قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)
Open in Telegram
قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.
Show moreThe country is not specifiedThe category is not specified
908
Subscribers
-324 hours
-157 days
+4830 days
Posts Archive
Repost from مَنَارُ السَّلَفِيِّينَ (መናሩ ሰለፍይይን)
ውሸትን የደዕዋ መሳሪያ ከማድረግ መጠንቀቅ
~ ~ ~ ~ ~ ~~ ~ ~ ~ ~ ~ ~~ ~
ወንድሜ ሆይ! ውሸትን ተጠንቀቅ! ሙብተዲዕ ነው ብለህ በምታምነው ሰው ላይ እንኳ ፈፅሞ አትዋሽ። ደዕዋ ላይ የተሰማራህ ስትሆን ደግሞ ይበልጥ ጥንቃቄ ይኑርህ። የዳዒያህ ውሸታም አደጋው ከሌሎች ውሸታሞች የከፋ ነው።
1- ውሸት ልፋቱን ከንቱ ያደርጋል። ለደዕዋ እየለፋ ዞሮ በየመሀሉ ሆነ ብሎ ውሸትን የሚሰነቅር ከሆነ እየፈጩ ጥሬ ነው የሚሆው።
2- ውሸት መቋጫ የሌለው ድርብርብ ወንጀል ላይ ይጥላል። በተለይ ውሸቱ በደዕዋው ላይ የሚንፀባረቅ ከሆነ (ለምሳሌ፦ ሰዎችን ዋሽቶ የሚወነጅል ቢሆን) ያ ውሸቱ ባሳደረው ጥፋት ሁሉ ተጠያቂ ይሆናል። በሱ ውሸት የተነሳ ደዕዋ ቢደናቀፍ፣ የሰዎች ስም ቢጎድፍ፣ ሰዎች ለኢስላም ወይም ለደዕዋው ያላቸው እይታ ቢበላሽ፣ ሰዎች ከኸይር ቢርቁ፣ በቀጥታ በራሱ ውሸችም ይሁን በሱ የውሸት ውንጀላ በተሸወዱ ሰዎችም ይሁን በየትኛውም መልኩ ሌሎች ላይ ጉዳት ቢደርስ የውሸቱ ጠንሳሽ ላይ ድርብርብ ወንጀል አለበት።
3- የውሸት ፀያፍነት ሰዎች ዘንድ ቀልሎ እንዲታይ ያደርጋል። ሸይኽ ወይም ኡስታዝ እከሌ እንዲህ የሚዋሸው ጉዳዩ ያን ያህል ከባድ ባይሆን ነው የሚል ሸፋፋ ሂሳብ የሚሰራ ሊያጋጥም ይችላል።
4- ውሸታም ሌሎች የዳዕዋ ሰዎችን ያስንቃል። የጥፋት አንጃዎች ዘንድ መሳለቂያ ያደርጋል። የዑለማእ፣ የዱዓት መናቅ ደግሞ ትምህርታቸው ተቀባይነት እንዲያጣ ያደርጋል።
5- ውሸታም ለሌሎች ክፉ ምሳሌ ይሆናል። አስተማሪው ሲዋሽ የተመለከተ ሰው ነፍሲያ በጎተጎተው ቁጥር ያለምንም ጥንቃቄ ሊዋሽ ይችላል። ውሸታም አስተማሪ ውሸታም ተማሪዎችን ያፈራል። ይሄ ደግሞ አጠቃላይ ደዕዋው ላይ ከባድ ጉዳት ነው የሚያደርሰው። ምክንያቱም የተቀየመውን ሁሉ በረድና ተሕዚር ስም ዋሽቶ ለማጠልሸች የማይመለስ መንጋ ይተካልና።
ወንድሜ ሆይ! አስተውል! ተውሒድ በሺርክ፣ ሱና በቢድዐ፣ እውነት በሀሰት አይታገዝም። ዲንን ለማስተማር ብለህ አታዋሽ። ዲንህ የውሸትን እርዳታ የሚፈልግ አይደለምና። አጥፊን ለማስጠንቀቅ ብለህ አትዋሽ። ሳትዋሽ ከአጥፊ ማስጠንቀቅ ካልቻልክ ከምታለማው የምታጠፋው ይበዛልና ይቅርብህ። አትሸወድ! የበደለኛን በደል በሌላ በደል አስቆማለሁ ማለት አጥፎቶ መጥፋት ነው። ተያይዞ ገደል! የትም ቦታ ቢሆን ፍትህ መጠበቅ አለበት። አላህ እንዳስፈላጊነቱ ከሀ*ዲዎችን ከፍ ስል በመሳሪያ ዝቅ ሲል በደዕዋ እንድንዋጋቸው አዞናል። ከመሆኑም ጋር ፍትህ እንዳናዛባ አሳስቦናል። ይሄውና አደራው፦
(یَـٰۤأَیُّهَا ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ كُونُوا۟ قَوَّ ٰمِینَ لِلَّهِ شُهَدَاۤءَ بِٱلۡقِسۡطِۖ وَلَا یَجۡرِمَنَّكُمۡ شَنَـَٔانُ قَوۡمٍ عَلَىٰۤ أَلَّا تَعۡدِلُوا۟ۚ ٱعۡدِلُوا۟ هُوَ أَقۡرَبُ لِلتَّقۡوَىٰۖ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَۚ إِنَّ ٱللَّهَ خَبِیرُۢ بِمَا تَعۡمَلُونَ)
"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለአላህ ቀጥተኞች በትክክል መስካሪዎች ሁኑ፡፡ ህዝቦችንም መጥላት ባለማስተካከል ላይ አይገፋፋችሁ፡፡ አስተካክሉ፡፡ እርሱ (ማስተካከል) ለአላህ ፍራቻ በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡" [አልማኢዳህ፡ 8]
እወቅ! ውሸት ተራ መስሊሞችም ላይ ቢሆን ፀያፍ ከመሆኑ ጋር ነገር ግን የሙስሊም መሪዎችና ዑለማዎች ላይ ሲሆን ክብደቱ ይጨምራል። ምክንያቱም በተራ ሙስሊሞች ላይ ከመዋሸት የከፋ ውጤት ያስከትላልና። ውሸቱ በአላህና በነብዩ ﷺ ላይ ሲሆን ደግሞ የበለጠ አደገኛ ይሆናል። የአንድን ሙስሊም ክብር የሚያጠለሽ ውሸት ተሻጋሪ ጉዳት ከሌለው ውሸት የከፋ ነው። በህዝብ ላይ፣ በደዕዋ ላይ ጉዳት የሚያስከትል ውሸት ደግሞ በግለሰብ ላይ ጉዳት ከሚያደርሰው ውሸት የከፋ ነው። ስለዚህ በጣም መጠንቀቅ ያስፈልጋል።
እና እልሃለሁ! ለሱና እከላከላለሁ ብለህ አትዋሽ! ቢድዐን እዋጋለሁ ብለህ አትዋሽ። ያለበለዚያ ይበልጥ ቆሻሻ ጥፋት ውስጥ እየተነከርክ ነው። ሸይኽ ረቢዕ - ሐፊዘሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦
الكذب أخبث من البدع يا إخوان والكذَّاب أخبث عند أهل السنة من المبتدع المبتدع يروى عنه, رَوَوْا عن القدرية رَوَوْا عن المرجئة ورَوَوْا عن غيرهم من أصناف أهل البدع ما لم تكن بدعة كفرية ما لم يكن كذابا. لو كان ينتمي إلى أهل السنة كذَّاب فهو عندهم أحط من أهل البدع .
ومن هنا عقد ابن عدي-رحمه الله- في كتابه "الكامل" حوالي تسعة وعشرين باباً للكذَّابين([1]) وبابًا واحداً لأهل البدع .
وقَبِل أهل السنة رواية أهل البدع الصادقين غير الدعاة .
"ውሸት ከቢድዐ ይበልጥ ቆሻሻ ነው፣ ወንድሞች። ውሸታም የሱና ሰዎች ዘንድ ከሙብተዲዕ የከፋ ቆሻሻ ነው። ሙብተዲዕ ከሱ ይዘገባል። (የሐዲሥ ምሁራን) ከቀደሪያ ዘግበዋል። ከሙርጂአ ዘግበዋል። ከሌሎች የቢድዐ አራማጅ አይነቶችም እንዲሁ። ይህም ቢድዐው ክህደት የሚደርስ እስካልሆነና ዋሾ እስካልሆነ ድረስ ነው። ይሁን እንጂ አንድ ውሸታም እራሱን ወደ አህለ ሱና የሚያስጠጋ ቢሆን እንኳ እሱ እነሱ ዘንድ ከቢድዐ ሰዎች በታች ናቸው። ለዚህም ነው ኢብኑ ዐዲይ - ረሒመሁላህ - አልካሚል በተሰኘው ኪታባቸው ውስጥ ሙሸታሞችን በተመለከተ ሃያ ዘጠኝ ርእሶችን ሲሰጡ፣ የቢድዐ ሰዎችን በተመለከተ ግን አንድ ርዕስ ብቻ መስጠታቸው።"
ልብ በሉ! ውሸትና ውሸታሞች ፀያፍ የሚሆኑበትን ገፅ አጉልተው ለማሳየት እንጂ ይህን ማለታቸው እንዳጠቃላይ ቢድዐውን እንደ ኢስላም መቃረቢያ አድርጎ የሚቆጥረው ሙብተዲዕ የከፋ ወንጀለኛ መሆኑ የሚያከራክር አይደለም።
ፅሁፌን የምቋጨው በተከታዩ የነብዩ ﷺ ሐዲሥ ነው፦
"وإيّاكم والكذِبَ، فإنّ الكَذِبَ يَهْدِي إلَى الفُجُورِ، وإِنّ الفُجُورَ يَهْدِي إِلَى النّارِ وَمَا يزَالُ العبْدُ يَكْذِبُ وَيَتَحَرّى الكَذِبَ حَتّى يُكْتَبَ عِنْدَ الله كَذّابا".
"ውሸትን አደራችሁን (ተጠንቀቁ)። ውሸት ወደ አመፅ ይመራልና። አመፅ ደግሞ ወደ እሳት ይመራል። አንድ ሰው ከመዋሸትና ውሸት ላይ ከማተኮር አይወገድም አላህ ዘንድ ውሸታም ተብሎ እስከሚመዘገብ ድረስ!" [ቡኻሪና ሙስሊም]
==
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے
ሁሉም ነገር ባለበት ይቀጥላል ብለህ አታስብ… የወጣ ሁሉ ይወርዳል … የኖረ ሁሉ ይሞታል… የማይነጋ ጨለማም አይኖርም… የሆነ ቀን ፀሃይ ራሱ ህጉን ጥሶ፣ ፍፃሜን ለመግለፅ ከምዕራብ የሚወጣበት ጊዜ አለ። የሰዎች ህይወትና የግንኙነት ሂደት ባልታሰበ ሁኔታ ሊለወጥ ይችላል። በጣም የወደደህ በመጨረሻ በጣም ይጠላህ ይሆናል። በጣም የጠላህ ደግሞ በጣም ይወድህ ይሆናል።
t.me/abdu_rheman_aman
t.me/abdu_rheman_aman
ድንቅ ንግግር በፍቅር ስም #ክብራቸውን ያጡ ስንት እና ስንት ናችው አላህ ይጠብቀን።
✍ደህና ነን’ የምንለው ሰው
ሰልችቶን ሳይሆን፣ የውስጣችን
ዝብርቅርቅ ህይወት አስረድተን
እነሱን ማስጨነቅ ስላልፈለግን
ነው።
⛔️ የሰውን ቀልብ እንደመጠገን ትልቅ ኢባዳ የለም፤ የሰውን ልብ እንደመስበርም ከባድ ነገር የለም።
አንዳንድ ልቦች በአንድ ቃል ይሰበራሉ፤
አንዳንድ ልቦች በአንድ ንቀት፣ በአንድ ክህደት፣ በአንድ ዝምታ፣ በአንድ ያልተገባ ተስፋ ይሰበራሉ።
አንተ የተናገርከውን ልትረሳው ትችላለህ፤
እሷ ግን ለዓመታት ልትረሳው ላትችል ትችላለች።
አንተ እንደ ቀልድ የተናገርከው ነገር፣ ሌላው ሰው ሌሊት ላይ እያሰበው የሚያለቅስበት ህመም ሊሆን ይችላል።
ስለዚህ… እንጠንቀቅ።
የሰው ልብ እንደ መስታወት ነው፤ አንዴ ከተሰበረ እንደበፊቱ ለመመለስ ከባድ ነው።
ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«مَنْ كَانَ يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ فَلْيَقُلْ خَيْرًا أَوْ لِيَصْمُتْ»
“በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምን ሰው መልካም ነገር ይናገር ወይም ዝም ይበል።”
አንዳንድ ጊዜ የምንሰጠው ትልቁ ስጦታ ገንዘብ አይደለም፤ ሰውን የሚያረጋጋ ቃል ነው።
አንዳንድ ጊዜ የምናደርገው ትልቁ ሰደቃ እጃችንን ወደ ኪሳችን ማስገባት አይደለም፤ የተሰበረን ልብ በመጠገን ላይ መሳተፍ ነው።
የሰበርናቸው ሰዎች ካሉ…
ዛሬ እንደገና እናስብ።
ምናልባት አንዲት እህት በእኛ ምክንያት በራሷ ላይ እምነቷን አጥታ ይሆናል።
ምናልባት አንድ ወንድም በእኛ ቃል ምክንያት ለሰዎች መታመን ተቸግሮ ይሆናል።
ምናልባት አንድ ሰው ፈገግ እያለ ቢታይም፣ በውስጡ ግን የእኛን ቃል ይዞ እየታገለ ይሆናል።
እንደገና እንቅረባቸው።
ይቅርታ እንጠይቃቸው።
ምክንያቱን እናስወግድ።
የተቻለንን ያህል ልባቸውን እንጠግን።
“እኔ ምንም አላደረግኩም” ብለን ከመከራከር ይልቅ፣
“በእኔ ምክንያት ከተጎዳህ ይቅርታ አድርግልኝ” ማለት ክብርን አያሳንስም።
ከዚህ ይልቅ የልብ ትልቅነትን ያሳያል።
የሰው ልብ ከፍ ያለ አማና ነው። ስለዚህ እንደ ፈለግን ልንጫወትበት የሚገባን ነገር አይደለም።
አላህ እንዲህ ይላል፦
﴿وَقُولُوا لِلنَّاسِ حُسْنًا﴾
“ለሰዎች መልካም ነገርን ተናገሩ።” [البقرة: 83]
እና ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«وَالْكَلِمَةُ الطَّيِّبَةُ صَدَقَةٌ»
“መልካም ቃል ሰደቃ ነው።”
ስለዚህ ዛሬ ከሰው ጋር ስትነጋገር፣ ከአፍህ የሚወጣው ቃል ምን እንደሚያደርግ አስብ።
ልብ ሊሰብር ይችላል…
ልብም ሊጠግን ይችላል።
እኛ ግን የሚሰብሩ ሳይሆን የሚጠግኑ ሰዎች እንሁን።
የሚያስለቅሱ ሳይሆን የሚያረጋጉ እንሁን።
የሚያንቋሽሹ ሳይሆን የሚያከብሩ እንሁን።
ከእኛ በኋላ ቁስል ሳይሆን መልካም አሻራ እንተው።
እናማ ወዳጆቼ የሰበርነው ልብ ካለ… ነገ ይቅርታ እንላለን ብለን አንዘግይ።
ዛሬውኑ ይቅርታ እንጠይቅ።
ዛሬ የሰበርነውን ነገር ለመጠገን አንሞክር።
ምክንያቱም አንዳንድ ይቅርታዎች በጊዜ ካልተባሉና ከዘገዩ የተሰበረውን ልብ ይበልጥ ያርቃሉ።
🌿 ሰዎች ሲያስታውሱህ፣ “እሱ ልቤን ሰብሮኛል” እንዳይሉህ ተጠንቀቅ፤ “ ይልቅ እሱ በአላህ ፈቃድ ልቤን ከብዙ ህመም አሳርፎኛል” ከሚሉት ሰው እንሁን።
ልቦችን እንጠግን… ምክንያቱም እኛም አንድ ቀን የተሰበረ ልብ ይዘን ሰው ወደ እኛ ሊመጣ ይችላልና።
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
t.me/Abu_hibetillah_AsselfiyRepost from ከ ቁርአን አያህ...
ምድር ድርቅ ሆና፣ ተስፋ ሁሉ ተቆርጦ፣ "ከእንግዲህ ምንም ነገር አይበቅልም" ተብሎ በተደመደመበት ቅፅበት ነው አላህ ዝናብን የሚያወርደው። የህይወትህም ሁኔታ እንዲሁ ነው፤ ሁሉም በር ተዘግቶ፣ ተስፋ የምታደርገው ሰበብ ሁሉ አልቆ "አበቃለት" ስትል እፎይታው ይወርዳል፦
وَهُوَ الَّذِي يُنَزِّلُ الْغَيْثَ مِن بَعْدِ مَا قَنَطُوا وَيَنشُرُ رَحْمَتَهُ
«እርሱም ያ ተስፋ ከቆረጡ በኋላ ዝናብን የሚያወርድ፣ እዝነቱንም የሚያሰራጭ ነው...» (ሱረቱ አሽ-ሹራ 42:28)
አኺዬ.. ተስፋ የቆረጥክበት ያ ቦታ፣ የአላህ እዝነትና እፎይታ የሚፈስበት የመጀመሪያው ቦታ ሊሆን ይችላል። አትጠራጠር ሀቢቢ!
🍂 ከ ቁርአን አያህ...
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ያያያዝኩት ቪዲዮ የሑሢዮች እንቅስቃሴ መስራቹ ሑሴን በድረዲን አልሑሢ ንግግር ነው። ምን እያለ ነው? ህዝበ ሙስሊሙን ከጥንት ጀምሮ ላገኘው መከራ ሁሉ፣ ለደረሰበት ዝቅጠት ሁሉ ቁጥር አንድ ተጠያቂው ዑመር ነው ይላል። ለንዲህ አይነቱ እR ^ኩስ ነው ኢኽዋንና የኢኽዋን ቫይረስ ተሸካሚ መንጋዎች የሚሟገቱት። ይህንን እያዩም እየሰሙም የሚደነግጡ እንዳይመስላችሁ። ከዑመር ብኑል ኸጧብ ክብር ይልቅ የነዚህ ራፊዷዎች ክብር ነው የሚበልጥባቸው። ዲናቸውን ብሽሽቅ አድርገው የያዙ አተላዎች!
በነገራችን ይሄ ሰውዬ የዐብዱልመሊክ አልሑሢ ወንድም ማለት ነው። ዐብዱልመሊክ አልሑሢ አሁን ላይ ራሳቸውን "አንሷሩ'ላህ" እያሉ የሚጠሩት ዘይዲያ ሺዐዎች መሪ ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Halal Jobs - ሐላል የስራ ማስታወቂያዎች
#ማስታወሻ!
#ለቀጣሪዎች፦ የቅጥር ማስታወቂያ በነፃ ነው የምንለቀው ማለት የተላከልን ማስታወቂያ ሁሉ ያለምንም ማጣራት ፖስት ይደረጋል ማለት አይደለም። አሰፈላጊ የሆኑ ማጣሪያዎች በሙሉ ይደረጋሉ።
#ለሰራተኞች፦ ለስራ ብቁ ናችሁ ወይም ስራ ከመጀመራችሁ በፊት መሰልጠን አለባችሁ ብለው ቅድመ ክፍያ ብር የሚጠይቋችሁ ድርጅቶች ካሉ ፈፅሞ እንዳትከፍሏቸው። ከቻላችሁ ወድያው በ @HalalJobsEthbot በኩል አሳውቁን። ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ነግርያቹሀለው። ስራ አገኛለሁ በሚል ጉጉት እንዳትሸወዱ።
===
Halal Jobs
ቴሌግራም👉 t.me/HalalJobsEth
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
አላህ ያወቀው፣ ሰው ባያውቀው ምን ሊያጣ?
~
የነሃወንድ ጦርነት የተካሄደው በኸሊፋው ዑመር ብኑል ኸጣብ ረዲየላሁ ዐንሁ ዘመን ነው። ጦርነቱ የተካሄደው ከፋርስ ጦር ጋር ነው። በዚህ ጦርነት ሙስሊሞች ትልቅ ድል ነበር የተጎናፀፉት። የድሉ ዜና ዑመር ዘንድ ሲደርስ በጦርነቱ የሞቱ ሙስሊሞችን ስም ይጠይቃሉ። ታዋቂ የሆኑትን ሰዎች ከዘረዘረላቸው በኋላ "ሌሎቹ አሚረል ሙእሚኒን የማያውቃቸው ተራ ሰዎች ናቸው" አላቸው አንዱ።
ዑመር እንዲህ እያሉ ማልቀስ ያዙ፦
"አሚረል ሙእሚኒን ባያውቃቸው ምን ሊጎዳቸው? ነገር ግን አላህ ያውቃቸዋል። በሸሂድነትም አክብሯቸዋል። ከዚህ በኋላ የዑመር ማወቅ ምን ሊሰራላቸው?!"
[አልቢዳያ ወኒሃያ፡ 10/124]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے
በህይወት ዘመኔ ካየኋቸው ጦርነቶች ውስጥ እንደዚህ ቪድዮ ያስደሰተኝም ሆነ ያሳዘነኝ የለም። ይህ ክስተት በሀገረ የመን የተከሰተ ነው፤ የመኖች በውጊያ ሰዓት "ጠላታችን" ብለው የሚያስቡት አካል በኢላማቸው ስር ወደቀ። ነገር ግን ሰውየው ሶላት እየሰገደ ነበር፤ እናም “ተውት! አትምቱት፤ እየሰገደ ልትመቱት ነው እንዴ? ኧረ በእኛ ላይ ነውር ነው! አንድ ሰው እንዳይመታው፤ እኛ እኮ ሙስሊሞች እንጂ አይሁዶች አይደለንም!” እየተባባሉ ነው።
ከዚህ ቪድዮ ምን ተማራቹህ ?
t.me/abdu_rheman_aman
t.me/abdu_rheman_aman
Repost from شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
+6
.....እስኪ አትነካኩኝ.....⁉️
👉#እሸት__።
--------------------------
ማኛና ሰርገኛ ነጭ ጤፍ ምስሩ፡
ሽንብራና ጓያ ባቄላና አተሩ፡
አረንጓደ ለብሶ ሲታዩት ማማሩ፡
ገጠር ሁሉም አለ ቀፎ ሞልቷል ማሩ፡
----------------------------------
ከዘንጋዳው መሀል ይመረጣል ጥንቅሽ፡
የትውልድ መንደሬ እስኪ ላስተዋውቅሽ፡
ገጠር ነሽ እያለ ማንም እንዳይንቅሽ፡
አዝመራሽን አይቶ ማንም እንዳልቅሽ፡
ሁሌ እሸት እንደሆንሽ ፈጣሪ ያዝልቅሽ፡
ከደግነትሽ ጋር ሰላም ላይ ያፅድቅሽ፡
------------------------------------
ከማሽሎች መሀል ጥንቅሽ ይመረጣል፡
ልጦ ለማላመጥ ሁሉም ይቋምጣል፡
ከገጠሩ ህዝቤ እሸት መች ይታጣል ፡
ባህሉ ነውና ሳትጠይቅ ይሰጣል፡
.....ገጠሬ ነኝ እሽ...
እናቴ ''ባለ አገር'' አባቴ ገበሬ፡
አንሸምትም እኛ ሽሮና በርበሬ፡
ሁሉም ከጓሮው ነው ፀጋ አለው ገጠሬ፡
እኔም ደስ ይለኛል እዚያ መፈጠሬ፡
---------------------------------
ተራራና ሜዳው አልባብ አልባብ ሲሸት፡
ገጠር ደስ ይለኛል ያለ ምንም ውሸት፡
መስከረም ጥቅምትን ይቀጠፋል እሸት፡
▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴
#በኑረዲን_አል_አረብ
▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴
http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi
Repost from N/a
➲ የሱና ቴሌግራም ቻናላችሁን እና ግሩፓችሁን
ባጭር ግዜ ዉስጥ በነፃ ማሳደግ የሚያስችል ዌቭ ጀምረን
100 ቻናሎችን ሰብስበናል አልሃምዱሊላህ አሁን ደሞ
ከ5ሺ በላይ ተከታይ ላላቸው ቻናሎች እድሉን አምጥተናል
ከ5k subscribers በላይ ያላቹ አሁኑኑ አናግሩን
በነፃ ነዉ ፈጥነው ያስመዝግቡ
የሱና ቻናል ለማስመዝገብ አናግሩኝ
👉 @Quran_mylife1
የሱና መስፈርት የማያሟሉ ቻናሎችን አንቀበልም
Repost from N/a
💰 የሚሸጥ 👇
➭የቴሌግራም (Telegram channel ) 5k+
➭የቲክቶክ (Tiktok account ) 15k+
➭የፌስቡክ (Facebook page) 5k+
➭ዩቲዩብ (YouTube channel ) 2k+
➭ኢሞ (imo room ) 1k+
⚠ እየገዛን ነው ለመሸጥ 👉 @selluhi
Repost from Mohammed Siraj Al kemissie
قال الحافظ ابن رجب رحمه الله:
«مراتبُ الدُنيا لا تُنال إلا بالصبرِ على البلاءِ في طلبِها، والمجاهدة، فكيف من أراد مقعد صدقٍ عند مليكٍ مُقتدر.»
•مجموع الرسائل (١/٢٢٤)•t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie
Repost from فوائد أ.د. صالح سندي
🔰 « أهل السنة لا يحكمون لأحد بجنة ولا نار »
🎙️ لفضيلة الشيخ أ.د. صالح بن عبدالعزيز السندي (حفظه الله تعالى ورعاه)
رابط دروس شرح العقيدة الطحاوية : https://youtube.com/playlist?list=PLVw9FtCy781ZSgNnw5hJm1QkniE2k6Jx8&si=G_9F_YHlqaUcScQG
