en
Feedback
የወራቤ ሰለፊዮች መገናኛ

የወራቤ ሰለፊዮች መገናኛ

Open in Telegram

📝👉በአላህ ፍቃድ በዚህ ቻነል በወራቤ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ መድረሳዎች የሚሰጡ የሰለፊዮች ደርስ ፣ሙሃደራ እንዲሁም መልእክቶች የሚተላለፉበት ይሆናል !!! https://t.me/ibnbaz1212

Show more
The country is not specifiedThe category is not specified
3 392
Subscribers
+4824 hours
+1687 days
+30830 days
Posts Archive
🎁ስጦታ እውቀትን ለምትወዱ ሰዎች ከታች ያለችውን OPEN የምትሉዋን ነገር በመጫን የሰለፊዮችን ቻናል ይቀላቀሉ

🚫ትንሽም ቢሆን ንግግሩ ቅድሚያ ሊሰጠውና ሊከበር ይገባዋል ❕ 🎙قال إبراهيم الحربي: «الصَّغِيرَ إِذَا أَخَذَ بِقَوْلِ رَسُولِ اللهِ ﷺ وَالصَّحَابَةِ وَالتَّابِعِينَ فَهُوَ كَبِيرٌ 📚شرح أصول اعتقاد أهل السنة للالكائي، دار طيبة، السعودية، الطبعة الثامنة، 1423هـ، ج1، ص95 ➽ኢብራሂም አል'ሐርቢ እንዲህ ብለዋል፡- "አንድ ሰው በዕድሜው ትንሽ ቢሆንም    የመልእክተኛን  ﷺ ፣ የሶሐባዎችን እና የታቢዖችንን ንግግር  አጥብቆ ከያዘ  እርሱ ታላቅ ነው" 📚ሸርሑ ኡሱሊ ኢዕቲቃዲ አህሊ አስ'ሱና ሊል'ላላካኢ፣ ዳር አጥ'ጦይባህ ማተሚያ ቤት፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ 8ኛ እትም፣ 1423 ዓ.ሂ.፣ ጥራዝ 1፣ ገጽ 95። 🎙قال السجزي: «فَالْمُتَّبَعُ لِلْأَثَرِ يَجِبُ تَقْدِيمُهُ وَإِكْرَامُهُ، وَإِنْ كَانَ صَغِيرَ السِّنِّ غَيْرَ نَسِيبٍ 📚 رسالة السجزي إلى أهل زبيد، عمادة البحث العلمي، المدينة المنورة، الطبعة الثانية، 1423هـ، ج1، ص340 ➲አስ'ሲጅዚይ እንዲህ ብለዋል፡- "የሐዲሥንና የአሰር መንገድ የተከተለ አካል ዕድሜው ትንሽ እነ ዝነኛ ባይሆንም እንኳን እሱን ማስቀደም እነ ማክበር ግዴታ ይሆናል"። 📚ሪሳላቱ አስ'ሲጅዚይ ኢላ ዙበይድ፣ መዲናቱ አል'ሙነወረህ የምርምር ማዕከል 2ኛ እትም፣ 1423 ዓ.ሂ.፣ ጥራዝ 1፣ ገጽ 340። 📝ተጨማሪ  ትምህርቶችን   ለማግኘት የቴሌግራም➷➴ Channeሉን  ይቀላቀሉ !!! https://t.me/MisbahMohammed_6682

مسألة_رفع_اليدين_في_تكبيرات_الجنازة_260809_222824.pdf0.35 KB

ታላቅ የሙሃዶራ ዝግጅት በ online በጉራጌ ዞን በእኖር ወረዳ በእንቡሻር መንደር መስጂድ የገቢ ማሰባሰቢያ ጉሩፕ ↘️↘️ https://t.me/+OeGJDGkF--FhOGRk 🗓 ቀን:- የፊታችን ሰኞ
ታላቅ የሙሃዶራ ዝግጅት በ online በጉራጌ ዞን በእኖር ወረዳ በእንቡሻር መንደር መስጂድ የገቢ ማሰባሰቢያ ጉሩፕ ↘️↘️ https://t.me/+OeGJDGkF--FhOGRk 🗓 ቀን:- የፊታችን ሰኞ 04/12/2018 ከምሽቱ 3:00 ሰኣት ጀምሮ 🪑በአሏህ ፈቃድ የእለቱ ተጋባዠ እንግዶቻችን፦ 🎙1️⃣  ኡስታዝ አቡ ሙዓዝ - ታጁዲን (ሀፊዘሁሏህ) 🎙2️⃣ ኡስታዝ ሙሀመድ ሰልማን (ሀፊዘሁሏህ) በጉራጌ ዞን በእኖር ወረዳ በእንቡሻር መንደር መስጂድ የገቢ ማሰባበሰቢያ የቴሌግራም ግሩፕ ላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰአት ጎራ በማለት ይሳተፉ ሌሎችንም ያሳትፉ በጉራጌ ዞን በእኖር ወረዳ እንቡሻር መንደር መስጂድ የሂሳብ አካውንት CBE 1000774749962 BOA 261020238  ኡመር አሊ&ሣሊህ ኩመል&አብድል ጀሊል አብድልሽኩር 🌐  👉ሼር 👉 ሼር  👍አድ👍 አድ በማድረግ ሀላፊነታችን እንወጣ  ለአኼራችን አሻራ እናሳርፍ !! 👇👇↘️↘️ https://t.me/+OeGJDGkF--FhOGRk

​💎 እውቀት የነቢያት ውርስ ነው! ​አሁኑኑ ይቀላቀሉን! 👇

"ባሌን ሌሎች ሴቶች ሲያዩት ዝንጀሮ ያስመስለው" አንድ ሴት ባሏን የግሏ ብቻ ለማድረግ ስትል ባሌን ሌሎች ሴቶች ሲያዩት ዝንጀሮ ያስመስለው ብላለች ይባላል።እናም እቺ ሴት ያስጨነቃት ባሏ የእርሷ ብቻ መሆኑ እንጂ የባሏ ገፅታ ሰዎች ዘንድ መበላሸቱ አላሳሰባትም።ልክ እንደዚሁም አንዳንድ ወንድሞች አላህ ይቅር ይበላቸውና ከደዓዋው መስለሃ ይልቅ የግል መስለሃቸውን ለማስጠበቅ በወንድሞቻቸው ላይ በደልን ይፈፅማሉ።ይህን ፁሁፌን እንድፅፍ ያነሳሳኝ የሚከተለው ክስተት ነው። ሀምሌ 29/2018 ከዓሱር ሰላት በኃላ አንድ ስልክ ከአንድ ወንድሜና የቀድሞ ተማሪዬ በኩል ተደወለልኝ።ሰላምታ ከተለዋወጥን በኃላ በመቀጠል እርሱ በሚገኝበት ጀመዓ የደዓዋና የኮርስ ፕሮግራም ለማስኬድ የጋበዟቸው የሱና መሻኢኾችና ኡስታዞች እንደነበሩ ብሎም ማስታወቂያ ጭምር ሰርተው አሰራጭተው እንደነበረ ነገር ግን አንድ ሰው እኔም የማውቀው ወንድሜም የሚያውቀው ወንድም ደውሎለት እገሌ የሚባለው ኡስታዝ ችግር ስላለበት ለምን ጋበዛችሁት ብሎ እንደተቃወመና የተለያዩ ምክንያት የሚላቸውን የትችት ነጥቦችን በመጥቀስ እንዳስጠነቀቀና በዚህ ምክንያት በዚህ ወንድም ማስጠንቀቂያ መሰረት በቦታው ያሉ ወንድሞች ለግዜው በነገሩ በመወዛገብ ፊትና ለመቀነስ በሚል ተወያይተው ያኛውን የሱና ተጋባዥ ኡስታዝ ከፕሮግራሙ እንዲሰረዝ በማድረግ ማስታወቂያውን በአዲስ መልክ ለመቀየር እንደተገደዱ ነግሮኝ ከፕሮግራሙ ስለተወገደው ተጋባዥ ኡስታዝ እውነታ የምታውቀው ነገር አለ ብሎ ጠየቀኝ።እኔም ጉዳዩን ወደ መሻኢኾች በማስጠጋት መረጃ ከእነርሱ እንዲወስድ ከአንዳንድ መንደርደሪያ ምክረሃሰቦች ጋር አቀጣጫ ሰጠውት። በጣም የተደነቁት ከዛም አልፎ ያስደነገጠኝ ነገር ቢኖር ደውሎ አስጠንቃቂውም ማስጠንቀቂያ የተደረገበትም ኡስታዝ የሱና ሰዎች ከመሆናቸውም ጋር በውስጥ መስመር በዚህ ልክ የማስጠንቀቅ እርምጃው ነበር።በእርግጥም ይህ አይነት የሰለፍዬችን አንድነት የሚንድ አካሄዶች ከጀመሩ ሰንበትበት ያለና  በተደጋጋሚ በየቦታው እየተበራከተ ያለ እውነታ ነው።እገሌን በዚህ ቻናል ላይ አትጋብዙት፣ እገሌን ከጋበዛችሁት እኛ አንሳተፍም፣ ለእገሌ መድረክ እንዳትሰጡት እና የመሳሰሉ ግፈኛ ፍርዶች ከተለያየ አቅጣጫ ይሰማሉ ናቅ ተደርገው ታልፈው እንጂ። ውድ ሰለፍይ ወንድምና እህቶች! ሰለፍያ በዚህ ብልሹ አካሄድ እንደማትረዳና ይልቁንም ሰለፍዬችን ወደ ተወገዘው ግሩብተኝነት የሚያደርስ ስለሆነ ከዚህ ተግባር መቆጠብና ከፊላችን ከፊላችንን በዚህ አካሄድ ላይ አላህን ፍራ በማለት ልንተራረም ይገባል። ይህን ዓይነት አካሄድ በግዜ የማንቀርፍ ከሆነ ከባድ ጥፋትን በሰለፍዬች አንድነት ላይ ስለሚያስከትል ከዚህ ብልሹ አካሄድ እንቆጠብ ባይነኝ። ጥፋቶች ካሉም የሸሪዓን ጥቅምና ጉዳት ሚዛንን በጠበቀ መልኩ ወደ ባለቤቶቹ (መሻኢኾች) በመመለስ እንዲታረም ማደረግ አማራጭ የሌለው ሸሪዓዊ መርሆ ነው።ሁሉም እየተነሳ ግልፅ ባልሆነ ምክንያትና ድብቅ በሆነ የአደረጃጀት መዋቅር በንፁሃን ወንድሞች ላይ  ግፈኛ ፍርድ የሚሰጥ ከሆነ በመጀመሪያ ደረጃ ተጎጂው ባለቤቱ ሲሆን በመቀጠልም የደዓዋውን ጤነኛ ተደራሽነት በማሰናከል ከባድ የሆነ ትርምስና ስርአትአልበኝነትን ያስከትላል። ሰለፍዬች በጥፋት ቡድን ከየቦታው እየታመሱ ባሉበት በዚህ ወቅት ውስጣዊ የሰለፍዬችን የአንድነት እሴታቸውን የሚንድ የጥፋት አካሄድ ማራመድ ከሸሪዓም ከዓቅልም ብሎም ከሞራልም አንፃር የተወገዘ ነው። የሸሪዓችን መርሆ የሚያዘውም አንድ ሙስሊም ሌላን ሙስሊም እንዳይበድለው ብቻ  ሳይሆን ወንድሙም ተበድሎ ያገኘው ግዜ አቅሙ በቻለው ልክ  ከጎኑ ሊቆምና ሃቁን ሊያስመልስለትና በተቃራኒው ደግሞ በዳዩን መታገል ነው። ይህንም በሚመለከት ታላቁ ነብይ صلى الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋል: "المُسلِمُ أخو المُسلِمِ لا يَظلِمُه ولا يُسلِمُه" (أخرجه البخاري) "አንድ ሙስሊም የሌላኛው ሙስሊም ወንድም ነው።አይበድለውምም፣ (ተበድሎም ሲያገኘው የማይረዳው ሳይሆን)  አሳልፎ  (ለበዳይ) አይሰጠውም።" ይህ ሀዲስ የሚጠቁመን በምንም መልኩ አንድ ሙስሊም ሌላኛውን ሙስሊም እንደማይበድለውና ሌሎች አካላትም ወንድሙን ሲበድሉት አይቶ እንዳላየ፣ ሰምቶ እንዳልሰማ ሆኖ የሚተወው እንዳልሆነ ነው። ዛሬ አላህ ያዘነላቸው ሲቀሩ ብዙዎቻችን ከተበደሉት ጎን ልንቆም ቀርቶ በዳይን በማገዝ ላይ በበደል ላይ በደልን እንጨምራለን።በደል አይደለም ሰለፍይ ወንድምህን ይቅርና እንስሳትን መበደልም ቢሆን ነገ ዕለተቂያማ የከፋ ውጤት ያስከትላል።ነብያችን صلى الله عليه وسلم እንደተናገሩት:— (اتَّقُوا الظُّلمَ ؛ فإنَّ الظُّلمَ ظُلُماتٌ يومَ القيامةِ) (أخرجه مسلم) "በደልን ተጠንቀቁ፣ በደል ነገ ዕለተ ቂያማ (ድቅድቅ) ጨለማዎች ነውና።" ውድ ሰለፍይ ወንድም እህቶች ዲን በስሜት፣ በእልክ ብሎም ግፈኛ በሆነች የሴራና የተንኮል አደረጃጀት አይረዳም ይልቁንም ዲን የሚረዳው በማስረጃ፣ በፍትህ፣ አላህን በመፍራትና የአላህን ተጠባባቂነት ብሎም ከመላእክቱም ተጠባባቂዎች እንዳሉብን በማወቅ በምናደርጋቸው እንቅስቃሴ መሆኑን በመገንዘብ አላስፈላጊ ከሆነ የፊትና፣የጥላቻ፣ የቂመኝነትና የእልክ  አካሄዶች አላህን በመፍራት ልንቆጠብና  አጥፊዎችንም ተው ልንላቸው ይገባል።ነገራቶች ስርአታቸውን በዚህ መልክ በግዜ እንዲይዙ ካልተደረገ ማብቂያ ለሌለው ስርአት አልበኝነትና ትርምስ ይዳርጋል። የጀመዓን እንቅስቃሴ በግለሰቦች መስለሃ ላይ ከማንጠልጠል በመቆጥብ እና በጀመዓ የአንድነት እሴት ላይ አሉታዊ የሆኑ የግል አመለካከቶችን በመከላከል የሰለፍዬችን አንድነት ማጠናከር ይገባናል። بارك الله فيكم ✍አቡ ሙዓዝ

በሠለፊዮች አንድነት ላይ የሸይኽ ረቢዕ ምክር!! ——— የዘመናችን የጀርህና ተዕዲል ባንዲራ ተሸካሚው ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ዶ/ር ረቢዕ ቢን ሓዲ'ል መድኸሊይ (ረሂመሁላህ) ሠለፊዮች አንድነታቸውን አጥብቀው መጠበቅ እንደሚገባቸው ጠንከር አድርገው ሲናገሩ እንዲህ አሉ:- “…እኔ አንድን ያጠፋ (ስህተት የሰራን) ሰው እመክራለሁ!! ስህተት ላይ ለመሆኑ ጥርጥር የለውምኮ፣ ግን እያወቅኩ ተደጋጋሚ ጥረቶችን በማድረግ ህክምና እሰጠዋለሁ፣ የሚሳሳተው ያውቃል። የታመመ ሰው ዝም ካለ ሃኪም ቤት እናደርሰዋለን እንጂ በዚያው አባብሰን አንገድለውም! ባረከላሁ ፊኩም። ሀዳዲዮች ግን አንድ ሰው ላይ ትንሽ ቁስል ካገኙበት ያባብሱበታል… ማቆሚያም የለውም፣ ይልቁንም ሌላ ነገር ካሰቡበት አለያም ተሳስቷል ብለው ከቀጠፉበት ግዴታ መታመም አለበት። ይህ ኢስላማዊም ሆነ ሰለፊያዊ አለያም የሰው ልጆች መንገድ አይደለም!፣ ይልቁንም ይህ መንገድ የዱር እንስሳት አለያም የጫካ ህይወት አይነት መንገድ ነው። ይህን እጅግ በጣም በደለኛና ግፈኛ የሆነ ባህሪ ባለቤት ሰው እንጂ አይሰራውም!። ይህ ተቀባይነት የሌለው መንሀጅ (አካሄድ) ነው። ይህ ሠለፊዮችን በመቦጫጨቅና በመሰነጣጠቅ ላይ የሚጓዝ መንሀጅ ነው። ሠለፊዮችን በመሰነጣጠቅና በመበጣጠስ ላይ የሚጓዝ የሆነ መንሀጅ ሁሉ የቢድዐህ መንሀጅ ለመሆኑ ምልክት ከመሆኑም ጋር እንደ ፀሃይ ፍንትው ያለ ግልፅ ነው። ከሠለፎች መንሀጅ አጀንዳ አንዱ በሐቅ ላይ መሰብሰብ፣ ንግግርን አንድ ማድረግ ነው። ከቢድዐህ አጀንዳ ደግሞ አንዱ መበታተን ነው፣ በሐቅ ሳይሆን በባቢጢል ፀንቶና ገጥሞ የሚጓዝን መንሀጅ ካየህ ይህ የባጢል መንሀጅ ነው እንጂ የሐቅ መንሀጅ አይደለም!!።” ከድምፅ⤵️ የተተረጎመ https://t.me/IbnShifa/7121 = ከ10 አመታት በላይ የተማሩባቸውና በቅርበትም በተለየ መልኩ የተኗኗሯቸው ተማሪያቸው ሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን አስ-ሲልጢይ (ሀፈዘሁላህ) በዚህ በሸይኽ ረቢዕ ምክር ላይ የሚከተለውን ማስታወሻ እንዲህ በማለት አንጠልጥለዋል:- “አላህ ሰፊ የሆነን እዝነት ይዘንላቸው!!። በቅርበት እንዳወቅናቸው በሁሉም ቦታ የሰለፊዮችን ስንጥቅ ለመዝጋትና ንግግራቸውን አንድ ለማድረግ ምንኛ የበረታ ጉጉት ነው የነበራቸው?!። => ሠለፊይ ወንድሜ ሆይ! በሠለፊይ ወንድምህ ላይ በሆነች በ1 ወይም በ2 ወደ ቢድዐህ በማትደርስና ከሱንና በማታስወጣ ስህተት ሰበብ አትሹምበት!። በወንድምህ ላይ ታገስ! ምከረው!  አዛኝም ሁንለት!። ሳታውቅ በሀዳዲያ ወጥመድ ላይ እንዳትወድቅ ተጠንቀቅ!!። ለዚያም ነው በርካታ ሰለፎች… "በአህሉሱናዎች ላይ በመልካም ነገር አደራ ተባባሉ!፣ እነሱኮ ከሰዎች ሁሉ አናሳዎች ናቸው።" ይሉ የነበረው። በሠለፊይ ወንድምህ ላይ ካልታገስክ በማን ላይ ነው ምትታገሰው?!፣ በነቢያት ፋና (ነቢያትን ተምሳሌት) አድርገህ ተመራ! ምን ያምር መመራትና መከተል ነው!!። ✍🏻ትርጉም:- ኢብን ሽፋ #Join ⤵️⤵️ ቴሌግራም ቻናል https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa Follow Ibn Shifa's WhatsApp Channel: ⤵️⤵️ https://whatsapp.com/channel/0029VbAU7moHgZWXXXnNiL3f

رحمه الله رحمة واسعة ما أشد حرصه في رأب الصدع وجمع كلمة السلفيين في كل مكان كما عهدناه . فلا تتسلط يا أخي السلفي على أخيك السلفي بمجرد غلطة أو غلطتين التي لا تصل إلى حد البدعة والخروج من السنة فاصبر على أخيك وانصحه وتلطف به واحذر أن تقع في شباك الحدادية وأنت لا تشعر . ولهذا قال عدد من السلف " واستوصوا بأهل السنة خيرا وهم أقل الناس" وإن لم تصبر على أخيك السلفي فعلى من تصبر ؟ وما مقدار الصبر عندك ؟ واقتد بالأنبياء فنعم المقتفى والمقتدى.

አዲስ                 👉 ይደመጥ!! 🔷 ልዩ ተከታታይ ኮርስ ርእስ:- ሺዐቱ ሸይጧን!! በታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሰዒድ ረስላን (ሀፊዘሁላህ) የተዘጋጀ Pdf↘️↘️ https://t.me/IbnShifa/6377 ⏯ ክፍል 23 🎙በኡስታዝ አቡ ሙዓዝ - ታጁዲን (ሀፊዘሁላህ) ኮርሱ የሚሰጠው በ t.me/ibnshifa ቴሌግራም ቻናል ዘውትር እሮብና ሀሙስ ከምሽቱ:- 4:00 ጀምሮ ነው፣ በሰኣቱ ቀጥታ ተከታተሉ #Join ⤵️⤵️ ቴሌግራም ቻናል https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa Follow Ibn Shifa's WhatsApp Channel: ⤵️⤵️ https://whatsapp.com/channel/0029VbAU7moHgZWXXXnNiL3f

⛔️ከእሳት ሸሽተን በእሳት አንገባም عَنْ عَلِيٍّ قَالَ: بَعَثَ النَّبِيُّ ﷺ سَرِيَّةً فَاسْتَعْمَلَ رَجُلًا مِنَ الأَنْصَارِ، وَأَمَرَهُمْ أَنْ يُطِيعُوهُ، فَغَضِبَ فَقَالَ: أَلَيْسَ أَمَرَكُمُ النَّبِيُّ ﷺ أَنْ تُطِيعُونِي. قَالُوا: بَلَى. قَالَ: فَاجْمَعُوا لِي حَطَبًا. فَجَمَعُوا، فَقَالَ: أَوْقِدُوا نَارًا. فَأَوْقَدُوهَا، فَقَالَ ادْخُلُوهَا. فَهَمُّوا، وَجَعَلَ بَعْضُهُمْ يُمْسِكُ بَعْضًا، وَيَقُولُونَ: فَرَرْنَا إِلَى النَّبِيِّ ﷺ مِنَ النَّارِ. فَمَا زَالُوا حَتَّى خَمَدَتِ النَّارُ، فَسَكَنَ غَضبُهُ، فَبَلَغَ النَّبِيَّ ﷺ فَقَال: «لَوْ دَخَلُوهَا مَا خَرَجُوا مِنْهَا إِلَى يَوْمِ الْقِيَامَةِ، الطَّاعَةُ فِي الْمَعْرُوفِ». 📚 رواه البخاري (٤٣٤٠)  ومسلم ( ١٨٤٠) ➤ዐሊ ረዲየ አላሁ ዐንሁ ባወራው ሐዲስ ነቢዩ ﷺ  ከአንሳሮች የሆነን  አንድ ሶሃባ  አሚር አድርገው ሰራዊትን ላኩ አሚሩ የሚያዛችሁን ነገር ታዘዙት አሉ። አሚሩ በባልደረቦቹ ተቆጣ ነቢዩ ﷺ ታዘዙት አላሉዋችሁም አላቸው እነሱም አዎ ብለውናል አሉት በሉ እንጨት ሰብስቡልኝ አለቸው ሰበሰቡለትም እሳትን አቀጣጥሉበት አላቸው እነሱም እሺ በማለት እሳትን አቀጣጠሉ እሳቱ ውስጥ ግቡ አላቸው ለመግባትም አሉ(ሞከሩ) ከፊላቸውም  ከፊሉን በእሳት እንዳይገባ ያዙ እንዲህም አሉ ከእሳት እኮ ነው ወደ ነቢዩ ﷺ የሸሸነው በዚሁ ሁኔታ አልተወገዱም እሳቲቱ እስክትጠፋ ድረስ ያኔ የአሚሩም ቁጣ በረደ ።ክስተቱም ለነቢዩ ﷺ ደረሳቸው እንዲህም አሉ ቢገቡ ኖሩ የውመል ቂያመህ ድረስ አይወጧትም ነበር አሚርን መታዘዝ እኮ በመልካም ነገር ነው አሉ ። 📚ቡኻሪና ሙስሊም ከላይ በተጠቀሰው የሐዲስ ቁጥር ዘግበውታል ➽ከዚህ ሐዲስ የምንማረው ትምህርት ፦ _አሚሮችንና  ዑለሞችን መታዘዝ የሚቻለው በመልካም ነገር ብቻ መሆኑን _አብዛኛውን ግዜ ንዴት እነ ቁጣ የኢኽላስና ፍትሕ መጥፋት የበደልና የጥፋት ምክንያት መሆኑን _ተከታዮች አሚሮቻቸውን በወንጀል በመታዘዛቸው ዑዝር እንደሌላቸው _ጭፍን ተከታይነት የተወቀሰ እነ ቅጣትን የሚያስከትል መሆኑን _አንድ ዓሊም ወይም አሚር  የሚለው በመተው በተቃራኒው እሱ የተወውን በመልካም ማዘዝ በመጥፎ መከልከል ግዴታ መሆኑን። _ይህም ተግባር ዑቀላዎች ዘንድ  የሚያስመሰግን እንጂ የሚያስተች አይደለም በርግጥ ሙሪዶችን ልያንጫጫ ይችላል ። _የብዙ ሙሪዶች ገበና ግልጽ የሚሆነውም በእንደዚህ አይነት ክስተት ወቅት ነው። _የሱና ዑለሞችና ሱኒዮች ለየት ብለው የሚታወቁት በዚህ አይነት ክስተት በሚያሳዩት በማያወላውል አቋማቸው ነው ። _የትኛውም ዓሊም የሚሰጠው ፈታዋ ፣ ሰዎችን የሚተቸው ትችቱና የሚያስተላልፈው ትእዛዙ ከማስረጃ የተራቆተ ከሆነ የሱና ዑለሞችና ሱኒዮች ጋ ክብሩና ደረጃው እንደተጠበቀ ሆኖ የተሳሳተበት ነገር ቅንጣት ተቀባይነት አይኖረውም ። ➲ምክንያቱም ከእሳት ሸሽቶ በእሳት መግባት የለምና ! 📝ተጨማሪ  ትምህርቶችን   ለማግኘት የቴሌግራም➷➴ Channeሉን  ይቀላቀሉ !!! https://t.me/MisbahMohammed_6682

ምርጫው የእናንተ ነው የተመቻቹን ንኩት👇👇👇

مختصر الفوائد 03.mp321.52 MB

مختصر الفوائد 02.mp316.35 MB

+1
ልዩ የዐቂዳ ደርስ 📚 የሚቀራው ሪሳላ:- ለሸይኽ ዱክቱር አቡ ሙዓዝ ሀሰን ኢብን ዓሊ አልመርዳዊ አልዒራቂይ የሆነችው: "ከኢማሙ አሕመድ ኡሱሉ ሱንና የተውጣጡ አጫጭር ጠቃሚ ዐቂዳዊ ት/ቶችና መንሀጃዊ መርሆዎች" "مختصر الفوائد العقدية والقواعد المنهجية المستنبطة من أصول السنة للإمام أحمد" pdf للشيخ: أبو معاذ حسن بن علي المرداوي العراقي Pdf ⤵️⤵️ https://t.me/ibnbaz1212/353 ⏯ ክፍል 00 (መግቢያ) በዚህ ክፍል የተዳሰሱ ነጥቦች: —ስለሪሳላዋ  ትውውቅ —የኡሱሉ ሱና ይዘት ጥቅል ዳሰሳ —ሸይኽ አቡ ሙዓዝን በሚመለከት —የኢማሙ አህመድ አጭር ታሪክ... 🎙በኡስታዝ አቡ ሙዓዝ   📆ዕለተ ጁሙዓ ሰፈር 03, 1448          🕌 በመድረሰቱል ኢኽላስ ለሁልባረግ የሴቶች ጀመዓ የተሰጠ ኮርስ የቴሌግራም ቻነል https://t.me/ibnbaz1212

🔷የተረጋጋች ነፍስ ነፍስ በጌታዋ ከተረጋጋች ፣ እርሱን በማስታወስ ካረፈች ፣  ጸጸት አድርጋ ወደርሱ ከተመለሰች ፣ እርሱን ለመገናኘት ከናፈቀች ፣ ወደእርሱ በመቅረቧ ከተጽናናች ሰላም ትሆናለች። እንዲህ አይነቷ ነፍስ ስትሞት እንዲህ ትባላለች :- يَا أَيَّتُهَا النَّفْسُ الْمُطْمَئِنَّةُ ارْجِعِي إِلَىٰ رَبِّكِ رَاضِيَةً مَّرْضِيَّةً  "(ለአመነች ነፍስም) «አንቺ የረካሺው ነፍስ ሆይ! «ወዳጅ ተወዳጅ ኾነሽ ወደ ጌታሽ ተመለሺ፡፡" (ፈጅር :27-28) ኢብን አባስ እንዲህ ብለዋል :- "አንች የረካሽው ነፍስ ሆይ!" - "አማኝ የሆነች ነፍስ" ማለት ነው። ቀታዳ እንዲህ አለ :- "አንች የረካሽው ነፍስ ሆይ!" - "እርሷ አማኝ ሆና ፤ አላህ ቃል በገባው ነገር የረካች ነፍስ" ማለት ነው። ሐሰን እንዲህ አለ:- "አንች የረካሽው ነፍስ ሆይ!" - "አላህ በተናገረው የረካች ፣ እውነት ያለች ነፍስ" ማለት ነው። ሙጃሂድ እንዲህ አለ :- "አንች የረካሽው ነፍስ ሆይ!" -   "ጌታዋ አሏህ መሆኑን ያረጋገጠች ፣ ወደርሱ የተጸጸተች ፣ ለእርሱ የተዋደቀች ፣ እርሱን እንደምትገናኝ ያረጋገጠች ትሁት ነፍስ" ማለት ነው። طب القلوب  (ص/٨٠) https://t.me/alateriqilhaq كن على بصيرة

Share 'مختصر الفوائد العقدية والقواعد المنهجية المستنبطة من أصول السنة للإمام .pdf'

قال الله تعالى: يا أيها الذين آمنوا اتقوا الله وكونوا مع الصادقين قال ابن تيمية : "الصدقُ مُستَلزم للعدل والإحسان إلى الخلق، ومن جُمِعَ فيه الصدقُ والعَدلُ والإحسانُ؛ لم يَكن ممّن يُخزِيه الله!. [ينظر شرح العقيدة الأصبهانية: (٢/٦٦٦)]

🔷አህለሱናዎች ተዋደዱ ከሸይኽ ረቢዕ - ረሂመሁሏህ - መልዕክት "እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ ፣ ወንድማማች ሁኑ። በኢስላማዊ ስነ-ምግባርና ስርዓት ተከባበሩ። እርስ በርሳችሁ ምህረትና ርህራሄ አሳዩ። ምክንያቱም የፈጠራና የስህተት ባለቤቶች ፣ የተለያዩ የእምነት አንጃዎች  በሱና ሰዎች ላይ አንድ ሆነው እየተዋጉ ነው። ሀዳድያ የሱና ሰዎችን በመዋጋት የአንበሳውን ድርሻ ይዟል። ነገር ግን አሏህ ቀደም ሲል ጦራቸውን እንደሰበረው - ኢንሻአሏህ - አሁንም ይሰብራል በኋላም ይሰብራል።" المجموع ٤٤٣/٩ العلامة ربيع بن هادي عمير https://t.me/alateriqilhaq كن على بصيرة

‏صورة من حسين عبد الله
‏صورة من حسين عبد الله