የቀጠናው ተመልካች
Kanalga Telegram’da o‘tish
በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።
Ko'proq ko'rsatishMamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
4 316
Obunachilar
-824 soatlar
-117 kun
-8230 kun
Postlar arxiv
4 315
🇺🇦⚡️ዘለንስኪ በአንካራ በተካሄደው የኔቶ ስብሰባ ላይ -
ሩሲያ ስትራቴጂካዊ የኋላ ደጀን አላት የሚለውን ሀሳብ ሙሉ በሙሉ አጥፍተነዋል። ሩሲያ የምትባለው ይህች ሀገር፣ ለረጅም ጊዜ የግዛት ብልጫ እንዳላት ታምን ነበር። ታውቃላችሁ፣ "ሠፊ ነኝ፣ ጥልቅ ነኝ፣ አይደረስብኝም ትል ነበር። ከእሷ የበለጠ ማንም ጥልቅየሆነ ደጀን አልነበረውም። ማንም ሊደርስባቸው እንደማይችል በማመን፣ ወታደራዊ ምርትን፣ ወታደራዊ መሳሪያዎችን እና ጦርነቱ የተመሠረተበትን ሁሉ፣ በአስተማማኝ ሁኔታ እያመረቱ መቆየት ይችሉ ነበር። ግንባር ይዋጋሉ፣ ከኋላ በነፃነት ለጦር ግብዓት ያቀርባሉ። ያ ጊዜ አብቅቷል ወዳጆቼ።
ልክ ትናንትና የዩክሬን ድሮኖች የሩስያን መከላከያ ሰብረው በመግባት 3000 ኪሜ ተጉዘው በሳይቤሪያ የሚገኘውን ግዙፉን የነዳጅ ማጣሪያዋን እንደመቱት፣ ወደፊትም እየመታን ማዳከማችንን እንቀጥላለን። የምትመካበት የኋላ ደጀን ላይ በዚህ መልኩ እርምጃ መውሰዳችንን እንቀጥላለን። ይህ አዲሱ እውነታ ነው! ዩክሬን ያልመታችው አንድም ትልቅ የሩሲያ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ የለም!
*-*-*-
ወንድሞቼ፣ ወደዳችሁም ጠላችሁም እውነታው ይሄ ነው። አልተሳሳተም! ሩሲያ፣ ያቺ ግዙፍና እና ስመ ጥሯ! ሩሲያ፣ የዓለም ባላንስ አስጠባቂዋ፣ ዛሬ ደክማለች። በሚጢጢዬዋ ዩክሬን፣ በተናቀው አይሁዳዊ መሪዋ፣ እየተቦጠቦጠች ነው።
ሩሲያ፣ መሪዎቿ ደካሞችና ደፋሮች ስላልሆኑ፣ ከዚህም በላይ መፍረክረኳን እያፈጠኑት ይገኛሉ። ይቅርታ፣ "ይህ አዲሱ እውነታ ነው!
4 315
🇺🇸⚡️🇮🇷 የዩናይትድ ስቴስት ኦፍ አሜሪካ ማዕከላዊ ወታደራዊ ዕዝ፣ CENTCOM 'ጠንካራ' ሲል የጠራውን ድብደባ በኢራን ላይ ማድረጉን አስታወቀ!
4 315
🇮🇷⚡️🇺🇸 ሰበር ዜና፡ በርካታ ፍንዳታዎች በደቡብ ኢራን እና በሆርሙዝ አቅራቢያ በሚገኙ ደሴቶች በመሰማት ላይ ናቸው። አሜሪካ፣ ሲጠበቅ የነበረውን ጥቃት እንደጀመረች ይታመናል።
4 315
🇷🇺⚡️🇺🇦 አውሮፓ ከሩሲያ ጋር ለመደራደር ፈቃደኛ አልሆነችም። አውሮፓ በጦርነቱ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ገብታበታለች። ለኪየቭ የገንዘብ፣ የቴክኖሎጂ እና የወታደራዊ ድጋፍ በመስጠት፣ የአየር ክልሎቿን የዩክሬን ድሮኖች በአቋራጭ ወደ ሩሲያ ጠልቀው በመግባት ጥቃት እንዲያደርሱ በመፍቀድ እና ወደ ሩሲያ ውስጥ ጥቃት የሚሰነዘርባቸውን ቦታዎችን ጨምሮ የAWACS አውሮፕላኖች መረጃን ወደ ኪየቭ እንዲተላለፉ በማድረግ፣ አውሮፓ ሩሲያን በመዋጋት ላይ ናት።
አውሮፓ አሁን በሩሲያ ላይ ስልታዊ ሽንፈት ለማድረስ በቂ ሃብት እንዳላት ታምናለች። ጦርነቱ መልኩን እንደቀየረ፣ ሩሲያ ከዓመታት በፊት ከነበረችበት እንደተዳከመች፣ ኢኮኖሚካሊ አጣብቂኝ ውስጥ እንደገባች፣ ብዙውን የኃይል መሠረተ-ልማቶቿን እና ወደ ውጭ ነዳጅ የመላክ አቅሟን እንዳጣች፣ አውሮፓ ታምናለች። በመሆኑም የውክልና ጦርነቱን እና አሻጥሮችን ማባባስ ትመርጣለች። አሁን ላይ እየታየ ባለው ውጤትም፣ አውሮፓ በቀጥታ ጦርነት ውስጥ መግባት አይጠበቅባትም።
ለአውሮፓ ቀጣዩ ዒላማ ቤላሩስ ናት። በቤላሩስ ውስጥ ለሩሲያ ያለው ድጋፍ ውስን ነው። ወጥ አይደለም። በዚህም አውሮፓ ልትበጠብጣት ይቀላታል። በርካታ የቤላሩስ ቡድኖች ከዩክሬን ጦር ጎን በመሆን ይዋጋሉ፣ በጎ ፈቃደኞችም (ቅጥረኞች) ከኪየቭ ጎን ናቸው። ይሄ የታጠቀ፣ ፀረ መንግሥት፣ ፀረ ሩሲያ ጦር ለአውሮፓ ጠቃሚ ነው። ከውስጥ ቤላሩስን ይውጧታል። ቤላሩስ ስትራቴጂካል የሆነ ጥንካሬ የላትም፣ ለድሮኖች እና ሚሳኤሎችም የተጋለጠች ናት። ሉካሼንኮ፣ ውሎ አድሮ ወደ ጎን ሊገፋ ይችላል፣ ከዚያ የሚከተለው የፊንላንድ፣ የቤላሩስ እና የዩክሬን ቀጠና የሆነ ወጥ ዞን ይሆናል፣ የሩስያን "የአውሮፓ መስኮት" ጥርቅም አድርጎ ለመዝጋት ያቀለዋል።
4 315
🇷🇺 የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የሩሲያ አትሌቶችን አስመልክቶ ለIOC ውሳኔ ምላሽ ሰጥቷል።
"ዓለም አቀፍ የስፖርት ውድድሮችን የሚያስተናግዱ ሀገሮች እና መንግሥታት፣ በግዛታቸው ላይ የሩሲያ ፌዴሬሽንን የመንግሥት ምልክቶች እንዳያሳዩ እንጠይቃለን። በዚህ ባንዲራ ሥር፣ በዩክሬን ላይ ያልተገባ ጦርነት ቀጥሏል፣ ሰላማዊ ሰዎች በየቀኑ ይገደላሉ እና የዩክሬን ከተሞች በመውደም ላይ ናቸው። የአጥቂው ግዛት ምልክቶች የስፖርት በዓል አካል ሊሆኑ አይችሉም"ሲል የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አጽንዖት ሰጥቷል።
4 315
🇺🇸❌🇮🇷 - የኢራን ዘይት ሽያጭ ፈቃድ ተሽሯል ሲል ሮይተርስ ዘገበ።
➡️ አሜሪካ የኢራን የነዳጅ ሽያጭ የሚፈቅደውን አጠቃላይ ፍቃድ እንደሰረዘች ታውቋል። ጋዜጣው ዋይት ሃውስን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ ውስጥ እየወሰደች ያለችው እርምጃና በቅርቡ የታንከሮች ጥቃቶችን ተከትሎ እየሆነ ያለውን ሁኔታ፣ "ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት የሌለው" ሲል ጠርቶታል።
➡️ እርምጃው፣ በቅርብ ቀናት ውስጥ በባሕር ዳርቻው አቅራቢያ ባልታወቁ ፕሮጀክታይሎች የተመቱ ሦስት ታንከሮችን ተከትሎ የመጣ ነው - እስካሁን ድረስ፣ ከቴህራን ምንም አስተያየት ወይም የተወሰደ ይፋዊ ኃላፊነት የለም።
4 315
🇮🇷🇸🇦የሳዑዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፡ ኢራን በሆርሙዝ ባህር ውስጥ በሚያልፈው የሳዑዲ ታንከር ላይ ጥቃት ሰንዝራለች።
ኢራን፣ ለእንደዚህ ዓይነት ጥቃቶች እና ለሚያስከትላቸው መዘዞች ሙሉ ኃላፊነቱን ትወስዳለች።
4 315
🇺🇸🇷🇺⚡️ - ከሁለቱም የአሜሪካ ሕግ አውጪዎች ቡድን (ከዲሞክራቶችና ከሪፐብሊካኖች) የተውጣጡ አባላት፣ በአንካራ እየተካሄደ ካለው የኔቶ ስብሰባ ጎን ለጎን በተደረገ ስብሰባ ላይ፣ የግምጃ ቤት ፀሐፊ ስካት ቤሴንትን ለረጅም ጊዜ የቆየውን የሩስያ ማዕቀብ ሕግን እንዲደግፍ ግፊት ማድረጋቸውን WSJ ዘግቧል።
➡️ በሊንዚ ግራሃም እና በሪቻርድ ብሉሜንታል በጋራ የተደገፈው ረቂቅ ሕግ፣ ፕሬዚዳንቱ ከሩሲያ ጋር የንግድ ሥራ በሚፈጽሙ ሀገራት ላይ ማዕቀብ እና ታሪፍ እንዲጥል ያስችለዋል ተብሏል። የሩስያ ዘይት እና ዩራኒየም ገዢዎችን፣ መንጥሮ በማውጣትም ማዕቀብ ይጥልባቸዋል። ይህም፣ ሀገራት ከሩሲያ ጋር ምንም ዓይነት የንግድ ልውውጥ እንዳያደርጉ ማረጋገጫ ይፈጥራል፣ ብለዋል።
➡️ የሕግ አውጭዎቹ፣ ቤሴንት በሩሲያ ዘይት ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ ማንሳቱን እንዳያራዝም ለማሳሰብ አቅደዋል።
4 315
🇺🇸 ብዛት ያላቸው የአሜሪካ ወታደራዊ ነዳጅ ጫኝ አይሮፕላኖች፣ በሆርሙዝ ወሽመጥ አካባቢ እየተርመሰመሱ ነው።
ቅድም እንዳልነው፣ በሚቀጥሉት 24 ወይም 48 ሰዓታት ውስጥ፣ በኢራን ላይ ድብደባ የሚደረግ ይመስላል።
4 315
🇷🇺 ኢንተርናሽናል ኦሎምፒክ ኮሚቴ (IOC) በሩሲያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ላይ ተጥሎ የነበረውን እገዳ አንስቷል። በሩሲያ አትሌቶች ላይ ሁሉንም ገደቦች ማንሳት ይገባል፣ ሲልም ምክረ ሐሳብ ሰጥቷል። IOC, "በኋላ ላይ በሩሲያ ባንዲራ እና መዝሙር ላይ ውሳኔ ለመስጠት" አቅዷል።
4 315
🇷🇺 ኢንተርናሽናል ኦሎምፒክ ኮሚቴ (IOC) በሩሲያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ላይ እገዳውን አንስቷል። በሩሲያ አትሌቶች ላይ ሁሉንም ገደቦች ማንሳት ይገባል፣ ሲልም ምክረ ሐሳብ ሰጥቷል። IOC "በኋላ ላይ በሩሲያ ባንዲራ እና መዝሙር ላይ ውሳኔ ለመስጠት" አቅዷል።
4 315
🇺🇸🚫🇮🇷 የማይቀር የሚመስል የመባባስ አደጋ፡ ዩናይትድ ስቴትስ በሚቀጥሉት 24 እና 48 ሰዓታት ውስጥ፣ በኢራን ላይ የታለመ ጥቃት ልታደርግ ትችላለች።
ይህ ጥቃት፣ በትናንትናው ዕለት በኦማን የባህር ዳርቻ ላይ በሁለት የነዳጅ ታንከሮች - አንድ የኳታር እና አንድ የሳዑዲ - 'በአሜሪካ ቁጥጥር ሥር' ባለው የባሕሩ አካባቢ በኢራን ተፈጸመ ለተባለው ጥቃት ምላሽ የሚሆን ነው። የኢራን ጦር፣ የበቀል ጥቃት ለመሰንዘር ከወዲሁ በጥብቅ እያሰበበት ነው።
4 315
🇺🇦🔹⚡️ - ዘለንስኪ በአንካራ የኔቶ ስብሰባ መሪዎች እራት ላይ ተገኝቶ ይበላል፣ ነገር ግን በሕብረቱ ስብሰባ ላይ እንዲገባ አልተፈቀደለትም - CNN
4 315
🇺🇸🇹🇷 ትራምፕ፡ በኔቶ በጣም አዝኛለሁ እና እውነቱን ለመናገር ስብሰባው፣ ጓደኛዬ - በጣም ጠንካራው መሪ፣ በጣም ጠንካራው ሰው፣ በሚመራት በቱርክ ባይካሄድ ኖሮ፣ እኔ ባልሳተፍኩ ነበር።
*-*-*-
ኤርዶጋን እንዴት ደስ ብሎት እንደሳቀ ብታዩ።
4 315
🇺🇸🇹🇷 ትራምፕ፡ በኔቶ በጣም አዝኛለሁ እና እውነቱን ለመናገር፣ ስብሰባው ጓደኛዬ - በጣም ጠንካራው መሪ፣ በጣም ጠንካራው ሰው፣ በሚመራት በቱርክ ባይካሄድ ኖሮ፣ እኔ ባልሳተፍኩ ነበር።
*-*-*-
ኤርዶጋን ደስ ብሎት በጣም ሳቀ።
4 315
🇺🇸🇹🇷🇮🇷🇮🇱⚡️ - ፕሬዝዳንት ትራምፕ ስለ ቱርክ-
ቱርክ ለእኛ ትልቅ አጋር ሆናለች። ኢራንን ጠንቅቀው ያውቋታል። እና አንዳንድ ሰዎች ከእስራኤል ጋር ስላላቸው ግንኙነት ሲናገሩ ሰምቻለሁ። በሌላኛው በኩል ወደ ትግሉ መግባት ይችሉ ነበር። እነሱ በጣም ኃይለኛ ወታደራዊ ሀገር ናቸው፣ ግን ያንን አላደረጉም ። ምናልባት በእኔ ምክንያት ያንን አላደረጉም። እነሱ በጣም በጣም ጥሩ ሀገር ሆነውልናል።
4 315
🇺🇸🇮🇹⚡️ - ጋዜጠኛ - ትናንት ከጠቅላይ ሚኒስትር ሜሎኒ ጋር በተያያዘ በ Truth Social Post ላይ "የእገዳ ትእዛዝ" ብለሃል፣ ምን ለማለት እንደፈለጉ ግልጽ ማድረግ ይችላሉ?
ትራምፕ ደህና፣ አላውቅም። በእውነቱ እሷ ጥሩ ሰው ነች ብዬ አስባለሁ። በሆርሙዝ ወሽመጥ እኛን ለመርዳት ፈቃደኛ ባለመሆኗ ትንሽ መጥፎ ሆነ፣ ወይም ከኢራን ጋር ለመሳተፍ ፈቃደኛ አልሆነችም ማለት ትችላላችሁ። ስለዚህ ከእሷ ጋር ያለኝን ግንኙነት ትንሽ አበላሸው። ግን እወዳታለሁ። በእውነቱ እሷ ጥሩ ሰው ነች ብዬ አስባለሁ። ግን ስህተት የሰራች ይመስለኛል።እንደ ትራምፕ ግን አራዳ፣ ጮሌ መሪ በዓለም ላይ አለ? ውሃ ቀቅሎ የሚበላ? በጣም አራዳ ነው፣ በደንብ የገባው።
4 315
🇺🇸🇺🇦🇷🇺⚡️ - ፕሬዝዳንት ትራምፕ በዩክሬን ጦርነት ላይ -
የጦር ሜዳዎችን አይቻለሁ። ፎቶግራፎችን ይልኩልኛል። አትላኩልኝ፣ እያልኩ ይልኩልኛል። ምን ይጠቅማል መላኩ? እላለሁ። ግን ፒት ሄግሲት ምስሎችን ይልክልኛል። አስቀያሚ፣ ዘግናኝ ናቸው። እንደዚህ ያለ ነገር አይቼ አላውቅም። እልቂት ነው እና መቆም አለበት።
4 315
🇫🇷🇸🇾 የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት፣ አማኑኤል ማክሮን፣ በደማስቆ ከተማ፣ ያረፈበት ሆቴል መግቢያ ላይ ፍንዳታ ተከስቷል።
በትናንትናው ዕለት፣ ማክሮን ከጦርነቱ በኋላ ደማስቆን የጎበኘ የመጀመሪያው የአውሮፓ መሪ ሆኗል።
በፍንዳታው የሶሪያ ቱሪዝም ሚኒስቴር የቆሰለ ሲሆን፣ የሶሪያ መንግሥት፣ ማክሮን ያደረው ሆቴል ሳይሆን ቤተ መንግሥት ነበር ብሏል።
ሮይተርስ፣ የዛሬውን ፍንዳታ "በማክሮን ላይ የተደረገ የመግደል ሙከራ" ብሎታል።
4 315
🇮🇱🇺🇸 እስራኤል ዳግም አሜሪካ ለቱርክ አየር ኃይል ምንም ነገር እንዳትሸጥላት ተማጽናለች። እስካሁን ባለው ምልከታ ግን፣ ትራምፕ ቱርክ F-35ቶችን እንድትገዛ ሊፈቅድላት እንደሆነ ነው።
