en
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

Open in Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

Show more
The country is not specifiedThe category is not specified
4 332
Subscribers
+424 hours
-367 days
-7930 days
Posts Archive
+3
🇮🇷/🇮🇶 ኢራን፣ በሰሜን ኢራቅ በሚገኙ ተገንጣይ ኩርዶች ላይ ከፍተኛ ጥቃት ከፍታ ውላለች። በጥቃቱ የመሳሪያ ግምጃ ቤትን ጨምሮ፣ ሌሎች በርካታ ወታደራዊ ዒላማዎች ተመተዋል። የጥቃቱ ሥፋትና ይዘት ለብዙዎች አስገራሚ ነበር። በኢራቅ የኩርድ መንግሥት እንዳለው፣ እስካሁን በውል ያልታወቁ፣ ወደ መቶ የሚጠጉ ተዋጊዎቹ ጠፍተውበታል። ኢራን፣ በኢራቅ የሚገኙ የኩርድ ወታደራዊ ዒላማዎችን፣ ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ እና አሜሪካ እና እስራኤል ኩርዶችን በመጠቀም ኢራንን ለመውረር አስበው ነበር፣ ከተባለበት ጊዜ ጀምሮ፣ ያለማቋረጥ ጥቃት ሲሰነዝሩባቸው ቆይተዋል።

🇷🇺 ይሄ ይችላል ቢያንስ፣ ተሽቀንጥሮ አልወደቀም። አፍሪካዊ አይመስለኝም፣ ቺቺኒያዊ ይሆን?

🇮🇷🇸🇦🇵🇰⚡ - "ከኢራን ጋር የተያያዘው የሁቲ ንቅናቄ፣ ሰኞ ዕለት በሳውዲ አረቢያ ላይ ጥቃት ከሰነዘረ በኋላ፣ የኒውክሌር ታጣቂዋ ፓኪስታን ለኢራን መንግሥት፣ በሳዑዲ ላይ የሚደርሰውን ማንኛውንም ጥቃት በራሷ ላይ እንደሚደርስ እንደምትቆጥረው በመናገር አስቦካክታለች" - ሮይተርስ።

🇮🇷⚡️🇧🇭 ምሽቱን የተመታው የባሕሬን ትልቁ ነዳጅ ማጣሪያ BAPCO, አሁንም ድረስ እየነደደ ነው። ጭሱ፣ ከተማውን ሸፍኖት ይታያል።

🇮🇷🇦🇪⚡️የUAE መከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ፡ የታሰረ ትንሽ ማገዶ እንጨትና ተከማችቶ የነበረ ደረቅ ቁጥቋጦ፣ በሸክ ዛይድ ጦር ሰፈር ውስጥ በእሳት ተቃጥሎ ነበር። የእሳት አደጋ ሰራተኞች በጊዜ
+1
🇮🇷🇦🇪⚡️የUAE መከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ፡ የታሰረ ትንሽ ማገዶ እንጨትና ተከማችቶ የነበረ ደረቅ ቁጥቋጦ፣ በሸክ ዛይድ ጦር ሰፈር ውስጥ በእሳት ተቃጥሎ ነበር። የእሳት አደጋ ሰራተኞች በጊዜ ደርሰው አጥፍተውታል። ለሚያስፈልግ ማንኛውም ኢንፖርሜሽን እኛ ጋር ብትመጡ፣ እውነቱን እንዲህ እንነግራችኋለን።

🇮🇷⚡️🇦🇪 የዩናይትድ አረብ ኤሜሬት መከላከያ ሚኒስቴር፣ በሸክ ዛይድ ወታደራዊ ከተማ ውስጥ፣ የተቃጠለ ትንሽ ማገዶ እንጨትና ደረቅ ቁጥቋጦ ነበር፣ እሳት አደጋዎች በቦታው ደርሰው አጥፍተዋል …
🇮🇷⚡️🇦🇪 የዩናይትድ አረብ ኤሜሬት መከላከያ ሚኒስቴር፣ በሸክ ዛይድ ወታደራዊ ከተማ ውስጥ፣ የተቃጠለ ትንሽ ማገዶ እንጨትና ደረቅ ቁጥቋጦ ነበር፣ እሳት አደጋዎች በቦታው ደርሰው አጥፍተዋል … ለምትፈልጉት ኢንፖርሜሽን እኛን ጠይቁን።

❗️🇮🇷/ 🇦🇪 ሰበር ዜና፡ የሳተላይት ምስሎች እንደሚያሳዩት፣ በሼክ ዛይድ ወታደራዊ ከተማ፣ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ሦስት ጠንካራ የማከማቻ ተቋማት፣ በኢራን ጥቃት ሙሉ በሙሉ ወድመዋል። ተቋማቱ፣ የአሜሪካን ብሎም የኤሜሬትን ሚሳዬሎችን፣ ማስወንጨፊያዎችን እና የተለያዩ ተተኳሾችን የያዙ ነበሩ ተብሏል።

🇮🇷🇺🇸⚡️ፕሬዚዳንት ትራምፕ ኢራንን በድጋሚ አሸንፈዋል! ፕሬዝዳንት ትራምፕ ምሽቱን ለአሜሪካ ሕዝብ፡
አሜሪካ በቅርቡ ከኢራን ጋር በተፈጠረው ግጭት ተጠቃሚ ትሆናለች - በጦር ሰራዊታችን ላይ ሪከርድ መጠን ኢንቨስት እያደረግን ነው፣ እና ዛሬ በዓለም ላይ በጣም ጠንካራው ወታደር አለን። በመጀመሪያው የስልጣን ዘመኔ ነው የገነባሁት፣ እና በሚያሳዝን ሁኔታ፣ አሁን ልንጠቀምበት እንገደዳለን። አሁን፣ በሚሊዮን የሚቆጠር በርሜል ዘይት ከቬንዙዌላ እየዛቅን ነው፣ አሸንፈናላ። በኢራን ውስጥም ትልቅ ድሎችን እያገኘን ነው፣ እና የዚህን የጉልበት ፍሬ በጣም እና በቅርቡ እናጣጥመዋለን።

🇮🇷⚡️🇧🇭/ 🇸🇦 ኢራን ባሕሬን እና ሳዑዲ አረቢያን የሚያገናኘውን የኪንግ ፋህድ ድልድይን ኢላማ አድርጋለች። *-*-*- ያነቡናል ማለት ነው? ይከታተሉናል እንዴ IRGCዎች? ሄደናል ማለት
🇮🇷⚡️🇧🇭/ 🇸🇦 ኢራን ባሕሬን እና ሳዑዲ አረቢያን የሚያገናኘውን የኪንግ ፋህድ ድልድይን ኢላማ አድርጋለች። *-*-*- ያነቡናል ማለት ነው? ይከታተሉናል እንዴ IRGCዎች? ሄደናል ማለት ነው ከሚጠበቀው በላይ፣ ኧረ ቀስ በል! ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ፣ እረ ይሄ ድልድል ስንል ነበር። ተሰማን። ድልድዩ ተቆረጠ ማለት ሳዑዲ ከባሕሬን ተቆረጠች ማለት ነው፣ ፓትሮል ነድታ በባሕሬን የውስጥ ጉዳይ እንደልቧ ጣልቃ አትገባም። ከዛ ኢራን ቀስ ብላ ባሕሬንን ታንቃታለች፣ ኳስ በመሬት ብላ።

🇮🇷🇺🇸⚡️ኢራን፣ በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ እና በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙትን የዶናልድ ትራምፕ ንብረቶችን፣ ለጥቃት ሕጋዊ ኢላማ አድርጋ አውጃለች፣ ሲል IRGC (እስላማዊ አብዮታዊ ጥበቃ ጓዶች)
🇮🇷🇺🇸⚡️ኢራን፣ በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ እና በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙትን የዶናልድ ትራምፕ ንብረቶችን፣ ለጥቃት ሕጋዊ ኢላማ አድርጋ አውጃለች፣ ሲል IRGC (እስላማዊ አብዮታዊ ጥበቃ ጓዶች) በሰጠው መግለጫ ገልጿል። እነዚህም የሚከተሉትን ያካትታሉ ትራምፕ ኢንተርናሽናል ሆቴል እና ታወር (ዱባይ)፣ ትራምፕ ፕላዛ (ጂዳ) እና ትራምፕ ታወር (ሪያድ)።

🇮🇷🇺🇸⚡️ትናንት እንዳልኩት፣ ኢራን ቆርጦላት ባሕሬንን ወይም ኩዌትን (ሁለቱንም በሂደት) የማትወር ከሆነ፣ አዝናለሁ፣ ኢራንን በእነዚህ በሁለት ሀገሮች በኩል ትወራታለች። ይቅደሙ ወይስ ይቀደሙ? የሚወሯቸው ከሆነ፣ በቀጠናው የአሜሪካ የጀርባ አጥንት፣ ሙሉ በሙሉ ይሰበራል። የማይወሯቸው ከሆነ ግን፣ በእነዚህ ነጥብ በሚያክሉ ሀገሮች በኩል፣ ዘላለማቸው ሲደሙ ይኖራሉ። ሁለቱንም ሀገሮች የምታዝበት አሜሪካ ነች፣ መሪዎቻቸው እና ሕዝባቸው ነገ ጠዋት ተነስተው 'አይ በቃ!' ቢሉ እንኳ፣ አይችሉም፣ ድምጣቸውንም፣ ኃይላቸውንም ተቀምተዋልና። ስለዚህ፣ ያለው አማራጭ ወረራ ነው። የማይቻል አይደለም። ትናንት እንዳነሳሁት፣ ሳዳም ኩዌትን በሁለት ሰዓታት መውረር ችሏል። ባሕሬኖች ሺዓ ስለሆኑ፣ ኢራኖች 'እንመጣለን' ቢሉ፣ ሕዝቡ እራሱ ከውስጥ ይነሳል።

🇮🇷🇺🇸⚡️ብዛት ያላቸው የኢራን ሚሳዬሎች፣ በዮርዳኖስ፣ በባሕሬን፣ በኩዌት ሰማዮች ላይ። ተጨማሪ ሚሳዬሎች ወደ ቦታዎቹ ተተኩሰዋል።

🇲🇾🇮🇱 የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስቴር አንዋር ኢብራሒም፡ በማሌዢያ የሚኖሩ እስራኤላዊያን ዜጎች እንደታወቁ፣ ያለ ምንም ቅድመ-ሁኔታ ወደ ሀገራቸው ይጠረዛሉ፣ ሲል አውጇል።
+1
🇲🇾🇮🇱 የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስቴር አንዋር ኢብራሒም፡ በማሌዢያ የሚኖሩ እስራኤላዊያን ዜጎች እንደታወቁ፣ ያለ ምንም ቅድመ-ሁኔታ ወደ ሀገራቸው ይጠረዛሉ፣ ሲል አውጇል።

🇺🇸🇮🇷 Trump: ኢራንን የዛሬ 47 ዓመት በመታናት ኖሮ፣ ዛሬ እንዲህ ባልከበደችን ነበር።

🇷🇺🇺🇦⚡️የዩክሬን የኔቶ ስፖንሰሮች ጥቁር ባሕርን ወደ ሩሲያ ሆርሙዝ ለመቀየር እየሞከሩ ናቸው። የአሜሪካ ሚዲያዎችም፣ ዩክሬን በአዞቭ ባሕር ላይ የጀመረችውን የድሮን ዘመቻ በድል አድራጊነት እየዘገቡላት ነው። CNN "ሩሲያ ወደ ጥቁር ባሕር መግቢያ በር ላይ ያላት ቁጥጥር እየተንሸራተተ ነው" ሲል፣ እንደ Washington Post ዓይነቶቹ፣ ዩክሬን ክራይሚያን ለመቁረጥ እና የሩስያ መርከቦችን ለማደናቀፍ ያለመውን ጦርነቷን፣ "አስገራሚ ስኬት" እያሉ ይገልጹታል። የዩክሬን ጦር፣ ሩሲያ ፔትሮሊየም ምርቶችን ለማጓጓዝ የምትጠቀምባቸውን፣ Shadow Fleet በመባል የሚጠራው አካል የሆኑትን፣ ከ100 በላይ መርከቦችን በአዞቭ ባሕር ውስጥ ኢላማ አድርጎ እንደመታና ብዙዎቹን እንዳይጓዙ አድርጎ እንደሰበረ ያወራል። "ይህ ገና ጅምር ነው" ብሏል።

🇮🇷🇺🇸⚡️ኢራን፣ በሁሉም አቅጣጫ ወደ ኩዌት መተኳኮስ ጀምራለች። በኩዌትም፣ በቀጥታ የመታችው የራዳር እና የHIMARS ሚሳዬል ሲስተሞች እንዳሉ በሚወጡ መረጃዎች እየተነገረ ነው። ተከታታይ ፍን
+4
🇮🇷🇺🇸⚡️ኢራን፣ በሁሉም አቅጣጫ ወደ ኩዌት መተኳኮስ ጀምራለች። በኩዌትም፣ በቀጥታ የመታችው የራዳር እና የHIMARS ሚሳዬል ሲስተሞች እንዳሉ በሚወጡ መረጃዎች እየተነገረ ነው። ተከታታይ ፍንዳታዎችም ጥቃቱን ተከትሎ ተሰምተዋል። የኢራን የአየር ትራንስፖርት ባለሥልጣን በበኩሉ፣ የሀገሩ አየር ክልል ሙሉ በሙሉ እንዲዘጋ ወስኗል። የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫዎች፣ ድልድዮች፣ አየር ማረፊያዎች እና ሌሎች መሠረተ ልማቶች፣ እስካሁን ባለው መረጃ፣ የአሜሪካ የጥቃት ሰለባ ሆነዋል። በሁለቱም በኩል ውጊያውን የማቆም አዝማሚያ አይታይም።

🇺🇸🇮🇷⚡️የአሜሪካ F-35 ጀት፣ ምሽቱን፣ የአደጋ ጊዜ ጩኸት እያሰማ በኩዌት ለማረፍ ተገዷል።
🇺🇸🇮🇷⚡️የአሜሪካ F-35 ጀት፣ ምሽቱን፣ የአደጋ ጊዜ ጩኸት እያሰማ በኩዌት ለማረፍ ተገዷል።

+1
🇮🇷🇺🇸⚡️ትራምፕ፣ በቀጣይ 'መሠረተ-ልማት ማፍረስ' የሚለውን ቃሉን ጠበቀ ይሆን? ዛሬ ምሽቱን፣ በዚህች ሰዓት፣ የአሜሪካ ጦር ኃይሎች በኢራን ላይ ከፍተኛ ድብደባ እየፈጸሙ ናቸው። እስከ አሁን ድረስ ከተመቱት መካከል፣ በሆርሞዝጋን እና በኮርስታን ክፍለ ሀገሮች የሚገኙ፣ ሁለት ቁልፍ ድልድዮች ይገኙበታል።