የቀጠናው ተመልካች
Open in Telegram
በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።
Show moreThe country is not specifiedThe category is not specified
4 332
Subscribers
+424 hours
-367 days
-7930 days
Posts Archive
4 332
🇺🇸🇮🇷 ኢራን ከአሜሪካ ጋር ከተደረሰው የመግባቢያ ስምምነት (MoU) ለጊዜው በይፋ መውጣቷን አስታወቀች። ለውሳኔዋ፣ አሜሪካን ሙሉ በሙሉ ተጠያቂ አድርጋለች።
"በእያንዳንዱ የስምምነት ነጥብ ላይ ጥሰት ፈጽማለች" ብላታለች፣ አሜሪካንን ኢራን።
4 332
🇮🇷❌🇺🇸🇯🇴 - የዩኤስ ማዕከላዊ ዕዝ እንዳስታወቀው፣ አርብ ዕለት በዮርዳኖስ ሁለት የአሜሪካ ወታደሮች በኢራን ባለስቲክ ሚሳኤል እና ሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃቶች ተገድለዋል።
➡️ አንድ ተጨማሪ የአሜሪካ ወታደር ጠፍቷል።
➡️ አራት የአሜሪካ ወታደሮች ለህክምና ወደ ዮርዳኖስ ሆስፒታሎች ቢወጡም፣ አሁን አገግመዋል፣ ሌሎች ደግሞ በቀላል ጉዳት የታከሙ ወደ ሥራ ተመልሰዋል።
4 332
🇮🇷🇺🇸⚡️ጦርነትና ድርድርን በአንድ ላይ የማስኬዱ ፖሊሲ አብቅቷል። በእነዚህ ተጨማሪ ሦስት ቀናት ጠላት መንገዱን ካልቀየረ፣ አጠቃላይ ጦርነት እና ጥፋት እንጀምራለን።
ሙሕሲን ረዛይ፣ የጠቅላይ መሪ ወታደራዊ አማካሪ።
*-*-*-
አሁን አሁን ሳስበው፣ ኢራን ሩሲያን በኃይልና በጉልበት ሳትበልጣት አልቀረችም። ማነው፣ "መቶ አንበሶችን (ጀግኖችን) አንድ በግ (ፈሪ፣ደካማ) ከሚመራቸው ይልቅ፣ መቶ በጎችን አንድ አንበሳ ቢመራቸው ያሸንፋሉ" ያለው?
እንደዚያ ነው። ሩሲያን የሚመሩ መሪዎች በጎች ናቸው። እንዲህ ለመቁረጥ ወኔ የላቸውም፣ አወላዋይ ናቸው። ስለዚህ ሳይወስኑ፣ ሁለት ልብ እንደሆኑ ሲቆስሉ፣ ሲደሙ፣ ሲቆረቁዙ እናያለን።
ምንም ሳይጎላቸው፣ ጉልበቱም፣ ኃይሉም እያላቸው፣ መሪ የላቸውምና ወደ ሽንፈት ጎዳና ያመራሉ። አንበሳ የሚመራት ሚጢጢ ዩክሬን፣ ታንበረክካታለች።
በእርግጥ የሚሆን አይመስልም ሲወራ፣ ግን እየሆነ ነው።
ሩሲያ አመራሮቿን ወይም አቅጣጫዋን በቶሎ ካልቀየረች፣ ጉድ ትሆናለች። ይሄ የእኔ ምልከታ ነው።
ኢራን ዩክሬንን ብትገጥም፣ ብላችሁ አስቡት ለማሰብ ያህል፣ ሩሲያ እየተንደፋደፈች እንዳለችው ትንደፋደፍ ነበር? ሩሲያስ፣ አሜሪካ እና እስራኤል ጦርነት ቢከፍቱባት… ?
4 332
⚡️🇮🇷/ 🇺🇸🇦🇪 የኢራን ፋርስ የዜና ወኪል የደህንነት ምንጭን በመጥቀስ - "አሜሪካ ዛሬ ማታ በኢራን የሚገኙትን የሲቪል መሠረተ ልማቶች ካጠቃች፣ በሀገሪቱ ውስጥ ያሉትን ዜጎች ሕይወት ለመጠበቅ የዱባይ እና የአቡ ዳቢ አየር ማረፊያዎች እንዲሁም የፉጃይራ እና የጀበል አሊ ወደቦች በአስቸኳይ መለቀቅ አለባቸው።
4 332
🇸🇦⚡🇮🇷 ሳዑዲ አረቢያ አሜሪካ ከመካ በ70 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘውን የአየር ማረፊያ በኢራን ላይ ለሚደረጉ ወታደራዊ ዘመቻዎች እንድትጠቀም ፈቅዳለች IRIB
*-*-*-
አሁን በሐጃጆች አናት ላይ ሚሳዬል ቢያልፍ ተጠያቂው ማነው? ሳዑዲ ኢራን መቼም ይሄን አታደርገውም ብላ ነው ከመካ በቅርብ ርቀት ጦር ሰፈር ለአሜሪካ ፈቅዳ የኢራንን ድልድዮችና መሠረተ ልማቶች የምታስፈርሰው? ኢራን ብታደርገው አላህ ይቆጣታል? ታደርገዋለች ከቻለችበት!
4 332
🇺🇸🇸🇦🇮🇷 - ዋይት ሃውስ ኢራን በሳውዲ አረቢያ በሚገኘው የአሜሪካ ጦር ሰፈር ላይ ባለስቲክ ሚሳዬሎችን እንደተኮሰች ተናግሯል። ይህ ኢራን በአራት ወራት ውስጥ በሳውዲ አረቢያ ላይ የፈፀመችው የመጀመሪያው ቀጥተኛ ጥቃት ነው። - AXIOS
4 332
🇮🇷⚡️🇺🇸 የኢራን IRGC,
በሆስፒታሎች፣ በድልድዮች፣ በባቡር ሀዲዶች፣ በአውሮፕላን ማረፊያዎች፣ በወደቦች፣ በመገናኛ ማዕከላት እና በሌሎች የሲቪል መሠረተ ልማቶች ላይ፣ የአሜሪካንን ጥቃት ለማስቆም ፈቃደኛ የሆነ ወይም የሚችል ዓለም አቀፍ አካል ባለመኖሩ፣ የቁርኣንን ትእዛዝ ከመከተል ውጪ ሌላ አማራጭ የለንም - "ቀኝህን ሲመቱህ፣ ግራቸውን አጣፋላቸው (ቢያጠቁህ፣ እንዳጠቁህ አጥቃቸው)። እንዲህም ሆኖ ግን፣ ለአሜሪካ አገዛዝ ዕድል ለመስጠትና አካሄዱን እንዲቀይር እንዲያስብ ለማስቻል፣ ጥቃቶቻችንን ወታደራዊ ዒላማዎች ላይ ብቻ ለመገደብ ወስነናል። ለጊዜው ነው!
4 332
🇮🇷🇺🇸⚡️እንደ ሌላ ጊዜዎች፣ ጦርነቱ እስከ አሁን አላባራም። ኢራን በዮርዳኖስ፣ በባሕሬን፣ በሰሜን ኢራቅ፣ በሳዑዲ ዓረቢያ፣ በኩዌት እና በኤሜሬት በሚገኙ ወታደራዊ ዒላማዎች ላይ፣ እንዲሁም በሆርሙዝ ወሽመጥ፣ ጥቃቷን እንደቀጠለች ነው። ፍንዳታዎች፣ ጭሶች፣ እሳቶች እና ያልተቋረጡ ሳይረኖች አየሮቻቸውን አጨናንቀዋል።
በሌላ በኩልም፣ አሜሪካ ድብደባውን ጋብ አላደረገችም። በአሁኑ ሰዓትም እየደበደበች ትገኛለች።
ኢራን ሰፊ ሀገር ከመሆኗ ጋር፣ የእስራኤል በጦርነቱ ያለመኖር አሜሪካንን ለጥጦ ያሰቃያት ይመስላል። አሜሪካ በድብደባዋ እስካሁን መሸፈን የቻለችው ባሕር ዳርቻዎችን እና በደቡብ ኢራን አንዳንድ ቦታዎችን ብቻ ነው። ኢራንን ጠልቃ ገብታ ማጥቃት የቻለች አይመስልም።
የኢራን ሚሳዬል መተኮሻዎች፣ በብዛት የሚገኙት በምዕራብ፣ በማዕከላዊው እና በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ነው፣ ስለሆነም አሜሪካ ሁሉንም በአንዴ መሸፈን ባለመቻሏ፣ የኢራን የሚሳዬል ጥቃት ከአሜሪካ ጥቃት በላይ ሊያይል ችሏል።
እስራኤል ብትኖር፣ ምሥራቁን፣ ማዕከላዊውን እና ሰሜኑን የኢራንን ክፍል ስትሸፍንላት (የኢራንን ሚሳዬል የማስወንጨፍ አቅም ማፈን)፣ አሜሪካ ሊቀላት ይችል ነበር።
የሚገርመው፣ ዋና ከተማዋ ቴህራን ከተመታች ወራቶች ተቆጠሩ። እስራኤል እያለች ግን፣ ቴህራን በየቀኑ ትጠቃ ነበር።
አሜሪካ ኢራንን መደብደብ ብቻ አይደለም የገጠማት እክል፣ አረብ ሀገሮችንም መከላከል ነው።
በሌላ በኩል፣ የኢራን በርካታ ሀገሮችን በአንዴ በማጥቃት መግጠም መቻል፣ የሚያስገርም አቅም ነው።
ጦርነቱ ያለበትን ሁኔታ በስሱ ያስዳስሳል በሚል ነው።
4 332
🇮🇷🇺🇸⚡️እንደ ሌላ ጊዜዎች፣ ጦርነቱ እስከ አሁን አላባራም። ኢራን በዮርዳኖስ፣ በባሕሬን፣ በሰሜን ኢራቅ፣ በሳዑዲ ዓረቢያ፣ በኩዌት እና በኤሜሬት በሚገኙ ወታደራዊ ዒላማዎች ላይ፣ እንዲሁም በሆርሙዝ ወሽመጥ፣ ጥቃቷን እንደቀጠለች ነው። ፍንዳታዎች፣ ጭሶች፣ እሳቶች እና ያልተቋጡ ሳይረኖች አየሮቻቸውን አጨናንቀዋል።
በሌላ በኩልም፣ አሜሪካ ድብደባውን ጋብ አላደረገችም። በአሁኑ ሰዓትም እየደበደበች ትገኛለች።
ኢራን ሰፊ ሀገር ከመሆኗ ጋር፣ የእስራኤል በጦርነቱ ያለመኖር አሜሪካንን ለጥጦ ያሰቃያት ይመስላል። አሜሪካ በድብደባዋ መሸፈን የቻለችው ባሕር ዳርቻዎችን እና በደቡብ ኢራን አንዳንድ ቦታዎችን ብቻ ነው። ኢራንን ጠልቃ ገብታ ማጥቃት የቻለች አይመስልም። የኢራን ሚሳዬል መተኮሻዎች በብዛት የሚገኙት በምዕራብ፣ በማዕከላዊው እና በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ነው፣ ስለሆነም አሜሪካ ሁሉንም በአንዴ መሸፈን ባለመቻሏ፣ የኢራን የሚሳዬል ጥቃት ከአሜሪካ ጥቃት በላይ ሊያይል ችሏል።
እስራኤል ብትኖር፣ ምሥራቁን፣ ማዕከላዊውን እና ሰሜኑን የኢራንን ክፍል ስትሸፍንላት (የኢራንን ሚሳዬል የማስወንጨፍ አቅም ማፈን)፣ አሜሪካ ሊቀላት ይችል ነበር።
አሜሪካ ኢራንን መደብደብ ብቻ አይደለም የገጠማት እክል፣ አረብ ሀገሮችንም መከላከል ነው።
በሌላ በኩል፣ የኢራን በርካታ ሀገሮችን በአንዴ በማጥቃት መግጠም መቻል፣ አቅም የሚያስገርም አቅም ነው።
4 332
🇮🇷⚡️🇺🇸🇯🇴 CBS: ኢራን በዮርዳኖስ ጦር ሰፈሮች ላይ ባደረጉት ጥቃት በርካታ የአሜሪካ ወታደሮች ቆስለዋል።
የአሜሪካ ባለስልጣናት ለCBS እና New York Times እንዳሉት፣ ኢራን በዚህ ሳምንት በዮርዳኖስ ቢያንስ ሁለት የአሜሪካ ጦር ሰፈሮች ላይ ኢላማ ማድረጓን እና በጥቃቱ በርካታ የአሜሪካ ወታደሮች ቆስለዋል።
4 332
🇺🇸🇺🇸❌🇮🇷 - MEHR NEWS: ከአፍታ በፊት በሀጂያባድ እና በባንዳር አባስ መካከል ዋነኛው የመጓጓዣ መንገድ የሆነው የሻሂድ ሚርዛይ ዋሻ፣ በከፍተኛ ሁኔታ በቦምብ የተደበደበ ሲሆን ዋሻው ሙሉ በሙሉ ወድሞ በሁለቱም አቅጣጫዎች ወድቋል።
እንዲሁም፣ ሚናብን ከባንዳር አባስ ጋር የሚያገናኘው ስልታዊ ጠቀሜታ ያለው ድልድይም በቦምብ ተመትቶ ወድሟል።
*-*-*-
አሜሪካ የሕዝብ መሠረተ-ልማቶችን ወደ መምታት phase ገብታለች ማለት ነው። ትናንትና በኢራን ከ6-8 ድልድዮችን እንዳወደመች ተነግሯል።
4 332
🇺🇸🇮🇷⚡ - "አሜሪካ በኢራን ላይ ካቀደችው አዲስ ስትራቴጂ አንፃር፣ ኢራን መላውን ክልል ለሚያጠቃልል ረዘም ላለ ጊዜ ግጭት በዝግጅት ላይ ትገኛለች።
አሜሪካና እስራኤልን የሚያግዙ የአረብ መንግሥታት፣ በዚህ 'የመጥፋት ጦርነት' የመጀመሪያ ሰለባዎች ይሆናሉ" - IRGC ኮማንደር ለIRIB NEWS።
4 332
+1
🇺🇦⚡️በዩክሬን፣ መከላከያ ሚኒስትሩ ያለ ምንም ተጨባጭ ምክኒያት እና በድንገት፣ ከሥልጣኑ በዘለንስኪ መነሳቱን በመቃወም፣ ዛሬም ሰልፎች ተደርገው ውለዋል። ፀረ-ዘለንስኪ ይዘት እያየለባቸውም መጥቷል።
የዩክሬን ቻናሎች እና ታዋቂ ግለሰቦች፣ ሰልፈኞቹን፣ "እባካችሁ፣ የሩሲያ መጠቀሚያ እንዳትሆኑ" እያሉ ለማስጠንቀቅ ቢሞክሩም፣ ሌሎች ግን፣ "ይበቃል!" ብለው ሰልፉ እንዲቀጥል እያበረታቱ ናቸው።
ሰልፎች፣ በበርካታ የዩክሬን ከተሞች፣ ተደርገው ውለዋል።
4 332
🇮🇷/🇮🇶 ኢራን፣ በሰሜን ኢራቅ በሚገኙ ተገንጣይ ኩርዶች ላይ ከፍተኛ ጥቃት ከፍታ ውላለች። በጥቃቱ የመሳሪያ ግምጃ ቤትን ጨምሮ፣ ሌሎች በርካታ ወታደራዊ ዒላማዎች ተመተዋል። የጥቃቱ ሥፋትና ይዘት ለብዙዎች አስገራሚ ነበር።
በኢራቅ የኩርድ መንግሥት እንዳለው፣ እስካሁን በውል ያልታወቁ፣ ወደ መቶ የሚጠጉ ተዋጊዎቹ ጠፍተውበታል።
ኢራን፣ በኢራቅ የሚገኙ የኩርድ ወታደራዊ ዒላማዎችን፣ ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ እና አሜሪካ እና እስራኤል ኩርዶችን በመጠቀም ኢራንን ለመውረር አስበው ነበር፣ ከተባለበት ጊዜ ጀምሮ፣ ያለማቋረጥ ጥቃት ሲሰነዝሩባቸው ቆይተዋል።
