uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

Kanalga Telegram’da o‘tish

قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
908
Obunachilar
-324 soatlar
-157 kun
+4830 kun
Postlar arxiv
ኢብራሂም– አንድ ሰው፣ ሁለት ስም! ~ አንተ ከሰዎች ዘንድ ማነህ? ደግ ወይስ ክፉ? ትሁት ወይስ በጥራራ? ፊተ በሻሻ ወይስ ጨፍጋጋ? ምራቅ የዋጠ በሳል ወይስ በቀዳዳ ሱሪ የሚጀነን ከንቱ ፍንዳታ? አንተ ማነህ? ሰዎች ስላንተ ምን ይላሉ? ምን እንደሚሉ ታውቃለህ? በክፉ መነሳት ያሳስብሀል? ወይስ የሰው ጉዳይ የማይጨንቅህ በራስህ ዛቢያ ላይ የምትሽከረከር ፍጡር ነህ? አንቺስ ከሰው ዘንድ ማነሽ? ማን መባል ያምርሻል? ምን ስም እንዳይወጣልሽ ይጨንቅሻል? ባገር በመንደሩ ምን ስም አለሽ? ጨዋ? ዘል.ዛላ? ምላሳም? ቁጥብ? አጉል ነቃሁ ባይ? ግብረ ገብ? ቀብራራ? ኮስታራ? ይህ ከሰው ዘንድ ነው። ከአላህ ዘንድስ እኛ ማነን? ምንስ ቦታ አለን? እስኪ ራሳችንን እንመልከት? አላህ ካዘዘብን ቦታ አለን? አላህ ከከለከለን ቦታ ርቀናል? ከሆነ ምንኛ መታደል ነው?! ከሆነ ከሰው ዘንድ ያለን ስም አያስጨንቀንም። ከሰዎች ዘንድ እፍኝ የማይሞሉ፣ አይን የማይገቡ፣ ቢናገሩ ቃላቸው የማይሰማ፣ ቢጠይቁ ፊት የማይስሰጣቸው፣ በሰዎች መለኪያ እዚህ ግባ የማይባሉ ከአላህ ዘንድ ግን የላቀ የራቀ ደረጃ ያላቸው ስንትና ስንት የአላህ ሰዎች አሉ?! አላህ ዘንድ "ሰው" ከሆኑ በኋላ ሰዎች እንደ ሰው ባይቆጥሯቸው ምን ያጣሉ?! ኢብራሂምን አታይም? ከነዚያ ከበርቴዎች ዘንድ ማን ነበሩ? አንድ ተራ ወጣት! (قَالُوا سَمِعْنَا فَتًى يَذْكُرُهُمْ يُقَالُ لَهُ إِبْرَاهِيمُ) "ኢብራሂም የሚባል #ወጣት (በመጥፎ) ሲያነሳቸው ሰምተናል ተባባሉ።" [አልአንቢያእ: 60] ከአላህ ዘንድስ ማን ነበሩ? (إِنَّ إِبْرَاهِيمَ كَانَ أُمَّةً قَانِتًا لِلَّهِ حَنِيفًا وَلَمْ يَكُ مِنَ الْمُشْرِكِينَ) "ኢብራሂም ለአላህ ታዛዥ ወደ ቀጥተኛ ሃይማኖት ተዘንባይ የሆነ #ሕዝብ ነበር፡፡ ከአጋሪዎቹም አልነበረም፡፡፡" [አንነሕል: 120] ከሰዎች ዘንድ እንደ ዋዛ "አንድ ወጣት" ተብለው የተቃለሉት ኢብራሂም ከአላህ ዘንድ "ህዝብ" ተብለው ነበር የተሞካሹት!! አንዱ ኢብራሂም ሁለት ስም ሲኖራቸው ተመልከት። አንዱ እንደ ምድር፣ አንዱ እንደ ሰማይ። አንዱ ከምድር፣ ሌላው ከሰማይ። ልዩነቱን አየኸው?! አላህ እንዲህ ከሰቀላቸው በኋላ ፍጡር ሊያወርዷቸው ቢጣጣር ምን ያመጣል?! በተውሒድ የነገሰን ማን ያወርደዋል?! · ድሮ ነው። ወሎ፣ ወረባቦ ወረዳ ውስጥ የሚኖሩ ዑካሻ የተሰኙ በተውሒድ ጠንካራ የሆኑ፣ ህዝቡን የወረረውን ሺርካ ሺርክ የሚነቅፉና የሚፀየፉ ሸይኽ ነበሩ። "ከዘልማዳችን ወጥጣ" ብለው በጊዜው የነበሩ መሻይኾች ተሰብስበው "ፌንጥ" አሏቸው። ("ፌንጥ" አሁንም ድረስ ያለ አደገኛ ማህበራዊ ማእቀብ ነው። "ፌንጥ" የተባለ ሰው ከየትኛውም ማህበራዊ ህይወት ይገለላል። ሰላምታ እንኳን ይነፈጋል። ከሕዝብ መሐል እየኖረ በጫካ ውስጥ ከመኖር በላይ እየተሳቀቀ ባይተዋርነትን ይገፋል።) ዑካሻ በጠንካራው የተውሒድ አቋማቸው የተነሳ አድማ ተመታባቸው። ከአቋማቸው ሊያሽመደምዷቸው በማለም ሸይኾቹ ተሰብስበው "ፌንጥ ብለንሀል" አሏቸው። የዑካሻ መልስ ግን ያልተጠበቀ ነበር። "እኔም ፌንጥ ብያችሁዋለሁ! ምን ታመጣላችሁ?!" · አዎ ሁለ ነገሩን ለአላህ የሰጠ ሰው፣ የሰው ሴራ ለአላህ ብሎ ከያዘው አቋሙ አያጥፈውም። የሰው ጭብጨባ በሙቀት አያቀልጠውም። አላህን የያዘ ምን አጥቷል! ከአላህ ጋር የሆነ ምን ያስፈራዋል! · ወንድሜ ሆይ! እህቴ ሆይ! ከምንም በፊት ከአላህ ዘንድ ሰው እንሁን። በምኞት ሳይሆን በተግባር ሰው ለመሆንም እንጣር። (ኢብኑ ሙነወር፣ ጥር 13/2011) = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor

📌محاضرة بعنوان①: مواعظ وعبر من حديث: "يامحمد عش ماشئت فإنك ميت " 🎙አቡ ዐኢሻ ሙሐመድ ሰዒድ https://telegram.me/abutoiba https://telegram.me/abutoiba

🔖ተከታታይ  ደርስ 📚 ሪያዱ ሷሊሒን 📄ክፍል:- 334   👈كتاب الأمور المنهي عنها 👉ሐዲስ ቁጥር:- 1642-1649 🎙አቅራቢ:-ሸይኽ ሙሐመድዘይን ኣደም 🕌የሚሰጥበት ቦታ፦ ፋሪ አቡበክር አስ-ሲዲቅ መስጂድ 📖የኪታቡ ሶፍት ኮፒ (በ pdf ):- https://t.me/SheikhMuhammedZainAdam/7959 🗓 ዛሬ ሰኞ ዙል ረቢዑ አሳኒ 03,1448 ሂጅሪ (04-01-2019) * የሚሰጥበት ቀንና ሰዓት :-ከሰኞ እስከ እሮብ ከመግሪብ እስከ ዒሻ *የቴሌግራም ቻናሎች፡- @SheikhMuhammedZain @SheikhMuhammedZainadam @abuhuzeyfashaikhmohammedzeyn

+1
▫️አዲስ ሙሐደራ: 💳 የሶላት አሳሳቢነት 🎙በኡስታዝ ሙሐመድ መኪን

هذا هو الإمام ربيع رحمه الله.. هل يجوز الكذب على أهل البدع وغيرهم من أهل الضلال؟ الجواب لا يجوز الكذب لا على كفار ولا على أهل بدع، ولا على أحد، لا يجوز، تفتري على أحد تقول فلان فيه وفيه والجماعة الفلانية فيها وفيها، نعوذ بالله، لا يجوز، نحن نبين ما عندهم من الضلال ننقله من كتبهم أو من الوسائل الأخرى بالحرف، ثم نناقشها علميا، هذا الذي نفعله، ونسأل الله أن كل السلفيين يفعل هذا، ولا نرى أبدا، ونعوذ بالله، لا نرى لمسلم أن يفتري على مسلم أو كافر أبدا. مج كتب ورسائل العلامةربيع١٦٢\١٤.... ❀══════❀ ♻️ سَاهِمُوا بِنَشْرِهَا فَالدّالُّ علَى الخَيرِ كَفَاعِلِه.

ዱንያ ቦታዋ ይሄ ነው ~ ﴿ وَمَا الْحَيَاةُ الدُّنْيَا إِلَّا مَتَاعُ الْغُرُورِ﴾ "የዚህች ዓለም ሕይወት ጊዜያዊ መደሰቻ እንጂ ሌላ አይደለችም፡፡" [ኣሊ ዒምራን፡
ዱንያ ቦታዋ ይሄ ነው ~ ﴿ وَمَا الْحَيَاةُ الدُّنْيَا إِلَّا مَتَاعُ الْغُرُورِ﴾ "የዚህች ዓለም ሕይወት ጊዜያዊ መደሰቻ እንጂ ሌላ አይደለችም፡፡" [ኣሊ ዒምራን፡ 185] = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

﴿وَمَنْ أَرَادَ الْآخِرَةَ وَسَعَىٰ لَهَا سَعْيَهَا وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَأُولَٰئِكَ كَانَ سَعْيُهُم مَّشْكُورًا﴾
القارئ : شايع التميمي

"عَلِمْتُ أنَّ رِزقي لا يأخذُهُ غيري؛ فاطمأنَّ قَلبي.. وعَلِمْتُ أنَّ عَمَلي لا يقومُ به غيري؛ فاشتغلتُ به". - الحسن البصري رحمه الله.

🔖ልብ ከምትደሰትባቼው ነገሮች ዉስጥ ቁርአን በተመስጦ ማዳመጥ ነው! ||

ውሸትን የደዕዋ መሳሪያ ከማድረግ መጠንቀቅ ~ ~ ~ ~ ~ ~~ ~ ~ ~ ~ ~ ~~ ~ ወንድሜ ሆይ! ውሸትን ተጠንቀቅ! ሙብተዲዕ ነው ብለህ በምታምነው ሰው ላይ እንኳ ፈፅሞ አትዋሽ። ደዕዋ ላይ የተሰማራህ ስትሆን ደግሞ ይበልጥ ጥንቃቄ ይኑርህ። የዳዒያህ ውሸታም አደጋው ከሌሎች ውሸታሞች የከፋ ነው። 1- ውሸት ልፋቱን ከንቱ ያደርጋል። ለደዕዋ እየለፋ ዞሮ በየመሀሉ ሆነ ብሎ ውሸትን የሚሰነቅር ከሆነ እየፈጩ ጥሬ ነው የሚሆው። 2- ውሸት መቋጫ የሌለው ድርብርብ ወንጀል ላይ ይጥላል። በተለይ ውሸቱ በደዕዋው ላይ የሚንፀባረቅ ከሆነ (ለምሳሌ፦ ሰዎችን ዋሽቶ የሚወነጅል ቢሆን) ያ ውሸቱ ባሳደረው ጥፋት ሁሉ ተጠያቂ ይሆናል። በሱ ውሸት የተነሳ ደዕዋ ቢደናቀፍ፣ የሰዎች ስም ቢጎድፍ፣ ሰዎች ለኢስላም ወይም ለደዕዋው ያላቸው እይታ ቢበላሽ፣ ሰዎች ከኸይር ቢርቁ፣ በቀጥታ በራሱ ውሸችም ይሁን በሱ የውሸት ውንጀላ በተሸወዱ ሰዎችም ይሁን በየትኛውም መልኩ ሌሎች ላይ ጉዳት ቢደርስ የውሸቱ ጠንሳሽ ላይ ድርብርብ ወንጀል አለበት። 3- የውሸት ፀያፍነት ሰዎች ዘንድ ቀልሎ እንዲታይ ያደርጋል። ሸይኽ ወይም ኡስታዝ እከሌ እንዲህ የሚዋሸው ጉዳዩ ያን ያህል ከባድ ባይሆን ነው የሚል ሸፋፋ ሂሳብ የሚሰራ ሊያጋጥም ይችላል። 4- ውሸታም ሌሎች የዳዕዋ ሰዎችን ያስንቃል። የጥፋት አንጃዎች ዘንድ መሳለቂያ ያደርጋል። የዑለማእ፣ የዱዓት መናቅ ደግሞ ትምህርታቸው ተቀባይነት እንዲያጣ ያደርጋል። 5- ውሸታም ለሌሎች ክፉ ምሳሌ ይሆናል። አስተማሪው ሲዋሽ የተመለከተ ሰው ነፍሲያ በጎተጎተው ቁጥር ያለምንም ጥንቃቄ ሊዋሽ ይችላል። ውሸታም አስተማሪ ውሸታም ተማሪዎችን ያፈራል። ይሄ ደግሞ አጠቃላይ ደዕዋው ላይ ከባድ ጉዳት ነው የሚያደርሰው። ምክንያቱም የተቀየመውን ሁሉ በረድና ተሕዚር ስም ዋሽቶ ለማጠልሸች የማይመለስ መንጋ ይተካልና። ወንድሜ ሆይ! አስተውል! ተውሒድ በሺርክ፣ ሱና በቢድዐ፣ እውነት በሀሰት አይታገዝም። ዲንን ለማስተማር ብለህ አታዋሽ። ዲንህ የውሸትን እርዳታ የሚፈልግ አይደለምና። አጥፊን ለማስጠንቀቅ ብለህ አትዋሽ። ሳትዋሽ ከአጥፊ ማስጠንቀቅ ካልቻልክ ከምታለማው የምታጠፋው ይበዛልና ይቅርብህ። አትሸወድ! የበደለኛን በደል በሌላ በደል አስቆማለሁ ማለት አጥፎቶ መጥፋት ነው። ተያይዞ ገደል! የትም ቦታ ቢሆን ፍትህ መጠበቅ አለበት። አላህ እንዳስፈላጊነቱ ከሀ*ዲዎችን ከፍ ስል በመሳሪያ ዝቅ ሲል በደዕዋ እንድንዋጋቸው አዞናል። ከመሆኑም ጋር ፍትህ እንዳናዛባ አሳስቦናል። ይሄውና አደራው፦ (یَـٰۤأَیُّهَا ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ كُونُوا۟ قَوَّ ٰ⁠مِینَ لِلَّهِ شُهَدَاۤءَ بِٱلۡقِسۡطِۖ وَلَا یَجۡرِمَنَّكُمۡ شَنَـَٔانُ قَوۡمٍ عَلَىٰۤ أَلَّا تَعۡدِلُوا۟ۚ ٱعۡدِلُوا۟ هُوَ أَقۡرَبُ لِلتَّقۡوَىٰۖ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَۚ إِنَّ ٱللَّهَ خَبِیرُۢ بِمَا تَعۡمَلُونَ) "እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለአላህ ቀጥተኞች በትክክል መስካሪዎች ሁኑ፡፡ ህዝቦችንም መጥላት ባለማስተካከል ላይ አይገፋፋችሁ፡፡ አስተካክሉ፡፡ እርሱ (ማስተካከል) ለአላህ ፍራቻ በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡" [አልማኢዳህ፡ 8] እወቅ! ውሸት ተራ መስሊሞችም ላይ ቢሆን ፀያፍ ከመሆኑ ጋር ነገር ግን የሙስሊም መሪዎችና ዑለማዎች ላይ ሲሆን ክብደቱ ይጨምራል። ምክንያቱም በተራ ሙስሊሞች ላይ ከመዋሸት የከፋ ውጤት ያስከትላልና። ውሸቱ በአላህና በነብዩ ﷺ ላይ ሲሆን ደግሞ የበለጠ አደገኛ ይሆናል። የአንድን ሙስሊም ክብር የሚያጠለሽ ውሸት ተሻጋሪ ጉዳት ከሌለው ውሸት የከፋ ነው። በህዝብ ላይ፣ በደዕዋ ላይ ጉዳት የሚያስከትል ውሸት ደግሞ በግለሰብ ላይ ጉዳት ከሚያደርሰው ውሸት የከፋ ነው። ስለዚህ በጣም መጠንቀቅ ያስፈልጋል። እና እልሃለሁ! ለሱና እከላከላለሁ ብለህ አትዋሽ! ቢድዐን እዋጋለሁ ብለህ አትዋሽ። ያለበለዚያ ይበልጥ ቆሻሻ ጥፋት ውስጥ እየተነከርክ ነው። ሸይኽ ረቢዕ - ሐፊዘሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦ الكذب أخبث من البدع يا إخوان والكذَّاب أخبث عند أهل السنة من المبتدع المبتدع يروى عنه, رَوَوْا عن القدرية رَوَوْا عن المرجئة ورَوَوْا عن غيرهم من أصناف أهل البدع ما لم تكن بدعة كفرية ما لم يكن كذابا. لو كان ينتمي إلى أهل السنة كذَّاب فهو عندهم أحط من أهل البدع . ومن هنا عقد ابن عدي-رحمه الله- في كتابه "الكامل" حوالي تسعة وعشرين باباً للكذَّابين([1]) وبابًا واحداً لأهل البدع . وقَبِل أهل السنة رواية أهل البدع الصادقين غير الدعاة . "ውሸት ከቢድዐ ይበልጥ ቆሻሻ ነው፣ ወንድሞች። ውሸታም የሱና ሰዎች ዘንድ ከሙብተዲዕ የከፋ ቆሻሻ ነው። ሙብተዲዕ ከሱ ይዘገባል። (የሐዲሥ ምሁራን) ከቀደሪያ ዘግበዋል። ከሙርጂአ ዘግበዋል። ከሌሎች የቢድዐ አራማጅ አይነቶችም እንዲሁ። ይህም ቢድዐው ክህደት የሚደርስ እስካልሆነና ዋሾ እስካልሆነ ድረስ ነው። ይሁን እንጂ አንድ ውሸታም እራሱን ወደ አህለ ሱና የሚያስጠጋ ቢሆን እንኳ እሱ እነሱ ዘንድ ከቢድዐ ሰዎች በታች ናቸው። ለዚህም ነው ኢብኑ ዐዲይ - ረሒመሁላህ - አልካሚል በተሰኘው ኪታባቸው ውስጥ ሙሸታሞችን በተመለከተ ሃያ ዘጠኝ ርእሶችን ሲሰጡ፣ የቢድዐ ሰዎችን በተመለከተ ግን አንድ ርዕስ ብቻ መስጠታቸው።" ልብ በሉ! ውሸትና ውሸታሞች ፀያፍ የሚሆኑበትን ገፅ አጉልተው ለማሳየት እንጂ ይህን ማለታቸው እንዳጠቃላይ ቢድዐውን እንደ ኢስላም መቃረቢያ አድርጎ የሚቆጥረው ሙብተዲዕ የከፋ ወንጀለኛ መሆኑ የሚያከራክር አይደለም። ፅሁፌን የምቋጨው በተከታዩ የነብዩ ﷺ ሐዲሥ ነው፦ "وإيّاكم والكذِبَ، فإنّ الكَذِبَ يَهْدِي إلَى الفُجُورِ، وإِنّ الفُجُورَ يَهْدِي إِلَى النّارِ وَمَا يزَالُ العبْدُ يَكْذِبُ وَيَتَحَرّى الكَذِبَ حَتّى يُكْتَبَ عِنْدَ الله كَذّابا". "ውሸትን አደራችሁን (ተጠንቀቁ)። ውሸት ወደ አመፅ ይመራልና። አመፅ ደግሞ ወደ እሳት ይመራል። አንድ ሰው ከመዋሸትና ውሸት ላይ ከማተኮር አይወገድም አላህ ዘንድ ውሸታም ተብሎ እስከሚመዘገብ ድረስ!" [ቡኻሪና ሙስሊም] == የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor

ዘመን መለወጫ የሚባለውን ኮተት በተመለከተ ከታላቁ ሸይኽ 🎙 ሸይኽ ሙሀመድ ዘይን https://t.me/Multeka_Selefiyin

ሁሉም ነገር ባለበት ይቀጥላል ብለህ አታስብ… የወጣ ሁሉ ይወርዳል … የኖረ ሁሉ ይሞታል… የማይነጋ ጨለማም አይኖርም… የሆነ ቀን ፀሃይ ራሱ ህጉን ጥሶ፣ ፍፃሜን ለመግለፅ ከምዕራብ የሚወጣበት ጊዜ አለ። የሰዎች ህይወትና የግንኙነት ሂደት ባልታሰበ ሁኔታ ሊለወጥ ይችላል። በጣም የወደደህ በመጨረሻ በጣም ይጠላህ ይሆናል። በጣም የጠላህ ደግሞ በጣም ይወድህ ይሆናል። t.me/abdu_rheman_aman t.me/abdu_rheman_aman

ድንቅ ንግግር በፍቅር ስም #ክብራቸውን ያጡ ስንት እና ስንት ናችው አላህ ይጠብቀን።

✍ደህና ነን’ የምንለው ሰው ሰልችቶን ሳይሆን፣ የውስጣችን ዝብርቅርቅ ህይወት አስረድተን እነሱን ማስጨነቅ ስላልፈለግን ነው።

⛔️ የሰውን ቀልብ እንደመጠገን ትልቅ ኢባዳ የለም፤ የሰውን ልብ እንደመስበርም ከባድ ነገር የለም። አንዳንድ ልቦች በአንድ ቃል ይሰበራሉ፤ አንዳንድ ልቦች በአንድ ንቀት፣ በአንድ ክህደት፣ በአንድ ዝምታ፣ በአንድ ያልተገባ ተስፋ ይሰበራሉ። አንተ የተናገርከውን ልትረሳው ትችላለህ፤ እሷ ግን ለዓመታት ልትረሳው ላትችል ትችላለች። አንተ እንደ ቀልድ የተናገርከው ነገር፣ ሌላው ሰው ሌሊት ላይ እያሰበው የሚያለቅስበት ህመም ሊሆን ይችላል። ስለዚህ… እንጠንቀቅ። የሰው ልብ እንደ መስታወት ነው፤ አንዴ ከተሰበረ እንደበፊቱ ለመመለስ ከባድ ነው። ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «مَنْ كَانَ يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ فَلْيَقُلْ خَيْرًا أَوْ لِيَصْمُتْ» “በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምን ሰው መልካም ነገር ይናገር ወይም ዝም ይበል።” አንዳንድ ጊዜ የምንሰጠው ትልቁ ስጦታ ገንዘብ አይደለም፤ ሰውን የሚያረጋጋ ቃል ነው። አንዳንድ ጊዜ የምናደርገው ትልቁ ሰደቃ እጃችንን ወደ ኪሳችን ማስገባት አይደለም፤ የተሰበረን ልብ በመጠገን ላይ መሳተፍ ነው። የሰበርናቸው ሰዎች ካሉ… ዛሬ እንደገና እናስብ። ምናልባት አንዲት እህት በእኛ ምክንያት በራሷ ላይ እምነቷን አጥታ ይሆናል። ምናልባት አንድ ወንድም በእኛ ቃል ምክንያት ለሰዎች መታመን ተቸግሮ ይሆናል። ምናልባት አንድ ሰው ፈገግ እያለ ቢታይም፣ በውስጡ ግን የእኛን ቃል ይዞ እየታገለ ይሆናል። እንደገና እንቅረባቸው። ይቅርታ እንጠይቃቸው። ምክንያቱን እናስወግድ። የተቻለንን ያህል ልባቸውን እንጠግን። “እኔ ምንም አላደረግኩም” ብለን ከመከራከር ይልቅ፣ “በእኔ ምክንያት ከተጎዳህ ይቅርታ አድርግልኝ” ማለት ክብርን አያሳንስም። ከዚህ ይልቅ የልብ ትልቅነትን ያሳያል። የሰው ልብ ከፍ ያለ አማና ነው። ስለዚህ እንደ ፈለግን ልንጫወትበት የሚገባን ነገር አይደለም። አላህ እንዲህ ይላል፦ ﴿وَقُولُوا لِلنَّاسِ حُسْنًا﴾ “ለሰዎች መልካም ነገርን ተናገሩ።” [البقرة: 83] እና ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «وَالْكَلِمَةُ الطَّيِّبَةُ صَدَقَةٌ» “መልካም ቃል ሰደቃ ነው።” ስለዚህ ዛሬ ከሰው ጋር ስትነጋገር፣ ከአፍህ የሚወጣው ቃል ምን እንደሚያደርግ አስብ። ልብ ሊሰብር ይችላል… ልብም ሊጠግን ይችላል። እኛ ግን የሚሰብሩ ሳይሆን የሚጠግኑ ሰዎች እንሁን። የሚያስለቅሱ ሳይሆን የሚያረጋጉ እንሁን። የሚያንቋሽሹ ሳይሆን የሚያከብሩ እንሁን። ከእኛ በኋላ ቁስል ሳይሆን መልካም አሻራ እንተው። እናማ ወዳጆቼ የሰበርነው ልብ ካለ… ነገ ይቅርታ እንላለን ብለን አንዘግይ። ዛሬውኑ ይቅርታ እንጠይቅ። ዛሬ የሰበርነውን ነገር ለመጠገን አንሞክር። ምክንያቱም አንዳንድ ይቅርታዎች በጊዜ ካልተባሉና ከዘገዩ የተሰበረውን ልብ ይበልጥ ያርቃሉ። 🌿 ሰዎች ሲያስታውሱህ፣ “እሱ ልቤን ሰብሮኛል” እንዳይሉህ ተጠንቀቅ፤ “ ይልቅ እሱ በአላህ ፈቃድ ልቤን ከብዙ ህመም አሳርፎኛል” ከሚሉት ሰው እንሁን። ልቦችን እንጠግን… ምክንያቱም እኛም አንድ ቀን የተሰበረ ልብ ይዘን ሰው ወደ እኛ ሊመጣ ይችላልና። t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy