የቀጠናው ተመልካች
Ir al canal en Telegram
በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።
Mostrar másEl país no está especificadoLa categoría no está especificada
4 303
Suscriptores
+824 horas
-47 días
-7130 días
Archivo de publicaciones
4 303
—❗️🇺🇸 የCNN፣ MSNOW እና Politico ጋዜጠኞች፣ ከአሁን በኋላ ከኋይት ሃውስ ታግደዋል ሲሉ ፕሬዝዳንት ትራምፕ አስታወቁ።
ፕሬዝዳንቱ ይህን ያሉት፣ ሚዲያዎቹ FAKE NEWS በማምረት ላይ ተጠምደዋል በሚል ነው።
4 303
🇩🇪🇷🇺⚡️የሩሲያ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ልዑክ፣ ኪሪል ዲሚትሪየቭ እና የጀርመን የAfd ፓርቲ መሪዎች፣ የሩሲያ ጋዝ አቅርቦትን ወደ ጀርመን ለማስመለስ ውይይቶችን እያዘጋጁ እያዘጋጁ እንደሆነ ተነገረ። ይህም የኖርድ ጋዝ ቧንቧዎችን እንደገና መክፈትን ሊያካትት ይችላል፣ እንደ ሮይተርስ ዘገባ።
ስብሰባው፣ መጋቢት 2027 ሊካሄድ እንደሚችል የተነገረ ሲሆን ነገር ግን፣ ከዚያ በፊት የሩሲያ-ዩክሬን የሰላም ማዕቀፍ ከተደረሰ ብቻ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
የAfD አሊስ ዌይዴል እና ቲኖ ቹሩፓላ ከቭላድሚር ፑቲን የቅርብ አማካሪ ከሆኑት ከዲሚትሪቭ ጋር ይሳተፋሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ AfD በተደጋጋሚ የሩሲያ ነዳጅ እና ጋዝ ላይ ገደቦችን ለማስቆም ሲሟገት ከመቆየቱም ባሻገር፣ ርካሽ ኃይል የጀርመንን ኢኮኖሚ ሊደግፍ ይችላል ሲል ይከራከራል።
አዘጋጆቹ እስራኤልን፣ አረብ ኤምሬቶችን ወይም ንድን እንደ ተደራሽ ቦታዎች እያሰቡ ሲሆን የአሜሪካ ልዑካን ስቲቭ ዊትኮፍ እና ጃሬድ ኩሽነር ሊሳተፉ እንደሚችሉ ተስፋ ያደርጋሉ፣ ምንም እንኳን አንድ ከፍተኛ የአሜሪካ ባለስልጣን እንደተናገሩት፣ እስካሁን የተነገራቸውም ነገር ሆነ የመጣላቸው ግብዣ ባይኖርም።
4 303
🇮🇱⚡️የIDF ዋና ኢታማዦር ሹም ኢያል ዛሚር፡ በሩቅ ሆነው ሥነምግባርን ለምትሰብኩ ተቺዎቻችን ሁሉ፡ እላለሁ፡ እናንተ ትችታችሁን ቀጥሉ፣ እኛ ትግላችንን እንቀጥላለን።
4 303
+1
🇵🇰🇮🇷🇸🇦 ፓኪስታን በኢራን በኩል መልእክት በመላክ በየመን ጣልቃ እንዲገቡና ሁቲዎች የሳዑዲ ዓረቢያ የነዳጅ መሠረተ ልማት ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን እንዲያቆሙ እንዲነግሯቸው ጠይቃለች፤ ኢራናውያን ግን ይህ ጉዳይ የሳዑዲ ዓረቢያ እና የየመን ሕዝብ ጉዳይ ነው በማለት ጣልቃ መግባት እንደማይፈልጉ ተናግረዋል።
ሳውዲ ዓረቢያ ቱርክን፣ ፓኪስታንን፣ እስራኤልን፣ አሜሪካን እና ቻይናን ከሁቲዎች ጋር በሚደረገው ጦርነት እንዲረዱ ጠይቀዋል፣ ሁሉም ግን ፈቃደኛ አልሆኑም።
FINANCIAL TIMES
4 303
🇾🇪🇸🇦| ⚡️የሳዑዲ-የመን ጦርነት፣ የኢራን የመንገደኞች አይሮፕላን በሰነዓ የአውሮፕላን ማረፊያ ላይ እንዳያርፍ ሳዑዲ ባደረገችው ጥቃት ምክኒያት ከተጀመረ ከሁለት ወር በኋላ፣ በሳዑዲ ባሉ 14 የነዳጅ ፋብሪካዎች፣ 3 የአየር ማረፊያ ጣቢያዎች፣ ንጉሥ ካሊድ ጦር ሰፈር፣ ንጉሥ ፋሃድ ጦር ሰፈር፣ በከሚስ ሙሻይት፣ በጣኢፍ እና በሌሎች ከተሞቿ ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን እና እየደረሰ እንዳለ የሰነድ መረጃዎች ያሳያሉ።
የኢራን የመንገደኞች አይሮፕላን እንዳያርፍ ባለመፈለጋቸው፣ የሳዑዲ ኢጎነት፣ ኩራት እና ትቢት እንዴት በመቶ ቢሊዮኖች የሚቆጠር ኪሳራ እንዳደረሰባቸው የታሪክ መዛግብት ይጽፋሉ።
4 303
🇪🇺🇺🇦 የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት እርሱላ ቫን ዴር ሌየን፡
ከዘለንስኪ ጋር ተነጋግሬያለሁ፣ ነገ ሌላ $4.3 ቢሊዮን ዩሮ ለሚሳኤል እና ሰው አልባ አውሮፕላኖች ምርት ወደ ዩክሬን እናስተላልፋለን።*-*- ፈጣሪ ጣልቃ ካልገባ፣ ይቅርታ፣ ሩሲያ አታሸንፍም! ሩሲያ ዩክሬንን መደምሰስ እየቻለች አልደመስስም ስትልና በሁለት ልብ ሆና (ድርድር እና ውጊያ) እየተዋጋች ስትንደፋደፍ፣ እንግዲያውስ እኛ እንደመስስሻለን ያሏት ይመስላል። እነሱ የሚዋጉት በአንድ ልብ ነው፣ ድርድር የሚሉትም ከአንገት በላይ፣ ሩሲያን ሳያኮሎጂካሊ ለማምታታት ነው። ገብቷታል ይሄ? አሁንም ደግሜ እላለሁ፡ አውሮፓ እስካለ ጦርነቱ አይቆምም፣ ዩክሬን እስካልተደመሰሰች ጦርነቱ አይቆምም! አሁን ያለው የሩሲያ አያያዝ ደግሞ ያንን ማድረግ የሚችል ነው ብዬ አላስብም። አውሮፓዊያን ከራሳቸው ዜጎች ላይ እየነጠቁ ለዩክሬን የሚያወጡት የገንዘብ መጠን የማይታመን ነው። ነገ ሩሲያ ተሸንፋ የሚዝቁትን ሀብት በሕልማቸው እያለሙ ለሃጫቸውን አዝረብርበዋል። ሩሲያ አውቃ ይሆን የምታስወጣቸው ጦርነቱን በማርዘም? ካዝናቸውንም መጋዘናቸውንም ልታደኸየው? ይሆን እንደዛ? ትችላቸዋለች 1 ለ 40 ?
4 303
🇪🇺🇺🇦 የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት እርሱላ ቫን ዴር ሌየን፡
ከዘለንስኪ ጋር ተነጋግሬያለሁ፣ ነገ ሌላ $4.3 ቢሊዮን ዩሮ ለሚሳኤል እና ሰው አልባ አውሮፕላኖች ምርት ወደ ዩክሬን እናስተላልፋለን።*-*- ፈጣሪ ጣልቃ ካልገባ፣ ይቅርታ፣ ሩሲያ አታሸንፍም! ሩሲያ ዩክሬንን መደምሰስ ስትችል አልደመስስም እያለች በሁለት ልብ ሆና (ድርድር እና ውጊያ) ስትንደፋደፍ፣ እንግዲያውስ እኛ እንደመስስሻለን ያሏት ይመስላል። እነሱ የሚዋጉት በአንድ ልብ ነው፣ ድርድር የሚሉትም ከአንገት በላይ፣ ሩሲያን ሳያኮሎጂካሊ ለማምታታት ነው። ገብቷታል ይሄ? አሁንም ደግሜ እላለሁ፡ አውሮፓ እስካለ ጦርነቱ አይቆምም፣ ዩክሬን እስካልተደመሰሰች ጦርነቱ አይቆምም! አሁን ያለው የሩሲያ አያያዝ ደግሞ ያንን ማድረግ የሚችል ነው ብዬ አላስብም። አውሮፓዊያን ከራሳቸው ዜጎች ላይ እየነጠቁ ለዩክሬን የሚያወጡት የገንዘብ መጠን የማይታመን ነው። ነገ ሩሲያ ተሸንፋ የሚዝቁትን ሀብት በሕልማቸው እያለሙ ለሃጫቸውን አዝረብርበዋል። ሩሲያ አውቃ ይሆን የምታስወጣቸው ጦርነቱን በማርዘም? ካዝናቸውንም መጋዘናቸውንም ልታደኸየው? ይሆን እንደዛ? ትችላቸዋለች 1 ለ 40 ?
4 303
🇸🇦🇺🇸⚡️ — በዋሽንግተን የሚገኘው የሳዑዲ ኤምባሲ፡-
የታቀደው የኤፍ-35 ሽያጭ፣ የሳዑዲ-አሜሪካን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ጥንካሬ እና ዘላቂ ባህሪ እና የመከላከያ ትብብራችንን ቀጣይ እድገት ያሳያል። ለበርካታ አስርት ዓመታት፣ የሳዑዲ-አሜሪካ የጸጥታ ትብብር፣ ለአካባቢው መረጋጋት አስተዋጾ አበርክቷል፣ የጋራ የመከላከል አቅማችንን ያጠናክራል፣ እንዲሁም የጋራ የደህንነት ፍላጎቶቻችንን ያሳድጋል።
4 303
🇺🇸/🇺🇳 ዛሬ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት በይፋ ወጣች። የተጠቀሱት ምክንያቶች፣ በእስራኤል ላይ አድልዎ ያደርጋል፣ ግብዝነት ያጠቃዋል እና እንደ ኢራን ላሉ የሽብር አገዛዞች ድጋፍን ይሰጣል፣ የሚሉ ናቸው።
4 303
🇵🇰🇸🇦⚡️ — የፓኪስታን ጦር ቃል አቀባይ ሌተናል ጀነራል አህመድ ሸሪፍ ቻውድሪ፡
ፓኪስታን ከሳውዲ ዓረቢያ መንግሥት ጋር በዲፕሎማሲያዊም ሆነ በአካል ሙሉ በሙሉ ትቆማለች። ለሳውዲ ዓረቢያ መንግሥት ደህንነት በማንኛውም ደረጃ እንሄድበታለን። የፓኪስታን ሕዝብ ከሳውዲ ወንድምና እህቶች ጋር ትከሻ ለትከሻ መቆሙ ግልጽ መሆን አለበት። በአጭር አነጋገር፣ እኛ እዚያ ነን፣ እናም የሳውዲ ዓረቢያን መንግሥት ከማንኛውም ጥቃት ለመከላከል ተዘጋጅተናል።
4 303
🇺🇦🇷🇺⚡️የዩክሬን STING ኢንተርሴፕተር ድሮን፣ የሩስያ ድሮን ከመሬት ወደ አየር በተወነጨፈ የዩክሬን ሚሳዬል በተደመሰሰበት ቅጽበት፣ ያስቀረው ምስል።
4 303
🇸🇦⚡️🇾🇪 በሳዑዲ ዓረቢያ ደቡባዊ ግዛት፣ ግዙፉ የያንቡ ወደብ፣ በአሁኑ ሰዓት የየመንን የምሽት ጥቃት ተከትሎ በእሳት እየነደደ ይታያል ።
4 303
🇺🇸🇶🇦🇮🇱⚡- ሌላ ሰበር፡ ኳታር ከሳዑዲ ዓረቢያ፣ ከተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ እና ከቱርክ በመቀጠል የኤፍ-35 ጀቶችን ግዥ ጥያቄ በማቅረብ ከመካከለኛው ምስራቅ አዲስ አባል ሆናለች።
እስራኤል ኤፍ-35 አውሮፕላኖችን ለዶሃ መሸጥን በመቃወም፣ ከቱርክ ጥያቄ ጋር እንዳደረገችው ተቃውሞዋን አሰምታለች።
*-*-*-
አማሪካ… አማሪካ እኮ ከልቡ ሀገር ነው፣ አላህ የምድር ገዥ አድርጓቸው … ቸብችበው!
4 303
🇸🇦🇺🇸 ሰበር ዜና፡ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ 48 የኤፍ-35 ተዋጊ አውሮፕላኖችን እና 49 የፕራት ኤንድ ዊትኒ ሞተሮችን ለሳዑዲ ዓረቢያ በ$24.3 ቢሊዮን ዶላር እንዲሸጥ አጸደቀ።
4 303
🇸🇦🇺🇸 ሰበር ዜና፡ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ 48 የኤፍ-35 ተዋጊ አውሮፕላኖችን እና 49 የፕራት ኤንድ ዊትኒ ሞተሮችን ለሳዑዲ ዓረቢያ በ$24.3 ቢሊዮን ዶላር እንዲሸጥ አጸደቀ።
4 303
🇺🇸 ፕሬዚዳንት ትራምፕ፣ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ጎን ለጎን ከሳዑዲ ዓረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ፣ ኳታር፣ ባሕሬን፣ ኩዌት እና ኦማን መሪዎች ጋር በማክሰኞ እንደሚገናኙ AXIOS ዘግቧል።
ትራምፕ፣ "የት እንዳሉና እንዴት እንደሆኑ ማወቅ እፈልጋለሁ። ደህና ናቸው ወይ? እኛ ለእነሱ ከፍተኛ ጥበቃ እያደረግን ነው" ብሏል።
ምርጫው ከመካሄዱ በፊት ወይም በኋላ፣ በጦርነቱ ዙሪያ ውሳኔ ይወስን እንደሆን ለተጠየቀው፣ ለመግለጽ ፈቃደኛ አልሆነም።
አንዳንድ የአሜሪካ ባለሥልጣናት፣ የአሁኑን "ጦርነትም፣ ሰላምም ያልሆነውን" ሁኔታ አደገኛና አሜሪካን የሚጎዳ ፖሊሲ አድርገው ይመለከቱታል፣ እናም ስምምነት ካልተደረሰ መጠነ ሠፊ ሌላ ዙር ጦርነት እንደገና ሊጀመር ይችላሉ ብለው ይፈራሉ ።
