fa
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

رفتن به کانال در Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
4 321
مشترکین
+824 ساعت
-47 روز
-7130 روز
آرشیو پست ها
🇩🇿🇦🇪⚡- "የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶችን ለማቋረጥ የተደረገውን ውሳኔ እንዲያከብሩ እና ሀገራችንን ለቅቀው እንዲወጡ፣ ለዩኤኢ አምባሳደር እና ኤምባሲ ሠራተኞች፣ 48 ሰዓታትን ሰጥተናል" - የአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር። *-*-* የአረቦች እርስ በእርስ መጠላላት፣ መሻኮት እና ጦር መማዘዝ፣ በሀገር እና በመንግሥት ደረጃ፣ መረን ለቋል። አረቦች አንድ ዓይነት ሕዝብና ተመሳሳይ ሥነ-ልቦና ያላቸው ናቸው የሚለውን አስተሳሰብ፣ (ምናልባት እንዲህ ዓይነት አስተሳሰብ ከብዙዎች፣ እነሱን ከውጭ ብቻ ከሚያውቋቸው ይንጸባረቃል) ገደል የከተተና የሰባበረ ነው። አሁን ያለው ሁኔታቸው ግን በቅርበት ለሚያውቃቸው እንኳ እጅግ አስደንጋጭ ደረጃ የደረሰ ነው።

+1
🇺🇦🇷🇺⚡️በሞስኮ በሚገኘው የብሪታንያ ኤምባሲ ውስጥ የሚሠራ ዘበኛ ተይዟል፣ እሱም በ SBU (የዩክሬን የደህንነት ቢሮ) የተመለመለ ሲሆን ስለ ዲፕሎማሲያዊው ተልዕኮ የደህንነት ሥርዓት ለዩክሬን ደህንነት መረጃ እየሰበሰበ እንደነበር ተነግሯል። 🇺🇦 የዩክሬን ተቆጣጣሪዎቹ በሞስኮ የሚገኘው ኤምባሲ እና የብሪታንያ አምባሳደር መኖሪያ ቤት እንዴት ጥበቃ እንደሚደረግላቸው፣ መክፈቻ ቁጥሮቹ እና ካርዶቹ ምን ያህ እንደሆኑ፣ የቁጥጥር እርምጃዎች እስከምን እንደሚደርሱ፣ በመኖሪያ ቤቱ ግቢ ውስጥ የሚካሄዱ ዝግጅቶች እና የደህንነት ሰራተኞች ብዛት፣ ወዘተ ን ለማወቅ ፍላጎት ነበራቸው። ➡️ በታሰረው ሰው መሠረት፣ መረጃው የዩክሬን ባለስልጣናት በብሪቲሽ ዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮ ላይ የሽብር ጥቃቶችን ለማዘጋጀት ያስፈልጋቸው ነበር፣ ይህም፣ ከዚያ በኋላ ለክስተቶቹ ሃላፊነት በሞስኮ ላይ እንዲወሰድ በሚያስችል መንገድ ሊቀረጽ ነበር።

🇩🇿/🇦🇪 አልጄሪያ ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ጋር የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷን ለማቋረጥ መወሰኗን አስታውቃለች። 'የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን ለማቆየት የሚያስችሉ ሁሉም መንገዶች ተሟጠዋል'፣ ከሚለው በስተቀር ምንም ኦፊሴላዊ ምክንያት አልገለጸችም። የአልጄሪያ የመንግስት ሚዲያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስን በብሔራዊ እና በቀጠናዊ ጉዳዮች ውስጥ ጣልቃ የምትገባ ረብሻ ፈጣሪ ኃይል እና የጽዮናውያን አሻንጉሊት ብሎ ጠርቷታል።

🇺🇸/🇮🇷 ፕሬዝዳንት ትራምፕ፦ '
ኢራን ይሄኔ የኒውክሊየር መሳሪያ ቢኖራት ኖሮ፣ ለበላዩ መሪ ደውዬ፣ 'እንዴት ኖት ጌታዬ፣ ሠላም ናችሁ? ልንረዳዎ የምንችለው ነገር አለ?' እል ነበር (ከማጎብደድ ተርፈናል!)

🇮🇱🇬🇧⚡️ — የእስራኤል የዲያስፖራ ጉዳዮች ሚኒስትር አሚቻይ ቺክሊ፦ ለብሪቲሽ ሕዝብ፣ ግልጽ ላድርግ፦ እኛ በእስራኤል ያለነው እናፍቃችኋለን፣ እና ስሙ አሁን ከአእምሮዬ የጠፋው፣ የእናንተ የው
🇮🇱🇬🇧⚡️ — የእስራኤል የዲያስፖራ ጉዳዮች ሚኒስትር አሚቻይ ቺክሊ፦
ለብሪቲሽ ሕዝብ፣ ግልጽ ላድርግ፦ እኛ በእስራኤል ያለነው እናፍቃችኋለን፣ እና ስሙ አሁን ከአእምሮዬ የጠፋው፣ የእናንተ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ በሚያወጣው ማዕቀቦች በምንም ዓይነት አንደናገጥም። ለአሁን ደካማ የግራ ክንፍ መንግሥት አላችሁ። ነገር ግን በብሪቲሽ ሕዝብ መካከል ባሉ ጓደኞቻችን ላይ እምነት አለን፣ እነዚያ አሁንም ከእኛ ጋር የጋራ እሴቶችን የሚጋሩ የሆኑ። የተሻሉ ቀናት ይመጣሉ። በእናንተ ላይ የሸሪዓ ሕግን ለመጫን በሚፈልጉት በዓለም አቀፋዊያን እና በእስላማዊያን ላይ አንድ ላይ በጋራ እንቆማለን። እናም፣ እነዚያ ቀናት በቅርቡ እየመጡ ናቸው።

🇸🇦/🇾🇪 በየመን የሁቲ ፕሬዝዳንት በአሁኑ ጊዜ በምዕራባዊው የባሕር ዳርቻ ላይ ለሚዋጉ ሁሉም በሳውዲ ለተደገፉ የPLC ኃይሎች ይቅርታ እንደሚያደርጉላቸው አስታውቀዋል፣ ጦር መሳሪያዎቻቸውን አሳ
🇸🇦/🇾🇪 በየመን የሁቲ ፕሬዝዳንት በአሁኑ ጊዜ በምዕራባዊው የባሕር ዳርቻ ላይ ለሚዋጉ ሁሉም በሳውዲ ለተደገፉ የPLC ኃይሎች ይቅርታ እንደሚያደርጉላቸው አስታውቀዋል፣ ጦር መሳሪያዎቻቸውን አሳልፈው ለአንሳረላህ (ሁቲ) ከሰጡ ብቻ! ያ የማይሆን ከሆነ፣ እንደሚደመሰሱ አስጠንቅቋል!

🇮🇷🇺🇸⚡️ — የኢራን ፓርላማ ብሔራዊ የደህንነት ኮሚሽን ኃላፊ፣ ኢብራሂም አዚዚ፦ የኢራን የባሕር ኃይል ግልጽ መልእክት ልኳል፦ የፋርስ ባሕረ-ሰላጤ ደህንነት እና መረጋጋት በኢራን የሚተዳደር
🇮🇷🇺🇸⚡️ — የኢራን ፓርላማ ብሔራዊ የደህንነት ኮሚሽን ኃላፊ፣ ኢብራሂም አዚዚ፦
የኢራን የባሕር ኃይል ግልጽ መልእክት ልኳል፦ የፋርስ ባሕረ-ሰላጤ ደህንነት እና መረጋጋት በኢራን የሚተዳደር ነው። ለቀሩት ኃይሎች፦ ከነመሳሪያዎቻችሁ የቀረውን አድኑና በምችሉበት መንገድ ወደ ሀገራችሁ ተመለሱ፣ እና የራሳችሁን ድንበሮች በመከላከል ላይ አተኩሩ!

🇺🇸🇹🇷🇸🇦🇵🇰🇾🇪⚡️ — የሪፐብሊካን ተወካይ ጆ ዊልሰን፦ የመካ መከላከያ አሊያንስ በአንዱ ላይ የሚደረግ ጥቃት በሁሉም ላይ የሚደረግ ጥቃት ነው ይላል — አሁን ቱርክ፣ ፓኪስታን እና
🇺🇸🇹🇷🇸🇦🇵🇰🇾🇪⚡️ — የሪፐብሊካን ተወካይ ጆ ዊልሰን፦
የመካ መከላከያ አሊያንስ በአንዱ ላይ የሚደረግ ጥቃት በሁሉም ላይ የሚደረግ ጥቃት ነው ይላል — አሁን ቱርክ፣ ፓኪስታን እና ሳዑዲ አረቢያ ሁቲዎችን የሚያጠፉበት ጊዜ ነው። ነጣነት ለየመን!

🇸🇦/🇾🇪 የሳውዲ ግንባር ቀደም ደጋፊ እና ተጽእኖ ፈጣሪ፣ ሳሊም አል-ሙሳቢ፣ በየመን በሳዑዲ የሚደገፉት ኃይሎች በዛሬ ውጊያ መደምሰሳቸውን ተከትሎ፦ 'ግታ ሆይ፣ ጦርነት በቃችሁ በለን፣ የሁሉን
🇸🇦/🇾🇪 የሳውዲ ግንባር ቀደም ደጋፊ እና ተጽእኖ ፈጣሪ፣ ሳሊም አል-ሙሳቢ፣ በየመን በሳዑዲ የሚደገፉት ኃይሎች በዛሬ ውጊያ መደምሰሳቸውን ተከትሎ፦ 'ግታ ሆይ፣ ጦርነት በቃችሁ በለን፣ የሁሉንም ደም ጠብቅ። ይበቃናል! ወደ ሠላም መንገድ ተመለሱ።'

+1
ሰበር | 🇺🇦 🇷🇺 — የዩክሬን ድሮኖች ከሪከርድ በላይ በሆነ የ3,300 ኪ.ሜ በረራ በሩሲያ የአርክቲክ ጋዝ ተቋምን አጥቅተዋል። የዩክሬን ድሮኖች በሩሲያ ያማሎ-ኔኔትስ ኦቶኖሚያል ኦክሩግ ውስጥ በሚገኘው ማጣሪያ ፋብሪካ ላይ በሴፕቴምበር 9 ጥቃት በመሰንዘር በጋዝፕሮም ፋሲሊቲ ላይ እሳት አነድደዋል። የጠቅላይ ግዛቱ ገዥ ዲሚትሪ አርትዩኮቭ ክስተቱን አረጋግጧል። ፋብሪካው በዓመት ወደ 19.5 ሚሊዮን ቶን የሚጠጋ ድፍድፍ የማጣራት አቅም አለው። በክልሉ የጋዝ-ኮንደንሴት መሠረተ ልማትም ውስጥ ቁልፍ አካል ነው። አካባቢው አብዛኛውን የሩሲያ የተፈጥሮ ጋዝ ምርት ይይዛል። በአካባቢው ላይ ሪፖርት የተደረገው የመጀመሪያው የድሮን ጥቃት እንደሆነም ነው የተዘገበው። የጉዳቱ መጠን አሁንም እየተገመገመ ነው።

🇸🇦🇾🇪❌🇾🇪 — ሁቲዎች (አንሳርአላህ) የሳዑዲ የጦር አውሮፕላኖች ባለፉት 12 ሰዓታት ውስጥ በአል-ጃውፍ፣ ማዕሪብ፣ ታይዝ፣ አል-ሁደይዳ፣ ሳዓዳ እና አል-ባይዳ ግዛቶች ላይ 48 የአየር ጥቃቶችን እንዳካሄዱ ተናግረዋል። ከኪንግ ኻሊድ አየር ማዕከል የመጡ የF-15S ተዋጊ አውሮፕላኖች የአየር ድብደባዎቹን እንዳካሄዱ፣ ከኪንግ ፋህድ አየር ማዕከል ደግሞ አንድ የታይፉን ተዋጊ በአል-ጃውፍ ላይ ጥቃት እንዳካሄደ ተናግረዋል። ሁቲዎች የበቀል እርምጃ ለመውሰድ ቃል ገብተዋል።

🇾🇪🇸🇦⚡- የሁቲ አንሳሩላህ ድሮኖች በሳዑዲ ግዛቶች በአሁኑ ሰዓት ገብተዋል። በደቡብ ሳዑዲ ዓረቢያ የማንቂያ ደውሎች እየጮኹ ናቸው።

⚡️🇵🇰🇸🇦🇾🇪  ፓኪስታን በሳዑዲ አረቢያ ጥያቄ መሠረት በየመን ውስጥ በሚገኙት ሁቲዎች ላይ የአየር ጥቃት ለመሰንዘር በቁም ነገር እያሰበችበት ነው። የፓኪስታን ምንጮች እንደገለጹት፣ በአሁኑ ሰዓት ኢስላማባድ ከሳዑዲ አረቢያ እና ከቱርክ ጋር የገባችውን የመካ የጋራ መከላከያ ስምምነትን ለመተግበር፣ እየተንቀሳቀሰች ነው። ምንጮቹ እንደገለጹት፣ ጥቃቶቹ በቀናት ውስጥ ሊጀምሩ ይችላሉ። አንዱ ዓላማ ሁቲዎችን ከሳዑዲ ድንበር አቅራቢያ ካለችው ዋና ማዕከላቸው፣ ሰዓዳ ከተማ፣ ማስወጣት ነው። ነገር ግን፣ የመጨረሻው ውሳኔ እስካሁን አልተወሰነም። ክስተቱ የተከሰተው የፓኪስታን የመከላከያ ሚኒስትር ካዋጃ አሲፍ የሁቲ ጥቃት ወይም የየመን ግጭት ወደ ሳዑዲ አረቢያ መስፋፋት የመካ ስምምነትን ተግባራዊ ያደርገዋል ብለው ከተናገሩ በኋላ ነው። ስምምነቱ፣ ከሦስቱ አባላት በአንዱ ላይ የሚሰነዘር ጥቃት በሦስቱም ላይ እንደ ጥቃት እንደሚቆጠር ይገልጻል።

🇩🇪 የAfD አሊስ ዊዴል ጀርመን ከሩሲያ ጋር የሰላም ድርድር እንድትጀምር ጥሪ አቅርባለች። 'አሜሪካ ጦርነቱን ለማቆም ሌላ ሙከራ እያደረገች ባለችበት ጊዜ፣ የኛዎቹ የጦርነት ፕሮፓጋንዳን እና ከሩሲያ ጋር ግጭትን እያጠናከሩ ናቸው፣ ብላለች።' አያይዛም፣ ይህን የሚያደርጉት 'ከራሳቸው አደገኛ የፖለቲካ ሪከርድ ትኩረትን ለማዞር ነው፣ የያዙት የመጨረሻዎቹን ድልድዮች ማፍረስ ነው' ስትል ተናግራለች። ቀኝ ዘመም ኮንሰርቫቲቩ AfD፣ ከፍተኛ መነጋገሪያ በነበረው የሰሞኑ የጀርመን ምርጫ፣ ብዙ መቀመጫዎችን በማሸነፍ ከጀርመን ባለፈ በመላው አውሮፓ ከፍተኛ ንዝረትን ለቋል። ፓርቲው፣ ለሩሲያ እና ለፑቲን በተለየ እዝነት እና ክብር ያለው ፓርቲ ነው፣ እንደ ነቃፊዎቹ መረጃ።

🇺🇸🇮🇷🇺🇦 ዘለንስኪ አሜሪካንን የፔትሪዮት ሚሳዬል ሲጠይቃት ዓመት አለፈው፣ ጨርሰናል፣ እባክሽን የተወሰነም ቢሆን ስጪን ሲላት። አሜሪካ ለራሴም የለኝም ነው ያለችው። ዘለንስኪ ከአውሮፓ ሕብረት ሀገሮች ፔትሪዮት ሚሳዬሎችን ሲጠይቅ እንዲሁ፣ ብዙ ጊዜው። የለንም ጨርሰናል፣ ምናልባት ግሪክና ስፔን አንድ 20 ቢኖራቸው እንዲሰጡህ እንጠይቅልሃለን ነበር ያሉት። ግሪክም ስፔንም ሲጠየቁ ለራሳችን ያስፈልገናል እምቢ ብለው ነግረውታል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ነው እንግዲህ፣ ዛሬ ሌሊቱን ብቻ፣ በግማሽ ቀን ውስጥ፣ አሜሪካ በዮርዳኖስ ከ100 በላይ ፔትሪዮት ሚሳዬሎችን በኢራን ሚሳዬሎች ላይ ተኩሳ ያደረችው። Imagine የዘለንስኪን ንዴት!

🇺🇸🇮🇷🇺🇦 ዘለንስኪ አሜሪካንን የፔትሪዮት ሚሳዬል ሲጠይቃት ዓመት አለፈው፣ ጨርሰናል  የተወሰነም ቢሆን ስጪን ሲላት። ዘለንስኪ ከአውሮፓ ፔትሪዮት ሚሳዬሎችን ሲጠይቅ እንዲሁ ብዙ ጊዜው። የለንም ጨርሰናል፣ ምናልባት ግሪክና ስፔን አንድ 20 ቢኖራቸው እንዲሰጡህ እንጠይቅልሃለን ሲሉት ነበር፣ አውሮፓ ሕብረት። ግሪክም ስፔንም እምቢ ብለው ነግረውታል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ነው እንግዲህ፣ ዛሬ ሌሊቱን ብቻ አሜሪካ በዮርዳኖስ ከ100 በላይ ፔትሪዮት ሚሳዬሎችን በኢራን ሚሳዬሎች ላይ ተኩሳ ያደረችው። Imagine የዘለንስኪን ንዴት!

+1
🇮🇷🇺🇸⚡️ዮርዳኖስ