en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

Open in Telegram

قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.

Show more
The country is not specifiedThe category is not specified
907
Subscribers
-224 hours
-127 days
+4630 days
Posts Archive
ሳይሸማቀቁ ችላ ሊሏቸው የሚገቡ አምስት ሰዎች ፡- 1- የደረሰበትን ችግር እንደፈተና ቆጥሮ የአንተን ግን እንደቅጣት የሚያይን ሰው። 2- ስህተቱን እንደጥረት ተመልክቶ ስህተትህን ደግሞ የምትቀጣበት ኃጢአት አድርጎ የሚያስብን ሰው። 3- ክብርህን ነክቶ ይቅርታ እንድትጠይቀው የሚጠብቅን ሰው። 4- ይቅርታ አድርገህለት እንደፈራኸው የሚያስብህን ሰው። 5- ጥፋቱን ችላ ስትለው ቂል አድርጎ የሚመለከትህን ሰው። https://t.me/Abulbuhari.

بسم اللــــه الرحمـــــــــن الرحيم. الســــــــــــؤال :- ما صحة هذه القاعدة: (من لم يبدع المبتدع فهو مبتدع) أو (من توقف في تبديع المبتدع فهو مبتدع)؟ الإجـــــــــابة :- بسم الله الرحمن الرحيم، الحمد لله، والصلاة والسلام على رسول الله وعلى آله، أما بعد: فما يتعلق بالبدع التي في أصول السنة الواضحة الجلية التي لا يحتاج فيها إلى إقامة الحجة لمن ابتدع فيها؛ لبيانها ووضوحها؛ فهذه القاعدة صحيحة فيما يتعلق بذلك. وعلى سبيل المثال: بدعة القول بخلق القرآن، وبدعة القدر، وبدعة تعطيل الله من صفاته، وما أشبه ذلك. وأما ما يتعلق بالبدعة والأخطاء الخفية التي قد يحصل فيها الخفاء النسبي، فمثلها لا يصلح أن يبدع فيها العالم المجتهد المتحري للحق؛ فضلًا عن أن يقال فيها: (من لم يبدع المبتدع فهو مبتدع)، أو (من توقف في تبديع المبتدع فهو مبتدع). إلا في حالة أن يتبين له فيها الحق، فيقدم هواه ويعاند الحق. ففي هذه الحالة يلتحق بالصورة الأولى؛ إذ أن من أصول أهل السنة تقديم أدلة الكتاب والسنة على العقل والهوى، وتقديم الحق على كل شيء سواه. ولكن الذي يحكم على العالم بأنه قد صار يتابع هواه، ويقدمه على الحق في مثل هذه القضايا الخفية هم العلماء الراسخون؛ لأنهم هم الذين يميزون الحق من الباطل، ويميزون صاحب الهوى من صاحب السنة، ويعلمون الأعذار الشرعية التي يعذر بها العالم، وقد ألف شيخ الإسلام ابن تيمية رحمه الله كتابا سماه: (رفع الملام عن الأئمة الأعلام)، ذكر فيه جملة من الأعذار الشرعية للمجتهدين، ننصح بقراءته والاستفادة منه. ثم بعد ذلك كيف تطبق القواعد المذكورة لو حصل خلاف بين علماء أهل السنة في ذلك العالم، أهو متبع لهواه أم له عذر شرعي. فإذا كان الخلاف موجودا بين العلماء في الاعتذار لعالم، فكيف يسوغ أن تطبق مثل هذه القواعد المجملة. ولو كان أكثر العلماء لا يرون لذلك العالم عذرا شرعيا،  وحكموا عليه باتباع الهوى، وتردد بعض العلماء عن الحكم عليه بذلك، لا تصويبا لخطئه، ولا اتباعا للهوى ، ولكن لاحتمالهم العذر الشرعي السائغ لذلك العالم، فكيف يسوغ أن تطبق عليهم القواعد المذكورة. فالحقيقة أن كثيرا من الغلاة والمبتدئين الحماسيين ينزلون هذه القواعد في غير موضعها مما سبب جناية عظيمة على الدعوة السلفية وعلمائها. ثم يأتي رجل جاهل، أو متعالم فيحكم على العالم باتباع الهوى، ويكتب الملازم نصيحة وإقامة للحجة فيما يزعم؛ فهذا من العجائب. فإن هؤلاء المتعالمين قد يحكمون على بعض الأخطاء بأنها بدع، وليست كذلك، بل قد يحكمون على بعض الكلام الصحيح بأنه مخالف لمنهج السلف، وهم المخالفون لمنهج السلف رضوان الله عليهم. وكم من عائب قولًا صحيحًا ** وآفته من الفهم السقيم ثم يبنون على أفهامهم السقيمة أنها بدع، وأنهم قد نصحوا، وأن العالم قد خالف نصيحتهم وعاند؛ فيبدعون علماء السنة الأبرياء، ثم يبدعون من لا يوافقهم على تبديعهم، بحجة أنهم قد نصحوا، وفي الحقيقة أن ملازمهم مليئة بالبهتان، والطعن في النوايا، وتحميل الكلام ما لا يحتمل، والإلزامات الباطلة. فهؤلاء الأصناف آلة هدم للدعوة السلفية شعروا أو لم يشعروا، ولذلك لا تجد لهم جهودًا ظاهرة في العلم والتعليم ونشر العقيدة الصحيحة والتوحيد والسنة، وتجدهم يظهرون عند الفتن، نسأل الله العظيم أن يسلم الدعوة من ضرر هؤلاء الغلاة المتعالمين، وأن يكبتهم، وأن يحفظ دينه وحملته والمدافعين عنه بالحق. والحمد لله رب العالمين، وصلى الله وسلم على نبينا محمد، وعلى آله وصحبه أجمعين. الشيج محمد بن حذام

..ዛሬ ግን..... -------------- ማን እየጣለኝ ነው የበዛው መውደቄ፡ የእምነት ምልክቴ የት አለ ሰንደቄ፡ መቼ በምን ዘመን እንደጠፋ ሳቄ፡ ማን እንደ ሰረቀኝ እኔ ምን አውቄ፡ ግና ልጅ እያለሁ መሳቅ ያምርብኛል፡ ለክፉም ለደጉም ፈገግታ ያምረኛል፡ በዚህች አለም መተት ገና ሳልሰበር፡ ፈገግታ እያበዛሁ ጨዋታ አውቅ ነበር፡ አሁንማ ደግሞ... በምን ለምን ከሰው እንደሸሸሁ፡ ከብቸኝነት ጋር የት ቦታ እንዳመሸሁ፡ ከማን አጭበርብሬ ከማንን እንደሸሸሁ፡ እንደዚህ ነው ብዬ ባላውቀውም ቅሉ፡ እያደከመኝ ነው ህይወት ምስቅልቅሉ፡ አወ.... በአዕምሮዬ ሀሳብ ስደግን፡ የመከራ ቆሎ ስዘግን፡ ፈገግታ ራቀኝ ዛሬ ግን.... ✍ኑረዲን አል አረቢ http://t.me/nuredinal_arebi

የማለዳ መልእክት (48) ~ መጅሊስ በታሪኩ ከመንግስት ተፅእኖ ነፃ ሆኖ አያውቅም። ለዚህ ዋናው ምክንያት መጅሊሱ ላይ የሚቀመጡ አካላት ባህሪ ሳይሆን የፖለቲከኞቹ ፍላጎትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ባህሪ ነው። ከዚያ የሚቀመጡ ሰዎች ድባቡን ያዩና ከ "አየር ንብረቱ" ጋር ራሳቸውን ያስማማሉ። የ1987ቱ የአንዋር መስጂድ ብጥብጥ ምክንያት ከጥቅም ግጭት ባለፈ የመንግስት አካላት ፍላጎት ከጀርባ ነበር። በሁለቱም ጎራ የተሰለፉ አካላት የተሻለ የመንግስት ድጋፍ እንዳላቸው ያስቡ ነበር። ኋላ ላይ አሕ^ባሽ ከሊባኖስ ተጋብዞ የገባውም ከመጅሊስ ሰዎች ፍላጎት ባለፈ የመንግስት ፍላጎት ስለነበር ነው። ዛሬ ላይ ያለው የፖለቲካውን ነፋስ ተከትሎ የመጣው የመጅሊስ ለውጥም ያለቀለትና የማይነካ አይነት አይደለም። ነገ ሊቀየር ይችላል። እንዲያውም በአንዳንድ አካባቢዎች ከወዲሁ አንዳንድ ደስ የማይሉ ሽታዎች ያሉ ይመስላል። መጅሊስ ላይ በየመዋቅሩ ያሉ አካላት ይህንን ተገንዝበው ለህዝባችን ዐቂዳውን ማስተማር ላይ ወይም ለማስተማር ምቹ ድባብ እንዲኖር ማድረግ ላይ መሬት የረገጠ ስራ ሊሰሩ ይገባ ነበር። ነበር የምለው በተግባር እየሆነ ስላላይደለ ነው። በተለይ አማራ ክልል ላይ ከ'ኮስሞቲክ' ስራዎች በመውጣት ዛሬ ላይ ቆፍጠን ብሎ መስራት ይሻል ነበር። ነገሮች ቢቀያየሩ ተፅእኖው ከሌሎች አካባቢዎች ይለያል። ሌላው ቢቀር ለተሻለ መስለሓ ብላችሁ የገባችሁ ወገኖች ራሱ ከልብ በመመካከር ህዝብ ላይ ብትሰሩ መልካም ነው። ጊዜው አሁንም አልረፈደም። ብዙ መራመድ የሚያስችላችሁ አቅም ባይኖራችሁ እንኳ በአቅማችሁ ልክ የምትችሉትን ሳትሰሩ ጊዜው እንዳያልፍ ብታስቡበት ይሻላል። እውነት ለመናገር በተበላሸ ዐቂዳውም ቢሆን ሳይልፈሰፈስ ቆፍጠን በማለት እና መሬት የወረደ ስራ በመስራት በኩል ከመጅሊስ ተቋማት የተባረረው አሕ^ባሽ የተሻለ ትጋት አለው። አሕ^ባሽ የመጅሊሱ መዋቅር በእጁ ሳለም ያለምንም ይሉኝታ ህዝብን ለመለወጥ እስከ ደም ጠብታ ታግሏል። የያዘው ዐቂዳ ክር^ፋትና የመንግስት ዓይን ያወጣ ጣልቃ ገብነት ነው ወደ ህዝብ ልብ ከመግባት እንቅፋት የሆነበት። ከመሆኑም ጋር ለብልሹ ዐቂዳው በመዋደቅ ላይ ከመጅሊሱ ደጅ ርቆም አልቆመም። ዳግም ከተመለሰም ከቀደመው የበለጠ እንደሚጠቀምበት ይጠበቃል። ያ እንዳይሆን ወይም እውን ቢሆን እንኳ ጉዳት ለመቀነስ ደግሞ ፖለቲከኛ ተደግፎ መተኛት ሳይሆን ህዝብን ትክክለኛውን አስተምህሮት ማስታጠቅ ነው የሚገባው። የሹማምንትን ጫና ለመጋፈጥ ወይም ለመቀነስ ትክክለኛው መንገድ ደሞ ከአላህ በታች ህዝብን ማንቃት ነው ሁነኛው ስራ። አላህ ልብ ይስጠን። = (ኢብኑ ሙነወር፣ ረቢዑል ኣኺር 02/1448) = የቴሌግራም ቻናል:- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

አላህ ከጎንህ ከሆነ ምንም አይነት ጭንቅ ቢኖር መጨረሻው ሁሌም ቀላል ይሆናል። _1. ኢብራሂም (ዐለይሂሰላም) ከእሳት_ ንጉሡ በላያቸው ውስጥ በጣለበት ጊዜ አላህ እሳቱን يا نار كوني برداً
አላህ ከጎንህ ከሆነ ምንም አይነት ጭንቅ ቢኖር መጨረሻው ሁሌም ቀላል ይሆናል። _1. ኢብራሂም (ዐለይሂሰላም) ከእሳት_ ንጉሡ በላያቸው ውስጥ በጣለበት ጊዜ አላህ እሳቱን يا نار كوني برداً وسلاماً ብሎ በረዶና ሰላም አደረገለት። _2. ኑህ (ዐለይሂ ሰላም) - ከጦፋን_ ህዝቡ አላመነም፣ አላህ ታላቅ ጎርፍ ሲያመጣ እሱን እና አማኞችን በመርከብ አዳናቸው። _3. ዩኑስ (ዐለይሂሰላም) - ከዓሣ ሆድ_ ከህዝቡ ተቆጥቶ ሲሄድ ዓሣ ዋጠችው። በጨለማው ውስጥ لا إله إلا أنت سبحانك ብሎ ሲያወድስ አላህ ከሆዷ አወጣው። _4. ዩሱፍ (ዐለይሂሰላም) - ከጉድጓድ እና ከእስር_ ወንድሞቹ በጉድጓድ ውስጥ ጣሉት፣ ከዚያም በሀሰት ክስ ታሰረ። በመጨረሻ ግን አላህ የግብጽ ንጉሥ አደረገው። _5. ሙሳ (ዐለይሂሰላም) - ባህር ተሰንጥቆ_ ፊርዐውን ሲያሳድዳቸው አላህ ባህሩን ከፍሎላቸው አሻገራቸው፣ ጠላቶቻቸውን ደግሞ አሰጠማቸው። _6. ሙሐመድ ﷺ - ጋረ-ሠውር (የሠውር ዋሻ)_ ከመካ ወደ መዲና ሲሄዱ በዋሻው ውስጥ ተደብቀው ሳሉ አላህ በሸረሪት ድር እና በርግብ እንቁላል አዳናቸው። አላህ ሁሉንም ፈተና ያቃልልልን! 🤲💦💦💦

መሰናክል በበዛ ቁጥር መንገዱ ይረዝማል እንጂ መዳረሻውን አይለውጠውም። ትክክለኛውን አቅጣጫ ይዘን ስንጓዝ የሚያጋጥሙን ፈተናዎች ተስፋ ሊያስቆርጡን ሳይሆን፣ ለድል የምንሰጠውን ዋጋ ከፍ አድርገው ሊያስተምሩን የመጡ ምዕራፎች ናቸው። ነፋሱ ኃይለኛ ሲሆን ጀልባው ትንቅንቅ ይፈጥራል፤ ነገር ግን ማዕበሉን አልፎ ወደቡ የሚደርሰው በጽናት የገሰገሰ ብቻ ነው። ስለዚህ፣ እምነታችንን አጽንተን፣ ቆራጥነትን አንግበን፣ እያንዳንዱን እክል ደረጃ በደረጃ ልንወጣው ይገባል። አቡ ዑበይዳ t.me/AbuOubeida

ክብር ለዑለሞቻችን! ሸይኽ ዐብዱል ሙሕሲ አል–ዓባድ ሐፊዞሁላህ፦ በዚህ ዘመን ከታላላቅ የሰለፊያ ዑለሞች መካከል በዒልምም ሆነ በእድሜ ከግንባር ቀደም የሚቆጠሩ ታላቅ የሐዲስ ሊቅ ናቸው። አይደለም ሸይኽ ዐብዱልሙሐሲን ይቅርና ተማሪዎቻቸው በዚህ ዘመን በእድሜም ሆነ በዒልም አቻ የሌላቸው ናቸው። ከተማሪወቻቸውም መካከል፦ 1.የየመኑ ሙሐዲስ ታላቁ ዐሊም ሸይኽ ሙቅቢል አል–ዋዲዒይ ረሒመሁላህ 2.ታላቁ ዐሊም ሸይኽ ረቢዕ ኢብኑ ሃዲ አል–መድኸሊይ ረሂመሁላህ 3.ሸይኽ ዑበይድ አል–ጃቢሪይ ረሂመሁላህ 4.ሸይኽ ሷሊሕ አስ–ሱሐይሚይ  ሐፊዘሁላህ ይገኙበታል። ✍🏻 ኢብኑ ሙሐመድዘይን

📍 تفريغ دورة دراسات في المنهج (بصيغة pdf) للشيخ سليمان الرحيلي وفقه الله ዐረበኛ የምትችሉ ኪታቡን አውርዳችሁ ብታነቡት በአላህ ፍቃድ እጅግ ተጠቃሚ ትሆናላችሁ። የተዳሰሱ  ነጥቦች፦ 1, መንሀጀ ሰለፍ 2, በዘመኑ ያሉ ጠማማ አንጃዎች 👉 ተብሊግ 👉 ኢኽዋን 👉 ዳዒሽ 3, ኢስላምን ያስጠሉ ግለሰቦች (ሐሰን አል–በና፣ሰይድ ቁጥብ፣አቡ አዕላእ አል–መውዱውዲ)  እና ሌሎችም የጥመት መሪዎች ረድ የተሰጠበት ዳሰሳ አካቶ ይዟል። ኪታቡ ከላይ እተጠቀሱት ነጥቦች ላይ ብቻ የተገደበ አይደለም። ሰፋ ባለሁኔታ ስለመንሀጅ የተዳሰሰበት ጥሩ ትምህርት ነው። አላህ ተጠቃሚ ያድርገን። አሚን። = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/Abulabas1444 https://t.me/Abulabas1444

ማነው ፖለቲካ የገባው? ~ የሰዎች የኋላ ዳራ (background)፣ ስሜት፣ ፍላጎት፣ የሚከተሉት አስተሳሰብ፣ ቡድናዊ አመለካከት፣ የንቃት መጠን፣ የትምህርት ደረጃ፣ የዲን ግንዛቤና አቋም፣ ወዘተ ይለያያሉ። ይህንን ተከትሎም የሚደግፉትና የሚቃወሙት የፖለቲካ ኃይል ይለያያል። እዚህ ድረስ መግባባት ይቻላል። የምንለያየው ይህንን እውነታ የሚያረጋግጥ ተግባራዊ ማሳያ ስንመዝ ነው። የሚገርመው እነሱ የሚደግፉትን የማይደግፍ፣ እነሱ የሚጠሉትን የሚወድን አካል "አንተ ፖለቲካ አልገባህም" የሚሉ ሰዎች ሁኔታ ነው። ልክ ፖለቲካ መረዳት ማለት ከነሱ ስሜት ጋር መግጠም የሆነ ይመስል። ስለ ፖለቲካ ብዙ የለቀለቀ ወይም የፈተፈተ ሁሉ ፖለቲካ ገብቶታል ማለት አይደለም። ዝም ያለም ሁሉ አልገባውም ማለት አይደለም። ነጋ ጠባ ዜና መዘገብ ፖለቲካ መረዳት አይደለም። ትንሽ ትልቁን ከሴራ ጋራ እያስተሳሰሩ መጎንጎንም የፖለቲካ ችሎታ ሳይሆን የራስን ስንፍና መሸፈኛ ሰበብ ነው። ይሄ ነገር በጣም ከመብዛቱ የተነሳ "ዐረብ ልጁ ትምህርት ቤት ቢወድቅበት የአይ^ ሁድ እጅ አለበት" ከማለት አይመለስም እስከማለት የተሳለቁ አሉ። ግነቱ በውስጡ የሆነ እውነት አለው። ለምሳሌ ያክል የሀገራችንን የዘር ፌዴራሊዝም በፅኑ የሚያወግዝ ብዙ ኃይል አለ። አሀዳዊ ስርአትን ከሺርክ በላይ የሚኮንንም ብዙ ወገን አለ። አስቡት እንግዲህ ሁሉም እየተነሳ ሌላኛውን አካል ፖለቲካ አልገባህም እያለ ሲያጣጥል። አተያያችን የተራራቀው በዋናነት በግንዛቤዎችን መበላለጥ ምክንያት አይደለም። ይልቁንም በብልጣብልጥና ስግብግል ባህሪያችን የተነሳ ነው። በትምህርት ዝግጅታቸውና ደረጃቸውም፣ በሚከተሉት እምነትም ተመሳሳይ የሆኑ ሁለት ከአማራና ከኦሮሞ የሆኑ ኢትዮጵያውያን በዘር ፌዴራሊዝምና በአሃዳዊ ስርአት ላይ ያላቸው ምርጫ ተቃራኒ ነው። ለምን? ግልፅ ነው። ታሪክን የሚረዱት በተራራቀ መልኩ ነው። የዛሬ ምርጫቸውም እንዲሁ የተራራቀ ነው። ልክ እንደዚሁ እኔና አንተ ዐቂዳችንና መንሀጃችን እስከተለያየ ድረስ በሙስሊም ሀገራትና ቡድኖች ላይ ያለን ፖለቲካዊ አተያያችንና ውግንናችንም ይለያያል። ላንተ የዑመር ጠላት የሆኑ ሺዐዎችን መውደድ ኖርማል ነው። ለኔ ደግሞ ይሄ ፈፅሞ ሊያቀራርበን የማይችል ቀይ መስመር ነው። ላንተ "ሙስሊም" የሚለው ስሙ እስካለ ድረስ የፈለገውን ቢያራምድ ዋናው "ሞት ለአሜሪካ!" ማለቱ ነው። ከአሜሪካ ጋር አይንና ናጫ የሆነችው ሰሜን ኮሪያ ራሱ የአሕመዲያ መዝሀብ ተከታይ ብትሆን ኖሮ ሱኒ ሙስሊሞችን እያነቀች ብትገ ^ድል እንኳ ከመደገፍ አትመለስም ነበር። ለማንኛውም እንደ ሙስሊም ነገሮችን ሁሉ የምንመለከትበት መነፅር ዲን ሊሆን ይገባል። የዲን መሰረቱ ደግሞ ተውሒድ ነው፣ ዐቂዳ ነው። ወላእና በራአችን ዐቂዳን መሰረት ያደረገ ሊሆን ይገባል። ይህንን ነጥብ ነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "ከኢስላም ቋጠሮዎች ሁሉ ጠንካራው" ሲሉ ነው የገለፁት። የዐቂዳ ጉዳይ ላንተ ውሃ የማያነሳበት ምክንያት ለምን እንደሆነ ራስህን ጠይቅ፣ ልብህን አድምጥ። ምናልባት ለማስተዋል ከጠቀመህ - እንዲያው ምናልባት - ሺዐ እና ሱኒን ለማቀራረብ በጣም ለረጅም ዘመናት የደከመው ዩሱፍ አልቀርዷዊይ በዚህ ጥረታችን ሺ0ዎች አተረፉበት እንጂ ለሱኒው ዓለም ከጉዳት በስተቀር ያተረፈው ፋይዳ የለውም ማለቱን ያዝ። = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

ጓደኛውን ማስተናገድ ላይ ድንበር የሚያልፍ እና ወንድሙን ችላ የሚል በርግጥም ሞኝ ነው። የትኛውም አይነት ከባድ ሁኔታ ቢፈጠር፣ የፈለገ ግኑኝነቱ ቢከፋ በወንድሞች መሃል ሊጠፋ የማይችል የስጋና የመንፈስ ትስስር አላህ አስቀምጧል። ይህ ትስስር ምንም እንኳን በ አንዳንድ ወንድሞች ላይኖር ቢችልም ህመም ወይም ሞት ቢመጣ ወዲያው ወደ ቦታቸው ይመለሳሉ።ምን ያህል ወንድሞች ወንድማቸውን አባረው ከሞተ ቡሃላ የተጸጸቱ ናቸው? "ምናለ እንዲህ ባላደረግኩ" ብለው የተቆጩ ብዙ ናቸው። ጓደኝነት ከሆነ ጊዜያዊ ነው። ጥንካሬው የሚወሰነው በሁኔታዎች መመቻቸት፣ ፍላጎትን በማሟላት ላይ የተመሰረተ ነው። ትንሽ ነገር ትስስራችሁን ያበላሻል።ፍላጎት ካላሟላችሁ ሁሉም ነገር ያበቃል። ባለፉት ጊዜያት ልክ እንደማንኛውም ሰው ቅርብ ጓደኝነት ከብዞዎቹ ጋር ነበረኝ።ለአመታትም የቆየ ነበር።በምንም ተአምር ሊደክም፣ ሊቋረጥ የማይችል እስኪመስለን ድረስም ደርሶ ነበር። ያ ጓደኝነት ከወንድሞቼ ጋር ካለኝ ግኑኝነትም በላይ ነበር። ይሁን እንጂ ከግዜ ቡሃላ ከአንዳንዱ ጋር ይደክም፣ከሌላው ጋር ይቋረጥ፣ አብሮ መቀጠል ከባድ እስኪሆን ድረስ ደርሶ ነበር። የሚገርመው ነገር ለዚህ ነገር ምክንያቱ ምን እንደሆነ አይታወቅም። "ምን ተፈጥሮ ይሁን የተራራቅነው?" ብላቹ አንዱን ብትጠይቁ በቂ ምላሽ አታገኙም። ብዙ ግዜያትን መከታ የሚሆን፣ ታማኝና ወዳጅነቱ ዘላቂ የሆነ ጓደኛ ስፈልግ ቆይቻለሁ። አንድንም ማግኘት አልቻልኩም። ከ አንድ ሰው ጋር ጓደኝነት ስንጀምር "በቃ! ይህ ነው የተበቅኩት ሰው" እንላለን። ከተወሰነ ቆያት ቡሃላ፣ ብዙ መቀላቀል ሲበዛ ጓደኛችሁ ግዴለሽ ሲሆን፣ አብራችሁ ስላላችሁ የሚሰላች፣ ጓደኝነታችሁ እንዲላላ ያለውን ፍላጎት ማየት ትጀምራላችሁ። ከዚህ ቡሃላ ነበር ከ አንድ ፍጹም የሆነ ድምዳሜ የደረስኩት። ምን ብትወዳጁ የገዛ ወንድም አይነት ወዳጅነት የትም እንደማይገኝ፤ከወንድም ውጪ በሙሉ ልብ የሚተማመኑበት መከታ እንደሌለ፣ ላይቋረጥ የሚችል ፍቅር ከወንድም ጋር ብቻ እንደሚገኝ ረፍዶም ቢሆን ገባኝ።ከወንድማችሁ ጋር ያለው ወዳጅነት አብራችሁ ብዙ ስለቆያችሁ የሚቀንስ አይደለም።የሆነ ችግር በመሃላችሁ ቢፈጠር እንኳን መልሳችሁ ማስተካከል፣ ወደ ቀድሞ ፍቅራችሁ መመለስ ቀላል ነው።እንዲህ አይነቱን ጠንካራ ወዳጅነት ስንት ሰው ነው ወዳጅነታቸውም ለማይዘልቅ ጓደኞቹ ሲል ያላላው፣ ወንድሞቹን ያራቀው?! እና አደራችሁን ለጓደኛ ብላችሁ የወንድማችሁን ወዳጅነት አታላሉ።"የኔው ነው የትም አይሄድም" ብላችሁ አትጣሉት። አንዳንዴ ላይመለስ መሄድም አለ። በቅርብም ይሁን በሩቅ ይጸጽታቹሃል። ከወንድማችሁ ጋር ምን ያህል ብትቆራረጡ፣ብትጣሉ፣ መግባባት ቢያቅታችሁ በዚህ ሁሉ ውስጥ ለናንተ ያስባል፣ ስለናንተ ይጨነቃል፣ ፍቅሩን ይዞ ያቆያል። "አጥፍቻለሁ" ብላችሁ ብትመለሱ በሱ ዘንድ የነበራችሁን ክብርና ደረጃ መልሳችሁ ታገኛላችሁ። ጓደኛ ግን አንድ ግዜ ብትጋጩ፣ ብትቆራረጡና የሆነ ነገር ብትሉት በልቡ ውስጥ ቁጣን፣ንዴትን እና ጥላቻን እንጂ ሌላ አታገኙም። ይቅርታ ብትጠይቁ እንኳን ያ የቀድሞ ክብራችሁን፣ደረጃችሁን፣ ፍቅራችሁ አይመለስም።ይህ በአብዛኛው ያለ እውነታ ነው። ለብዙ ግዜያት የተቆራረጡ ፣ ብዙ ደረጃ የደረሱ ወንድሞች ከሆነ ግዜ ቡሃላ አንድ ሆነው፣ ጥሩ ሁኔታ ላይ የደረሱ ሰዎችን አይቻለሁ።እስከመዘላለፍና መለያየት የደረሰ ጓደኝነት ግን ወደቀድሞ ፍቅር ተመልሶ ሲመጣ አላየሁም። ሂወት ስለሚቀጥል አብሮ ተኮነ እንጂ በልብ እንደቀድሞ መሆን ከባድ ነው። በቃ ምን አለፋችሁ ከተራራቃችሁት ጓደኛችሁ ጋር ዳግም መገናኘትና እንደቀድሞ መሆን ማለት ሶስቴ የተፈታች ሴት ወደ ባሏ እደምትመለሰው ነው!…(ሌላ አግብታ ፈታ ካልሆነ ሚስቱ መሆን አትችልም) #ትዝብት ከደጋጎች አለም ክፍል 65 @Jemalendro33 https://t.me/daewaselefiyaArbaminch/16482

🔶 ታቢዒዩ ኢብራሂም አተይሚ ረሂመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦ ﴿شيئان قطعا عني لذة الدنيا : ذكر الموت وذكر الموقف بين يدي الله تعالى﴾ “ሁለት ነገሮች የዱኒያን ጥፍጥና ከውስጤ እንዲወጣልኝ (እንዲቆርጥልኝ) አድርገውኛል። ሞትን ማስታወሴና በላቀው አላህ ፊት ለፍርድ መቆሜን ማስታወስ።” ተዝኪራ ቢዓህዋሊል መውታ አልአኼራ፡ (125) = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/DeewaSelefyya1448 https://t.me/DeewaSelefyya1448.

➐ ቱን የቁረአን ተፍሲር አፕ የያዝ 🥇بن كشير 🥈القرطبى 🥉الطبرى ⓸اللغوى ⓹السعدى ➅الوسيط ➆الميسر በጣም አስፈላጊ አፕ ነው አውርዳችሁ ተጠቀሙበት እዛውም ላይ ቁረአን የሚታይ የሚቀራ አለው ። 🇸🇦የቴሌግራም ቻናል https://t.me/KedmiyaLetewhid9

ወሰጥያ ምን ማለት ነው⁉️ ➖➖➖➖➖➖➖ 📌ﻗﻨﺎﺓ الحرمين📌 📧Telegram: 👉 https://t.me/A1R2O3A4

{ ۞ قُلۡ یَـٰعِبَادِیَ ٱلَّذِینَ أَسۡرَفُوا۟ عَلَىٰۤ أَنفُسِهِمۡ لَا تَقۡنَطُوا۟ مِن رَّحۡمَةِ ٱللَّهِۚ إِنَّ ٱللَّهَ یَغۡفِرُ ٱلذُّنُوبَ جَمِیعًاۚ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلۡغَفُورُ ٱلرَّحِیمُ } [سُورَةُ الزُّمَرِ: ٥٣]

✍ኢላሂ..     እየወደቅኩም እየተነሳሁም፣ እያጠፋሁም እያለማሁም፣ መልካም ሥሠራ ደስ እያለኝ፣ ሳጠፋ በቁጭት እየነደድኩ ..እዚህ ደርሻለሁ። 🍁ብዙ መልካም ሥራ የለኝም አውቃለሁ፡፡ ግና የተውሒድን ቃል በመያዜ ብቻ  በአላህ ላይ ያለኝ ተስፋ ከፍ ያለ ነው፡፡  ባጎደልኩት ነገር ሁሉ እንዲሞላልኝ በየዕለቱ እማፀነዋለሁ፡፡ ♻️ሕይወት አድካሚ ጉዞ ናት ወዳጆቼ ፡፡ በጉዞዬ ላይ ሁሉ አምላኬ ረሂሙ ባይለየኝ እመርጣለሁ፡፡ እሱ ካልመራኝ እጠፋለሁ፣ እሱ ካላፀናኝ እንሸራተታለሁ፣ እሱ ካልደገፈኝ እወድቃለሁና፡፡ ☝️ኢላሂ … ጌታዬ ሆይ! በተቸገርኩ ሰሞን ረድተህኛል፣ በታመምኩ ጊዜ አሽረህኛል፣ በፈራሁ ጊዜ ደርሰህልኛል፣ በብቸኝነቴ ጊዜ ደግፈህኛል፣ በደስታም በሐዘንም፣ በመከራም በችግርም ከጎኔ ነበርክ … ☝️ያ ረብ! ስል ሁሉ ነገር ይቀለኛል …. ➙መከራዬ ሲበዛ፣ ➙ ፈተናዬ ሲበረታ፣ ➙ ሸክሜ ሲከብድ፣ ➙ጉዳዬ ሁሉ ሲጠና፣ ➙ ስደኸይ፣ ስቸገር፣ ሰዉነቴ ሲደክም፣ ኢማኔ ሲሟሽሽ፣ ጉልበቴ ሲዝል፣ ቀልቤ ስትደርቅ …. ወዳንተ እዋደቃለሁ ያ አላህ! ያ አላህ!! እላላሁ፡፡ • ጌታዬ ሆይ በየትንፋሼ ሁሉ ወዳንተ የምቀርብ አድርገኝ፡፡ ኢላሂ…💔💔💔

የረሳነው መስታዎት ~~ ° አካልህ ተውቦ ገፅታህ አብቦ ሰውነትህ ደምቆ መልክህ አሸብርቆ • መደነቅ ያማረው፣ መኮፈስ ያጓጓው፣ መስታወት ያሰኘው፣ ‘እየኝ’ ያለህ ’ለታ፣ እፍኝ አፈር ዘግነህ ተመልከት በጌታ!! ተመልከት በአላህ! ተመልከት በቃሉ ቋንቋ ብሄር ሰጥቶ ቢያግባባህ ጀሊሉ ዘር እየመነዘርክ ትጎራለህ አሉ! • ወንድማለም! እስኪ ተመልከት ከጭቃው፣ ተመልከት ከምድሩ አንተን አንተን ይላል፣ ዘመድ ከዘመዱ ሰውም ከ አፈሩ! • መልክህ ረጋፊ ነው፣ ቀለምህ ጠፊ ነው፣ ቋንቋህ አላፊ ነው፣ ብሄርህ ትርፍ ነው፣ አካልህ ፈራሽ ነው፣ ዋናው ማንነትህ አፈር ነው ጭቃ ነው። • ወንድሜ! እስኪ አትንጠራራ አትደርስም ተራራ! እስኪ አትንገዳገድ ምድር ላትሰረጉድ አፈር ነህ ያ’ፈር ልጅ የግም ጭቃ ውላጅ! • አፈር ነው መነሻህ አፈር ነው መድረሻህ አፈር መጀመሪያህ አፈር መጨረሻህ ነገም ከ አፈር ነው ዳግም ’ምትወጣ እንደተበተነ እንደ መንጋ አንበጣ!! • ከጭቃ ተሰርቶ፣ ከጭቃ ተነስቶ፣ በቆሻሻ መውጫ ሁለት ጊዜ ወጥቶ፣ መሬት አይንካኝ ሲል በኩራት ሲፏልል፣ በትእቢት ሲሸልል፣ አይደንቅም ወይ ከቶ!! አይ የሰው ልጅ!! = (ኢብኑ ሙነወር፣ ነሃሴ 29/2011) የቴሌግራም ቻናል፦ t.me/IbnuMunewor

ቢያውቁ ኖሮ......! "ይህች የዱኒያ ህይወት በውስጧ ከያዘቻቸው ሃብትና አጓጊ ጌጣ-ጌጦች ጋር በሙሉ መታለያና ከጊዜ በኋላ የሚያበቃ ጨዋታ ብቻ እንጂ ሌላ ምንም አይደለችም። "እውነተኛ እና የዘላለም ህይወት ማለት የኣኺራ ሀገር ህይወት ነው። ሰዎች "ይህን #ቢያውቁ ኖሮ የዚችን ጠፊና አላቂ ዓለም ህይወት ከኣኺራ ባላስበለጡ፤ በርሷም ተታለው ኣኺራቸውን የሚያበላሽ ስራ ባልሰሩ ነበር። አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል:- 【وَتَزَوَّدُوا فَإِنَّ خَيْرَ الزَّادِ التَّقْوَىٰ ۚ وَاتَّقُونِ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ】 【ስንቅ ያዙ፤ ከስንቆች ሁሉ በላጩ አላህን መፍራት ነው፤ የአእምሮ/ የልብ ባለቤቶች ሆይ ፍሩኝ!】 ሱረቱ'ል በቀራ/197 https://t.me/Abulabas1444 https://t.me/Abulabas1444

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته የሥራ ቅጥር ማስታወቂያ በጉራጌ ዞን በተለያዩ አካባቢዎች የዳዕዋና የትምህርት አገልግሎት ሊሰጡ የሚችሉ ኡስታዞችን መቅጠር እንፈልጋለን። የሥራው መስፈርቶች አመልካቾች፦ - ቁርአንን በተጅዊድ ማስተማር የሚችሉ፤ - ሙኽተሰር ኪታቦችን ማስቀራትና ማስተማር የሚችሉ፤ - ኹጥባ ማድረግ የሚችሉ፤ - ዳዕዋ ማድረግ የሚችሉ፤ - በአማርኛ ወይም በጉራጌኛ ቋንቋ መግባባት የሚችሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል። የደመወዝ ሁኔታ ደመወዝ፦ በስምምነት የሚወሰን። ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ኡስታዞች፣ ለበለጠ መረጃና ለማመልከት በሚከተለው የቴሌግራም ሊንክ ያናግሩን፦ የቴሌግራም ሊንክ፦ https://t.me/Alwio1446 وفق الله الجميع لما يحبه ويرضاه

قال الشاعر : وإذا رزقت بمن يحبك صادقا حافظ عليه فمثله لا يوجد يكفيك قلب واحد عن أمة تحظى به بعد العناء وتسعد https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie