የቀጠናው ተመልካች
Open in Telegram
በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።
Show moreThe country is not specifiedThe category is not specified
4 330
Subscribers
-924 hours
-407 days
-8130 days
Posts Archive
4 333
🇸🇦🇺🇸⚡️— የሳዑዲ የመከላከያ ሚኒስትር፣ ልዑል ካሊድ ቢን ሰልማን፣ ዛሬ ቀደም ብሎ በዋሽንግተን ከምክትል ፕሬዝዳንት JD Vance ጋር ተገናኝተዋል፣ እንደ CNN ዘግቧል።
➡️ ልዑል ካሊድ በቅርቡ ስለተካሄዱት የጋራ ጥቃቶች እና በመሠረተ ልማቷ ላይ ለተደረጉ ጥቃቶች ሳውዲ አረቢያ ስለሰጠችው ምላሽ፣ ተነጋግረዋል፣ እንዲሁም ከዘውድ ወራሹ ልዑል መሐመድ ቢን ሰልማን የግል መልእክት አስተላልፏል።
➡️ የሳዑዲ አመራር፣ ኢራን በተጨማሪ በአካባቢው በተለያየ መንገድ ተጽዕኖ ለማሳደር ትፈልጋለች፣ ሁኔታው በአደገኛ ሁኔታ አንዣቧል፣ ኢራንም ከጊዜ ወደ ጊዜ በእሷ በሚደገፉ ቀጠናዊ ታጋዮችን፣ በኢራቅ እና ሁቲዎችን (አንሳራላህ) በየመን፣ በመጠቀም በመላው ቀጠናው ጫና እየጨመረች ነው ብሏል።
*-*-*-
ሚንስትሩ፣ ለምን ከማርኮ ሩቢዮ ይልቅ ጄዲ ቫንስን ለመገናኘት እና መልዕክቱን ለእሱ ለመስጠት መረጠ?
በኢራን ጦርነት ምክኒያት JD Vance እና ማርኮ ሩቢዮ ቁርሾ ውስጥ ገብተዋል።
በጦርነቱ እና በውጭ ፖሊሲው፣ የፕሬዝዳንቱን ብዙውን ውሳኔዎቹን የሚያዘውረው ጄዲ ቫንስ ነው። ጦርነቱን አርግበው፣ ተደራደር፣ ውጣ እና የመሳሰሉትን የሚለው።
በዚህም ምክኒያት ምክትል ፕሬዝዳንቱ በጦርነት አቀንቃኞች፣ የጦርነቱን መባባስ በሚደግፉ ታዋቂ ሰዎች እና በእስራኤል ጥርስ ውስጥ ገብቷል። በይፋ እየወጡም ማርኮ ሩቢዮ ምርጫቸው እንደሆነ እስከመናገር እየደረሱ ናቸው።
የውሳኔው ቁልፉ ግን አሁንም JD Vance እጅ ላይ ነው፣ በስልጣንም የሩቢዮ አለቃ ነው፣ የሚሰነዘሩበት ትችቶች ከዓላማው አላሳቱትም፣ ከማርኮ ሩቢዮ በላይም አሁንም የፕሬዝዳንቱ ጆሮ ያለው ለእሱ ነው።
እና፣ የሳዑዲው ሚንስትር JD Vanceን ምን ሊለው ፈልጎ ከማርኮ ሩቢዮ ይልቅ ተገናኘው? ደብዳቤውስ?
4 333
🇺🇦🇮🇱 ኔታንያሁ ዘለንስኪን፣ ከሌሎች ጋር በነበረው ምስጢር ንግግር "ምስጋና ቢስ ዲቃላ" ብሎታል ብለዋል።
ኔታንያሁ በተጨማሪም፣ ትናንት በአሜሪካ ዘለንስኪን በግል ለማግኘት አልፈቀደም ነበር። ዘለንስኪም "ችግርህ ምንድነው" ያለው ሲሆን፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪዎች "የፕሮግራም መደራረብ" ስላለበት ሊገናኝህ አይችልም፣ ብለውታል።
4 333
🇺🇸🇪🇬 አንድ ድሮን በግብፅ የሜዲትራኒያን የዳሚዬታ ወደብ የአሜሪካ ባለቤትነት ያለው የጋዝ ማጠራቀሚያ ታንከርን መታ። መርከቡ በአሁኑ ሰዓት እየተቃጠለ ነው። ድሮኑን ማን ይተኩሰው፣ ከየት ይምጣ የታወቀ ነገር የለም። እስካሁን ሃላፊነቱን የወሰደ አካል የለም - ሮይተርስ
*-*-*-
ግብጥ ደንግጣ፣ ከሽንት ቤት የተነሳ እሳት አደጋ ነው እያለች ነው። ድሮን… ሞተር ክፍል… ፍንዳታ… በእሳቱ ዘመን … ግብጥ ብትረጋጋ ጥሩ ነው።
ሳዑዲ በቀይ ባሕር ስትከለከል በግብጥ ሜድትሬንያን ዞራ፣ ሩቅ ቢሆንም፣ አዲስ መስመር መጠቀም ጀምራ ነበር፣ ከሰሞኑ።
4 333
🇺🇸🇸🇦❌🇮🇶— አስቸኳይ ዜና፦ CENTCOM, አሜሪካ እና ሳዑዲ አረቢያ በኢራቅ ላይ የአየር ጥቃት መፈጸማቸውን አረጋግጧል።
*-*-*-
'ሳዑዲዎች ከአሜሪካ ጋር በመሆን ኢራቅን ደበደቡ' ሲባሉ ተቆጥተው ነበር፣ እኛ ብቻችንን፣ ራሳችንን ችለን ነው፣ የደበደብነው ብለው።
አልነበረም!
ሳዑዲ ብቻዋን እንደመታች ተደርጎ እንዲቆጠርላት ፈልጋ ነበር። አሜሪካ ግን አይሆንም ብላለች።
አሜሪካን መከተል እንጂ፣ ከአሜሪካ ተነጥላ አማፂ የመዋጋት አቅም የላትም ሳዑዲ።
አጠቃላይ የገልፍ አረቦች እንደዚያ ናቸው፣ አቅም የላቸውም። እነ ሶሪያ አቅም ነበራቸው፣ እነ ኢራቅ አቅም ነበራቸው፣ ግብፅ አቅም አላት። ገልፎችና ሳዑዲ ግን የሉበትም።
በአንድ በኩል ፈሪ መሆናቸው ጠቅሟቸዋል ብሎ የሚያስብ አለ፣ ምክኒያቱም ሌሎቹ (ሶሪያ፣ ኢራቅ፣ ሊቢያ… ) ሲጠፉ እነሱ አሉና።
በሌላ በኩል ደግሞ፣ እድሜ ዘመናቸውን ለምዕራባዊያን፣ በተለይ ለአሜሪካ፣ በካዳሚነትና በአስተናጋጅነት በመኖር አርጅተዋል።
"ከዘላለም ባርነት፣ የአንድ ቀን ነፃነት" ያለው ማን ነበር? እንደዚያ ነው?
4 333
🇸🇦🇺🇸⚡️🇮🇶🇮🇷 ሰበር ዜና፣ ሁለት አረብ ሀገሮች እርስ በርሳቸው መዋጋት ጀመሩ። ሳዑዲ ከአሜሪካ እርዳታ ጋር ጦርነቱን ጀምራለች። በአሁኑ ሰዓትም ኢራቅን እያጠቃች ነው።
ባስራ፣ ነኒቪህ፣ ባግዳድ እና ሰመራ የተለያዩ ዒላማዎች ተመትተዋል ተብሏል።
የሳዑዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፦
በኢራን የሚደገፉ ሚሊሻዎች አግባብነት የሌለው እና የሚያባብስ አካሄድ መርጠዋል። በኢራቅ ውስጥ ለኢራን ታማኝ በሆኑ ሚሊሻዎች ላይ የተደረጉት ጥቃቶች መንግሥቱ የመመለስ መብት ላይ በመመስረት የተካሄዱ ነበሩ።የኢራቅ ጠቅላይ ሚኒስቴር፣ ሳዑዲ ዓረቢያ ኢራቅን በጠላትነት መፈረጇ አዲስ እንዳልሆነ እና ታሪካዊ መሆኑን በመጥቀስ፣ ለደረሰባት ያልተጠበቀ ጥቃት፣ ኢራቅ፣ አፀፋዊውን እርምጃ እንደምትወስድ አስገንዝቧል። ከጥቂት ሰዓታት በፊት፣ የኢራቅ ባለስልጣናት፣ ሳዑዲን የደበደቡት የመኖች ሆነው ሳለ፣ ሳዑዲ ግን ኢራቅን ማውገዟ ከህመምተኛ አእምሮ መሆኑንና የመንን ለመደብደብ ያስፈራት ነገር እንዳልገባቸው ተናግረው ነበር።
4 333
🇺🇸🇮🇷 አሜሪካ፣ ባሻት እና በፈለገችው ሰበብ፣ ቀድማ ማጥቃት ልምድ አላት። ካጠቃች በኋላ ሌላው እንደ አቅሙ በመልስ ምት ለመመለስ ይሞክራል። በኢራን ጦርነት ይሄ ሲሆን ነው የቆየው፣ ኢራን ከተጠቃች በኋላ ነው የምትመልስ የነበረው።
ባለፈው ሳምንት ጀምሮ፣ የኢራን መንግሥት አቀንቃኞች፣ ለምን እንደ ዳክዬ እስክንመታ ቁጭ ብለን እንጠብቃለን? እንዲያ መሆን የድክመት ምልክት ነው፣ እኛም አስፈላጊ መስሎ ሲታየን ቀድመን ልናጠቃ ይገባል፣ እያሉ በቻናሎቻቸው ሲወያዩ ነበር።
ይሄ ሆኖ ይሆን? ከሆነ፣ የኃይል ሚዛኑ እጅግ በጣም ከፍተኛ በሆነ መንገድ ወደ ኢራን ማዘንበሉን ያሳያል።
አሜሪካን በወታደራዊ ጥቃት፣ በአካል፣ ቀድሞ ማጥቃት አይደለም፣ ማሰቡ በራሱ ከባድ ነው። ኢራን ይሄንን ሳይክል ሰበረችው?
4 333
🇮🇷⚡️🇺🇸 ሰበር ዜና፡ ኢራን፣ በዮርዳኖስ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮች ላይ፣ ያልተጠበቀ፣ ድንገተኛ ጥቃት ጀምራለች። ከኢራን የተተኮሱ በርካታ ባለስቲክ ሚሳዬሎች፣ በዮርዳኖስ የአየር ክልል በአሁኑ ሰዓት ደርሰዋል።
4 333
+1
🇮🇱🇺🇸🇺🇦 ፕሬዝዳንት ትራምፕ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁን እና የዩክሬን ፕሬዝዳንት ዜሌንስኪን ዛሬ በሁለት የተለያዩ ስብሰባዎች በዋይት ሃውስ ተቀብለዋቸዋል።
*-*-*-
ፕሬዝዳንት ትራምፕን ቢዚ አደረጉት እነዚህ ሁለት ዓለም- አንቀጥቅጥ አይሁዳዊያን መሪዎች።
4 333
+1
🇮🇱🇺🇸🇺🇦 ፕሬዝዳንት ትራምፕ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁን እና የዩክሬን ፕሬዝዳንት ዜሌንስኪን ዛሬ በሁለት የተለያዩ ስብሰባዎች በዋይት ሃውስ ተቀብለዋቸዋል።
*-*-*-
ፕሬዝዳንት ትራምፕን ቢዚ አደረጉት እነዚህ ሁለት ዓለም- አንቀጥቅጥ አይሁዳዊያን መሪዎች።
4 333
🇺🇦🇮🇱 በነገራችን ላይ፣ ኔታንያሁ እና ዘለንስኪ ቁርሾ አላቸው፣ አይዋደደም። ምክኒያቱ ደግሞ እስራኤል በሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ላድ ያላት ገለልተኛ አቋም ነው። በሁለቱ መሃል መግባት አልፈለገችም። ገለልተኛ እንደመሆኗ ልታስታርቃቸውም ሞክራለች፣ በተደጋጋሚ። ሳይሳካ ቀርቷል።
ዘለንስኪ እስራኤልን የማይወደው መሳሪያ ስለከለከለችው ነው። ገለልተኝነቴን እጠብቃለሁ ስላለችው ነው። ከዚያ በኋላ ዘለንስኪ አኩርፏታል። አውሮፓዊያን፣ አሜሪካ፣ አውስትራሊያ፣ ካናዳ፣ ደቡብ ኮሪያና ሌሎችም ዩክሬንን በአንድም በሌላም ሲረዱ፣ እስራኤል አልረዳቻትም።
ብዙ የእስራኤል ባለስልጣናት፣ ወታደራዊ አመራሮች እና ሲቪሊያኑ ሕብረተሰብ፣ ሥር መሠረታቸው ሩሲያ ናት።
ሁለቱ መሪዎች ዛሬ በዋሽንግተን ሲተላለፉ ቃላት ተለዋውጠዋል።
4 333
🇮🇷/🇺🇦 ሰበር ዜና፦ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ፣ ከሰሞኑ በካዝቢያን ባሕር በአንድ የኢራን መርከብ ላይ የተደረገው ጥቃት 'በስህተት' እንደሆነ እና ዩክሬን ወታደራዊ መባባስ እንደማትፈልግ፣ በዩክሬን እንደተረጋገጠለት ተናግረዋል።
ዩክሬን ለደረሰው ኪሳራም ካሳ እንደምትከፍል ተናግሯል
*-*-*
ኢራን እንደ ሩሲያ ግራ የተጋባች አይደለችም ብዬ፣ በአጥር ተንጠልጥዬ፣ አልነገርኳችሁም?
ኢራን፣ በጦርነት ወቅት ሀገር ሊመሩ የሚችሉ አመራሮች አሏት። ሩሲያ የሰላም ወቅት አመራሮች ናቸው በጦርነት ወቅት እየመሯት ያሉት።
Russia needs war time leadership!
4 333
🇸🇦⚡️🇮🇶 ሰበር ዜና፦ የሳዑዲ አረቢያ የመከላከያ ሚኒስቴር፣ ባለፉት ጥቂት ሰዓታት ውስጥ እንደገና በድሮኖች ጥቃት እንደተደረገበት አስታውቋል።
መግለጫው እንደሚያመለክተው፣ ድሮኖቹ በምስራቅ ሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ የነዳጅ ተቋማት ላይ ለማነጣጠር ሞክረዋል፣ የደረሰ ጉዳት እንዳለም እየተጣራ ነው ብሏል።
ሳዑዲ፣ ድሮኖቹ የተወነጨፉት ከኢራቅ ነውም ብላለች።
*-*-*
ሳዑዲ፣ ሩሲያ የገጠማት ዓይነት እጣ ፋንታ ሊገጥማት ይሆን? እንዲገጥማትስ ተፈልጓል?
ሩሲያ፣ 40% የነዳጅና ጋዝ ኢንዱስትሪዋ በዩክሬን ድሮኖች ዶግ አመድ እንደሆነው፣ የሳዑዲንም… …?
እንደ እኔ፣ ሳዑዲ የማትችለውን ጦርነት ለማድረግ ከመውተርተር ይልቅ፣ አርፋ ብትቀመጥ ይሻላታል ባይ ነኝ። በየመንም፣ በኢራቅም እያለች ባትቀብጥ ጥሩ ይሆናል። ማንም የሚያድናት አይኖርም።
ያለበለዚያ እንደ ሩሲያ፣ የኃይል ኢንዱስትሪዋን ያነዱላታል።
4 333
🇮🇱🇺🇸⚡️🇮🇷 ቤንጃሚን ኔታንያሁ፣ ኢራን ምስጢራዊ በሆነው የፒካክስ ተራራ ጣቢያዋ ላይ፣ የኑውክሊየር ተቋማቷን እየገነባች መሆኑን በመግለጽ፣ ለፕሬዝዳንት ትራምፕ የስለላ መረጃ እንደሚያቀርብ ይጠበቃል።
ሁለቱ፣ ዛሬ በዋይት ሃውስ ተገናኝተው ሻይ ቡና ብለዋል።
4 333
🇸🇦🇾🇪💢 የየመን ጦር ሰራዊት፣ በሳውዲ አረቢያ ከሚደገፈው ሚሊሻ ሰራዊት ብዙ መጠን ያለው የጦር መሳሪያዎችን እና ጥይቶችን፣ በምርኮ (ገኒማ) መያዙን አስታወቀ።
4 333
💢🇸🇦🇮🇶 ኢራቅ፣ በአብቃይቅ የነዳጅ ማጣሪያ ጥቃት ላይ በሳዑዲ አረቢያ ለተሰነዘሩባት ክሶች ላይ ምላሽ ሰጥታለች።
ጥቃቱ የተፈጸመው በየመን እንጂ በኢራቅ አለመሆኑን ተናግሯል።
ሳዑዲ በኢራቅ ላይ ያላት ጠላትነት ረጅም ጊዜ የሆነው ቢሆንም፣ ለምን እንደሆነ አይገባንም ብሏል፣ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሯ።
አክሎም፣ "በኢራቅ ላይ የሚደረግ ማንኛውም የሳዑዲ ጥቃት 'ጠንካራ ምላሽ' እንደሚሰጠው አስጠንቅቋል።
ሪያድ በየመን ላይ የምታደርገውን "ፍትሃዊ ያልሆነ ከበባ" … "በእናንተ ውስጥ ማንኛውም እንጥፍጣፊ ሰዋዊነት ቀርቶ ከሆነ' በማለት እንድታነሳ ጠይቋል።
4 333
🇷🇺🇺🇦⚡️ሩሲያ 356 የዩክሬን ድሮኖችን መጣሏን አስታውቃለች።
🔹የሩሲያ የመከላከያ ሚኒስቴር ባለፈው ቀን እና ሌሊት፣ የሀገሪቱ የአየር መከላከያ ሥርዓቶች፣ 356 የዩክሬን ድሮኖችን በተለያዩ አካባቢዎች ላይ መጣላቸውን እና ማጥፋታቸውን አስታውቋል።
*-*-*-
በየቀኑ ግን 200 እና 300 ድሮን እየተጣለ ይዘለቃል? ይሄ ተመትቶ የወደቀው ነው፣ ምናልባት ያለፈው እኩሌታ የሆነ ቁጥር ይሆናል።
ምንድነው መደረግ ያለበት? የት ብትመታው ነው የሥርዓቱን ወገብ የምትሰብረው እና ይሄን የምታስቆመው? ይሰበራልስ?
የድሮኑ ቁጥር እየጨመረ እንጂ የሚመጣው አይቀንስም። ትችለዋለህ?
ሩሲያ ግን እዚህ ድረስ ምን አስጠበቃት? በጊዜ እና በፍጥነት ኃይል ተጠቅማ መጨረስ ትችል የነበረውን ጦርነት፣ ለምን ልትጎትተው ፈለገች? ለምን እራሷን እዚህ አረንቋ ለማስገባት ፈቀደች? ፑቲን በሩሲያ ላይ ያለው ዓላማ ምንድነው?
4 333
🇨🇴⚡️— የኮሎምቢያ ፕሬዝዳንት አቤላርዶ ዴ ላ ኤስፕሪዬላ፣ የመንግስት ወጪን ለመቀነስ እና የኮሎምቢያን የውጭ ዲፕሎማሲያዊ ውርውርነት ጋብ ለማድረግ፣ 14 ኤምባሲዎችን እና 15 ቆንስላዎችን ለመዝጋት እቅድ እንዳለው አስታውቋል።
➡️ እንዲዘጉ የታቀዱት ኤምባሲዎች፣ በአልጄሪያ፣ በአዘርባጃን፣ በባርቤዶስ፣ በኩባ፣ በጊኒ ቢሳዎ፣ በኢትዮጵያ፣ በጋና፣ በሄይቲ፣ በሃንጋሪ፣ በማሌዥያ፣ በኒካራጓ፣ በሮማኒያ፣ በሴኔጋል እና በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ናቸው።
➡️ ዴ ላ ኤስፕሪዬላ በተጨማሪም፣ ኮሎምቢያ፣ "አምባገነኖች" ብሎ ከገለጻቸው፣ ከኩባ እና ኒካራጓ ጋር የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷን እንደምታቋርጥ ተናግሯል።
➡️ በፍልስጤም ኤምባሲ ለመክፈት የታቀደው እቅድ እንደሚሰረዝ እና በፈረንሳይ የሚገኘው የኮሎምቢያ የዩኔስኮ ዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮ እና በጣሊያን የሚገኘው የፋኦ ዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮ እንደሚዋሃዱ አስታውቋል።
*-*-*-
"ፖሮሲሪር ኢንሲያር ፕሮሰሬሱ፣ ኤሮራ ፕሪሜራ ታፓ አደሲዮስ……" ንግግር ብሎ ዝም! ስፓኒሾች ይናገሯት፣ ልብ ተርታሪ ንግግር።
4 333
🇸🇦⚡️— የኢንሹራንስ ኩባንያዎች በቀይ ባሕር ውስጥ ከሳዑዲ አረቢያ ጋር ግንኙነት ላላቸው መርከቦች መድን መስጠት አቁመዋል፣ ይህም የተገለጸው በፋይናንሺያል ታይምስ ሲሆን ሎይድስ ኦፍ ለንደንን በመጥቀስ ነው።
የየመን የሁቲ አመጠኞች በባብ አል-ማንዳብ የባሕር መተላለፊያ ውስጥ በሳውዲ ታንከሮች ላይ ጥቃት ከፈጸሙ በኋላ ኢንሹራንሶች አሁን ያሉትን ፖሊሲዎች ለመሰረዝ እየተዘጋጁ መሆናቸውም ተዘግቧል።
በአሁኑ ጊዜ፣ ሳዑዲ አረቢያ ለኢንሹራንስ አቅራቢዎች ከፍተኛ የአደጋ ደረጃ ባላቸው ሀገራት ዝርዝር ውስጥ ተካትታለች።
*-*-*-
ዋው፣ ይኼን ክፍተት የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ቢጠቀመው ጥሩ ነው። ሀብታም ይሆንበታል። ያን ልምዱን ደግሞ ይዞ ወደ ሆርሙዝ ወሽመጥ ይወርድና ዓለም አንቀጥቅጥ ኢንሹራንስ ኩባንያ ይሆናል።
