Usmanic Islamic psychology/ ስለ ሰው ልቡና
Open in Telegram
በኢስላማዊ ሳይኮሎጂስት ኡስማን ሙስጠፋ የተመሠረተ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የሙስሊሞች የስነልቦና ህክምና The Virtual Center for Usmanic Islamic Psychology was founded by Usman Mustofa, a psychology student, researcher in Islamic psychology, and writer ለጥያቄ እና አገልግሎት ለማግኘት @usmanoman ላይ ያናግሩን።
Show moreThe country is not specifiedThe category is not specified
585
Subscribers
+1124 hours
+577 days
+19030 days
Posts Archive
በአመስጋኝነት ፀጋን የሚያቆይ ዱአ
رَبِّ أَوْزِعْنِي أَنْ أَشْكُرَ نِعْمَتَكَ
'ረቢ አውዚእኒ አን አሽኩረ ኒእመተክ'
ትርጉም ጌታዬ ያደረክልኝን መልካም ነገር አመሠግን ዘንድ እውቀት እና ግንዛቤ ስጠኝ
የዚህ ዱአ ስነልቦናዊ ጠቀሜታዎች
-አመስጋኝነትን ያሳድጋል
-ከውድቀት የማንሰራራት አቅም ይሰጣል
-በጎ አስተሳሰብን ያሳድጋል
ተዝኪየቱ ነፍስ/ነፍስን ለማፅዳት
4 ነገር መቀነስ 1 ነገር ማብዛት
- ወሬን
- ምግብን
- ልክ የሌለው ከሰዎች ጋር መቀላቀልን
- እንቅልፍ
ቀንሱ!
1 ነገር ማብዛት
- አዝካር/አላህን ዘውትር ማስታወስ
ጥያቄ 3
ቅናት እና ምቀኝነት ፈተነኝ!
እኔ የ28 አመት ወጣት ሴት ስሆን ።ውስጤን እረፍት የሚነሳኝ የስብእና ቀውስ እና ህመም እንዳለብኝ ይሰማኛል።ይህም ሂስድ/ምቀኝነት ነው ብዬ አምናለሁ።
ሰዎች በእውቀት በገንዘብ እና በውበት ከኔ የተሻሉ ከመሰለኝ እርቃቸዋለው።
አንዳንዴ በምቀኝነት ተነሳስቼ ልጎዳቸው አስቤ አላህን በመፍራት ትቼዋለው።
ከኔ የተሻሉ ሰዎች ሳይ ያላቸው ነገር እንዲጠፋ እፈልጋለው ከስረው ወይም ታመው ማየት ውስጤ ይመኛል።
በቃ ውስጤ ሰዎች ከኔ አንሰው እንጂ በልጠው ማየት አይፈልግም።
በራሴ ክፋት ተፈተንኩኝ። እረፍት አጣሁኝ። በኢስቲግፋር እና በተውበት ፈጣሪዬ ደጅ ተመላለስኩኝ ህመሜ ግን ጋብ ብሎ ዳግም ያገረሻል። እባክህ ከዚህ ነገር የምድንበትን ምክር ብትለግሰኝ። በፀፀት ታማሚዋ እህታቹ ነኝ።
(የጥያቄውን ምላሽ ቻናላችን ላይ ይጠብቁ ኢንሻአላህ!)
#ኡስማኒክ_ኢስላማዊ_ስነልቦና
ለጥያቄ እና አገልግሎት ለማግኘት @psychosman1 ላይ ያናግሩን።
2. ለ ትእግስት እና ለፅናት የሚጠቅም ዱአ
رَبَّنَا أَفْرِغْ عَلَيْنَا صَبْرًا وَثَبِّتْ أَقْدَامَنَا
"ረበና አፍሪጝ አለይና ሶብረን ወሰቢት አቅዳመና"
"ጌታችን ሆይ! ትእግስትን በኛ ላይ አዝንብ እግራችንንም አፅና(አደላድል) "
የዚህ ዱአ ስነ-ልቦናዊ ጥቅሞች
ወደ አላህ መጠጋት - ይህ ፀሎት በችግር ወቅት ወደ አላህ መጠጋት እንደሚያስፈልገን በማስታወስ ሰዎች ከሚያስጨንቃቸው ችግር ጋር የመታገልን አቅም ይለግሳቸዋል።
ፅናት - የመፅናትን እና የማገገምን ውስጣዊ አቅም ያሳድጋል።
ትእግስት • በትዕግሥት ከባድ የህይወት ውጣ ውረዶችን ማለፍ እንደሚቻል ያስታውሳል።
ሰዎችን በሀሜት ማንሳት ማቆም ካቃታችሁ ከሰዎች ጋር ስትገናኙ ስለ ዲን እውቀት ፥ ስለ ፖለቲካ ወይም ስለ ቴክኖሎጂ ብቻ አውሩ ወይም ስለ ስራ። ግን በዛው ባልደረባችሁን ድንገት ማማት እንዳትጀምሩ¡ እየተጠነቀቅን!😉#anti_backbiting_method_Muslims #hamet_hack
ጥሪ ለቻናል ባለቤቶች!
ወደ 500 ብሎም ወደ አንድ ሺ subscribers ለመድረስ የምናደርገውን ጉዞ በፍጥነት ለማሳካት የቴሌግራም ወይም የፌስቡክ ቻናል ያላችሁ ሰዎች
@usmanoman ላይ አናግሩኝ። ወይም ☝️ከላይ የተያያዘውን ቻሌንጅ ቻናላችሁ ላይ አጋሩ
ጀዛከላሁ ኸይረን!
to join usmanic islamic psychology 👇
https://t.me/usmanic_psychology
ኢስላሚክ ሳይኮሎጂ/ኢልመ- ነፍስ
ክፍል 3. ሩህ /رُوح (መንፈስ)
-ፊጥራ
-ነፍስ
-ሩህ
-አቅል/አይምሮ
-ቀልብ/ልብ
-ተዝኪየቱ ነፍስ/ራስን ከወንጀል ማፅዳት
ለዛሬ ሩህን በጣም በአጭሩ እናያለን ኢንሸአላህ!
ሩህ የሰው ልጅ መሠረታዊ
❮Essence❭ የማንነቱ ረቂቅ ክፍል ሲሆን ከማይታየው አለም ጋር ያለው የግንኙነት መስመር የተዘረጋበት ሚስጢራዊ መገለጫው ነው።
ስነመለኮታዊ እሳቤውን ስናይ:- ሩህ ሳናይ ከምናምንባቸው አበይት የእምነት ክፍሎች አንዱ ሲሆን አላህ ምንነቱን ምስጢር አድርጎ ከፍጡራን የደበቀው የስውሩ አለም እውነታ እንዲሁም ከሩህ አላህ የሰው ልጆች ላይ በመንፋት ሰው መሆንን ያላቀበት የክብር መገለጫ ነው።
ሩህ በኢስላሚክ ሳይኮሎጂ ጥናት ውስጥ:-
የምእራብያውያን ሳይኮሎጂ በክህደት ቆርጦ ከጣላቸው የሰው ልጆች የተፈጥሯቸው ምንነት የመኖራቸው መሠረት የሆነውን ሩህ ኢስላማዊ ሳይኮሎጂ ማዕከላዊ የትኩረት አካሉ አድርጎ የሰው ልጆችን ወደ ላቀ የስብእና የማንነት ብቃት የህሊና እና የአይምሮ ጤንነት እንዲመለሱ ሀያል የመዳን መሣሪያ አድርጎ ይጠቀምበታል።
ሩሀችን ከአላህ ጋር ባላት ትስስር የጎደላትን ነገር በመመርመር ሰዎችን በመንፈሳዊ እና ሀይማኖታዊ መመሪያዎች ከፍተኛ አምልኮአዊ ጥራት ላይ በማድረስ ሁለንተናዊ ደህንነታቸው ወደ ተፈጥሯዊ ጤናው የሚመለስበት ህክምናዊ ጥበቦችን የሚጠቀም አንድ አበይት የጥናት መስክ ነው።
✍️
ኢስላማዊ ሳይኮሎጂ መፅሀፍ
አዘጋጅ እና ፀሀፊ ኢስላሚክ ሳይኮሎጂስት ኡስማን ሙስጠፋ)
ኢንሻአላህ ይቀጥላል...
1, ከሁሉም አይነት የህይወት ጭንቀቶች እፎይታ ለማግኘት የሚያግዝ ዱአ:-
اللّهُمَّ إِنِّي أَعُوذُ بِكَ مِنَ الْهَمِّ وَالْحَزَنِ، وَأَعُوذُ بِكَ مِنَ الْعَجْزِ وَالْكَسَلِ، وَأَعُوذُ بِكَ مِنْ جُبْنِ وَبُخْلِ، وَأَعُوذُ بِكَ مِنْ غَلَبَةِ الدَّيْنِ وَقَهْرِ الرِّجَالِ
"አላህ ሆይ እኔ ከሃዘን እና ከጭንቀት ፣ አቅም ከማጣት እና ከስንፍና ፣ ከፍርሀት እና ከስስት ፣ በእዳ ከመያዝ እና ከሽንፈት በአንተ እጠብቃለሁ።"
የዚህ ዱአ ስነልቦናዊ ጠቀሜታዎች
-ጭንቀትን ያስወግዳል
- ስሜታዊ መረጋጋትን ይለግሳል
- ሀይል እና አቅም በመስጠት ችግሮችን ጥሶ የማለፍ አቅም ይሰጣል።
የሰው ልጅ ፈተናዎች እና የቁርአን ማፅናኛዎች
ሱራ አልበቀራህ 2:286
አላህ ነፍስን ከምትችለው በላይ አያስገድዳትም...
– ከዚህ አያ የምንማረው የሚገጥመን ሁሉም ፈተና እኛ ልንሸከመው የምንችለው ብቻ እንደሆነ ይገልፃል።
ሱራ አል ሸርህ 94:5-6
..."በእርግጥም ከመከራ ጋር እፎይታ/እረፍት አለ።
– ይህ አያ ችግር ብቻውን እንደማይመጣ ችግር ውስጥም እረፍት እና ሰላም ተጣምሮ እንደሚገኝ ያስታውሰናል
የሰው ልቦና (የስነ - ልቦና) ሀኪሙ ነቢዩ (ﷺ)
ሰውየው መጣ! ፍትወት ባነደደው ድምፀት ፣ ፍላጎት ባናረው አንደበት 'ዝሙት ይፈቀድልኝ' አላቸው።
አልተቆጡትም ፣ አማከሩት ፣ ሰሙት። በእናቱ እና በእህቶቹ ይህ ነገር ቢደረግ ይወድ እንደሆነ ጠየቁት (ይህ cbt/cognitive behavioral therapy ይለዋል የዘመኑ ስነልቦና) እንደማይወድ ነገራቸው። እንደዛ ማሰቡንም ፣ ምኞቱንም ተፀየፈ።
ከዛም ልቡ ላይ እጃቸውን አሳርፈው ዱአ አደረጉለት። ይህ መንፈሳዊ ህክምና ይባላል በእስልምና ወይም በኢስላሚክ ሳይኮሎጂ -
ከዛም በኋላ ዝሙትን በጣም ጠላ።
የተሳካ የማማከር የማከም እና የማዳን አገልግሎት።
ይህን ነው ኢልመ ነፍስ/ኢስላሚክ ሳይኮሎጂ። ኢስላማዊ መሠረት ይዘን ነው የተነሳነው።
ኢስላሚክ ሳይኮሎጂ/ኢልመ- ነፍስ አጭር ፅሁፎች
ክፍል 1 ፊጥራ 👈
ክፍል 2. ነፍስ 👈
ክፍል 3. ሩህ
ሌሎች እስካሁን የተለቀቁ የቻናሉ ጠቃሚ ፅሁፎች
- የመፅሐፍ ሽያጭ
የስነልቦና ጥያቄ ና መልሶች (case studies)
ጥያቄ 1
ሙስሊም የ 31 አመት ሴት ስሆን እስካሁን የትዳርን ወግ አላየሁም።
መልስ .1
መረጃዎች እንደሚያሳዩት በአለም አቀፍ ደረጃ የሴቶች የጋብቻ እድሜ ድሮ ከነበረበት በብዙ እጥፍ ከፍ ብሏል።
ጥያቄ ሁለት
አሰላሙአለይኩም እኔ የ 27 አመት ወጣት ወንድ ነኝ።በአንድ አሳሳቢ ነገር ተለክፍያለው።
መልስ ሁለት ክፍል 1
በአይን የሚገባው የዘመኑ አደገኛው እፅ (የፖርን ፊልም)
መልስ/ ክፍል ሁለት
ይህን የወንድማችንን ጥያቄ በሁለት ዙር እንድናየው ያስገደደን ነገር...
የሚስጥራዊነት ደህንነት ማስታወሻ/ confidentiality alert
እዚህ ጋር ለህዝብ የምናቀርባቸው ታሪኮች በራሳቸው በባለታሪኮቹ ፍቃድ ወይም ተጠይቀን ነው።
በውስጥ የሚሰሩ የማማከር ስራዎች ምስጢራውነታቸው የተጠበቀ መሆኑንን በጥብቅ እናስታውሳለን።
ታሪኳን ካነበባችሁ በኋላ ትክክል ነው የምትሉትን ውሳኔ ምረጡ (ምርጫው ከአምስት ቀን በኋላ ይዘጋል)
+1
ታሪክ ሁለት
የእህታችን ልብ የሚነካ ታሪክ! እንደዚህ አጋርታናለች።ካነበባችሁ በኋላ ሃሳባችሁን ከታች የምናያይዘው poll/መምርጫው ላይ አስፍሩ።
