fa
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

رفتن به کانال در Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
4 318
مشترکین
-824 ساعت
-117 روز
-8230 روز
آرشیو پست ها
🇷🇺 ኢንተርናሽናል ኦሎምፒክ ኮሚቴ (IOC) በሩሲያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ላይ ተጥሎ የነበረውን እገዳ አንስቷል። በሩሲያ አትሌቶች ላይ ሁሉንም ገደቦች ማንሳት ይገባል፣ ሲልም ምክረ ሐሳብ ሰጥቷል። IOC, "በኋላ ላይ በሩሲያ ባንዲራ እና መዝሙር ላይ ውሳኔ ለመስጠት" አቅዷል።

🇷🇺 ኢንተርናሽናል ኦሎምፒክ ኮሚቴ (IOC) በሩሲያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ላይ እገዳውን አንስቷል። በሩሲያ አትሌቶች ላይ ሁሉንም ገደቦች ማንሳት ይገባል፣ ሲልም ምክረ ሐሳብ ሰጥቷል። IOC "በኋላ ላይ በሩሲያ ባንዲራ እና መዝሙር ላይ ውሳኔ ለመስጠት" አቅዷል።

🇺🇸🚫🇮🇷 የማይቀር የሚመስል የመባባስ አደጋ፡ ዩናይትድ ስቴትስ በሚቀጥሉት 24 እና 48 ሰዓታት ውስጥ፣ በኢራን ላይ የታለመ ጥቃት ልታደርግ ትችላለች። ይህ ጥቃት፣ በትናንትናው ዕለት በኦማን የባህር ዳርቻ ላይ በሁለት የነዳጅ ታንከሮች - አንድ የኳታር እና አንድ የሳዑዲ - 'በአሜሪካ ቁጥጥር ሥር' ባለው የባሕሩ አካባቢ በኢራን ተፈጸመ ለተባለው ጥቃት ምላሽ የሚሆን ነው። የኢራን ጦር፣ የበቀል ጥቃት ለመሰንዘር ከወዲሁ በጥብቅ እያሰበበት ነው።

🇺🇦🔹⚡️ - ዘለንስኪ በአንካራ የኔቶ ስብሰባ መሪዎች እራት ላይ ተገኝቶ ይበላል፣ ነገር ግን በሕብረቱ ስብሰባ ላይ እንዲገባ አልተፈቀደለትም - CNN

🇺🇸🇹🇷 ትራምፕ፡ በኔቶ በጣም አዝኛለሁ እና እውነቱን ለመናገር ስብሰባው፣ ጓደኛዬ - በጣም ጠንካራው መሪ፣ በጣም ጠንካራው ሰው፣ በሚመራት በቱርክ ባይካሄድ ኖሮ፣ እኔ ባልሳተፍኩ ነበር። *-*
🇺🇸🇹🇷 ትራምፕ፡ በኔቶ በጣም አዝኛለሁ እና እውነቱን ለመናገር ስብሰባው፣ ጓደኛዬ - በጣም ጠንካራው መሪ፣ በጣም ጠንካራው ሰው፣ በሚመራት በቱርክ ባይካሄድ ኖሮ፣ እኔ ባልሳተፍኩ ነበር። *-*-*- ኤርዶጋን እንዴት ደስ ብሎት እንደሳቀ ብታዩ።

🇺🇸🇹🇷 ትራምፕ፡ በኔቶ በጣም አዝኛለሁ እና እውነቱን ለመናገር፣ ስብሰባው ጓደኛዬ - በጣም ጠንካራው መሪ፣ በጣም ጠንካራው ሰው፣ በሚመራት በቱርክ ባይካሄድ ኖሮ፣ እኔ ባልሳተፍኩ ነበር። *-*
🇺🇸🇹🇷 ትራምፕ፡ በኔቶ በጣም አዝኛለሁ እና እውነቱን ለመናገር፣ ስብሰባው ጓደኛዬ - በጣም ጠንካራው መሪ፣ በጣም ጠንካራው ሰው፣ በሚመራት በቱርክ ባይካሄድ ኖሮ፣ እኔ ባልሳተፍኩ ነበር። *-*-*- ኤርዶጋን ደስ ብሎት በጣም ሳቀ።

🇺🇸🇹🇷🇮🇷🇮🇱⚡️ - ፕሬዝዳንት ትራምፕ ስለ ቱርክ-
ቱርክ ለእኛ ትልቅ አጋር ሆናለች። ኢራንን ጠንቅቀው ያውቋታል። እና አንዳንድ ሰዎች ከእስራኤል ጋር ስላላቸው ግንኙነት ሲናገሩ ሰምቻለሁ። በሌላኛው በኩል ወደ ትግሉ መግባት ይችሉ ነበር። እነሱ በጣም ኃይለኛ ወታደራዊ ሀገር ናቸው፣ ግን ያንን አላደረጉም ። ምናልባት በእኔ ምክንያት ያንን አላደረጉም። እነሱ በጣም በጣም ጥሩ ሀገር ሆነውልናል።


🇺🇸🇮🇹⚡️ - ጋዜጠኛ - ትናንት ከጠቅላይ ሚኒስትር ሜሎኒ ጋር በተያያዘ በ Truth Social Post ላይ "የእገዳ ትእዛዝ" ብለሃል፣ ምን ለማለት እንደፈለጉ ግልጽ ማድረግ ይችላሉ?
ትራምፕ ደህና፣ አላውቅም። በእውነቱ እሷ ጥሩ ሰው ነች ብዬ አስባለሁ። በሆርሙዝ ወሽመጥ እኛን ለመርዳት ፈቃደኛ ባለመሆኗ ትንሽ መጥፎ ሆነ፣ ወይም ከኢራን ጋር ለመሳተፍ ፈቃደኛ አልሆነችም ማለት ትችላላችሁ። ስለዚህ ከእሷ ጋር ያለኝን ግንኙነት ትንሽ አበላሸው። ግን እወዳታለሁ። በእውነቱ እሷ ጥሩ ሰው ነች ብዬ አስባለሁ። ግን ስህተት የሰራች ይመስለኛል።
እንደ ትራምፕ ግን አራዳ፣ ጮሌ መሪ በዓለም ላይ አለ? ውሃ ቀቅሎ የሚበላ? በጣም አራዳ ነው፣ በደንብ የገባው።

🇺🇸🇺🇦🇷🇺⚡️ - ፕሬዝዳንት ትራምፕ በዩክሬን ጦርነት ላይ -
የጦር ሜዳዎችን አይቻለሁ። ፎቶግራፎችን ይልኩልኛል። አትላኩልኝ፣ እያልኩ ይልኩልኛል። ምን ይጠቅማል መላኩ? እላለሁ። ግን ፒት ሄግሲት ምስሎችን ይልክልኛል። አስቀያሚ፣ ዘግናኝ ናቸው። እንደዚህ ያለ ነገር አይቼ አላውቅም። እልቂት ነው እና መቆም አለበት።

🇫🇷🇸🇾 የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት፣ አማኑኤል ማክሮን፣ በደማስቆ ከተማ፣ ያረፈበት ሆቴል መግቢያ ላይ ፍንዳታ ተከስቷል። በትናንትናው ዕለት፣ ማክሮን ከጦርነቱ በኋላ ደማስቆን የጎበኘ የመጀመሪያው የአውሮፓ መሪ ሆኗል። በፍንዳታው የሶሪያ ቱሪዝም ሚኒስቴር የቆሰለ ሲሆን፣ የሶሪያ መንግሥት፣ ማክሮን ያደረው ሆቴል ሳይሆን ቤተ መንግሥት ነበር ብሏል። ሮይተርስ፣ የዛሬውን ፍንዳታ "በማክሮን ላይ የተደረገ የመግደል ሙከራ" ብሎታል።

🇮🇱🇺🇸 እስራኤል ዳግም አሜሪካ ለቱርክ አየር ኃይል ምንም ነገር እንዳትሸጥላት ተማጽናለች። እስካሁን ባለው ምልከታ ግን፣ ትራምፕ ቱርክ F-35ቶችን እንድትገዛ ሊፈቅድላት እንደሆነ ነው።

+4
🇮🇷⚡️ - በሰማዕቱ መሪ አያቶላ ኻሜኔይ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ያለው ከፍተኛ ተሳትፎ ማደጉን ቀጥሏል። - ይህ ልኬት የምዕራባውያን ሚዲያዎችን ያስደነገጠ ሲሆን ኢራናውያን እስላማዊ ሪፐብሊክን በከፍተኛ ሁኔታ ይቃወማሉ የሚለውን የረዥም ጊዜ አባባል አሁን በአብዛኛው ውድቅ ሆኗል። የቀብሩ ሥነ-ሥርዓት ዛሬም በሺዓዎች ቅዱስ ከተማ በምትባለው ቃም፣ ቀጥሏል። ከዚያ፣ ወደ ኢራቅ ይቀጥላል።

🪖🇹🇷⚡️ - የኔቶ ዋና ፀሃፊ ማርክ ሩቴ በአንካራ - ቱርክ በኔቶ ውስጥ ካሉ ትላልቅ የጦር ኃይሎች አንዷ ናት። በደንብ የሰለጠነ ኃይል አላት። - በተለይም ባለፉት 5-10 ዓመታት ውስጥ፣ የመከ
🪖🇹🇷⚡️ - የኔቶ ዋና ፀሃፊ ማርክ ሩቴ በአንካራ
- ቱርክ በኔቶ ውስጥ ካሉ ትላልቅ የጦር ኃይሎች አንዷ ናት። በደንብ የሰለጠነ ኃይል አላት። - በተለይም ባለፉት 5-10 ዓመታት ውስጥ፣ የመከላከያ ኢንዱስትሪ መሠረትዋን በፍጥነት አዳብራለች። አሁን በየቀኑ ወደ 3,000 የሚጠጉ የጦር ኩባንያዎቿ ዩኒፎርም የለበሱ ወንዶቻችን እና ሴቶቻችን እራሳቸውን ለመከላከል የሚያስፈልጋቸውን የመከላከያ ኢንዱስትሪ ምርት የሚያመርቱ ናቸው። አንካራ፣ ኢስታንቡል፣ በአጠቃላይ ቱርክ በጣም አስፈላጊ ናት። በኔቶ ውስጥ ያላት አመራር አስፈላጊ ነው። ይህንን ስብሰባ በአንካራ ማደራጀት መቻሏ ለዚህ ማስረጃ ነው።
*-*-*-*- ቱርክ ተካበች፣ ደስም አላት። ትራምፕም ወደዚያ ማምሻውን አቅንቷል። ቱርክ ብትካብም፣ ደስ ቢላትም ግን፣ የአውሮፓ ሕብረት አባልነትን ከልክለዋታል። 'አንደኛ እጩ ተጠባባቂ' ተብላ ወንበር ስታሞቅ፣ ሃያ አመት አልፏታል። ኤርዶጋን ከመጣ ጀምሮ አስገቡን እያለ ደጅ ሲጠና፣ ይኸው አርጅቶ በከዘራ ሊሄድ ትንሽ ቀርቶታል። ከእሱ በፊት ሞልዶቫና ዩክሬን ቻንስ አላችሁ ተብለዋል። ዛሬ ግን፣ 'ጠላ ጠጡ' እንድታዘጋጅ በማድረግ፣ ጠጅና ጠላ አስጠምቀው፣ ወይፈንና ሙክት አስጥለው (ፐ! የቱርክ ወይፈን እኮ፣ እሱን አንዴ በልተህ ብትሞት ራሱ እኮ በቃ) ድግሷን ጥርግ አድርገው ሊበሉላት እየተሰናዱ፣ 'ቱርክዬ ምርጥ ሀገር' እያሉ ጀርባዋን ቿ ያደርጓታል።

🇺🇦⚡️ፊንላንድ፣ ዩክሬን ሩሲያን አጠናክራ እና ውስጥ ድረስ ዘልቃ በመምታት ጦርነቱን ለሩሲያዊያን አሳማሚ እንዲሆንና ለያንዳንዱ ሩሲያዊ 'ግላዊ' እንድታደርገው ትፈልጋለች። ፕሬዝዳንት ስተብ የሩሲ
🇺🇦⚡️ፊንላንድ፣ ዩክሬን ሩሲያን አጠናክራ እና ውስጥ ድረስ ዘልቃ በመምታት ጦርነቱን ለሩሲያዊያን አሳማሚ እንዲሆንና ለያንዳንዱ ሩሲያዊ 'ግላዊ' እንድታደርገው ትፈልጋለች። ፕሬዝዳንት ስተብ የሩሲያ ሕዝብ መሪዎቹ ላይ እንዲዞር ምኞቱ ነው። ዩክሬን በውጊያ ሜዳው ላይ የበላይነቱን ይዛለች ብሎ ያምናል።

🇬🇪 የአውሮፓ ህብረት በፍናፍንቶች አቋም ላይ፣ በጆርጂያ ቤተ ክርስቲያን ላይ ጫና ፈጽሟል ተብሎ ተከሷል። 'ፈናፍንትነት በእምነታችን ክልክል ነው ስንል፣ እሱ የሩስያ ፕሮፓጋንዳ ብለው ይጠሩታል'
🇬🇪 የአውሮፓ ህብረት በፍናፍንቶች አቋም ላይ፣ በጆርጂያ ቤተ ክርስቲያን ላይ ጫና ፈጽሟል ተብሎ ተከሷል። 'ፈናፍንትነት በእምነታችን ክልክል ነው ስንል፣ እሱ የሩስያ ፕሮፓጋንዳ ብለው ይጠሩታል' - የጆርጂያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቃል አቀባይ። የአውሮፓ ህብረት ባለስልጣናት፣ ቤተክርስቲያኗ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን ለመደገፍ ፈቃደኛ ባለመሆኗ ተችተው፣ 'ከ21ኛው ክፍለ ዘመን አዝማሚያዎች' ጋር እንድትስማማና አብራ እንድትራመድ አሳስበዋል። 

🇷🇺❌🇺🇦 - ኪየቭ ድብልቅልቋ ወጥቷል። ሩሲያ፣ በኪየቭ ላይ፣ ሌሊቱን እና ሊነጋጋ ሲል፣ ባደረሰችው ጥቃት፣ በአንድ ጀምበር በርካታ የዩክሬን ድሮን ማምረቻ ፋብሪካዎች ከጥቅም ውጭ ሆነዋል፣ እንደ ሩሲያ መከላከያ ሚንስትር ሪፖርት። ➡️  የቡሬቬስትኒክ፣ ኪየቭ-71፣ ኪየቭ-79 እና የክቫንት ፋብሪካዎች፣ በዙሊያኒ የሚሳኤል ፋብሪካ እና በቪሽኔቭ የነዳጅ መጋዘን ተመትተዋል። ➡️ በዛፖሪዝሂያ ክልል፣ ለዩክሬን ጦር ኃይሎች ነዳጅ የሚያቀርብ መጋዘን ተመትቷል። ➡️ በምዕራብ ዩክሬን፣ ግዙፉ S-300 የአየር መቃወሚያ ሚሳዬሎች ፋብሪካ፣ ተደምስሷል፣ ሁለተኛ ፍንዳታዎች እስካሁን ከኢንዱስትሪው በመፈንዳት ላይ ናቸው።

🇷🇺🇺🇸🇺🇦 ፕሬዝዳንት ትራምፕ፡ ፑቲን ጦርነቱን ማቆም ይፈልጋል፣ በነበረን ጥሩ የስልክ ጥሪ ነግሮኛል። ዘለንስኪም ጦርነቱን አሁን ማቆም ይፈልጋል። ብዙ ሰው ከሚያስበው በላይ ወደዚያ እየተጠጋን ነው። በአንካራ የኔቶ ስብሰባ ይህን እናነሳለን። *-*-*- ፑቲን ለማቆም የጣረውን ያህል ቢጥር፣ ዘለንስኪ አሁን እናቁም ብሎ ቢቆርጥለት፣ ትራምፕ የፈለገውን ያህል ጦርነቱ በሰላም ሊፈታ ነው ቢል፣  አውሮፓዊያን ጦርነቱ እንዲቆም አይፈልጉምና ጦርነቱ አይቆምም። አውሮፓዊያን (እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን) ጦርነት ማቆም አይፈልጉም። በመጪው ኔቶ ስብሰባ፣ ይህን ነው ለትራምፕ የሚሉት "ሩሲያ እየደቀቀች ነው፣ ጊዜ ስጠን እንጨርሳት።" ትራምፕ፣ ሩሲያ ጋር መገናኘት የሚችለው በስልክ ብቻ ነው። ካልሆነ በሦስተኛ ወገን ነው። ፊት ለፊት እንኳ እንዳይገናኙ አውሮፓዊያን ድልድዩን አፍርሰውባቸዋል። በስልክና በሦስተኛ ወገን ደግሞ የምታመጣው ምንም ለውጥ የለም። ጦርነቱ ይቀጥላል!

ፕሬዝዳንት ትራምፕ፡ ፑቲን ጦርነቱን ማቆም ይፈልጋል፣ በነበረን ጥሩ የስልክ ጥሪ ነግሮኛል። ዘለንስኪም ጦርነቱን አሁን ማቆም ይፈልጋል። ብዙ ሰው ከሚያስበው በላይ ወደዚያ እየተጠጋን ነው። በአንካራ የኔቶ ስብሰባ ይህን እናነሳለን። *-*-*- ፑቲን ለማቆም የጣረውን ያህል ቢጥር፣ ዘለንስኪ አሁን እናቁም ብሎ ቢቆርጥለት፣ ትራምፕ የፈለገውን ያህል ጦርነቱ በሰላም ሊፈታ ነው ቢል፣ አውሮፓዊያን ጦርነቱ እንዲቆም አይፈልጉምና ጦርነቱ አይቆምም። አውሮፓዊያን (እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን) ጦርነት ማቆም አይፈልጉም። በመጪው ኔቶ ስብሰባ፣ ይህን ነው ለትራምፕ የሚሉት "ሩሲያ እየደቀቀች ነው፣ ጊዜ ስጠን እንጨርሳት።" ትራምፕ፣ ሩሲያ ጋር መገናኘት የሚችለው በስልክ ብቻ ነው። ካልሆነ በሦስተኛ ወገን ነው። ፊት ለፊት እንኳ እንዳይገናኙ አውሮፓዊያን ድልድዩን አፍርሰውባቸዋል። በስልክና በሦስተኛ ወገን ደግሞ የምታመጣው ምንም ለውጥ የለም። ጦርነቱ ይቀጥላል!

🇺🇸⚽️ - ፕሬዝዳንት ትራምፕ በባሎጉን ቀይ ካርድ ላይ
- ቀይ ካርድ ምን እንደሆነ አላውቅም ነበር። ሳውቅ "እየቀለድክ ነው?" አልኩት። ዳኛው ዝም ብሎ እጁን ወደ ላይ ያወጣል። እሺ፣ ከዚያ ያንተን ምርጥ ተጫዋች በሚቀጥለው ሳምንት ወይም በሚቀጥለው ጨዋታ እንዳትጫወት ይላል። ይሄ እኮ ብዙ ሥልጣን ነው፣ ብዙ አምባገነንነት ነው። ያ በጣም አስፈሪ ነው። ግን ከዚያ የዳኛውን ያለፈ ታሪክ ተመለከትኩ እና ያን ያህል ጥሩ እንዳልነበረ ተረዳሁ።

🇺🇦 ዩክሬናዊያን፣ በስተመጨረሻ ስለታችን ሰመረ። ስንጠብቀው የነበረው ቀን፣ ይኸው ሆነ ዛሬ፣ የኦምስክ ነዳጅ ማጣሪያን አገኘነው፣ 3000 ኪ.ሜ ገብተን መታነው፣ እያሉ በመደሰት ላይ ናቸው። ኦምስክ ነዳጅ ማጣሪያ የሩሲያ ግዙፉ ነዳጅ ማጣሪያ ነው።