en
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

Open in Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

Show more
The country is not specifiedThe category is not specified
4 332
Subscribers
+424 hours
-367 days
-7930 days
Posts Archive
🇺🇸🇮🇷⚡️The Washington Post, የፔንታገን ባለሥልጣናት ከኢራን ጥሩ ዜና ባለማምጣት ቅጣት እንዳይደርስባቸው በመፍራት፣ የሚሳይሉን እጥረት ጉዳይ ከመከላከያ ሚኒስትር ፒት ሄግሴት እና
+1
🇺🇸🇮🇷⚡️The Washington Post, የፔንታገን ባለሥልጣናት ከኢራን ጥሩ ዜና ባለማምጣት ቅጣት እንዳይደርስባቸው በመፍራት፣ የሚሳይሉን እጥረት ጉዳይ ከመከላከያ ሚኒስትር ፒት ሄግሴት እና ከሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት እየደበቁ መሆናቸውን ዘግቧል።

🇺🇸🇱🇧⚡️ — ፕሬዝዳንት ትራምፕ በTruth Social በኩል፦ ሀገሩን ለመለወጥ አስደናቂ ስራ ከሰራው ከሊባኖስ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ አውን ጋር ከተገናኘሁ በኋላ፣ አሜሪካውያን ይህችን ውብ ሀገር
🇺🇸🇱🇧⚡️ — ፕሬዝዳንት ትራምፕ በTruth Social በኩል፦
ሀገሩን ለመለወጥ አስደናቂ ስራ ከሰራው ከሊባኖስ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ አውን ጋር ከተገናኘሁ በኋላ፣ አሜሪካውያን ይህችን ውብ ሀገር በቀላሉ እንዲጎበኙ ሁሉም የአሜሪካ አየር መንገዶች በቀጥታ ወደ ሊባኖስ እንዲበሩ አስተዳደሬን አዝዣለሁ። ተስፋ እናደርጋለን፣ ሌሎች ሀገራትም ተመሳሳይ ነገር ያደርጋሉ። ይደሰቱ!
*-*-*- - እረ የኛንም መጥተው ይጎብኙልን፣ ሚስተር ፕሬዝዳንት፣ ቀበና ወንዝን ሰርተናል። - ሂዲ፣ ግማታም!

🇸🇦⚡️🇾🇪 የሁቲ የባህር ኃይል እገታ የሳዑዲ የነዳጅ ታንከሮች በቀይ ባሕር ውስጥ ወደ ኋላ እንዲመለሱ አስገድዷቸዋል፣ ሲል ሮይተርስ ዘግቧል። ➡️ የሳዑዲ ነዳጅ የሚጭኑ ሁለት ታንከሮች — አን
🇸🇦⚡️🇾🇪 የሁቲ የባህር ኃይል እገታ የሳዑዲ የነዳጅ ታንከሮች በቀይ ባሕር ውስጥ ወደ ኋላ እንዲመለሱ አስገድዷቸዋል፣ ሲል ሮይተርስ ዘግቧል። ➡️ የሳዑዲ ነዳጅ የሚጭኑ ሁለት ታንከሮች — አንዱ ወደ ቻይና፣ አንዱ ወደ ሕንድ — ሁቲዎች መርከቦች በሳዑዲ ወደቦች እንዳይጭኑ ወይም እንዳያወርዱ ካስጠነቀቁ በኋላ፣ ወደ ግብፁ ሱዊዝ አቅጣጫ መስመራቸውን ቀይረው ተመልሰዋል። ➡️ ሦስተኛው ታንከር ለመጫን ያኑብ መጫኛ ጣቢያ ከመድረሱ በፊት ተመልሷል። ➡️ በሱዊዝ በኩል ወደ እስያ ዞሮ ለመሄድ ጭነቶች ላይ ሳምንታትን የጉዞ ጊዜን ይጨምራል። *-*-*- ሳዑዲዎች በሰው ውሃ፣ ሌሎች በሚያዙበት፣ ተከበው እንደሚኖሩ የገባቸው ገና አሁን ነው። በሌላ አባባል፣ የትራምፕን ቃል ልበደርና፣ "መጫወቻ ካርድ" የላቸውም። መውጫቸውም መግቢያቸውም የሌሎች ነው።

+2
🇮🇷🇺🇸⚡️ኢራን በባሕሬን የእስራኤል ኤምባሲን አጥቅታለች። የከተማው ሰማይም በተለያዩ ጥቃቶች ጭስ ጥቁር ለብሶ ይታያል። በተመሳሳይ፣ በሰሜን ኢራቅ ኢርቢል (ኩርድ) ከተማ ያልተቋረጡ የሚሳዬልና የድሮን ጥቃቶች፣ በኢራን ኃይሎች እየተሰነዘሩ ናቸው። በዚህም፣ ቁጥራቸው ያልታወቀ የአሜሪካ ወታደራዊ አባላቶች ሳይቆስሉ ወይም ሳይሞቱ እንዳልቀረ ተነግሯል። በሌላ በኩል፣ በእንግሊዝ ከአሜሪካ የጦር ሰፈር በርካታ B-1 ቦንብ ጣይ አይሮፕላኖች ወደ ቀጠናው እያመሩ ታይተዋል።

🇪🇹⚡️በኢትዮጵያ፣ የአማራ ግዛቶች ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ቦታዎች፣ በአማራ ታጣቂዎች (ፋኖ) እና በገዢው ፓርቲ ሰራዊት መካከል፣ የሚደረገው ጦርነት አሁንም እንደቀጠለ ነው። አብዛኛው የአማራ ግዛቶች፣ እንደ ትግራይ ግዛቶች ሁሉ፣ በአሁኑ ጊዜ ሙሉ በሙሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ አብይ አህመድ ከሚመራው መንግሥት፣ ቁጥጥር ውጭ ናቸው።

🇷🇺⚡️🇺🇦🚨 ሌሊቱን፣ የሩሲያ የአየር መቃወሚያዎች፣ 209 የዩክሬን ድሮኖችን በሩሲያ ክፍለ ሀገራት፣ በአዞቭ ባሕር እና በጥቁር ባሕር ላይ ጥለዋል -- የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር።

🇮🇷🇺🇸⚡️እኔ እኮ ተጠራጥሬአለሁ፣ ኢራን አሁንም፣ እየተደራደረችም እየተዋጋችም፣ ነገርየውን ውስጥ ለውስጥ እያብላላች ነው። ይሄን ሁለት ሦስት ቀን እንዲያውም፣ በኢራን ምዕራቡ ክፍል፣ በሬክታል ስኬል ከ4.3-4.6 የተለኩ፣ የመሬት መንቀጥቀጦች ተከስተዋል። ሰዎቹ ወደ ሙከራው ደረጃ ጭራሽ ገብተውልኛል እንዴ? እረ የcia ስልክ ያላችሁ ላኩልኝ በውስጥ?

🇮🇷🇺🇸⚡️እኔኮ ተጠራጥሬአለሁ፣ ኢራን አሁንም፣ እየተደራደረችም እየተዋጋችም፣ ነገርየው እያብላላች ነው። ይሄን ሁለት ሦስት ቀን እንዲያውም፣ በኢራን ምዕራቡ ክፍል፣ በሬክታል ስኬል ከ4.3-4.6 የተለኩ፣ የመሬት መንቀጥቀጦች ተከስተዋል። ሰዎቹ ወደ ሙከራው ደረጃ ገብተዋል እንዴ? እረ የcia ስልክ ያላችሁ ላኩልኝ በውስጥ?

🇮🇷🇺🇸⚡️🇮🇱 እስራኤል 'አነፍንፌ ደርሼበታለሁ' እንደምትለው ከሆነ፣ ኢራን በሺዎች የሚቆጠሩ የኒውክሊየር ማጣሪያዎችን (Centrifuges) ናታንዝ አቅራቢያ ወደ ሚገኘው እና በጣም የተጠና
🇮🇷🇺🇸⚡️🇮🇱 እስራኤል 'አነፍንፌ ደርሼበታለሁ' እንደምትለው ከሆነ፣ ኢራን በሺዎች የሚቆጠሩ የኒውክሊየር ማጣሪያዎችን (Centrifuges) ናታንዝ አቅራቢያ ወደ ሚገኘው እና በጣም የተጠናከረ የመሬት ውስጥ የኒውክሊየር ጣቢያ ወደ ሆነው፣ ፒክክስ ተራራ፣ እንዳዘዋወረች ገምግማለች። በእነዚህ ማጣሪያዎች፣ ኢራን አሁን ያለውን 60% HEU ክምችት በድብቅ ወደ ጦር መሳሪያ ደረጃ ማበልጸግ ትችላለች፣ ይህም ለሚሳዬሉ ፈንጂ ጭንቅላት ጥቅም ላይ ይውላል። እስራኤል እንደምትለው፣ በእርግጥም ኢራን ማጣሪያዎቹን ወደ ተባለው የተራራ ውስጥ ተቋም ካዘዋወረችው፣ እንደ ፔንታገን ባለስልጣናት፣ የአሜሪካ ጦር፣ ከዋሻዎቹ ጥልቀት፣ ጥንካሬ እና ውስብስብነት አንፃር፣ ምንም ማድረግ የማይችልበት ጉዳይ ሊፈጠር ይችላል የሚል ስጋት አድሮባቸዋል -- WSJ *-*-*- ለማውቃቸው የዕቡህ አደረጃጀቱ አባላት፣ በውስጥ መስመር ነግሬአለሁ፣ ካስፈለገ እነ ማዘር ጋር ላስቀምጥላቸው እችላለሁ ነገርየውን፣ የተነሳው አውሎ ነፋስ እስኪያልፍ ድረስ።

🇮🇷❌🇺🇸🇰🇼 - የኢራን IRGC ዛሬ ማታ ቀደም ብሎ ሚሳኤሎችን እና ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በመጠቀም በኩዌት የሚገኘውን የአሜሪካን የረዥም ርቀት ራዳር፣ የመገናኛ ማእከል፣ የሳተላይት መቀበያ ስርዓቶችን እና የሚሳኤል መከላከያ ራዳርን በመምታት አውድሜአለሁ ብሏል። ➡️ ቡድኑ፣ በዓሊ አል ሳሊም አየር ማረፊያ በሚገኘው MQ-9 ሰው አልባ አውሮፕላኖች ሃንገር ላይም ዒላማ ማድረጉን ገልጾ፣ በርካታ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ወድመዋል ወይም ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል፣ በማለት የበቀል ጥቃቱ 'ይቀጥላ' ብሏል

🇺🇸🇮🇷⚡️ - "በአሁኑ ጊዜ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኢራን የመግባቢያ ስምምነቱን በመጣሷ እና በሆርሙዝ ባሕር ውስጥ ለሚያደርጉት የሽብርተኝነት ድርጊት ዋጋ እንድትከፍል በማድረግ ላይ ያተኮሩ ናቸው። በተጨማሪም ፕሬዚዳንቱ፣ በቅርቡ ለአሜሪካ ወታደሮች ሞት ኢራን የሚገባትን ቅጣት እንድትከፍል ያደርጋል። ፕሬዚዳንቱ ሐሳቡን እስኪለውጥ እና በሌላ መንገድ እስኪያምን ድረስ፣ እነዚህ አስከፊ ድብደባዎች በኢራን ላይ ይቀጥላሉ። በተመሳሳይ ግን፣ በሁለቱ ሀገሮች መካከል የሚደረጉ ውይይቶች ቀጥለዋል" - የአሜሪካ ባለሥልጣን ለAXIOS።

🇸🇦🇺🇸 ሳዑዲ አረቢያ ለኒውክሊየር የሚሆን ዩራኒየም ለማብላላት ትችል ዘንድ የአሜሪካን መንግሥት ፍቃድ እየጠበቀች ቢሆንም፣ እስካሁን ትራምፕ በፍቃዱ ላይ ለመፈረም ችላ እንዳለ ነው - CNN *
🇸🇦🇺🇸 ሳዑዲ አረቢያ ለኒውክሊየር የሚሆን ዩራኒየም ለማብላላት ትችል ዘንድ የአሜሪካን መንግሥት ፍቃድ እየጠበቀች ቢሆንም፣ እስካሁን ትራምፕ በፍቃዱ ላይ ለመፈረም ችላ እንዳለ ነው - CNN *-*-*-* አሜሪካን በደንብ ለምኑ፣ ስግደታችሁ ጦማችሁ አይቋረጥ፣ ሰደቃውንም ስጡ የሚገባትን አሜሪካ። "አንኳኩ በሩ ይከፈትላችኋል"፣ አይዟችሁ።

🇫🇷🇸🇦🇦🇪⚡️ - የፈረንሳይ አየር መንገድ (Air France) ወደ ሳዑዲ አረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የሚደረጉ በረራዎችን ለሚቀጥሉት ሰባት ቀናት አግዷል ።

🇮🇷⚡️🇺🇸🇯🇴 🇮🇱 ዮርዳኖስ እስራኤልን የምትከላከል ቁልፍ፣ የመጨረሻዋ እና በጣም አስፈላጊው ንብርብር ጋሻ ናት። በዮርዳኖስ ላይ እየጨመረ የመጣው የኢራን የቀጥታ ምቶች መጠን፣ ከዚህ በ
 🇮🇷⚡️🇺🇸🇯🇴 🇮🇱 ዮርዳኖስ እስራኤልን የምትከላከል ቁልፍ፣ የመጨረሻዋ እና በጣም አስፈላጊው ንብርብር ጋሻ ናት። በዮርዳኖስ ላይ እየጨመረ የመጣው የኢራን የቀጥታ ምቶች መጠን፣ ከዚህ በፊት ኢራን በኩዌት፣ በባህሬን፣ በኤሜሬት እና በኳታር የደመሰሰቻቸው ራዳሮች እና ሌሎች የአሜሪካ መሣሪያዎች ቀጥተኛ ውጤት ነው። ኢራን እነዚህን ሀገራት፣ በዓመታት በቀላሉ የማይተኩትን የአየር መቃወሚያ ሚሳዬሎቻቸውን አሟጠው እንዲጠቀሙ አስገድዳቸዋለችም። በመሆኑም፣ ሰማዩ ለኢራን ሚሳዬሎች ክፍት ሆኗል። በ20 ዓመታት ውስጥ CENTCOM የአረብ ሀገራትን እስራኤልን የሚከላከሉ የብረት ጉልላት አድርጓቸዋል፣ እና ኢራን አሁን በዘዴ እያፈረሰችው ያለችው ይሄንን ነው። 📎

+1
—❗️🇮🇷/🇴🇲 "ማለፍ ክልክል ነው" የሚለውን የIRGC ትዕዛዝ በመጣስ ሊያልፉ የሞከሩ ሁለት መርከቦች፣ በሆርሙዝ ወሽመጥ ውስጥ ተመትተዋል - ኢራን ጦር።

🇺🇸🇮🇷⚡️ - ትራምፕ በኢራን ላይ የሚደረገውን ጦርነት ለማስፋት በማሰብ፣ አሜሪካ ተጨማሪ F-16 እና F-35 ተዋጊ ጄቶችን ከአውሮፓ ወደ መካከለኛው ምስራቅ፣ እንዲሁም ተጨማሪ የአየር ላይ ነ
🇺🇸🇮🇷⚡️ - ትራምፕ በኢራን ላይ የሚደረገውን ጦርነት ለማስፋት በማሰብ፣ አሜሪካ ተጨማሪ F-16 እና F-35 ተዋጊ ጄቶችን ከአውሮፓ ወደ መካከለኛው ምስራቅ፣ እንዲሁም ተጨማሪ የአየር ላይ ነዳጅ ሞይ ታንከሮችን ለመላክ አቅዳለች ሲል CNN ዘግቧል።

🇺🇸🇮🇷⚡️ - ትራምፕ በኢራን ላይ የሚደረገውን ጦርነት ለማስፋት በማሰብ፣ አሜሪካ ተጨማሪ F-16 እና F-35 ተዋጊ ጄቶችን ከአውሮፓ ወደ መካከለኛው ምስራቅ፣ እንዲሁም ተጨማሪ የአየር ላይ ነ
🇺🇸🇮🇷⚡️ - ትራምፕ በኢራን ላይ የሚደረገውን ጦርነት ለማስፋት በማሰብ፣ አሜሪካ ተጨማሪ F-16 እና F-35 ተዋጊ ጄቶችን ከአውሮፓ ወደ መካከለኛው ምስራቅ፣ እንዲሁም ተጨማሪ የአየር ላይ ነዳጅ ሞይ ታንከሮችን ለመላክ አቅዳለች ሲል ሲኤንኤን ዘግቧል።

+1
🇮🇷🇺🇸⚡️IRGC ትናንት ሌሊት በጎረቤት አረብ ሀገራት የአሜሪካ ዒላማዎች ላይ፣ የሰነዘራቸውን ጥቃቶች የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ለቋል። ጥቃቱ በአሜሪካ ጦር ላይ፣ የሳተላይት ምስሎችን በመመልከት እና የአሜሪካ መረጃ ምንጮችን ዋቢ በማድረግ፣ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል። ተዋጊ ጀቶች፣ ሄሊኮፕተሮች፣ ሎጀስቲክ ሴንተሮች፣ ሚሳዬል ማስወንጨፊያዎች እና ራዳሮች የወደሙ ሲሆን፣ የበርካታ ወታደሮችንም ሕይወት የቀጠፈ ጥቃት ሆኗል። በዚህ ቪዲዮ የሚገርመው፣ IRGC ለቪዲዮው ማጀቢያ በተለምዶ ሂዝቦላ ለራሱ የጥቃት ቪዲዮዎች የሚጠቀምበትን ሙዚቃን መጠቀሙ ነው። ሙዚቃዋ በጣም ፌመስ ሆናለች። ይሄ የኢራን ሥራ ከኢትዮጵያ የደራሲዎች ማሕበር የኮፒ ራይት ጥያቄን አስነስቷል። አሁን ስጋቱ ዩትዩብ የኢራንን መንግሥት ከፕላትፎርሙ ላይ እንዳያወርደው ነው። ይሄ ከሆነ፣ በዩትዩቡ የሚሠሩ፣ ወደ 31 የሚጠጉ ሠራተኞቹን የኢራን መንግሥት ከሥራ እንዳያባርራቸው ተሰግቷል። ላይቭ ካላዘጋጁ፣ ምናልባት ጎ ፈንድ ሚ ካልከፈቱ፣ ቻናሉና ቤተሰቡ አደጋ ላይ ይወድቃል። *-*-* የመጀመሪያው የ IRGC ነው፣ ሁለተኛው የሂዝቦላ ነው።

🇮🇷🇺🇸⚡️ያልተቋረጡ የኢራን ጥቃቶች፣ የአሜሪካን ንብረቶችን፣ በኩዌት እና በባሕሬን፣ እየመቱ ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ፣ ከተወቻት ወራት በኋላ፣ ኢራን ኤሜሬትን እንደገና መታታለች። አሜሪካ በበኩሏ፣ እንደ ኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር እኩለ-ሌሊት ገደማ በኢራን የጀመረችው ጥቃት፣ እስከ አሁን ሰዓት ድረስ አላባራም።

🇮🇷 IRGC ምሽቱን ባወጣው መግለጫ …
🇮🇷 IRGC ምሽቱን ባወጣው መግለጫ …