en
Feedback
HOP Ministry

HOP Ministry

Open in Telegram

HOP Ministry — Hear. Obey. Practice. A discipleship platform sharing devotionals, revival histories, spiritual biographies, testimonies, and Amharic Christian literature to build Christ-like lives. Based on Luke 11:28.

Show more
The country is not specifiedThe category is not specified
563
Subscribers
+324 hours
+217 days
+5530 days
Posts Archive
ሰቆ. 3 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ³¹ እግዚአብሔር ሰውን፣ ለዘላለም አይጥልምና፤ ³² መከራን ቢያመጣ እንኳ ይራራል፤ ታላቅ ፍቅሩ አይለወጥምና ³³ ሆን ብሎ ችግርን፣ ወይም መከራን በሰው ልጆች ላይ አያመጣምና። https://t.me/hopministry10

ሰቆ. 3 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²¹ ሆኖም ይህን አስባለሁ እንግዲያስ ተስፋ አለኝ፤ ²² ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ታላቅ ፍቅር የተነሣ ነው፤ ርኅራኄው አያልቅምና። ²³ ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው፤ ታማኝነትህም ብዙ ነው። ²⁴ ራሴን እንዲህ አልሁት፤ “እግዚአብሔር ዕድል ፈንታዬ ነው፤ ስለዚህ ተስፋ አደርገዋለሁ። ²⁵ እርሱን ተስፋ ለሚያደርጉት፣ ለሚፈልገውም ሰው እግዚአብሔር መልካም ነው። ²⁶ ሰው የእግዚአብሔርን ማዳን፣ ዝም ብሎ ተስፋ ቢያደርግ መልካም ነው። ²⁷ ሰው በወጣትነቱ፣ ቀንበር ቢሸከም መልካም ነው። ²⁸ ብቻውን ዝም ብሎ ይቀመጥ፤ እግዚአብሔር አሸክሞታልና። ²⁹ ፊቱን በዐቧራ ውስጥ ይቅበር፤ ተስፋ ሊኖር ይችላልና። ³⁰ ጒንጩን ለሚመታው ሰው ይስጥ፤ ውርደትንም ይጥገብ። ³¹ እግዚአብሔር ሰውን፣ ለዘላለም አይጥልምና፤ ³² መከራን ቢያመጣ እንኳ ይራራል፤ ታላቅ ፍቅሩ አይለወጥምና ³³ ሆን ብሎ ችግርን፣ ወይም መከራን በሰው ልጆች ላይ አያመጣምና። #HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional

#የትውልድን_ሸክም_ከልባችን_የሰረቀው_ማንነው? https://t.me/hopministry10

2ኛ ቆሮንቶስ 5 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁸ ይህ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፤ እርሱ በክርስቶስ አማካይነት ከራሱ ጋር አስታረቀን፤ የማስታረቅንም አገልግሎት ሰጠን፤ ¹⁹ እግዚአብሔር በክርስቶስ ዓለምን ከራሱ ጋር ሲያስታርቅ የሰዎችን በደል አይቈጥርባቸውም ነበር፤ ለእኛም ደግሞ የማስታረቅ ቃል ሰጠን። ²⁰ ስለዚህ እኛ የክርስቶስ እንደራሴዎች ነን፤ እግዚአብሔርም በእኛ አማካይነት ጥሪውን ያቀርባል፤ እኛም ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን በክርስቶስ እንለምናችኋለን። #HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional

ጌታ_ሆይ_እኔ_ምለምንህ_አንድ_ነገር_Tamrat_Haile_#protestant_mezmur_#viral_#መዝሙር.m4a4.40 MB

#የክርስቶስ_ግልጽ_ደብዳቤ 2ኛ ቆሮንቶስ 3 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ እንደ ገና ራሳችንን ልናመሰግን እንጀምራለንን? ወይስ እንደ ሌሎቹ ለእናንተ ወይም ከእናንተ የተጻፈ የምስጋና ደብዳቤ ያስፈልገን ይሆንን? ² እናንተኮ ሰው ሁሉ የሚያውቃችሁና የሚያነባችሁ በልባችን ላይ የተጻፋችሁ ደብዳቤዎቻችን ናችሁ፤ ³ እናንተ በቀለም ሳይሆን በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ፣ በድንጋይ ጽላት ላይ ሳይሆን በሰው ልብ ጽላት ላይ የተጻፋችሁና በእኛ የተገለገላችሁ የክርስቶስ ግልጽ ደብዳቤ ናችሁ። 2 Corinthians 3: 3 (ESV) "And you show that you are a letter from Christ delivered by us, written not with ink but with the Spirit of the living God, not on tablets of stone but on tablets of human hearts." #HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional

"You are a letter from Christ" https://t.me/hopministry10

Amharic_song_Meheret_Etefa_EWEDEHALEHU_ምህረት_ኢተፋ_እወድሃለሁ128k.m4a5.93 MB

"Remain Teachable!" https://t.me/hopministry10

እግዚአብሄር_ደግ_ቤተልሄም_ተዘራ_Egeziyabeher_Deg_Betelhem_Tezera_New_Protstant.m4a4.05 MB

1ኛ ዮሐንስ 5 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹³ በእግዚአብሔር ልጅ ስም የምታምኑ እናንተ፣ የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ታውቁ ዘንድ ይህን እጽፍላችኋለሁ፤ ¹⁴ በእግዚአብሔር ፊት ለመቅረብ ያለን ድፍረት ይህ ነው፤ ማንኛውንም ነገር እንደ ፈቃዱ ብንለምን እርሱ ይሰማናል፤ ¹⁵ የምንለምነውን ሁሉ እንደሚሰማን ካወቅን፣ የለመነውንም ነገር እንደ ተቀበልን እናውቃለን። #HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional

“በእግዚአብሔር ፊት ለመቅረብ ያለን ድፍረት ይህ ነው፤ ማንኛውንም ነገር እንደ ፈቃዱ ብንለምን እርሱ ይሰማናል፤”   — 1ኛ ዮሐንስ 5፥14 (አዲሱ መ.ት) https://t.me/hopministry10

“በመንገድህ ሁሉ እርሱን ዕወቅ፤ እርሱም ጐዳናህን ቀና ያደርገዋል።”   — ምሳሌ 3፥6 (አዲሱ መ.ት) "In all your ways acknowledge him, and he will make straight your paths."    — Proverbs 3: 6 (ESV)

ትቼዋለሁ_-Bethlehem_Wolde-tichewalew(128k).m4a5.00 MB

ዘጸአት 13 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁷ ፈርዖን ሕዝቡን በለቀቀ ጊዜ አቋራጭ ቢሆንም እንኳ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) በፍልስጥኤም ምድር በሚያልፈው መንገድ አልመራቸውም “ጦርነት ቢያጋጥማቸው ሐሳባቸውን ለውጠው ወደ ግብፅ ይመለሱ ይሆናል” ብሎአልና። ¹⁸ ስለዚህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ሕዝቡን ዙሪያ በሆነው በምድረ በዳው መንገድ ወደ ቀይ ባሕር መራቸው፤ እስራኤላውያንም ለጦርነት ዝግጁ ሆነው ከግብፅ ወጡ። ¹⁹ ዮሴፍ፤ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) በእርግጥ ይጐበኛችኋል፤ በዚያን ጊዜም ዐፅሜን ይዛችሁ ከዚች ምድር መውጣት አለባችሁ ብሎ የእስራኤልን ልጆች አስምሎአቸው ስለ ነበር ሙሴ የዮሴፍን ዐፅም ይዞ ወጣ። እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ሕዝቡን ዙሪያ በሆነው በምድረ በዳው መንገድ ወደ ቀይ ባህር መራቸው፤ እስራኤላውያንም ለጦርነት ዝግጁ ሆነው ከግብፅ ወጡ። ²⁰ እነርሱም ከሱኮት ከተነሡ በኋላ ከምድረ በዳው ጥግ ባለው በኤታም ሰፈሩ። ²¹ ስለዚህ በቀንም ሆነ በሌሊት መጓዝ ይችሉ ዘንድ፣ እግዚአብሔር (ያህዌ) በቀን በመንገዳቸው ሊመራቸው በደመና ዓምድ፣ በሌሊት ደግሞ ብርሃን ሊሰጣቸው በእሳት ዓምድ በፊታቸው ይሄድ ነበር። ²² በቀንም ሆነ በሌሊት የደመናውና የእሳቱ ዓምድ ከሕዝቡ ፊት የተለየበት ጊዜ አልነበረም። #HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional

እግዚአብሔር ሲመራ አቋራጩን አይመርጥም። https://t.me/hopministry10

ናፈቀኝ_Nafekegn_Live_Version_Yohannes_Girma_ft_Zetseat_Choir128k.m4a15.65 MB

በፀሎት የሚፈለገው፣ የሚገኘውም ሕያው አምላክ እንደሆነ ሲገባን፦ ፍለጋችን፣ ናፍቆታችን፣ ወደ እርሱ መገስገሳችን፣ ረሃባችን ያለ ማቋረጥ ይሆናል። https://t.me/hopministry10

#እግዚአብሔርን_መውደድ፤ #ፀሎትን_መውደድ በምድር እስካለን ድረስ እግዚአብሔርን ከምናይባቸውና ከምናገኝባቸው መንገዶች አንዱ ፀሎት ነው። ከእግዚአብሔር ከራሱ ፍቅር ሲይዘን ፀሎትን መውደድ እንችላለን። እግዚአብሔርን ለማግኘት ስንል በፊቱ እንሆናለን፤ እርሱ እንዲገኝልን አብዝተን እንሻዋለን። በፀሎት እግዚአብሔር እንደሚገኝ፣ ፀሎት የእግዚአብሔር መገኛ እንደሆነ ሲገባን፦ ፀሎት ለእኛ መሰረታዊ ነገር ይሆናል። ያስፈልገናል ስጠን ብለን እግዚአብሔር ፊት ከምንቀርበው ጥያቄ በላይ፤ ሰጪው፣ የጥያቄያችን መላሽ ራሱ እግዚአብሔር ተፈላጊ ይሆንልናል። ፀሎት ራበኝ፣ ውስጤ መጸለይ ፈለገ፣ ፀሎት ናፈቀኝ ማለት መቻል፤ እንዳሉትም መሆን እንዴት መታደል ነው?! ይሄኮ በእግዚአብሔር ከተነካ ማንነት ውጪ በማንም ሊሆን አይችልም። እግዚአብሔር ናፈቀኝ፣ ህልውናው ናፈቀኝ ብሎ ወደ ፀሎት ጥድፍ ማለት የእግዚአብሔር ረሃብ ከበዛለት ሰው ዘንድ እንጂ ከወዴት ይገኛል?! ፀሎት የእግዚአብሔርን አብሮነት፣ መገኘት የምናጣጥምበት መነካካት፣ ስፍራ ካልሆነ፦ ስራ፣ ሸክም ይሆናል፤ ሥጋንም ያዝላል፤ ለነፍስም ጠብ የሚል ነገር አይገኝበትም። ፀሎት በእግዚአብሔር ህልውና ሲሞላ፣ በመንፈስ ቅዱስ ሲሆን ግን ትቶ ለመውጣት የሚያሳሳ ስፍራ፣ ከራቁበትም እያጣደፈ የሚያመጣ ረሃብ ይሆናል። በፀሎት የሚፈለገው፣ የሚገኘውም ሕያው አምላክ እንደሆነ ሲገባን፦ ፍለጋችን፣ ናፍቆታችን፣ ወደ እርሱ መገስገሳችን፣ ረሃባችን ያለ ማቋረጥ ይሆናል። መዝሙር 42 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹   ዋላ የምንጭ ውሃ እንደምትናፍቅ፣ አምላክ ሆይ፤ ነፍሴም እንዲሁ አንተን ትናፍቃለች። ² ነፍሴ አምላክን፣ ሕያው አምላክን ተጠማች፤ መቼ ደርሼ ነው የአምላክን ፊት የማየው? ✍️ መክሊት አየለ 📆 August 1, 2026 #HOPMinistry #HearObeyPractice #DailyDevotional

🔥ኢየሱስ_ይላል_ውስጤ!!_EYESUS_YILAL_EBENEZER_TAGESSE_#TESEFAYE_GABISO17.m4a8.26 MB