የቀጠናው ተመልካች
Open in Telegram
በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።
Show moreThe country is not specifiedThe category is not specified
4 311
Subscribers
-524 hours
-227 days
-8430 days
Posts Archive
4 312
🇮🇷⚡️🇺🇸 ሰበር ዜና፡ የኃይል ማመንጫዎችን ጨምሮ፣ ቡሸር የኒውክሊየር ማብላሊያ ጣቢያ በአሜሪካ ጥቃት እንደደረሰባቸው መረጃዎች እየወጡ ነው። የኃይል መቆራረጥ በተለያዩ ቦታዎች መከሰታቸው ተነግሯል።
እንደሚባለው እውነት ከሆነ፣ ይሄ መባባስ እጅግ ከፍተኛና አደገኛ ነው።
4 312
🇮🇷⚡️🇺🇸 ሰበር ዜና፡ የኃይል ማመንጫዎችን ጨምሮ፣ ቡሸር የኒውክሊየር ማብላሊያ ጣቢያ በአሜሪካ ጥቃት እንደደረሰባቸው መረጃዎች እየወጡ ነው። የኃይል መቆራረጥ በተለያዩ ቦታዎች መከሰታቸው ተነግሯል።
እንደሚባለው እውነት ከሆነ፣ ይሄ መባባስ እጅግ ከፍተኛና አደገኛ ነው።
4 312
🇮🇱🇺🇸❌🇮🇷 - የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ -
ትራምፕ ኢራናውያን እያጭበረበሩ እና ይህን ሂደት እየጎተቱ እንደሆነ ያውቃሉ። ይህንንም ይናገራል። ለማንኛውም ሁኔታ ዝግጁ ነን።ይቅርታ የተከበሩ ጠቅላይ ሚኒስቴር፣ አርፈው ይቀመጡ! የእርሶ ተሳትፎ እዚህ ውስጥ አያስፈልግም። የእስራኤል መግባት፣ ከማባባስ ውጭ መፍትሄ አያመጣም።
4 312
🇮🇷⚡️🇺🇸 በኢራን ላይ የተጠበቀው የአሜሪካ ወታደራዊ ጥቃት፣ አሁን ተጀምሯል። ደቡብ ኢራን ያሉ ወታደራዊ ዒላማዎች እና ሲሪክ፣ ካሽም እንዲሁም ባንዳር አባስ ደሴቶች በአሁኑ ሰዓት በአሜሪካ ወታደራዊ ጥቃት ሥር ናቸው።
ምናልባት አሜሪካ ኢራን ቀብር ላይ ስላለች፣ አጸፋዋ እምብዛም ነው ብላ አስባ ይሆናል።
በሌላ መልኩ፣ ኢራን በቀጠናው ያሉ አረብ ሀገሮችን፣ በምንም መልኩ ለአሜሪካ ጦር ማስወንጨፊያነት የምታገለግሉ ከሆነ፣ አጸፋዋን በእነሱ ላይ እንደምታደርግ አስጠንቅቃለች።
እስራኤል በበኩሏ፣ አጋጣሚውን ተጠቅማ ለመግባት ብትቋምጥም፣ ለአሁን ዳር ናት።
4 312
Repost from Sputnik Africa
Rosatom Begins Manufacturing Fourth Reactor Vessel for Egypt's El Dabaa Nuclear Plant
⚛️ The first metal blanks—weighing over 65 tonnes — have arrived for the fourth VVER-1200 reactor. These massive pieces will be machined to precise specifications and coated with anti-corrosion cladding to ensure decades of durability.
🇷🇺🤝🇪🇬 Rosatom has already delivered reactor vessels for Units 1 and 2. Production is now underway for:
⚡️Unit 3 reactor vessel;
⚡️12 steam generators for Units 2–4;
⚡️other key nuclear island equipment.
⚛️ The manufacturing involves Rosatom's plants across Russia — in St. Petersburg, Moscow, Rostov, and Karelia.
Subscribe to @sputnik_africa
🔸 Sputnik Africa | X 🔸
4 312
🇷🇺🇺🇦 ፑቲን ከዘለንስኪ ጋር ከሞስኮ ውጭ ለመገናኘት የፈራው ለምንድነው? 'ሩሲያ መነጋገር ትፈልጋለች' ካለ፣ ለምን ገለልተኛ ሀገር ከዘለንስኪ ጋር አይገናኝም? ምን አስፈራው? ይሄ ግትርነት የዥል አይደለም ወይ? ሁሉን ትቶ በሙሉ ልብ ቆርጦለት አልተዋጋ፣ ወይ አልተነጋገረ፣ ምንድነው ዓላማው?
እስከ አሁን በወር 35ሺ ወታደሩን እያስጨረሰ፣ የምድር ሲዖሉን፣ 'ጦርነት' ብሎ መጥራት የማይፈልግ ሰው ነው ፑቲን። ሩሲያ ውስጥ ሁኔታውን 'ጦርነት' ብለህ ከዘገብክ፣ ትታሰራለህ። SMO ነው የሚባለው፣ Special Military Operation. 'War' ማለት ጉላግ ያስልካል። እንደ ፀረ ሽብር አነስተኛ ዘመቻ፣ ልዩ የፖሊስ ዘመቻ እንጂ ወይም እኛ ሀገር 'ግጭት' እንደሚሉት፣ 'ጦርነት' 'War' አይባልም።
እንግዲህ ይህን 'ጦርነት' ብሎ ለመጥራት ጉሮሮውን የሚያንቀው ሰው ነው፣ ሩሲያን በዚህ ጦርነት እየመራ ለዚህ ያደረሰው። ምክኒያቱ ምንም ይሁን ምንም፣ ይሄ አጉል ጉራ እና የዥል ግትርነት ሽንፈትን ያመጣል እንጂ የትም አያደርሰም።
ለሰላም ድርድር ያድርግ አይደለም እያልኩኝ ያለሁት። ማድረግም አይጠበቅበትም። ጉዳዩን በጦርነት ብቻና ብቻ ነው የምፈታው፣ 'ከናዚና' ከሽብርተኛ ጋር ድርድር አይሆንም፣ ፖሊሲያችንም አይደለም፣ ካለ መብቱ ነው። በውጊያ በኪየቭ ያለውን መንግሥት አንበረክካለሁ፣ ማለት ይችላል። አቅሙም አለው። ነገር ግን፣ 'ሩሲያ ለሰላም ድርድር ዝግጁ ናት፣ ጦርነቱን በድርድር ማቆም እንፈልጋለን' ካለ፣ አለቀ! የትም ይሁን፣ ሁለቱ ሀገሮች በሚስማሙበት፣ ቻይናም ይሁን፣ መደራደር ነው፣ መነጋገር ነው። 'አይ፣ ሞስኮ ካልሆነ ሞቼ እገኛለሁ' ካለ ግን፣ ሌላ ነገር ነው። በዚህ መሃል፣ በእሱ ግራ በገባውና በማይታወቅ ምክኒያቱ፣ ሩሲያ ደማች።
ተመልከቱ አሜሪካን፣ ስዊዘርላንድ ሄዳ ከኢራን ጋር ተደራደረች። በጉራ መነፋት እና በትዕቢት እምቢ ማለት ቢኖርባት፣ ያለባት አሜሪካ ነበረች።
ባለፈው እንዳልኩት፣ የአውሮፓዊያን ጦርነቱን ለመጨረስ ያለመፈለግ ዝንባሌ እንዳለ ሆኖ፣ የፑቲንም ውሳኔ ለመወሰን ያለመቻል ተደምሮበት፣ ጦርነቱን ለሩሲያ ሲዖል እያመጣባት ነው።
4 312
🇺🇸🇺🇦🇷🇺 - ዘሌንስኪ እና ትራምፕ ዛሬ በአንካራ ተገናኝተዋል፣ ከፕረሱ ጋር ከተደረገው ንግግር ትንሹ ክሊፕ ይኸውና።
ትራምፕ፡
ፑቲንን ካነጋገርኩት ነገሮች አንዱ፣ 'የት መገናኘት ትፈልጋለህ?' የሚል ነበር። እናም 'በሐሳብ ደረጃ በሞስኮ' አለኝ። 'በሞስኮ አትገናኝም፣ እሱ የማይቻል ነገር ነው' አልኩት። … ወደ ሞስኮ ትሄዳለህ ዘለንስኪ?ዘለንስኪ፡
ከባድ ነው። እዚያ ብዙ የዩክሬን ድሮኖች አሉ።
4 312
🇮🇷⚡️🇺🇸 ኢራናዊያን፣ 'መንግሥታችን ምን እያደረገ ነው? ለተሰነዘረብን ጥቃት አፀፋው ለምን አነሰ? ሚሳዬሎቻችን እና ድሮኖቻችን የት አሉ? አሜሪካ በግልፁ ዛሬ፣ ነገ፣ ምሽቱን … እደበድባችኋለሁ እያለች በምታውጅበት፣ የእኛ መቀመጥ ከምን የመጣ ነው? የጦሩ ምላሽ የት ነው? እያሉ እየጠየቁ ናቸው።
በኢራናዊያን ዘንድ ከፍተኛ ሕዝባዊ ብስጭት ይስተዋላል።
አስታውሱ፡ አብዛኛው የኢራን ሕዝብ የተኩስ አቁም መግባቢያ ስምምነቱን በከፍተኛ ደረጃ የተቃወመ ነው። 'የተረገመ' ሲሉ ይጠሩታል መግባቢያ ሰነዱን። ተፈረመ በተባለ ምሽት እና ተከታታይ ቀናቶች፣ ሰልፎችና ከፀጥታ አካላት ጋር ግጭቶች ነበሩ።
ተደራዳሪዎቹን፣ በተለይም ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን ሰይድ አባስ አራጋቺን እና የፖርላማ ቃል አቀባዩን መሐመድ ባጋር ጋሊባፍን ከሃዲዎች፣ ሀገር ሻጮች፣ ይያዙ፣ ይሰቀሉ እስከማለት ተደርሶ ነበር።
4 312
🇮🇷⚡️🇺🇸 ትራምፕ፡ ኢራንን፣ ትናንት እንደመታናት፣ ዛሬ ማታም በደንብ እንመታታለን ብዬ እጠብቃለሁ። የተማሩት ነገር ያለ አይመስለኝም፣ አሁንም እዚያው የጥፋት ሥራቸው ላይ ናቸው። ለ47 ዓመታት የአካባቢው ጉልቤ ሆነው ቆይተዋል። ይቅርታ፣ ይሄ አይቀጥልም ከአሁን በኋላ።
4 312
🇨🇦🇦🇪 ካናዳ ለዩናይትድ አረብ ኤምሬት፡ $70 ቢሊዮን ዶላር ኢንቬስትመንትሽን የምመራበት ፕሮጀክት ስለሌለኝ አልፈልገውም፣ ማለቷ ተሰማ Financial Times
ካናዳ፣ የተባበሩት አረብ ኤሜሬትን ኢንቬስትመንት ውድቅ አድርጋለች።
*-*-*-
ባክህ ፈጣሪም ላለው ነው የሚጨምርለት ያለው ማን ነበር?
ኧረ ልጨምርልህም ሲባል እምቢ እያለ ነው ያለው፣ አሁን አሁን ያለው፣ ጥጋቡ!
ፈረንጅ እኮ ኩራቱ አይቻልም። ቱርክ አሜሪካ F35 ጀቶችንና መለዋወጫ ብረታብረቶችን እንድትሸጥላት ስትለምናት ስንት ዓመቷ። በቢሊዮን እኮ የሚቆጠር ሽያጭ ነው፣ ግን በቃ እንግዛችሁ እየተባሉ፣ የራሳቸውን ነገር ሲጠብቁ፣ እምቢ! አይሸጡም ለማንም አልፎ ሄያጅ ችስታ፣ የፈለገ ገንዘብ ተሸክሞ ቢመጣ።
ለነገሩ እነዚህ እነዚህ የሚያመጡት ገንዘቡ ራሱ የስንት ምስኪን እምባና ደም የፈሰሰበት ስለሆነ፣ እሱን ተቀብለው አይቀላቅሉም ካላቸው ጋር፣ ያላቸውንም ይዞባቸው ነው የሚጠፋው።
እስኪ አስቡት፣ $70 ቢሊዮን ዶላር እንስጣችሁ እየተባለ … እምቢ? እኛ ብንሆንስ? ለ$70 ቢሊዮን ዶላር አይደለም፣ $50 ሚሊዮን ሀገር ሁሉ አንሸጥም እንዴ? ይሄ የድህንነት ጉዳይ አይደለም፣ የክብር ጉዳይ ነው። $70 ቢሊዮኑ ከኋላው ምን ይዟል? ይጠይቃሉ በደንብ። ያዩና፣ አይ ይቅርብን thank you very much ይሏቸዋል።
የኢትዮጵያ የጥንት አባት አያቶቻችን እንዲህ ነበሩ፣ ማንም የያዘውን ይዞ ቢመጣ፣ አይጓጉም ነበር። አጥንተው እምቢ ይላሉ። ሀገር፣ ሕዝብ፣ ተቋም ለሳንቲም አይሸጡም።
4 312
🇮🇷⚡️🇺🇸 የኢራን አብዛኞቹ ከፍተኛ ባለሥልጣናት በአሁኑ ሰዓት ለቀብር ስነ ሥርዓት በኢራቅ ይገኛሉ። በሌሉበት ነው ሀገራቸው ላይ ድብደባ የተከፈተው። በወጡበት ተገድለው ሊቀሩ ይችላሉ፣ በሚለው ሕዝባዊ ፍራቻ የተነሳ፣ ፕሬዝዳንቱን ጨምሮ ጥቂት ባለሥልጣናቱ፣ አሁን ቀብሩን አቋርጠው ወደ ኢራን በአስቸኳይ ተመልሰዋል።
4 312
🇮🇷⚡️🇺🇸 ባንደር አባስ ደቡብ ኢራን፣ የአሜሪካ ሚሳዬል ሲወድቅ ይታያል። ድብደባው አሁንም ቀጥሏል።
ይህን አጋጣሚ በመጠቀም፣ እስራኤል ደቡብ ሊባኖስ ላይ ድብደባ ከፍታለች።
4 312
🇺🇦⚡️ዘለንስኪ በአንካራ በተካሄደው የኔቶ ስብሰባ ላይ -
ሩሲያ ስትራቴጂካዊ የኋላ ደጀን አላት የሚለውን ሀሳብ ሙሉ በሙሉ አጥፍተነዋል። ሩሲያ የምትባለው ይህች ሀገር፣ ለረጅም ጊዜ የግዛት ብልጫ እንዳላት ታምን ነበር። ታውቃላችሁ፣ "ሠፊ ነኝ፣ ጥልቅ ነኝ፣ አይደረስብኝም ትል ነበር። ከእሷ የበለጠ ማንም ጥልቅየሆነ ደጀን አልነበረውም። ማንም ሊደርስባቸው እንደማይችል በማመን፣ ወታደራዊ ምርትን፣ ወታደራዊ መሳሪያዎችን እና ጦርነቱ የተመሠረተበትን ሁሉ፣ በአስተማማኝ ሁኔታ እያመረቱ መቆየት ይችሉ ነበር። ግንባር ይዋጋሉ፣ ከኋላ በነፃነት ለጦር ግብዓት ያቀርባሉ። ያ ጊዜ አብቅቷል ወዳጆቼ።
ልክ ትናንትና የዩክሬን ድሮኖች የሩስያን መከላከያ ሰብረው በመግባት 3000 ኪሜ ተጉዘው በሳይቤሪያ የሚገኘውን ግዙፉን የነዳጅ ማጣሪያዋን እንደመቱት፣ ወደፊትም እየመታን ማዳከማችንን እንቀጥላለን። የምትመካበት የኋላ ደጀን ላይ በዚህ መልኩ እርምጃ መውሰዳችንን እንቀጥላለን። ይህ አዲሱ እውነታ ነው! ዩክሬን ያልመታችው አንድም ትልቅ የሩሲያ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ የለም!
*-*-*-
ወንድሞቼ፣ ወደዳችሁም ጠላችሁም እውነታው ይሄ ነው። አልተሳሳተም! ሩሲያ፣ ያቺ ግዙፍና እና ስመ ጥሯ! ሩሲያ፣ የዓለም ባላንስ አስጠባቂዋ፣ ዛሬ ደክማለች። በሚጢጢዬዋ ዩክሬን፣ በተናቀው አይሁዳዊ መሪዋ፣ እየተቦጠቦጠች ነው።
ሩሲያ፣ መሪዎቿ ደካሞችና ደፋሮች ስላልሆኑ፣ ከዚህም በላይ መፍረክረኳን እያፈጠኑት ይገኛሉ። ይቅርታ፣ "ይህ አዲሱ እውነታ ነው!
4 312
🇺🇸⚡️🇮🇷 የዩናይትድ ስቴስት ኦፍ አሜሪካ ማዕከላዊ ወታደራዊ ዕዝ፣ CENTCOM 'ጠንካራ' ሲል የጠራውን ድብደባ በኢራን ላይ ማድረጉን አስታወቀ!
4 312
🇮🇷⚡️🇺🇸 ሰበር ዜና፡ በርካታ ፍንዳታዎች በደቡብ ኢራን እና በሆርሙዝ አቅራቢያ በሚገኙ ደሴቶች በመሰማት ላይ ናቸው። አሜሪካ፣ ሲጠበቅ የነበረውን ጥቃት እንደጀመረች ይታመናል።
