ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

الذهاب إلى القناة على Telegram

قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
908
المشتركون
-324 ساعات
-157 أيام
+4830 أيام
أرشيف المشاركات
ጓደኛውን ማስተናገድ ላይ ድንበር የሚያልፍ እና ወንድሙን ችላ የሚል በርግጥም ሞኝ ነው። የትኛውም አይነት ከባድ ሁኔታ ቢፈጠር፣ የፈለገ ግኑኝነቱ ቢከፋ በወንድሞች መሃል ሊጠፋ የማይችል የስጋና የመንፈስ ትስስር አላህ አስቀምጧል። ይህ ትስስር ምንም እንኳን በ አንዳንድ ወንድሞች ላይኖር ቢችልም ህመም ወይም ሞት ቢመጣ ወዲያው ወደ ቦታቸው ይመለሳሉ።ምን ያህል ወንድሞች ወንድማቸውን አባረው ከሞተ ቡሃላ የተጸጸቱ ናቸው? "ምናለ እንዲህ ባላደረግኩ" ብለው የተቆጩ ብዙ ናቸው። ጓደኝነት ከሆነ ጊዜያዊ ነው። ጥንካሬው የሚወሰነው በሁኔታዎች መመቻቸት፣ ፍላጎትን በማሟላት ላይ የተመሰረተ ነው። ትንሽ ነገር ትስስራችሁን ያበላሻል።ፍላጎት ካላሟላችሁ ሁሉም ነገር ያበቃል። ባለፉት ጊዜያት ልክ እንደማንኛውም ሰው ቅርብ ጓደኝነት ከብዞዎቹ ጋር ነበረኝ።ለአመታትም የቆየ ነበር።በምንም ተአምር ሊደክም፣ ሊቋረጥ የማይችል እስኪመስለን ድረስም ደርሶ ነበር። ያ ጓደኝነት ከወንድሞቼ ጋር ካለኝ ግኑኝነትም በላይ ነበር። ይሁን እንጂ ከግዜ ቡሃላ ከአንዳንዱ ጋር ይደክም፣ከሌላው ጋር ይቋረጥ፣ አብሮ መቀጠል ከባድ እስኪሆን ድረስ ደርሶ ነበር። የሚገርመው ነገር ለዚህ ነገር ምክንያቱ ምን እንደሆነ አይታወቅም። "ምን ተፈጥሮ ይሁን የተራራቅነው?" ብላቹ አንዱን ብትጠይቁ በቂ ምላሽ አታገኙም። ብዙ ግዜያትን መከታ የሚሆን፣ ታማኝና ወዳጅነቱ ዘላቂ የሆነ ጓደኛ ስፈልግ ቆይቻለሁ። አንድንም ማግኘት አልቻልኩም። ከ አንድ ሰው ጋር ጓደኝነት ስንጀምር "በቃ! ይህ ነው የተበቅኩት ሰው" እንላለን። ከተወሰነ ቆያት ቡሃላ፣ ብዙ መቀላቀል ሲበዛ ጓደኛችሁ ግዴለሽ ሲሆን፣ አብራችሁ ስላላችሁ የሚሰላች፣ ጓደኝነታችሁ እንዲላላ ያለውን ፍላጎት ማየት ትጀምራላችሁ። ከዚህ ቡሃላ ነበር ከ አንድ ፍጹም የሆነ ድምዳሜ የደረስኩት። ምን ብትወዳጁ የገዛ ወንድም አይነት ወዳጅነት የትም እንደማይገኝ፤ከወንድም ውጪ በሙሉ ልብ የሚተማመኑበት መከታ እንደሌለ፣ ላይቋረጥ የሚችል ፍቅር ከወንድም ጋር ብቻ እንደሚገኝ ረፍዶም ቢሆን ገባኝ።ከወንድማችሁ ጋር ያለው ወዳጅነት አብራችሁ ብዙ ስለቆያችሁ የሚቀንስ አይደለም።የሆነ ችግር በመሃላችሁ ቢፈጠር እንኳን መልሳችሁ ማስተካከል፣ ወደ ቀድሞ ፍቅራችሁ መመለስ ቀላል ነው።እንዲህ አይነቱን ጠንካራ ወዳጅነት ስንት ሰው ነው ወዳጅነታቸውም ለማይዘልቅ ጓደኞቹ ሲል ያላላው፣ ወንድሞቹን ያራቀው?! እና አደራችሁን ለጓደኛ ብላችሁ የወንድማችሁን ወዳጅነት አታላሉ።"የኔው ነው የትም አይሄድም" ብላችሁ አትጣሉት። አንዳንዴ ላይመለስ መሄድም አለ። በቅርብም ይሁን በሩቅ ይጸጽታቹሃል። ከወንድማችሁ ጋር ምን ያህል ብትቆራረጡ፣ብትጣሉ፣ መግባባት ቢያቅታችሁ በዚህ ሁሉ ውስጥ ለናንተ ያስባል፣ ስለናንተ ይጨነቃል፣ ፍቅሩን ይዞ ያቆያል። "አጥፍቻለሁ" ብላችሁ ብትመለሱ በሱ ዘንድ የነበራችሁን ክብርና ደረጃ መልሳችሁ ታገኛላችሁ። ጓደኛ ግን አንድ ግዜ ብትጋጩ፣ ብትቆራረጡና የሆነ ነገር ብትሉት በልቡ ውስጥ ቁጣን፣ንዴትን እና ጥላቻን እንጂ ሌላ አታገኙም። ይቅርታ ብትጠይቁ እንኳን ያ የቀድሞ ክብራችሁን፣ደረጃችሁን፣ ፍቅራችሁ አይመለስም።ይህ በአብዛኛው ያለ እውነታ ነው። ለብዙ ግዜያት የተቆራረጡ ፣ ብዙ ደረጃ የደረሱ ወንድሞች ከሆነ ግዜ ቡሃላ አንድ ሆነው፣ ጥሩ ሁኔታ ላይ የደረሱ ሰዎችን አይቻለሁ።እስከመዘላለፍና መለያየት የደረሰ ጓደኝነት ግን ወደቀድሞ ፍቅር ተመልሶ ሲመጣ አላየሁም። ሂወት ስለሚቀጥል አብሮ ተኮነ እንጂ በልብ እንደቀድሞ መሆን ከባድ ነው። በቃ ምን አለፋችሁ ከተራራቃችሁት ጓደኛችሁ ጋር ዳግም መገናኘትና እንደቀድሞ መሆን ማለት ሶስቴ የተፈታች ሴት ወደ ባሏ እደምትመለሰው ነው!…(ሌላ አግብታ ፈታ ካልሆነ ሚስቱ መሆን አትችልም) #ትዝብት ከደጋጎች አለም ክፍል 65 @Jemalendro33 https://t.me/daewaselefiyaArbaminch/16482

🔶 ታቢዒዩ ኢብራሂም አተይሚ ረሂመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦ ﴿شيئان قطعا عني لذة الدنيا : ذكر الموت وذكر الموقف بين يدي الله تعالى﴾ “ሁለት ነገሮች የዱኒያን ጥፍጥና ከውስጤ እንዲወጣልኝ (እንዲቆርጥልኝ) አድርገውኛል። ሞትን ማስታወሴና በላቀው አላህ ፊት ለፍርድ መቆሜን ማስታወስ።” ተዝኪራ ቢዓህዋሊል መውታ አልአኼራ፡ (125) = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/DeewaSelefyya1448 https://t.me/DeewaSelefyya1448.

➐ ቱን የቁረአን ተፍሲር አፕ የያዝ 🥇بن كشير 🥈القرطبى 🥉الطبرى ⓸اللغوى ⓹السعدى ➅الوسيط ➆الميسر በጣም አስፈላጊ አፕ ነው አውርዳችሁ ተጠቀሙበት እዛውም ላይ ቁረአን የሚታይ የሚቀራ አለው ። 🇸🇦የቴሌግራም ቻናል https://t.me/KedmiyaLetewhid9

ወሰጥያ ምን ማለት ነው⁉️ ➖➖➖➖➖➖➖ 📌ﻗﻨﺎﺓ الحرمين📌 📧Telegram: 👉 https://t.me/A1R2O3A4

{ ۞ قُلۡ یَـٰعِبَادِیَ ٱلَّذِینَ أَسۡرَفُوا۟ عَلَىٰۤ أَنفُسِهِمۡ لَا تَقۡنَطُوا۟ مِن رَّحۡمَةِ ٱللَّهِۚ إِنَّ ٱللَّهَ یَغۡفِرُ ٱلذُّنُوبَ جَمِیعًاۚ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلۡغَفُورُ ٱلرَّحِیمُ } [سُورَةُ الزُّمَرِ: ٥٣]

✍ኢላሂ..     እየወደቅኩም እየተነሳሁም፣ እያጠፋሁም እያለማሁም፣ መልካም ሥሠራ ደስ እያለኝ፣ ሳጠፋ በቁጭት እየነደድኩ ..እዚህ ደርሻለሁ። 🍁ብዙ መልካም ሥራ የለኝም አውቃለሁ፡፡ ግና የተውሒድን ቃል በመያዜ ብቻ  በአላህ ላይ ያለኝ ተስፋ ከፍ ያለ ነው፡፡  ባጎደልኩት ነገር ሁሉ እንዲሞላልኝ በየዕለቱ እማፀነዋለሁ፡፡ ♻️ሕይወት አድካሚ ጉዞ ናት ወዳጆቼ ፡፡ በጉዞዬ ላይ ሁሉ አምላኬ ረሂሙ ባይለየኝ እመርጣለሁ፡፡ እሱ ካልመራኝ እጠፋለሁ፣ እሱ ካላፀናኝ እንሸራተታለሁ፣ እሱ ካልደገፈኝ እወድቃለሁና፡፡ ☝️ኢላሂ … ጌታዬ ሆይ! በተቸገርኩ ሰሞን ረድተህኛል፣ በታመምኩ ጊዜ አሽረህኛል፣ በፈራሁ ጊዜ ደርሰህልኛል፣ በብቸኝነቴ ጊዜ ደግፈህኛል፣ በደስታም በሐዘንም፣ በመከራም በችግርም ከጎኔ ነበርክ … ☝️ያ ረብ! ስል ሁሉ ነገር ይቀለኛል …. ➙መከራዬ ሲበዛ፣ ➙ ፈተናዬ ሲበረታ፣ ➙ ሸክሜ ሲከብድ፣ ➙ጉዳዬ ሁሉ ሲጠና፣ ➙ ስደኸይ፣ ስቸገር፣ ሰዉነቴ ሲደክም፣ ኢማኔ ሲሟሽሽ፣ ጉልበቴ ሲዝል፣ ቀልቤ ስትደርቅ …. ወዳንተ እዋደቃለሁ ያ አላህ! ያ አላህ!! እላላሁ፡፡ • ጌታዬ ሆይ በየትንፋሼ ሁሉ ወዳንተ የምቀርብ አድርገኝ፡፡ ኢላሂ…💔💔💔

የረሳነው መስታዎት ~~ ° አካልህ ተውቦ ገፅታህ አብቦ ሰውነትህ ደምቆ መልክህ አሸብርቆ • መደነቅ ያማረው፣ መኮፈስ ያጓጓው፣ መስታወት ያሰኘው፣ ‘እየኝ’ ያለህ ’ለታ፣ እፍኝ አፈር ዘግነህ ተመልከት በጌታ!! ተመልከት በአላህ! ተመልከት በቃሉ ቋንቋ ብሄር ሰጥቶ ቢያግባባህ ጀሊሉ ዘር እየመነዘርክ ትጎራለህ አሉ! • ወንድማለም! እስኪ ተመልከት ከጭቃው፣ ተመልከት ከምድሩ አንተን አንተን ይላል፣ ዘመድ ከዘመዱ ሰውም ከ አፈሩ! • መልክህ ረጋፊ ነው፣ ቀለምህ ጠፊ ነው፣ ቋንቋህ አላፊ ነው፣ ብሄርህ ትርፍ ነው፣ አካልህ ፈራሽ ነው፣ ዋናው ማንነትህ አፈር ነው ጭቃ ነው። • ወንድሜ! እስኪ አትንጠራራ አትደርስም ተራራ! እስኪ አትንገዳገድ ምድር ላትሰረጉድ አፈር ነህ ያ’ፈር ልጅ የግም ጭቃ ውላጅ! • አፈር ነው መነሻህ አፈር ነው መድረሻህ አፈር መጀመሪያህ አፈር መጨረሻህ ነገም ከ አፈር ነው ዳግም ’ምትወጣ እንደተበተነ እንደ መንጋ አንበጣ!! • ከጭቃ ተሰርቶ፣ ከጭቃ ተነስቶ፣ በቆሻሻ መውጫ ሁለት ጊዜ ወጥቶ፣ መሬት አይንካኝ ሲል በኩራት ሲፏልል፣ በትእቢት ሲሸልል፣ አይደንቅም ወይ ከቶ!! አይ የሰው ልጅ!! = (ኢብኑ ሙነወር፣ ነሃሴ 29/2011) የቴሌግራም ቻናል፦ t.me/IbnuMunewor

ቢያውቁ ኖሮ......! "ይህች የዱኒያ ህይወት በውስጧ ከያዘቻቸው ሃብትና አጓጊ ጌጣ-ጌጦች ጋር በሙሉ መታለያና ከጊዜ በኋላ የሚያበቃ ጨዋታ ብቻ እንጂ ሌላ ምንም አይደለችም። "እውነተኛ እና የዘላለም ህይወት ማለት የኣኺራ ሀገር ህይወት ነው። ሰዎች "ይህን #ቢያውቁ ኖሮ የዚችን ጠፊና አላቂ ዓለም ህይወት ከኣኺራ ባላስበለጡ፤ በርሷም ተታለው ኣኺራቸውን የሚያበላሽ ስራ ባልሰሩ ነበር። አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል:- 【وَتَزَوَّدُوا فَإِنَّ خَيْرَ الزَّادِ التَّقْوَىٰ ۚ وَاتَّقُونِ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ】 【ስንቅ ያዙ፤ ከስንቆች ሁሉ በላጩ አላህን መፍራት ነው፤ የአእምሮ/ የልብ ባለቤቶች ሆይ ፍሩኝ!】 ሱረቱ'ል በቀራ/197 https://t.me/Abulabas1444 https://t.me/Abulabas1444

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته የሥራ ቅጥር ማስታወቂያ በጉራጌ ዞን በተለያዩ አካባቢዎች የዳዕዋና የትምህርት አገልግሎት ሊሰጡ የሚችሉ ኡስታዞችን መቅጠር እንፈልጋለን። የሥራው መስፈርቶች አመልካቾች፦ - ቁርአንን በተጅዊድ ማስተማር የሚችሉ፤ - ሙኽተሰር ኪታቦችን ማስቀራትና ማስተማር የሚችሉ፤ - ኹጥባ ማድረግ የሚችሉ፤ - ዳዕዋ ማድረግ የሚችሉ፤ - በአማርኛ ወይም በጉራጌኛ ቋንቋ መግባባት የሚችሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል። የደመወዝ ሁኔታ ደመወዝ፦ በስምምነት የሚወሰን። ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ኡስታዞች፣ ለበለጠ መረጃና ለማመልከት በሚከተለው የቴሌግራም ሊንክ ያናግሩን፦ የቴሌግራም ሊንክ፦ https://t.me/Alwio1446 وفق الله الجميع لما يحبه ويرضاه

قال الشاعر : وإذا رزقت بمن يحبك صادقا حافظ عليه فمثله لا يوجد يكفيك قلب واحد عن أمة تحظى به بعد العناء وتسعد https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie

📆 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ ⏰#ሰብት 0⃣1⃣ #ረቢዓል‐አኽር1⃣4⃣4⃣8⃣ ሂ
📆 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ ⏰#ሰብት 0⃣1⃣ #ረቢዓል‐አኽር1⃣4⃣4⃣8⃣ ሂ

አላህ ሆይ!.... እርዳታህን ከጅዬ - አንገቴን ደፍቼ : ወገቤ አጎንብሶ - ሱጁድ ተደፍቼ : ልቤ ተወክሎህ - እጆቼን አንስቼ : ተስፋን በአንተ ጥዬ - አንብተው አይኖቼ : እርዳኝ ጌታዬ ሆይ! - ይላል አንደበቴ : ደስታን ከኔ አድርጋት - አውጣኝ ከጭንቀቴ : በመልካም ስሞች - በላቁ ባህሪዎችህ : እርዳኝ ጌታዬ ብዬ - ሁሌም ልለምንህ : ከዱኒያ እስከ አኺራ - አንተን እስካገኘህ : t.me/abdu_rheman_aman t.me/abdu_rheman_aman

​«ጌታዬ ሆይ! የቁርኣንን በረካ፣ የቁርኣን መጅሊሶችን እና የቁርኣን ወዳጅነትን አትንሳን። » http://t.me/ibrahim_furii
​«ጌታዬ ሆይ! የቁርኣንን በረካ፣ የቁርኣን መጅሊሶችን እና የቁርኣን ወዳጅነትን አትንሳን። » http://t.me/ibrahim_furii

መረጃዎች ብዥታ በማያጭር መልኩ ፍንትው ብለው የመጡባቸውን ሸሪዐዊ ጉዳዮች ላይ በተለይም የዐቂዳ ርእሶች ላይ መተራረም እንጂ እንደዋዛ እያቃለሉ መተላለፍ አይቻልም። እንዲህ አይነት ጉዳዮችን መተላለፍ የሚቻልባቸው ቀለል ያሉ የኺላፍ ርእሶች አድርጎ ማሰብ መረጃዎችን መደፍጠጥ እና እውነታዎችን ማደባለቅ ነው። እንዲህ አይነት አካሄድ * የዲን ቀይ መስመሮችን ያደበዝዛል፣ * ለቁርአንና ሐዲሥ ያለንን አክብሮት በእጅጉ ይቀንሳል። * ስሜትን እየተከተሉ ከየመዝሀቡ ገርገሩን የማሳደድን አመልን ያመጣል። ከየመዝሀቡ ወይም ከየ ዓሊሙ ነፍሲያን እየተከተሉ ቀላል ቀላሉን ማሳደድ ደግሞ ከልባችን ውስጥ አላህን መፍራትን በማጥፋት አፈንጋጭነት እንዲያቆጠቁጥ ያደርጋል ይላሉ ቀደምት ዑለማኦች። = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

አቡ ሙዓዝ ለትሚዮች በስህተት ላይ እንደሆኑ ያምናል። ሰምታችሁ ፍረዱ ምናልባት ከሱ በላይ መናገር ይዘገንናል። አሁን ላይ በነሱ ዙሪያ ምን ለውጥ አግኝቶ ነው። ነው ዱሮም በነሱ ላይ ሲናገር #በሞቅታ ነው ወላሂ ያ አባ ሙዓዝ  በአለህበት ላይ ቁመህ አስብ ያለበለዚያ ሰለፊዮችን ትተህ እራስ ወዳልከው  ቅሬ ላይ እንኳ የማይጠበቅ አርካባስ ጭፍራ ገብተሀል። ሁላችንም ለራሳችን ነፍስ እንዘንላት ያጀምዓ የቴሌግራም ቻናል፦ http://t.me/Abulabas1444 http://t.me/Abulabas1444.

ኺላፍ ሁሉ መጠኑ አንድ አይደለም። ዑለማእ እነሱ ዘንድ ሚዛን የሚደፋውን በማስረጃ እያበጠሩ በመግለፅ የሚተላለፉባቸውን ነጥቦች በሆደ ሰፊነት ማስተናገድ ያስፈልጋል። በእንዲህ አይነት ነጥቦች ላይ ያላግባብ የከረረ አቋም መያዝ * የዑለማእ አያያዝ አይደለም። * ለጭቅጭቅና ልዩነት ይዳርጋል። * በሌሎች ላይ ድንበር በማሳለፍ በደል ላይ ይጥላል። * የሆነ ወቅት ላይ በመረጃ ገምግመን ሃሳብ ብንቀይር ለሐቅ እጅ መስጠት እንዲከብደን ያደርጋል። * ተመሳሳይ መጠን ባላቸው ጉዳዮች ላይ የተለያየ አቋም በማራመድ ተቃርኖ ላይ ይጥላል። ይሄ ከመሆኑ በፊት የኺላፍ ጉዳዮችን ዑለማእ በሚይዙበት መጠን እየያዝን መሆናችንን እርግጠኛ መሆን ያስፈልጋል። = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

ተስፋችን በ2019 ላይ ሳይሆን፣ የዘመናት ጌታ በሆነው በአላህ ላይ ነው! አላህ ሁልጊዜም የተሻለውን ይወፍቀን፤ የተሰበረውን ይጠግንልን፤ ያጣነውንም በበጎ ይተካልን! አሚን።

الشيخ العلامة الفقيه صالح بن فوزان الفوزان حفظه الله فصيلة الشيخ العلامة زيد بن محمد بن هادي المدخلي رحمه الله فصيلة الشيخ العلامة المحدث ربيع بن هادي عمير المدخلي رحمه الله فضيلة الشيخ العلامة سليمان بن سليم الله الرحيلي حفظه الله فضيلة الشيخ عايد بن خليف الشمري حفظه الله https://t.me/DrRabeeM/4347 الدال على الخير كفاعله #ربيع_السنة #ربيع_المدخلي

ጀዛኩሙላሁ ኸይረን ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር አላህ ይጠብቅህ!
ይህ ማሳሰቢያ ለእያንዳንዳችን ትልቅ የንቅናቄ ደወል ነው።
​በእውነትም ከሸይኽ ወይም ከኡስታዝ የሚቀሰመው ትምህርት የመነሻ ቁልፍ እንጂ የመጨረሻው ማጠቃለያ አይደለም።

ይህ ያነሳኸው ነጥብ የብዙዎቻችንን ሕመም የነካ፣ የእውቀት መንገድ  (ጦለቡል ዒልም) ላይ ለሌለንም  ላሉም ሰዎች ትልቅ የቤት ሥራ የሚሰጥ ድንቅ ማስታወሻ ነው።

​የሸይኽ ሷሊሕ ኣሊ-ሸይኽ ታሪክ በጣም ያስደነግጣል! “አንተ ሰነፍ ስለሆንክ አታነብም” የሚለው የሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ኢብራሂም ምላሽ ለእያንዳንዳችን የተላከ የግሳጼ መልእክት ነው። 

ዛሬ እኛም በተመሳሳይ የፍለጋ እና የማንበብ ሰነፍነታችን ምክንያት በትንሽ በትልቁ የሰዎችን ጊዜ እያባከንን፣ የራሳችንን አእምሮ ከማንበብ እና ከማንቆርቆር አግደነዋል።

ኡስታዝ በሩን ይከፍትልናል፤ በሩን አልፈን የዒልሙን ማዕድ የምንጎበኘውና የምንመገበው ግን በራሳችን ጠንካራ የንባብና የጥናት ጥረት ነው። 

የሸይኽ ሷሊሕ ኣሊ-ሸይኽ ታሪክ ደግሞ ጥገኛ የመሆንን አደጋና የራስን ጥረት አስፈላጊነት በግልጽ ያሳያል።

​እንደ አላህ ፈቃድ፣ ያለፈው ዓመት የነበረንን ክፍተትና ድክመት አምነን በመቀበል፣ ከዚህ ቀንና  ዓመት ጀምሮ ራሳችንን ሙሉ በሙሉ ለዒልምና ለንባብ ለመስጠት መጣር አለብን።
​
​ወንድሞችና እህቶች! ሰነፍ መሆን የተፈጥሮ ግዴታችን አይደለም፤ ልማዳችን ነው፤ ልማድን ደግሞ በትግል መለወጥ ይቻላል። እውቀት በምኞትና በስነ-ስርዓት አልበኝነት አይገኝም።

​የቀረበውን ምክር መነሻ በማድረግ ራሳችንን ለመለወጥ ተግባራዊ  የሆነን እርምጃዎች መውሰድ ግድ ይለናል፦

​
የደርስ አጥባቂነት (ኢስቲቃማ)፦
በየቀኑ የምንከታተላቸውን የቂርአት ደርሶች ያለ ምክንያት አለማቋረጥና በሰዓቱ መገኘት። ደርስ ማቋረጥ የጅህልና መጀመሪያ ነው።
​የቀን ተቀን የንባብ ፕሮግራም ማውጣት፦ "ጊዜ ሲኖረኝ አነባለሁ" የሚል ሰው ፈጽሞ አያነብም። ይልቁንም በቀን ቢያንስ ከ1 እስከ 2 ሰዓት ለግል ንባብና ሙራጃዐ (ክለሳ) የተወሰነ ቋሚ ጊዜ መመደብ።

​ከጥራዝ ነጠቅነት መራቅ፦ አንድን ኪታብ ስንጀምር ከመጨረሻው ሳናደርስ ወደ ሌላ አለመሸጋገር። ኪታቦችን ከነሐሺያቸውና ከነሸርሃቸው በጥልቀት መመርመር።

​ማስታወሻ መያዝ ፦ በምናነብበትና በምናጠናበት ጊዜ አዳዲስ ነጥቦችን፣ የዑለማዎችን ልዩነቶችና ማስረጃዎችን በደብተር ላይ ማስፈር።

​የንባብ ባህልን ማዳበር፦ በትንሽ በትልቁ ሌላውን ሰው ከመጠየቅ በፊት፣ ራሳችን ኪታቦችን ገልጠን የመፈለግና የማጣራት ልምድ ማሳደግ።
የእውቀት መንገድ በትግል እና በሶብር እንጂ በምቾት እና በፍላጎት አይገኝም። ዛሬ ወጣትነታችንን በቲክቶክ ስክሪን ላይ ከምናጠፋው፣ ነገ ለአል-ኢስላምና ለኡምማው የሚጠቅሙ፣ ጥራዝ-ነጠቅ ያልሆኑ ባለሙሉ እውቀት ጧሊቦችን ለመሆን አሁኑኑ መነሳት አለብን።
​
ባለፈው ዓመት ያጣነውን ጊዜ አንመልሰውም፤ የዚህን ዓመት እድል ግን በቁርጠኝነት እና በማንበብ እንጠቀምበት!
​አላህ እውነተኛና ጠቃሚ እውቀትን ይለግሰን፤ ከስንፍናም ይጠብቀን!

ወንድሞቼ! ይህንን መልእክት ለእናንተ ስጽፍላችሁ እኔ ከእናንተ በላይ አውቄ ወይም የበላይ ሆኜ አይደለም፤ ነገር ግን ኡስታዝ የላከው መልዕክት ልቤን ስለነካውና ለእኔም ለእናንተም ትልቅ ማስታወሻ ይሆናል ብዬ ስላሰብኩ ነው:: አፉ በሉኝ፤ አላህ ሁላችንንም ወደ መልካሙ መንገድ ይመራን፣ ሰነፍነታችንንም አስወግዶ ጠቃሚ እውቀትን ይለግሰን።"
​«الرَّاجِي رَحْمَةَ رَبِّهِ، العَبْدُ الفَقِيرُ: أَبُو مَاحِي بْنُ إِدْرِيس» https://t.me/Abu_Mahi_Ibnu_Idris https://t.me/Abu_Mahi_Ibnu_Idris