en
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

Open in Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

Show more
The country is not specifiedThe category is not specified
4 332
Subscribers
+424 hours
-367 days
-7930 days
Posts Archive
🇮🇷 IRGC ምሽቱን ባወጣው መግለጫ …
🇮🇷 IRGC ምሽቱን ባወጣው መግለጫ …

photo content
+2

🇺🇸 በአሜሪካ አዘጋጅነት ሲካሄድ የቆየው የዓለም ዋንጫ ማለቁ ይታወቃል። ስፔንም አሸንፋለች። በስፔን (የቀድሞ ገዢ) ማሸነፍ መላው ላቲን አሜሪካ ደስተኛ ነው። ላቲኖች ለአርጀንቲና በታሪክ ብዙም ፍቅር የላቸውም። ዘረኛ፣ ከሀገሩ ሕዝብ ይልቅ ለፈረንጅ ባዕዳን የሚሰግዱ፣ እያሉ ያሟቸዋል። አርጀንቲናዎች በበኩላቸው፣ ላቲኑ የሚጠላን እና የሚቀናብን፣ ሀብታም ስለሆንን፣ እኛን ፈልጎ ለሥራ ስለሚሰደድ፣ ሁልቀን ሥጋ ስለምንበላ፣ ሀገራችን በመሰልጠኑ ነው ይላሉ። ያም ሆኖ፣ መላው ላቲን በአርጀንቲና ሽንፈት ደስተኛ ነው። በተቃራኒው፣ በአርጀንቲና መሸነፍ አይሁድ እስራኤል አዝኗል። አርጀንቲና የብዙ አይሁዶች መኖሪያ በመሆኗ፣ የአሁኑ መንግሥትዋ ግንባር ቀደም የእስራኤል ደጋፊ በመሆኑ፣ ፕሬዝዳንትዋ ዣቪየር ሜሊ አይሁድ በመሆኑ - ካቶሊክ ነኝ እያለ ቢፎግርም - እና ኔታንያሁን ጨምሮ የእስራኤል ባለሥልጣናት፣ አርጀንቲና እንድታሸንፍ ፍላጎታቸውን ሲያንፀባርቁ በመክረማቸው፣ የአርጀንቲና ሽንፈት ለአይሁድ እስራኤል ሐዘን ነው። በሌላ በኩል ደግሞ፣ በስፔን ማሸነፍ መላው አረብ ተደስቷል። ስፔን በምዕራቡ ዓለም አንደኛ ፀረ- እስራኤል መንግሥት ሀገር ሆናለች። አውሮፓ በታሪክ ጠንካራ የፍልስጤም ደጋፊ እና የእስራኤል ነቃፊ ቢሆንም፣ ስፔን ያንን ታሪካዊ የአውሮፓ አቋም ሺ ጊዜ አብልጣ ከፍ አድርገዋለች። በሁሉም መንግሥታዊ እና ሕዝባዊ ፖሊሲዎቿ፣ ባሁኑ ጊዜ፣ ስፔን ከእስራኤል በተፃራሪ የቆመች ሆናለች። ስፔን የእስልምና ታሪኳም ሰፊ ነው። በዚህና በሌሎችም ተመሳሳይ ምክኒያቶች፣ የአረቡ ዓለም በስፔን ማሸነፍ ጮቤ ረግጧል። ስፔን ለአሜሪካ የኢራን ጦርነት፣ አየሬንም፣ ውሃዬንም፣ አላስጠቅምም ማለቷ እና የአሜሪካን ጦር ከሀገሯ ማስወጣቷ፣ በብዙ ዓለም ዘንድም አስከብሯታል። አውሮፓዊያን ደግሞ፣ ጎረቤታቸው ስፔን በማሸነፏ ደስተኛ ሆነዋል። ጥያቄ የለውም። የሚገርመው፣ አውሮፓዊያን አንድ ወር በነበራቸው የአሜሪካ ቆይታ፣ በሁሉም ነገር፣ በሚበላውም፣ በሚጠጣውም፣ በቤቱም፣ በመንገዱም፣ በሳሩም በባሕሉም፣ በስርዓቱም፣ በሀብቱም … ብቻ በአጠቃላይ አሜሪካ፣ እንዲህም ያለ ሀገር አለ እንዴ? ብለው እጃቸውን አፋቸው ላይ ጭነው ሲገረሙ ነው የከረሙት። ዩቲዩብ እና ኢንስትግራም በእንዲህ ያሉ ቪዲዮዎች ተጨናንቀው ይገኛሉ። አዎ፣ እንደ አሜሪካ ዓይነት በረከቱ የተትረፈረፈለት ሀገር፣ እውነት ነው፣ በምድር ላይ የለም። አሜሪካኖች በበኩላቸው፣ የዓለም ዋንጫ በመጠናቀቁ ደስተኛ ናቸው። አሁን "እፎይ፣ የማንወደውን ስፖርት እንደምንወደው መስለን መንቀሳቀሱ አበቃልን" እያሉ እየቀለዱ ናቸው። ብዙ ሚምስ፣ ብዙ ጽሑፍ እንዲህ በማለት እያወጡ ናቸው። ከብዙ አንግል፣ የዘንድሮ የዓለም ዋንጫ የተዋጣለት ነበር።

🇪🇸 የስፔን እስላማዊ ሪፐብሊክ ጄኔራል ፌራን ቶረስ፣ በአርጀንቲና ላይ ግብ አስቆጥሯል።
🇪🇸 የስፔን እስላማዊ ሪፐብሊክ ጄኔራል ፌራን ቶረስ፣ በአርጀንቲና ላይ ግብ አስቆጥሯል።

🇮🇱🇺🇸⚡️🇮🇷 እስራኤል ወደ ጦርነቱ መልሳ ለመግባት በከፍተኛ ሁኔታ ቋምጣለች። አሜሪካ ብቻዋን ጦርነቱን ስላልቻለችውም፣ እስራኤል በሰበባ ሰበብ እንድትገባ እና ድብደባዋን እንድትጀምር እየወተወተቻት ይገኛል። መግቢያ ሰበብ ቢያጡ፣ አሜሪካ እስራኤልን ገና ለገና "አያቶላህ ሙጅተባ ጥቃት ሊሰነዝርብኝ እያሰበ ነው" በሚል ምክኒያት፣ ወደ ጦርነቱ እንድትገባ ለማስቻል ዳር ዳር እያሉ ናቸው። ኢራን በገልፍ ሀገራት ላይ ጥቃቶቿን እንደቀጠለች ነው። በኩዌት፣ በባሕሬን እና በዮርዳኖስ ላይ፣ በአሁኑ ሰዓት ጥቃት ከፍታለች። የኃይል ማመንጫዎች፣ የኤሌክትሪክ ሰብ ስቴሽኖች እና የውሃ ማጣሪያዎች በኩዌትና በባሕሬን፣ እንዲሁም የአየር ማረፊያዎች እና ጦር ሰፈሮች በዮርዳኖስ እየተጠቁ ናቸው። አሜሪካም በበኩሏ፣ ከጠዋት ጀምሮ እስከ አሁን በዘለቀ ጥቃት፣ ኢራንን እየመታች ትገኛለች።

🇮🇷🇺🇸⚡️አያቶላህ ኻመኒይ፡ - የተከበሩ ፕሬዝዳንት፣ ዋነኛ ጠላትዎ ማነው? - አምሪካ

🇮🇷🇺🇸⚡️የኩዌት አየር ኃይል ሁለት የዩሮተዋጊ ታይፎን ጀቶች፣ በዓሊ አል ሠሊም አየር ማረፊያ የጠነከረ የአውሮፕላን መጠለያዎች ላይ ባነጣጠረ የኢራን ባለስቲክ ሚሳኤል ጥቃት፣ ወድመዋል - Al
🇮🇷🇺🇸⚡️የኩዌት አየር ኃይል ሁለት የዩሮተዋጊ ታይፎን ጀቶች፣ በዓሊ አል ሠሊም አየር ማረፊያ የጠነከረ የአውሮፕላን መጠለያዎች ላይ ባነጣጠረ የኢራን ባለስቲክ ሚሳኤል ጥቃት፣ ወድመዋል - Al Mannar

🇮🇷❌🇯🇴🇺🇸 - The New York Times እንደዘገበው፣ ኢራን በዮርዳኖስ ላይ ያደረገችው ጥቃት "ከፍተኛ ቁጥር" ያላቸው የዩኤች-60 ብላክ ሃውክ ሄሊኮፕተሮችን አበላሽቷል። እንደ WSJ
🇮🇷❌🇯🇴🇺🇸 - The New York Times እንደዘገበው፣ ኢራን በዮርዳኖስ ላይ ያደረገችው ጥቃት "ከፍተኛ ቁጥር" ያላቸው የዩኤች-60 ብላክ ሃውክ ሄሊኮፕተሮችን አበላሽቷል። እንደ WSJ ዘገባ ከሆነ ደግሞ፣ ኢራን በዮርዳኖስ ላይ ባደረገችው ጥቃት፣ ሰው ሰራሽ እና ሰው አልባ አውሮፕላኖች ኢላማ ተደርጓል። አንድ ምንጭ እንደገለጸው፣ ኢራን በሙዋፋክ ሳልቲ አየር ማረፊያ ላይ ባደረገችው ጥቃት፣ የዩኤስ አየር ኃይል (USAF) F-15E አድማ ንስር ወድሟል፣ ሌሎች በርካታ አውሮፕላኖች ተጎድተዋል።

🇺🇦⚡️🇷🇺 አዳዲስ ሚሳኤሎች ወደ ኪየቭ እያመሩ ነው፣ ጦርነቱ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ባለስቲክ ሚሳኤሎች ወደ ኪየቭ ተተኩሰዋል። የሩስያ ጦር በአንድ ሰአት ውስጥ ወደ 50
🇺🇦⚡️🇷🇺 አዳዲስ ሚሳኤሎች ወደ ኪየቭ እያመሩ ነው፣ ጦርነቱ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ባለስቲክ ሚሳኤሎች ወደ ኪየቭ ተተኩሰዋል። የሩስያ ጦር በአንድ ሰአት ውስጥ ወደ 50 የሚጠጉ ሚሳኤሎችን በዩክሬን ዋና ከተማ ጥሏል።

📢 🇸🇾 🇮🇷 የሶሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከቅርብ ቀናት ወዲህ ኢራን በባሕረ ሰላጤው ጎረቤቶቻቸው ላይ የምታደርገውን የታደሰ እና የተስፋፋ ጥቃት አውግዟል፣ ጥቃቱን "የሀገራትን ሉዓላዊነት በ
📢 🇸🇾 🇮🇷 የሶሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከቅርብ ቀናት ወዲህ ኢራን በባሕረ ሰላጤው ጎረቤቶቻቸው ላይ የምታደርገውን የታደሰ እና የተስፋፋ ጥቃት አውግዟል፣ ጥቃቱን "የሀገራትን ሉዓላዊነት በግልፅ መጣስ እና ለደህንነታቸው እና መረጋጋታቸው ቀጥተኛ ስጋት ነው" በማለትም ተናግሯል 📎 *-*-** አሃ፣ ታዲያ ኢራን ዝም ብላ ብቻ ትመታ እንዴ? አትመልስ ምንም? በነገራችን ላይ ከጥቂት ቀናት በፊት ማንም ብዙም ሲዘግበው ያልታየ ክስተት በሶሪያ ሆኗል። ኢራን ለመጀመሪያ ጊዜ በሶሪያ የአሜሪካ ጦርን ድብቅ ሰፈር ደብድባለች። ብዙዎች ያልዘገቡት አሜሪካ በሶሪያ ውስጥ ጦር ሰፈር የላትም፣ ከየት የመጣ ነው በሚል ነው። ኢራን ግን፣ የደረሰችበት ነገር አለ፣ አሜሪካ በድብቅ፣ ይፋ ያላደረገችው፣ በሶሪያ ውስጥ የምትዘውራቸው፣ የድሮን ቤዞች፣ የደህንነት መ/ቤቶች እና command and control ጣቢያዎች እንዳሏት ደርሳበት አጥቅታታለች። ምናልባት ሶሪያ ደንግጣ ነው ይሄን መግለጫ ያወጣችው።

የፓኪስታን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በድጋሚ "የኢስላማባድ የመግባቢያ ስምምነት (MoU) መከበር እና ተጨማሪ መባባስ መወገድ እንዳለበት ተናገረ።" በመካሄድ ላይ ባለው የአሜሪካ እና የኢራን ግጭት፣ ሁሉም ወገኖች ከማባባስ ከፍተኛ ጥንቃቄ እና እቀባ እንዲያደርጉም አሳስቧል። ከአንድ ቀን በፊት፣ ሐምሌ 17 ቀን፣ ፓኪስታን በሳውዲ አረቢያ ላይ የሚደርስ ማንኛውም ጥቃት በፓኪስታን ላይ እንደደረሰ አድርጋ እንደምትቆጠር ማስጠንቀቋ የሚታወስ ነው፣ እናም ለሪያድ ያላትን የፀጥታ ቃል በድጋሚ አረጋግጣለች።

🇺🇸🇮🇷 ኢራን ከአሜሪካ ጋር ከተደረሰው የመግባቢያ ስምምነት (MoU) ለጊዜው በይፋ መውጣቷን አስታወቀች። ለውሳኔዋ፣ አሜሪካን ሙሉ በሙሉ ተጠያቂ አድርጋለች። "በእያንዳንዱ የስምምነት ነጥብ ላይ ጥሰት ፈጽማለች" ብላታለች፣ አሜሪካንን ኢራን።

🇮🇷⚡️የአሜሪካ ወታደሮች የሞቱበት የትናንቱ የኢራን ጥቃት በዮርዳኖስ።

🇮🇷🇺🇸⚡️የቀድሞ የአሜሪኣ አየር ኃይል አብራሪ፡ ቆስለው ሆስፒታል ከተጓጓዙት መካከል ከ3-5 የሚሆኑት የሚተርፉ አይመስለኝም።
🇮🇷🇺🇸⚡️የቀድሞ የአሜሪኣ አየር ኃይል አብራሪ፡ ቆስለው ሆስፒታል ከተጓጓዙት መካከል ከ3-5 የሚሆኑት የሚተርፉ አይመስለኝም።

🇺🇸⚡️🇮🇷 የአሜሪካ ጦር ሚኒስቴር፣ ፒት ሄግሲት፣ ጦርነቱን ለማባባስ ዝቷል።
🇺🇸⚡️🇮🇷 የአሜሪካ ጦር ሚኒስቴር፣ ፒት ሄግሲት፣ ጦርነቱን ለማባባስ ዝቷል።

🇮🇷❌🇺🇸🇯🇴 - የዩኤስ ማዕከላዊ ዕዝ እንዳስታወቀው፣ አርብ ዕለት በዮርዳኖስ ሁለት የአሜሪካ ወታደሮች በኢራን ባለስቲክ ሚሳኤል እና ሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃቶች ተገድለዋል። ➡️ አንድ
🇮🇷❌🇺🇸🇯🇴 - የዩኤስ ማዕከላዊ ዕዝ እንዳስታወቀው፣ አርብ ዕለት በዮርዳኖስ ሁለት የአሜሪካ ወታደሮች በኢራን ባለስቲክ ሚሳኤል እና ሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃቶች ተገድለዋል። ➡️ አንድ ተጨማሪ የአሜሪካ ወታደር ጠፍቷል። ➡️ አራት የአሜሪካ ወታደሮች ለህክምና ወደ ዮርዳኖስ ሆስፒታሎች ቢወጡም፣ አሁን አገግመዋል፣ ሌሎች ደግሞ በቀላል ጉዳት የታከሙ ወደ ሥራ ተመልሰዋል።

🇮🇷🇺🇸⚡️ጦርነትና ድርድርን በአንድ ላይ የማስኬዱ ፖሊሲ አብቅቷል። በእነዚህ ተጨማሪ ሦስት ቀናት ጠላት መንገዱን ካልቀየረ፣ አጠቃላይ ጦርነት እና ጥፋት እንጀምራለን። ሙሕሲን ረዛይ፣ የጠቅላይ መሪ ወታደራዊ አማካሪ። *-*-*- አሁን አሁን ሳስበው፣ ኢራን ሩሲያን በኃይልና በጉልበት ሳትበልጣት አልቀረችም። ማነው፣ "መቶ አንበሶችን (ጀግኖችን) አንድ በግ (ፈሪ፣ደካማ) ከሚመራቸው ይልቅ፣ መቶ በጎችን አንድ አንበሳ ቢመራቸው ያሸንፋሉ" ያለው? እንደዚያ ነው። ሩሲያን የሚመሩ መሪዎች በጎች ናቸው። እንዲህ ለመቁረጥ ወኔ የላቸውም፣ አወላዋይ ናቸው። ስለዚህ ሳይወስኑ፣ ሁለት ልብ እንደሆኑ ሲቆስሉ፣ ሲደሙ፣ ሲቆረቁዙ እናያለን። ምንም ሳይጎላቸው፣ ጉልበቱም፣ ኃይሉም እያላቸው፣ መሪ የላቸውምና ወደ ሽንፈት ጎዳና ያመራሉ። አንበሳ የሚመራት ሚጢጢ ዩክሬን፣ ታንበረክካታለች። በእርግጥ የሚሆን አይመስልም ሲወራ፣ ግን እየሆነ ነው። ሩሲያ አመራሮቿን ወይም አቅጣጫዋን በቶሎ ካልቀየረች፣ ጉድ ትሆናለች። ይሄ የእኔ ምልከታ ነው። ኢራን ዩክሬንን ብትገጥም፣ ብላችሁ አስቡት ለማሰብ ያህል፣ ሩሲያ እየተንደፋደፈች እንዳለችው ትንደፋደፍ ነበር? ሩሲያስ፣ አሜሪካ እና እስራኤል ጦርነት ቢከፍቱባት… ?

⚡️🇮🇷/ 🇺🇸🇦🇪 የኢራን ፋርስ የዜና ወኪል የደህንነት ምንጭን በመጥቀስ - "አሜሪካ ዛሬ ማታ በኢራን የሚገኙትን የሲቪል መሠረተ ልማቶች ካጠቃች፣ በሀገሪቱ ውስጥ ያሉትን ዜጎች ሕይወት ለመጠበቅ የዱባይ እና የአቡ ዳቢ አየር ማረፊያዎች እንዲሁም የፉጃይራ እና የጀበል አሊ ወደቦች በአስቸኳይ መለቀቅ አለባቸው። 

🇸🇦⚡🇮🇷 ሳዑዲ አረቢያ አሜሪካ ከመካ በ70 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘውን የአየር ማረፊያ በኢራን ላይ ለሚደረጉ ወታደራዊ ዘመቻዎች እንድትጠቀም ፈቅዳለች IRIB *-*-*- አሁን በሐጃጆች አናት ላይ ሚሳዬል ቢያልፍ ተጠያቂው ማነው? ሳዑዲ ኢራን መቼም ይሄን አታደርገውም ብላ ነው ከመካ በቅርብ ርቀት ጦር ሰፈር ለአሜሪካ ፈቅዳ የኢራንን ድልድዮችና መሠረተ ልማቶች የምታስፈርሰው? ኢራን ብታደርገው አላህ ይቆጣታል? ታደርገዋለች ከቻለችበት!

🇮🇷⚡️🇵🇰🇸🇦 ነይ አንቺ ፓኪስታን፣ ኢራን ሳዑዲን መታታለች አንድ ነገር አድርጊ። ስትፎክሪ አልነበር ጠዋት?