cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ወሒድ የንጽጽር ማኅደር

ወንድም ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!

Show more
Advertising posts
34 039Subscribers
+1024 hours
+1007 days
+43930 days
Posts Archive
አሥ ሠላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ ያ ጀመዓህ! "የተደበቀው እውነት" የሚለው ስድስተኛው መጽሐፌ በገበያ ላይ ውሏል። "የተደበቀው እውነት" የሚያውጠነጥነው ስለ ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" መምጣት በተውራት እና በኢንጂል ተነግሮ የመጽሐፉ ሰዎች ይህንን እውነት እንዴት እንደደበቁት የሚገልጥ እና የሚያጋልጥ ነው። ዝርዝሩን መጽሐፉ ላይ ያንብቡ እና ለሎች የሂዳያህ ሠበብ እንዲሆን አስነብቡ! መጽሐፉን መርካርቶ አንዋር መሥጂድ ኢሥላማዊ መጻሕፍት መደብር ውስጥ ያገኙታል፥ የበለጠ ለመረጃ +251920781016 ዐብዱ ብለው ይደውሉ! መጽሐፉ ተደራሽነት እንዲኖረው ባለው የማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን ሼር በማድረግ ሠበቡል ሂዳያህ ይሁኑ! ወጀዛኩሙላህ ኸይራ! ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom
Show all...
owdHDfiZEE0QIDiRJgmgFBjfQgR4AFsuYBwFCs.mp4
Show all...
ኤጲስ ቆጶሱ ማር ማሪ ኢማኑኤል በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 2፥120 አይሁዶች እና ክርስቲያኖች ሃይማኖታቸውን እስከምትከተል ድረስ ከአንተ ፈጽሞ አይወዱም፡፡ وَلَن تَرْضَىٰ عَنكَ الْيَهُودُ وَلَا النَّصَارَىٰ حَتَّىٰ تَتَّبِعَ مِلَّتَهُمْ ኤጲስ ቆጶስ ማር ማሪ ኢማኑኤል"Bishop Mar Mari Emmanuel" በሲድኒ አውስትራሊያ በሚገኘው የሶሪያውያን ቤተ ክርስቲያን"Assyrian Church" ሊቀ ጳጳስ ሲሆኑ በአሁን ሰዓት "ክርስቶስ መልካም እረኛ ቤተ ክርስቲያን"Christ The Good Shepherd Church" ውስጥ ያገለግሉ ነበር። የሶሪያውያን ቤተክርስቲያን የንስጥሮስ ትምህርት ተከታይ ሲሆኑ የንስጥሮስ ትምህርት "ኢየሱስ በአንድ ስም ሁለት ማንነት"person" አለው፥ በፍጹም አምላካዊ ማንነት የአብ ልጅ በፍጹም ሰዋዊ ማንነት የማርያም ልጅ" የሚል ትምህርት ነው፥ ይህ ትምህርት በ 431 የኤፌሶን ጉባኤ የተወገዘ ሲሆን ኤጲስ ቆጶስ ማር ማሪ ኢማኑኤል የእዛ እሳቤ አራማጅ ናቸው። በዓለም ላይ ያሉ ብዙ ኦርቶዶክሶች እኚህን አባት እንደ ኦርቶዶክስ አባት አርገው የሚመለከቱት ትምህርታቸው ከራሳቸው ትምህርት ጋር አነጻጽረው በቅጡ መረዳት የማይችሉት ናቸው፥ ቅሉ እና ጥቅሉ ግን የንስጥሮስ ትምህርት በካቶሊክ፣ በምሥራቅ ኦርቶዶክስ፣ በጽብሐዊ ኦርቶዶክስ እና በፕሮቴስታንት የተወገዘ ምንፍቅ ና ነው። ኤጲስ ቆጶስ ማር ማሪ ኢማኑኤል በተለያየ ርእሰ ጉዳይ በእንግሊዝኛ መርሐ ግብር የተለያ እሳቦትን በመተናኮል እና በመጎንተል በዓለም ላይ ይታወቃሉ። እስራኤልን፣ ምዕራባውያንን፣ አሜሪካንን፣ ግብረ ሰዶማ ውያንን ሳይቀር ይተቻሉ፥ አልፎ አልፎ ካቶሊክን፣ ፕሮቴስታንትን ሲላቸውም ዲኑል ኢሥላምን ሲወርፉ ይሰማል። ትላንት አንድ ሰው በሚያስተምሩበት ቤተክርስቲያን አደጋ አድርሶባቸው ህክምና ላይ እዳሉ እየተሰማ ነው። አደጋ ያደረሰባቸው ማንነት እስካሁን እንዳልተጣራ እየታወቀ ክርፋታቸው በተገኘው አጋጣሚ የሚያዝረከርኩ ክርስቲያኖች ለሙሥሊም ያላቸው ጥላቻ ምን ያክል የከፋ እና የከረፋ መሆኑን የምታውቁት ሰውዬውን "ሙሥሊም ነው" በማለት ዲናችንን መዝለፍ እና ማብጠልጠል ተያይዘውታል። ሰውዬው ሙሥሊም ቢሆንስ? ሰውዬውን "ትክክል አይደለም" ብሎ እራሱን ማውገዝ እንጂ ዲናችንን ለምን አሳቻ ሰዓት ላይ ጠብቃችሁ ትጎነትላላችሁ? ስንት እና ስንት ሙሥሊሞች በክርስቲያኖች ተገለው እንደ ኖርማል እየታየ አንድ ክርስቲያን ስለተገደለ ክርስትናን የእውነት ሚዛን አርጎ መውሰድ ቂልነት ነው። በእርግጥም ኤጲስ ቆጶሱ ማር ማሪ ኢማኑኤል ለዲኑል ኢሥላም ያላቸው ጥላቻ አይጣል ነው፥ በአገኙት አጋጣሚ ዲናችንን በማበሻቀጥ እና በማብጠልጠል የዘመኑን ዋንጫ ወስደዋል። ከዚህ ሁሉ የገረመኝ ተከታዮቻቸው "ዓይን ስለ ዓይን ጥርስ ስለ ጥርስ" የሚለውን ሕግ ይዘው "የእጁን እንስጠው" ብለው ግብግብ ሲይዙ ነበር። "ዳሩ ግን ቀኝ ጉንጭህን በጥፊ ለሚመታህ ሁሉ ሁለተኛውን ደግሞ አዙርለት" የሚለው የሚሠራው ስብከት ላይ ብቻ ነው፦ ማቴዎስ 5፥38 ‘ዓይን ስለ ዓይን ጥርስም ስለ ጥርስ፡’ እንደ ተባለ ሰምታችኋል። እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ክፉውን አትቃወሙ፤ ዳሩ ግን ቀኝ ጉንጭህን በጥፊ ለሚመታህ ሁሉ ሁለተኛውን ደግሞ አዙርለት። አይሁዶች እና ክርስቲያኖች ሃይማኖታቸውን እስከምንከተል ድረስ እንዳይወዱን አሏህ በቁርኣኑ ነግሮናል፦ 2፥120 አይሁዶች እና ክርስቲያኖች ሃይማኖታቸውን እስከምትከተል ድረስ ከአንተ ፈጽሞ አይወዱም፡፡ وَلَن تَرْضَىٰ عَنكَ الْيَهُودُ وَلَا النَّصَارَىٰ حَتَّىٰ تَتَّبِعَ مِلَّتَهُمْ አሏህ ለእነርሱ ልብ ይስጣቸው! ለእኛም ትእግስቱን ይስጠን! አሚን። አንብበው ሼር በማድረግ አስነብቡ! ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Show all...
የሃይማኖት ንጽጽር ኮርስ በወሒድ ዕቅበተ ኢሥላም ማኅበር"Wahid islamic apologetics society" 12ኛ ዙር የሙቃረናህ ደርሥ! "ሙቃረናህ" مُقَارَنَة የሚለው ቃል "ቃረነ" قَارَنَ ማለትም "አነጻጸረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ንጽጽር" ማለት ነው፥ ሙቃረናህ የሃይማኖት ንጽጽር"Comparative Religion" ሲሆን በዱኑል ኢሥላም እና እና በክርስትና መካከል ያለው የሥነ መለኮት አንድነት እና ልዩነት እየተነጻጸረ የሚቀርብበት ጥናት ነው። ደርሡ (ትምህርቱ) የሚፈጀው 7 ወር ኢንሻሏህ ሲሆን ሁለት ተርም አለው። ፨ የመጀመሪያው ተርም ዐጽመ አሳብ በፈጣሪ እሳቦት ላይ የሚያውጠነጥነው፦ 1.በነገረ ሥላሴ ጥናት"Triadogy" 2.በነገረ ክርስቶስ ጥናት"Christology" 3.በነገረ ማርያም ጥናት"Mariology" 4. በነገረ መላእክት ጥናት"angelology" 5. በነገረ ምስል ጥናት"Iconlogy" ላይ ነው። ፨ የሁለተኛው ተርም ዐጽመ-አሳብ በቅዱሳን መጽሐፍት ላይ የሚያውጠነጥነው፦ 1.በአህሉል ኪታብ"People of the Book" 2.በመጽሐፍት"scriptures" 3. በመጽሐፍ አጠባበቅ"preservation" 4.በመጽሐፍት ልኬት"Standardization" 5. በባይብል ግጭት"Contradiction" 6. በኦሪት"Torah" 7. በወንጌል"Gospel" ላይ ነው። አባሪ ኮርሶች፦ 1. ዐቂዳህ"creed" 2. ሥነ ምግባር"ethics" 3. ሥነ አመክንዮ"logic" 4. ሥነ ልቦና"psychology" 5. ሥነ ቋንቋ"linguistics" ናቸው። ለመመዝገብ ከታች የተዘረዘሩት አድሚናት በውስጥ ያናግሩ! ወንድም አቡ ኑዓይም፦https://t.me/arhmanu እኅት ሰላም፦ http://t.me/SeuweSe አኅት ዘሃራ፦ https://t.me/Zhara_mustefa እኅት አበባ፦ http://t.me/selemtewa ቦታ ሳይያዝ ይመዝገቡ! መልካም የትምህርት ጊዜ ይሁንልዎ! ወጀዛኩሙላህ ኸይራ!
Show all...
አምላካችን አሏህ ሰው እርስ በእርስ ሥጋውን እንዲበላላ ሐላል አላደረግም፥ ከዚያ በተቃራኒ የሰው ሥጋ መብላት ሐራም ነው፦ 49፥12 ከፊላችሁም ከፊሉን አይማ! አንደኛችሁ የወንድሙን ሥጋ የሞተ ኾኖ ሊበላው ይወዳልን? መብላቱን ጠላችሁት ሐሜቱንም ጥሉት፡፡ አሏህን ፍሩ! አሏህ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነውና፡፡ وَلَا يَغْتَب بَّعْضُكُم بَعْضًا ۚ أَيُحِبُّ أَحَدُكُمْ أَن يَأْكُلَ لَحْمَ أَخِيهِ مَيْتًا فَكَرِهْتُمُوهُ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ تَوَّابٌ رَّحِيمٌ ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 43, ሐዲስ 106 አነሥ ኢብኑ-ማሊክ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ወደ ሰማይ በተወሰድኩኝ ጊዜ ከነሐስ የሆነ ጥፍር ኖሯቸው ፊቶቻቸውን እና ደረቶቻቸውን የሚቧጥጡ በሆኑ ሰዎች በኩል አለፍኩ። እኔም፡- "ጂብሪል ሆይ! እነማናቸው እነዚህ? ስለው፥ እርሱም፦ "እነዚህ የሰዎችን ሥጋ የሚበሉ እና ክብራቸውን የሚነኩ ናቸው" አለኝ"። عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ لَمَّا عُرِجَ بِي مَرَرْتُ بِقَوْمٍ لَهُمْ أَظْفَارٌ مِنْ نُحَاسٍ يَخْمِشُونَ وُجُوهَهُمْ وَصُدُورَهُمْ فَقُلْتُ مَنْ هَؤُلاَءِ يَا جِبْرِيلُ قَالَ هَؤُلاَءِ الَّذِينَ يَأْكُلُونَ لُحُومَ النَّاسِ وَيَقَعُونَ فِي أَعْرَاضِهِمْ ‏"‏ እዚህ ቁርኣን እና እዚህ ሐዲስ ላይ ሐሜት ልክ የሰውን ሥጋ እንደ መብላት ሐራም ከሆነ የሰውን ሥጋ ለምግብነት መጠቀም ሐራም ነው። ሰው ከሞተ በኃላ ሥጋው ሬሳ ነውና መቅበር እንጂ የሞተ ሰው ሥጋ መብላት በቁሙ ያለው ሰው ሥጋ እንደ መብላት ይቆጠራል፦ ሡነን እብኑ ማጃህ መጽሐፍ 6, ሐዲስ 184 ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "የሞተ ሰው አጥንት መስበር በሕይወት እያለ እንደ መሰባበር ነው"። عَنْ عَائِشَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ كَسْرُ عَظْمِ الْمَيِّتِ كَكَسْرِهِ حَيًّا ‏"‏ ‏ ኢማም ሙሐመድ ኢብኑ ኢድሪሥ አሽ ሻፊዒይ "የሞተ ሰው ሥጋ ሕይወትን ለማትረፍ በረሃብ ጊዜ ይፈቀዳል" ብለዋል፥ ለዚህ አባባል ምንም ዓይነት የቁርኣን ሆነ የሐዲስ ደሊል እንከሌለ ድረስ ንግግራቸው ውድቅ ይሆናል። እርሳቸው በ 204 ዓመተ ሒጅራህ በትህትና "የእኔን ንግግር የሚቃወም ሶሒሕ ሐዲስ ሲኖር በሐዲሱን ተግብሩ! ቃሌን ተዉት" ብለዋል፦ "የእኔን ንግግር የሚቃወም ሶሒሕ ሐዲስ ሲኖር በሐዲሱን ተግብሩ! ቃሌን ተዉት"። إذا صح الحديث خلاف قولي فاعملوا بالحديث واتركوا قولي ጃሚዒ አት ቲርሚዚይ መጽሐፍ 37 ሐዲስ 106 አቢ ሠዒድ አል ኹድሪይ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ማንም ይሁን መልካሙን የበላ፣ በሡናህ የተገበረ እና ሰዎች ከሚያስከትለው መዘዝ የታደገ ወደ ጀናህ ይገባል"። عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ مَنْ أَكَلَ طَيِّبًا وَعَمِلَ فِي سُنَّةٍ وَأَمِنَ النَّاسُ بَوَائِقَهُ دَخَلَ الْجَنَّةَ ‏"‏ ‏.‏ "ሐላል" حَلاَل ማለት "የተፈቀደ" ማለት ሲሆን በተቃራኒው "ሐራም" حَرَام "የተከለከለ" ማለት ነው። አንድ ጉዳይ ሐላል ወይም ሐራም ማለት የሚቻለው የዓለማቱ ጌታ አሏህ በቁርኣን የነገረን እና ተወዳጁ ነቢያችን”ﷺ” በሐዲሳቸው የነገሩን ብቻ እና ብቻ ነው፥ ሐላል የሆነ ጉዳይ ሆነ ሐራም የሆነ ጉዳይ በሸሪዓችን በግልጽ የተቀመጡት ብቻ ናቸው፦ 7፥157 "መልካም ነገሮችንም ለነርሱ ይፈቅድላቸዋል፥ መጥፎ ነገሮችንም በእነርሱ ላይ እርም ያደርግባቸዋል"፡፡ وَيُحِلُّ لَهُمُ الطَّيِّبَاتِ وَيُحَرِّمُ عَلَيْهِمُ الْخَبَائِثَ ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 23, ሐዲስ 4 አን-ኑዕማን ኢብኑ በሺር እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ሐላል ግልጽ ነው፥ ሐራምም ግልጽ ነው። በሁለቱ መካከል ያለው ግን አጠራጣሪ ነገር ነው”። قَالَ سَمِعْتُ النُّعْمَانَ بْنَ بَشِيرٍ، – وَلاَ أَسْمَعُ أَحَدًا بَعْدَهُ يَقُولُ – سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏”‏ إِنَّ الْحَلاَلَ بَيِّنٌ وَإِنَّ الْحَرَامَ بَيِّنٌ وَبَيْنَهُمَا أُمُورٌ مُشْتَبِهَاتٌ ‏”‏ አንድ ጉዳይ በግልጽ መፈቀዱ እና መከልከሉ ካልተገለጸ "ተፈቅዷል" "ተከልክሏል" ማለት የለብንም፥ ያልተፈቀደ እና ያልተከለከለ ነገር ጉዳይ አጠራጣሪ ነው፥ ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ደግሞ፦ "የሚያጠራጥርህን ትተህ ወደ ማያጠራጥርህ ሂድ! እውነት ያረጋጋል፥ ውሸት ግን ያጠራጥራል" ብለውናል፦ ጃምዒ አት ቲርሚዚይ መጽሐፍ 37, ሐዲስ 2708 አቢል ሐውራእ አሥ-ሠዕዲይ እንደተረከው፦ "እኔ ለሐሠን ኢብኑ ዐሊይ፦ "ከአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" ምን ሐፈዝክ? ብዬ አልኩኝ፥ እርሱም፦ "ከአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ ሲሉ ሐፈዝኩኝ፦ "የሚያጠራጥርህን ትተህ ወደ ማያጠራጥርህ ሂድ! እውነት ያረጋጋል፥ ውሸት ግን ያጠራጥራል"። عَنْ أَبِي الْحَوْرَاءِ السَّعْدِيِّ، قَالَ قُلْتُ لِلْحَسَنِ بْنِ عَلِيٍّ مَا حَفِظْتَ مِنْ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ حَفِظْتُ مِنْ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ دَعْ مَا يَرِيبُكَ إِلَى مَا لاَ يَرِيبُكَ فَإِنَّ الصِّدْقَ طُمَأْنِينَةٌ وَإِنَّ الْكَذِبَ رِيبَةٌ ‏"‏ "መሽቡህ" مَشْبُوه የሆኑ ነገሮችን መተው ተመራጩ ሒክማህ ነው። አምላካችን አሏህ በግልጠተ መለኮት "ሐላል" ያለው "ሐላል" ማለት "ሐራም" ያለው "ሐራም" ማለት ትልቅ ታዛዥነት ነው፦ ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 29, ሐዲስ 117 ሠልማን አል ፋርሢይ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” ስለ ቅቤ፣ ስለ ዓይብ እና ስለ አህዮች ተጠየቁ፥ እርሳቸው እንዲህ አሉ፦ "ሐላል አሏህ በመጽሐፉ የፈቀደው ነው፥ ሐራም አሏህ በመጽሐፉ የከለከለው ነው። عَنْ سَلْمَانَ الْفَارِسِيِّ، قَالَ سُئِلَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ عَنِ السَّمْنِ وَالْجُبْنِ وَالْفِرَاءِ قَالَ ‏ "‏ الْحَلاَلُ مَا أَحَلَّ اللَّهُ فِي كِتَابِهِ وَالْحَرَامُ مَا حَرَّمَ اللَّهُ فِي كِتَابِهِ "‏ ‏.‏ አምላካችን አሏህ ሡናን ከሚተገብሩ ሙእሚን ያድርገን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Show all...
ን የሚቧጥጡ በሆኑ ሰዎች በኩል አለፍኩ። እኔም፡- "ጂብሪል ሆይ! እነማናቸው እነዚህ? ስለው፥ እርሱም፦ "እነዚህ የሰዎችን ሥጋ የሚበሉ እና ክብራቸውን የሚነኩ ናቸው" አለኝ"። عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ لَمَّا عُرِجَ بِي مَرَرْتُ بِقَوْمٍ لَهُمْ أَظْفَارٌ مِنْ نُحَاسٍ يَخْمِشُونَ وُجُوهَهُمْ وَصُدُورَهُمْ فَقُلْتُ مَنْ هَؤُلاَءِ يَا جِبْرِيلُ قَالَ هَؤُلاَءِ الَّذِينَ يَأْكُلُونَ لُحُومَ النَّاسِ وَيَقَعُونَ فِي أَعْرَاضِهِمْ ‏"‏
Show all...
የሰው ሥጋ ይበላልን? በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡ 7፥70 የአደምንም ልጆች በእርግጥ አከበርናቸው፡፡ وَلَقَدْ كَرَّمْنَا بَنِي آدَمَ አምላካችን አሏህ በመልእክተኞች በኩል "ከመልካሞቹ ምግቦች ብሉ" ብሎ ነግሮናል፥ እነዚህ መልካም ምግቦት የሰጠን ሲሳይ ናቸው፦ 23፥51 እናንተ መልእክተኞች ሆይ! ከመልካሞቹ ምግቦች ብሉ፡፡ በጎ ሥራንም ሥሩ፡፡ እኔ የምተሠሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነኝ፡፡ يَا أَيُّهَا الرُّسُلُ كُلُوا مِنَ الطَّيِّبَاتِ وَاعْمَلُوا صَالِحًا ۖ إِنِّي بِمَا تَعْمَلُونَ عَلِيمٌ 2፥172 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከእነዚያ ከሰጠናችሁ ሲሳይ መልካሞቹን ብሉ፡፡ እርሱን ብቻ የምታመልኩ እንደኾናችሁ አሏህን አመስግኑ፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُلُوا مِن طَيِّبَاتِ مَا رَزَقْنَاكُمْ وَاشْكُرُوا لِلَّهِ إِن كُنتُمْ إِيَّاهُ تَعْبُدُونَ ጃሚዒ አት ቲርሚዚይ መጽሐፍ 47 ሐዲስ 41 አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህም መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "እናንተ ሰዎች ሆይ! አሏህ መልካም ነው፥ እርሱ መልካም እንጂ አይቀበልም። አሏህ ምእመናንን መልእክተኞችን ባዘዘው መሠረት አዘዛቸው። እርሱም፦ "እናንተ መልእክተኞች ሆይ! ከመልካሞቹ ምግቦች ብሉ፡፡ በጎ ሥራንም ሥሩ፡፡ እኔ የምተሠሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነኝ" አለ፥ እርሱም፦ "እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከእነዚያ ከሰጠናችሁ ሲሳይ መልካሞቹን ብሉ" አለ"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ يَا أَيُّهَا النَّاسُ إِنَّ اللَّهَ طَيِّبٌ وَلاَ يَقْبَلُ إِلاَّ طَيِّبًا وَإِنَّ اللَّهَ أَمَرَ الْمُؤْمِنِينَ بِمَا أَمَرَ بِهِ الْمُرْسَلِينَ فَقَالَ ‏:‏ ‏(‏يَا أَيُّهَا الرُّسُلُ كُلُوا مِنَ الطَّيِّبَاتِ وَاعْمَلُوا صَالِحًا إِنِّي بِمَا تَعْمَلُونَ عَلِيمٌ ‏)‏ وَقَالَ أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُلُوا مِنْ طَيِّبَاتِ مَا رَزَقْنَاكُمْ ‏)‏ ‏"‏ ‏.‏ በተቃራኒው በክትን፣ ደምን፣ የእሪያ ሥጋን እና ከአሏህ ስም ሌላ የተነሳበትን ነገር መብላት ሐራም ነው፦ 2፥173 በእናንተ ላይ እርም ያደረገው በክትን፣ ደምን፣ የእሪያ ሥጋን እና በእርሱም ማረድ ከአሏህ ስም ሌላ የተነሳበትን ነገር ብቻ ነው፡፡ إِنَّمَا حَرَّمَ عَلَيْكُمُ الْمَيْتَةَ وَالدَّمَ وَلَحْمَ الْخِنزِيرِ وَمَا أُهِلَّ بِهِ لِغَيْرِ اللَّهِ በክትን፣ ደምን፣ የእሪያ ሥጋን እና ከአሏህ ስም ሌላ የተነሳበትን ነገር መብላት ቢሆንም በረሃብ ምክንያት በሞት አፋፍ ላይ ላለ ሰው ሕይወት ለማትረፍ ተፈቅዷል፦ 2፥173 ሽፍታ እና ወሰን አላፊ ሳይኾን ለመብላት የተገደደ ሰውም በእርሱ ላይ ኃጢአት የለበትም። አሏህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡ فَمَنِ اضْطُرَّ غَيْرَ بَاغٍ وَلَا عَادٍ فَلَا إِثْمَ عَلَيْهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ ነገር ግን በማንኛውም ወቅት እና ሁኔታ ሁለት ዓይነት የሞተ ሥጋ እና ሁለት ዓይነት ደም መብላት ሐላል ነው፥ ሁለት ዓይነት የሞተ ሥጋ ዓሣ እና አንበጣ ሲሆኑ ዓሣ እና አንበጣ የማይታረዱ ሥጋ ናቸው። ሁለት ዓይነት ደም ደግሞ ጉበት እና ጣፊያ ናቸው፦ 16፥14 እርሱም ያ ባሕርን ከእርሱ እርጥብ ሥጋን ልትበሉ እና ከእርሱም የምትለብሱትን ጌጣጌጥ ታወጡ ዘንድ ያገራ ነው፡፡ وَهُوَ الَّذِي سَخَّرَ الْبَحْرَ لِتَأْكُلُوا مِنْهُ لَحْمًا طَرِيًّا وَتَسْتَخْرِجُوا مِنْهُ حِلْيَةً تَلْبَسُونَهَا 5፥96 የባሕር ታዳኝ እና ምግቡ ለእናንተ እና ለመንገደኞችም መጠቀሚያ ይኾን ዘንድ ለእናንተ ተፈቀደ፡፡ የየብስ አውሬ በእናንተ ላይ እርም ተደረገ፡፡ أُحِلَّ لَكُمْ صَيْدُ الْبَحْرِ وَطَعَامُهُ مَتَاعًا لَّكُمْ وَلِلسَّيَّارَةِ ۖ وَحُرِّمَ عَلَيْكُمْ صَيْدُ الْبَرِّ مَا دُمْتُمْ حُرُمًا ۗ ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 29, ሐዲስ 64 ዐብደሏህ ኢብኑ ዑመር እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ሁለት ዓይነት የሞተ ሥጋ እና ሁለት ዓይነት ደም ለእኛ ተፈቅዶልናል፥ ሁለት ዓይነት የሞተ ሥጋ ዓሣ እና አንበጣ ሲሆን ሁለት ዓይነት ደም ደግሞ ጉበት እና ጣፊያ ነው"። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عُمَرَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ قَالَ ‏ "‏ أُحِلَّتْ لَنَا مَيْتَتَانِ وَدَمَانِ فَأَمَّا الْمَيْتَتَانِ فَالْحُوتُ وَالْجَرَادُ وَأَمَّا الدَّمَانِ فَالْكَبِدُ وَالطِّحَالُ ‏"‏ ‏.‏ ቡሉጉል መራም መጽሐፍ 1 ሐዲስ 1 አቢ ሁረይራህ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "የአሏህም መልእክተኛ"ﷺ" ስለ ባሕር እንዲህ አሉ፦ "እርሱ ውኃው ንጹሕ ነው፥ ሙታኑ እንስሳት ለመብላት ሐላል ነው"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ‏- رضى الله عنه ‏- قَالَ: قَالَ رَسُولُ اَللَّهِ ‏- صلى الله عليه وسلم ‏-فِي اَلْبَحْرِ: { هُوَ اَلطُّهُورُ مَاؤُهُ, اَلْحِلُّ مَيْتَتُهُ } ይህንን ከተረዳን ዘንዳ አምላካችን አሏህ የሰውን ልጅ ያከበረው ፍጡር ነው፥ ሐላል ምግብ ከየብስ እና ከባሕር እንዲመገቡት የአደምን ልጆች አሏህ በየብስ እና በባሕር አሳፈራቸው። ከፈጠርናቸውም ፍጡሮች ከማዕድናት፣ ከዕጽዋት፣ ከእንስሳት በብዙዎቹ ላይ ማብለጥን አበለጣቸው፦ 7፥70 የአደምንም ልጆች በእርግጥ አከበርናቸው፡፡ وَلَقَدْ كَرَّمْنَا بَنِي آدَمَ 7፥70 በየብስ እና በባሕር አሳፈርናቸው፥ ከመልካሞች ሲሳዮች ሰጠናቸው፡፡ وَحَمَلْنَاهُمْ فِي الْبَرِّ وَالْبَحْرِ وَرَزَقْنَاهُم مِّنَ الطَّيِّبَاتِ 7፥70 ከፈጠርናቸውም ፍጡሮች በብዙዎቹ ላይ ማብለጥን አበለጥናቸው፡፡ وَفَضَّلْنَاهُمْ عَلَىٰ كَثِيرٍ مِّمَّنْ خَلَقْنَا تَفْضِيلًا አምላካችን አሏህ ሰው እርስ በእርስ ሥጋውን እንዲበላላ ሐላል አላደረግም፥ ከዚያ በተቃራኒ የሰው ሥጋ መብላት ሐራም ነው፦ 49፥12 ከፊላችሁም ከፊሉን አይማ! አንደኛችሁ የወንድሙን ሥጋ የሞተ ኾኖ ሊበላው ይወዳልን? መብላቱን ጠላችሁት ሐሜቱንም ጥሉት፡፡ አሏህን ፍሩ! አሏህ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነውና፡፡ وَلَا يَغْتَب بَّعْضُكُم بَعْضًا ۚ أَيُحِبُّ أَحَدُكُمْ أَن يَأْكُلَ لَحْمَ أَخِيهِ مَيْتًا فَكَرِهْتُمُوهُ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ تَوَّابٌ رَّحِيمٌ ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 43, ሐዲስ 106 አነሥ ኢብኑ-ማሊክ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ወደ ሰማይ በተወሰድኩኝ ጊዜ ከነሐስ የሆነ ጥፍር ኖሯቸው ፊቶቻቸውን እና ደረቶቻቸው
Show all...
አሥ-ሠላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ! እንኳን የዒዱል ፊጥር በሰላም አደረሳችሁ! ተናፍቆ የሚመጣ እና ሳይጠገብ የሚሄድ ብቸኛው ወር የረመዷን ወር ነው። አሏህ ከእኛም ከእናንተ መልካም ሥራዎችን ይቀበለን! አሚን። ዒድ ሙባረክ!
Show all...
"ኢየሱስ በቀጣይ እሑድ ይመጣል" ልደታ ቤተክርስቲያን መምህርት አስካለ በልጅነታችን ኢየሱስ፦ ፨በዕለተ እሑድ ፨በቀኑ 29 ቀን ፨በወሩ መጋቢት ወር ፨በዘመኑ ዘመነ ዮሐንስ ከገጠመ ይመጣል ብላ አስተምራናለች። ባሕረ አሳብን ቀምረው የአገራችን ሊቃውንት "በዘመነ ዮሐንስ እሑድ በመጋቢት 29 ቀን ይመጣል" ባሉት መሠረት እየጠበቅን ነው። ይህን ካልሆነ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከሐሰተኛ ነቢያት ተለይታ አትለይም። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom
Show all...
ዘካህ ለሠለምቴዎች በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። 2፥219 ”ምንን እንደሚመጸውቱም መጠኑን ይጠይቁሃል፡፡ «ትርፍን መጽውቱ» በላቸው”፡፡ እንደዚሁ ታስተነትኑ ዘንድ አላህ ለእናንተ አንቀጾችን ይገልጽላችኋል፡፡ وَيَسْأَلُونَكَ مَاذَا يُنفِقُونَ قُلِ الْعَفْوَ ۗ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ اللَّهُ لَكُمُ الْآيَاتِ لَعَلَّكُمْ تَتَفَكَّرُونَ “ዘካህ” زَكَاة ጥቅላዊ የግዴታ ምፅዋት ማለት ሲሆን የዘካህ ብዙ ቁጥር “ዘካት” زَكَوَات ሲሆን በተናጥል ዘካት በሁለት ይከፈላል፥ እነርሱም “ዘካቱል ማል” زَكَاة المَال እና “ዘካቱል ፊጥር” زَكَاة الفِطْر ናቸው። “ማል” مَال ማለት “ሀብት” ማለት ሲሆን የማል ብዙ ቁጥር ደግሞ “አምዋል” أَمْوَال ነው፥ ከተቀማጭ ሀብት ላይ ወይም ከትርፍ ላይ የሚሰጠው ዘካህ “ዘካቱል ማል” زَكَاة المَال ይባላል። በነቢያችን”ﷺ” ሸሪዓህ ግን ዘካቱል ማል ከካፒታል ላይ ከመቶ 2.5 % የሚሰጥ ነው፥ ነቢያችን”ﷺ” ከሁለት መቶ ዲርሀም 5% ዘካህ እንደሚወጣ ተናግረዋል። ያ ማለት የዘካህ ሒሳብ በመቶ ዲርሀም 5፥2=2.5 ይሆናል፦ 2፥219 ”ምንን እንደሚመጸውቱም መጠኑን ይጠይቁሃል፡፡ «ትርፍን መጽውቱ» በላቸው”፡፡ እንደዚሁ ታስተነትኑ ዘንድ አላህ ለእናንተ አንቀጾችን ይገልጽላችኋል፡፡ وَيَسْأَلُونَكَ مَاذَا يُنفِقُونَ قُلِ الْعَفْوَ ۗ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ اللَّهُ لَكُمُ الْآيَاتِ لَعَلَّكُمْ تَتَفَكَّرُونَ ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 9, ሐዲስ 18 ዐሊይ”ረ.ዐ” እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ ”ሁለት መቶ ዲርሀም ለአንተ በሆነች ጊዜና ዓመት ከሞላች አምስት ደራሂም ይወጣል፥ በአንተ ምንም ነገር አይሆንም ሃያ ዲናር እስኪሆን ድረስ”። عَنْ عَلِيٍّ، – رضى الله عنه – عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم بِبَعْضِ أَوَّلِ هَذَا الْحَدِيثِ قَالَ ‏”‏ فَإِذَا كَانَتْ لَكَ مِائَتَا دِرْهَمٍ وَحَالَ عَلَيْهَا الْحَوْلُ فَفِيهَا خَمْسَةُ دَرَاهِمَ وَلَيْسَ عَلَيْكَ شَىْءٌ – يَعْنِي فِي الذَّهَبِ – حَتَّى يَكُونَ لَكَ عِشْرُونَ دِينَارًا “ፊጥር” فِطْر ማለት “ፆም መግደፊያ” ማለት ሲሆን የፊጥር ብዙ ቁጥር ደግሞ “ፉጡር” فُطُور ነው፥ የረመዷን ፆም ማብቂያ በዓል እራሱ “ዒዱል ፊጥር” عِيدُ ٱلْفِطْر ይባላል። “ዘካቱል ፊጥር” زَكَاة الفِطْر ደግሞ ለመሣኪን በዒዱል ፊጥር ቀን ለማስፈጠሪያነት የሚውል ገንዘብ ነው፥ “መሣኪን” مَسَاكِين ማለት የዕለት ጉርስ የዓመት ልብስ የሌላቸው “ነዳያን” ማለት ነው። “ለግው” لَّغْو ማለት “ውድቅ ንግግር” ማለት ሲሆን “ረፈስ” رَّفَث ማለት ደግሞ “ስሜት ቀስቃሽ ንግግር” ማለት ነው፥ ዘካቱል ፊጥር ለፆመኛ ውድቅ ንግግር እና ስሜት ቀስቃሽ ንግግር ማፅጃ እንዲሁ ለመሣኪን መብል ነው፦ ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 45 ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” ዘካቱል ፊጥርን ለፆመኛ ለግው እና ረፈስ ማፅጃ እንዲሁ ለመሣኪን መብል እንዲሆን ግዴታ አድርገዋል”። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ فَرَضَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ زَكَاةَ الْفِطْرِ طُهْرَةً لِلصَّائِمِ مِنَ اللَّغْوِ وَالرَّفَثِ وَطُعْمَةً لِلْمَسَاكِينِ .‏ “ግዴታ አድርገዋል” ለሚለው የገባው የግስ መደብ “ፈረዶ” فَرَضَ መሆኑ በራሱ ዘካቱል ፊጥር ፈርድ መሆኑ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፥ “ፈርድ” فَرْض የሚለው ቃል እራሱ “ፈረዶ” فَرَضَ ማለትም “ግዴታ አደረገ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ግዴታ” ማለት ነው። ዘካቱል ማል ከቤት ለተባረሩ ሠለምቴዎች መቋቋሚያ መስጠት ከፈለጋችሁ እና ዘካቱል ፊጥር ለመሣኪን ሠለምቴዎች መስጠት ከፈለጋችሁ ከዚህ በታች ያሉትን አድሚናት አናግሩ፦ ወንድም አቡ ኑዓይም፦https://t.me/arhmanu እኅት ሰላም፦ http://t.me/SeuweSe አኅት ዘሃራ፦ https://t.me/Zhara_mustefa ወጀዛኩሙላህ ኸይራ! ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Show all...
የሥላሴ እሳቤ 2ኛ ዕትም የምትፈልጉ ልጆች አዲስ አበባ አየርጤና በ 0920781016 አዳማና አካባቢው @arhmanu ደሴ :– ሸርፍ ተራ አህመድ ኪታብ ቤት አረብ ገንዳ ሸህ አብዱ መክተባ ሸርፍ ተራ ፋጡማ መክተባ
Show all...
ወደ ዲኑል ኢሥላም ስንመጣ "ዐቅመ ጋብቻ" ማለት አንድ ተባእት ለዐቅመ አደም ሲደርስ እና አንዲት እንስት ለዐቅመ ሐዋህ ስትደርስ ማለት ነው። ለምሳሌ፦ የቲሞች እራሳቸው ይችሉ ወይም አይችሉ እንደሆነ ይፈተናሉ፥ ይህም ፈተና ለጋብቻ እስከሚደርሱበት ድረስ ነው፦ 4፥6 የቲሞችንም ጋብቻን እስከደረሱ ጊዜ ድረስ ፈትኑዋቸው፡፡ وَابْتَلُوا الْيَتَامَىٰ حَتَّىٰ إِذَا بَلَغُوا النِّكَاحَ "ኢዛ"  إِذَا ማለት "ጊዜ" ማለት ሲሆን የጊዜ ተውሳከ ግሥ ሲሆን ጋብቻ የራሱ የሆነ ጊዜ እንዳለው አመላካች ነው፥ ይህም ጊዜ ለማመልከት "ጋብቻን እስከደረሱ" ድረስ በማለት ይናገራል። እዚህ አንቀጽ ላይ  "ጋብቻን እስከደረሱ" ለሚለው የገባው ቃል "በለጉ" بَلَغُوا ሲሆን "ለጋብቻ በሰሉ" ማለት ነው፥ "በለገ" بَلَغَ ማለት እራሱ "ለጋብቻ በሰለ" ማለት ሲሆን "በለገት" بَلَغَت ማለት ደግሞ "ለጋብቻ በሰለች" ማለት ነው። "ባሊግ" بَٰلِغ ማለት እራሱ "ዐቅመ ጋብቻ"Puberty" ማለት ነው፦ ተፍሢሩል ኢብኑ ከሲር 4፥6 "ጋብቻን እስከደረሱ ጊዜ" የሚለውን ሙጃሂድ፦ "ለዐቅመ ጋብቻ ነው" ብሏል፥ ዐበይት ምሁራን፦ "ለዐቅመ ጋብቻ" ለጋዎች "ኢሕቲላም" ሲኖራቸው ነው" ብለዋል። አቢ ዳውድ በሡናው እንደዘገበው፥ ዐሊይ ኢብኑ አቢ ጧሊብ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ "ከዐቅመ ጋብቻ በኃላ የቲምነት የለም"። ( حتى إذا بلغوا النكاح ) قال مجاهد : يعني : الحلم . قال الجمهور من العلماء : البلوغ في الغلام تارة يكون بالحلم ، وهو أن يرى في منامه ما ينزل به الماء الدافق الذي يكون منه الولد . وقد روى أبو داود في سننه عن أمير المؤمنين علي بن أبي طالب ، رضي الله عنه ، قال : حفظت من رسول الله صلى الله عليه وسلم : " لا يتم بعد احتلام ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 18, ሐዲስ 12 ዐሊይ ኢብኑ አቢ ጧሊብ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ "ከዐቅመ ጋብቻ በኃላ የቲምነት የለም"።  قَالَ عَلِيُّ بْنُ أَبِي طَالِبٍ حَفِظْتُ عَنْ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ لاَ يُتْمَ بَعْدَ احْتِلاَمٍ "ዐቅመ ጋብቻ" አካል ተራክቦ ለማድረግ ሲበስል ነው፥ ከዐቅመ ጋብቻ በኃላ የቲምነት ስለሌለ የቲሞች እራሳቸው እንዲችሉ ይፈተናሉ። "ኢሕቲላም" احْتِلاَم ማለት አንድ ልጅ ወይም አንዲት ልጂት ተራክቦ ለማድረግ የሚኖራቸው ፈሳሽ ነው። አንድ ለጋ ሕጻን ለዐቅመ አደም ከደረሰ የሰው ቤት ዘው ብሎ አይገባም፥ ከዚያ ይልቅ አንኳክቶ ያስፈቅዳል፦ 24፥59 ከእናንተም ሕፃናቶቹ "ዐቅመ አዳምን" በደረሱ ጊዜ እነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩት እንዳስፈቀዱ ያስፈቅዱ፡፡ وَإِذَا بَلَغَ الْأَطْفَالُ مِنكُمُ الْحُلُمَ فَلْيَسْتَأْذِنُوا كَمَا اسْتَأْذَنَ الَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ አሁን እዚህ አንቀጽ ላይ "ኢዛ"  إِذَا የሚለው የጊዜ ተውሳከ ግሥ የዐቅመ ጋብቻ ጊዜ አመላካች ነው፥ ይህንን ዐቅመ ጋብቻ ለማመልከት "ዐቅመ አዳም" ለሚለው ቃል "በለገ" بَلَغَ  የሚል የግሥ መደብ ይጠቀማል። አንዲት እንስት ለዐቅመ ሐዋህ ደረሰች የሚባለው አካሏ ለተራክቦ ዝግጁ ሲሆን የመድረሷ የመጀመሪያው እና ዐቢይ ምልክት ደግሞ ጡቷ ሲያጎጠጉጥ እና ብብቷና ብልቷ አካባቢ ጸጉር መብቀል ሲጀምር ነው። ይህ የምታመነጨው ፈሳሽ "ኢሕቲላም" احْتِلاَم ሲባል ትርጉሙ "ከረቤዛዊ ፈሳሽ"Vaginal lubrication" ነው፥ ይህ ፈሳሽ ከጨቅላነት ወደ ዐቅመ ሐዋህ የምትሸጋገርበት አካላዊ ሽግግር"physical transition" ነው። ይህንን ታሳቢ እና ዋቢ በማድረግ እናታችን ዓኢሻህ"ረ.ዐ." ለነቢያችን"ﷺ" የተዳረችው በስድስት ዓመቷ ሲሆን ለዐቅመ ሐዋህ እስክትደርስ ድረስ ለሦስት ዓመት ከተጠበቀ በኃላ በዘጠኝ ዓመቷ ወደ ነቢያችን"ﷺ" ቤት ገብታለች፦ ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 16, ሐዲስ 82 ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ "ነቢዩ"ﷺ" ሲያገቡኝ የስድስት ዓመት እንስት ነበርኩኝ፥ የዘጠኝ ዓመት እንስት ስሆን ወደ ቤቱ ገባሁኝ"። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ تَزَوَّجَنِي النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم وَأَنَا بِنْتُ سِتِّ سِنِينَ وَبَنَى بِي وَأَنَا بِنْتُ تِسْعِ سِنِينَ ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 67, ሐዲስ 69 ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ "ነቢዩ"ﷺ" ሲያገቧ የስድስት ዓመት ነበረች፥ የዘጠኝ ዓመት እንስት ሲሆናት ደረሱባት"። عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم تَزَوَّجَهَا وَهْىَ بِنْتُ سِتِّ سِنِينَ በስድስት ዓመቷ ተድራ ሦስት ዓመት የመቆየቷ ጉዳይ ለዐቅመ ሐዋህ እስክትደርስ ድረስ ነው፥ "በስድስት ዓመቷ ተድራ በዘጠኝ ዓመቷ ለምን ተራከበች" ብለህ እርር እና ምርር የምትል ከሆነ እንግዲያውስ ይስሐቅ ርብቃን በሦስት ዓመቷ ማግባቱን እና በስድስት ዓመቷ ተራክቦ ማድረጉን ስትሰማ ልትንጨረጨር እና ልትንተከተክ ይገባካል። የምጣዱ እያለ የዕንቅቡ ተንጣጣ ይሉካል እንደዚህ ነው፥ ወይም ቅቤ አንጣሪዋ እያለች ጎመን ቀንጣሿ ምች መታት ይሉካል እንደዚህ ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Show all...
የርብቃ ጋብቻ በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። 4፥6 የቲሞችንም ጋብቻን እስከደረሱ ጊዜ ድረስ ፈትኑዋቸው፡፡ وَابْتَلُوا الْيَتَامَىٰ حَتَّىٰ إِذَا بَلَغُوا النِّكَاحَ እንደ ዘፍጥረት ዘገባ አብርሃም ልጁ ይስሐቅን ሊሠዋ እንደነበር ተዘግቧል። በዚያን ይስሐቅ የሠላሳ ስድስት ዓመት ልጅ እንደነበር በታርገም ዮናታን ተዘግቧል፦ ታርገም ዮናታን ዘፍጥረት 22፥1 ይስሐቅም እንዲህ ሲል መለሰ፦ "እነሆ፥ ዛሬ የሠላሳ ስድስት ዓመት ልጅ ነኝ"። ויען יצחק: "הנה אני בן שלושים ושש שנה היום". ምሁራን ይስሐቅ በሞርያ ተራራ ሠላሳ ስድስት ዓመት ከመንፈቅ ስላለፈ ሠላሳ ሰባት ዓመቱ እንደነበር ይዘግባሉ፦ ራሺ ዘፍጥረት 25፥20 "አብርሃም ከሞሪያ ተራራ በመጣ ጊዜ ርብቃ መወለዱን ሰምቷልና፥ በዚያ ጊዜ ይስሐቅ የሠላሳ ሰባት ዓመት ልጅ ነበር። ምክንያቱም በዚያን ጊዜ ሣራ ስለሞተች። שֶׁהֲרֵי כְּשֶׁבָּא אַבְרָהָם מֵהַר הַמּוֹרִיָּה נִתְבַּשֵּׂר שֶׁנּוֹלְדָה רִבְקָה, וְיִצְחָק הָיָה בֶּן ל"ז שָׁנָה, שֶׁהֲרֵי בּוֹ בַּפֶּרֶק מֵתָה שָׂרָה, וּמִשֶּׁנּוֹלַד יִצְחָק עַד הָעֲקֵדָה שֶׁמֵּתָה שָׂרָה, ל"ז שָׁנָה הָיוּ "ይህም ከሆነ በኋላ" ማለትም "ይስሐቅ ሊሠዋ ከሆነ በኃላ" ለአብርሃም ሚልካ ለወንድሙ ለናኮር ልጆችን ወለደች፦ ዘፍጥረት 22፥20 ይህም ከሆነ በኋላ ለአብርሃም እንዲህ ተብሎ ተነገረ፦ “እነሆ፥ ሚልካ ደግሞ ለወንድምህ ለናኮር ልጆችን ወለደች። ሚልካ የናኮር ሚስት ስትሆን የአብርሃም ወንድም ናኮር ዑፅ፣ ቡዝ፣ ቀሙኤል፣ ኮዛት፥ ሐዞ፣ ፊልዳሥ፣ የድላፍ፣ እና ባቱኤል የሚባሉ ስምንት ልጆችን ወለደች፦ ዘፍጥረት 22፥21-22 እነርሱም በኵሩ ዑፅ፥ ወንድሙ ቡዝ፥ የአራም አባት ቀሙኤል፥ ኮዛት፥ ሐዞ፥ ፊልዳሥ፥ የድላፍ፥ ባቱኤል ናቸው። ባቱኤል የናኮር የመጨረሻ ልጅ ሲሆን ባቱኤል ርብቃን ወለደ፦ ዘፍጥረት 22፥23 ባቱኤልም ርብቃን ወለደ። በትንሹ ይስሐቅ ርብቃን በሠላሳ ሰባት ዓመት ይበልጣታል፥ ይስሐቅ አርባ ዓመት ሲሆነው ርብቃን አገባ፦ ዘፍጥረት 25፥20 ይስሐቅም አርባ ዓመት ሲሆነው ርብቃን አገባ። ይስሐቅ ርብቃን ሲያገባት የሦስትት ዓመት ልጅ ነበረች፥ ምክንያቱም 40-37=7 ይሆናልና። ከጋብቻ በኃላ ይስሐቅ ከርብቃ ጋር በተራክቦ ለመራከብ የነበረው የጊዜ ክፍተት ሦስት ዓመት እንደነበር በራሺ ዘፍጥረት ላይ እንዲህ ተዘግቧል፦ ራሺ ዘፍጥረት 25፥20 "ለጋብቻ ብቁ እስክትሆን ድረስ ሦስት ዓመት ጠበቀ፥ ከዚያም ደረሰባት። הִמְתִּין לָהּ עַד שֶׁתְּהֵא רְאוּיָה לְבִיאָה ג' שָׁנִים וּנְשָׂאָהּ: ስለዚህ የሦስት ዓመት ልጅ ለአርባ ዓመት ሰው መዳር በጥንት ጊዜ የተለመደ ጉዳይ መሆኑ ይህ ታሪክ ጉልኅ ማሳያ ነው። እንደ ታሪኩማ ይስሐቅ በተራክቦ ሲራከባት ርብቃ መካን ነበረችና ይስሐቅም ስለሚስቱ ወደ አምላክ ጸለየ፥ አምላክም ስለተለመነው ርብቃም ሚስቱ ፀነሰች፦ ዘፍጥረት 25፥21 ይስሐቅም ስለሚስቱ ወደ ያህዌህ ጸለየ፥ መካን ነበረችና ያህዌህም ተለመነው፥ ርብቃም ሚስቱ ፀነሰች።
Show all...
ይህንን ታሳቢ እና ዋቢ በማድረግ እናታችን ዓኢሻህ"ረ.ዐ." ለነቢያችን"ﷺ" የተዳረችው በስድስት ዓመቷ ሲሆን ለዐቅመ ሐዋህ እስክትደርስ ድረስ ለሦስት ዓመት ከተጠበቀ በኃላ በዘጠኝ ዓመቷ ወደ ነቢያችን"ﷺ" ቤት ገብታለች፦ ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 16, ሐዲስ 82 ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ "ነቢዩ"ﷺ" ሲያገቡኝ የስድስት ዓመት እንስት ነበርኩኝ፥ የዘጠኝ ዓመት እንስት ስሆን ወደ ቤቱ ገባሁኝ"። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ تَزَوَّجَنِي النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم وَأَنَا بِنْتُ سِتِّ سِنِينَ وَبَنَى بِي وَأَنَا بِنْتُ تِسْعِ سِنِينَ ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 67, ሐዲስ 69 ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ "ነቢዩ"ﷺ" ሲያገቧ የስድስት ዓመት ነበረች፥ የዘጠኝ ዓመት እንስት ሲሆናት ደረሱባት"። عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم تَزَوَّجَهَا وَهْىَ بِنْتُ سِتِّ سِنِينَ በስድስት ዓመቷ ተድራ ሦስት ዓመት የመቆየቷ ጉዳይ ለዐቅመ ሐዋህ እስክትደርስ ድረስ ነው፥ "በስድስት ዓመቷ ተድራ በዘጠኝ ዓመቷ ለምን ተራከበች" ብለህ እርር እና ምርር የምትል ከሆነ እንግዲያውስ ይስሐቅ ርብቃን በሦስት ዓመቷ ማግባቱን እና በስድስት ዓመቷ ተራክቦ ማድረጉን ስትሰማ ልትንጨረጨር እና ልትንተከተክ ይገባካል። የምጣዱ እያለ የዕንቅቡ ተንጣጣ ይሉካል እንደዚህ ነው፥ ወይም ቅቤ አንጣሪዋ እያለች ጎመን ቀንጣሿ ምች መታት ይሉካል እንደዚህ ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Show all...
የርብቃ ጋብቻ በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። 4፥6 የቲሞችንም ጋብቻን እስከደረሱ ጊዜ ድረስ ፈትኑዋቸው፡፡ وَابْتَلُوا الْيَتَامَىٰ حَتَّىٰ إِذَا بَلَغُوا النِّكَاحَ እንደ ዘፍጥረት ዘገባ አብርሃም ልጁ ይስሐቅን ሊሠዋ እንደነበር ተዘግቧል። በዚያን ይስሐቅ የሠላሳ ስድስት ዓመት ልጅ እንደነበር በታርገም ዮናታን ተዘግቧል፦ ታርገም ዮናታን ዘፍጥረት 22፥1 ይስሐቅም እንዲህ ሲል መለሰ፦ "እነሆ፥ ዛሬ የሠላሳ ስድስት ዓመት ልጅ ነኝ"። ויען יצחק: "הנה אני בן שלושים ושש שנה היום". ምሁራን ይስሐቅ በሞርያ ተራራ ሠላሳ ስድስት ዓመት ከመንፈቅ ስላለፈ ሠላሳ ሰባት ዓመቱ እንደነበር ይዘግባሉ፦ ራሺ ዘፍጥረት 25፥20 "አብርሃም ከሞሪያ ተራራ በመጣ ጊዜ ርብቃ መወለዱን ሰምቷልና፥ በዚያ ጊዜ ይስሐቅ የሠላሳ ሰባት ዓመት ልጅ ነበር። ምክንያቱም በዚያን ጊዜ ሣራ ስለሞተች። שֶׁהֲרֵי כְּשֶׁבָּא אַבְרָהָם מֵהַר הַמּוֹרִיָּה נִתְבַּשֵּׂר שֶׁנּוֹלְדָה רִבְקָה, וְיִצְחָק הָיָה בֶּן ל"ז שָׁנָה, שֶׁהֲרֵי בּוֹ בַּפֶּרֶק מֵתָה שָׂרָה, וּמִשֶּׁנּוֹלַד יִצְחָק עַד הָעֲקֵדָה שֶׁמֵּתָה שָׂרָה, ל"ז שָׁנָה הָיוּ "ይህም ከሆነ በኋላ" ማለትም "ይስሐቅ ሊሠዋ ከሆነ በኃላ" ለአብርሃም ሚልካ ለወንድሙ ለናኮር ልጆችን ወለደች፦ ዘፍጥረት 22፥20 ይህም ከሆነ በኋላ ለአብርሃም እንዲህ ተብሎ ተነገረ፦ “እነሆ፥ ሚልካ ደግሞ ለወንድምህ ለናኮር ልጆችን ወለደች። ሚልካ የናኮር ሚስት ስትሆን የአብርሃም ወንድም ናኮር ዑፅ፣ ቡዝ፣ ቀሙኤል፣ ኮዛት፥ ሐዞ፣ ፊልዳሥ፣ የድላፍ፣ እና ባቱኤል የሚባሉ ስምንት ልጆችን ወለደች፦ ዘፍጥረት 22፥21-22 እነርሱም በኵሩ ዑፅ፥ ወንድሙ ቡዝ፥ የአራም አባት ቀሙኤል፥ ኮዛት፥ ሐዞ፥ ፊልዳሥ፥ የድላፍ፥ ባቱኤል ናቸው። ባቱኤል የናኮር የመጨረሻ ልጅ ሲሆን ባቱኤል ርብቃን ወለደ፦ ዘፍጥረት 22፥23 ባቱኤልም ርብቃን ወለደ። በትንሹ ይስሐቅ ርብቃን በሠላሳ ሰባት ዓመት ይበልጣታል፥ ይስሐቅ አርባ ዓመት ሲሆነው ርብቃን አገባ፦ ዘፍጥረት 25፥20 ይስሐቅም አርባ ዓመት ሲሆነው ርብቃን አገባ። ይስሐቅ ርብቃን ሲያገባት የሦስትት ዓመት ልጅ ነበረች፥ ምክንያቱም 40-37=7 ይሆናልና። ከጋብቻ በኃላ ይስሐቅ ከርብቃ ጋር በተራክቦ ለመራከብ የነበረው የጊዜ ክፍተት ሦስት ዓመት እንደነበር በራሺ ዘፍጥረት ላይ እንዲህ ተዘግቧል፦ ራሺ ዘፍጥረት 25፥20 "ለጋብቻ ብቁ እስክትሆን ድረስ ሦስት ዓመት ጠበቀ፥ ከዚያም ደረሰባት። הִמְתִּין לָהּ עַד שֶׁתְּהֵא רְאוּיָה לְבִיאָה ג' שָׁנִים וּנְשָׂאָהּ: ስለዚህ የሦስት ዓመት ልጅ ለአርባ ዓመት ሰው መዳር በጥንት ጊዜ የተለመደ ጉዳይ መሆኑ ይህ ታሪክ ጉልኅ ማሳያ ነው። እንደ ታሪኩማ ይስሐቅ በተራክቦ ሲራከባት ርብቃ መካን ነበረችና ይስሐቅም ስለሚስቱ ወደ አምላክ ጸለየ፥ አምላክም ስለተለመነው ርብቃም ሚስቱ ፀነሰች፦ ዘፍጥረት 25፥21 ይስሐቅም ስለሚስቱ ወደ ያህዌህ ጸለየ፥ መካን ነበረችና ያህዌህም ተለመነው፥ ርብቃም ሚስቱ ፀነሰች። ወደ ዲኑል ኢሥላም ስንመጣ "ዐቅመ ጋብቻ" ማለት አንድ ተባእት ለዐቅመ አደም ሲደርስ እና አንዲት እንስት ለዐቅመ ሐዋህ ስትደርስ ማለት ነው። ለምሳሌ፦ የቲሞች እራሳቸው ይችሉ ወይም አይችሉ እንደሆነ ይፈተናሉ፥ ይህም ፈተና ለጋብቻ እስከሚደርሱበት ድረስ ነው፦ 4፥6 የቲሞችንም ጋብቻን እስከደረሱ ጊዜ ድረስ ፈትኑዋቸው፡፡ وَابْتَلُوا الْيَتَامَىٰ حَتَّىٰ إِذَا بَلَغُوا النِّكَاحَ "ኢዛ" إِذَا ማለት "ጊዜ" ማለት ሲሆን የጊዜ ተውሳከ ግሥ ሲሆን ጋብቻ የራሱ የሆነ ጊዜ እንዳለው አመላካች ነው፥ ይህም ጊዜ ለማመልከት "ጋብቻን እስከደረሱ" ድረስ በማለት ይናገራል። እዚህ አንቀጽ ላይ "ጋብቻን እስከደረሱ" ለሚለው የገባው ቃል "በለጉ" بَلَغُوا ሲሆን "ለጋብቻ በሰሉ" ማለት ነው፥ "በለገ" بَلَغَ ማለት እራሱ "ለጋብቻ በሰለ" ማለት ሲሆን "በለገት" بَلَغَت ማለት ደግሞ "ለጋብቻ በሰለች" ማለት ነው። "ባሊግ" بَٰلِغ ማለት እራሱ "ዐቅመ ጋብቻ"Puberty" ማለት ነው፦ ተፍሢሩል ኢብኑ ከሲር 4፥6 "ጋብቻን እስከደረሱ ጊዜ" የሚለውን ሙጃሂድ፦ "ለዐቅመ ጋብቻ ነው" ብሏል፥ ዐበይት ምሁራን፦ "ለዐቅመ ጋብቻ" ለጋዎች "ኢሕቲላም" ሲኖራቸው ነው" ብለዋል። አቢ ዳውድ በሡናው እንደዘገበው፥ ዐሊይ ኢብኑ አቢ ጧሊብ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ "ከዐቅመ ጋብቻ በኃላ የቲምነት የለም"። ( حتى إذا بلغوا النكاح ) قال مجاهد : يعني : الحلم . قال الجمهور من العلماء : البلوغ في الغلام تارة يكون بالحلم ، وهو أن يرى في منامه ما ينزل به الماء الدافق الذي يكون منه الولد . وقد روى أبو داود في سننه عن أمير المؤمنين علي بن أبي طالب ، رضي الله عنه ، قال : حفظت من رسول الله صلى الله عليه وسلم : " لا يتم بعد احتلام ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 18, ሐዲስ 12 ዐሊይ ኢብኑ አቢ ጧሊብ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ "ከዐቅመ ጋብቻ በኃላ የቲምነት የለም"። قَالَ عَلِيُّ بْنُ أَبِي طَالِبٍ حَفِظْتُ عَنْ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ لاَ يُتْمَ بَعْدَ احْتِلاَمٍ "ዐቅመ ጋብቻ" አካል ተራክቦ ለማድረግ ሲበስል ነው፥ ከዐቅመ ጋብቻ በኃላ የቲምነት ስለሌለ የቲሞች እራሳቸው እንዲችሉ ይፈተናሉ። "ኢሕቲላም" احْتِلاَم ማለት አንድ ልጅ ወይም አንዲት ልጂት ተራክቦ ለማድረግ የሚኖራቸው ፈሳሽ ነው። አንድ ለጋ ሕጻን ለዐቅመ አደም ከደረሰ የሰው ቤት ዘው ብሎ አይገባም፥ ከዚያ ይልቅ አንኳክቶ ያስፈቅዳል፦ 24፥59 ከእናንተም ሕፃናቶቹ "ዐቅመ አዳምን" በደረሱ ጊዜ እነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩት እንዳስፈቀዱ ያስፈቅዱ፡፡ وَإِذَا بَلَغَ الْأَطْفَالُ مِنكُمُ الْحُلُمَ فَلْيَسْتَأْذِنُوا كَمَا اسْتَأْذَنَ الَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ አሁን እዚህ አንቀጽ ላይ "ኢዛ" إِذَا የሚለው የጊዜ ተውሳከ ግሥ የዐቅመ ጋብቻ ጊዜ አመላካች ነው፥ ይህንን ዐቅመ ጋብቻ ለማመልከት "ዐቅመ አዳም" ለሚለው ቃል "በለገ" بَلَغَ የሚል የግሥ መደብ ይጠቀማል። አንዲት እንስት ለዐቅመ ሐዋህ ደረሰች የሚባለው አካሏ ለተራክቦ ዝግጁ ሲሆን የመድረሷ የመጀመሪያው እና ዐቢይ ምልክት ደግሞ ጡቷ ሲያጎጠጉጥ እና ብብቷና ብልቷ አካባቢ ጸጉር መብቀል ሲጀምር ነው። ይህ የምታመነጨው ፈሳሽ "ኢሕቲላም" احْتِلاَم ሲባል ትርጉሙ "ከረቤዛዊ ፈሳሽ"Vaginal lubrication" ነው፥ ይህ ፈሳሽ ከጨቅላነት ወደ ዐቅመ ሐዋህ የምትሸጋገርበት አካላዊ ሽግግር"physical transition" ነው።
Show all...
ይህቺ ሴት በሮም ቫቲካን አላውያን ነገሥታት ላይ የነገሠች ኩላዊት ታላቂቱ ቤተክርስቲያን ነች፥ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ፣ ታላቁ እና ፊተኛው ቴዎዶስዮስ፣ ደኃራይ ቴዎዶስዮስ፣ መርቅያኖስ የመሳሰሉት ነገሥታት ከሴትይዋ ጋር በጉባኤያት ሲሴስኑ እና ከዝሙትዋ ወይን ጠጅ ሲሰክሩ በታሪክ ታይተዋል፦ ራእይ 17፥18 ያየሃትም ሴት በምድር ነገሥታት ላይ የምትነግሥ ታላቂቱ ከተማ ናት። ራእይ 17፥2 የምድርም ነገሥታት ከእርስዋ ጋር ሴሰኑ በምድርም የሚኖሩ ከዝሙትዋ ወይን ጠጅ ሰከሩ” ብሎ ተናገረኝ። ራእይ ዐውድ ላይ "ዝሙት" "መሴሰን" "መጎልሞት" ምሳሌአዊ ሲሆን ከታጨላት ዓላማ እና ዒላማ መውጣትን ለማመልከት የገባ ፍካሬአዊ አገላለጽ ነው። የሚያሳዝነው ግን ይህቺ ሴት መጨረሻዋ ስለማያምር ተመልሶ የሚያንሰራራው አውሬ የሮም መንግሥት እና እርሱ ሲያንሰራራ የሚነግሡት የቀዩ አውሬ አሥሩ ቀንዶች ነገሥታት ይህቺን ሴት ያጠፏታል፦ ራእይ 17፥12 ያየሃቸውም አሥሩ ቀንዶች ገና መንግሥትን ያልተቀበሉ አሥር ነገሥታት ናቸው። ራእይ 17፥16 ያየኃቸውም አሥር ቀንዶች እና አውሬው ጋለሞታይቱን ይጣላሉ፥ ባዶዋን እና ራቁትዋንም ያደርጓታል። ሥጋዋንም ይበላሉ፥ በእሳትም ያቃጥሉአታል። ከዚያ በተቃራኒው የመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረችው የሐዋርያት ስብስብ አሥራ ሁለቱ ሐዋርያት መሠረት የሆኑላት አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ናት፦ ገላትያ 4፥26 ላይኛይቱ ኢየሩሳሌም ግን በነጻነት የምትኖር ናት እርስዋም እናታችን ናት። ራእይ 21፥14 ለከተማይቱም ቅጥር አሥራ ሁለት መሠረቶች ነበሩአት፥ በእነርሱም ውስጥ የአሥራ ሁለቱ የበጉ ሐዋርያት ስሞች ተጽፈው ነበር። "የሩሻሌም" יְרוּשָׁלַם ማለት "የሠላም መሠረት" ማለት ነው፥ የአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ስብስብ እውነተኛ ስብስብ ነበር። ይህቺ መሠረት ያላት ከተማ አሁን ላይ ምድር ላይ የምትኖር ሳይሆን ኢየሱስ ሲመጣ በአምላክ ሕግ የምትመሠረት የመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን ሞዴት ናት፥ ራእይ 21፥2 ዕብራውያን 11፥10 ዕብራውያን 13፥14 ተመልከት! አምላካችን አሏህ ስለ ሐዋርያት እንዲህ ይለናል፦ 5፥111 ወደ ሐዋርያትም «በእኔ እና በመልእክተኛዬ እመኑ» በማለት ባዘዝኩ ጊዜ አስታውስ፡፡ وَإِذْ أَوْحَيْتُ إِلَى الْحَوَارِيِّينَ أَنْ آمِنُوا بِي وَبِرَسُولِي አሏህ ለዒሣ በሰጠው ወሕይ በኢንጂል ለሐዋርያት፦ "በእኔ እና በመልእክተኛዬ እመኑ" ብሎ ሲያዛቸው እነርሱም፦ «አመንን፥ እኛ ሙሥሊሞች መኾናችንን መስክር» አሉ፦ 5፥111 «አመንን፥ እኛ ሙሥሊሞች መኾናችንን መስክር» አሉ፡፡ قَالُوا آمَنَّا وَاشْهَدْ بِأَنَّنَا مُسْلِمُونَ አንዱን አምላክ በብቸኝነት ታዛዥ፣ ተገዢ፣ አምላኪ ደግሞ በነጠላ "ሙሥሊም" مُسْلِم በብዜት "ሙሥሊሚን" مُسْلِمِين ወይም "ሙሥሊሙን" مُسْلِمُون ይባላል። ከሐዋርያት በኃላ የመጡት ከቀጥተኛ መንገድ የተሳሳቱ ሲሆን ያልተሳሳቱት ሐዋርያት የሄዱበትን ቀጥተኛውን መንገድ እስከ መጨረሻው እንዲመራን በሶላት ላይ ስንቆም "ያልተሳሳቱትን ሰዎች መንገድ ምራን" በማለት እንቀራለን፦ 1፥7 የእነዚያን በነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን በነሱ ላይ ያልተቆጣህባቸውን እና ያልተሳሳቱትን ሰዎች መንገድ ምራን" በሉ፡፡ صِرَاطَ الَّذِينَ أَنْعَمْتَ عَلَيْهِمْ غَيْرِ الْمَغْضُوبِ عَلَيْهِمْ وَلَا الضَّالِّينَ አምላካችን አሏህ የዒሣ ሐዋርያት በሄዱበት በቀጥተኛው መንገድ ላይ ያጽናን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Show all...
ታላቂቱ ባቢሎን ክፍል ሁለት በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርኅሩኅ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። 5፥111 ወደ ሐዋርያትም «በእኔ እና በመልእክተኛዬ እመኑ» በማለት ባዘዝኩ ጊዜ አስታውስ፡፡ وَإِذْ أَوْحَيْتُ إِلَى الْحَوَارِيِّينَ أَنْ آمِنُوا بِي وَبِرَسُولِي "ኤክሌሲያ" ἐκκλησία ማለት "ጉባኤ" "ማኅበር" "ስብሰባ" ማለት ሲሆን በብሉይ ኪዳን ግሪክ ሰፕቱአጀንት እና በአዲስ ኪዳን ግሪክ ኮይኔ "ጉባኤ" "ማኅበር" "ስብሰባ" ለሚለው የገባው ቃል ነው፥ በተለምዶ "ቤተክርስቲያን"church" ይባል። ኢየሱስ ጴጥሮስን መሠረት በማድረግ የራሱን ስብስብ እንደሚሠራ ተናግሮ ነበር፦ ማቴዎስ 16፥18 እኔም እልሃለሁ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚህም ዓለት ላይ ኤክሌሲያዬን እሠራለሁ፥ የሲዖል ደጆችም አይችሉአትም። κἀγὼ δέ σοι λέγω ὅτι σὺ εἶ Πέτρος, καὶ ἐπὶ ταύτῃ τῇ πέτρᾳ οἰκοδομήσω μου τὴν ἐκκλησίαν, καὶ πύλαι Ἅιδου οὐ κατισχύσουσιν αὐτῆς. ይህ ስብስብ መቀመጫው ኢየሩሳሌም የነበረ ሲሆን በ 70 ድኅረ ልደት የሮማው ጄኔራል ጢጦስ ቤተመቅደሱን እና ኢየሩሳሌምን ሲያነዳት ተበተነ። ከዚያም ከ 180 እስከ 313 ድኅረ ልደት በዓለም ዐቀፍ ደረጃ "ኤክሌሲያ ሜጋሌ" ἐκκλησία μεγάλη "ኤክሌሲያ ማግና" "ታላቂቱ ቤተክርስቲያን"Great Church" ተብላ በሮም መንግሥት መቀመጫ ያደረገች ታላቂቱ ቤተክርስቲያን በአበው ተዋቅራ ተደራጀች፥ ይህቺ ሴት በሮም መንግሥት የተቀመጠችው ኩላዊት ቤተክርስቲያን ናት። ይህቺ ሴት በዚህ ጊዜ ውስጥ የሥላሴ እሳቤ፣ የተሠግዎት ትምህርት፣ ስለ ማርያም ስግደት እና እርገት፣ ወደ መላእክት እና ወደ ሙታን መጸለይ፣ ለመስቀል እና ለስዕል መስገድ፣ ምንኩስና እና ብህትውና የመሳሰሉት ትምህርት ስርዋጽ አርጋ ከግሪክ ወሮም ፍልስፍና ጋር ቀይጣለች። "ካቶሊኮስ" καθολικός ማለት "ዓለም ዐቀፍ" በግዕዝ "ኩላዊት" በሮማይስጥ "ካቶሊክ" ማለት ነው፥ ለመጀመሪያ ጊዜ ኤክሌሲያን "ካቶሊኮስ" ብሎ የጠራት የአንጾኪያው ኤጲስ ቆጶስ አግናጥዮስ በ 110 ድኅረ ልደት ነው፦ "ኤጲስ ቆጶሱ በሚገለጥበት ቦታ ሁሉ በዚያ ብዙኃኑ ይሁኑ! ኢየሱስ ባለበትም ቢሆን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን አለች"። Epistle to the Smyrnaeans (St. Ignatius) Chapter 8 የፈረንሳዩ ኤጲስ ቆጶስ ሔራንዮስ ደግሞ በ 180 ድኅረ ልደት ላይ፦ "እውነታው ያለው በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንጂ ሌላ በየትም አይደለም" ብሏል፦ "እውነታው ያለው በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንጂ ሌላ በየትም አይደለም"። Against Heresies(St. Irenaeus) Book III(3) Chapter 4 ይህቺ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የግሪክ እና የሮም ፍልስፍና የተጠናወታቸው የፈላስፎች ስብስብ ናት፥ ፈላስፋው ዮስጦስ ሰማዕቱ፣ ፈላስፋው አርጌንስ፣ ፈላስፋው ጠርጡሊያኖስ፣ ፈላስፋው ቀሌሜንጦስ ዘእስክንድርያ፣ ፈላስፋው አውግስጢኖስ ወዘተ አደራጅተው ያዋቀሯት ስብስብ ናት። የእስክንድርያው የትርጓሜ ትምህርት ቤት በአፍላጦን ፍልስፍና ሰርጎገብ መሠረት ማድረጉ እንዲሁ የአንጾኪያው ትምህርት ቤት ደግሞ በአሪስጣጣሊስ ፍልስፍና ሰርጎገብ ማድረጉ ጉልኅ ማሳያ ነው። ፨ ይህቺ ሴት በ325 ድኅረ ልደት በንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ሊቀ መንበርነት ኩላዊት የኒቂያ ጉባኤ ላይ 318 ኤጲጵ ቆጶሳት ከመላው ዓለም በመሰብሰብ "የሮሙ የጴጥሮስ በዓለ መንበር ሐዋርያት እንዳዘዙ አለቃም ፈራጅም ይሁን" በማለት ወሰነች፦ ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 4 ቁጥር 40 "ሊቃነ ጳጳሳት በዓለም ሁሉ አራት ብቻ እንዲሆኑ በኒቂያ የተሰበሰቡት የቅዱሳን ማኅበር አዘዙ። ከእነርሱም የሮሙ የጴጥሮስ በዓለ መንበር ሐዋርያት እንዳዘዙ አለቃም ፈራጅም ይሁን"። ኩላዊት የክርስትና ቤተ ክርስቲያን የምትመራው በሮማ ግዛት በአምስት ኤጲስ ቆጶሳዊ ፓትሪያሪኮች"Pentarchy" ነው፥ እነርሱም የሮሙ የጴጥሮስ መንበር፣ የቁስጥንጥንያው የእንድርያስ መንበር፣ የእስክንድርያው የማርቆስ መንበር፣ የአንጾኪያው የጴጥሮስ መንበር እና የኢየሩሳሌሙ የያዕቆብ መንበር ናቸው። ይህቺ የኒቂያ ጉባኤ ፓትሪያሪኩን "ካቶሊኮስ በሚባል ታላቅ ስም ያክብሩት" በማለት ተናግራለች፥ በተጨማሪም ኤጲስ ቆጶስ "የጸጋ አምላካችሁም ነውና" ተብሏል፦ ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 4 ቁጥር 43 "ካቶሊኮስ በሚባል ታላቅ ስም ያክብሩት" ዲድስቅልያ 8፥6 ከእውነተኛው አምላክ በታችም በምድር ላይ አለቃችሁ ፣ መምህራችሁና ኃይላችሁ "የጸጋ አምላካችሁም ነውና"። ፨ ይህቺ ሴት በ 381 ድኅረ ልደት በሮሙ ንጉሥ በታላቁ እና ፊተኛው ቴዎዶስዮስ ሊቀ መንበርነት የተዘጋጀው የቆስጠንጥኒያ ኩላዊ ጉባኤ በ150 ኤጲስ ቆጶሳት በመሰብሰብ "በአንዲት፣ ቅድስት፣ "ካቶሊካዊት" እና ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን"we believe in one, holy, Catholic and Apostolic Church" ብላለች። ፨ ይህቺ ሴት 431 ድኅረ ልደት በንጉሥ ደኃራይ ቴዎዶስዮስ ሊቀ መንበርነት የኤፌሶን ኩላዊ ጉባኤ ላይ 200 ኤጲጵ ቆጶሳት ከመላው ዓለም በመሰብሰብ የአንጾኪያን መንበርን ከንስጥሮሳውያን ጋር አውግዛለች። ፨ ይህቺ ሴት 451 ድኅረ ልደት በንጉሥ መርቅያኖስ ሊቀ መንበርነት የኬልቄዶን ኩላዊ ጉባኤ ላይ 130 ኤጲጵ ቆጶሳት ከመላው ዓለም በመሰብሰብ የእስክንድርያውን መንበር ከጽብሓውያን ቤተክርስቲያን"oriental church" ጋር አውግዛለች። ፨ ይህቺ ሴት በመቀጠል በ 1954 ድኅረ ልደት የቁስጥንጥንያን መንበር ከምሥራቃውያን ቤተክርስቲያን"eastern church" ጋር አውግዛለች። ፨ ይህቺ ሴት በስተመጨረሻም የፕሮቴስታንትን ሐዳሲያንን የሚባሉትን ሉተራውያንን፣ ዝውንግሊያውያንን፣ ካልቪናውያንን ወዘተ አውግዛለች። በእርግጥም ይህቺ ሴት በቀዩ አውሬ በሮም መንግሥት ላይ የተቀመጠች ጋለሞታይቷ ሴት ናት፦ 1ኛ ጴጥሮስ 5፥13 ከእናንተ ጋር ተመርጣ "በባቢሎን ያለች ቤተ ክርስቲያን" ልጄም ማርቆስ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። "ባቢሎን" ደግሞ የሮም ምሥጢራዊ ስም እንደሆነ የቂሳሪያው አውሳቢዮስ ይህንን አንቀጽ ታሳቢ እና ዋቢ አርጎ ተናግሯል፦ "ጴጥሮስም በመጀመሪያው መልእክቱ ውስጥ ስለ ማርቆስ ሲያነሳ እንዳመለከተው ከተማይቱን በምሳሌ "ባቢሎን" ብሎ ሲጠራ እርሱ ራሱ በሮም እንደ ጻፈው ይናገራሉ"። Church History (Eusebius) > Book II(2) Chapter 15 Number 2 ዛሬ በዓለም ላይ ከተለያየ ብሔር፣ ቋንቋ፣ ዘውግ ከ 1.3 ቢሊዮን ምእመናን ያቀፈው አባላት ያላት እና ሮም መቀመጫ ያረገች የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ነች። የካቶሊክ ቤተክርስቲያን እነዚህን ከመስመር የወጡ ትምህርታት የሚያርማትን ግለሰብ ሆነ ቡድን "ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ፣ ሐዋርያዊ መተካካት የያዘውን የጴጥሮስን መንበር እና የመፍታትና የማሰር ቁልፍ ተቀብያለው" በማለት "መ-ናፍቅ" እያለች በግዝት እና በግዞት ስታሰቃይ ነበር፥ በታሪክ ውስጥ ይህቺ ተቋም ሲያሰኛት በጉልበት፣ በበባርነት እና በቅኝ ግዛት ሰዎች ክርስትናን እንዲቀበሉ አርጋለች። ይህቺ ቤተክርስቲያን ባይብልን ወደ ሌላ ቋንቋ የተረጎሙ ሰዎች በመስቀል አቃጥላለች፥ ቤተክርስቲያን ዓለምን ለመውረር እና ዲኑል ኢሥላምን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት የመስቀል ጦርነት በመስቀለኞች ዘጠኝ ጊዜ አርጋለች።
Show all...
ይህቺ ሴት በሮም ቫቲካን አላውያን ነገሥታት ላይ የነገሠች ኩላዊት ታላቂቱ ቤተክርስቲያን ነች፥ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ፣ ታላቁ እና ፊተኛው ቴዎዶስዮስ፣ ደኃራይ ቴዎዶስዮስ፣ መርቅያኖስ የመሳሰሉት ነገሥታት ከሴትይዋ ጋር በጉባኤያት ሲሴስኑ እና ከዝሙትዋ ወይን ጠጅ ሲሰክሩ በታሪክ ታይተዋል፦ ራእይ 17፥18 ያየሃትም ሴት በምድር ነገሥታት ላይ የምትነግሥ ታላቂቱ ከተማ ናት። ራእይ 17፥2 የምድርም ነገሥታት ከእርስዋ ጋር ሴሰኑ በምድርም የሚኖሩ ከዝሙትዋ ወይን ጠጅ ሰከሩ” ብሎ ተናገረኝ። ራእይ ዐውድ ላይ "ዝሙት" "መሴሰን" "መጎልሞት" ምሳሌአዊ ሲሆን ከታጨላት ዓላማ እና ዒላማ መውጣትን ለማመልከት የገባ ፍካሬአዊ አገላለጽ ነው። የሚያሳዝነው ግን ይህቺ ሴት መጨረሻዋ ስለማያምር ተመልሶ የሚያንሰራራው አውሬ የሮም መንግሥት እና እርሱ ሲያንሰራራ የሚነግሡት የቀዩ አውሬ አሥሩ ቀንዶች ነገሥታት ይህቺን ሴት ያጠፏታል፦ ራእይ 17፥12 ያየሃቸውም አሥሩ ቀንዶች ገና መንግሥትን ያልተቀበሉ አሥር ነገሥታት ናቸው። ራእይ 17፥16 ያየኃቸውም አሥር ቀንዶች እና አውሬው ጋለሞታይቱን ይጣላሉ፥ ባዶዋን እና ራቁትዋንም ያደርጓታል። ሥጋዋንም ይበላሉ፥ በእሳትም ያቃጥሉአታል። ከዚያ በተቃራኒው የመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረችው የሐዋርያት ስብስብ አሥራ ሁለቱ ሐዋርያት መሠረት የሆኑላት አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ናት፦ ገላትያ 4፥26 ላይኛይቱ ኢየሩሳሌም ግን በነጻነት የምትኖር ናት እርስዋም እናታችን ናት። ራእይ 21፥14 ለከተማይቱም ቅጥር አሥራ ሁለት መሠረቶች ነበሩአት፥ በእነርሱም ውስጥ የአሥራ ሁለቱ የበጉ ሐዋርያት ስሞች ተጽፈው ነበር። "የሩሻሌም" יְרוּשָׁלַם ማለት "የሠላም መሠረት" ማለት ነው፥ የአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ስብስብ እውነተኛ ስብስብ ነበር። ይህቺ መሠረት ያላት ከተማ አሁን ላይ ምድር ላይ የምትኖር ሳይሆን ኢየሱስ ሲመጣ በአምላክ ሕግ የምትመሠረት የመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን ሞዴት ናት፥ ራእይ 21፥2 ዕብራውያን 11፥10 ዕብራውያን 13፥14 ተመልከት! አምላካችን አሏህ ስለ ሐዋርያት እንዲህ ይለናል፦ 5፥111 ወደ ሐዋርያትም «በእኔ እና በመልእክተኛዬ እመኑ» በማለት ባዘዝኩ ጊዜ አስታውስ፡፡ وَإِذْ أَوْحَيْتُ إِلَى الْحَوَارِيِّينَ أَنْ آمِنُوا بِي وَبِرَسُولِي አሏህ ለዒሣ በሰጠው ወሕይ በኢንጂል ለሐዋርያት፦ "በእኔ እና በመልእክተኛዬ እመኑ" ብሎ ሲያዛቸው እነርሱም፦ «አመንን፥ እኛ ሙሥሊሞች መኾናችንን መስክር» አሉ፦ 5፥111 «አመንን፥ እኛ ሙሥሊሞች መኾናችንን መስክር» አሉ፡፡ قَالُوا آمَنَّا وَاشْهَدْ بِأَنَّنَا مُسْلِمُونَ አንዱን አምላክ በብቸኝነት ታዛዥ፣ ተገዢ፣ አምላኪ ደግሞ በነጠላ "ሙሥሊም" مُسْلِم በብዜት "ሙሥሊሚን" مُسْلِمِين ወይም "ሙሥሊሙን" مُسْلِمُون ይባላል። ከሐዋርያት በኃላ የመጡት ከቀጥተኛ መንገድ የተሳሳቱ ሲሆን ያልተሳሳቱት ሐዋርያት የሄዱበትን ቀጥተኛውን መንገድ እስከ መጨረሻው እንዲመራን በሶላት ላይ ስንቆም "ያልተሳሳቱትን ሰዎች መንገድ ምራን" በማለት እንቀራለን፦ 1፥7 የእነዚያን በነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን በነሱ ላይ ያልተቆጣህባቸውን እና ያልተሳሳቱትን ሰዎች መንገድ ምራን" በሉ፡፡ صِرَاطَ الَّذِينَ أَنْعَمْتَ عَلَيْهِمْ غَيْرِ الْمَغْضُوبِ عَلَيْهِمْ وَلَا الضَّالِّينَ አምላካችን አሏህ የዒሣ ሐዋርያት በሄዱበት በቀጥተኛው መንገድ ላይ ያጽናን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Show all...
ታላቂቱ ባቢሎን ክፍል ሁለት በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርኅሩኅ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። 5፥111 ወደ ሐዋርያትም «በእኔ እና በመልእክተኛዬ እመኑ» በማለት ባዘዝኩ ጊዜ አስታውስ፡፡ وَإِذْ أَوْحَيْتُ إِلَى الْحَوَارِيِّينَ أَنْ آمِنُوا بِي وَبِرَسُولِي "ኤክሌሲያ" ἐκκλησία ማለት "ጉባኤ" "ማኅበር" "ስብሰባ" ማለት ሲሆን በብሉይ ኪዳን ግሪክ ሰፕቱአጀንት እና በአዲስ ኪዳን ግሪክ ኮይኔ "ጉባኤ" "ማኅበር" "ስብሰባ" ለሚለው የገባው ቃል ነው፥ በተለምዶ "ቤተክርስቲያን"church" ይባል። ኢየሱስ ጴጥሮስን መሠረት በማድረግ የራሱን ስብስብ እንደሚሠራ ተናግሮ ነበር፦ ማቴዎስ 16፥18 እኔም እልሃለሁ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚህም ዓለት ላይ ኤክሌሲያዬን እሠራለሁ፥ የሲዖል ደጆችም አይችሉአትም። κἀγὼ δέ σοι λέγω ὅτι σὺ εἶ Πέτρος, καὶ ἐπὶ ταύτῃ τῇ πέτρᾳ οἰκοδομήσω μου τὴν ἐκκλησίαν, καὶ πύλαι Ἅιδου οὐ κατισχύσουσιν αὐτῆς. ይህ ስብስብ መቀመጫው ኢየሩሳሌም የነበረ ሲሆን በ 70 ድኅረ ልደት የሮማው ጄኔራል ጢጦስ ቤተመቅደሱን እና ኢየሩሳሌምን ሲያነዳት ተበተነ። ከዚያም ከ 180 እስከ 313 ድኅረ ልደት በዓለም ዐቀፍ ደረጃ "ኤክሌሲያ ሜጋሌ" ἐκκλησία μεγάλη "ኤክሌሲያ ማግና" "ታላቂቱ ቤተክርስቲያን"Great Church" ተብላ በሮም መንግሥት መቀመጫ ያደረገች ታላቂቱ ቤተክርስቲያን በአበው ተዋቅራ ተደራጀች፥ ይህቺ ሴት በሮም መንግሥት የተቀመጠችው ኩላዊት ቤተክርስቲያን ናት። ይህቺ ሴት በዚህ ጊዜ ውስጥ የሥላሴ እሳቤ፣ የተሠግዎት ትምህርት፣ ስለ ማርያም ስግደት እና እርገት፣ ወደ መላእክት እና ወደ ሙታን መጸለይ፣ ለመስቀል እና ለስዕል መስገድ፣ ምንኩስና እና ብህትውና የመሳሰሉት ትምህርት ስርዋጽ አርጋ ከግሪክ ወሮም ፍልስፍና ጋር ቀይጣለች። "ካቶሊኮስ" καθολικός ማለት "ዓለም ዐቀፍ" በግዕዝ "ኩላዊት" በሮማይስጥ "ካቶሊክ" ማለት ነው፥ ለመጀመሪያ ጊዜ ኤክሌሲያን "ካቶሊኮስ" ብሎ የጠራት የአንጾኪያው ኤጲስ ቆጶስ አግናጥዮስ በ 110 ድኅረ ልደት ነው፦ "ኤጲስ ቆጶሱ በሚገለጥበት ቦታ ሁሉ በዚያ ብዙኃኑ ይሁኑ! ኢየሱስ ባለበትም ቢሆን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን አለች"። Epistle to the Smyrnaeans (St. Ignatius) Chapter 8 የፈረንሳዩ ኤጲስ ቆጶስ ሔራንዮስ ደግሞ በ 180 ድኅረ ልደት ላይ፦ "እውነታው ያለው በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንጂ ሌላ በየትም አይደለም" ብሏል፦ "እውነታው ያለው በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንጂ ሌላ በየትም አይደለም"። Against Heresies(St. Irenaeus) Book III(3) Chapter 4 ይህቺ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የግሪክ እና የሮም ፍልስፍና የተጠናወታቸው የፈላስፎች ስብስብ ናት፥ ፈላስፋው ዮስጦስ ሰማዕቱ፣ ፈላስፋው አርጌንስ፣ ፈላስፋው ጠርጡሊያኖስ፣ ፈላስፋው ቀሌሜንጦስ ዘእስክንድርያ፣ ፈላስፋው አውግስጢኖስ ወዘተ አደራጅተው ያዋቀሯት ስብስብ ናት። የእስክንድርያው የትርጓሜ ትምህርት ቤት በአፍላጦን ፍልስፍና ሰርጎገብ መሠረት ማድረጉ እንዲሁ የአንጾኪያው ትምህርት ቤት ደግሞ በአሪስጣጣሊስ ፍልስፍና ሰርጎገብ ማድረጉ ጉልኅ ማሳያ ነው። ፨ ይህቺ ሴት በ325 ድኅረ ልደት በንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ሊቀ መንበርነት ኩላዊት የኒቂያ ጉባኤ ላይ 318 ኤጲጵ ቆጶሳት ከመላው ዓለም በመሰብሰብ "የሮሙ የጴጥሮስ በዓለ መንበር ሐዋርያት እንዳዘዙ አለቃም ፈራጅም ይሁን" በማለት ወሰነች፦ ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 4 ቁጥር 40 "ሊቃነ ጳጳሳት በዓለም ሁሉ አራት ብቻ እንዲሆኑ በኒቂያ የተሰበሰቡት የቅዱሳን ማኅበር አዘዙ። ከእነርሱም የሮሙ የጴጥሮስ በዓለ መንበር ሐዋርያት እንዳዘዙ አለቃም ፈራጅም ይሁን"። ኩላዊት የክርስትና ቤተ ክርስቲያን የምትመራው በሮማ ግዛት በአምስት ኤጲስ ቆጶሳዊ ፓትሪያሪኮች"Pentarchy" ነው፥ እነርሱም የሮሙ የጴጥሮስ መንበር፣ የቁስጥንጥንያው የእንድርያስ መንበር፣ የእስክንድርያው የማርቆስ መንበር፣ የአንጾኪያው የጴጥሮስ መንበር እና የኢየሩሳሌሙ የያዕቆብ መንበር ናቸው። ይህቺ የኒቂያ ጉባኤ ፓትሪያሪኩን "ካቶሊኮስ በሚባል ታላቅ ስም ያክብሩት" በማለት ተናግራለች፥ በተጨማሪም ኤጲስ ቆጶስ "የጸጋ አምላካችሁም ነውና" ተብሏል፦ ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 4 ቁጥር 43 "ካቶሊኮስ በሚባል ታላቅ ስም ያክብሩት" ዲድስቅልያ 8፥6 ከእውነተኛው አምላክ በታችም በምድር ላይ አለቃችሁ ፣ መምህራችሁና ኃይላችሁ "የጸጋ አምላካችሁም ነውና"። ፨ ይህቺ ሴት በ 381 ድኅረ ልደት በሮሙ ንጉሥ በታላቁ እና ፊተኛው ቴዎዶስዮስ ሊቀ መንበርነት የተዘጋጀው የቆስጠንጥኒያ ኩላዊ ጉባኤ በ150 ኤጲስ ቆጶሳት በመሰብሰብ "በአንዲት፣ ቅድስት፣ "ካቶሊካዊት" እና ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን"we believe in one, holy, Catholic and Apostolic Church" ብላለች። ፨ ይህቺ ሴት 431 ድኅረ ልደት በንጉሥ ደኃራይ ቴዎዶስዮስ ሊቀ መንበርነት የኤፌሶን ኩላዊ ጉባኤ ላይ 200 ኤጲጵ ቆጶሳት ከመላው ዓለም በመሰብሰብ የአንጾኪያን መንበርን ከንስጥሮሳውያን ጋር አውግዛለች። ፨ ይህቺ ሴት 451 ድኅረ ልደት በንጉሥ መርቅያኖስ ሊቀ መንበርነት የኬልቄዶን ኩላዊ ጉባኤ ላይ 130 ኤጲጵ ቆጶሳት ከመላው ዓለም በመሰብሰብ የእስክንድርያውን መንበር ከጽብሓውያን ቤተክርስቲያን"oriental church" ጋር አውግዛለች። ፨ ይህቺ ሴት በመቀጠል በ 1954 ድኅረ ልደት የቁስጥንጥንያን መንበር ከምሥራቃውያን ቤተክርስቲያን"eastern church" ጋር አውግዛለች። ፨ ይህቺ ሴት በስተመጨረሻም የፕሮቴስታንትን ሐዳሲያንን የሚባሉትን ሉተራውያንን፣ ዝውንግሊያውያንን፣ ካልቪናውያንን ወዘተ አውግዛለች። በእርግጥም ይህቺ ሴት በቀዩ አውሬ በሮም መንግሥት ላይ የተቀመጠች ጋለሞታይቷ ሴት ናት፦ 1ኛ ጴጥሮስ 5፥13 ከእናንተ ጋር ተመርጣ "በባቢሎን ያለች ቤተ ክርስቲያን" ልጄም ማርቆስ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። "ባቢሎን" ደግሞ የሮም ምሥጢራዊ ስም እንደሆነ የቂሳሪያው አውሳቢዮስ ይህንን አንቀጽ ታሳቢ እና ዋቢ አርጎ ተናግሯል፦ "ጴጥሮስም በመጀመሪያው መልእክቱ ውስጥ ስለ ማርቆስ ሲያነሳ እንዳመለከተው ከተማይቱን በምሳሌ "ባቢሎን" ብሎ ሲጠራ እርሱ ራሱ በሮም እንደ ጻፈው ይናገራሉ"። Church History (Eusebius) > Book II(2) Chapter 15 Number 2 ዛሬ በዓለም ላይ ከተለያየ ብሔር፣ ቋንቋ፣ ዘውግ ከ 1.3 ቢሊዮን ምእመናን ያቀፈው አባላት ያላት እና ሮም መቀመጫ ያረገች የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ነች። የካቶሊክ ቤተክርስቲያን እነዚህን ከመስመር የወጡ ትምህርታት የሚያርማትን ግለሰብ ሆነ ቡድን "ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ፣ ሐዋርያዊ መተካካት የያዘውን የጴጥሮስን መንበር እና የመፍታትና የማሰር ቁልፍ ተቀብያለው" በማለት "መ-ናፍቅ" እያለች በግዝት እና በግዞት ስታሰቃይ ነበር፥ በታሪክ ውስጥ ይህቺ ተቋም ሲያሰኛት በጉልበት፣ በበባርነት እና በቅኝ ግዛት ሰዎች ክርስትናን እንዲቀበሉ አርጋለች። ይህቺ ቤተክርስቲያን ባይብልን ወደ ሌላ ቋንቋ የተረጎሙ ሰዎች በመስቀል አቃጥላለች፥ ቤተክርስቲያን ዓለምን ለመውረር እና ዲኑል ኢሥላምን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት የመስቀል ጦርነት በመስቀለኞች ዘጠኝ ጊዜ አርጋለች።
Show all...
ታላቂቱ ባቢሎን ክፍል አንድ በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርኅሩኅ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። 5፥111 «አመንን፥ እኛ ሙሥሊሞች መኾናችንን መስክር» አሉ፡፡ قَالُوا آمَنَّا وَاشْهَدْ بِأَنَّنَا مُسْلِمُونَ "አፓካሉፕሲስ" ἀποκάλυψις ማለት "ቀለምሲስ" "ራእይ" "መገለጥ"revelation" ማለት ሲሆን መሠረታዊ ትርጉሙ "የተሸፈ ነገር ማራቆት" ማለት ነው፥ ቀለምሲስ የጴጥሮስ ራእይ፣ የጳውሎስ ራእይ፣ የያዕቆብ ራእይ እና የዮሐንስ ራእይ ተብለው ይታወቃሉ። ፨ የጴጥሮስ ራእይ 1672 ድኅረ ልደት በሙራቶሪያን ቀኖና ውስጥ የተገኘ ሲሆን በ 170 ድኅረ ልደት አካባቢ የነበረ ቅጂ ነው፣ ፨የጳውሎስ ራእይ 1845 ድኅረ ልደት የናግ ሐማዲ ኮዴክስ 172 ውስጥ የተገኘ ሲሆን በሁለተኛው ክፍለ ዘመን ድኅረ ልደት አካባቢ የነበረ ቅጂ ነው፣ ፨ የያዕቆብ ራእይ 1845 ድኅረ ልደት የናግ ሐማዲ ኮዴክስ 172 ውስጥ የተገኘ ሲሆን በ 200 ድኅረ ልደት አካባቢ የነበረ ቅጂ ነው፣ ፨ የዮሐንስ ራእይ ዲዮናስዮስ ዘእስክንድርያ በተናገረው መሠረት ከ 50-100 ድኅረ ልደት ይኖር የነበረው የሴሪንቶሳውያን"Cerinthian" መሥራች ሴሪንቶስ"Cerinthus" እንደጻፈው ተናግሯል፦ "እንዲህም ይላሉ፦ "የዮሐንስ ሥራ አይደለም እንዲሁ መገለጥም አይደለም፥ ምክንያቱም በወፍራም እና ጥቅጥቅ ባለ ጨለማ መጋረጃ የተሸፈነ ነው። እነሱም ከሐዋርያት፣ ከቅዱሳን አንዳቸውም ወይም ከቤተክርስቲያን ውስጥ አንድም ደራሲ እንዳልሆኑ ያረጋግጣሉ፥ ነገር ግን ሴሪንቶስ ከእሱ በኋላ ሴሪንቶሳውያን የተባለውን አንጃ የመሠረተው ለስሙ ልቦለድ የተከበረ ስልጣንን በመፈለግ ስሙን ቅድመ ቅጥያ አደረገ። Church History (Eusebius) > Book VII(7) Chapter 25 Number 2 በ 363 የተካሄደው የሎዶቅያ ጉባኤ የዮሐንስን ራእይ በጉባኤ ደረጃ ውድቅ አድርጓታል፥ "Synod of Laodicea Canon 60" ተመልከት! አውሳብዮስ ደግሞ የዮሐንስ ራእይ ውድቅ ከተደረገባቸው መጻሕፍት መካከል አንዱ እንደሆነ ተናግሯል፦ "ውድቅ ከተደረጉ መጻሕፍት መካከል ደግሞ የጳውሎስ ሥራ፣ ኖላዊ ዘሔርሜንስ ተብሎ የሚጠራው፣ የጴጥሮስ ራእይ የግድ ይቆጠራሉ፥ በተጨማሪም የበርናባስ መልእክት እና ዲድስቅሊያ እንደነዚ ያሉት እና እኔ እንዳልኩት የዮሐንስ ራእይ ነው"። Church History (Book III(3) Chapter 25 Number 4) የፐሺታ(ቬሺታ) ቀኖና የሚባለው ቀኖና በ 3ኛ ክፍለ ዘመን ከግሪክ ወደ ዐረማይስጥ የተዘጋጀ ሲሆን ራእይ ዮሐንስን አያካትትም። በጣም ስመ ጥር እና ዝነኛ ኮዴክስ ቫቲካነስ የዮሐንስን ራእይ አያካትትም። ከቤተክርስቲያን አበው መካከል ዲዮናስዩስ ዘእስክንድርያ፣ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም፣ ጂሊየስ አፍሪካነስ፣ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ ራእይ ዮሐንስን አይቀበሉም ነበር፦ "ከእኛ በፊት የነበሩት አንዳንዶቹ መጽሐፉን ወደ ጎን በመተው ሙሉ በሙሉ ውድቅ አድርገዋል"። Church History (Eusebius) > Book VII(7) Chapter 25 Number 1 A New Translation with Introduction and Commentary" የተባለው ማብራሪያ ራእየ ዮሐንስ በዲዮናስዮስ፣ በታላቁ ባስልዮስ፣ በጎርጎርዮስ ዘኑሲስ፣ በዮሐንስ አፈወርቅ ዘንድ ከተቀጠፉ ሥራዎች ጋር እንደሚታይ ተናግሯል፦ "ራእይ ቀኖናዊ ጽሑፎች ባልሆኑ ስብስቦች ውስጥም ተቀምጧል፥ በዲዮናስዮስ፣ በታላቁ ባስልዮስ፣ በጎርጎርዮስ ዘኑሲስ፣ በዮሐንስ አፈወርቅ እና በሌሎች ጸሐፊያን ከተቀጠፉ ሥራዎች ጋር ይታያል"። Revelation: A New Translation with Introduction and Commentary. Page 145 የፕሮቴስታንት ሐዳሲያን ማርቲን ሉተር፣ ዮሐንስ ካልቪን እና ሉድሪች ዝውንግሊ የራእይን መጽሐፍ አይቀበሉም ነበር። "አንቲሌ ጉሜና"antile gomena" የሚለው ቃል "አንቲሌጉሜንያ" ἀντιλεγόμενα ከሚል ቃል የመጣ ነው፥ "አንቲሌ ጉሜና" የሚባሉት በሁሉም የቀኖና ጉባኤ ጭቅጭቅ ያለባቸው የአዲስ ኪዳን 7 መጻሕፍት ሲሆኑ ከሰባቱ አንዱ ራእይ ዮሐንስ ነው። የዮሐንስን ራእይ ታሪካዊ ዳራ በወፍ በረር ለቅምሻ ያክል ካየን ዘንዳ በዮሐንስ ራእይ ላይ በቀይ አውሬ ላይ አንዲት ሴት ተቀምጣ ታይታለች፦ ራእይ 17፥3 በመንፈስም ወደ በረሀ ወሰደኝ፤ የስድብም ስሞች በሞሉበት፥ ሰባት ራሶች እና አሥር ቀንዶችም ባሉበት በቀይ አውሬ ላይ አንዲት ሴት ተቀምጣ አየሁ። የዚህችን ሴት ማንነት ከማወቃችን በፊት ሰባት ራሶች እና አሥር ቀንዶች ስላሉት ስለ ቀዩ አውሬ እንመልከት! "አውሬ" ማለት "ጨካኝ" "በላተኛ" "ረጋጭ" የሚል ጠባይ ሲኖረው በፍካሬአዊ "ጨካኝ መንግሥት" ያመለክታል፥ ለምሳሌ፦ "አራት ታላላቅ አራዊት" ማለት "አራት የምድር መንግሥታት" ለማመልከት መጥቷል፦ ዳንኤል 7፥3 አራትም ታላላቅ አራዊት ከባሕር ወጡ። ዳንኤል 7፥17 እነዚህ አራቱ ታላላቅ አራዊት ከምድር የሚነሡ አራት ነገሥታት ናቸው። እነዚህ አራት መንግሥታት የፋርስ፣ የባቢሎን፣ የግሪክ እና የሮምን መንግሥታት ናቸው። ይህ ከተረዳን ቀዩ አውሬ የሮም መንግሥት ሲሆን ሰባት ራሶቹ ሰባቱ የሮም ተራሮች ናቸው፦ ራእይ 17፥9 ሰባቱ ራሶች ሴቲቱ የተቀመጠችባቸው ሰባት ተራራዎች ናቸው። ሰባት ራሶቹ ሰባቱ የሮም አላውያን ነገሥታት ናቸው፥ አምስቱ የወደቁት ከጂሊየስ ቄሳር እስከ ገላውዲዮስ ቆሳር ያሉት ነገሥታት ናቸው፦ ራእይ 17፥10 ሰባት ነገሥታት ደግሞ ናቸው፥ አምስቱ ወድቀዋል። አንዱም አለ፥ የቀረውም ገና አልመጣም፤ ሲመጣም፥ ጥቂት ጊዜ ሊቆይ ይገባዋል። "አንዱም አለ" የተባለው ሴሪንቶስ በነበረበት ጊዜ የነበረው ኔሮ ቄሳር ሲሆን 7ኛው ወደ ፊት የሚያንሰራራው የሮም መንግሥት ንጉሥ ነው፦ ራእይ 17፥11 የነበረው እና የሌለውም አውሬ ራሱ ደግሞ ስምንተኛው ነው ከሰባቱም አንዱ ነው፥ ወደ ጥፋትም ይሄዳል። ከሰባቱ ራሶች አንዱ የሆነው እራሱ ስምንተኛ ሆኖ ወደፊት ይነሳል። በቀዩ አውሬ ላይ የተቀመጠችው ሴት በብዙም ውኃዎች ላይ የተቀመጠች ስትሆን የውኃዎቹ ትርጉም ወገኖች፣ ብዙ ሰዎች፣ አሕዛብ፣ ቋንቋዎች ናቸው፦ ራእይ 17፥1 ና በብዙም ውኃዎች ላይ የተቀመጠችውን የታላቂቱን ጋለሞታ ፍርድ አሳይሃለሁ። ራእይ 17፥15 ጋለሞታይቱ የተቀመጠችባቸው ያየሃቸው ውኃዎች ወገኖች፣ ብዙ ሰዎች፣ አሕዛብ፣ ቋንቋዎች ናቸው። ይህቺ ሴት የታጨላትን ወንድ ትታ ከሮም መንግሥት ነገሥታት ጋር ጎልምታለች፥ በግምባርዋ ምሥጢር የሆነ "ታላቂቱ ባቢሎን" የሚል ተጽፎዋል፦ ራእይ 17፥5 በግምባርዋ ምሥጢር የሆነ ስም፦ "ታላቂቱ ባቢሎን፥ የጋለሞታዎች እና የምድር ርኵሰት እናት" ተብሎ ተጻፈ። "ባቬል" בבל የሚለው የዕብራይስጥ ቃል፣ "ባቤል" בבל የሚለው የዐረማይስጥ ቃል፣ "ባቢሎን" የሚለው የግዕዝ ቃል ትርጉማቸው "ድብልቅል" "ምስቅልቅል" ማለት ሲሆን ይህቺ ሴት የሙሽራውን ትምህርት ከዐረማዊ ትምህርት በመቀየጥ፣ በመደባለቅ፣ በማመሰቃቀል የጋለሞታዎች እናት ናት፥ እውነተኛ የኢየሱስን ተከታዮች በመግደል እና በማስገደል በደማቸው ስለሰከረች የምድር ርኵሰት እናት ናት፦ ራእይ 17፥6 ሴቲቱም በቅዱሳን ደም እና በኢየሱስ ምስክሮች ደም ሰክራ አየኋት። ይህቺ ሴት ማን ናት? ኢንሻላህ ይቀጥላል..... ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Show all...
ታላቂቱ ባቢሎን ክፍል አንድ በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርኅሩኅ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። 5፥111 «አመንን፥ እኛ ሙሥሊሞች መኾናችንን መስክር» አሉ፡፡ قَالُوا آمَنَّا وَاشْهَدْ بِأَنَّنَا مُسْلِمُونَ "አፓካሉፕሲስ" ἀποκάλυψις ማለት "ቀለምሲስ" "ራእይ" "መገለጥ"revelation" ማለት ሲሆን መሠረታዊ ትርጉሙ "የተሸፈ ነገር ማራቆት" ማለት ነው፥ ቀለምሲስ የጴጥሮስ ራእይ፣ የጳውሎስ ራእይ፣ የያዕቆብ ራእይ እና የዮሐንስ ራእይ ተብለው ይታወቃሉ። ፨ የጴጥሮስ ራእይ 1672 ድኅረ ልደት በሙራቶሪያን ቀኖና ውስጥ የተገኘ ሲሆን በ 170 ድኅረ ልደት አካባቢ የነበረ ቅጂ ነው፣ ፨የጳውሎስ ራእይ 1845 ድኅረ ልደት የናግ ሐማዲ ኮዴክስ 172 ውስጥ የተገኘ ሲሆን በሁለተኛው ክፍለ ዘመን ድኅረ ልደት አካባቢ የነበረ ቅጂ ነው፣ ፨ የያዕቆብ ራእይ 1845 ድኅረ ልደት የናግ ሐማዲ ኮዴክስ 172 ውስጥ የተገኘ ሲሆን በ 200 ድኅረ ልደት አካባቢ የነበረ ቅጂ ነው፣ ፨ የዮሐንስ ራእይ ዲዮናስዮስ ዘእስክንድርያ በተናገረው መሠረት ከ 50-100 ድኅረ ልደት ይኖር የነበረው የሴሪንቶሳውያን"Cerinthian" መሥራች ሴሪንቶስ"Cerinthus" እንደጻፈው ተናግሯል፦ "እንዲህም ይላሉ፦ "የዮሐንስ ሥራ አይደለም እንዲሁ መገለጥም አይደለም፥ ምክንያቱም በወፍራም እና ጥቅጥቅ ባለ ጨለማ መጋረጃ የተሸፈነ ነው። እነሱም ከሐዋርያት፣ ከቅዱሳን አንዳቸውም ወይም ከቤተክርስቲያን ውስጥ አንድም ደራሲ እንዳልሆኑ ያረጋግጣሉ፥ ነገር ግን ሴሪንቶስ ከእሱ በኋላ ሴሪንቶሳውያን የተባለውን አንጃ የመሠረተው ለስሙ ልቦለድ የተከበረ ስልጣንን በመፈለግ ስሙን ቅድመ ቅጥያ አደረገ። Church History (Eusebius) > Book VII(7) Chapter 25 Number 2 በ 363 የተካሄደው የሎዶቅያ ጉባኤ የዮሐንስን ራእይ በጉባኤ ደረጃ ውድቅ አድርጓታል፥ "Synod of Laodicea Canon 60" ተመልከት! አውሳብዮስ ደግሞ የዮሐንስ ራእይ ውድቅ ከተደረገባቸው መጻሕፍት መካከል አንዱ እንደሆነ ተናግሯል፦ "ውድቅ ከተደረጉ መጻሕፍት መካከል ደግሞ የጳውሎስ ሥራ፣ ኖላዊ ዘሔርሜንስ ተብሎ የሚጠራው፣ የጴጥሮስ ራእይ የግድ ይቆጠራሉ፥ በተጨማሪም የበርናባስ መልእክት እና ዲድስቅሊያ እንደነዚ ያሉት እና እኔ እንዳልኩት የዮሐንስ ራእይ ነው"። Church History (Book III(3) Chapter 25 Number 4) የፐሺታ(ቬሺታ) ቀኖና የሚባለው ቀኖና በ 3ኛ ክፍለ ዘመን ከግሪክ ወደ ዐረማይስጥ የተዘጋጀ ሲሆን ራእይ ዮሐንስን አያካትትም። በጣም ስመ ጥር እና ዝነኛ ኮዴክስ ቫቲካነስ የዮሐንስን ራእይ አያካትትም። ከቤተክርስቲያን አበው መካከል ዲዮናስዩስ ዘእስክንድርያ፣ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም፣ ጂሊየስ አፍሪካነስ፣ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ ራእይ ዮሐንስን አይቀበሉም ነበር፦ "ከእኛ በፊት የነበሩት አንዳንዶቹ መጽሐፉን ወደ ጎን በመተው ሙሉ በሙሉ ውድቅ አድርገዋል"። Church History (Eusebius) > Book VII(7) Chapter 25 Number 1 A New Translation with Introduction and Commentary" የተባለው ማብራሪያ ራእየ ዮሐንስ በዲዮናስዮስ፣ በታላቁ ባስልዮስ፣ በጎርጎርዮስ ዘኑሲስ፣ በዮሐንስ አፈወርቅ ዘንድ ከተቀጠፉ ሥራዎች ጋር እንደሚታይ ተናግሯል፦ "ራእይ ቀኖናዊ ጽሑፎች ባልሆኑ ስብስቦች ውስጥም ተቀምጧል፥ በዲዮናስዮስ፣ በታላቁ ባስልዮስ፣ በጎርጎርዮስ ዘኑሲስ፣ በዮሐንስ አፈወርቅ እና በሌሎች ጸሐፊያን ከተቀጠፉ ሥራዎች ጋር ይታያል"። Revelation: A New Translation with Introduction and Commentary. Page 145 የፕሮቴስታንት ሐዳሲያን ማርቲን ሉተር፣ ዮሐንስ ካልቪን እና ሉድሪች ዝውንግሊ የራእይን መጽሐፍ አይቀበሉም ነበር። "አንቲሌ ጉሜና"antile gomena" የሚለው ቃል "አንቲሌጉሜንያ" ἀντιλεγόμενα ከሚል ቃል የመጣ ነው፥ "አንቲሌ ጉሜና" የሚባሉት በሁሉም የቀኖና ጉባኤ ጭቅጭቅ ያለባቸው የአዲስ ኪዳን 7 መጻሕፍት ሲሆኑ ከሰባቱ አንዱ ራእይ ዮሐንስ ነው። የዮሐንስን ራእይ ታሪካዊ ዳራ በወፍ በረር ለቅምሻ ያክል ካየን ዘንዳ በዮሐንስ ራእይ ላይ በቀይ አውሬ ላይ አንዲት ሴት ተቀምጣ ታይታለች፦ ራእይ 17፥3 በመንፈስም ወደ በረሀ ወሰደኝ፤ የስድብም ስሞች በሞሉበት፥ ሰባት ራሶች እና አሥር ቀንዶችም ባሉበት በቀይ አውሬ ላይ አንዲት ሴት ተቀምጣ አየሁ። የዚህችን ሴት ማንነት ከማወቃችን በፊት ሰባት ራሶች እና አሥር ቀንዶች ስላሉት ስለ ቀዩ አውሬ እንመልከት! "አውሬ" ማለት "ጨካኝ" "በላተኛ" "ረጋጭ" የሚል ጠባይ ሲኖረው በፍካሬአዊ "ጨካኝ መንግሥት" ያመለክታል፥ ለምሳሌ፦ "አራት ታላላቅ አራዊት" ማለት "አራት የምድር መንግሥታት" ለማመልከት መጥቷል፦ ዳንኤል 7፥3 አራትም ታላላቅ አራዊት ከባሕር ወጡ። ዳንኤል 7፥17 እነዚህ አራቱ ታላላቅ አራዊት ከምድር የሚነሡ አራት ነገሥታት ናቸው። እነዚህ አራት መንግሥታት የፋርስ፣ የባቢሎን፣ የግሪክ እና የሮምን መንግሥታት ናቸው። ይህ ከተረዳን ቀዩ አውሬ የሮም መንግሥት ሲሆን ሰባት ራሶቹ ሰባቱ የሮም ተራሮች ናቸው፦ ራእይ 17፥9 ሰባቱ ራሶች ሴቲቱ የተቀመጠችባቸው ሰባት ተራራዎች ናቸው። ሰባት ራሶቹ ሰባቱ የሮም አላውያን ነገሥታት ናቸው፥ አምስቱ የወደቁት ከጂሊየስ ቄሳር እስከ ገላውዲዮስ ቆሳር ያሉት ነገሥታት ናቸው፦ ራእይ 17፥10 ሰባት ነገሥታት ደግሞ ናቸው፥ አምስቱ ወድቀዋል። አንዱም አለ፥ የቀረውም ገና አልመጣም፤ ሲመጣም፥ ጥቂት ጊዜ ሊቆይ ይገባዋል። "አንዱም አለ" የተባለው ሴሪንቶስ በነበረበት ጊዜ የነበረው ኔሮ ቄሳር ሲሆን 7ኛው ወደ ፊት የሚያንሰራራው የሮም መንግሥት ንጉሥ ነው፦ ራእይ 17፥11 የነበረው እና የሌለውም አውሬ ራሱ ደግሞ ስምንተኛው ነው ከሰባቱም አንዱ ነው፥ ወደ ጥፋትም ይሄዳል። ከሰባቱ ራሶች አንዱ የሆነው እራሱ ስምንተኛ ሆኖ ወደፊት ይነሳል። በቀዩ አውሬ ላይ የተቀመጠችው ሴት በብዙም ውኃዎች ላይ የተቀመጠች ስትሆን የውኃዎቹ ትርጉም ወገኖች፣ ብዙ ሰዎች፣ አሕዛብ፣ ቋንቋዎች ናቸው፦ ራእይ 17፥1 ና በብዙም ውኃዎች ላይ የተቀመጠችውን የታላቂቱን ጋለሞታ ፍርድ አሳይሃለሁ። ራእይ 17፥15 ጋለሞታይቱ የተቀመጠችባቸው ያየሃቸው ውኃዎች ወገኖች፣ ብዙ ሰዎች፣ አሕዛብ፣ ቋንቋዎች ናቸው። ይህቺ ሴት የታጨላትን ወንድ ትታ ከሮም መንግሥት ነገሥታት ጋር ጎልምታለች፥ በግምባርዋ ምሥጢር የሆነ "ታላቂቱ ባቢሎን" የሚል ተጽፎዋል፦ ራእይ 17፥5 በግምባርዋ ምሥጢር የሆነ ስም፦ "ታላቂቱ ባቢሎን፥ የጋለሞታዎች እና የምድር ርኵሰት እናት" ተብሎ ተጻፈ። "ባቬል" בבל የሚለው የዕብራይስጥ ቃል፣ "ባቤል" בבל የሚለው የዐረማይስጥ ቃል፣ "ባቢሎን" የሚለው የግዕዝ ቃል ትርጉማቸው "ድብልቅል" "ምስቅልቅል" ማለት ሲሆን ይህቺ ሴት የሙሽራውን ትምህርት ከዐረማዊ ትምህርት በመቀየጥ፣ በመደባለቅ፣ በማመሰቃቀል የጋለሞታዎች እናት ናት፥ እውነተኛ የኢየሱስን ተከታዮች በመግደል እና በማስገደል በደማቸው ስለሰከረች የምድር ርኵሰት እናት ናት፦ ራእይ 17፥6 ሴቲቱም በቅዱሳን ደም እና በኢየሱስ ምስክሮች ደም ሰክራ አየኋት። ይህቺ ሴት ማን ናት? ኢንሻላህ ይቀጥላል..... ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Show all...
በጉራጊኛ ደርሥ ተለቋል። ጉራጊኛ ተናጋሪዎች ገብታችሁ ኮምኩሙ፦ https://t.me/wahidcomguragiga/36
Show all...
፨ "ኸሚሥ" خَمِيس ማለት "አምስት" ማለት ሲሆን "ሐሙስ" ማለት ነው፥ "ሐሙስ" ማለት "አምሽት" "አምስት" ማለት ነው። ፨ "ጁሙዓህ" جُمُعَة ማለት "ስብስብ" ማለት ሲሆን "ዓርብ" ማለት ነው፥ "ዓርብ" የሚለው "ረበዐ" ማለትም "ሰበሰበ" ማለት ሲሆን "መሰብሰቢያ" "ስድስተኛ" ማለት ነው። አሏህ ለመላእክት፦ "እኔ ሰውን ከጭቃ እፈጥራለሁ፥ በምድር ላይ ምትክን አድራጊ ነኝ" ብሎ በነገራቸው መሠረት ሰውን በስድስተኛው ቀን ፈጠረ፦ 38፥71 ጌታህ ለመላእክት «እኔ ሰውን ከጭቃ እፈጥራለሁ» ባለ ጊዜ አስታውስ፡፡ إِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلَائِكَةِ إِنِّي خَالِقٌ بَشَرًا مِّن طِينٍ 2፥30 ጌታህ ለመላእክት፡- «እኔ በምድር ላይ ምትክን አድራጊ ነኝ» ባለ ጊዜ አስታውስ! وَإِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلَائِكَةِ إِنِّي جَاعِلٌ فِي الْأَرْضِ خَلِيفَةً ተፍሢር ኢብኑ ከሲር 7፥54 "እነዚህ ስድስት ቀናት አሐድ፣ ኢስነይን፣ ሱላሳእ፣ አርቢዓእ፣ ኸሚሥ፣ ጁሙዓህ ናቸው። ፍጥረት ሁሉ በጁሙዓህ ቀን ተሰብስቦ ነበር፥ በዚያ ቀን አደም ተፈጠረ። والستة الأيام هي : الأحد ، والاثنين ، والثلاثاء ، والأربعاء ، والخميس ، والجمعة - وفيه اجتمع الخلق كله ، وفيه خلق آدم. ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 4, ሐዲስ 1 አቡ ሁራይራህ እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "መልካም ቀን ፀሐይ ከወጣችበት የጁሙዓህ ቀን ነው፥ በዚያ ቀን አደም ተፈጠረ"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ خَيْرُ يَوْمٍ طَلَعَتْ فِيهِ الشَّمْسُ يَوْمُ الْجُمُعَةِ فِيهِ خُلِقَ آدَمُ ለመሆኑ ባይብል ላይ ፈጣሪ ሰማይን እና ምድርን የፈጠረው በየትኛው ቀን ነው ይላል? ዘፍጥረት በመጀመርያው ቀን ይለናል፦ ዘፍጥረት 1፥1 በመጀመሪያ ኤሎሂም ሰማይን እና ምድርን ፈጠረ። בְּרֵאשִׁ֖ית בָּרָ֣א אֱלֹהִ֑ים אֵ֥ת הַשָּׁמַ֖יִם וְאֵ֥ת הָאָֽרֶץ׃ ዘፍጥረት 1፥5 ኤሎሂምም ብርሃኑን "ቀን" ብሎ ጠራው፥ ጨለማውንም ሌሊት፡ አለው። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ አንድ ቀን። וַיִּקְרָ֨א אֱלֹהִ֤ים לָאֹור֙ יֹ֔ום וְלַחֹ֖שֶׁךְ קָ֣רָא לָ֑יְלָה וַֽיְהִי־עֶ֥רֶב וַֽיְהִי־בֹ֖קֶר יֹ֥ום אֶחָֽד׃ פ "ዮም" י֥וֹם ማለት በነጠላ "ቀን" ማለት ሲሆን ይህ የመጀመሪያ ቀን ስለሆነ "አንድ" ለሚለው "ኤኻድ" אֶחָֽד በማለት ይነግረናል። ዘጸአት ደግሞ በስድስት ቀናት ይለናል፦ ዘጸአት 31፥17 ያህዌህ ሰማይን እና ምድርን በስድስት ቀናት ፈጠረ። כִּי־שֵׁ֣שֶׁת יָמִ֗ים עָשָׂ֤ה יְהוָה֙ אֶת־הַשָּׁמַ֣יִם וְאֶת־הָאָ֔רֶץ "ያሚም" יָמִ֗ים ማለት "ቀናት" ማለት ሲሆን "ዮም" י֥וֹם ለሚለው ቃል ብዜት ነው፥ "ሼሼት" שֵׁ֣שֶׁת ማለት "ስድስት" ማለት ነው። ኤሎሂም ሰማይን እና ምድርን የፈጠረው በስድስት ቀናት ወይም በመጀመርያው ቀን? "ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ አንድ ቀን" "ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ ሁለተኛ ቀን" "ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ ሦስተኛ ቀን" የሚሉ አገላለፆችን ስናይ "ቀን" የተባለው 12 ሰዓት የያዘውን የመአልት ክፍል እና 12 ሰዓት የያዘውን የሌሊት ክፍል በጥቅሉ ባለ 24 ሰዓቱን እንደሆነ አመላካች ነው። በቁርኣን ግን ፍጥረት የተፈጠረበት "ቀን" የሚለው ባለ 24 ሰዓት ቀን ሳይሆን በትንሹ አንድ ሺህ ዓመት ነው፦ 22፥47 እጌታህም ዘንድ አንዱ ቀን ከምትቆጥሩት ቀን እንደ ሺህ ዓመት ነው፡፡ إِنَّ يَوْمًا عِندَ رَبِّكَ كَأَلْفِ سَنَةٍ مِّمَّا تَعُدُّونَ ተፍሢር ኢብኑ ዐባሥ 7፥53 "ጌታችሁ ያ ሰማያትን እና ምድርን በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ አሏህ ነው" ከአያሙል ዱንያ እያንዳንዱ ቀን አንድ ሺህ ዓመት ነው"። { إِنَّ رَبَّكُمُ ٱللَّهُ ٱلَّذِي خَلَقَ ٱلسَمَاوَاتِ وَٱلأَرْضَ فِي سِتَّةِ أَيَّامٍ } من أيام الدنيا طول كل يوم ألف سنة ሌላው ሰማያትን እና ምድርን እንዲሁ በውስጣቸው ያለው ሁሉ ኅልቅቆ መሳፍርት ፍጥረት ሁሉ በጥቅሉ በስድስት ቀናት ውስጥ እንደፈጠ አሏህ ነግሮናል፥ ባይብል ላይ መላእክት መቼ እንደተፈጠሩ በግልጽ አይናገርም። ከዚያ ይልቅ በጥቅሉ አምላክ ከጥንት ጀምሮ እስከ ፍጻሜ ድረስ የሠራውን ሥራ ሰው መርምሮ እንዳማያገኝ ይናገራል፦ መክብብ 3፥11 አምላክ ከጥንት ጀምሮ እስከ ፍጻሜ ድረስ የሠራውን ሥራ ሰው መርምሮ እንዳያገኝ ዘላለምነትን በልቡ ሰጠው። גַּ֤ם אֶת־הָעֹלָם֙ נָתַ֣ן בְּלִבָּ֔ם מִבְּלִ֞י אֲשֶׁ֧ר לֹא־יִמְצָ֣א הָאָדָ֗ם אֶת־הַֽמַּעֲשֶׂ֛ה אֲשֶׁר־עָשָׂ֥ה הָאֱלֹהִ֖ים מֵרֹ֥אשׁ וְעַד־סֹֽוף׃ እኛም በሰማያት እና በምድር አፈጣጠር በማስተንተን፦ «ጌታችን ሆይ! ይህን በከንቱ አልፈጠርከውም፥ ጥራት ይገባህ! ከእሳትም ቅጣት ጠብቀን» እንላለን፦ 3፥191 እነርሱም እነዚያ ቆመው፣ ተቀምጠውም እና በጎኖቻቸው ተጋድመው አሏህን የሚያወሱ፥ በሰማያት እና በምድር አፈጣጠር የሚያስተነትኑ፦ «ጌታችን ሆይ! ይህን በከንቱ አልፈጠርከውም፥ ጥራት ይገባህ! ከእሳትም ቅጣት ጠብቀን» የሚሉ ናቸው፡፡ الَّذِينَ يَذْكُرُونَ اللَّهَ قِيَامًا وَقُعُودًا وَعَلَىٰ جُنُوبِهِمْ وَيَتَفَكَّرُونَ فِي خَلْقِ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ رَبَّنَا مَا خَلَقْتَ هَـٰذَا بَاطِلًا سُبْحَانَكَ فَقِنَا عَذَابَ النَّارِ "ተፈኩር" تَفَكُّر የሚለው ቃል "ተፈከረ" تَفَكَّرَ ማለትም "አስተነተነ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ማስተንተን" ማለት ነው፥ የአሏህ ፍጥረት ማስተንተን የሥነ ፍጥረት ዕውቀታችንን ያጎለብተዋል። አምላካችን አሏህ ፍጥረቱን ከሚያስተነትኑ ባሮቹ ያድርገን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Show all...
ሥነ ፍጥረት ክፍል ሁለት በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 22፥47 እጌታህም ዘንድ አንዱ ቀን ከምትቆጥሩት ቀን እንደ ሺህ ዓመት ነው፡፡ إِنَّ يَوْمًا عِندَ رَبِّكَ كَأَلْفِ سَنَةٍ مِّمَّا تَعُدُّونَ ሰማይን ከፈጠረ በኃላ በሁለት ቀን የፈጠራትን ምድርን የእንቁላል ቅርጽ አርጎ ዘረጋት፥ "ዘረጋ" እንጂ "ፈጠረ" አይልም። "ዘረጋ" ለሚለው የገባው የግሥ መደብ "ደሓ" دَحَا ሲሆን የስም መደቡ "አድ ደሕያ” الدِّحْيَّة ነው፦ 79፥30 ምድርንም ከዚህ በኋላ ዘረጋት፡፡ وَالْأَرْضَ بَعْدَ ذَٰلِكَ دَحَاهَا "ከዚህ በኋላ" ማለት ከሰማይ መፈጠር በኃላ ማለት ነው፥ "አድ ደሕያ” الدِّحْيَّة ማለት “የሰጎን እንቁላል” ማለት ሲሆን አሏህ ምድርን “የሰጎን እንቁላል ቅርጽ አደረጋት” የሚል ትርጉም አለው። ፦ Dr. Kamal Omar Translation ፦ Ali Unal Translation ፦ Shabbir Ahmed Translation፦ “የሰጎን እንቁላል ቅርጽ አደረጋት”He made the earth egg-shaped” ብለው ተርጉመውታል። አሏህ ምድርን እንደ ሰጎን እንቁላል ቅርጽ አርጎ ያደላደላት ለእኛ ስለሆነ "ለእናንተ" በማለት ይናገራል፦ 55፥10 ምድርንም ለፍጡሩ አደላደላት፡፡ وَالْأَرْضَ وَضَعَهَا لِلْأَنَامِ 71፥19 አላህም ምድርን “ለእናንተ” ምንጣፍ አደረጋት፡፡ وَاللَّهُ جَعَلَ لَكُمُ الْأَرْضَ بِسَاطًا 2፥29 እርሱ ያ በምድር ያለውን ሁሉ ለእናንተ የፈጠረ ነው፡፡ هُوَ ٱلَّذِى خَلَقَ لَكُم مَّا فِى ٱلْأَرْضِ جَمِيعًۭا አሏህ ምድርን እንደ ሰጎን እንቁላል ቅርጽ አርጎ አደላድሎ በምድር ያለውን ማዕድናት፣ እጽዋት እና እንስሳት ለእኛ ፈጠረ፥ "በምድር ያለውን ሁሉ" የሚለው ማዕድናትን፣ እጽዋትን እና እንስሳትን ያካትታል። ከዚያ በጭስ መልክ የነበረችውን ሰማይ ሰባት ሰማያት አርጎ ጨረሳት አስተካከላት፦ 41፥12 በሁለት ቀናት ውስጥ ሰባት ሰማያት "አደረጋቸው"፡፡ فَقَضَىٰهُنَّ سَبْعَ سَمَٰوَاتٍۢ فِى يَوْمَيْنِ 2፥29 ከዚያም ወደ ሰማይ አሰበ፥ ሰባት ሰማያትም "አደረጋቸው"፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ ثُمَّ ٱسْتَوَىٰٓ إِلَى ٱلسَّمَآءِ فَسَوَّىٰهُنَّ سَبْعَ سَمَٰوَٰتٍۢ ۚ وَهُوَ بِكُلِّ شَىْءٍ عَلِيمٌۭ "ወደ ሰማይ አሰበ" "ወደ ሰማይ እርሷ ጭስ ኾና ሳለች አሰበ" ማለቱ በራሱ ሰማይ በጋዝ ደረጃ ተፈጥራ እንደነበረ ጉልህ ማሳያ ነው፥ "ከዚያም" ማለት ምድር እና ምድር ላይ ያለውን ከፈጠረ በኃላ ማለት ነው። 41፥12 ላይ "አደረገ" ለሚለው የገባው ቃል "ቀዷ" قَضَىٰ ሲሆን "ጨረሰ" በሚል ይመጣል፦ 27፥29 ሙሳም ጊዜውን በ-"ጨረሰ" እና ከቤተሰቦቹ ጋር በኼደ ጊዜ ከጡር ተራራ ጎን እሳትን አየ፡፡ فَلَمَّا قَضَىٰ مُوسَى الْأَجَلَ وَسَارَ بِأَهْلِهِ آنَسَ مِن جَانِبِ الطُّورِ نَارًا እዚህ አንቀጽ ላይ "ጨረሰ" ለሚለው የገባው "ቀዷ" قَضَىٰ እንደሆነ በአጽንዖት ልብ አድርግ! በተጨማሪ 2፥29 ላይ "አደረገ" ለሚለው የገባው ቃል "ሠዋ" سَوَّىٰ ሲሆን "አስተካከለ" በሚል ይመጣል፦ 87፥2 የዚያን ሁሉን ነገር የፈጠረውን እና ያስተካከለውን፡፡ الَّذِي خَلَقَ فَسَوَّىٰ እዚህ አንቀጽ ላይ "ያስተካከለ" ለሚለው የገባው "ሠዋ" سَوَّىٰ እንደሆነ በአንክሮት ልብ አድርግ! ስለዚህ ምድር እንደ ሰጎን እንቁላል ከመደላደሏ በፊት የፈጠራትን ጭሳዊ ሰማይ ሰባት ሰማያት አርጎ ፈጸማት አስተካከላት። "ቀዷሁነ" قَضَىٰهُنَّ "ሠዋሁነ" سَوَّىٰهُنَّ በሚል መድረሻ ቅጥያ ላይ ያለው "ሁነ" هُنَّ የሚለው ሦስተኛ አንስታይ መደብ "ሂየ" ‏هِيَ ለሚለው ብዜት ነው፥ "ሂየ" ‏هِيَ ማለት "እርሷ" ማለት ሲሆን "ሠማእ" سَّمَآء የሚለውን ተክቶ የመጣ ነው። ሰማይን ሰባት ሰማያት አድርጎ የጨረሰው እና ያስተካከለው በሁለት ቀናት ውስጥ ነው፥ እነዚህ "ሁለት ቀኖች" የተባሉት አምስተኛው ቀን "አል ኸሚሥ" ٱلْخَمِيس እና ስድስተኛው ቀን "አል ጁሙዓህ" ٱلْجُمُعَة እንደሆኑ ሙፈሢሮች አስቀምጠዋል፦ ተፍሢር ኢብኑ ከሲር 41፥12 "በሁለት ቀናት ውስጥ ሰባት ሰማያት አደረጋቸው" ከዚያ ፈጽሞ በሁለት ቀናት ውስጥ ሰባት ሰማያት አስተካከላቸው፥ ሌላው ሁለቱ ቀናት አምስተኛው ቀን እና ስድስተኛው ቀን ናቸው። ( فقضاهن سبع سموات في يومين ) أي : ففرغ من تسويتهن سبع سموات في يومين ، أي : آخرين ، وهما يوم الخميس ويوم الجمعة .
Show all...
ሥነ ፍጥረት ክፍል አንድ በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 7፥54 ጌታችሁ ያ ሰማያትን እና ምድርን በስድስት ቀናት ውስጥ የፈጠረ አሏህ ነው፡፡ إِنَّ رَبَّكُمُ اللَّهُ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ فِي سِتَّةِ أَيَّام አምላካችን አሏህ ሰማያትን፣ ምድርን እና በመካከላቸው ያለውን ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ በእርግጥ ፈጠረ፦ 50፥38 ሰማያትን፣ ምድርን እና በመካከላቸው ያለውን ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ በእርግጥ ፈጠርን፡፡ ድካምም ምንም አልነካንም፡፡ وَلَقَدْ خَلَقْنَا السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا فِي سِتَّةِ أَيَّامٍ وَمَا مَسَّنَا مِن لُّغُوبٍ "ፊ" فِي ማለት "ውስጥ" ማለት ሲሆን በጥቅል ስድስት ቀናት ውስጥ ሰማያትን እና ምድርን እንደፈጠረ ጉልኅ ማሳያ ነው፦ 7፥54 ጌታችሁ ያ ሰማያትን እና ምድርን በስድስት ቀናት ውስጥ የፈጠረ አሏህ ነው፡፡ إِنَّ رَبَّكُمُ اللَّهُ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ فِي سِتَّةِ أَيَّام "በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ አሏህ ነው" የሚለው ኃይለ ቃል ይሰመርበት! እዚህ አንቀጽ ላይ "ፈጠረ" ለሚለው የገባው ቃል "ኸለቀ" خَلَقَ ሲሆን "ፊ" فِي የሚለው መስተዋድድ በጥቅል አገላለጽ ፍጥረት በስድስት ቀናት ውስጥ መፈጠራቸውን አመላካች ነው። በተናጥል ሌላ አንቀጽ ላይ ምድርን በሁለት ቀናት ውስጥ መፍጠሩትን ይናገራል፦ 41፥9 በላቸው «እናንተ በዚያ "ምድርን በሁለት ቀናት ውስጥ በፈጠረው አምላክ በእርግጥ ትክዳላችሁን?" ለእርሱም ባለንጣዎችን ታደርጋላችሁን? ያ ይህንን የሠራው የዓለማት ጌታ ነው፡፡ قُلْ أَئِنَّكُمْ لَتَكْفُرُونَ بِٱلَّذِى خَلَقَ ٱلْأَرْضَ فِى يَوْمَيْنِ وَتَجْعَلُونَ لَهُۥٓ أَندَادًۭا ۚ ذَٰلِكَ رَبُّ ٱلْعَٰلَمِينَ እዚህ አንቀጽ ላይ "ፈጠረ" ለሚለው የገባው ቃል "ኸለቀ" خَلَقَ ሲሆን "ሁለት ቀናት" የተባሉት የመጀመሪያው ቀን "አል አሐድ" ٱلْأحَد እና ሁለተኛው ቀን "አል ኢስነይን" ٱلْاِثْنَيْن‎ እንደሆኑ ሙፈሢሮች አስቀምጠዋል፦ ተፍሢር ኢብኑ ከሲር 41፥9 "ምድርን በሁለት ቀናት ውስጥ በፈጠረው" ሲል "የመጀመሪያው ቀን እና ሁለተኛው ቀን ነው" ማለት ነው"። فقوله : ( خلق الأرض في يومين ) يعني : يوم الأحد ويوم الاثنين . ፨ "አሐድ" أحَد ማለት "አንድ" ማለት ሲሆን "እሑድ" ማለት ነው፥ "እሑድ" የሚለው የግዕዙ ቃል በራሱ “አሐደ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "አንድ" ማለት ነው። ፨ "ኢስነይን" اِثْنَيْن‎ ማለት "ሁለት" ማለት ሲሆን "ሰኞ" ማለት ነው፥ "ሰኞ" ማለት "ሰነየ" ማለትም "ደገመ" ከሚል የመጣ ሲሆን "ሁለተኛ" ማለት ነው። አሏህ በምድር ከበላይዋ የረጉ ጋራዎችን አደረገ፥ በውስጧም ባረከ፦ 42፥10 በእርሷ ከበላይዋ የረጉ ጋራዎችን አደረገ፥ በውስጧም ባረከ፡፡ وَجَعَلَ فِيهَا رَوَٰسِىَ مِن فَوْقِهَا وَبَٰرَكَ فِيهَا "ባረከ" بَٰرَكَ ማለት "ባረከ" ማለት ሲሆን በውስጧም ምግቦችዋን በአራት ቀናት ውሰጥ ለጠያቂዎች ትክክል ሲኾኑ ወሰነ፦ 42፥10 "በውስጧም ምግቦችዋን በአራት ቀናት ውሰጥ ለጠያቂዎች ትክክል ሲኾኑ ወሰነ"፡፡ وَقَدَّرَ فِيهَآ أَقْوَٰتَهَا فِىٓ أَرْبَعَةِ أَيَّامٍۢ سَوَآءًۭ لِّلسَّآئِلِينَ "በአራት ቀናት ውሰጥ ለጠያቂዎች ትክክል ሲኾኑ ወሰነ" አለ እንጂ "በአራት ቀናት ውሰጥ ለጠያቂዎች ትክክል ሲኾኑ ፈጠረ" አላለም፥ "ወሰነ" ለሚለው የገባው ቃል "ቀደረ" قَدَّرَ ሲሆን "መጠነ" "አዘጋጀ" በሚል ይመጣል፦ 80፥19 ከፍትወት ጠብታ ፈጠረው እና መጠነው፡፡ مِن نُّطْفَةٍ خَلَقَهُ فَقَدَّرَهُ 25፥2 ነገሩንም ሁሉ የፈጠረ እና በትክክልም ያዘጋጀው ነው፡፡ وَخَلَقَ كُلَّ شَيْءٍ فَقَدَّرَهُ تَقْدِيرًا እነዚህ አናቅጽ ላይ "ፈጠረ" ለሚለው የገባው ቃል "ኸለቀ" خَلَقَ ሲሆን "መጠነ" "አዘጋጀ" ለሚለው የገባው ቃል ግን "ቀደረ" قَدَّرَ ነው፥ በአራት ቀናት የመጠነው እና ያዘጋጀው ምግቧን እንጂ ፈጠረ አይልም። ምድርን የፈጠረበት 2 ቀናት እና ምግቧን የወሰነበትን 4 ቀናት ደምራችሁ 6 ቀናት ብላችሁ ለማጋጨት የሞከራችሁት ሙከራ ፉርሽ ሆኗል። ሲጀመር "ተዳኹል" تَدَاخُل የሚለው ቃል "ተዳኸለ" تَدَاخَلَ ማለትም "ተጠላለፈ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "መጠላለፍ"intersection" ማለት ነው፥ አራት ቀናት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ተዳኹል የሆኑት "አል አሐድ" ٱلْأحَد "አል ኢስነይን" ٱلْاِثْنَيْن‎ "አል ሱላሳእ" ٱلْثُّلَاثَاء "አል አርቢዓእ" أَرْبِعَاء ናቸው፦ ተፍሢሩል ጀላለይን 41፥10 "በአራት ሙሉ ቀናት በሌላ አነጋገር በውስጧ ያለው የተራሮች አቀማመጥ ከሥስተኛው እና ከአራተኛው ቀን ጋር ተያይዞ የተከናወነው በትክክል "ሠዋእ" በተሳቢ ምክንያቱም ግሣዊ ስም ነው፥ አራቱ ቀናት ያነሱም ያልበዙም ለጠያቂዎች ሁሉ ስለ ምድር አፈጣጠር እና በውስጧ ስላለው ሁሉ በትክክል አራት ነበሩ"። "ሠዋእ" سَوَآء ማለት "በትክክል" ማለት ሲሆን በሰዋስው አወቃቀር አራት ቀናት በሁለት ቀናት ውስጥ ተለጣጥፎ"overlap" የመጣ ነው። ፨ "ሱላሳእ" ثُّلَاثَاء ማለት "ሦስት" ማለት ሲሆን "ማክሰኞ" ማለት ነው። "ማክሰኞ" ማለት "ማግስት" ማለት ነው፥ የእሁድ ማግስት "ሦስተኛ" ቀን ነው። ፨ "አርቢዓእ" أَرْبِعَاء ማለት "አራት" ማለት ሲሆን "ረቡዕ" ማለት ነው፥ "ረቡዕ" ማለት "ረበዓ" ከሚል የመጣ ሲሆን "አራተኛ" ማለት ነው። አምላካችን አሏህ ምድርን በፈጠረበት ጊዜ ሰማይን ጋዝ አርጎ ፈጠራት፥ ሰማይ የተገነባችበት ጋዝ ምድር በተፈጠረች ጊዜ ከእርሷ የሚወጣውን ጋዝ ነበረ፦ 79፥27 ባፈጣጠር እናንተ ይበልጥ የበረታችሁ ናችሁን? ወይንስ ሰማይ? አሏህ ገነባት፡፡ أَأَنتُمْ أَشَدُّ خَلْقًا أَمِ السَّمَاءُ ۚ بَنَاهَا ተፍሢር ኢብኑ ከሲር 42፥11 እርሱ(ጋዙ) ምድር በተፈጠረች ጊዜ ከእርሷ የሚወጣው ጭስ ነው"። وهو : بخار الماء المتصاعد منه حين خلقت الأرض “ጭስ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ዱኻን” دُخَان ሲሆን “ጋዝ”gas" ማለት ነው፥ ሰማይ በጋዝ ደረጃ እያለች አሏህ ለሰማይ እና ለምድር፦ «ወዳችሁም ኾነ ወይም ጠልታችሁ ኑ» አላቸው፡፡ እነርሱም፦ «ታዛዦች ኾነን መጣን» አሉ፦ 42፥11 "ከዚያም ወደ ሰማይ እርሷ ጭስ ኾና ሳለች አሰበ፡፡ ለእርሷም ለምድርም «ወዳችሁም ኾነ ወይም ጠልታችሁ ኑ» አላቸው፡፡ «ታዛዦች ኾነን መጣን» አሉ፡፡ ثُمَّ ٱسْتَوَىٰٓ إِلَى ٱلسَّمَآءِ وَهِىَ دُخَانٌۭ فَقَالَ لَهَا وَلِلْأَرْضِ ٱئْتِيَا طَوْعًا أَوْ كَرْهًۭا قَالَتَآ أَتَيْنَا طَآئِعِينَ ኢሻላህ ይቀጥላል..... ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Show all...
ይህ የወንድም ሙከሚል ቻናል ነው። ጎራ ይበሉ፦ ttps://t.me/mukamil12/1488
Show all...
ሙቀረቡን በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 56፥11 እነዚያ ባለሟሎቹ ናቸው፡፡ أُولَـٰئِكَ الْمُقَرَّبُونَ "ሙቀረብ" مُقَرَّب የሚለው ቃል "ቀሪበ" قَرِبَ ማለትም "ቀረበ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ቀራቢ" "ባለሟል" ማለት ነው፥ "ሙቀረቡን" مُقَرَّبُون ወይም "ሙቀረቢን" مُقَرَّبِين ደግሞ የሙቀረብ ብዙ ቁጥር ሲሆን "ቀራቢዎች" "ባለሟሎች" ማለት ነው። ከአስሓቡል የሚን ለበጎ ሥራ ቀዳሚዎቹ ለገነት ቀዳሚዎች ሲሆኑ እነርሱ አሏህ ዘንድ "ሙቀረቡን" ናቸው፦ 56፥11 እነዚያ ባለሟሎቹ ናቸው፡፡ أُولَـٰئِكَ الْمُقَرَّبُونَ የእውነተኞቹ ምእምናን መጽሐፍ በዒሊዮን ውስጥ ሲሆን እነርሱም "ሙቀረቡን" ናቸው፦ 83፥21 "ባለሟልዎቹ" ይጣዱታል፡፡ يَشْهَدُهُ الْمُقَرَّبُونَ 83፥28 "ባለሟሎቹ" ከእርሷ የሚጠጡላት ምንጭ ናት፡፡ عَيْنًا يَشْرَبُ بِهَا الْمُقَرَّبُونَ አንድ አማኝ ካመነ በኃላ የሚሠራው መልካም ሥራ ወደ አሏህ መቃረቢያ ሲሆን "ቁርባን" ይባላል፥ "ቁርባን" قُرْبَان ማለት "መቃረቢያ" ማለት ነው፦ 5፥35 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አሏህን ፍሩ! ወደ እርሱም መቃረቢያ መልካም ሥራን ፈልጉ፡፡ ትድኑ ዘንድም በእርሱ መንገድ ታገሉ፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ وَابْتَغُوا إِلَيْهِ الْوَسِيلَةَ وَجَاهِدُوا فِي سَبِيلِهِ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ 9፥99 ከአዕራቦችም በአሏህ እና በመጨረሻው ቀን የሚያምን፣ የሚሰጣቸውን ምጽዋቶች አሏህ ዘንድ መቃረቢያዎች እና ወደ መልእክተኛው ጸሎቶች መዳረሻ አድርጎ የሚይዝ ሰው አለ፡፡ ንቁ! እርሷ ለእነርሱ በእርግጥ አቃራቢ ናት፥ አሏህ በችሮታው ውስጥ (በገነቱ) በእርግጥ ያስገባቸዋል፡፡ አሏህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡ وَمِنَ الْأَعْرَابِ مَن يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ وَيَتَّخِذُ مَا يُنفِقُ قُرُبَاتٍ عِندَ اللَّهِ وَصَلَوَاتِ الرَّسُولِ ۚ أَلَا إِنَّهَا قُرْبَةٌ لَّهُمْ ۚ سَيُدْخِلُهُمُ اللَّهُ فِي رَحْمَتِهِ ۗ إِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ "አዕራብ" أَعْرَاب ማለት "ገጠሬ" ማለት ሲሆን ከዐረብ ገጠሬዎች በአሏህ እና በመጨረሻው ቀን አምነው የሚሰጣቸውን ምጽዋቶች አሏህ ዘንድ መቃረቢያዎች አድርገው የሚይዙ ሰዎች አሉ፥ ስለዚህ አሏህ ዘንድ ከሰዎች መካከል ሙቀረቡን አሉ። በተመሳሳይ መላእክት የአሏህ ባመሟሎች ስለሆኑ "ሙቀረቢን" مُقَرَّبِين ተብለዋል፦ 4፥172 አልመሢሕ ለአሏህ ባሪያ ከመኾን ፈጽሞ አይጠየፍም፡፡ "ቀራቢዎች" የኾኑት መላእክት አይጠየፉም፡፡ لَّن يَسْتَنكِفَ الْمَسِيحُ أَن يَكُونَ عَبْدًا لِّلَّهِ وَلَا الْمَلَائِكَةُ الْمُقَرَّبُونَ መላእክት ወደ መርየም መጥተው ለመርየም ያሏት "ባለሟል በኾነ ልጅ" ሳይሆን "ከባለሟሎችም በኾነ ልጅ" የሚል ነው፦ 3፥45 መላእክት ያሉትን አስታውስ፡- «መርየም ሆይ! አሏህ ከእርሱ በኾነው ቃል ስሙ አልመሢሕ ዒሣ የመርየም ልጅ በዚህ ዓለም እና በመጨረሻውም ዓለም የተከበረ ከባለሟሎችም በኾነ ልጅ ያበስርሻል»። إِذْ قَالَتِ الْمَلَائِكَةُ يَا مَرْيَمُ إِنَّ اللَّهَ يُبَشِّرُكِ بِكَلِمَةٍ مِّنْهُ اسْمُهُ الْمَسِيحُ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ وَجِيهًا فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ وَمِنَ الْمُقَرَّبِينَ እዚህ አንቀጽ ላይ "አል ሙቀረቢን" الْمُقَرَّبِين የተባሉ ከላይ እንደተገለጸው የአሏህ ባሮች ሲሆኑ ይህ አንቀጽ ጭራሽኑ ከሙቃሪቢን መካከል አንዱ ዒሣ መሆኑን ቁልጭ እና ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው፥ "ዒሣ ብቻ "ባለሟል" ነው" የሚል ሽታው ቁርኣን ላይ የለም። አምላካችን አሏህ ሙቀረቡን ከሚላቸው ባሮቹ ያድርገን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Show all...
የሥላሴ እሳቤ "ድጋሚ ይታተም" ብላችሁ በጠየቃችሁት መሠረት ድጋሚ ታትሟል። የምትፈልጉ +251920781016 ዐብዱ ረሕማን ብላችሁ ደውላችሁ ውሰዱ!
Show all...
ቀጥተኛው መንገድ በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 36፥4 "በቀጥታም መንገድ ላይ ነህ"፡፡ عَلَىٰ صِرَٰطٍۢ مُّسْتَقِيمٍۢ "ሲሯጥ" صِرَٰط ማለት በመነሻ እና በመዳረሻ መካከል ያለ "መንገድ" ማለት ሲሆን እዚህ ዐውድ ላይ "መንገድ" እያልን የምንጦምረው እማሬአዊ የሆነውን የአስፋት መንገድ ሳይሆን ወደ ጀነት የሚያደርሰውን ፍካሬአዊ የሆነውን መንገድ ነው። አምላካችን አሏህን በብቸኝነት ማምለክ ወደ ጀነት የሚያደርስ "ቀጥተኛው መንገድ" ነው፦ 36፥61 "አምልኩኝ! ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው" በማለትም አላዘዝኩምን? وَأَنِ ٱعْبُدُونِى ۚ هَٰذَا صِرَٰطٌۭ مُّسْتَقِيمٌۭ "ይህ" የሚለው አመልካች ተውላጠ ስም "አምልኩኝ" የሚለውን ቃል አመላካች ነው። ዒሣም በተልኮው አሏህን በብቸኝነት ማምለክ "ቀጥተኛ መንገድ" እንደሆነ አበክሮ እና አዘክሮ ነግሮናል፦ 3፥51 «አሏህ ጌታዬ እና ጌታችሁ ነዉና "አምልኩት! ይህ "ቀጥተኛ መንገድ" ነው»። አላቸዉ። إِنَّ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبُّكُمْ فَٱعْبُدُوهُ ۗ هَٰذَا صِرَٰطٌۭ مُّسْتَقِيمٌۭ 43፥64 «አሏህ ጌታዬ ጌታችሁም ነውና "አምልኩት! ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው»። إِنَّ اللَّهَ هُوَ رَبِّي وَرَبُّكُمْ فَاعْبُدُوهُ ۚ هَـٰذَا صِرَاطٌ مُّسْتَقِيمٌ እነዚህም አናቅጽ ላይ "ይህ" የሚለው አመልካች ተውላጠ ስም "አምልኩት" የሚለውን ቃል አመላካች ነው። "ሙስተቂም" مُّسْتَقِيم ማለት "ቀጥተኛ" ማለት ሲሆን አምላካችን አሏህን በብቸኝነት ማምለክ ቀጥተኛ መንገድ ነው፥ ከዚያ ውጪ ያሉት መንገዶች የጥመት መንገዶች ናቸው፦ 6፥153 «ይህም ቀጥተኛ ሲኾን መንገዴ ነው፤ ተከተሉትም፡፡ የጥመት መንገዶችንም አትከተሉ፡፡ ከቀጥተኛው መንገዱ እናንተን ይለያዩዋችኋልና» በላቸው። وَأَنَّ هَـٰذَا صِرَاطِي مُسْتَقِيمًا فَاتَّبِعُوهُ ۖ وَلَا تَتَّبِعُوا السُّبُلَ فَتَفَرَّقَ بِكُمْ عَن سَبِيلِهِ ይህ አንዱን አምላክ በብቸንነት ማምለክ ለኢብራሂም የተገለጠ የኢብራሂም መንገድ ነው፥ አምላካችን አሏህ የኢብራሂምን መንገድ መርቶናል፦ 6፥161 «እኔ ጌታዬ ወደ "ቀጥተኛው መንገድ" ትክክለኛን ሃይማኖት ወደ እውነት አዘንባይ ሲኾን የአብርሃምን መንገድ መራኝ፡፡ እርሱም ከአጋሪዎቹ አልነበረም» በል፡፡ قُلْ إِنَّنِى هَدَىٰنِى رَبِّىٓ إِلَىٰ صِرَٰطٍۢ مُّسْتَقِيمٍۢ دِينًۭا قِيَمًۭا مِّلَّةَ إِبْرَٰهِيمَ حَنِيفًۭا ۚ وَمَا كَانَ مِنَ ٱلْمُشْرِكِينَ አሁንም "ቀጥተኛው መንገድ" የሚለው ኃይለ ቃል ይሰመርበት! አንድ ሰው ከነበረበት ሺርክ እና ኩፍር ወደ አምላካችን አሏህ በንስሓ ከተመለሰ አሏህ በንስሓ የሚመለውን ሰው ወደ እርሱ ይመራዋል፦ 42፥13 አሏህ የሚሻውን ሰው ወደ እርሱ ይመርጣል፡፡ "የሚመለስንም ሰው ወደ እርሱ ይመራል"፡፡ اللَّهُ يَجْتَبِي إِلَيْهِ مَن يَشَاءُ وَيَهْدِي إِلَيْهِ مَن يُنِيبُ "የሚመለስንም ሰው ወደ እርሱ ይመራል" የሚለው በአጽንዖት ይሰመርበት! አንድ ሙሥሊም በቀጥተኛው መንገድ ላይ ስለሆነ አምላካችን አሏህ፦ "በቀጥታ መንገድ ላይ ነህ" ብሏል፦ 36፥4 "በቀጥታም መንገድ ላይ ነህ"፡፡ عَلَىٰ صِرَٰطٍۢ مُّسْتَقِيمٍۢ 43፥43 ያንንም ወደ አንተ የተወረደልህን አጥብቀህ ያዝ! አንተ "በቀጥተኛው መንገድ ላይ ነህና"።فَاسْتَمْسِكْ بِالَّذِي أُوحِيَ إِلَيْكَ ۖ إِنَّكَ عَلَىٰ صِرَاطٍ مُّسْتَقِيمٍ ሙሥሊም በቀጥተኛው መንገድ እንደሆነ በቁና ጥቅስ ማቅረብ ይቻላል። አንድ ዳዒ ሙሥሊም በቀጥተኛ መንገድ ስለሆነ እና ይህም ቀጥተኛ መንገድ አሏህን በብቸኝነት ማምለክ እንደሆነ ተረድቶ ሰዎችን ወደ ቀጥተኛው መንገድ ይጣራል፦ 23፥73 አንተም ወደ "ቀጥተኛው መንገድ" በእርግጥ ትጠራቸዋለህ። وَإِنَّكَ لَتَدْعُوهُمْ إِلَىٰ صِرَٰطٍۢ مُّسْتَقِيمٍۢ 16፥125 "ወደ ጌታህ መንገድ" በጥበብ እና በመልካም ግሳጼ ጥራ፡፡ ادْعُ إِلَىٰ سَبِيلِ رَبِّكَ بِالْحِكْمَةِ وَالْمَوْعِظَةِ الْحَسَنَةِ አንድ ሙሥሊም በቀጥተኛ መንገድ ላይ ባይሆን ኖሮ ወደ ቀጥተኛ መንገድ መጥራቱ ትርጉም አልባ ይሆን ነበር። ይህ ቀጥተኛ መንገድ መነሻው ዱንያህ ሲሆን መዳረሻው አኺራ ነው፥ አሁን ጉዞ ላይ ነን። ለምሳሌ፦ እኔ ፒያሳ መሄድ ፈልጌ የፒያሳን መንገድ መነሻውን አየር ጤና አንድ ሰው ከመራኝ በኃላ መንገዱ በጉዞ ላይ ጦር ኃይሎች ጋር ስደርስ ወደ ኮልፌ መንገዱት እንዳልስት፣ ልደታ ጋር ስደርስ ወደ መርካቶ አሊያ ወደ ኦልድ ኤር ፓርት መንገዱን እንዳልስት፣ ሜክሲኮ ጋር ስደርስ ወደ መካኒሳ አሊያም ወደ ተክለ ሃይማኖት መንገዱን እንዳልስት፣ ብሔራዊ ጋር ስደርስ መንገዱን ወደ ፍሉ ውኃ እንዳልስት እስከመጨረሻው ምሪት ያስፈልገኛል። በተመሳሳይ ይህ ቀጥተኛ መንገድ መነሻውን አሏህ ከመራን በኃላ በጉዞ ላይ እያለን ከመንገዱ እንዳንወጣ ምሪት እስከመጨረሻው ለማግኘት አሏህን "ቀጥተኛውን መንገድ ምራን" እያልን በሶላት ላይ ስንቆም እንጠይቀዋለን፥ አሏህም እነዚያን ያመኑትን ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ መሪ ነው፦ 1፥6 "ቀጥተኛውን መንገድ ምራን"። ٱهْدِنَا ٱلصِّرَٰطَ ٱلْمُسْتَقِيمَ 22፥54 አሏህ እነዚያን ያመኑትን ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ "መሪ" ነው፡፡ وَإِنَّ اللَّهَ لَهَادِ الَّذِينَ آمَنُوا إِلَىٰ صِرَاطٍ مُّسْتَقِيمٍ አምላካችን አሏህ ሰዎችን ወደ ቀጥተኛው መንገድ የምንጠራ ዳዒዎች ያድርገን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Show all...
"አንቀጾቻችን በተነበቡ ጊዜ ኢማን የሚጨምሩላቸው" የሚለው ይሰመርበት! በኢማም አቡ መንሱር አል ማቱሪዲይ የተቀመረው ማቱሪዲያህ የሚባለው ስሑት ዐቂዳህ፦ "ኢማን የማይጨምር እና የማይቀንስ ቋሚ ነው" የሚል እሳቤ በዚህ ጥቅስ ድባቅ ይገባል። ኢማኑ በአሏህ አንቀጾች እየጨመረ የሚሄድ ሙእሚን አሏህ ዘንድ ደረጃዎች አሉት፦ 8፥4 እነዚያ በእውነት አማኞች እነርሱ ብቻ ናቸው፡፡ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ደረጃዎች ምሕረት እና የከበረ ሲሳይም አላቸው፡፡ أُولَـٰئِكَ هُمُ الْمُؤْمِنُونَ حَقًّا ۚ لَّهُمْ دَرَجَاتٌ عِندَ رَبِّهِمْ وَمَغْفِرَةٌ وَرِزْقٌ كَرِيمٌ "ደረጃት" دَرَجَات የሚለው ቃል "ደረጃህ" دَرَجَة ለሚለው ብዙ ቁጥር ሲሆን አሏህ ዘንድ ጀናህ መቶ ጀረዎች አሏት፥ ተጀናህ ከፍተኛ ደረጃዋ ፊርደውሥ ነው፦ ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 37, ሐዲስ 4474 ሙዓዝ ኢብኑ ጀበል የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ ሲሉ ሰማው ብሎ እንደተረከው፦ "እርሳቸውም አሉ፦ "ጀናህ መቶ ጀረዎች አሏት፥ ደረጃዎቿም ያላቸው እርቀት ልክ የሰማይ እና የምድር እርቀት ያክል ነው። ከፍተኛ ደረጃዋ ፊርደውሥ ነው፥ أَنَّ مُعَاذَ بْنَ جَبَلٍ، قَالَ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ يَقُولُ ‏ "‏ الْجَنَّةُ مِائَةُ دَرَجَةٍ كُلُّ دَرَجَةٍ مِنْهَا مَا بَيْنَ السَّمَاءِ وَالأَرْضِ وَإِنَّ أَعْلاَهَا الْفِرْدَوْسُ አማኞች በእምነት የሚሠሩት መልካም ሥራ በሚሠሩት መልካም ሥራ መጠን የተለያየ ደረጃዎችን በጀነት ውስጥ ያገኙበታል፦ 20፥75 በጎ ሥራዎችን በእርግጥ የሠራ ምእመን ኾኖ የመጣውም ሰው እነዚያ ለእነርሱ ከፍተኛ ደረጃዎች አላቸው፡፡ وَمَن يَأْتِهِ مُؤْمِنًا قَدْ عَمِلَ الصَّالِحَاتِ فَأُولَـٰئِكَ لَهُمُ الدَّرَجَاتُ الْعُلَىٰ 3፥163 እነርሱ አላህ ዘንድ ባለ ደረጃዎች ናቸው፡፡ አላህም የሚሠሩትን ነገር ተመልካች ነው፡፡ هُمْ دَرَجَاتٌ عِندَ اللَّهِ ۗ وَاللَّهُ بَصِيرٌ بِمَا يَعْمَلُونَ 6፥132 ለሁሉም ከሠሩት ሥራ ደረጃዎች አላቸው፡፡ ጌታህም ከሚሠሩት ሁሉ ዘንጊ አይደለም፡፡ وَلِكُلٍّ دَرَجَاتٌ مِّمَّا عَمِلُوا ۚ وَمَا رَبُّكَ بِغَافِلٍ عَمَّا يَعْمَلُونَ 46፥19 ለሁሉም ከሠሩት ሥራ ደረጃዎች አላቸው፡፡ ሥራዎቻቸውንም ይሞላላቸው ዘንድ ይህንን መነዳቸው፥ እነርሱም አይበደሉም፡፡ وَلِكُلٍّ دَرَجَاتٌ مِّمَّا عَمِلُوا ۖ وَلِيُوَفِّيَهُمْ أَعْمَالَهُمْ وَهُمْ لَا يُظْلَمُونَ "ጀናህ" جَنَّة በ "ታ" ة መርቡጧህ በነጠላ ሲሆን አጠቃላይ ጀነትን ያመለክታል፥ በአጠቃላዩ ጀነት ውስጥ ለመግባት ቁልፉ "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" ሲሆን በጀነት ውስጥ ያሉትን ጀረጃዎች ውስጥ ለመግባት እና ለመመንዳት መልካም ሥራ ያስፈልጋል። በጀነት ውስጥ ያሉት መቶ የተለያዩ ደረጃዎች እራሱ "ጀናት" جَنَّات‎ ተብለዋል፥ "ጀናት" جَنَّات‎ በ "ታ" ت መፍቱሓህ ሲሆን በብዜት "ጀነቶች" "ገነቶች" ማለት ነው። እነዚህ የተለያየ ደረጃዎች የሆኑ ጀነቶች አምነው መልካም ለሚሠሩ የሚሰጥ ምንዳ፣ ትሩፋት፣ ወሮታ፣ ስርጉት፣ ትርሲት ነው፦ 31፥8 እነዚያ ያመኑ እና መልካሞችንም የሠሩ ለእነርሱ የጸጋ "ገነቶች" አላቸው፡፡ إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ لَهُمْ جَنَّاتُ النَّعِيمِ እዚህ አንቀጽ ላይ "ገነቶች" ለሚለው የገባው በብዙ ቁጥር "ጀናት" جَنَّات‎ እንደሆነ ልብ አድርግ! እያንዳንዱ ደረጃ "ጀነቱል ዐድን" جَنَّةُ العَدْن "ጀነቱ አን-ነዒም" جَنَّةُ النَّعِيمِ "ጀነቱል መእዋ" جَنَّةُ المَأْوَىٰ "ጀነቱል ፊርደውሥ" جَنَّةُ الفِرْدَوْسُ እየተባለ ይጠራል። አምላካችን አሏህ የኢማንን ኃይል ተረድተው መልካም ሥራ ከሚሠሩ ሙእሚን ያድርገን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Show all...
ቁወቱል ኢማን በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 92፥6 በመልካሚቱም እምነት ያረጋገጠ። وَصَدَّقَ بِالْحُسْنَىٰ "ቁዋህ" قُوَّة የሚለው ቃል "ቀዊየ" قَوِيَ ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ኃይል" ማለት ነው፥ "ኢማን" إِيمَٰن የሚለው ቃል "አሚነ" أَمِنَ ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "እምነት" ማለት ነው። በጥቅሉ "ቁወቱል ኢማን" قُوَّة الإِيمَان ማለት "የእምነት ኃይል" ማለት ነው። "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" لَا إِلَـٰهَ إِلَّا اللَّه ትልቁ የኢማን ቅርንጫፍ ነው፦ ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 60 አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ ”ኢማን ከሰባ ወይም ከስልሳ በላይ ቅርንጫፎች አሉት፥ ትልቁ ቅርንጫፍ “ላ ኢላሀ ኢለሏህ” ማለት ነው። ትንሹ ደግሞ ከመንገድ ላይ እንቅፋት ማስወገድ ነው፥ ሐያእ የኢማን ቅርንጫፍ ነው"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الإِيمَانُ بِضْعٌ وَسَبْعُونَ أَوْ بِضْعٌ وَسِتُّونَ شُعْبَةً فَأَفْضَلُهَا قَوْلُ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ وَأَدْنَاهَا إِمَاطَةُ الأَذَى عَنِ الطَّرِيقِ وَالْحَيَاءُ شُعْبَةٌ مِنَ الإِيمَانِ ‏ "ሐያእ" حَيَاء ማለት "ዓይናፋርነት" "ጨዋነት" ማለት ነው፥ ሐያእ ከኢማን ነው። ኢማን ደግሞ ወደ ጀነት ይመራል፦ ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 27, ሐዲስ 115 አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ "ሐያእ ከኢማን ነው፥ ኢማን ደግሞ ወደ ጀነት ይመራል። ብልግና ከብሉሽነት ነው፥ ብሉሽነት ወደ እሳት ይመራል”። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الْحَيَاءُ مِنَ الإِيمَانِ وَالإِيمَانُ فِي الْجَنَّةِ وَالْبَذَاءُ مِنَ الْجَفَاءِ وَالْجَفَاءُ فِي النَّارِ ‏ "በዛእ" بَذَاء ማለት ደግሞ "ዓይናውጣነት" "ብልግና" ማለት ነው፥ ብልግና ከብሉሽነት(ኩፍር) ሲሆን ኩፍር ወደ እሳት ይመራል። "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" መልካሚቱም እምነት ናት፦ 92፥6 በመልካሚቱም እምነት ያረጋገጠ። وَصَدَّقَ بِالْحُسْنَىٰ 92፥7 ለገሪቱ ሥራ እናዘጋጀዋለን፡፡ فَسَنُيَسِّرُهُ لِلْيُسْرَىٰ "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" لَا إِلَـٰهَ إِلَّا اللَّه በምትባለው መልካሚቱም እምነት ያረጋገጠ አሏህ መልካም ሥራን ያገራለታል፥ "ዩሥር" يُسْرَىٰ ማለት "ቀላል" "ገር" "መልካም" ማለት ሲሆን ኢማን ወደ ጀነት የሚያመራው በመልካም ሥራ ነው። "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" لَا إِلَـٰهَ إِلَّا اللَّه የምትለዋን መልካሚቱን እምነት ሰምቶ የካደ አሏህ መልካም ሥራን ያከብድበታል፦ 92፥9 በመልካሚቱ እምነት ያሰተባበለም። وَكَذَّبَ بِالْحُسْنَىٰ 92፥10 ለክፉይቱ ሥራ እናዘጋጀዋለን፡፡ فَسَنُيَسِّرُهُ لِلْعُسْرَىٰ "ዑሥራ" عُسْرَىٰ ማለት "ከባድ" "ሸካራ" "ክፉ" ማለት ሲሆን ኩፍር ወደ እሳት የሚመራው በመጥፎ ሥራ ነው። ኢማን የሚጨምር እና የሚቀንስ ነው፦ 8፥2 ፍጹም ምእምናን እነዚያ አሏህ በተወሳ ጊዜ ልቦቻቸው የሚፈሩት፣ በእነርሱም ላይ አንቀጾቻችን በተነበቡ ጊዜ ኢማን የሚጨምሩላቸው፣ በጌታቸውም ላይ ብቻ የሚመኩት ናቸው፡፡ إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ الَّذِينَ إِذَا ذُكِرَ اللَّهُ وَجِلَتْ قُلُوبُهُمْ وَإِذَا تُلِيَتْ عَلَيْهِمْ آيَاتُهُ زَادَتْهُمْ إِيمَانًا وَعَلَىٰ رَبِّهِمْ يَتَوَكَّلُونَ
Show all...
31፥8 እነዚያ ያመኑ እና መልካሞችንም የሠሩ ለእነርሱ የጸጋ "ገነቶች" አላቸው፡፡ إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ لَهُمْ جَنَّاتُ النَّعِيمِ እዚህ አንቀጽ ላይ "ገነቶች" ለሚለው የገባው በብዙ ቁጥር "ጀናት" جَنَّات‎ እንደሆነ ልብ አድርግ! እያንዳንዱ ደረጃ "ጀነቱል ዐድን" جَنَّةُ العَدْن "ጀነቱ አን-ነዒም" جَنَّةُ النَّعِيمِ "ጀነቱል መእዋ" جَنَّةُ المَأْوَىٰ "ጀነቱል ፊርደውሥ" جَنَّةُ الفِرْدَوْسُ እየተባለ ይጠራል። አምላካችን አሏህ የኢማንን ኃይል ተረድተው መልካም ሥራ ከሚሠሩ ሙእሚን ያድርገን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Show all...
ቁወቱል ኢማን በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 92፥6 በመልካሚቱም እምነት ያረጋገጠ። وَصَدَّقَ بِالْحُسْنَىٰ "ቁዋህ" قُوَّة የሚለው ቃል "ቀዊየ" قَوِيَ ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ኃይል" ማለት ነው፥ "ኢማን" إِيمَٰن የሚለው ቃል "አሚነ" أَمِنَ ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "እምነት" ማለት ነው። በጥቅሉ "ቁወቱል ኢማን" قُوَّة الإِيمَان ማለት "የእምነት ኃይል" ማለት ነው። "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" لَا إِلَـٰهَ إِلَّا اللَّه ትልቁ የኢማን ቅርንጫፍ ነው፦ ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 60 አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ ”ኢማን ከሰባ ወይም ከስልሳ በላይ ቅርንጫፎች አሉት፥ ትልቁ ቅርንጫፍ “ላ ኢላሀ ኢለሏህ” ማለት ነው። ትንሹ ደግሞ ከመንገድ ላይ እንቅፋት ማስወገድ ነው፥ ሐያእ የኢማን ቅርንጫፍ ነው"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الإِيمَانُ بِضْعٌ وَسَبْعُونَ أَوْ بِضْعٌ وَسِتُّونَ شُعْبَةً فَأَفْضَلُهَا قَوْلُ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ وَأَدْنَاهَا إِمَاطَةُ الأَذَى عَنِ الطَّرِيقِ وَالْحَيَاءُ شُعْبَةٌ مِنَ الإِيمَانِ ‏ "ሐያእ" حَيَاء ማለት "ዓይናፋርነት" "ጨዋነት" ማለት ነው፥ ሐያእ ከኢማን ነው። ኢማን ደግሞ ወደ ጀነት ይመራል፦ ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 27, ሐዲስ 115 አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ "ሐያእ ከኢማን ነው፥ ኢማን ደግሞ ወደ ጀነት ይመራል። ብልግና ከብሉሽነት ነው፥ ብሉሽነት ወደ እሳት ይመራል”። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الْحَيَاءُ مِنَ الإِيمَانِ وَالإِيمَانُ فِي الْجَنَّةِ وَالْبَذَاءُ مِنَ الْجَفَاءِ وَالْجَفَاءُ فِي النَّارِ ‏ "በዛእ" بَذَاء ማለት ደግሞ "ዓይናውጣነት" "ብልግና" ማለት ነው፥ ብልግና ከብሉሽነት(ኩፍር) ሲሆን ኩፍር ወደ እሳት ይመራል። "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" መልካሚቱም እምነት ናት፦ 92፥6 በመልካሚቱም እምነት ያረጋገጠ። وَصَدَّقَ بِالْحُسْنَىٰ 92፥7 ለገሪቱ ሥራ እናዘጋጀዋለን፡፡ فَسَنُيَسِّرُهُ لِلْيُسْرَىٰ "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" لَا إِلَـٰهَ إِلَّا اللَّه በምትባለው መልካሚቱም እምነት ያረጋገጠ አሏህ መልካም ሥራን ያገራለታል፥ "ዩሥር" يُسْرَىٰ ማለት "ቀላል" "ገር" "መልካም" ማለት ሲሆን ኢማን ወደ ጀነት የሚያመራው በመልካም ሥራ ነው። "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" لَا إِلَـٰهَ إِلَّا اللَّه የምትለዋን መልካሚቱን እምነት ሰምቶ የካደ አሏህ መልካም ሥራን ያከብድበታል፦ 92፥9 በመልካሚቱ እምነት ያሰተባበለም። وَكَذَّبَ بِالْحُسْنَىٰ 92፥10 ለክፉይቱ ሥራ እናዘጋጀዋለን፡፡ فَسَنُيَسِّرُهُ لِلْعُسْرَىٰ "ዑሥራ" عُسْرَىٰ ማለት "ከባድ" "ሸካራ" "ክፉ" ማለት ሲሆን ኩፍር ወደ እሳት የሚመራው በመጥፎ ሥራ ነው። ኢማን የሚጨምር እና የሚቀንስ ነው፦ 8፥2 ፍጹም ምእምናን እነዚያ አሏህ በተወሳ ጊዜ ልቦቻቸው የሚፈሩት፣ በእነርሱም ላይ አንቀጾቻችን በተነበቡ ጊዜ ኢማን የሚጨምሩላቸው፣ በጌታቸውም ላይ ብቻ የሚመኩት ናቸው፡፡ إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ الَّذِينَ إِذَا ذُكِرَ اللَّهُ وَجِلَتْ قُلُوبُهُمْ وَإِذَا تُلِيَتْ عَلَيْهِمْ آيَاتُهُ زَادَتْهُمْ إِيمَانًا وَعَلَىٰ رَبِّهِمْ يَتَوَكَّلُونَ "አንቀጾቻችን በተነበቡ ጊዜ ኢማን የሚጨምሩላቸው" የሚለው ይሰመርበት! በኢማም አቡ መንሱር አል ማቱሪዲይ የተቀመረው ማቱሪዲያህ የሚባለው ስሑት ዐቂዳህ፦ "ኢማን የማይጨምር እና የማይቀንስ ቋሚ ነው" የሚል እሳቤ በዚህ ጥቅስ ድባቅ ይገባል። ኢማኑ በአሏህ አንቀጾች እየጨመረ የሚሄድ ሙእሚን አሏህ ዘንድ ደረጃዎች አሉት፦ 8፥4 እነዚያ በእውነት አማኞች እነርሱ ብቻ ናቸው፡፡ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ደረጃዎች ምሕረት እና የከበረ ሲሳይም አላቸው፡፡ أُولَـٰئِكَ هُمُ الْمُؤْمِنُونَ حَقًّا ۚ لَّهُمْ دَرَجَاتٌ عِندَ رَبِّهِمْ وَمَغْفِرَةٌ وَرِزْقٌ كَرِيمٌ "ደረጃት" دَرَجَات የሚለው ቃል "ደረጃህ" دَرَجَة ለሚለው ብዙ ቁጥር ሲሆን አሏህ ዘንድ ጀናህ መቶ ጀረዎች አሏት፥ ተጀናህ ከፍተኛ ደረጃዋ ፊርደውሥ ነው፦ ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 37, ሐዲስ 4474 ሙዓዝ ኢብኑ ጀበል የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ ሲሉ ሰማው ብሎ እንደተረከው፦ "እርሳቸውም አሉ፦ "ጀናህ መቶ ጀረዎች አሏት፥ ደረጃዎቿም ያላቸው እርቀት ልክ የሰማይ እና የምድር እርቀት ያክል ነው። ከፍተኛ ደረጃዋ ፊርደውሥ ነው፥ أَنَّ مُعَاذَ بْنَ جَبَلٍ، قَالَ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ يَقُولُ ‏ "‏ الْجَنَّةُ مِائَةُ دَرَجَةٍ كُلُّ دَرَجَةٍ مِنْهَا مَا بَيْنَ السَّمَاءِ وَالأَرْضِ وَإِنَّ أَعْلاَهَا الْفِرْدَوْسُ አማኞች በእምነት የሚሠሩት መልካም ሥራ በሚሠሩት መልካም ሥራ መጠን የተለያየ ደረጃዎችን በጀነት ውስጥ ያገኙበታል፦ 20፥75 በጎ ሥራዎችን በእርግጥ የሠራ ምእመን ኾኖ የመጣውም ሰው እነዚያ ለእነርሱ ከፍተኛ ደረጃዎች አላቸው፡፡ وَمَن يَأْتِهِ مُؤْمِنًا قَدْ عَمِلَ الصَّالِحَاتِ فَأُولَـٰئِكَ لَهُمُ الدَّرَجَاتُ الْعُلَىٰ 3፥163 እነርሱ አላህ ዘንድ ባለ ደረጃዎች ናቸው፡፡ አላህም የሚሠሩትን ነገር ተመልካች ነው፡፡ هُمْ دَرَجَاتٌ عِندَ اللَّهِ ۗ وَاللَّهُ بَصِيرٌ بِمَا يَعْمَلُونَ 6፥132 ለሁሉም ከሠሩት ሥራ ደረጃዎች አላቸው፡፡ ጌታህም ከሚሠሩት ሁሉ ዘንጊ አይደለም፡፡ وَلِكُلٍّ دَرَجَاتٌ مِّمَّا عَمِلُوا ۚ وَمَا رَبُّكَ بِغَافِلٍ عَمَّا يَعْمَلُونَ 46፥19 ለሁሉም ከሠሩት ሥራ ደረጃዎች አላቸው፡፡ ሥራዎቻቸውንም ይሞላላቸው ዘንድ ይህንን መነዳቸው፥ እነርሱም አይበደሉም፡፡ وَلِكُلٍّ دَرَجَاتٌ مِّمَّا عَمِلُوا ۖ وَلِيُوَفِّيَهُمْ أَعْمَالَهُمْ وَهُمْ لَا يُظْلَمُونَ "ጀናህ" جَنَّة በ "ታ" ة መርቡጧህ በነጠላ ሲሆን አጠቃላይ ጀነትን ያመለክታል፥ በአጠቃላዩ ጀነት ውስጥ ለመግባት ቁልፉ "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" ሲሆን በጀነት ውስጥ ያሉትን ጀረጃዎች ውስጥ ለመግባት እና ለመመንዳት መልካም ሥራ ያስፈልጋል። በጀነት ውስጥ ያሉት መቶ የተለያዩ ደረጃዎች እራሱ "ጀናት" جَنَّات‎ ተብለዋል፥ "ጀናት" جَنَّات‎ በ "ታ" ت መፍቱሓህ ሲሆን በብዜት "ጀነቶች" "ገነቶች" ማለት ነው። እነዚህ የተለያየ ደረጃዎች የሆኑ ጀነቶች አምነው መልካም ለሚሠሩ የሚሰጥ ምንዳ፣ ትሩፋት፣ ወሮታ፣ ስርጉት፣ ትርሲት ነው፦
Show all...
፨ "ገይሪ ሹሩጢይ" غَيْرِ شُرْطِيّ ማለት "ሁኔታዊ አልባ"unconditional" ማለት ሲሆን በጥቅሉ "ኢንቲኻብ ገይሪ ሹሩጢይ" اِنْتِخَاب غَيْرِ شُرْطِيّ ማለት "ሁኔታዊ አልባ ምርጫ"unconditional election" ማለት ነው። ለምሳሌ፦ አሏህ የሚሻውን ይፈጥራል፦ 28፥68 ጌታህም የሚሻውን ይፈጥራል፤ ይመርጣልም፡፡ ለእነርሱ ምርጫ የላቸውም፡፡ አሏህ ከማይግገባው ሁሉ ጠራ፡፡ ከሚያጋሯቸውም ላቀ፡፡ وَرَبُّكَ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ وَيَخْتَارُ ۗ مَا كَانَ لَهُمُ الْخِيَرَةُ ۚ سُبْحَانَ اللَّهِ وَتَعَالَىٰ عَمَّا يُشْرِكُونَ "የሚሻውን ይፈጥራል" በሚል ኃይለ ቃል "ይመርጣል" የሚለው ቃል አሏህ የሚሻውን ሰው፣ የሚሻውን እንስሳ፣ የሚሻውን አታክልት፣ የሚሻውን ማዕድን አርጎ መፍጠሩ የእርሱ ሁኔታዊ አልባ ምርጫ ነው፥ "ለእነርሱ ምርጫ የላቸውም" ማለት ፍጡራን "ይህንን ሆኜ ልፈጠር" የሚል ምርጫ የላቸውም። ወንድነት እና ሴትነት የእኛ ምርጫ ሳይሆን የእርሱ ምርጫ ብቻ ነው፦ 42፥49 የሰማያትና የምድር ንግሥና የአሏህ ነው፡፡ የሚሻውን ይፈጥራል፤ ለሚሻው ሴቶችን ይሰጣል፥ ለሚሻውም ወንዶችን ይሰጣል፡፡ لِّلَّهِ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ يَهَبُ لِمَن يَشَاءُ إِنَاثًا وَيَهَبُ لِمَن يَشَاءُ الذُّكُورَ "የሚሻውን ይፈጥራል" በሚል ኃይለ ቃል "ለሚሻው ሴቶችን ይሰጣል፥ ለሚሻውም ወንዶችን ይሰጣል" የሚለው ቃል ሴት መሆን እና ወንድ መሆን የአሏህ ሁኔታዊ አልባ ምርጫ ነው፥ የእኛ ምርጫ፣ ድርሻ፣ ፈቃድ ስለሌለበት ወንድነት እና ሴትነት ቅጣት እና ሽልማት አሊያም ተጠያቂነት የለበትም። አምላካችን አሏህ ከመላእክት ውስጥ መልእክተኞችን ይመርጣል፦ 40፥7 እነዚያ "ዙፋኑን የሚሸከሙት" እና እነዚያ በዙሪያው ያሉት በጌታቸው ምስጋና ያወድሳሉ፡፡ በእርሱም ያምናሉ፡፡ الَّذِينَ يَحْمِلُونَ الْعَرْشَ وَمَنْ حَوْلَهُ يُسَبِّحُونَ بِحَمْدِ رَبِّهِمْ وَيُؤْمِنُونَ بِهِ 22፥75 አሏህ ከመላእክት ውስጥ መልእክተኞችን ይመርጣል፥ ከሰዎችም እንደዚሁ ይመርጣል። አላህ ሰሚ ተመልካች ነው፡፡ اللَّهُ يَصْطَفِي مِنَ الْمَلَائِكَةِ رُسُلًا وَمِنَ النَّاسِ ۚ إِنَّ اللَّهَ سَمِيعٌ بَصِيرٌ "ከሩቢዩን" كَرُوبِيُّون የሚባሉት መላእክት የአሏህን ዐርሽ የሚሸከሙ ሲሆን በዐርሹ ዙሪያ ካሉት መላእክት ወደ ሰዎች የሚልካቸው መላእክት የእርሱ ሁኔታ አልባ ምርጫ ነው። "ከሰዎችም እንደዚሁ ይመርጣል" ስለሚል አሏህ ከሰዎች ለመልእክተኛነት መምረጡ ይህ የእርሱ ሁኔታ አልባ ምርጫ ነው፦ 2፥105 አሏህም በችሮታው (በነቢይነት) የሚሻውን ይመርጣል፡፡ አላህም የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው፡፡ وَاللَّهُ يَخْتَصُّ بِرَحْمَتِهِ مَن يَشَاءُ ۚ وَاللَّهُ ذُو الْفَضْلِ الْعَظِيمِ 3፥74 በችሮታው (በነቢይነት) የሚሻውን ይመርጣል፡፡ አሏህም የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው፡፡ يَخْتَصُّ بِرَحْمَتِهِ مَن يَشَاءُ ۗ وَاللَّهُ ذُو الْفَضْلِ الْعَظِيمِ አሏህ አንድ ሰው በነቢይነት ቢመርጠው ሆነ ባይመርጠው ሽልማት እና ቅጣት አሊያም ተጠያቂነት ስለሌለበት ይህ "ኢንቲኻብ ገይሪ ሹሩጢይ" اِنْتِخَاب غَيْرِ شُرْطِيّ ነው። የአሏህን ምርጫ "አሚን" ብሎ መቀበል ከአርካኑል ኢማን ክፍል የሆነውን ቀደርን መቀበል ነው፥ አሏህ የእርሱን ምርጫ "አሚን" ብለው ከሚቀበሉት ምእመናን ያርገን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Show all...
የአሏህ ምርጫ በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 42፥13 አሏህ የሚሻውን ሰው ወደ እርሱ ይመርጣል፡፡ የሚመለስንም ሰው ወደ እርሱ ይመራል፡፡ اللَّهُ يَجْتَبِي إِلَيْهِ مَن يَشَاءُ وَيَهْدِي إِلَيْهِ مَن يُنِيبُ "ኢንቲኻብ" اِنْتِخَاب ማለት "ምርጫ"election" ማለት ነው፥ ኢንቲኻብ እራሱ "ኢንቲኻብ ሹሩጢይ" اِنْتِخَاب شُرْطِيّ እና "ኢንቲኻብ ገይሪ ሹሩጢይ" اِنْتِخَاب غَيْرِ شُرْطِيّ ተብለው ለሁለት ይከፈላሉ። ፨ "ሹሩጢይ" شُرْطِيّ ማለት "ሁኔታዊ"conditional" ማለት ሲሆን በጥቅሉ "ኢንቲኻብ ሹሩጢይ" اِنْتِخَاب شُرْطِيّ ማለት "ሁኔታዊ ምርጫ"conditional election" ማለት ነው። ለምሳሌ፦ አደም በሠራው ኃጢአት "ጌታችን ሆይ! እራሳችችንን በደልን፥ ለእኛ ባትምረን እና ባታዝንልን በእርግጥ ከከሳሪዎቹ እንኾናለን" ብሎ ተጸጸተ፦ 7፥23 «ጌታችን ሆይ! እራሳችችንን በደልን፥ ለእኛ ባትምረን እና ባታዝንልን በእርግጥ ከከሳሪዎቹ እንኾናለን» አሉ፡፡ قَالَا رَبَّنَا ظَلَمْنَا أَنفُسَنَا وَإِن لَّمْ تَغْفِرْ لَنَا وَتَرْحَمْنَا لَنَكُونَنَّ مِنَ الْخَاسِرِينَ አደም ተጸጽቶ በንስሓ ወደ አሏህ ሲመለስ አሏህ ጸጸትን በመቀበል ተመለሰለት፥ እነሆ እርሱ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነውና፦ 2፥37 አደምም ከጌታው ቃላትን ተቀበለ፡፡ በእርሱ ላይም ጌታው ጸጸትን በመቀበል ተመለሰለት፥ እነሆ እርሱ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነውና፡፡ فَتَلَقَّىٰ آدَمُ مِن رَّبِّهِ كَلِمَاتٍ فَتَابَ عَلَيْهِ ۚ إِنَّهُ هُوَ التَّوَّابُ الرَّحِيمُ አደም ተጸጽቶ ንስሓ ወደ አሏህ በመግባቱ አሏህ ጸጸትን በመቀበል መረጠው፦ 20፥122 ከዚያም "ጌታው መረጠው" ከእርሱም ጸጸቱን ተቀበለው መራውም፡፡ ثُمَّ اجْتَبَاهُ رَبُّهُ فَتَابَ عَلَيْهِ وَهَدَىٰ "ጌታው መረጠው" የሚለው ይሰመርበት! ማንኛውም ሰው ከነበረበት ኩፍር ወይም ሺርክ አሊያም ዘንብ ወደ አሏህ በንስሓ ቢመለስ አሏህ ወደ ራሱ ለጀነት ይመርጠዋል፦ 42፥13 አሏህ የሚሻውን ሰው ወደ እርሱ ይመርጣል፡፡ የሚመለስንም ሰው ወደ እርሱ ይመራል፡፡ اللَّهُ يَجْتَبِي إِلَيْهِ مَن يَشَاءُ وَيَهْدِي إِلَيْهِ مَن يُنِيبُ "አሏህ የሚሻውን ሰው ወደ እርሱ ይመርጣል" የሚለው "ዓም" ሆኖ የመጣ ነው፥ "ዓም" عَامّ ማለት "ጥቅል"general" ማለት ነው። ነገር ግን "አሏህ የሚሻውን ሰው ወደ እርሱ ይመርጣል" የሚለው ዓም "የሚመለስንም ሰው ወደ እርሱ ይመራል" በሚል "ኻስ" ሆኖ እዛው ላይ መጥቷል፥ "ኻስ" خَاصّ ማለት "ተናጥል"specifical" ማለት ነው። መመራትን ሰው የሚያገኘው በማመን መሆኑ "ኻስ" ሆኖ የሚመጣ ነው፦ 22፥54 አሏህ እነዚያን ያመኑትን ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ "መሪ" ነው፡፡ وَإِنَّ اللَّهَ لَهَادِ الَّذِينَ آمَنُوا إِلَىٰ صِرَاطٍ مُّسْتَقِيمٍ "እነዚያን ያመኑትን" የሚለው ይሰመርበት! ያላመነው እና ንስሓ ያልገባ ሰው የሸይጧን ተከታይ ነው፥ ሸይጧን የተከተለውን ሰው ወደ ጀሀነም ይመራዋል፦ 22፥4 "እነሆ! የተከተለውን ሰው እርሱ ያጠመዋል፡፡ ወደ ነዳጅ እሳት ስቃይም ይመራዋል" ማለት በእርሱ ላይ ተጽፏል፡፡ كُتِبَ عَلَيْهِ أَنَّهُ مَن تَوَلَّاهُ فَأَنَّهُ يُضِلُّهُ وَيَهْدِيهِ إِلَىٰ عَذَابِ السَّعِيرِ ወደ ጀሀነም የሚገባ ሰው አሏህ ለጀነት ያልመረጠው በገዛ ፈቃዱ ሸይጧንን በመከተሉ ነው፥ ይህ የእኛ ጣልቃ ገብነት እና ድርሻ ያለበት የአሏህ ምርጫ "ኢንቲኻብ ሹሩጢይ" اِنْتِخَاب شُرْطِيّ ይባላል።
Show all...
አሏህ አንድ ሰው በነቢይነት ቢመርጠው ሆነ ባይመርጠው ሽልማት እና ቅጣት አሊያም ተጠያቂነት ስለሌለበት ይህ "ኢንቲኻብ ገይሪ ሹሩጢይ" اِنْتِخَاب غَيْرِ شُرْطِيّ ነው። የአሏህን ምርጫ "አሚን" ብሎ መቀበል ከአርካኑል ኢማን ክፍል የሆነውን ቀደርን መቀበል ነው፥ አሏህ የእርሱን ምርጫ "አሚን" ብለው ከሚቀበሉት ምእመናን ያርገን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
Show all...