cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

አዲስ ነገር መረጃ

አዲስ ነገር መረጃዎች መረጃዎች በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇 @Addisnegermereja_bot

Show more
Advertising posts
76 232Subscribers
-2024 hours
-1597 days
-68530 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

አንጋፋዋ ድምፃዊት ቻቺ ታደሰ "ደርሷል ሰዓቱ" የተሰኘ ነጠላ ዜማ መልቀቋን ገለፀች አንጋፋዋ የበጎ ፈቃድና የሰላም አምባሳደር አርቲስት ቻቺ ታደሰ "ደርሷል ሰዓቱ!" የተሰኘ ከረጅም አመት በኋላ አዲስ ነጠላ ዜማ ዛሬ ሚያዝያ 18/2016 ዓ.ም በአርቲስቷ ዩቲዩብ ቻናል እንደተለቀቀ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጿል። አርቲስት ቻቺ በጋዜጣዊ መግለጫ እንደተናገረችው «እኛ ውድ ኢትዮጵያዊያን ፤ ስለፍቅር የኖረ አባት ልጆች የሆን እኛ የምንወደው አምላክ ያለን ጥንተ አማኝ ህዝቦች በባህሉ በእምነቱ የኮራ፣ የሚዋደድ እንጅ የማይጠላላ እንዲሆን፣ የሚተቃቀፍ እንጅ የሚገፋፋ እንዳይሆን፣ በየእምነቱ ጎራ ለይቶ የሚናቆር ሳይሆን ተከባብሮ አንተ ትብስ አንች ትብስ ተባብሎ ተሳስቦ የሚኖርበት አዲስ ደስታ፣ አዲስ ተስፋ፣ አዲስ ውበት፣ አዲስ ግርማ ሊመጣ ይሄው ቀኑ ደረሰ» ብላለች። «ሰማያችን ሊጠራ ጉም ተኖ ከአድማስ ማዶ እየተፍለቀለቀች እንደምትወጣ የፈካች ውብ ጸሀይ ልትወጣ ይሄው "ደርሷል ሰዓቱ !" ምርታችን ሊያብብ አዝመራችን ሊያጠግበን ሰላማችን ሊበዛ ይሄው "ደርሷል ሰዓቱ" እንድንል የሚያስችለን ብሩህ ዘመን ለሁላችንም እንዲመጣልን ሁላችንም ለሰላምና ለፍቅር እጅለእጅ መያያዝ አለብን» ስትል አክላለች። "ደርሷል ሰዓቱ" ነጠላ ዜማን ግጥምና ዜማ ቻቺ ታደሰ እና ወንድሟ ጳውሎስ ታደሰ ሰርተውታል። @Addis_News
Show all...
በዓልን ምክንያት በማድረግ የእሁድ ገበያዎች ሳምንቱን ሙሉ አገልግሎት እንዲሰጡ መደረጉ ተነግሯል የትንሳዔ በዓልን አስመልክቶ 188 የእሁድ ገበያዎች ሳምንቱን ሙሉ አገልግሎት እንዲሰጡ መደረጉን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስውቋል፡፡ በዓልን አስመልክቶ የምርት እጥረት እንዳይከሰት በመዲናዋ የሚገኙ 188 የእሁድ ገበያዎች በመደበኛነት ቅዳሜ እና እሁድ የሚካሄደውን የእሁድ ገበያዎች፤ ሳምንቱን ሙሉ እንዲካሄዱ መደረጉን የቢሮ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሰውነት አየለ ተናግረዋል፡፡ ይህም በዓልን አስመልክቶ የሚፈጠር የምርት እጥረት፣ ህገ ወጥ ንግድን እና ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ እንዳይከሰት እንደሚረዳ ተነግሯል፡፡ የእሁድ ገበያዎቹ የትራስፖርት አገልግሎት ላይ መጨናነቅ የማይፈጥሩት ተለይተው መሆኑን አንስተው፤ በእነዚህ የገበያ ቦታዎች ላይ የገበያ ዋጋ ጥናት በቢሮ በየ 3 ቀኑ የሚከናወን እና የዋጋ ተመን እንደሚዘጋጅ እና የክትትል ስራ እንደሚከናወን ተጠቁሟል፡፡ @Addis_News
Show all...
👍 11😐 2
የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት የት እንዳሉ እንደማይታወቅ ተገለጸ። ከሶስት ዓመት በፊት የደብረ ብርሀን ዩንቨርስቲ ፕሬዝዳንት ሆነው የተሾሙት ንጉስ ታደሰ (ዶ/ር) በቢሯቸው ከታዩ አንድ ወር አልፏቸዋል ተብሏል። ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የዩንቨርሲቲው አስተዳድር አመራር አባል "ፕሬዝዳንቱ ከመጋቢት 17 ቀን 2016 ዓ. ም ጀምሮ በስራ ላይ አይተናቸው አናውቅም" ሲሉ ለአል ዐይን አማርኛ ዘጋቢ ነግረውታል። "ፕሬዝዳንቱ ንጉስ ታደሰ ከተጠቀሰው ቀን አንስቶ የት እንደሄዱ እና መቼ እንደሚመለሱ አናውቅም" ሲሉም እኝህ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አመራር ነግረውናል። ይሁንና ፕሬዝዳንቱ በቢሮ መታየት ካቆሙ ከተወሰኑ ቀናት በኋላ ባልታወቁ ሀይሎች መታገታቸውን ሰምተናል ሲሉም አክለዋል። የሰማን ሸዋ ዞን ፖሊስ፣ ኮማንድ ፖስት፣ ትምህርት ሚንስቴር እና የደብረብረሀን ከተማ ፖሊስ ስለ ደብረ ብርሀን ዩንቨርስቲ ፕሬዝንት ንጉስ ታደሰ (ዶ/ር) ጉዳይ ምላሽ እንዲሰጡን ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።ከቤተሰብም የተገኘ መረጃ የለም። የፌደራል መንግሥት ከአንድ ዓመት በፊት የክልል ልዩ ሀይሎችን "መልሼ አደራጃለሁ" የሚል ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ ነበር በአማራ ክልል ግጭት የተከሰተው። ግጭቱ በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች እና የፋኖ ታጣቂዎች መካከል የተካሄደ ሲሆን ግጭቱ ተባብሶ መቀጠሉን ተከትሎ በአማራ ክልል ለስድስት ወራት የሚዘልቅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጇል። ከሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የታወጀው ይህ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለተጨማሪ አራት ወራት የተራዘመ ሲሆን ይህ አዋጅ ሊጠናቀቅ ከሁለት ወራት ያነሰ ጊዜ ቀርቶታል ሲል አል ዓይን አማርኛ ዘግቧል። ፕሬዝደንቱ ከወር በፊት ከመኖሪያ ቤታቸው ታግተው እንደተወሰዱ በዚህ ቻናል ላይ መዘገቡ ይታወሳል። @Addis_News
Show all...
የከባድ ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች በፍተሻ ኬላዎች አላግባብ ከፍተኛ ገንዘብ እንዲከፍሉ እየተጠየቁ ነው ተባለ ለአገር አጠቃላይ የምጣኔ ሀብት እንቅስቃሴ ዋነኛ መሆኑ የሚነገርለት የትራንስፖርቱ ዘርፍ በርካታ ፈተናዎች እንደተጋረጡበት ያስታወቀው የከባድ ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች ማህበር ነው፡፡ የማህበሩ ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን ዘውዴ ከዚህ ቀደም የረጅም ርቀት አሽከርካሪዎች እገታ፤ ዝርፊያ፤ ግድያ እና ሌሎች ጥቃቶችም ሲደርስባቸው እንደነበር ገልጸው፤ አሁን ላይ ግን በአንጻራዊነት መሻሻሎች እንዳሉ ጠቁመዋል፡፡ ይሁን እንጂ አሁን ላይ አሽከርካሪዎች በሚያቀኑባቸው አከባቢዎች ባሉ የፍተሻ ኬላዎች አላግባብ እንዲከፍሉ የሚጠየቁት ገንዘብ ከፍተኛ መሆኑን እና ይህም በዘርፉ ላይ ችግር እየፈጠረ እንዳለ ተናግረዋል፡፡ ስራ አስኪያጁ እንደሚሉት ከሆነ ተሸከርካሪዎች በሚንቀሳቀሱባቸው ኬላዎች ከ5ሺህ እስከ 30 ሺህ የሚደርስ ገንዘብ እንዲከፍሉ እየተገደዱ ነው፡፡ ዘርፉ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የተለያዩ ፈተናዎች እንደተጋረጡበት ማህበሩ ያስታወቀ ሲሆን፤ የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር በበኩሉ በአሽከርካሪ እና ተሽከርካሪዎች ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት ለማስቆም ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እየሰራው ነው ማለቱ የሚታወቅ ነው፡፡ Via:መናኸሪያ ሬዲዮ @Addis_News
Show all...
👍 14
ዩኒሊቨር ኢትዮጵያ በፀጥታ ችግር ምክንያት ለመስራት ተቸግሪያለሁ አለ ኩባንያው ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው ፣ በሀገሪቱ የሚስ ስተዋሉት ግጭቶች በንግድ እንቅክስቃሴው ላይ ችግር እየፈጠሩብኝ ነው ብሏል። ዩኒሊቨር ኩባንያ የንፅህና መጠበቂያዎችን፣ ምግብ ነክ ምርቶችን በማምረት የሚታወቅ ሲሆን ከሰባት ዓመት በፊት በኢትዮጵያ  ኢንዱስትሪ ዞን ወደስራ የገባ ተቋም ነው ተብሏል ። የዩኒሊቨር ኢትዮጵያ የኮርፖሬት ጉዳዮች ሃላፊ አቶ ደግ ሰው አማኖ ኩባንያቸው ባለው የሰላምና ፀጥታ ችግር ምክንያት ቀላል የማይባል ጉዳት እየደረሰበት መሆኑን ለጣቢያችን ተናግረዋል። ድርጅቱ በአሁኑ ጊዜ ከሰባት ሺህ በላይ ለሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠሩን ጠቁመው፤ በቀጣይም የጀመሩትን ሥራ ለማስፋፋት ዕቅድ እንዳላቸው ጠቁመዋል። ይሁን እንጅ ድርጅቱ በይበልጥ አቅሙን አሟጦ ስራውን እንዳይሰራ የፀጥታው ሁኔታ ችግር እንደፈጠረበት አንስተዋል ። በተጨማሪም የታክስ ፖሊሲ ችግር፣የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ በይበልጥ እንዳይሰራ አድርጎታል ብለዋል። ከቦታ ቦታ በፃነት ተዘዋውረው መስራት፤ ምርትን በተገቢው ሰዓት ለፈላጊዎቹ ማድረስና ማከፋፈል አለመቻላየው የዋጋ ጭማሬ ለማድረግ እንደተገደዱም ሰምተናል ። @Addis_News
Show all...
👍 15
የኤርትራ ጦር  ከዛላንበሳና አጎራባች ወረዳዎች ሰዎችን አግቶ እየወሰደ ነው ተባለ የዛላ  አንበሳ ከተማ ከንቲባ ብርሃነ በርሄ ለጣቢያችን እንደተናገሩት ከምስራቃዊ ዞን  ከአንድ መቶ በላይ ሰዎች ታግተዉ ተወስደዋል  ብለዋል፡፡ ከዛላ አንበሳ 26 ሰዎች፣ ከጉለም ወረዳ  50  እንዲሁም ከኢሮፕ 28 ሰው በኤርትራ ሰራዊት እንደተወሰደ  ገልፀው በዚህ ሳምንት ደግሞ ቁጥሩ መጨመሩን ተናግረዋል። አሁን ላይ ዛላንበሳ ከተማን ጨምሮ  ምስራቃዊው ዞን ሙሉ በሙሉ በኤርትራ ጦር ቁጥጥር ስር እንደሆነ የሚናገሩት የከተማዋ ከንቲባ ማህብረሰቡም  ብዙ በደል እና ጥቃት እየደረሰበት ነዉ ብለዋል፡፡ የኤርትራ ጦር  የአካባቢዉን ነዋሪዎቹ በአልጀርስ ስምምነት መሰረት  ኤርትራዊ እንደሆኑ በመግለጽ  በኃይል  እንደተቆጣጠረም ሰምተናል፡፡ የፌድራል መንግስት ምንም አይነት ትኩረት አልሰጠንም የሚሉት አቶ ብርሀነ ዳግም ጦርነት አንፈልግም ግን ደግሞ ማንነታችንን እና ህልውናችንን ሊያስከብርልን ይገባል ብወዋል። በከተማዋ የሚገኙ መሰረተ ልማቶች በጦሩ  ሙሉ በሙሉ እንደወደሙ ተነስቶ  በከተማው እንዲሁም በአካባቢው ያለው ነዋሪ ለከፋ ችግር እንደተጋለጠም ተናግረዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ ከ30ሺ በላይ ነዋሪ ተፈናቅሎ በመቀሌ፤ በአዲግራት እንዲሁም በተለያዩ አከባቢዎች በመጠለያ ጣቢያ እንደሚገኝ አቶ ብርሀነ ገልፀዋል፡፡ @Addis_News
Show all...
👍 28🤔 1
በቅርቡ በራሱ ሰራተኞች ጉዳት የደረሰበት የአይደር ሆስፒታል የላብራቶሪ ክፍል አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተነገረ የሆስፒታሉ ዳይሬክተር ዶ/ር አብርሃ ገ/እግዚአብሔር ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ማሽኑ በተለያዮ አቅጣጫዎች ውድመት ደርሶበት  ለሁለት ሳምንት ያህል ከአገልግሎት ውጪ እንደነበር ተናግረዋል። ድርጊቱን ፈፅመዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች 4 ግለሰቦች መሆናቸውን እና በቁጥጥር ስር ዉለው ምርመራ እየተደረገባቸው ነው ብለዋል። ተጠርጣሪዎቹም ማሽኑ በነበረበት የስራ ክፍል ላይ ተመሳሳይ የስራ ድርሻ የነበራቸው መሆኑን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል ። እስካሁንም ድርጊቱ ለምን እንደተፈፀመ የተደረሰበት ነገር አለመኖሩን እና አሁንም በምርመራ ላይ እንደሆነ አንስተዋል ። ድርጊቱ የተፈፀመው መጋቢት 21 ለሊት ሲሆን በሚሊዮኖች የሚገመት ዋጋ ያለው የህክምና መሳሪያ ጉዳት ደርሶበት እንደነበር የሚታወስ ነው። @Addis_News
Show all...
👍 5
የአዉሮፓ ህብረት የውጭ ፖሊሲ ሃላፊ ጆሴፍ ቦሬል በአማራ ክልል የቀጠለዉ ግጭት ህብረቱን እንዳሳሰበዉ ገለጹ፡፡ የአዉሮፓ ህብረት በአማራ ክልል የቀጠለዉ የትጥቅ ግጭት እንዳሳሰበዉ የገለጹት ሃላፊዉ፤ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፣ የንጹሃን ዜጎች መሞት እና መጎዳት በእጅጉ ያሳስበዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀበት ጊዜ አንስቶም በአገሪቱ ከፍተኛ እስር መኖሩን አንስተዋል፡፡ ህብረቱ፤የአፍሪካ ህብረት፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እና የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለንጹሃን ጥበቃ እንዲደረግ ፣ ግጭቶች እንዲቆሙ እና በሁለቱ ሃይሎች መካከል ንግግር እንዲደረግ የሚያደርጉትን ጥረት መቀላቀሉንም ነዉ ቦሬል ያስታወቁት፡፡ ህብረቱ በፖለቲካዊ ስምምነት ሰላም ለማምጣት የሚደረግ ንግግር፣ ስምምነት እንዲሁም ማንኛዉንም ጥረት ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን ነዉ የገለጹት፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ለአገሪቱ የወደፊት ሰላም በጋራ እንዲሰሩ እጠይቃለሁ ያሉት ቦሬል፤ ለዚህም በአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ በሚቀመጠዉ አሰራር መሰረት የንግግር እና የስምምነት መንገድን መከተል አለባቸዉ ነዉ ያሉት፡፡ @Addis_News
Show all...
👍 17
ዐቃቤ ሕግ የሽብር ተከሳሾችን ክስ እንዲያሻሽል በተሰጠው ብይን ላይ አቤቱታ አቀረበ! ዐቃቤ ሕግ፣ በሽብር ወንጀል የተከሰሱትን የእነዶር. ወንድወሰን አሰፋን ክስ አሻሽሎ እንዲያቀርብ ፍርድ ቤት ዛሬ ኀሙስ በሰጠው ብይን ላይ፣ “ምስክሮቼን ያጋልጥብኛል” በማለት አቤቱታ አቅርቧል፤ የተከሳሽ ጠበቆች በበኩላቸው ክሱ ካልተሸሻለ እንዲቋረጥ ጠይቀዋል፡፡በተከሳሶቹ የወንጀል ድርጊት “ተገድለዋል” የተባሉ ሰዎች፣ በክሱ ላይ በስም እንዲጠቀሱ ብይን ሰጥቶ የነበረው ፍርድ ቤቱ፣ በዛሬው ክርክር ላይ ትዕዛዝ ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን፣ ከተከሳሾች ጠበቆች አንዱ ሰሎሞን ገዛኸኝ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡ በእነዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ መዝገብ፣ ሰኔ 1 ቀን 2015 ዓ.ም. በዐቃቤ ሕግ የሽብር ክስ የተመሠረተባቸው ተከሳሾች፣ ዛሬ ሚያዝያ 17 ቀን 2016 ዓ.ም. ችሎት ቀርበዋል፡፡የዛሬው ችሎት የተቀጠረው፣ ዐቃቤ ሕግ በፍርድ ቤት በታዘዘው መሠረት ክሱን አሻሽሎ ማቅረቡን ለመመልከት ነበር፡፡ የዐቃቤ ሕግ ክስ፣ ተከሳሾቹ በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈጸሙት የሽብር ወንጀል፣ የ217 ሰዎች ሕይወት ማለፉን፣ ብዙዎች መጎዳታቸውንና ከፍተኛ ንብረትም መውደሙን ሲያስረዳ፣ በተከሳሽ ጠበቆች ጥያቄ መሠረት፣ ሟቾቹ በስም ተጠቅሰው፣ ሌሎች ጉዳቶችም በዝርዝር ተገልጸው ክሱ እንዲሻሻል፣ ፍርድ ቤቱ ባለፈው ኅዳር 12 ቀን በይኖ ነበር፡፡ ኾኖም፣ ዐቃቤ ሕግ፣ ክሱ እንዲሻሻል የተሰጠው ብይን እንዲሻር በደብዳቤ አቤቱታ አቅርቧል፡፡ ለዚኽም በምክንያትነት ያቀረበው፣ እንደ ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ የሟቾቹን ስም መጥቀስ “ምስክሮቹን ለጉዳት የሚዳርግ ነው፤” የሚል እንደኾነ፣ ከተከሳሽ ጠበቆች አንዱ ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ሰሎሞን ገዛኸኝ አስረድተዋል፡፡ጠበቆች በበኩላቸው፣ ዐቃቤ ሕግ የፍርድ ቤቱን ብያኔ አክብሮ ክሱን የማያሻሽል ከኾነ ክሱ እንዲነሣ መጠየቃቸውንም ተናግረዋል፡፡የግራ ቀኙን ክርክር ያደመጠው ችሎቱ፣ በጉዳዩ ላይ ትእዛዝ ለመስጠት ለግንቦት 12 ቀን መቅጠሩን፣ ጠበቃ ሰሎሞን ገዛኸኝ አመልክተዋል፡፡ በክስ መዝገቡ ላይ ከተጠቀሱ 51 የሽብር ወንጀል ተከሳሾች መካከል አራት የመገናኛ ብዙኀን ባለሞያዎችን ጨምሮ 23ቱ በቁጥጥር ሥር ውለው ጉዳያቸውን በመከታተል ላይ የነበሩ ናቸው፡፡ ከመካከላቸው አንዱ ለሕክምና እንደወጡ ማምለጣቸውን፣ የፌዴራል ማረሚያ ቤት ተወካዮች ከዚኽ ቀደም ለፍርድ ቤት ማሳወቃቸውን ጠበቆቹ ገልጸዋል፡፡ጉዳያቸው በሌሉበት እየታየ የሚገኙ ተከሳሾችን፣ በጋዜጣ ጥሪ ተደርጎላቸው ውጤቱ ለቀጣዩ ችሎት እንዲቀርብም ፍርድ ቤቱ አዟል፡፡ Via :VoA @Addis_News
Show all...
👍 14
ዲ/ን ዕዝራ ኃይለ ሚካኤል ወደ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በይቅርታ መመለሳቸው ተገለጸ። ዲ/ን ዕዝራ ኃይለ ሚካኤል ወደ እናት ቤተ ክርስቲያን በይቅርታ መመለሳቸውን ቋሚ ቅዱስ ሲኖዶስ ማሳወቁ ተገለጸ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ቅዱስ ሲኖዶስ ይቅርታውን የተቀበለው ሚያዚያ 9/2016 ዓ/ም ባደረገው ስብሰባ ሲሆን ዲ/ን ዕዝራ ኃይለ ሚካኤል "በምንፍቅና መንገድ ስጓዝ የነበርኩ ስሆን በአሁኑ ወቅት የስህተት መንገዴን አርሜ ወደ እናት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን በይቅርታ ልመለስ" ብለው ያቀረቡትን ጥያቄ ተክሎ መሆኑም ተገልጿል። ቋሚ ቅዱስ ሲኖዶስም ዲ/ን ዕዝራ ኃይለ ሚካኤል በጠየቁት መሠረት በድጋሚ እንዳይበድሉ ምክርና ተግሣጽ ተሰጥቷቸው ወደ እናት ቤተ ክርስቲያን በይቅርታ መመለሳቸውን አሳውቋል። በቋሚ ቅዱስ ሲኖዶስ ተቀባይነት ያገኘው የይቅርታ ጥያቄ እንዳለ ሆኖ በቅዱስ ሲኖዶስ በታዘዘው መሠረት ዲ/ን ዕዝራ ኃይለ ሚካኤል በይፋ ወጥተው በይቅርታ መመለሳቸውንና ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንን ይቅርታ መጠየቃቸውን የገለጹ መሆኑን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መገናኛ ብዙኃን አገልግሎት ድርጅት ካስተላለፈው መረጃ ለማወቅ ተችሏል። ከዚህ በተጨማሪም በይቅርታ የተመለሱትን ዲ/ን ዕዝራ ኃይለ ሚካኤልን በምክር የሚያጸኑና በተግሳጽ የሚያቀኑና የሚከታተሉ አባቶች መኖራቸውም ታውቋል። ዲ/ን ዕዝራ ኃይለ ሚካኤል ቀደም ባለ ታሪካቸው ገና በልጅነታቸው ዕድሜ ለዝማሬ አገልግሎት በቤተ ክርስቲያን ዐውደ ምሕረት ከቆሙ አገልጋዮች አንዱ እንደነበሩ የሚታወስ ነው። የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ @Addis_News
Show all...
👍 62😐 3🤔 2❤‍🔥 1