ar
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

الذهاب إلى القناة على Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
4 330
المشتركون
+2824 ساعات
+307 أيام
-4230 أيام
أرشيف المشاركات
🇸🇦⚡️🇾🇪 በአሁኑ ሰዓት የሳዑዲ አየር ኃይል ጦር፣ በተደጋጋሚ እና ባልተቋረጠ መልኩ በየመን ድበደባ በማድረግ ላይ ይገኛል።

— 🇾🇪 የየመን ጦር ኃይሎች (አንሳርአላህ-ሁቲ)፣ በቀይ ባሕር ባብ አል-ማንዳብ ወሽመጥ የመጀመሪያ የባሕር ወታደራዊ ጥበቃቸውን በማካሄድ፣ በመስመሩ ውስጥ ባለው የመርከብ ትራንስፖርት ላይ ክትትል እያደረጉ ነው።

🇮🇷🇾🇪 መካከለኛው ምሥራቅ በእምቢተኞች ትግል መሠረት፣ ወደ አዲስ ምዕራፍ ተሸጋግሯ። ሆርሙዝ ወሽመጥ፣ በኢራን ቀይ ባሕር ወሽመጥ፣ በየመን፣ ተገድቧል!
🇮🇷🇾🇪 መካከለኛው ምሥራቅ በእምቢተኞች ትግል መሠረት፣ ወደ አዲስ ምዕራፍ ተሸጋግሯ። ሆርሙዝ ወሽመጥ፣ በኢራን ቀይ ባሕር ወሽመጥ፣ በየመን፣ ተገድቧል!

— 🇾🇪 በምዕራባዊው የባሕር ዳርቻ የአንሳረላህን (ሁቲ)፣ በሳዑዲና በግብአበሮቿ ላይ ያስመዘገበውን ድል እና ያሳካውን ዘመቻ ለማክበር፣ በርካታ የየመን ሕዝብ በዋና ከተማዋ፣ ሰንዓ፣ ተሰብስበዋል።

🇸🇦/🇾🇪 ሰበር ዜና፦ የጦር ተሽከርካሪዎችን፣ የጭነት መኪናዎችን እና ተዋጊ ቅጥረኞችን ጨምሮ አዲስ የደረሱ ብዙ የሳዑዲ ተጨማሪ ኃይሎች፣ በምሥራቃዊ የአል-ጃውፍ ግዛት በባለስቲክ ሚሳይሎች ዒላ
🇸🇦/🇾🇪 ሰበር ዜና፦ የጦር ተሽከርካሪዎችን፣ የጭነት መኪናዎችን እና ተዋጊ ቅጥረኞችን ጨምሮ አዲስ የደረሱ ብዙ የሳዑዲ ተጨማሪ ኃይሎች፣ በምሥራቃዊ የአል-ጃውፍ ግዛት በባለስቲክ ሚሳይሎች ዒላማ ተደርገዋል – Saba News

🇮🇱🇾🇪⚡️ — አንድ የእስራኤል ከፍተኛ ባለሥልጣን ለቻናል 12 እንደተናገረው፣ የሁቲ (አንሳርአላህ) የባብ አል-ማንደብ የባሕር ወሽመጥ ቁጥጥር በዋነኝነት በጂኦግራፊው ምክንያት አሁን በሆርሙዝ
+1
🇮🇱🇾🇪⚡️ — አንድ የእስራኤል ከፍተኛ ባለሥልጣን ለቻናል 12 እንደተናገረው፣ የሁቲ (አንሳርአላህ) የባብ አል-ማንደብ የባሕር ወሽመጥ ቁጥጥር በዋነኝነት በጂኦግራፊው ምክንያት አሁን በሆርሙዝ ካለው ሁኔታ የበለጠ ለመርከብ ትራንስፖርት ስጋት ይፈጥራል፣ ብሏል። ከፔሪም (ማዩን) ደሴት አልፎ ያለው የምሥራቃዊ የመርከብ መተላለፊያ ስፋቱ ወደ ሦስት ኪሎ ሜትር ብቻ ሲሆን፣ የሚያልፉ መርከቦች በቀጥታ በሁቲ ዓይኖች እይታ ውስጥ ያስገባቸዋል። “በፀረ-ታንክ ሚሳይሎች በፈለጉት ሁሉ ላይ መተኮስ ይችላሉ። መርከቦቹን በገዛ ዓይኖቻቸው ማየት ይችላሉ። ልዩነቱ ይህ ነው” ብሏል ባለሥልጣኑ። በአንፃሩ በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦችን ለመቆጣጠር ኢራን፣ ሳተላይት ምስሎችን፣ guided ሚሳዬሎችን፣ ፈጣን ጀልባዎችን እና ድሮኖችን መጠቀም ያስፈልጋታል፣ ሲል ተናግሯል። *-*-*- እያለ ያለው፣ እነዚህ ሽርጣም የየመን ተዋጊዎች ድንጋይ ላይ ቁጭ ብለው ጥርሳቸው እየፋቁ አላፊ አግዳሚ መርከብን መቆጣጠር ይችላሉ ነው፣ ና አንተ በዚ ግባ፣ ምን ታያለህ እዛጋ? ና ወደዚ … ምናምን እያሉ። ሳዑዲን በምታክል ሀገር ላይ እነዚህን ሲቢሮ የላከ ፈጣሪ …

🇸🇦⚡️🇾🇪 ሳዑዲ ዓረቢያ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን እና በሺዎች የሚቆጠሩ ተዋጊዎችን በአል-ዋዳህ ድንበር በኩል ወደ የመን ለማስገባት እየተዘጋጀች ነው።

🇸🇦🇺🇸❌🇾🇪一 የሳዑዲው ልዑል መሐመድ ቢን ሰልማን፣ በትንትናው ዕለት ለትራምፕ ሁለት የስልክ ጥሪዎችን በማድረግ፣ አንሳረላህ (ሁቲ) ወደ ባብ አል-መንደብ የባሕር ወሽመጥ እየገሰገሱ በመሆኑ በአሜሪካ በኩል ጥቃቶችን እንዲያደርግ አሳስቦት ነበር፤ ይሁን እንጂ ትራምፕ እምቢ ብሏል። በሌላ በኩል ደግሞ፣ ዋሽንግተን ለሪያድ ዒላማዎችን ለመለየት የሚያስችሉ መረጃዎችን እና ዳታዎችን እንደምትሰጥ Axios ዘግቧል። አሁን አልአንሳር ወሽመጡን ተቆጣጥሯል።

🇾🇪 🇸🇦⚡️የየመን ጦር ኃይሎች፣ 'አላህ በኃይል ከሁሉ የላቀ፣ በቅጣት ከሁሉ የከበደ ነው' በሚል የሰየሙትን ወታደራዊ ዘመቻ በተሳካ ሁኔታ ማጠናቀቃቸውን አስታውቀዋል። በቀይ ባሕር ዳርቻ ላይም
🇾🇪 🇸🇦⚡️የየመን ጦር ኃይሎች፣ 'አላህ በኃይል ከሁሉ የላቀ፣ በቅጣት ከሁሉ የከበደ ነው' በሚል የሰየሙትን ወታደራዊ ዘመቻ በተሳካ ሁኔታ ማጠናቀቃቸውን አስታውቀዋል። በቀይ ባሕር ዳርቻ ላይም 5,400 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ግዛት ነፃ እንዳወጡም ተናግረዋል። የሳዑዲ ዓረቢያ የሆኑ እና ከሳዑዲ ጋር ግንኙነት ያላቸው መርከቦች ብቻ ሲቀሩ፣ የሌሎች ሀገራት መርከቦች ጉዞ ደህንነቱ የተጠበቀ እና የተፈቀደ እንደሚሆንም አክለው ገልጸዋል። በጥቃቱ ወቅት በአጠቃላይ 19 የሳዑዲ ድሮኖች ተመትተው ወድቀዋል፣ እና በሺዎች የሚቆጠሩ በሳዑዲ የሚደገፉ ኃይሎችም ተማርከዋል፣ ተብሏል። የየመን ጦር ኃይሎች በሳዑዲ ዓረቢያ ላይ የሚደረገው ከበባ እንደሚቀጥል ደግመው አስታውቀዋል።

🚨🇾🇪 ሁቲዎች (አንሳረላህ) መላውን የየመን የቀይ ባሕር ዳርቻ፣ ዱባብ እና ሙራድ ከተሞችን በመቆጣጠር፣ ነፃ ማውጣታቸውን አስታወቁ። 📌 በአካባቢው የሳዑዲ ቅጥረኛ ኃይሎች (PLC) ሙሉ በሙሉ
🚨🇾🇪 ሁቲዎች (አንሳረላህ) መላውን የየመን የቀይ ባሕር ዳርቻ፣ ዱባብ እና ሙራድ ከተሞችን በመቆጣጠር፣ ነፃ ማውጣታቸውን አስታወቁ። 📌 በአካባቢው የሳዑዲ ቅጥረኛ ኃይሎች (PLC) ሙሉ በሙሉ ፈርሰዋል፣ የቀሩት እጃቸውን ለመስጠት ድርድር አድርገዋል። የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና ሳዑዲ አረቢያ በደቡብ የመን በፉክክር የየራሳቸውን ኃይሎች ለመገንባት ዓመታት ያሳለፉ ሲሆን፣ አሁን እነዚያ ኃይሎች በአንድ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ተንደዋል፣ እንደ ዛሬው የአል ጀዚራ ዘገባ። ሁቲዎች (አንሳረላህ) ከኋላቸው እየተጠናከሩ ሳለ እነዚህ ሁለት ኃይሎች -የሳዑዲና የኤሜሬት- መሳሪያቸውን እርስ በራሳቸው ላይ በማዞር እየተዋጉም ናቸው። የሁለቱ እርስ በእርስ መዋጋት፣ ኤደን ከተማን በመያዝ ላይ፣ ለሁቲዎች ግስጋሴ ትልቅ በር ከፍቶ ይገኛል። ኤደን ከተማ፣ በደቡብ የመን የመጨረሻዋ በሳዑዲና በኤሜሬት ቅጥረኞች ቁጥጥር ሥር ያለች ከተማ ናት። በሚቀጥሉት 24 ሰዓታት ውስጥ፣ ምናልባት ኤደን በሁቲዎች ሥር ትወድቃለች ተብሎ ይጠበቃል።

🇱🇧⚡️🇮🇱 የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ቤኒያሚን ኔታንያሁ፡ ♫⋆。♪ ₊˚♬ ゚. ዘመቻውን ፈጥመናል፣ ዘመቻውን ፈጥሜያለሁ …

+2
🇮🇱❌🇱🇧🇱🇧 — በዛሬው ዕለት፣ IDF በደቡብ ሊባኖስ ከአሊ ታሄር ተራራ በታች ያለውን የሒዝቦላ የዋሻ መሠረተ ልማት ለማውደም፣ ከ1,100 ቶን በላይ ፈንጂዎችን ጥቅም ላይ እንዳዋለ ተናግሯል። የኒውክሌር ዓይነት ፍንዳታ ነበር የተባለው ይህ ፍንዳታ፣ የደቡብ ሊባኖስን ሰማይ ብርቱካናማ አድርጎታል። ምድርን ያናወጠው ፍንዳታ፣ በደቡብ ሊባኖስ፣ በቤቃ ሸለቆ እና በሰሜን እስራኤል በሬክታል ስኬል 4.2 ማግኒቲውድ የንዝረት ሞገድ አስከትሏል፣ ተብሏል።

🇮🇱⚡️'የሐማስ ከፍተኛ አባል' በጋዛ ከተማ በእስራኤል ጥቃት ተገድሏል — Shin Bet/IDF ፋራህ ሐመድ 'በሐማስ የዌስት ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት ውስጥ ከፍተኛ ባለሥልጣን' ነበር።

🇺🇸/🇮🇷/🇧🇭 የአሜሪካ የባህር ኃይል ሚኒስትር ሁንግ ካዎ ለCBS በሰጠው ቃለ መጠይቅ፦ ' ኢራናውያን ባሕሬንን ፈጽመው አውድመዋታል፣ በዚያ የነበረን የጦር ሰፈር አሁን የለም፣ የአሜሪካ የ
🇺🇸/🇮🇷/🇧🇭 የአሜሪካ የባህር ኃይል ሚኒስትር ሁንግ ካዎ ለCBS በሰጠው ቃለ መጠይቅ፦ '
ኢራናውያን ባሕሬንን ፈጽመው አውድመዋታል፣ በዚያ የነበረን የጦር ሰፈር አሁን የለም፣ የአሜሪካ የባሕር ኃይል የሚቆምበት ቦታ የለውም። ቦታውን [NSA ባሕሬን] መተው ይኖርብን፣ አይኖርብን የሚለውን እያጣራ ያለ የሥራ ቡድን በዚያ አለ። ከውትድና እይታ አንፃር፣ መመለስ የሚቻል አይመስለኝም።'

🇳🇱 የኔቶ ዋና ፀሐፊ ሩቶ (የውሃ ማጠራቀሚያ አይደለም)፣ ከፑቲን ጋር የሚደረግ ውይይትን ውድቅ አድርጓል። ሩቶ፣ የረጅም ጊዜ ስጋትን በመጥቀስ ከሩሲያ መሪ ጋር ድርድር እንደማያደርግ ገልጿል። ከ2029-2031 ለአውሮፓ ከሩሲያ አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ ዓመታት እንደሆኑም ተናግሮ፣ "መዘጋጀት ነው ያለብን እንጂ የምን መነጋገር ነው" ብሏል። ሩሲያ ከብሔራዊ ገቢዋ ከ10% በላይ እና ከግማሽ የሚጠጋውን የመንግስት በጀት ለጦር ኃይል ስትጠቀም፣ መላውን የኢንዱስትሪ መሠረቷን ወደ ወታደራዊ ዓላማዎች ስታዞር እና የጦር መሳሪያዎችን እያደራረበች ስታመርት፣ ዝም ብለን አናይም፣ ብሏል። ሩቶ ለዩክሬን ተጨማሪ ድጋፍ እንደሚሰጥ ቃል ገብቶ፣ የኔቶን አንድነት በማረጋገጥ፣ የሩሲያ አጋሮችን የመከፋፈል ሙከራዎች ቢኖሩም ለዩክሬን "የበለጠ" ነገር ለማድረግ ዝግጅታችንን ጨርሰናል ሲል አክሏል። የሩሲያ ዕጣ ፋንታ በዩክሬን ውስጥ ባለው ውድቀት ምክንያት ሽንፈት እንደሚያሳይ ተናግሯል። *-*-*- አሜሪካ ሠላም ለማምጣት ትጥራለች፣ አውሮፓ ያደናቅፋል። ከዚህ በፊት በዚህ ጉዳይ ብዙ አንስቻለው። አውሮፓ ከሩሲያ ጋር ሠላም አይፈልግም። አውሮፓ የሚፈልገው ጦርነት ነው፣ በእንግሊዝ፣ በጀርመን እና በፈረንሳድ ተመርቶ። ሩሲያ፣ አዎ የወደፊት ዕጣ ፋንታዋ ከባድ ነው የሚሆነው፣ አልተሳሳተም። ፑቲን ለዚህ በአንደኝነት ተጠያቂ ነው፣ ጦርነቱን በቶሎ የሚጨርስበትን አጋጣሚዎች ሁሉ አባክኖ ከዚህ ደርሷል። ጦርነቱን በማራዘም ለክፉ ጎረቤቶቹ የልብ ልብ የሰጠው እሱ ነው።

🇮🇱⚡️ — የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ በWestern Wall ላይ “ለሀገሪቱ ሰላም” ጸለዩ። *-*-* እነሱም የኛን አዲስ ዓመት ማክበር ጀመሩ እንዴ ውስጥ ውስጡን? ይሻላቸዋል!

🇸🇦 💥 — የሳተላይት ምስሎች፣ በሳዑዲ አረቢያ ከመዲና በስተ ደቡብ በኩል ትልቅ እሳት ያሳያሉ፣ ይህም ምናልባት በአካባቢው የነዳጅ ቧንቧዎችን ዒላማ ባደረገው በሁቲ አንሳርአላህ ጥቃት ምክንያት
🇸🇦 💥 — የሳተላይት ምስሎች፣ በሳዑዲ አረቢያ ከመዲና በስተ ደቡብ በኩል ትልቅ እሳት ያሳያሉ፣ ይህም ምናልባት በአካባቢው የነዳጅ ቧንቧዎችን ዒላማ ባደረገው በሁቲ አንሳርአላህ ጥቃት ምክንያት ሊሆን ይችላል።

🇾🇪 ❌ 🇸🇦 💥 — ለመጀመሪያ ጊዜ፣ የሳተላይት ምስሎች እንደሚያሳዩት፣ አንሳርአላህ ጥሬ ዘይትን ከባሕረ ሰላጤው ዳርቻ ከሚገኘው አብቃይቅ ወደ ቀይ ባሕር ወደሚገኘው ያንቡ የሚያጓጉዘውን የሳው
🇾🇪 ❌ 🇸🇦 💥 — ለመጀመሪያ ጊዜ፣ የሳተላይት ምስሎች እንደሚያሳዩት፣ አንሳርአላህ ጥሬ ዘይትን ከባሕረ ሰላጤው ዳርቻ ከሚገኘው አብቃይቅ ወደ ቀይ ባሕር ወደሚገኘው ያንቡ የሚያጓጉዘውን የሳውዲ ምስራቅ-ምዕራብ ቧንቧ ዒላማ አድርጎ መምታቱ ተገለጸ። 🔴 በግምት፣ በተመሳሳይ ጊዜ በቧንቧው መስመር ላይ በስድስት ቦታዎች እሳት ተነስቶ ይታያል።

💚💛 ❤️ በሀገር ውስጥም ሆነ ባሕር ማዶ ላላችሁ መላው ኢትዮጵያዊያን ወገኖቼ፣ እንዲሁም ለአፍሪካውያን ወንድሞቼ እና ለመላው የዓለም ሕዝብ፣ እንኳን ለ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት በሠላም እና በጤና
+3
💚💛 ❤️ በሀገር ውስጥም ሆነ ባሕር ማዶ ላላችሁ መላው ኢትዮጵያዊያን ወገኖቼ፣ እንዲሁም ለአፍሪካውያን ወንድሞቼ እና ለመላው የዓለም ሕዝብ፣ እንኳን ለ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት በሠላም እና በጤና አደረሳችሁ፣ ለማላት እወዳለሁ። በድጋሜ፣ መልካም አዲስ ዓመት 💐

⚡️🇸🇦🛢 – ሳዑዲ አረቢያ ባለፈው ወር የነዳጅ ምርቷ በሁቲዎች በተፈጠረው መስተጓጎል ምክንያት፣ በቀን ወደ 6.24 ሚሊዮን በርሜል ወድቋል፣ ይህም ከ1990 ወዲህ ዝቅተኛው ደረጃ እንደሆነ ለOP
⚡️🇸🇦🛢 – ሳዑዲ አረቢያ ባለፈው ወር የነዳጅ ምርቷ በሁቲዎች በተፈጠረው መስተጓጎል ምክንያት፣ በቀን ወደ 6.24 ሚሊዮን በርሜል ወድቋል፣ ይህም ከ1990 ወዲህ ዝቅተኛው ደረጃ እንደሆነ ለOPEC ሪፖርት አድርጋለች። ከሰሞኑ በጃዛን እና በአብሃ የነዳጅ ኢንዱስትሪዎቿ ላይ ከተደረጉት ጥቃቶች በኋላ፣ በዚህ ወር ይበልጥ ዝቅ ሊል ይችላል።