ch
Feedback
Usmanic Islamic psychology/ ስለ ሰው ልቡና

Usmanic Islamic psychology/ ስለ ሰው ልቡና

前往频道在 Telegram

- እውነተኛ የህይወት ታሪኮች - ኢስላማዊ የስነልቦና ምክሮች ፣ ጥያቄዎች እና አገልግሎቶችን ያገኛሉ። - ስለ ኢስላማዊ ሳይኮሎጂ ይማራሉ። - ሳምንታዊ ሽልማቶች ለሁሉም በማጋራት የሙስሊሙ ኡማ የአይምሮ ጤና የሚጠበቅበትን ይህን ቻናል እናሳድግ ጥያቄ ለማቅረብ እና አገልግሎት ለማግኘት @usmanoman ላይ ያናግሩን።

显示更多
未指定国家未指定类别
761
订阅者
+2324 小时
+1617 天
+36130 天
帖子存档
ሂስድ/ምቀኝነት መንስኤዎች እና መዳኛዎቹ መልስ/ ክፍል ሁለት (የማጠቃለያ መልስ) የሰው ልጅ ትልቁ ፈተናው በነፍሱ ጉትጎታ ወንጀል ለመስራት ሲፈተን ባለው ትግል ውስጥ ነው።ይህን ሀሳብም ይበልጥ ግልፅ የሚያደርግ ዘውትር የምንሰማው ወይም የምንለው ግን ትርጉሙን ብዙም ያላስተዋልነው ታላቅ ዱአ አለ። أعوذ بالله من شرور أنفسنا ومن سيئات أعمالنا ትርጉሙም 'ከነፍሳችን ሸር እና ከመጥፎ ስራችን ውጤት ወይም ህይወታችን ላይ ከሚያስከትለው ተፅእኖ በአላህ እንጠብቃለን' ማለት ነው። የሰው ልጅ ትልቁ ጀሀዱ/ትግሉ ከሌሎች ጋር አይደለም። ከውስጣዊ መሻቱ እና ከተፈጥሮው መጥፎ ዝንባሌ ጋር የሚያደርገው እንጂ። ሰው በብስጭት ፣ በዝሙት በስርቆት እና በብዙ እኩይ የተግባር ዝንባሌዎች እንደሚፈተነው ሁላ በምቀኝነት/ሌሎችን በመመቅኘት ሊፈተን ይችላል። እህቴም ያጋጠማት ተመሳሳይ የችግር አይነት ነው።ይህ በሽታም ነፍስን ሳያቋርጡ በመፈተሽ ፣ በማፅዳት ፣ እና በመመርመር ወደ አላህ በተውበት በመመላለስ የሚድን የልብ ህመም ነው። እህቴ አንቺ የተፈተነሽበት ጉዳይ የአለምን ህዝብ እና የነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) ኡማ እየተገዳደረ ያለ የብዙ ቤተሰቦችን ህብረት የበጠሰ ለበርካታ ወንጀሎች መንስኤ በሆነው ነገር ነው። እህት እህቷን በመመቀኝነት ምክንያት ጎድታለች ፣ እናት እና ልጅ በዚህ ምክንያት ተቆራርጠዋል ፣ ልጅ አባቱን ገድሎ ወደ ዘላለማዊ የህሊና ወህኒ እና ለምድር እስር ቤት ተዳርጓል ፣ ወንድም ወንድሙ ላይ ተነስቷል ጓደኛማችነት ፈርሷል። የብዙ ሲህር የማድረግ መሠረታዊ መንስኤ ከስሩ ያልታከመ ምቀኝነት እንጂ ሌላ አይደለም። ቅናት የወለደው መጠላለፍ የሰው ልጆች የተተበተቡበት የፅልመት ድር ነው። እንዳንቺ የነፍሱን እኩይ ባህሪ ለይቶ እና አውቆ ፣አምኖ የሚፀፀት ሰው ጥቂት ነው። ይልቅስ ራሱን በማፅደቅ እና ነፍሱን ከእንከን የጠራች አድርጎ የሌሎችን ጎዶሎ ለማየት ሁሉም በሚጥርበት አለም ያንቺ ራስን የመፈተሽ አቅም እና እንከንን ለራስ ሳያደሉ ከነፍስያ መንቀስ መቻል ትልቅ የሚደነቅ ባህሪ ስለሆነ ቀጥይበት ለማለት እወዳለሁ። ለዛሬ ግን ለብዙ ቀናት ያንከባለልነውን ጥያቄ መፍትሔዎቹ ያልናቸውን የተወሰኑ ነጥቦች በመጥቀስ እናጠቃልላለን። 1ኛ, ይህ ስሜት ሲሰማሽ 'አኡዙቢላሂ ሚነሸይጧን ረጂም' (ከሰይጣን ተንኮል በአላህ እጠበቃለው) በማለት እኩይ የሆነውን የሰይጣን አላማ ቶሎ አክሽፊበት 2ኛ, እኛን ሊያስቀናን የሚችል ፀጋን ሰዎች ዘንድ ስናይ 'ማሻአላህ' ወይም 'ተባረከላህ' ማለት መርሳት የለብንም አላህ የተባረከ እና ብሩክ ነገሮችም በሙሉ ከሱ መገኘታቸውን እውቅና መስጠት እና የፀጋውን ምንጭ ወደሱ በመመለስ አስገኚውን ማክበር በማድነቅ እና በማመስገን ልብን በአላህ ውሳኔ ማረጋጋት ያስችላል ። 3ተኛ, ምንም ነገር ላንቺ ተፅፎልሽ የቀረ ወይም የሚቀር አለመኖሩን አስታውሺ በቀደር ያለሽን እምነት አዳብሪ። 4ተኛ, የዚችን አለም ማጣት እና ማግኘትም ፈተና ብቻ እንደሆኑ አውቀሽ የተመኘሽው ፀጋ ወዳንቺ ቢመጣ ምንአልባት ከአላህ ጎዳና የሚያርቅ እና ለሁለት አለም ኪሳራ ሊዳርግ በሚችል ፊትና ልትወድቂ ስለምትችይ አላህ ጠብቆሽ ሊሆን እንደሚችል በማስታወስ አላህን ማመስገን እና ውሳኔውን መውደድን ልመጂ። 5,ካንቺ በታች ያሉትን ሰዎች አስታውሺ። አንቺ ያለሽን ነገር ዘወትር እንዲያገኙ አላህን በሚማፀኑ ሰዎች እና አንቺ ያገኘሽውን ፀጋ ላንዳፍታ ቢያገኙ ትልቁ ህልማቸው እንደተሳካ በሚያልሙ ሚሊዮን የአለም ህዝቦች ጎን እራስሽን አስተያዪ። 6, ይህን ስሜት እንዲያጠፋልሽ አላህን በመጠየቅ በዱአ በርቺ። 7,የጠዋት እና የማታ አዝካሮችን አዘውትሪ። በተለይ ከሸር እና በሂስድ የሚታደጉትን ሁለቱን አያ አዘውትሪ :- ቁል አኡዙ ቢረቢናስ እና ቁልአኡዙ ቢረቢል ፈለቅ ✍️ ኡስማን ሙስጠፋ ከኡስማኒክ ሳይኮሎጂ። ለጥያቄ እና አገልግሎት ለማግኘት @psychosman1 ላይ ያናግሩን

ከህመም እረፍት በኋላ በምን እንጀምር ? (ከ8 ሰአት በኋላ የምርጫ ፖሉ ይዘጋል)
Anonymous voting

ተጨንቃችሁ ለደወላችሁልኝ ለፃፋችሁልኝም እንዲሁም በድብቅ ዱአቹህ ላሰባችሁኝ በሙሉ በአላህ ስም ከልብ አመሠግናለሁ። አሁን በተሻለ የጤንነት ደረጃ ላይ ስልምገኝ ጉዟችንን እንቀጥላለን።ኢንሻአላህ

"በታመመኩኝ ጊዜ እሱ ይፈውሰኛል!" እኔ የናንተ ኢስላሚክ ሳይኮሎጂስት ከብዙ በጤና መንቀባረር እና መንደላቀቅ በኋላ ከህመም እንቅፋት ጠጠሯ አደናቀፈችኝ! 🥹😭 አልሃምዱሊላህ! 🙏 እመለሳለሁ! እስከዛው በዱአቹህ አትርሱኝ ሰላሙላሂ አለይኩም! ✨

አሁን ያሉበት ሁኔታ ? (status)
Anonymous voting

የሰው ልጅ ህይወት በብዙ የደሰታ እና የሀዘን ትዕይንት የተሞላ እስከ ሞት የተዘረጋ የእንቆቅልሽ መስመር ነው። ይህም የህይወት ታሪክ እህታችን ከዲያሪዋ (ከማስታወሻ ደብተሯ) ላይ የተወሰኑ መስመሮችን
+1
የሰው ልጅ ህይወት በብዙ የደሰታ እና የሀዘን ትዕይንት የተሞላ እስከ ሞት የተዘረጋ የእንቆቅልሽ መስመር ነው። ይህም የህይወት ታሪክ እህታችን ከዲያሪዋ (ከማስታወሻ ደብተሯ) ላይ የተወሰኑ መስመሮችን ከላከችልን የተወሰደ እና ለሰው እንዲጋራ የፈቀደችው ነው።

በተውበት/በንስሀ ውሀ ታጥበን ፣ በኢስቲግፋር ብርሀን የወንጀላችንን ትብታብ በጣጥሰን ፣ በአዝካር ጌጥ ደምቀን በሰለዋት ቁልፍ የህይወታችንን በር እንከፍታለን።

አሁን ምን እየተሰማችሁ ነው? What do u feel now?
Anonymous voting

የሳምንታዊ የኢንተርኔት ጥቅል ተሻለሚ 🏅🏆 - ሀያት በድሩ - ከ አዲስ አበባ - ቀድማ በመመለስ የሽልማቱ አሸናፊ መሆን ችላለች። ሁላችሁም ስለተሳተፋችሁ ከልብ እናመሠግናለን። ቀጣዩን ለማሸነፍ ዝ
የሳምንታዊ የኢንተርኔት ጥቅል ተሻለሚ 🏅🏆 - ሀያት በድሩ - ከ አዲስ አበባ - ቀድማ በመመለስ የሽልማቱ አሸናፊ መሆን ችላለች። ሁላችሁም ስለተሳተፋችሁ ከልብ እናመሠግናለን። ቀጣዩን ለማሸነፍ ዝግጁ ይሁኑ።

#1 ሽልማት የሚያስገኝ ጥያቄ ደስታ ብለን ሀዘን ካልን ድህነት ብለን A.ብልፅግና B.ሀብት C.መትረፍረፍ የ 780 ሜ.ባ የኢንተርኔት ፖኬጅ ሽልማት የሚከተለውን ጥያቄ ቀድሞ ለመለሰ #ከኡስማኒክ_ኢስ
#1 ሽልማት የሚያስገኝ ጥያቄ ደስታ ብለን ሀዘን ካልን ድህነት ብለን A.ብልፅግና B.ሀብት C.መትረፍረፍ የ 780 ሜ.ባ የኢንተርኔት ፖኬጅ ሽልማት የሚከተለውን ጥያቄ ቀድሞ ለመለሰ #ከኡስማኒክ_ኢስላሚክ_ሳይኮሎጂ

ከየት ናችሁ?
Anonymous voting

The final test of freedom is this: can u remain the same person praise, in insult, in gain, and in loss "ታላቁ የነፃነት ፈተና በአድናቆት በመሰደብ በማጣት ፣ በማግኘት እና በማጣት አንተ ያው መሆን ትችላለህ ወይ? የሚለው ነው።"

አገጋሚነት/ Resiliency "በመከራዎች ሰርጥ ውስጥ አልፈዋል። ጥልቅ ህመም እና መከራ በሳቸው ላይ ተነባብሮ ሄዷል።  ፈተና ረሀብ እና ተቀባይነትን ማጣት መገፋት እና ውድቀት ለሳቸው የነገ ሻማቸውን የሚለኩሱበት የማገገም ሀይላቸው እንጂ ተሽመድምደው የሚወድቁበት ጋሬጣቸው አይደለም። ጠንክረው አገግመው ይነሳሉ መውደቃቸው የሚበረቱበት ፅናት ነው ትግላቸው ዳግም ህያው የሚያደርጋቸው ብርሀን ነው። በመሰበራቸው ባህር ውስጥ የፅናታቸውን መርከብ ሰርተዋል። በመውደቃቸው ረጅም መንገድ የማይፈርስን ድልድይ ገንብተዋል" (ገፅ 32 'ፍፁም ሰው ፍፁም ነቢይ' መፅሀፍ ከ ነቢዩ ስነ ባህሪያት የተወሰደ (ፀሀፊ ኡስማን ሙስጠፋ ) ይህ የረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ስነልቦናዊ የፅናት ተምሳሌትነት ነው። እኛም ጥንካሬን ከሳቸው እንማር ወድቆ መነሳትን ተሰብሮ መጠገንን ከአርአያችን እንቅሰም።

የህይወት እይታ ጥራት (clarity) ሲጎድለን ፤ ያስተካክለዋል
Anonymous voting

የህይወታችን እይታ ጥራት (clarity) ሲጎድለን ለማጥራት ___?
Anonymous voting

የጥያቄ ሶስት መልስ ክፍል 1 በጎ ስራዎችን በልቶ የሚጨርሰው ;የልብ በሽታ' ምቀኝነት/ሀሰድ - (حسد/envy) -: ኢስላማዊ ፍቺው የተመቀኘነው ሰው ያገኘው ፀጋ እንዲወገድ መመኘት ማለት ነው። ሀሰድ/ምቀኝነት ወይም መጥፎ ቅናት ብዙ ሰው የሚፈተንበት የቀልብ/የልብ ህመም አይነት ነው። ነፍሳችን የታችኛው ደረጃ ላይ ሆና (ነፍሱል - አማራ-) መጥፎ ሀሳቦችን ሳታቋርጥ በምታመነጭበት እርከን ላይ የውስጥ መጥፎ (ውስዋስ) ጉትጎታ እና ደመነፍሳዊ ራስን ያለ ቅጥ የመውደድ ሁሉንም ለራስ ብቻ የመከጀል የተዛባ ውስጣዊ ባህሪ ነው። ጤናማ ቅናት (Benign Envy):- በሀብት እና በእውቀት ከኛ የተሻለ ሰው ጋር ለመድረስ የሚደረግ ጤናማ ውድድር ልኩን እስካላለፈ ድረስ ለእድገት ይጠቅማል። በሁለት የሰው አይነትም መቅናት እንደሚቻል ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ነግረውናል። እሱም አላህ ሀብት ሰጥቶት በልኩ በሚለግስ ሰው እና እወቀት ተሰጥቶት በስርአት በሚሰራበት ሰው ነው። ይህ ይቅናት አይነትም ለበጎ ምግባር የሚያነሳሳ ነው። የቅናታችን ደረጃ ልኩን አልፎ ተንኮልን ሲይዝ ወይም የሌላውን ሰው የፀጋ መወገድ ልባችን ሲከጅል አሁን ስሜታችን ከጤነኛ የቅናት ደረጃ ወደ ምቀኝነት ተሸጋግሯል። ምቀኝነት ሌላው ትርጉሙ አላህ ለሌላ ሰው የመደበው ፀጋ ለሱ አይገባውም ማለት ስለሆነ ከአላህ ውሳኔ/ቀደር ጋር ያላትማል። ስለዚህ ሂስድ- ተውበት/ንስሐ የሚፈልግ ድብቅ ውስጣዊ የወንጀል አይነት ነው። ነቢዩ ሙሀመድም (ሰ.ዐ.ወ) ከዚህ ነገር ሲያስጠነቅቁ እንዲህ ብለዋል – "ምቀኝነትን ተጠንቀቁ እሳት ነገራትን አቃጥሎ እንደሚጨርሰው ምቀኝነትም መልካም ስራን ይበላል"።ብለዋል (አቡዳውድ) (ይህ ስለ ነገሩ አሳሳቢነት ጥያቄውን እንደመነሻ በመጠቀም የቀረበ የክፍል 1 ማስታወሻ ሲሆን ለእህታችን ጥያቄ ቀጥተኛ ምላሽ በክፍል 2 ምላሽ ላይ ይሰጣል) ኢንሻአላህ ✍️ ኡስማን ሙስጠፋ ከኡስማኒክ ሳይኮሎጂ። ለጥያቄ እና አገልግሎት ለማግኘት @usmanoman ላይ ያናግሩን።

ሀሰድ/ምቀኝነት ወይም መጥፎ ቅናት ብዙ ሰው የሚፈተንበት የቀልብ ህመም አይነት ነው። ነፍሳችን የታችኛው ደረጃ ላይ ሆና መጥፎ ሀሳቦችን እና ተግባሮችን ሳታቋርጥ በምታመነጭበት እርከን ላይ

የታመመ ልብ __ይፈወሳል
Anonymous voting