የወራቤ ሰለፊዮች መገናኛ
Открыть в Telegram
📝👉በአላህ ፍቃድ በዚህ ቻነል በወራቤ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ መድረሳዎች የሚሰጡ የሰለፊዮች ደርስ ፣ሙሃደራ እንዲሁም መልእክቶች የሚተላለፉበት ይሆናል !!! https://t.me/ibnbaz1212
БольшеСтрана не указанаКатегория не указана
3 433
Подписчики
+4224 часа
+2007 дней
+35230 дней
Архив постов
3 437
Repost from አቡ ኑህ አስ'ስልጢይ [Abu Nuh Assiltiy ]
📖 በአዲስ መልክ ተዘጋጅቶ የተለቀቀ መፅሐፍ 📖
🟪
በመውሊድ ዙሪያ የሚነሱ 33 ብዥታዎች እና መልሶቻቸው🖋በአቡ ዐብዲልዐዚዝ/ ሸይኽ ዩሱፍ አሕመድ ሐፊዞሁሏህ የተዘጋጀ፤ 🔻መውሊድን ሐይማኖታዊ በዓል አድርገው ለማክበር የሚጠቅሷቸው ማስረጃዎች፤ 🔻ከቁርኣን፣ ከሀዲስ፣ ከሶሓቦች እና ከዑለሞች ንግግር የተውጣጡ መልሶች፤ 🔻ሁሉም ሰው ሊያውቃቸው የሚገቡ ብዥታዎች እና መልሶቻቸውን ያካተተ፤
❗️ስንት ሐቁን ያላገኘ መልካም አሳቢ አለ!!❗️ሼር በማድረግ የአጅሩ ተካፋይ እንሁን‼️ አላህ አንብበው ከሚጠቀሙት ያድርገን‼️ የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ 🔳 ▫️ 🔳 ▫️ 🔳 ▫️ 🔳 ▫️ 🔳 كن على بصيرة https://t.me/alateriqilhaq
3 437
☪ሰለፊይ የሆናቹ ብቻ OPEN በሉ☪
🇸🇦ሰለፊይ የሆናቹ ብቻ OPEN በሉ🇸🇦
☪ሰለፊይ የሆናቹ ብቻ OPEN በሉ☪
🇸🇦ሰለፊይ የሆናቹ ብቻ OPEN በሉ🇸🇦
☪ሰለፊይ የሆናቹ ብቻ OPEN በሉ☪
🇸🇦ሰለፊይ የሆናቹ ብቻ OPEN በሉ🇸🇦
☪ሰለፊይ የሆናቹ ብቻ OPEN በሉ☪
🇸🇦ሰለፊይ የሆናቹ ብቻ OPEN በሉ🇸🇦
☪ሰለፊይ የሆናቹ ብቻ OPEN በሉ☪
🇸🇦ሰለፊይ የሆናቹ ብቻ OPEN በሉ🇸🇦
☪ሰለፊይ የሆናቹ ብቻ OPEN በሉ☪
🇸🇦ሰለፊይ የሆናቹ ብቻ OPEN በሉ🇸🇦
🇸🇦🇸🇦🇸🇦🇸🇦🇸🇦🇸🇦🇸🇦🇸🇦🇸🇦🇸🇦🇸🇦
🇸🇦 O P E N 🇸🇦
🇸🇦🇸🇦🇸🇦🇸🇦🇸🇦🇸🇦🇸🇦🇸🇦🇸🇦🇸🇦🇸🇦
3 437
Repost from አቡ ኑህ አስ'ስልጢይ [Abu Nuh Assiltiy ]
አዲስ ሙሐደራ ቁ. 330
🚫 بيان مفاسد وشرور وبدع ما يسمى (إدر) من أكثر من ثلاثين وجها والرد على القائلين أنه من العادات
⛔️ በእድር ያለውን ሸር፣ብልሽትና ቢድዐህ ከ30 በላይ በሆነ አቅጣጫ ግልፅ ማድረግና "ከባህል ነው እንጂ ቢድዐህ አይደለም" በሚሉ ሰዎች ላይም ምላሽ ተሰጥቷል።
📍በአዲስ አበባ በዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል የተደረገ ሙሐደራ።
📝 በዚህ ሙሓዶራ ከተዳሰሱ ወሳኝና ቁልፍ ነጥቦች መካከል እነሆ በጥቂቱ፡
—እድር የሚለው ትርጓሜ...
— እድር እና እስልምና ይተዋዋቃሉን?
እድር አስፈላጊ ቢሆን ኖሮ ለመልእክተኛው (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ባስፈለጋቸው ነበር...
— መደጋገፍ፣መቀባበር... እንዳለብን ኢስላም አዟል..
— ኢስላም ቡድንተኝነትን አጥብቆ ያወግዛል..
— እነዚያ ሃይማኖታቸውን የለያዩ አሕዛብም የኾኑ በምንም ከእነሱ አይደለህም፡፡ ነገራቸው ወደ አላህ ብቻ ነው፡፡ ከዚያም ይሠሩት የነበሩትን ሁሉ ይነገራቸዋል፡፡ (የሚለው የቁርኣን አንቀጽ ማብራሪያ)
— እድር የመልእከተኛው (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ፣የሶሃቦች፣የታቢዒዮች፣የአትባዑ ታቢዒንም መንገድ አይደለም...
— ጥቁት ስለ ወንድማማችነት...
— ሰዎች አላህን ካልፈሩ እንዲሁም ስሜታቸውን ከተከተሉ ለሐቅ እጅ አይሰጡም...
— እድር ውስጥ ኢስላምን የሚያፈርሱ፣ ሱናን የሚገረስሱ ብዙ ፀያፍ ተግባራት እየተሰሩ ባህል ነው እየተባለ ሽፋን ሚሰጥበት ሁኔታ አለ...
— እድርን አይደለም ሙስሊሞች ከሙስሊም ውጭም ያሉ ሰዎች እየተቃወሙት (እያወገዙት ይገኛሉ)...እንዲሁም እድር የፈሪዎች ስብስብ ነው ይላሉ... (የድምፅ ቅጂውም ይገኛል ያድምጡት)
— ከሃይማኖት አላህ በእርሱ ያልፈቀደውን ለእነርሱ የደነገጉ ተጋሪዎች ለእነርሱ አልሏቸውን? የፍርዱ ቃል ባልነበረ ኖሮ በመካከላቸው (አሁን) በተፈረደ ነበር፡፡ በደለኞችም ለእነርሱ አሳማሚ ቅጣት በእርግጥ አልላቸው፡፡ «ይህም ቀጥተኛ ሲኾን መንገዴ ነው፤ ተከተሉትም፡፡ (የጥመት) መንገዶችንም አትከተሉ፡፡ ከ(ቀጥተኛው) መንገዱ እናንተን ይለያዩዋችኋልና፡፡እነሆ ትጠነቀቁ ዘንድ በርሱ አዘዛችሁ፡፡»
● ሙስሊም በሙስሊም ላይ ያለው ሐቆች:
[1]- ጀናዛን መከተል—ማብራሪያውን ገብተው ያድምጡ...
[2]- ሰላምታን መመለስ...
[3]- ያስነጠሰ ሰው—አልሃምዱሊላህ ካለ ምላሽ መስጠት...
[4]-የታመመን መጠየቅ...
● ለለቅሶ ተብሎ መሰብሰብ:
— የእደር መሰረቱ ከነሳራዎች የመጣ ስለመሆኑ...
— የአላህ መልእክተኛ (ሶላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በሰዎች የተመሳሰለ ከነሱ ነው ስለ ማለታቸው...
— የአይሁድና የናሷራዎች መንገድ...
● የጃሃሊያ መታወቂያዎች:
— በዘር መኮፈስ፣
— ዘርን መተቸት፣
— በከዋክብት ዝናብን መፈለግ
— በለቅሶ መጮህ (ማስለቀስ)
— እያንዳንዱ እድር ውስጥ አስለቃሽ አለ፣
— የአስለቃሽ አስከፊ ቅጣት፣
— እድር በሸሪዓችን የለም፣
— ማንኛውም ሁክም በሸሪዓ ከሌለ ውድቅ ስለመሆኑ...
— ለሶስት ቀን ለቅሶ ተብሎ ስለሚባለው...
— ጃቢር ቢን ዐብዲላህ (ረዲየላሁ ዐንሁ)
መሳባሰብን፣ምግብንም ማዘጋጀት ከለቅሶ እንቆጥረው ነበር ስለማለቱ...
— በእድር ውስጥ የሺርክ መንዙማ ይባላል...
ማብራሪያውን ገብተው ያድምጡ...
📝 ከ30 በላይ በሸሪዓችን የሚጋጩ የእድር (የሴራ) ህግና ደምቦች:
1. የእድር መሠረቱ ከካፊሮች የመጣ ስለመሆኑ...
2. እድር በሸሪዓ የለም...
3. ከሽርክ መንዙማዎች መካከል ለምሳሌ...
4. በእድር ውስጥ የየቲም ገንዘብ ይበላል፣
5. ጫት ይቃማል የጫት አቅራቢ ይደረጋል...
6. ሴትና ወንድ ይቀላቀላሉ ከአስለቃሽ ጋር...
7. የእድር ብር ባንክ ይቀመጣል። ወለድም አለው፣ የወለደው ገዘብ ደግሞ ይበላል...
8. ለቅሶ ላይ አስለቃሽ አለ...
9. መሬት "ወለድ-አገድ" ተብሎ ይያዛል...
10 በቀብር ላይ ያሲን ይቀራል...
11. የፈረስ ግልቢያ...
12. ለቅሶ በአሁን ጊዜ በገጠር በከተማው 12፣7፣3...ቀን ተብሎ ይያዛል...
13. የእድር ህግ ላይ የማይሰገድ የሚሰገድም ሰው፣ የመቅበር ግዴታ አለበት...
14. መስጂድ ውስጥ ጫት ይቃማል...
15. በእድር የሌለ ሰው አይቀበረም
16. በየ ሶላት ሰኣት ቡና ከነጫት ግዴታ ነው...
17. አንድ ሰውም 10 ሰው ያለበት ቤት ኡኩል ብር ያዋጣል...
18. ለቅሶ ያልመጣ ይቀጣል...
19. ጉዳይ ገጥሞት ባይመጣ ይከፍላል (ይቀጣል)
20. ሟች ከመሞቱ በበፊት ለቅሶ ሊያዝበት የሚያሳድገው እንጨት አለ... ወይም ከሰው ይመጣል
21. ጡሩምባ ይነፋል...
22. በመጨረሻ ቁርኣን ይቀራል...
23. መዝገብ ተይዞ መመገብና ገንዘብ.. መቀበል እንዲሁም ያልመጣን ሰው፣ ጠላት አድርጎ መቅጣት...
24. አሳድሮ ማልቀስ ....
25. በመጨረሻ ቤት ማጠብ ...
26. የሟች ዘመድ ወደቤቱ ሲመለስ በአዲስ መልኩ ለቅሶ መያዝ...
27. አንዳንድ የአገርቤት ሸይኾች ለቅሶ ቤት ምግብ አይበሉም...
28. ለቅሶ ለመጣ ሰው በጉሩፕ (በቡድን) ፋቲያ ይቀራል ...
29. ለቅሶ ካለቀ በኃላ ቤት ይፀዳል...
30. ለቅሶ ላይ አንደ አይነት ልብስ ይለብሳል (ጋቢ)...
31 በቀብር ላይ ቴምር መብላት....
32. በለቅሶ ያለ መህረም ጉዞ አለበት...
#ማሳሰቢያ፦ ይህ ድምፅ እጅግ በጣም ወሳኝና አንገብጋቢ ስለሆነ ለወዳጅ፣ ዘመዶዎ፣በማጋራት የአጅሩ ተቋዳሽ ይሁኑ ባረከላሁ ፊኩም!!!!!!
https://t.me/shakirsultan/2487
3 437
Repost from قناة الشيخ الدكتور حسين بن محمد
جزاك الله خيرا وبارك فيك وزادك من فضله قد استمعت إلى هذه المحاضرة فألفيتها نافعة طيبة مستوفية وطافحة بأدلة من الكتاب والسنة وفيها وقائع وحقائق واضحة جلية عن هذه البدعة القبيحة المنتشرة في بلاد الحبشة. وقد طلب مني بعض الإخوة الكتابة حول ما يسمى (إدر) فهذه الصوتية شافية كافية فريدة في بابها ولا تحتاج إلى مزيد بسط وإيضاح وتعليق لأن الأستاذ الفاضل قد أعطى الموضوع حقه واستوعب فيه كل ما يحتاج إليه بسؤال المتخصصين والقائمين على هذه البدعة التي هي من بؤر الشرك والقبائح والجاهلية . لو قام بعض مترجمي أهل السنة بتفريغها ثم مراجعتها وتنسيقها وتنقيحها لكان في ذلك نفع عظيم وخير كثير بإذن الله تعالى .
3 437
Repost from Shakir Sultan (Channel)
🔶#በእድር ያለውን ሸር፣ብልሽትና ቢድዐህ ከ30 በላይ በሆነ አቅጣጫ ግልፅ ማድረግና "ባህል ነው እንጂ ቢድዐህ አይደለም" ብሎ በሞገተ ሰው ላይም ምላሽ ተሰጥቷል
🔶 በአዲስ አበባ በዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል የተደረገ ሙሐደራ።
🎙በኡስታዝ ሻኪር ቢን ሱልጣን (ሀፊዘውላህ)
📌 ትምህርቱን ለመከታተል ይህን ቻናል ይቀላቀሉ
👇👇👇
🌐 https://t.me/shakirsultan
3 437
Repost from አቡ ኑህ አስ'ስልጢይ [Abu Nuh Assiltiy ]
🚫ትንሽም ቢሆን ንግግሩ ቅድሚያ ሊሰጠውና ሊከበር ይገባዋል ❕
🎙قال إبراهيم الحربي: «الصَّغِيرَ إِذَا أَخَذَ بِقَوْلِ رَسُولِ اللهِ ﷺ وَالصَّحَابَةِ وَالتَّابِعِينَ فَهُوَ كَبِيرٌ
📚شرح أصول اعتقاد أهل السنة للالكائي، دار طيبة، السعودية، الطبعة الثامنة، 1423هـ، ج1، ص95
➽ኢብራሂም አል'ሐርቢ እንዲህ ብለዋል፡- "አንድ ሰው በዕድሜው ትንሽ ቢሆንም የመልእክተኛን ﷺ ፣ የሶሐባዎችን እና የታቢዖችንን ንግግር አጥብቆ ከያዘ እርሱ ታላቅ ነው"
📚ሸርሑ ኡሱሊ ኢዕቲቃዲ አህሊ አስ'ሱና ሊል'ላላካኢ፣ ዳር አጥ'ጦይባህ ማተሚያ ቤት፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ 8ኛ እትም፣ 1423 ዓ.ሂ.፣ ጥራዝ 1፣ ገጽ 95።
🎙قال السجزي: «فَالْمُتَّبَعُ لِلْأَثَرِ يَجِبُ تَقْدِيمُهُ وَإِكْرَامُهُ، وَإِنْ كَانَ صَغِيرَ السِّنِّ غَيْرَ نَسِيبٍ
📚 رسالة السجزي إلى أهل زبيد، عمادة البحث العلمي، المدينة المنورة، الطبعة الثانية، 1423هـ، ج1، ص340
➲አስ'ሲጅዚይ እንዲህ ብለዋል፡- "የሐዲሥንና የአሰር መንገድ የተከተለ አካል ዕድሜው ትንሽ እነ ዝነኛ ባይሆንም እንኳን እሱን ማስቀደም እነ ማክበር ግዴታ ይሆናል"።
📚ሪሳላቱ አስ'ሲጅዚይ ኢላ
ዙበይድ፣ መዲናቱ አል'ሙነወረህ የምርምር ማዕከል 2ኛ እትም፣ 1423 ዓ.ሂ.፣ ጥራዝ 1፣ ገጽ 340።
📝ተጨማሪ ትምህርቶችን ለማግኘት የቴሌግራም➷➴ Channeሉን ይቀላቀሉ !!!
https://t.me/MisbahMohammed_6682
3 437
Repost from قناة الشيخ الدكتور حسين بن محمد
مسألة_رفع_اليدين_في_تكبيرات_الجنازة_260809_222824.pdf0.35 KB
3 437
ታላቅ የሙሃዶራ ዝግጅት በ online በጉራጌ ዞን በእኖር ወረዳ በእንቡሻር መንደር መስጂድ የገቢ ማሰባሰቢያ ጉሩፕ ↘️↘️
https://t.me/+OeGJDGkF--FhOGRk
🗓 ቀን:- የፊታችን ሰኞ 04/12/2018
ከምሽቱ 3:00 ሰኣት ጀምሮ
🪑በአሏህ ፈቃድ የእለቱ ተጋባዠ እንግዶቻችን፦
🎙1️⃣ ኡስታዝ አቡ ሙዓዝ - ታጁዲን (ሀፊዘሁሏህ)
🎙2️⃣ ኡስታዝ ሙሀመድ ሰልማን (ሀፊዘሁሏህ)
በጉራጌ ዞን በእኖር ወረዳ በእንቡሻር መንደር መስጂድ የገቢ ማሰባበሰቢያ የቴሌግራም ግሩፕ ላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰአት ጎራ በማለት ይሳተፉ ሌሎችንም ያሳትፉ
በጉራጌ ዞን በእኖር ወረዳ እንቡሻር መንደር መስጂድ የሂሳብ አካውንት
CBE 1000774749962
BOA 261020238
ኡመር አሊ&ሣሊህ ኩመል&አብድል ጀሊል አብድልሽኩር
🌐 👉ሼር 👉 ሼር 👍አድ👍 አድ በማድረግ ሀላፊነታችን እንወጣ ለአኼራችን አሻራ እናሳርፍ !!
👇👇↘️↘️
https://t.me/+OeGJDGkF--FhOGRk
3 437
"ባሌን ሌሎች ሴቶች ሲያዩት ዝንጀሮ ያስመስለው"
አንድ ሴት ባሏን የግሏ ብቻ ለማድረግ ስትል ባሌን ሌሎች ሴቶች ሲያዩት ዝንጀሮ ያስመስለው ብላለች ይባላል።እናም እቺ ሴት ያስጨነቃት ባሏ የእርሷ ብቻ መሆኑ እንጂ የባሏ ገፅታ ሰዎች ዘንድ መበላሸቱ አላሳሰባትም።ልክ እንደዚሁም አንዳንድ ወንድሞች አላህ ይቅር ይበላቸውና ከደዓዋው መስለሃ ይልቅ የግል መስለሃቸውን ለማስጠበቅ በወንድሞቻቸው ላይ በደልን ይፈፅማሉ።ይህን ፁሁፌን እንድፅፍ ያነሳሳኝ የሚከተለው ክስተት ነው።
ሀምሌ 29/2018 ከዓሱር ሰላት በኃላ አንድ ስልክ ከአንድ ወንድሜና የቀድሞ ተማሪዬ በኩል ተደወለልኝ።ሰላምታ ከተለዋወጥን በኃላ በመቀጠል እርሱ በሚገኝበት ጀመዓ የደዓዋና የኮርስ ፕሮግራም ለማስኬድ የጋበዟቸው የሱና መሻኢኾችና ኡስታዞች እንደነበሩ ብሎም ማስታወቂያ ጭምር ሰርተው አሰራጭተው እንደነበረ ነገር ግን አንድ ሰው እኔም የማውቀው ወንድሜም የሚያውቀው ወንድም ደውሎለት እገሌ የሚባለው ኡስታዝ ችግር ስላለበት ለምን ጋበዛችሁት ብሎ እንደተቃወመና የተለያዩ ምክንያት የሚላቸውን የትችት ነጥቦችን በመጥቀስ እንዳስጠነቀቀና በዚህ ምክንያት በዚህ ወንድም ማስጠንቀቂያ መሰረት በቦታው ያሉ ወንድሞች ለግዜው በነገሩ በመወዛገብ ፊትና ለመቀነስ በሚል ተወያይተው ያኛውን የሱና ተጋባዥ ኡስታዝ ከፕሮግራሙ እንዲሰረዝ በማድረግ ማስታወቂያውን በአዲስ መልክ ለመቀየር እንደተገደዱ ነግሮኝ ከፕሮግራሙ ስለተወገደው ተጋባዥ ኡስታዝ እውነታ የምታውቀው ነገር አለ ብሎ ጠየቀኝ።እኔም ጉዳዩን ወደ መሻኢኾች በማስጠጋት መረጃ ከእነርሱ እንዲወስድ ከአንዳንድ መንደርደሪያ ምክረሃሰቦች ጋር አቀጣጫ ሰጠውት።
በጣም የተደነቁት ከዛም አልፎ ያስደነገጠኝ ነገር ቢኖር ደውሎ አስጠንቃቂውም ማስጠንቀቂያ የተደረገበትም ኡስታዝ የሱና ሰዎች ከመሆናቸውም ጋር በውስጥ መስመር በዚህ ልክ የማስጠንቀቅ እርምጃው ነበር።በእርግጥም ይህ አይነት የሰለፍዬችን አንድነት የሚንድ አካሄዶች ከጀመሩ ሰንበትበት ያለና በተደጋጋሚ በየቦታው እየተበራከተ ያለ እውነታ ነው።እገሌን በዚህ ቻናል ላይ አትጋብዙት፣ እገሌን ከጋበዛችሁት እኛ አንሳተፍም፣ ለእገሌ መድረክ እንዳትሰጡት እና የመሳሰሉ ግፈኛ ፍርዶች ከተለያየ አቅጣጫ ይሰማሉ ናቅ ተደርገው ታልፈው እንጂ።
ውድ ሰለፍይ ወንድምና እህቶች! ሰለፍያ በዚህ ብልሹ አካሄድ እንደማትረዳና ይልቁንም ሰለፍዬችን ወደ ተወገዘው ግሩብተኝነት የሚያደርስ ስለሆነ ከዚህ ተግባር መቆጠብና ከፊላችን ከፊላችንን በዚህ አካሄድ ላይ አላህን ፍራ በማለት ልንተራረም ይገባል። ይህን ዓይነት አካሄድ በግዜ የማንቀርፍ ከሆነ ከባድ ጥፋትን በሰለፍዬች አንድነት ላይ ስለሚያስከትል ከዚህ ብልሹ አካሄድ እንቆጠብ ባይነኝ።
ጥፋቶች ካሉም የሸሪዓን ጥቅምና ጉዳት ሚዛንን በጠበቀ መልኩ ወደ ባለቤቶቹ (መሻኢኾች) በመመለስ እንዲታረም ማደረግ አማራጭ የሌለው ሸሪዓዊ መርሆ ነው።ሁሉም እየተነሳ ግልፅ ባልሆነ ምክንያትና ድብቅ በሆነ የአደረጃጀት መዋቅር በንፁሃን ወንድሞች ላይ ግፈኛ ፍርድ የሚሰጥ ከሆነ በመጀመሪያ ደረጃ ተጎጂው ባለቤቱ ሲሆን በመቀጠልም የደዓዋውን ጤነኛ ተደራሽነት በማሰናከል ከባድ የሆነ ትርምስና ስርአትአልበኝነትን ያስከትላል።
ሰለፍዬች በጥፋት ቡድን ከየቦታው እየታመሱ ባሉበት በዚህ ወቅት ውስጣዊ የሰለፍዬችን የአንድነት እሴታቸውን የሚንድ የጥፋት አካሄድ ማራመድ ከሸሪዓም ከዓቅልም ብሎም ከሞራልም አንፃር የተወገዘ ነው።
የሸሪዓችን መርሆ የሚያዘውም አንድ ሙስሊም ሌላን ሙስሊም እንዳይበድለው ብቻ ሳይሆን ወንድሙም ተበድሎ ያገኘው ግዜ አቅሙ በቻለው ልክ ከጎኑ ሊቆምና ሃቁን ሊያስመልስለትና በተቃራኒው ደግሞ በዳዩን መታገል ነው። ይህንም በሚመለከት ታላቁ ነብይ صلى الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋል:
"المُسلِمُ أخو المُسلِمِ لا يَظلِمُه ولا يُسلِمُه"
(أخرجه البخاري)
"አንድ ሙስሊም የሌላኛው ሙስሊም ወንድም ነው።አይበድለውምም፣ (ተበድሎም ሲያገኘው የማይረዳው ሳይሆን) አሳልፎ (ለበዳይ) አይሰጠውም።" ይህ ሀዲስ የሚጠቁመን በምንም መልኩ አንድ ሙስሊም ሌላኛውን ሙስሊም እንደማይበድለውና ሌሎች አካላትም ወንድሙን ሲበድሉት አይቶ እንዳላየ፣ ሰምቶ እንዳልሰማ ሆኖ የሚተወው እንዳልሆነ ነው።
ዛሬ አላህ ያዘነላቸው ሲቀሩ ብዙዎቻችን ከተበደሉት ጎን ልንቆም ቀርቶ በዳይን በማገዝ ላይ በበደል ላይ በደልን እንጨምራለን።በደል አይደለም ሰለፍይ ወንድምህን ይቅርና እንስሳትን መበደልም ቢሆን ነገ ዕለተቂያማ የከፋ ውጤት ያስከትላል።ነብያችን صلى الله عليه وسلم እንደተናገሩት:—
(اتَّقُوا الظُّلمَ ؛ فإنَّ الظُّلمَ ظُلُماتٌ يومَ القيامةِ) (أخرجه مسلم)
"በደልን ተጠንቀቁ፣ በደል ነገ ዕለተ ቂያማ (ድቅድቅ) ጨለማዎች ነውና።"
ውድ ሰለፍይ ወንድም እህቶች ዲን በስሜት፣ በእልክ ብሎም ግፈኛ በሆነች የሴራና የተንኮል አደረጃጀት አይረዳም ይልቁንም ዲን የሚረዳው በማስረጃ፣ በፍትህ፣ አላህን በመፍራትና የአላህን ተጠባባቂነት ብሎም ከመላእክቱም ተጠባባቂዎች እንዳሉብን በማወቅ በምናደርጋቸው እንቅስቃሴ መሆኑን በመገንዘብ አላስፈላጊ ከሆነ የፊትና፣የጥላቻ፣ የቂመኝነትና የእልክ አካሄዶች አላህን በመፍራት ልንቆጠብና አጥፊዎችንም ተው ልንላቸው ይገባል።ነገራቶች ስርአታቸውን በዚህ መልክ በግዜ እንዲይዙ ካልተደረገ ማብቂያ ለሌለው ስርአት አልበኝነትና ትርምስ ይዳርጋል።
የጀመዓን እንቅስቃሴ በግለሰቦች መስለሃ ላይ ከማንጠልጠል በመቆጥብ እና በጀመዓ የአንድነት እሴት ላይ አሉታዊ የሆኑ የግል አመለካከቶችን በመከላከል የሰለፍዬችን አንድነት ማጠናከር ይገባናል።
بارك الله فيكم
✍አቡ ሙዓዝ
3 437
Repost from ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa
በሠለፊዮች አንድነት ላይ የሸይኽ ረቢዕ ምክር!!
———
የዘመናችን የጀርህና ተዕዲል ባንዲራ ተሸካሚው ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ዶ/ር ረቢዕ ቢን ሓዲ'ል መድኸሊይ (ረሂመሁላህ) ሠለፊዮች አንድነታቸውን አጥብቀው መጠበቅ እንደሚገባቸው ጠንከር አድርገው ሲናገሩ እንዲህ አሉ:-
“…እኔ አንድን ያጠፋ (ስህተት የሰራን) ሰው እመክራለሁ!! ስህተት ላይ ለመሆኑ ጥርጥር የለውምኮ፣ ግን እያወቅኩ ተደጋጋሚ ጥረቶችን በማድረግ ህክምና እሰጠዋለሁ፣ የሚሳሳተው ያውቃል። የታመመ ሰው ዝም ካለ ሃኪም ቤት እናደርሰዋለን እንጂ በዚያው አባብሰን አንገድለውም! ባረከላሁ ፊኩም። ሀዳዲዮች ግን አንድ ሰው ላይ ትንሽ ቁስል ካገኙበት ያባብሱበታል… ማቆሚያም የለውም፣ ይልቁንም ሌላ ነገር ካሰቡበት አለያም ተሳስቷል ብለው ከቀጠፉበት ግዴታ መታመም አለበት። ይህ ኢስላማዊም ሆነ ሰለፊያዊ አለያም የሰው ልጆች መንገድ አይደለም!፣ ይልቁንም ይህ መንገድ የዱር እንስሳት አለያም የጫካ ህይወት አይነት መንገድ ነው። ይህን እጅግ በጣም በደለኛና ግፈኛ የሆነ ባህሪ ባለቤት ሰው እንጂ አይሰራውም!። ይህ ተቀባይነት የሌለው መንሀጅ (አካሄድ) ነው። ይህ ሠለፊዮችን በመቦጫጨቅና በመሰነጣጠቅ ላይ የሚጓዝ መንሀጅ ነው። ሠለፊዮችን በመሰነጣጠቅና በመበጣጠስ ላይ የሚጓዝ የሆነ መንሀጅ ሁሉ የቢድዐህ መንሀጅ ለመሆኑ ምልክት ከመሆኑም ጋር እንደ ፀሃይ ፍንትው ያለ ግልፅ ነው። ከሠለፎች መንሀጅ አጀንዳ አንዱ በሐቅ ላይ መሰብሰብ፣ ንግግርን አንድ ማድረግ ነው። ከቢድዐህ አጀንዳ ደግሞ አንዱ መበታተን ነው፣ በሐቅ ሳይሆን በባቢጢል ፀንቶና ገጥሞ የሚጓዝን መንሀጅ ካየህ ይህ የባጢል መንሀጅ ነው እንጂ የሐቅ መንሀጅ አይደለም!!።” ከድምፅ⤵️ የተተረጎመ
https://t.me/IbnShifa/7121
= ከ10 አመታት በላይ የተማሩባቸውና በቅርበትም በተለየ መልኩ የተኗኗሯቸው ተማሪያቸው ሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን አስ-ሲልጢይ (ሀፈዘሁላህ) በዚህ በሸይኽ ረቢዕ ምክር ላይ የሚከተለውን ማስታወሻ እንዲህ በማለት አንጠልጥለዋል:-
“አላህ ሰፊ የሆነን እዝነት ይዘንላቸው!!። በቅርበት እንዳወቅናቸው በሁሉም ቦታ የሰለፊዮችን ስንጥቅ ለመዝጋትና ንግግራቸውን አንድ ለማድረግ ምንኛ የበረታ ጉጉት ነው የነበራቸው?!።
=> ሠለፊይ ወንድሜ ሆይ! በሠለፊይ ወንድምህ ላይ በሆነች በ1 ወይም በ2 ወደ ቢድዐህ በማትደርስና ከሱንና በማታስወጣ ስህተት ሰበብ አትሹምበት!። በወንድምህ ላይ ታገስ! ምከረው! አዛኝም ሁንለት!። ሳታውቅ በሀዳዲያ ወጥመድ ላይ እንዳትወድቅ ተጠንቀቅ!!። ለዚያም ነው በርካታ ሰለፎች… "በአህሉሱናዎች ላይ በመልካም ነገር አደራ ተባባሉ!፣ እነሱኮ ከሰዎች ሁሉ አናሳዎች ናቸው።" ይሉ የነበረው። በሠለፊይ ወንድምህ ላይ ካልታገስክ በማን ላይ ነው ምትታገሰው?!፣ በነቢያት ፋና (ነቢያትን ተምሳሌት) አድርገህ ተመራ! ምን ያምር መመራትና መከተል ነው!!።
✍🏻ትርጉም:- ኢብን ሽፋ
#Join ⤵️⤵️ ቴሌግራም ቻናል
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa
Follow Ibn Shifa's WhatsApp Channel: ⤵️⤵️ https://whatsapp.com/channel/0029VbAU7moHgZWXXXnNiL3f
3 437
Repost from قناة الشيخ الدكتور حسين بن محمد
رحمه الله رحمة واسعة ما أشد حرصه في رأب الصدع وجمع كلمة السلفيين في كل مكان كما عهدناه . فلا تتسلط يا أخي السلفي على أخيك السلفي بمجرد غلطة أو غلطتين التي لا تصل إلى حد البدعة والخروج من السنة فاصبر على أخيك وانصحه وتلطف به واحذر أن تقع في شباك الحدادية وأنت لا تشعر . ولهذا قال عدد من السلف " واستوصوا بأهل السنة خيرا وهم أقل الناس" وإن لم تصبر على أخيك السلفي فعلى من تصبر ؟ وما مقدار الصبر عندك ؟ واقتد بالأنبياء فنعم المقتفى والمقتدى.
3 437
Repost from ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa
አዲስ 👉 ይደመጥ!!
🔷 ልዩ ተከታታይ ኮርስ
ርእስ:- ሺዐቱ ሸይጧን!!
በታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሰዒድ ረስላን (ሀፊዘሁላህ) የተዘጋጀ
Pdf↘️↘️
https://t.me/IbnShifa/6377
⏯ ክፍል 23
🎙በኡስታዝ አቡ ሙዓዝ - ታጁዲን (ሀፊዘሁላህ)
ኮርሱ የሚሰጠው በ t.me/ibnshifa ቴሌግራም ቻናል ዘውትር እሮብና ሀሙስ ከምሽቱ:- 4:00 ጀምሮ ነው፣ በሰኣቱ ቀጥታ ተከታተሉ
#Join ⤵️⤵️ ቴሌግራም ቻናል
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa
Follow Ibn Shifa's WhatsApp Channel: ⤵️⤵️ https://whatsapp.com/channel/0029VbAU7moHgZWXXXnNiL3f
3 437
Repost from አቡ ኑህ አስ'ስልጢይ [Abu Nuh Assiltiy ]
⛔️ከእሳት ሸሽተን በእሳት አንገባም
عَنْ عَلِيٍّ قَالَ: بَعَثَ النَّبِيُّ ﷺ سَرِيَّةً فَاسْتَعْمَلَ رَجُلًا مِنَ الأَنْصَارِ، وَأَمَرَهُمْ أَنْ يُطِيعُوهُ، فَغَضِبَ فَقَالَ: أَلَيْسَ أَمَرَكُمُ النَّبِيُّ ﷺ أَنْ تُطِيعُونِي. قَالُوا: بَلَى. قَالَ: فَاجْمَعُوا لِي حَطَبًا. فَجَمَعُوا، فَقَالَ: أَوْقِدُوا نَارًا. فَأَوْقَدُوهَا، فَقَالَ ادْخُلُوهَا. فَهَمُّوا، وَجَعَلَ بَعْضُهُمْ يُمْسِكُ بَعْضًا، وَيَقُولُونَ: فَرَرْنَا إِلَى النَّبِيِّ ﷺ مِنَ النَّارِ. فَمَا زَالُوا حَتَّى خَمَدَتِ النَّارُ، فَسَكَنَ غَضبُهُ، فَبَلَغَ النَّبِيَّ ﷺ فَقَال: «لَوْ دَخَلُوهَا مَا خَرَجُوا مِنْهَا إِلَى يَوْمِ الْقِيَامَةِ، الطَّاعَةُ فِي الْمَعْرُوفِ».
📚 رواه البخاري (٤٣٤٠)
ومسلم ( ١٨٤٠)
➤ዐሊ ረዲየ አላሁ ዐንሁ ባወራው ሐዲስ ነቢዩ ﷺ ከአንሳሮች የሆነን አንድ ሶሃባ አሚር አድርገው ሰራዊትን ላኩ አሚሩ የሚያዛችሁን ነገር ታዘዙት አሉ።
አሚሩ በባልደረቦቹ ተቆጣ ነቢዩ ﷺ ታዘዙት አላሉዋችሁም አላቸው እነሱም አዎ ብለውናል አሉት በሉ እንጨት ሰብስቡልኝ አለቸው ሰበሰቡለትም እሳትን አቀጣጥሉበት አላቸው እነሱም እሺ በማለት እሳትን አቀጣጠሉ እሳቱ ውስጥ ግቡ አላቸው ለመግባትም አሉ(ሞከሩ) ከፊላቸውም ከፊሉን በእሳት እንዳይገባ ያዙ እንዲህም አሉ ከእሳት እኮ ነው ወደ ነቢዩ ﷺ የሸሸነው
በዚሁ ሁኔታ አልተወገዱም እሳቲቱ እስክትጠፋ ድረስ ያኔ የአሚሩም ቁጣ በረደ ።ክስተቱም ለነቢዩ ﷺ ደረሳቸው እንዲህም አሉ ቢገቡ ኖሩ የውመል ቂያመህ ድረስ አይወጧትም ነበር አሚርን መታዘዝ እኮ በመልካም ነገር ነው አሉ ።
📚ቡኻሪና ሙስሊም ከላይ በተጠቀሰው የሐዲስ ቁጥር ዘግበውታል
➽ከዚህ ሐዲስ የምንማረው ትምህርት ፦
_አሚሮችንና ዑለሞችን መታዘዝ የሚቻለው በመልካም ነገር ብቻ መሆኑን
_አብዛኛውን ግዜ ንዴት እነ ቁጣ የኢኽላስና ፍትሕ መጥፋት የበደልና የጥፋት ምክንያት መሆኑን
_ተከታዮች አሚሮቻቸውን በወንጀል በመታዘዛቸው ዑዝር እንደሌላቸው
_ጭፍን ተከታይነት የተወቀሰ እነ ቅጣትን የሚያስከትል መሆኑን
_አንድ ዓሊም ወይም አሚር የሚለው በመተው በተቃራኒው እሱ የተወውን በመልካም ማዘዝ በመጥፎ መከልከል ግዴታ መሆኑን።
_ይህም ተግባር ዑቀላዎች ዘንድ የሚያስመሰግን እንጂ የሚያስተች አይደለም በርግጥ ሙሪዶችን ልያንጫጫ ይችላል ።
_የብዙ ሙሪዶች ገበና ግልጽ የሚሆነውም በእንደዚህ አይነት ክስተት ወቅት ነው።
_የሱና ዑለሞችና ሱኒዮች ለየት ብለው የሚታወቁት በዚህ አይነት ክስተት በሚያሳዩት በማያወላውል አቋማቸው ነው ።
_የትኛውም ዓሊም የሚሰጠው ፈታዋ ፣ ሰዎችን የሚተቸው ትችቱና የሚያስተላልፈው ትእዛዙ ከማስረጃ የተራቆተ ከሆነ የሱና ዑለሞችና ሱኒዮች ጋ ክብሩና ደረጃው እንደተጠበቀ ሆኖ የተሳሳተበት ነገር ቅንጣት ተቀባይነት አይኖረውም ።
➲ምክንያቱም ከእሳት ሸሽቶ በእሳት መግባት የለምና !
📝ተጨማሪ ትምህርቶችን ለማግኘት የቴሌግራም➷➴ Channeሉን ይቀላቀሉ !!!
https://t.me/MisbahMohammed_6682
3 437
Repost from የወራቤ ሰለፊዮች መገናኛ
ልዩ የዐቂዳ ደርስ
📚 የሚቀራው ሪሳላ:-
ለሸይኽ ዱክቱር አቡ ሙዓዝ ሀሰን ኢብን ዓሊ አልመርዳዊ አልዒራቂይ የሆነችው:
"ከኢማሙ አሕመድ ኡሱሉ ሱንና የተውጣጡ አጫጭር ጠቃሚ ዐቂዳዊ ት/ቶችና መንሀጃዊ መርሆዎች"
"مختصر الفوائد العقدية والقواعد المنهجية المستنبطة من أصول السنة للإمام أحمد" pdf
للشيخ: أبو معاذ حسن بن علي المرداوي العراقي
Pdf ⤵️⤵️
https://t.me/ibnbaz1212/353
⏯ ክፍል 00 (መግቢያ)
በዚህ ክፍል የተዳሰሱ ነጥቦች:
—ስለሪሳላዋ ትውውቅ
—የኡሱሉ ሱና ይዘት ጥቅል ዳሰሳ
—ሸይኽ አቡ ሙዓዝን በሚመለከት
—የኢማሙ አህመድ አጭር ታሪክ...
🎙በኡስታዝ አቡ ሙዓዝ
📆ዕለተ ጁሙዓ ሰፈር 03, 1448
🕌 በመድረሰቱል ኢኽላስ ለሁልባረግ የሴቶች ጀመዓ የተሰጠ ኮርስ
የቴሌግራም ቻነል
https://t.me/ibnbaz1212
3 437
Repost from የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ
🔷የተረጋጋች ነፍስ
ነፍስ በጌታዋ ከተረጋጋች ፣ እርሱን በማስታወስ ካረፈች ፣ ጸጸት አድርጋ ወደርሱ ከተመለሰች ፣ እርሱን ለመገናኘት ከናፈቀች ፣ ወደእርሱ በመቅረቧ ከተጽናናች ሰላም ትሆናለች።
እንዲህ አይነቷ ነፍስ ስትሞት እንዲህ ትባላለች :-
يَا أَيَّتُهَا النَّفْسُ الْمُطْمَئِنَّةُ ارْجِعِي إِلَىٰ رَبِّكِ رَاضِيَةً مَّرْضِيَّةً
"(ለአመነች ነፍስም) «አንቺ የረካሺው ነፍስ ሆይ!
«ወዳጅ ተወዳጅ ኾነሽ ወደ ጌታሽ ተመለሺ፡፡"
(ፈጅር :27-28)
ኢብን አባስ እንዲህ ብለዋል :-
"አንች የረካሽው ነፍስ ሆይ!" - "አማኝ የሆነች ነፍስ" ማለት ነው።
ቀታዳ እንዲህ አለ :-
"አንች የረካሽው ነፍስ ሆይ!" - "እርሷ አማኝ ሆና ፤ አላህ ቃል በገባው ነገር የረካች ነፍስ" ማለት ነው።
ሐሰን እንዲህ አለ:-
"አንች የረካሽው ነፍስ ሆይ!" - "አላህ በተናገረው የረካች ፣ እውነት ያለች ነፍስ" ማለት ነው።
ሙጃሂድ እንዲህ አለ :-
"አንች የረካሽው ነፍስ ሆይ!" - "ጌታዋ አሏህ መሆኑን ያረጋገጠች ፣ ወደርሱ የተጸጸተች ፣ ለእርሱ የተዋደቀች ፣ እርሱን እንደምትገናኝ ያረጋገጠች ትሁት ነፍስ" ማለት ነው።
طب القلوب (ص/٨٠)
https://t.me/alateriqilhaq
كن على بصيرة
