Abu Hayder Aliy
Open in Telegram
نشرالكتاب والسنة وقول العلمآء بائذن الله الباري بأبي حيدر علي إبن سليمان إبن أحمد الولغاوي
Show moreThe country is not specifiedThe category is not specified
558
Subscribers
+1224 hours
+187 days
+4930 days
Posts Archive
Repost from []سَكِينَةُ الْقُلُوبِ ሰኪነቱል-ቁሉብ[]
إِنَّا لِلَّهِ وَإِنَّا إِلَيْهِ رَاجِعُونَ
ይህንን የመሰለ ልብ የሚነካ ድምፅ ከእንግዲህ አንሰማውም ብንል፣ ማን አምኖ ይቀበላል?
ያ አላህ…
አላህ እዝነቱን ያውርድባቸው እነሱማ በደግነት ኖረው፣ በመልካም ሥራ አሳልፈው አለፉ አላህ መልካም ሥራቸውን ተቀብሎ በጀነት ያክብራቸው።
የእኛ ነገር ግን እውነትም ያሳዝናል…
ዕድሜያችን እየጨመረ ነው ቀናቶቻችንም እያለፉ ነው እኛ ግን ዛሬም እዚያው ነን ምንም ለውጥ የለንም።
እነሱ ሄዱ… ሥራቸው ግን ቀረ።
እኛ ገና እዚህ ነን… የምንሰራው ግን ምንድነው?
ከባድ ነው…
አላህ ይዘንልን ከዝንጋታችን ያንቃን የቀረልንን ጊዜ በመልካም ሥራ እንድንጠቀምበት ይርዳን መጨረሻችነንም ያሳምርልን።
«የዑለማዎችና የሷሊሆች መሞት የቂያማ መቅረብ ምልክት ነው»የመስጂደል ሀራም ሙአዚን የነበሩት ሼክ ኢብራሂም አል-መደኒ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። አላህ ይርሃማቸው መቃብራቸውን ከጀነት ገነቶች አንዱ ያድርግላቸው።
Repost from مركز الإمام أحمد الإسلامي
አሏህን መፍራት ነው ...
መማር ብቻ አይደለም ሩቅ ቦታ 'ሚያደርሰው
ማስተማርም አይደል ሰው የሚቀድሰው
አሏህን መፍራት ነው የሚያረግ ሙሉ ሰው !
https://t.me/MerkezulimamiAhmed
እስኪ ልብ እነበል ወላሂ ሀቂቃ ዛሬ አብዛኛዎቻን በእንዱኒያ ምቾትን ለማግኜት የምንሯሯጥ ብዙ የተሟላ ነገሮች እያሉን ከእነከሌ በላይ ለመሆን
እርበእርሳችን በምቀኚኘት እና በሂስድ ውስጥ ገብተናል በምን ምክንይት ብትሉኚ በእዱኒያ ጥቅም ሱባሀ አላህ
ነገር ግን የኦላማዎች ሁኔታ ከቀድምቶችም አንስቶ ብንያው ታሪካቸው ይህን ተመሳሳይ ሁኔታ ነበር በማይመች ሁኔታ ሆነው መሆናቸውን ማንም ሳያቅ ሙሉ ህይወታቸው ዲን በማስተማር የተለያዩ ኩቱቦችን በመግዛት እና በመፃፍ ተውሂድ ፡ የበላይ እንዲሆን ነበር እንድሚቸውን የሚፈጁት በጣም ልብ የሚነካ መልእክት ወላሂ አላህ ይዘንል ያረቢ
https://t.me/abu_hayder_aliy
የሰዎችን ስህተት በመፈለግ ጊዜ ከማጥፋት ይልቅ፣ የራስህን ድክመቶች አርም፤ የሌሎችን ብቻ መከታተል የመጥፎ ዕድል ምልክት ነው!»
https://t.me/abu_hayder_aliy
+1
📢ታላቅ የነፍስ አድን ጥሪ ለወንድማችን መስዑድ አወል
ይህ በፎቶ ላይ የምትመለከቱት ለጋ ወጣት ወንድማችን መስዑድ አወል ይባላል። የ16 አመት ልጅ ሲሆን ተወልዶ ያደገው በኦሮሚያ ልዩ ዞን ከሚሴ ከተማ ሲሆን እንደማንኛውም ሰው ህይወቱን ለመለወጥ በማሰብ ከቤት ከወጣ ወር ከአስራ አምስት ቀን ሆኖታል እሱም ወደ ሳዑዲ ለመሄድ በበረሃ ጉዞ የጀመረ ቢሆንም አሏህን በማይፈሩ እና አጭበርባሪ ደላሎች አማካኝነት ወደ ሊቢያ የወሰዱት ሲሆን፣አሁን ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ታስሮ እና ተዘቅዝቆ እየተደበደበ ህይወት ውጭ ህይወት ግቢ ላይ ይገኛል።ለዚህ ወንድማችን አጋቾች የጠየኩት ገንዘብ ሶስት ሚሊየን(3,000 000) ብር ቢሆንም ቤተሰብ ያለውን በሙሉ አሟጦ 500 000 ሺ ብር አጊንተዋል።ነገር ግን አጋቾቹ ሙሉው ገንዘብ የማይገባላቸው ከሆነ ወንድማችንን እንደሚገሉት እየነገሩን ይገኛሉ። እና የተከበራቹህ የሱና ወንድም እህቶቸ የተቻላችሁን በማድረግ ወንድማችንን ከሞት ቤተሰቡን ደግሞ ከጭንቀት ትገላግሉን ዘንድ በአሏህ ስም ሁላችሁም በቻላችሁ አቅም እንድትረዱን እንጠይቃቹሀለን።ባረከሏሁ ፊኩም!
🔹ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት👇 1000365388184
ስም፡Saliha Hassen Endris
🔹ደውለው ስለልጁ ሁኔታ ለመጠየቅና ለመርዳት የቤተሰብ ስልክ
📞 0945697003
📞 0943725521
اللَّهُمَّ أَصْلِحْ قُلُوبَنَا، وَاسْتُرْ عُيُوبَنَا، وَاغْفِرْ ذُنُوبَنَا، وَأَحْسِنْ خَاتِمَتَنَا، يَا رَبَّ الْعَالَمِينَ.
አላህ ሆይ! ልቦቻችንን አስተካክልልን፣ ጉድለቶቻችንን ሸፍንልን፣ ኃጢአቶቻችንን ማርልን፣ መጨረሻችንንም አሳምርልን መልካም አድርግልን! 🤲
በሰዎች (በፍጥረታት) ኃይልና ክብርን የፈለገ ሰው በውርደታቸው ይዋረዳል፤»
በአል-ረሕማን (በአላህ) ኃይልና ክብርን የፈለገ ግን የተከበረ ሆኖ ይኖራል።»
https://t.me/abu_hayder_aliy
🌿🌿🌿🌹🌹🌹❤️❤️❤️ልባችንን ከምቀኝነት እንጠብቅ፤ ደግነትን እንለማመድ
ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ!
አንድ ሙስሊም ሰው ልቡን ከሚያበላሹ ነገሮች መጠበቅ ይገባዋል። ከእነዚህም መካከል ምቀኝነት፣ ጥላቻ፣ ቂምና ለሌላ ሰው የሚደርሰውን መልካም ነገር አለመውደድ ናቸው። በተቃራኒው ደግነት፣ መልካም ምግባር፣ ለሌሎች መልካም መመኘትና ልብን ከጥላቻ ማጽዳት ከታላላቅ የኢስላም ባሕርያት ናቸው።
1. ምቀኝነት አደገኛ የልብ በሽታ ነው
አላህ سبحانه وتعالى ምቀኝነትን ከክፉ ነገሮች መካከል ጠቅሶ እንዲህ ብሏል፦
﴿وَمِن شَرِّ حَاسِدٍ إِذَا حَسَدَ﴾
«ከሚቀና ሰው በሚቀናበት ጊዜ ከሚያመጣው ክፋት እጠበቃለሁ።»
— ሱረቱል-ፈለቅ፦ 5
ይህ አንድ ትልቅ ትምህርት አለው፤ ምቀኝነት በልብ ውስጥ ብቻ ተቀምጦ የሚቀር ሳይሆን ሰውን ወደ ክፉ ተግባር ሊመራው ይችላል።
ስለዚህ ሙስሊም ሰው ልቡን ይመርምር፦
«ወንድሜ በረከት ሲያገኝ ደስ ይለኛልን? ወይስ ከእኔ እንዲወገድ እመኛለሁ?»
ብሎ ራሱን መጠየቅ ይገባዋል።
2. ነቢዩ ﷺ እርስ በርሳችን እንዳንቀና አስጠንቅቀዋል
ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«لا تَحاسَدوا، ولا تَباغَضوا، ولا تَدابَروا، وكونوا عبادَ اللهِ إخوانًا»
«እርስ በርሳችሁ አትቀናኑ፤ አትጠላሉ፤ እርስ በርሳችሁ ጀርባ አትስጡ፤ የአላህም ባሮች እንደ ወንድማማች ሁኑ።»
— ሶሒሕ አል-ቡኻሪ፣ ሶሒሕ ሙስሊም
እዚህ ላይ ነቢዩ ﷺ ምቀኝነትን ከጥላቻና ከመተያየት ጋር አብረው ጠቅሰዋል። ምክንያቱም ምቀኝነት ካልታከመ ጥላቻን ያመጣል፤ ጥላቻም ወደ ግጭትና ወደ ዝምድና መቋረጥ ሊመራ ይችላል።
3. ለወንድምህ የምትወደውን ለራስህ ውደድለት
ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«لا يؤمن أحدكم حتى يحب لأخيه ما يحب لنفسه»
«ከእናንተ አንዳችሁ ለራሱ የሚወደውን ለወንድሙ እስከሚወድ ድረስ ፍጹም አማኝ አይሆንም።»
— ሶሒሕ አል-ቡኻሪና ሶሒሕ ሙስሊም
ይህ ሐዲስ ምቀኝነትን ለማስወገድ ትልቅ መድኃኒት ነው።
አንተ ገንዘብ እንዲኖርህ እንደምትፈልግ፣ ለወንድምህም እንዲኖረው ውደድ።
አንተ ጤና እንዲኖርህ እንደምትፈልግ፣ ለወንድምህም ጤና ውደድ።
አንተ አላህ እንዲመራህ እንደምትፈልግ፣ ለወንድምህም ሂዳያ ውደድ።
ይህ ነው እውነተኛ የእምነት ባሕርይ።
4. ለሌሎች መልካም ማድረግ
አላህ سبحانه وتعالى እንዲህ ይላል፦
﴿إِنَّ اللَّهَ يَأْمُرُ بِالْعَدْلِ وَالإِحْسَانِ﴾
«እርግጥ አላህ በፍትሕና በመልካም ሥራ ያዛል።»
— ሱረቱ አን-ነሕል፦ 90
ደግነት በገንዘብ ብቻ አይደለም። ጥሩ ቃል መናገር፣ የተቸገረን መርዳት፣ የተራበን ማብላት፣ የታመመን መጠየቅ፣ ለሰው መልካም መመኘትና ከሰዎች ጉዳትን ማራቅም ደግነት ነው።
5. የምቀኝነት ተቃራኒ የሆነው መልካም ልብ
አላህ سبحانه وتعالى ስለ ምእመናን እንዲህ ብሏል፦
﴿وَالَّذِينَ جَاءُوا مِن بَعْدِهِمْ يَقُولُونَ رَبَّنَا اغْفِرْ لَنَا وَلِإِخْوَانِنَا الَّذِينَ سَبَقُونَا بِالإِيمَانِ وَلَا تَجْعَلْ فِي قُلُوبِنَا غِلًّا لِّلَّذِينَ آمَنُوا﴾
«ከእነርሱ በኋላ የመጡትም፦ ‘ጌታችን ሆይ! ለእኛና በእምነት ከእኛ በፊት ለቀደሙት ወንድሞቻችን ምሕረትን ስጠን፤ በልባችንም በአማኞች ላይ ቂም አታድርግብን’ ይላሉ።»
— ሱረቱል-ሐሽር፦ 10
ይህ ለእያንዳንዱ ሙስሊም ታላቅ ዱዓ ነው። ልባችን ከቂም፣ ከጥላቻና ከምቀኝነት እንዲጸዳ አላህን እንጠይቅ።
6. ምቀኝነት ሲመጣ ምን እናድርግ?
አንድ ሰው አንተ የሌለህ ነገር ቢያገኝ፣ ልብህ ቢቀና፣ ወዲያውኑ እንዲህ በል፦
«اللهم بارك له، وارزقني من فضلك»
«አላህ ሆይ! ለእርሱ በረከት ስጠው፤ ከችሮታህም ለእኔ ስጠኝ።»
ከዚያም ለእርሱ መልካም ዱዓ አድርግ። ይህ ልብህን ከምቀኝነት ለማጽዳት ይረዳሃል።
አላህ የሰጠውን በማየት ከመቀናት ይልቅ የሰጠህን ተመልከት፤ አላህም ከችሮታው እንዲጨምርልህ ጠይቅ።
7. ደግነት የሰውን ልብ ይለውጣል
የሙስሊም ሰው ባሕርይ ለሌሎች መልካም መሆን ነው። እርሱ ቢበደልም በቻለው መጠን ይቅር ይላል፤ ሰው ቢያስቸግረውም እርሱ ግን ክፉን በክፉ ለመመለስ አይቸኩልም።
አላህ سبحانه وتعالى እንዲህ ይላል፦
﴿وَالْكَاظِمِينَ الْغَيْظَ وَالْعَافِينَ عَنِ النَّاسِ وَاللَّهُ يُحِبُّ الْمُحْسِنِينَ﴾
«ቁጣቸውን የሚቆጣጠሩ፣ ከሰዎችም የሚምሩ ናቸው፤ አላህም መልካም አድራጊዎችን ይወዳል።»
— ሱረቱ አሊ ዒምራን፦ 134
ስለዚህ ወንድሜና እህቴ! ልብህን አጽዳ። ለሰዎች መልካም ተመኝ። የሌላውን በረከት አትመኝ። አላህ ለሌላው የሰጠውን አንተም እንዲሰጥህ ጠይቅ። የሌላው ስኬት የአንተ ውድቀት አይደለም፤ አላህ ለእያንዳንዱ ባሪያ የሚሆነውን ያውቃል።
👇👇 ☝️☝️
ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚነገር አንድ ታሪክ እንዲህ ይተረካል፦
አንድ ጊዜ አንድ ሸይኽ ነበሩ። አንዲት ሴትንም አግብተው ነበር። ባለቤታቸው ግን ሁልጊዜ ጥያቄ መጠየቅ ትወድ ነበር።
አንድ ቀን፦
«የሸይኽ ሆይ! ሰውን ጀነት እንዲገባ ከሚያደርጉት ነገሮች ታላቁ ምንድን ነው?» ብላ ጠየቀቻቸው።
ሸይኹም፦
«ደግነትና መልካም ስነ-ምግባር ነው» ብለው መለሱላት።
ከጊዜ በኋላ ሸይኹ ለጉዞ ሊወጡ ሲሉ ከቤተሰባቸው ተሰናብተው ለመሄድ ፈቃድ ጠየቁ።
ባለቤታቸው ግን የባሏን ምክር ትታ፣ በልቧ ምቀኝነት ተሞልታ ነበር። እንዲህም አለች፦
«ቆይ፣ ስንቅ ልስጥህ» ብላ ስንቅ አዘጋጀችላቸው።
ነገር ግን በስንቁ ውስጥ መርዝ አድርጋ ሰጠቻቸው።
ሸይኹ ግን ይህንን ሳያውቁ የተሰጣቸውን ስንቅ ይዘው ጉዟቸውን ቀጠሉ።
ወደ ሰፈራቸው ሲደርሱ ምግብ ፍለጋ የወጡ ሁለት ደረሶች ከሸይኹ ጋር ተገናኙ።
ሸይኹም ልጆቹን አይተው በደግነት፦
«አቦ! ከእኔ ይልቅ እናንተ ትበሉት» ብለው፣ የያዙትን ምግብ ለሁለቱ ልጆች ሰጧቸው።
ልጆቹም ምግቡን በሉ። ምግቡ ግን መርዝ ስለነበረበት ሁለቱም ልጆች ሞቱ።
የሰፈሩ ነዋሪዎችም ልጆቹ የሷ መሆናቸውን የሚያውቁት ስለነበሩ፣ ሟቾቹን ወደ እናታቸው ወስደው አደረሱላት።
እናታቸውም ልጆቿን ሞተው ባየች ጊዜ እጅግ አዘነች፣ እያለቀሰችም እንዲህ አለች፦
«ቀን ሳለቅስ ውዬ ደገምኩት ሌሊቱን፤
ሥራ ይጓዳል ወይ እንዲህ ባለቤቱን!»
ይህ ታሪክ እንደ ተረት ቢነገርም፣ የሚያስተምረን ትምህርት ግን ከቁርኣንና ከሶሒሕ ሐዲስ መሠረቶች ጋር የሚስማማ ነው፤ ማለትም ምቀኝነትንና ጥላቻን መተው፣ ለሌሎች መልካም መመኘትና ደግነትን መለማመድ ነው።
የመጨረሻ ምክር
ወንድሜ! ከሰዎች ጋር ስትኖር ልብህን አታበላሽ። ማንም ሰው አላህ የሰጠውን በረከት ሲያገኝ አትቀና። ይልቁንም በረከቱ እንዲጨምርለት ዱዓ አድርግ።
አላህ ልባችንን ከምቀኝነት፣ ከጥላቻና ከቂም ያጽዳልን። ለሙስሊሞች ሁሉ መልካም የምንመኝ ባሮቹ ያድርገን። ደግነትንና መልካም ምግባርን ይስጠን። ከእኛም የሚወደውን ይቀበል።
اللهم طهّر قلوبنا من الحسد والحقد والبغضاء، واجعلنا من أهل الإحسان وحسن الخلق، ووفّقنا لمحبة الخير للمسلمين، وبارك لنا ولهم فيما أعطيتنا وأعطيتهم. آمين.
አሰላሙ ዐለይኮም ወራህመቱላሂ ወበረከትሁ
ውድ እህት ወንድሞች ከቂቃዎች በኋላ በእህታችን ሀናን አህመድ ጉዳይ
ላይቭ ስለምንገባ እርቃችሁ እንዳትሄዱ ጠብቁን
የእህታችን ጉዳይ የእኛም ጉዳይ ነው
http://t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
يقول ابن تيمية رحمه الله :
«الذِّكرُ للقلبِ بمنزلةِ الماءِ للسمك، فماذا يكونُ حالُ السمكِ إذا فارقَ الماء؟!»
📚 مجموع الفتاوى 【10/85】
ኢብኑ_ተይሚያህ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : -
«ዚክር ለቀልብ ያለው አስፈላጊነት ልክ ውሀ ለዓሳ ያለውን አስፈላጊነት ያክል ነው። ዓሳው ከውሀ የተለየ ጊዜ ምን ይሆናል?!።»
📚 ۞ مجموع الفتاوى 【10/85】۞
https://t.me/abu_hayder_aliy
https://t.me/abu_hayder_aliy
Repost from ስለ ቀልባችን
➔ በሃላል መተያየት፣
➔ ከዚያም እጮኝነት፣
➔ ከዚያም ኒካህ፣
➔ ከዚያም ሰርግ።
ይህ ነው ትክክለኛው መንገድ፤ የእውነት የሚወድሽ ከሆነ መንገዱ ይሄው ነው፣ ከዚህ ውጭ ሌላ አማራጭ የለም።
የሰፈር። አሰቃቂነት የስደት አስቸጋሪነት
ኡስታዝ ኸድር አህመድ ኬሚሴ ገብቷል
https://t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy?livestream=bd6002580c2304c158☎️ የመጀመሪያው ፕሮግራም
🎙በወንድም አቡ ሂበቲላህ
📚 ርዕስ አላህን መፍራት
ተ
ጀ
መ
ረ
ገባ ገባ በሉ ሊንኩን ሸር ሸር አድርጉት
http://t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
http://t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ፕሮግራማችን ቀጥታ ስርጭት
ሊ
ጀ
መ
ር ነው
ገባ ገባ በሉ ሊንኩን ሸር ሸር አድርጉት
http://t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
http://t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
ኢማሙል_አልባኒይ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : -
«ልክ ከአላህ ውጪ በእውነት የሚገዙት አምላክ እንደሌለ ሁሉ፥ በእውነት የሚከተሉትም የለም ረሱል ﷺ ብቻ ቢሆኑ እንጂ።»
📚 ۞ متفرقات شريط رقم【6】۞
https://t.me/abu_hayder_aliy
https://t.me/abu_hayder_aliy
⚠️ሀጃውን አላህ እንዲያወጣለት የፈለገ
●ችግሩን አላህ እንዲያስወግድለት የፈለገ
● ከበሽታው አላህ እንዲያድነው የፈለገ ሰው
●ከቂያማ ቀን ጭንቀት አላህ እንዲያድነው የፈለገ ሰው
●የአላህን እዝነት የፈለገ ሰው........?!!
📣የወንድሙን ሀጃ ያውጣ !
📣የወንድሙን ችግር ያስወግድ
📣 የወንድሙን ጭንቀት ያቅልል
📣ለወንድሙ ይዘን
🎙በአቡ ሒበቲላህ ሑሰይን ኢስማኢል
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
Repost from N/a
📢 አስደሳች ዜና!
ከዳሩል ዒልም የቁርአን ሒፍዝ
እና የተርቢያ ማዕከል
💎 ዳሩል ዒልም የቁርአን ሒፍዝ እና የተርቢያ ማዕከል ለ2019 ዓ. ል የትምህርት ዘመን በአዳሪ መርሃግብር ተማሪዎችን ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቆ በምዝገባ ላይ ይገኛል።
☑️ የመመዝገቢያ መስፈርቶች፦
📍ጾታ፦ ለወንዶች ብቻ (አዳሪ)
📍 እድሜ፦ ከ10 - 20 ዓመት
📍 ጤንነት፦ ከማንኛውም በሽታ ነፃ የሆነ
📍 ስነ-ምግባር፦ለመርከዙ ህግና ደንቦች ተገዢ የሆነ
📍 ፍላጎት፦ ለመቅራት ከፍተኛ ፍላጎት ያለው
📍ክፍያ፦ ወርሃዊ ክፍያን መክፈል የሚችል
☑️ የሚሰጡ የትምህርት አይነቶች፦
📌 የቁርአን ሒፍዝ (በቃል መያዝ)
📌 የቁርአን ነዘር (ንባብ) እና ሙራጀዓ (ክለሳ)
📌 ቃዒደቱን ኑራኒያ እና የተጅዊድ ትምህርቶች
📌 የተለያዩ የዲን ኪታቦች
☎️ ለምዝገባ እና ለበለጠ መረጃ፡
+251911171786 | +251910034682
በቴሌግራም ለመመዝገብ ይህን ይጫኑ👈
በዋትስ አፕ ለመመዝገብ ይህን ይጫኑ👈
የቴሌግራም አድራሻ፡
🔗https://t.me/darulilmmerkezofficial
🔗https://t.me/darulilmmerkezofficial
🏢 አድራሻ: አንፎ 105 ከዘቢዳር ሆቴል ጀርባ
