት ነው።
📌 2. መሠረታዊ የገንዘብ አያያዝ ሕጎችን ማክበር
ብዙ ገንዘብ ማግኘት ብቻውን ሃብታም አያደርግም፤ ዋናው ቁልፍ አያያዙ ላይ ነው። መጀመሪያ ለራስህ መክፈል ወይም ቁጠባን መልመድ ነው። ከምናገኘው ማንኛውም ገቢ ላይ ቢያንስ 10 በመቶውን አስቀድመን ለወደፊት ህልማችን ማስቀመጥ አለብን። ሁለተኛው ወጪን መግታት ነው። ፍላጎትና አስፈላጊ ነገሮችን መለየትና ወጪያችን ከገቢያችን እንዲያንስ ማድረግ። ሦስተኛው መርህ ገንዘብህ እንዲሠራ ማድረግ ነው። የተቀመጠ ገንዘብ ዋጋው እየወረደ ይሄዳል። ስለዚህ ቁጠባችንን በጥበብና ጥናት በተደረገበት መንገድ ኢንቨስት በማድረግ ተጨማሪ ገቢ እንዲያስገኝልን ማድረግ ይኖርብናል።
📌 3. የንግድ ሥርዓቶችን (Systems) መገንባትና ማፋጠን
ጊዜያችንን ብቻ በገንዘብ በመለወጥ (በሰዓት በመከፈል) የሚመጣ ሃብት ወሰን አለው። እውነተኛ የፋይናንስ ነፃነት የሚመጣው እኛ ባለንበትም በሌለንበትም ቦታ ገቢ የሚያስገኙ የንግድ ሥርዓቶችን፣ ምርቶችን ወይም አገልግሎቶችን መፍጠር ስንችል ነው። ብዙ ሰዎችን ሊጠቅም የሚችል መፍትሔ በመፍጠርና አውቶሜትድ የሆነ አሠራር በመዘርጋት የፋይናንስ ጉዟችንን ማፋጠን እንችላለን።
ከእነዚህ 3 መርሆች ውስጥ በአሁኑ ወቅት የትኛውን እየተገበራችሁት ትገኛላችሁ? የትኛውስ ላይ ክፍተት አለባችሁ? ሐሳባችሁን በኮሜንት ጻፍልኝ!
#ፋይናንስ #የፋይናንስ_ነፃነት #ቢዝነስ #የግል_እድገት #እውቀት #ስኬት #BusinessMindset | 64 |
| 8 | No text... | 80 |
| 9 | “አሳዳጅ በደጅ “
(በዕውቀቱ ስዩም)
የጎጃሙ ገዢ ደጃዝማች ብሩ ደፋርና ኃይለኛ ተዋጊ ነበሩ፤ ተድላ ጉዋሉ የተባለ የሥልጣን ተፎካካሪ ነበራቸው ፤ ከዕለታት አንድ ቀን፤ ተድላ ለደኅንነቱ ስለ ሰጋ ዓባይን ተሻግሮ በሌሎች ገዥዎች ክንድ ስር ለመጠለል አሰበ፤ ጥቂት ቦታዎች ያልተሳካ ጥረት ካደረገ በኋላ መጨረሻ ላይ ነገዎ ገመዳ የተባለ የጃርሶ (ሰላሌ) ጌታ ጥገኝነት ሊሰጠው ተስማማ፤
ደጃች ብሩ ይህንን እንደ ሰማ በንዴት ጤሰ! “ ጠላቴን ሸሽገህ ይዘሀልና መጣሁልህ “ ብሎ ለነገዎ ማስጠንቀቂያ ላከበት!
ነገዎ ገመዳ ማስፈራርያው እንደደረሰው፥ ሠራዊቱን ከየቦታው በአዋጅ ጠርቶ ሰላሌ ሜዳ ላይ ጉግስ ጨዋታ አካሄደ፤ ዓላማው የፈረሰኞቹን ብዛት እና ንቃት ለጠላቶቹ ለማሳየት ነበር፤ በዛሬው አነጋገር ወታደራዊ ሰልፍ ማካሄዱ ነው፤ ይህንን የተመለከቱ የብሩ ሰላዮች ጉዳዩን ለጌታቸው አመለከቱ፤
ብሩ ግን ከውሳኔው ንቅንቅ አላለም፤ ወደ ሰላሌ ሄዶ የነገዎ ገመዳን ፈረሶች “ ቂጥለቂጥ እንደሚያማታ” ዛተ፤
መካሪ መኮንንኖች ግን እንዲህ አሉት’
“ ግዴለም ይቅርብን! አሳዳጅ በደጅ አንሁን! “
ዋናዋ ነጥብ “ አሳዳጅ በደጅ አንሁን “ የምትለው ምክር ናት! በሰፈራቸው፥ በሜዳቸው ብንገጥማቸው ያሸንፉናል ማለት ነው፤ (ናፖሊዮን ቦናፖርት እንዲህ የተባ መካሪ ቢኖረው ሩስያ ገብቶ አይዋረድም ነበር)። ደጃች ብሩ የመኳንንቱን ምክር ተቀብሎ ዘመቻውን አጠፈው።
ፍቅር እስከመቃብር “ በተባለው የሀዲስ አለማየሁ ዝነኛ ልቦለድ ውስጥ ካሉት ዋና ታሪኮች አንዱ የባላገሮች አድማ ነው፤ ፊታውራሪ መሸሻ የተባሉት ጌታ የዓመት በዓል መዋያ የሚል አዲስ ግብር በባላገሮች ላይ ጣሉባቸው፤ ባላገሮች እምቢ አንከፍልም አሉ፤ ፊታውራሪ ጉልበታቸውን ተማምነው የሚንቁትን ያመጸ ባላገር በዘመቻ ለመቅጣት ቆረጡ፤
መካሮች ተሰበሰቡ፤ የድሮ መካር እንደ ዛሬ“ በለው ! በለው !“ አይልም፤ ጌታው ፈረስ ከሆነ መካሩ ልጉዋም ይሆናል፤ መካሮች ተናገሩ፤ “ባላገር ሕይወቱንም ጥይቱንም ቆጥቦ ነው እሚዋጋ ፥ ጠላቱ እሱን በመፈለግና በራብና በጥም እስኪደክም ፊትለፊት ተሰልፎ አይገጥምም! ባገሩ እኅል ውኃው የሱ ስለሆነ ዱር ገደሉ ተራራው ሸንተረሩ፥ ሁሉም የሱ ስለሆነ ፥ እኅል ውኃውን ሸሽጎ፥ እሱ በዱር ገደሉ ተሸሽጎ ብዙ ሰው ሳይሞትበት ፥ ብዙ ጥይት እንኩዋ ሳይጠፋበት፥ ድል ያደርጋል! ያደመ ባላገርን አሸንፋለሁ ብሎ ማሰብ ውቅያኖስን ጠልቄ እጨርሳለሁ እንደማለት ነው “
ፊታውራሪ መሸሻ እንደ ደጃች ብሩ ምክር የሚሰሙ አልነበሩም፤ አሻፈረኝ ብለው ጦራቸውን አስከትለው ወደ አደሙት ባላገሮች ዘመቱ! ባላገሮች አበጀ በለው በተባለ ሽፍታ መሪነት የሚደንቅ ነገር አደረጉ፤ ፊታውራሪ መሸሻ ወደ ሰፈራቸው ዘው ብለው እንዲገቡ በሩን ከከፈቱላቸው በኋላ አዘናግተው ፥ ከብበው ፥ ከምክትል ሚስታቸው ጋር በተኙበት ማረኳቸው፤
የምንኖረው በቅራኔዎች በተሞላ ዓለም ውስጥ ነው፤ ከቅራኔዎች እሚገላግለን ምናልባት ሞት ሳይሆን አይቀርም፤ ፖለቲካ ማለት ቅራኔዎችን ከናካቴው ማስቀረት ሳይሆን ቅራኔዎችን ለከፋ ጉዳት እንዳይዳርጉ አድርጎ ማርገብ ነው፤
የሆነ አካባቢ ማኅበረስብ ሲያምጽ የአመጽ ምንጭ የሆኑትን ሮሮዎች እህ ብሎ መስማት፤ ችግሮችን ማዳመጥ እና ለመፍታት መፍቀድ የመንግሥት ዋና ሥራ መሆን አለበት።
ለገበሬ ማዳበርያ በጊዜው ማቅረብ፤ ሕዝቡ አስተዳዳሪዎቹን ራሱ እንዲመርጥና እንዲሽር መፍቀድ፥ በሰላም ተዘዋውሮ እንዲኖር ፥ እንዲሠራና የቤት ንብረቱ ባለቤት እንዲሆን ማገዝ፤ ወዘተረፈ...
በተረፈ በገዛ መንደሩ ላይ ወታደር አሰማርቶ ብሶቱን ለማፈን መሞከር ከታሪክም ከስነጽሑም አለመማር ነው፤ ቅራኔዎችን ማራገብ ትተን ቅራኔዎችን ማርገብ ይልመድብን! | 123 |
| 10 | No text... | 96 |
| 11 | ከሆነ እነሱም ያንኑ ይቀጥላሉ፤ ታማኝነትን፣ ፍትሕንና ተጠያቂነትን ካስተማርናቸው ግን የተሻለች ሀገር ይገነባሉ።
ሙስናን መቃወም ሀገርን መውደድ ነው።
ጉቦን አለመቀበል የራስን ክብር መጠበቅ ነው።
የሕዝብን ሃብት አለመዝረፍ ለሚመጣው ትውልድ መኖር ነው።
ዛሬ ሙስናን ካልቆምነው፣ ነገ የሚከፍለው ዋጋ የእኛ ብቻ ሳይሆን የልጆቻችንም ይሆናል። ስለዚህ የትውልድ ገዳይ የሆነውን ይህን ክፉ በሽታ ለመዋጋት ከሌላው ሳንጠብቅ ከራሳችን መጀመር አለብን።
ደምሴ ገረመው
🌐 🌐 ተከተሉን፦
🔴 YouTube -
-https://lnkd.in/ev5z22Hz
🔵 Facebook -
- https://lnkd.in/e9FF6J-3
🟦 LinkedIn
https://lnkd.in/ejVyVbc2
✈️ Telegram
- https://lnkd.in/epKeuarQ
🎵Tiktalk
- https://lnkd.in/eQ8EsfYf | 113 |
| 12 | ሙስና — ትውልድ ገዳይ በሽታ
ሙስና የአንድ ሰው የግል ጥፋት ብቻ አይደለም፤ የሕዝብን እምነት፣ የሀገርን ሃብት፣ የተቋማትን ጥንካሬና የትውልድን ተስፋ የሚያጠፋ አደገኛ በሽታ ነው። ሙስና በሚስፋፋበት ሀገር ውስጥ ትክክለኛው ሰው ከሥራው ይልቅ በመስረቅ ስልቱ ይመዘናል፤ ታማኝነት በጥቅም ይሸነፋል፤ ሕግ ከገንዘብ ይሸነፋል።
በሙስና የተገኘ ጥቅም ለጥቂት ሰዎች የአጭር ጊዜ ምቾት ሊሰጥ ይችላል፤ ዋጋውን ግን ሙሉ ሕዝብ ይከፍላል። የተሰረቀ የሕዝብ ገንዘብ ማለት ያልተገነባ መንገድ፣ ያልተሠራ ሆስፒታል፣ ያልተገነባ ትምህርት ቤት፣ ያልተፈጠረ የሥራ ዕድል እና የተሰረቀ የወጣቶች ተስፋ ማለት ነው። ስለዚህ ሙስና ገንዘብ ብቻ አይሰርቅም፤ የሰው ልጅ ዕድልን ይሰርቃል።
የበለጠ አሳዛኙ ጉዳይ ደግሞ ሙስና ወደ ባሕልነትና ልምድነት ሲቀየር ነው። “ሁሉም ያደርገዋል”፣ “ካልተቀበልክ ሥራህ አይሄድም”፣ “ያለ ጉቦ ምንም አይሆንም” የሚሉ አመለካከቶች ሲያድጉ ሕገወጥነት እንደ መደበኛ ነገር ይቆጠራል። በዚህ ሁኔታ የሚያድገው ትውልድ ትጋትንና ብቃትን ሳይሆን ያልተገባ የሌብነት ግንኙነትንና ጉቦን የስኬት መንገድ እንደሆነ ይማራል።
ሙስናን መዋጋት የመንግሥት ብቻ ኃላፊነት አይደለም። ባለሥልጣኑ ሥልጣኑን ለግል ጥቅም እንዳይጠቀም፣ ነጋዴው ሕግን በገንዘብ እንዳይገዛ፣ ሠራተኛው ታማኝነቱን እንዳይሸጥ፣ ዜጋውም ጉቦን እንደ “መፍትሔ” እንዳይቀበል ሁላችንም የራሳችን ድርሻ አለን።
አንድ ሀገር ሙስናን ሲታገል በመጀመሪያ የሚገነባው ሕግን ብቻ አይደለም፤ የሰዎችን እምነት ነው። ሕግ ለሁሉም እኩል ሲሆን፣ ተጠያቂነት ሲኖር፣ የሕዝብ ሃብት በግልጽነት ሲተዳደር እና ታማኝነት ሲከበር ሙስና የሚያገኘው ቦታ ይጠብባል።
የዛሬ ምርጫችን የነገ ትውልድ ዕጣ ፈንታ ነው። ልጆቻችን ከእኛ የሚማሩት ሙስናን መቀበል | 100 |
| 13 | "ውድቀት የስኬት ተቃራኒ አይደለም። ይልቁንም ገና በሚገባ ያልተረዳነው ጠቃሚ መረጃ እና ለመነሣታችን ትልቅ ጉልበት መሆን የሚችል ምልክት ነው።"
በቅርቡ ለንባብ ከሚበቃውና እያንዳንዱ ችግር ቢዝነስ ነው ከተሰኘው መጽሐፌ ገጽ 110 የተወሰደ | 158 |
| 14 | ይህ ምስል የሰውን ልጅ አላስፈላጊ ሸክም፣ የተሳሳተ መንገድና ዕጣ ፈንታን ያሳያል። በመጀመሪያ ደረጃ በሕይወታችን የተሳሳተ ሸክም ተሸክመን እየኖርን መሆኑን ይነግረናል። በሕይወት ውስጥ አብዛኛው ድካማችንና ሕመማችን የሚመጣው ከራሳችን ሸክም ሳይሆን ያልተገባና የእኛ ያልሆነን ሸክም በባዶ ተሸክመን ስንዞር ነው። ቀንበሩ አንገት ላይ ተጭኖ ትክሻን እንደሚያጥፍ ሁሉ በሰው ልጅ ሕይወት ውስጥም የሰዎች ፍላጎትና ጫና ወይም የተሳሳተ ሥርዓታዊ አሠራር በላያችን ላይ ሲጫን ሕይወታችንን ሙሉ በሙሉ ትርጉም አልባ በሆነ ድካም እናሳልፋለን።
ሌላኛው ከምስሉ የምንረዳው ጉዳይ ደግሞ የተሳሳተ ጥምረት እንዴት አንደሚጎዳን ይነግረናል። በሕይወት ጉዞ ውስጥ ከአንድ አካል ጋር ስንጣመር (በጋብቻ፣ በጓደኝነት ወይም በንግድ) አቅጣጫችንና ራዕያችን ካልተጣጣመ አንደኛው የሌላኛውን ጉዞ ያደናቅፋል። ምስሉ ላይ አንደኛው አካል ወደ ፊት ሲሄድ ሌላኛው ወደ ኋላ እየጎተተ የሌላኛውን እንቅስቃሴ እንደሚገድበው ሁሉ፣ የተሳሳተ ስብስብና ጥምረት አብሮ ወደ ፊት ከመሄድ ይልቅ ቁልቁል ይዞ ይወርዳል።
ሰው የራሱን ነፃነትና እውነተኛ ዐቅም ለማግኘት መጀመሪያ አላስፈላጊ የሆኑ የሌሎች ሰዎችን ሸክም ከጀርባው ማውረድ አለበት። ተፈጥሮና እንስሳት ሳይቀሩ ባልተስተካከለ አሠራር ሲሰቃዩ ማየት፤ የሰው ልጅ የሥርዓት አልበኝነትና የደመነፍስ ጉዞ ውጤት ነው። ቀንበሩን አስተካክሎ የበሬዎቹ ጫንቃ ላይ ያልጫነው አካል ስቃዩን አያይም፤ ወዴት ሊነዳቸውና እንዴት አርሶና አምርቶ ቤተሰቡን ሊያስተዳድር እንደሚችል በፍጹም አያውቅም። ሕይወትም እንዲሁ ናት፤ መዋቅሯና መንገዷ ካልተስተካከለ ድካሙ እንጂ ፍሬው አይገኝም።
የእኛ ያልሆነን ቀንበር ማነጠቢያውን በጥሰንም ቢሆን ከአንገታችን አሽቀንጥረን እንጣለው። አቅጣጫችንን ከማያስተካክሉ አካላት ጋር አንጠመድ። | 203 |
| 15 | ሰላም ቤተሰቦች! ዛሬ ኪሳችን ባዶ ቢሆንም እንኳን፤ በ10 ዓመታት ውስጥ ትልቅ ደረጃ ላይ እንደምንደርስ የሚያሳዩ 7 ምልክቶችን እንይ። እስኪ ከእነዚህ ውስጥ ስንቱን እንደጀመራችሁ እራሳችሁን ፈትሹ! 👇
1️⃣ በዓመታት ያስባሉ — በወራት አይደለም
(የዛሬዋን ጥቅምና ደስታ ብቻ ሳይሆን፣ የረጅም ጊዜ ጉዞዎን ያያሉ)
2️⃣ ስለ ገንዘብ መማርን መቼም አያቆሙም
(የፋይናንስ መጽሐፍትን ማንበብ፣ ጠቃሚ ቪዲዮዎችን ማየት ደስ ይሎታል)
3️⃣ ከማውጣት በፊት ኢንቨስት ያደርጋሉ
(ገንዘብ ሲያገኙ መጀመሪያ ወጪ ከማሰብ ይልቅ፣ ለወደፊትዎ ማስቀመጥ ይጀምራሉ)
4️⃣ ከሚያገኙት ገቢ በታች ይኖራሉ
(ለሰው ለማሳየት ብለው አላስፈላጊ ወጪ ውስጥ አይገቡም)
5️⃣ ተጨማሪ የገቢ ምንጮችን እየፈለጉ ነው
(በአንድ ደመወዝ ወይም በአንድ ገቢ ብቻ አይወሰኑም)
6️⃣ ለኪሳቸው ሙሉ ኃላፊነት ይወስዳሉ
(ለገንዘብ እጥረት ሌላ ሰውን ወይም ሁኔታዎችን ብቻ አያማርሩም)
7️⃣ በግልጽ የተጻፈ የፋይናንስ ግብ አላቸው
(የት መድረስ እንደሚፈልጉ እና ምን ያህል እንደሚያስፈልጋቸው በትክክል ያውቃሉ)
💡ምክር
ትልቁ ምሥጢር ምን መሰላችሁ? ሃብታም መሆን ዛሬ ከምናገኘው የገንዘብ መጠን ጋር በፍጹም አይገናኝም። ሁልጊዜም ዛሬ ከምናሳየው መልካም የገንዘብ አያያዝ ባሕርይና ጥረት ጋር ነው የሚያያዘው!
💬 እስቲ እንወያይ
ከእነዚህ 7 ምልክቶች ውስጥ የእናንተ የሆኑት ስንቶቹ ናቸው? ምንም ባይኖራችሁ እንኳን ምንም ችግር የለውም፤ ዛሬ መጀመር ይቻላል! ቁጥሩን ኮሜንት ላይ አጋሩኝ 👇
#FinancialFreedom #TensiuPsychoBusiness #ተንሥኡሳይኮቢዝነስ #viral #due | 173 |
| 16 | No text... | 191 |
| 17 | No text... | 234 |
| 18 | "በሚሊዮን አንድ ጊዜ የሚከሰት ታሪክ!"
ሊዮኔል ሜሲ እና ላሚን ያማል በ2026ቱ የፊፋ ዓለም ዋንጫ ፍጻሜ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድ ሜዳ ላይ ለመገናኘት ተዘጋጅተዋል።
ነገር ግን በመካከላቸው ያለው አስገራሚ ግንኙነት የተጀመረው ከሁለት አስርት ዓመታት ገደማ በፊት ነበር።
እ.አ.አ. በታኅሣሥ 2007 የ20 ዓመቱ ወጣት ሊዮኔል ሜሲ ለባርሴሎና ፋውንዴሽን የበጎ አድራጎት ቀን በሚዘጋጅ የፎቶ ግራፍ መርኃ ግብር ላይ ተሳትፎ ነበር።
በወቅቱ ሜሲ አምስት ወር ከሆነው ሕፃን ላሚን ያማል ጋር አብሮ ፎቶ የተነሳ ሲሆን፣ ሕፃኑን በገንዳ ውስጥ ሲያጥበውና ሲንከባከበው የሚያሳዩት እነዚህ ምስሎች ለዩኒሴፍ እና ለሌሎች በጎ አድራጎት ድርጅቶች ገቢ ማሰባሰቢያነት ታትመው ወጥተዋል።
ይህን ታሪካዊ ምስል የቀረጸው ፎቶ ግራፍ አንሺ ጆአን ሞንፎርት በሰጠው አስተያየት፤ በወቅቱ የወደፊቱን ማንም እንዳልገመተው ተናግሯል።
በዚያን ጊዜ ሜሲ የምንግዜም ታላቁ እግር ኳስ ተጫዋች ለመሆን ገና ጉዞውን የጀመረበት ወቅት የነበረ ሲሆን፣ ያማል ደግሞ በፕሮጀክቱ ላይ ከተሳተፉት በርካታ ሕፃናት መካከል አንዱ ነበር።
ይህ ታሪካዊ ፎቶ ግራፍ የመገናኛ ብዙኃንን ትኩረት የሳበው በ2024ቱ የአውሮፓ ዋንጫ ወቅት የያማል አባት በማኅበራዊ ሚዲያ ካጋሩት በኋላ ነበር።
ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ምስሉ የሁለቱን የባርሴሎና ትውልድ ኮከቦች የሚወክል የእግር ኳስ ታሪክ ተምሳሌት ሆኗል።
ያማል በ2014 የባርሴሎናውን ላማሲያ አካዳሚን የተቀላቀለ ሲሆን፣ ፈጣን ዕድገት በማሳየት ገና በ15 ዓመቱ ለዋናው ቡድን መጫወት ችሏል።
አሁን ላይ የስፔን እግር ኳስ ትልቁ ተስፋ የሆነው ያማል፣ በባርሴሎና ቤት የሜሲን ታሪካዊ የ10 ቁጥር መለያ የሚለብስ ሲሆን በብዙዎች ዘንድም የሜሲ ተተኪ ተደርጎም ይወሰዳል።
አሁን ግን የእግር ኳስ ታሪክ አስደናቂውን ምዕራፍ ሊያሳየን ተቃርቧል።
በአንድ ወቅት በሜሲ እቅፍ ውስጥ የነበረው ያ ሕፃን፣ አሁን በትልቁ መድረክ ማለትም በዓለም ዋንጫ ፍጻሜ ላይ የልጅነት አርአያውን ፊት ለፊት ለመጋፈጥ እየተዘጋጀ ይገኛል።
ፎቶግራፍ አንሺው ጆአን ሞንፎርት ይህንን ታሪክ "በሚሊዮን አንድ ጊዜ ብቻ የሚከሰት" ሲል ገልጾታል።
በእሱባለው ተሾመ
🌐 🌐 ተከተሉን፦
📞 ስልክ፦ +251 91 269 1049
🔴 YouTube -
-https://tensiu.openinapp.co/psychobusiness
🔵 Facebook -
- https://www.facebook.com/share/1Dd7eJrkgj/
✈️ Telegram
- https://t.me/tensiupsychobusiness
🎵Tiktalk
- tiktok.com/@tensiupsychobusiness
#worldcup #sports #messi #lamineyamal | 184 |
| 19 | ተንሥኡ ሳይኮ ቢዝነስ
ያግኙን
📞 ስልክ፦ +251 91 269 1049
🌐 ተከተሉን፦
🔵 Facebook -
- https://www.facebook.com/share/1Dd7eJrkgj/
🔴 YouTube -
-https://tensiu.openinapp.co/psychobusiness
✈️ Telegram
- https://t.me/tensiupsychobusiness
🎵Tiktalk
- tiktok.com/@tensiupsychobusiness
---
#ተንሥኡ #ተንሥኡሳይኮቢዝነስ #ቢዝነስ #ሥነልቦና #ሥራፈጠራ #የንግድምክር #አነቃቂምክሮች #Tensiu #TensiuPsychoBusiness #PsychoBusiness #EthiopianBusiness #BusinessMindset #MotivationEthiopia #PersonalGrowth | 115 |
| 20 | 📚 ታላቅ የምሥራች ለሥራ ፈጣሪዎችና ለውጥ ለሚፈልጉ በሙሉ!
አዲስ መጽሐፍ በቅርቡ ለንባብ ይበቃል! በቢዝነስ እና በሥነ-ልቦና ዕውቀት ላይ የተመሠረተው አዲሱ መጽሐፍ በቅርቡ እናንተ እጅ ይገባል።
የመጽሐፉ ርዕስ፦ እያንዳንዱ ችግር ቢዝነስ ነው። Every Problem is a Business"
ደራሲ፦ ደምሴ ገረመው (MBA & BEd in Psychology)
💡 ይህ መጽሐፍ ምን ይዞላችሁ ይመጣል?
ይህ መጽሐፍ በሕይወትዎም ሆነ በሥራ መስክዎ ውስጥ የሚያጋጥሙዎትን ፈተናዎችና ዕለታዊ ችግሮች ወደ ታላቅ የንግድ ዕድል፣ የሥራ ፈጠራ እና የስኬት ስልት እንዴት መለወጥ እንደሚችሉ በሥነ-ልቦናዊ ዝግጁነት እና በቢዝነስ ስልቶች አስደግፎ በምሳሌዎች ያሳየዎታል።
🌟 ከመጽሐፉ ምን ይማራሉ?
• ችግሮችን በአዲስ መነጽር ማየት፦በዙሪያችን ያሉ ተግዳሮቶችን እንደ እንቅፋት ሳይሆን እንደ መሸጋገሪያ ድልድይ መቁጠር።
• ዕድሎችን መለየትና መፍጠር፦ ሌሎች ችግር ብቻ በሚያዩበት ቦታ ላይ እርስዎ አዋጭ የቢዝነስ ዕድል ማውጣትን ይለማመዳሉ።
•
ዘላቂ መፍትሔዎችን ማመንጨት፦ ለሰዎችና ለማኅበረሰቡ ጠቃሚ ዕሴት በመፍጠር ረገድ ስኬታማ መሆን።
ችግሮችን ወደ ስኬት መቀየር እንልመድ።
ይህንን ድንቅ መጽሐፍ ለማግኘትና የአስተሳሰብ አድማስዎን ለማስፋት ዝግጁ ይሁኑ። በቅርቡ በሁሉም መጻሕፍት መደብሮችና በአከፋፋዮች እጅ ይደርሳል!
ይጠብቁን! Coming Soon!
ያግኙን
📞 ስልክ፦ +251 91 269 1049
🌐 ተከተሉን፦
🔵 Facebook -
- https://www.facebook.com/share/1Dd7eJrkgj/
🔴 YouTube -
-https://tensiu.openinapp.co/psychobusiness
🎵Tiktalk
- tiktok.com/@tensiupsychobusiness | 93 |
