የቀጠናው ተመልካች
Open in Telegram
በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።
Show moreThe country is not specifiedThe category is not specified
4 330
Subscribers
-924 hours
-407 days
-8130 days
Posts Archive
4 332
🇪🇹⚡️በኢትዮጵያ፣ በገዢው ፓርቲ ብልጽግና ሰራዊት እና በሕዝባዊ ሰራዊቶች መካከል የሚደረገው ጦርነት ተፋፍሞ የቀጠለ ሲሆን፣ በውጭ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች፣ ለትግራይ ተዋጊዎች የላኳቸው FPV ድሮኖች፣ በቦታው ደርሰው በተዋጊዎች እጅ ሲከፈቱ የሚያሳይ ምስል፣ ሲዘዋወር ታይቷል።
በዩክሬን፣ በስፋት በሩሲያ ጦር ላይ የሚውሉት እነዚህ ጨዋታውን የቀየሩት ድሮኖች፣ አብዛኞቹ፣ በተመሳሳይ በውጭ በሚኖሩ የሀገሩ ተወላጆች ተገዝተው ወደ ዩክሬን የሚገቡ ናቸው።
ከ$100-$1500 ዶላር በሚያወጣ ወጪ የሚገዙት እነዚህ ድሮኖች፣ ካሜራ የተገጠመላቸው ሲሆን የተለያዩ ዓይነት ፈንጂዎችን፣ እና እንዸ ሞርታር ቅንቡላ ያሉ ተተኳሾችን መታጠቅ የሚችሉ ናቸው።
4 332
🇺🇸🇻🇪⚡️— የተባረረው የቬንዙዌላ ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ እና ባለቤቱ ሲሊያ ፍሎሬስ፣ የፍርድ ሂደታቸው ዛሬ በኒው ዮርክ ዳኛ ትዕዛዝ መሠረት፣ ከአንድ ዓመት በኋላ፣ በጁን 1፣ 2027 እንዲጀመር ታቅዷል።
*-*-*-
አስባችሁታል አሜሪካ በኢራን ቢሳካላት ኖሮ? አያቶላውን እንዲህ ሊያሳዩን ነበር። ጨቃኝ እኮ ናት አሜሪካን፣ ዊ! ኢራኖችን ላቲን አርጋ አስባቸው።
4 332
🇮🇷❌🇺🇸🇰🇼— የሳተላይት ምስሎች፣ በቅርቡ የተካሄደው የኢራን ጥቃት በኩዌት በሚገኘው አህመድ አል-ጃበር አየር ኃይል ማእከል የAN/FPS-117 ረጅም ርቀት ያለው የቅድመ-ማስጠንቀቂያ ራዳርን እንዳወደመ ያሳያሉ።
➡️በ Lockheed Martin የተመረተው AN/FPS-117፣ በግምት 470 ኪሎ ሜትር ርቀት ያለው የ3D የአየር ክትትል ራዳር ሲሆን፣ ከአሜሪካ እና ከጥምረት የአየር መከላከያ አውታረ መረቦች ጋር በመዋሃድ በኩዌት ሲሰራ ነበር።
4 332
🇮🇷⚡️የኢራን ጦር ሃይሎች ቃል አቀባይ፣ ብርጋዴር ጄኔራል ሼካርቺ፦ እንድንገባ በተገደድንበት በሦስተኛው ዙር የጠላት ጦርነት፣ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ውስጥ የሚገኘውን፣ ግዙፍ የጠላት የዳታ ማዕከልን አውድመናል። ይህ ማዕከል፣ በአረብ ኤምሬትስ ውስጥ ተሠርቶ ለመጠናቀቅ 20 ዓመታት የወሰደበት ሲሆን፣ የተቋቋመው፣ በአውሮፓውያን፣ በጽዮናዊው አካላት እና በአሜሪካ እርዳታ እና ኢንቨስትመንት ቀጠናውን ለመቆጣጠር ነበር። የዳታ ማዕከሉን በመምታታችን ዓይናቸውን አውጥተነዋል።
4 332
🇮🇷 🔻🇸🇦| የኢራን ጥቃት በሳዑዲ አረቢያ የኪንግ አብዱል አዚዝ አየር ኃይል ማእከልን ዒላማ አድርጎ የተወሰደ ሲሆን፣ በአካባቢው ፍንዳታዎች እንደተከሰቱ ተዘግቧል።
4 332
🇮🇷 🔻🇸🇦| በሳውዲ አረቢያ ኮባር ውስጥ ፍንዳታዎች ተሰምተዋል። በኪንግ ፋሐድ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የሚካሄዱ ተግባራት እንደተቋረጡ ተዘግቧል። በኪንግ ፋሐድ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያም፣ ተጨማሪ ፍንዳታዎች ሪፖርት ተደርገዋል።
4 332
🇸🇦 | የሳዑዲ ተቃዋሚ ሚዲያ እንደዘገበው፡ በየመን ጦር ሃይሎች የተሰጠውን እና በብሪጋዲየር ጄኔራል ያህያ ሳሪ የተገለጸውን መግለጫ ተከትሎ፣ እና በመባባስ ላይ ባለው የቀጠናው ክስተቶች ምክኒያት፣ ሙሐመድ ቢን ሰልማን ወደ Bunker (ጥብቅ ዋሻ) በመሸሽ ተደብቋል።
4 332
🇮🇷⚡️🇺🇸 በአሁኑ ሰዓት አሜሪካ በኢራን ላይ ከባድ ድብደባ እየፈጸመች ትገኛለች። ድብደባው፣ ከሌላው ጊዜ በበለጠ መጠኑ እና ስፋት ከፍተኛ ነው።
በዚህ ሰዓት የሚሰሙ ፍንዳታዎች፣ ከጥቃቱ ቦታ ሩቅ አካባቢ ያሉ ቤቶችን መስኮቶች እያንቀጠቀጠ ነው ይላሉ፣ ነዋሪዎች።
4 332
🇺🇸🇮🇷⚡️— The Atlantic ጋዜጣ የጠቀሰው ከፍተኛ የአሜሪካ ባለሥልጣን እንደተናገረው፣ የመጀመሪያ የአሜሪካ የስለላ ግምገማዎች እንደሚያመለክቱት፣ የቅርብ ጊዜው የአሜሪካ ጥቃቶች የኢራንን ባሕሪ ለመለወጥ ብዙም አልረዱም፣ ሲል ተናግሯል።
"ጥቃቶቹ ኢራንን ተስፋ እንዳደረግነው፣ መንገዳቸውን እንዲለውጡ አላደረጋቸውም፣ እንዲያውም አባብሷቸዋል።"
➡️ ለፕሬዝዳንት ትራምፕ ቅርብ የሆኑ ሁለት ሰዎች በመጪው ምርጫ የሪፐብሊካን ተስፋዎችን ለማጠናከር በመጨረሻው ደቂቃ ትራምፕ ጦርነቱን ለማቆም ሊያስብ እንደሚችል ተናግረዋል።
➡️ የአሜሪካ ባለሥልጣናት ለThe Atlantic እንደተናገሩት፣ ኢራን የአሜሪካ የባሕር ኃይል መርከቦችን ዒላማ ማድረጓን አጠናክራለች፣ ሁለቱም ወገኖች ግጭቱን አባብሰውት ቀጥለዋል፣ ብለዋል።
4 332
🇷🇺⚡️የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አምባሳደር፣ ማራት በርድዬቭ፣ ለTASS እንደተናገሩት፣ አሜሪካ ፕሬዝዳንት ፑቲን በነሐሴ 2026 በማያሚ በሚካሄደው የG20 ጉባኤ ላይ እንዲገኙ እንደምትፈልግ ምልክት እያሳየች ነው።
ዲፕሎማቱ እንደተናገሩት፣ ትራምፕ ተሳትፎውን፣ "ጠቃሚ" ብሎ በይፋ ገልጾታል፣ ይህም "የፖለቲካ መስተንግዶ ሳይሆን ምክንያታዊ አመክንዮ ነው"፣ ምክንያቱም በመሪዎች መካከል የሚደረግ ውይይት ወሳኝ ነው እና "ያለ ሩሲያ አደጋዎችን እና ቀውሶችን መቆጣጠር አይቻልም።"
*-*-*-
አይገርማችሁም? የዛሬ 5 ዓመት ሩሲያ የG8 አባል ነበረች። G7 ቡድን፣ ሩሲያን ለመጨመር ሲል በ1997 G8 ተብሏል።
ከዚያ በኋላ፣ አሁን በመሪዎቿ እንዝህላልነት የተነሳ በጦርነቱ ስትንደፋደፍ፣ ከG8 ስብስብ አባረሯት።
ዛሬ G20፣ እነ ሕንድ፣ እነ ኢንዶኒዢያ፣ እነ ሜክሲኮ፣ እነ ቱርክ እና ቻይና …… ያሉበት ስብስብ ለመካተት "አሜሪካ ምልክት" እያሳየችን ነው ይላሉ። በዚህ ደረጃ ነው መሪዎቿ የፈጠፈጧት ሩሲያን።
ይታያችሁ፣ ለG20ም የሉበትም፣ እንደው ብጋበዝ ብላ ነው የፑቲን ሩሲያ ከውጭ የምትቀላውጠው።
አሁንም ለሩሲያ ጊዜው አልረፈደም፣ ይሄን ጦርነት ባለ በሌለ ኃይል ማሸነፍና ማጠናቀቅ ይገባል። ሌሎች ኃይሏን እንዲያዩ እና እንዲያከብሯት ይገባል።
በዚህ ዓለም ላይ፣ በጥንካሬና በጥንካሬ ብቻ ነው፣ ደረጃ ማግኘት የምትችለው!
ፑቲን ዩክሬን ላይ እንደሚልፈሰፈሰው፣ G50 የሚባል ስብስብ ቢኖርም እንኳ፣ የሚጋብዘው አይኖርም። ስለተልፈሰፈሰ፣ አይመጥነውም።
4 332
🇸🇾🇱🇧🇮🇱 ሶሪያ ከእስራኤል ጎን በመሆን እሷን ለመከላከል ትመጣለች፣ በካን ኒውስ ዘገባ መሠረት።
የሶሪያ የደህንነት ተቋም አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ በሂዝቦላ ላይ ለሚደረጉ ክንዋኔዎች የአደጋ ጊዜ ዕቅዶችን፣ ከእስራኤል አመራሮች ጋር በትብብር እያዘጋጀ ነው።
ለመንግሥት ቅርብ የሆነ የሶሪያ የደህንነት ምንጭ እንደተናገረው፣ በደማስቆ ይፋዊ መልእክት እና ከመድረክ በስተጀርባ በሚደረገው እቅድ መካከል፣ ልዩነት አለ።
የሶሪያ የፀጥታ ኃይሎች፣ በሶሪያ ውስጥ ያለውን ማንኛውንም የሂዝቦላ መገኘት እንዲገጥሙ ታዝዘዋል።
ትራምፕ በሊባኖስ ከሂዝቦላ ጋር ያለውን ሥራ እንዲጨርስ የሶሪያውን ፕሬዝዳንት አሕመድ አል- ሻርን እንደላከው በተደጋጋሚ ገልጿል።
*-*-*-*-
4 332
+1
🇺🇦 ሰበር ዜና፡ ኦሌክሳንድር ሲርስኪ ከዩክሬን የጦር ዋና አዛዥነት ቦታው ተነስቷል።
ሚካይሎ ድራፓቲ (ኩስምንም ያለው) አዲሱ የዩክሬን የጦር ኃይሎች አዛዥ ሆኖ ተሾሟል።
*-*-*-
ዩክሬን ከፍተኛ ወታደራዊ ምስቅልቅል ውስጥ እየገባች ይመስላል። ዘለንስኪ ባለፈው ሳምንት በሕዝቡ ዘንድ ተወዳጅ የነበረውን የመከላከያ ሚንስትሩን ማንሳቱን ተከትሎ የተፈጠረው ፖለቲካዊ ቀውስ፣ እስካሁን አልበረደም። የተቃውሞ ሰልፎችም በተለያዩ ከተሞች እንደቀጠሉ ናቸው። ባለፈው ሳምንት በዚህ ጉዳይ በስፋት ዘግበናል።
የመከላከያ ሚኒስትሩ ለመነሳቱ ሕዝቡ ተጠያቂ ያደረገው፣ ዛሬ የተነሳውን የጦር ሠራዊቱን ዋና አዛዥ ነበር።
ምናልባት፣ ዘለንስኪ ይህን አዛዥ ዛሬ ያነሳው፣ የሕዝቡን ቁጣ ለማብረድ ይሆናል።
ይበርዳል?
4 332
+1
🇬🇧🇮🇷 ሰበር ዜና፡ ወደ ሥልጣን ከመጣ ገና 2ኛ ቀኑን የያዘው የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር በርናም፣ እንግሊዝን ወደ ጦርነት እየወሰዳት ነው።
አዲሱ የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር በርናም፣ አሜሪካ በኢራን ላይ ለምታደርገው ጥቃቶች የዩናይትድ ኪንግደምን ጦር ሰፈኖችመጠቀምን አጽድቋል፣ እንደ በCBS ዘገባ
4 332
+1
🇺🇸🇮🇷⚡️The Washington Post, የፔንታገን ባለሥልጣናት ከኢራን ጥሩ ዜና ባለማምጣት ቅጣት እንዳይደርስባቸው በመፍራት፣ የሚሳይሉን እጥረት ጉዳይ ከመከላከያ ሚኒስትር ፒት ሄግሴት እና ከሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት እየደበቁ መሆናቸውን ዘግቧል።
4 332
🇺🇸🇱🇧⚡️ — ፕሬዝዳንት ትራምፕ በTruth Social በኩል፦
ሀገሩን ለመለወጥ አስደናቂ ስራ ከሰራው ከሊባኖስ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ አውን ጋር ከተገናኘሁ በኋላ፣ አሜሪካውያን ይህችን ውብ ሀገር በቀላሉ እንዲጎበኙ ሁሉም የአሜሪካ አየር መንገዶች በቀጥታ ወደ ሊባኖስ እንዲበሩ አስተዳደሬን አዝዣለሁ። ተስፋ እናደርጋለን፣ ሌሎች ሀገራትም ተመሳሳይ ነገር ያደርጋሉ። ይደሰቱ!*-*-*- - እረ የኛንም መጥተው ይጎብኙልን፣ ሚስተር ፕሬዝዳንት፣ ቀበና ወንዝን ሰርተናል። - ሂዲ፣ ግማታም!
4 332
🇸🇦⚡️🇾🇪 የሁቲ የባህር ኃይል እገታ የሳዑዲ የነዳጅ ታንከሮች በቀይ ባሕር ውስጥ ወደ ኋላ እንዲመለሱ አስገድዷቸዋል፣ ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
➡️ የሳዑዲ ነዳጅ የሚጭኑ ሁለት ታንከሮች — አንዱ ወደ ቻይና፣ አንዱ ወደ ሕንድ — ሁቲዎች መርከቦች በሳዑዲ ወደቦች እንዳይጭኑ ወይም እንዳያወርዱ ካስጠነቀቁ በኋላ፣ ወደ ግብፁ ሱዊዝ አቅጣጫ መስመራቸውን ቀይረው ተመልሰዋል።
➡️ ሦስተኛው ታንከር ለመጫን ያኑብ መጫኛ ጣቢያ ከመድረሱ በፊት ተመልሷል።
➡️ በሱዊዝ በኩል ወደ እስያ ዞሮ ለመሄድ ጭነቶች ላይ ሳምንታትን የጉዞ ጊዜን ይጨምራል።
*-*-*-
ሳዑዲዎች በሰው ውሃ፣ ሌሎች በሚያዙበት፣ ተከበው እንደሚኖሩ የገባቸው ገና አሁን ነው።
በሌላ አባባል፣ የትራምፕን ቃል ልበደርና፣ "መጫወቻ ካርድ" የላቸውም።
መውጫቸውም መግቢያቸውም የሌሎች ነው።
4 332
🇮🇷🇺🇸⚡️ኢራን በባሕሬን የእስራኤል ኤምባሲን አጥቅታለች። የከተማው ሰማይም በተለያዩ ጥቃቶች ጭስ ጥቁር ለብሶ ይታያል።
በተመሳሳይ፣ በሰሜን ኢራቅ ኢርቢል (ኩርድ) ከተማ ያልተቋረጡ የሚሳዬልና የድሮን ጥቃቶች፣ በኢራን ኃይሎች እየተሰነዘሩ ናቸው። በዚህም፣ ቁጥራቸው ያልታወቀ የአሜሪካ ወታደራዊ አባላቶች ሳይቆስሉ ወይም ሳይሞቱ እንዳልቀረ ተነግሯል።
በሌላ በኩል፣ በእንግሊዝ ከአሜሪካ የጦር ሰፈር በርካታ B-1 ቦንብ ጣይ አይሮፕላኖች ወደ ቀጠናው እያመሩ ታይተዋል።
4 332
🇪🇹⚡️በኢትዮጵያ፣ የአማራ ግዛቶች ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ቦታዎች፣ በአማራ ታጣቂዎች (ፋኖ) እና በገዢው ፓርቲ ሰራዊት መካከል፣ የሚደረገው ጦርነት አሁንም እንደቀጠለ ነው።
አብዛኛው የአማራ ግዛቶች፣ እንደ ትግራይ ግዛቶች ሁሉ፣ በአሁኑ ጊዜ ሙሉ በሙሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ አብይ አህመድ ከሚመራው መንግሥት፣ ቁጥጥር ውጭ ናቸው።
4 332
🇷🇺⚡️🇺🇦🚨 ሌሊቱን፣ የሩሲያ የአየር መቃወሚያዎች፣ 209 የዩክሬን ድሮኖችን በሩሲያ ክፍለ ሀገራት፣ በአዞቭ ባሕር እና በጥቁር ባሕር ላይ ጥለዋል -- የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር።
