የቀጠናው ተመልካች
前往频道在 Telegram
በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።
显示更多未指定国家未指定类别
4 321
订阅者
+824 小时
-47 天
-7130 天
帖子存档
4 321
🇾🇪የሕያ ሰዓር፣ የየመን የጦር ኃይል ቃል አቀባይ፦
🔴 ባለፉት 48 ሰዓታት ውስጥ፣ በሳዑዲ የሚመራው ጥምረት 129 የአየር ድብደባዎችን በማካሄድ የታኢዝ፣ የማእሪብ፣ የሁደይዳ፣ የአል-ጃውፍ፣ የሳዓዳ፣ የኦምራን እና የሃጃ አውራጃዎችን ዒላማ አድርጓል።
✈️❌✈️ እነዚህ የአየር ድብደባዎች የተካሄዱት በ F15 እና ታይፎን አውሮፕላኖች ሲሆን፣ እነዚህም በካሚስ ሙሻይት እና ታይፍ ከሚገኙት የሳዑዲ ጥምረት ወታደራዊ ማእከላት ተነስተው ነው።
በአላህ ጸጋ እና ኃይል፣ በሕዝባችን ላይ የተፈጸሙት እነዚህ ጥቃቶች ያለ ቅጣት እና በቀል አይቀሩም።
4 321
🇾🇪❌🇸🇦 — ከትናንት የተገኙ የሳተላይት ምስሎች እንደሚያሳዩት፣ በሁቲ (አንሳርአላህ) ጥቃቶች ምክንያት በአራምኮ የአብሃ ነዳጅና ጋዝ ኢንዱስትሪ ላይ ከፍተኛ የሆነ ጉዳት ደርሷል፣ ቢያንስ ስምንት የነዳጅ ማከማቻና ማጠራቀሚያዎች ሙሉ በሙሉ የወደሙ ሲሆን ስምንት ሌሎች ደግሞ ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል።
ተቋሙ በአሁኑ ሰዓት ከአገልግሎት ውጭ ሆኗል።
4 321
🇺🇸 🇮🇪 🇬🇧 — የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቅዳሜ ዕለት ከታኦይሴች ሚሼል ማርቲን ጋር በደብሊን ባደረገው ጉብኝት ላይ ንግግር ሲያደርግ፣ አየርላንድ አንድ ሆና ማየት “በጣም እንደሚፈልግ” ተናግሯል።
ምንም አይነት ችግር መፍጠር አልፈልግም፣ ነገር ግን ሊነገራችሁ ይገባል፣ አንድ ሆናችሁ ማየትን እወዳለሁ። በሁለቱም በኩል ወዳጆች አሉኝ፣ ጥሩ ሰዎች። ሁለታችሁም አንድ ዓይነት ሕዝብ ናችሁ፣ የአየርላንድ ሰዎች ናችሁ። እርቅና ውህደት በመጨረሻ የሚከሰት ነው፣ አሁንም እንኳን ሊከሰት የሚችል ነው፣ እና ያንን አስባችሁ ሥሩበት፣ ነገር ግን ዩናይትድ ኪንግደም ስለዚህ ጉዳይ የምትናገረው ይኖራት ይሆናል፣ አላውቅም፣ብሏል።
4 321
🇺🇸 🇮🇪 🇬🇧 — የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቅዳሜ ዕለት ከታኦይሴች ሚሼል ማርቲን ጋር በደብሊን ባደረገው ጉብኝት ላይ ንግግር ሲያደርግ፣ አየርላንድ አንድ ሆና ማየት “በጣም እንደሚፈልግ” ተናግሯል።
ምንም አይነት ችግር መፍጠር አልፈልግም፣ ነገር ግን ሊነገራችሁ ይገባል፣ አንድ ሆናችሁ ማየትን እወዳለሁ። በሁለቱም በኩል ወዳጆች አሉኝ፣ ጥሩ ሰዎች። ሁለታችሁም አንድ ዓይነት ሕዝብ ናችሁ፣ የአየርላንድ ሰዎች ናችሁ። እርቅና ውህደት በመጨረሻ የሚከሰት ነው፣ አሁንም እንኳን ሊከሰት የሚችል ነው፣ እና ያንን አስባችሁ ሥሩበት፣ ነገር ግን ዩናይትድ ኪንግደም ስለዚህ ጉዳይ የምትናገረው ይኖራት ይሆናል፣ አላውቅም፣ብሏል።
4 321
📊 🇺🇦⚡️🇷🇺 የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው አሃዝ፣ በአጠቃላይ፣ ልዩ ወታደራዊ ዘመቻው ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ፣ ጠላት ይህን አጥቷል፡
▫️ 674 አይሮፕላን፣
▫️ 284 ሄሊኮፕተር፣
▫️ 234,073 ሰው አልባ ድሮኖች፣
▫️ 672 የአየር መቃወሚያ ሲስተሞች፣
▫️ 30,899 ታንኮች፣
▫️ 7, 101 ሰው አልባ ተሽከርካሪዎች፣
▫️ 36,435 መድፎች እና
▫️ 71,692 ብረት ለበስ ወታደራዊ መኪኖች።
*-*-*-
ማስታወሻ፡ የዩክሬን መንግሥት ከሞላ ጎደል በዚህ ሩሲያ በምታወጣው አሃዝ ላይ ተቃውሞ ሲያሰማ አይደመጥም። አሃዙ፣ ከብዙ መመሳከሪያዎች ጋር የሚወጣ በመሆኑ፣ ወደ እውነተኛው የተጠጋ መረጃ ስለሆነ።
በተመሳሳይ ሩሲያም በዩክሬን ጦርነት ያጣችው ቁስና ንብረት፣ ከዚህ ቢያንስ፣ ምናልባትም ቢቀራረብ እንጂ፣ አይበልጥም
4 321
🇺🇦⚡️🇷🇺 ዜሌንስኪ እሱ እና ፑቲን በማያሚ በሚካሄደው የG20 ስብሰባ ላይ መገናኘት እንዳለባቸው ተናግሯል፦ “እመጣለሁ። መድረስ፣ መገናኘት፣ መነጋገር እና ውሳኔዎችን መወሰን አለብን። ጉዳዩ በቃላት አይደለም - እኔ ለእሱ የምናገረው ወይም እሱ ሊነግረኝ የሚፈልገው። ያ ጉዳይ አይደለም። ውጤቱ ብቻ ነው የሚያስፈልገው። ውጤቱ አስፈላጊ ነው። ያ ብቻ ነው። አይፍራኝ።"
4 321
🇷🇺🇺🇸 አሜሪካ ሩሲያን ወደ G20 የኢነርጂ ሚኒስትሮች ስብሰባ ጋብዛለች።
ዩናይትድ ስቴትስ ሩሲያን ከሴፕቴምበር 14-16 በሂዩስተን ወደ ሚካሄደው የG20 የኢነርጂ ሚኒስትሮች ስብሰባ ጋብዛለች፣ ሲል ሮይተርስ የዋይት ሃውስ ተወካይን ጠቅሶ ዘግቧል።
4 321
🇸🇦⚡️ — ላለፉት ስድስት ወራት ለሳውዲ አረቢያ መንግስት እና ለሀገሪቱ፦
— ኢራን ሆርሙዝን ተቆጣጠረች፣ — የአርማኮ መሠረተ ልማቶች በኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ጦር ተመቱ፣ — የአርማኮ መሠረተ ልማቶች በሁቲዎች ተመቱ — ሁቲዎች የቀይ ባሕር መሿለኪያውን ተቆጣጠሩ፣ — ሁቲዎች በሳዑዲ ላይ ኬላ ዘርግተው ማዕቀብ ጣሉ፣ — በየመን ለዓመታት የገነባችው ኃይሏ፣ በአንድ ሳምንት ውጊያ እንደ ጉም በኖ ጠፋ፣ — የነዳጅ ምርቷ ከ1990 ወዲህ እጅግ ዝቅተኛው ሆኖ ታየ፣ — ከምዕራብ ወደ ምሥራቅ የተዘረጋው የነዳጅ ማስተላለፊያ ትቦዋ በድሮን ተመትቶ ተዘጋ፣ — ከቱርክ እና ከፓኪስታን ጋር የተጣመረችበት የመካ መከላከያ ጥምረት፣ ሥራው ማውገዝ ብቻ ሆኖ ተገለጠ።*-*-*- የናንተን አላውቅም፣ እኔ ግን ሳዑዲ እንዲህ ስትሆን ቁጭ ብዬ ማየት አልችልም፣ ጅሃድ ሄጄ ልዋጋላት፣ እቅርታ!
4 321
⚡️🇺🇸🇸🇦🇾🇪 ሪያድ የመጨረሻ ውሳኔ ባትሰጥም፣ ከአሜሪካ ተሳትፎ ነጻ በሆነ መልኩ በሁቲዎች ላይ ትልቅ ወታደራዊ ዘመቻ ልትጀምር እንደምትችል ምልክት ሰጥታለች።
በየመን ውስጥ ውጊያው እየቀጠለ ባለበት ወቅት ዩናይትድ ስቴትስ ሁኔታውን በቅርብ እየተከታተለች ሲሆን ለሳዑዲ አረቢያ የስለላ መረጃ እና የዒላማ ድጋፍ እያደረገች ነው ABC NEWS
4 321
+1
🇳🇴 የኖርዌይ ልዕልት አስትሪድ ዛሬ በ94 ዓመቷ፣ ከወንድሟ ከንጉሥ ሃራልድ V ከሁለት ሳምንታት ሞት በኋላ እና በተሽከርካሪ ወንበር የመንግስት የቀብር ሥነ ሥርዓቱን ከተካፈለች ከሁለት ቀናት በኋላ፣ ሞታለች።
ቤተ መንግሥቱ ከዚህ ቀደም በቤተ መንግሥቱ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከወንድሟ መቃብር አጠገብ ብቻዋን ተቀምጣ የሚያሳዩ ፎቶዎችን አውጥቷል።
*-*-*-
አውርፓዊያን ብልህ ናቸው፣ ሁሉም በሚባል ደረጃ የንግሥና ሥርዓታቸውን ጠብቀው ይዘዋል። ኔዘርላንድ፣ ዴኒማርክ፣ ኖርዌይ፣ ስዊድን፣ እንግሊዝ … ። ዳግም ለማምጣት የሚያስቡ፣ አልባኒያ፣ ሮማኒያ፣ ጆርጂያ …።
አንዱና ዋናው የስኬቶቻቸው ምንጭ! እለዋለሁ እኔ፣ የንግሥናን ሥርዓት። የእኛን በገዛ እጆቻችን አሳ*ርደው አስጠፉን።
ከዚያ ጊዜ በኋላ ታዲያ፣ ጉዟችን ቁልቁል ገደል ሆኗል።
4 321
🇸🇦⚡️ — ሰበር ዜና፦ የሳዑዲ ዓረቢያ የኃይል ሚኒስቴር፣ ሐሙስ ዕለት፣ በሪያድ እና በመዲና አካባቢዎች በነዳጅ መስመር ላይ በተከታታይ በደረሱ የሁቲ ጥቃቶች ምክንያት፣ እንደ ቅድመ ጥንቃቄ እርምጃ፣ ምሥራቅ-ምዕራብ የነዳጅ መተላለፊያ የቧንቧ መሥመርን ለጊዜው እንደዘጋ አስታወቀ።
ጥቃቶቹ በርካታ የአካል ጉዳት እንዲደርስ ምክንያትም ሆነዋል።
CNN እንደዘገበው፣ የአሜሪካ ወታደራዊ ባለስልጣናት ሁቲዎች ቁልፍ መሠረተ-ልማት የሆነውን ይህን መተላለፊያ ቧንቧ ማን በሰጣቸው መረጃ ሊመቱ እንደቻሉ በማጣራት ላይ ናቸው።
4 321
🇸🇦⚡️ — ሰበር ዜና፦ የሳዑዲ ዓረቢያ የኃይል ሚኒስቴር ሐሙስ ዕለት በሪያድ እና በመዲና አካባቢዎች በነዳጅ መስመር ላይ በተከታታይ በደረሱ ጥቃቶች ምክንያት፣ እንደ ቅድመ ጥንቃቄ እርምጃ፣ ምሥራቅ-ምዕራብ የነዳጅ መተላለፊያ የቧንቧ መሥመርን ለጊዜው እንደዘጋ አስታውቋል።
ጥቃቶቹ በርካታ የአካል ጉዳት እንዲደርስ ምክንያትም ሆነዋል።
CNN እንደዘገበው፣ የአሜሪካ ወታደራዊ ባለስልጣናት ሁቲዎች ቁልፍ መሠረተ-ልማት የሆነውን ይህን መተላለፊያ ቧንቧ ማን በሰጣቸው መረጃ ሊመቱ እንደቻሉ በማጣራት ላይ ናቸው።
4 321
— 🇾🇪 የየመን ጦር ኃይሎች (አንሳርአላህ-ሁቲ)፣ በቀይ ባሕር ባብ አል-ማንዳብ ወሽመጥ የመጀመሪያ የባሕር ወታደራዊ ጥበቃቸውን በማካሄድ፣ በመስመሩ ውስጥ ባለው የመርከብ ትራንስፖርት ላይ ክትትል እያደረጉ ነው።
4 321
🇮🇷🇾🇪 መካከለኛው ምሥራቅ በእምቢተኞች ትግል መሠረት፣ ወደ አዲስ ምዕራፍ ተሸጋግሯ።
ሆርሙዝ ወሽመጥ፣ በኢራን
ቀይ ባሕር ወሽመጥ፣ በየመን፣
ተገድቧል!
4 321
— 🇾🇪 በምዕራባዊው የባሕር ዳርቻ የአንሳረላህን (ሁቲ)፣ በሳዑዲና በግብአበሮቿ ላይ ያስመዘገበውን ድል እና ያሳካውን ዘመቻ ለማክበር፣ በርካታ የየመን ሕዝብ በዋና ከተማዋ፣ ሰንዓ፣ ተሰብስበዋል።
4 321
🇸🇦/🇾🇪 ሰበር ዜና፦ የጦር ተሽከርካሪዎችን፣ የጭነት መኪናዎችን እና ተዋጊ ቅጥረኞችን ጨምሮ አዲስ የደረሱ ብዙ የሳዑዲ ተጨማሪ ኃይሎች፣ በምሥራቃዊ የአል-ጃውፍ ግዛት በባለስቲክ ሚሳይሎች ዒላማ ተደርገዋል – Saba News
4 321
+1
🇮🇱🇾🇪⚡️ — አንድ የእስራኤል ከፍተኛ ባለሥልጣን ለቻናል 12 እንደተናገረው፣ የሁቲ (አንሳርአላህ) የባብ አል-ማንደብ የባሕር ወሽመጥ ቁጥጥር በዋነኝነት በጂኦግራፊው ምክንያት አሁን በሆርሙዝ ካለው ሁኔታ የበለጠ ለመርከብ ትራንስፖርት ስጋት ይፈጥራል፣ ብሏል።
ከፔሪም (ማዩን) ደሴት አልፎ ያለው የምሥራቃዊ የመርከብ መተላለፊያ ስፋቱ ወደ ሦስት ኪሎ ሜትር ብቻ ሲሆን፣ የሚያልፉ መርከቦች በቀጥታ በሁቲ ዓይኖች እይታ ውስጥ ያስገባቸዋል።
“በፀረ-ታንክ ሚሳይሎች በፈለጉት ሁሉ ላይ መተኮስ ይችላሉ። መርከቦቹን በገዛ ዓይኖቻቸው ማየት ይችላሉ። ልዩነቱ ይህ ነው” ብሏል ባለሥልጣኑ።
በአንፃሩ በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦችን ለመቆጣጠር ኢራን፣ ሳተላይት ምስሎችን፣ guided ሚሳዬሎችን፣ ፈጣን ጀልባዎችን እና ድሮኖችን መጠቀም ያስፈልጋታል፣ ሲል ተናግሯል።
*-*-*-
እያለ ያለው፣ እነዚህ ሽርጣም የየመን ተዋጊዎች ድንጋይ ላይ ቁጭ ብለው ጥርሳቸው እየፋቁ አላፊ አግዳሚ መርከብን መቆጣጠር ይችላሉ ነው፣ ና አንተ በዚ ግባ፣ ምን ታያለህ እዛጋ? ና ወደዚ … ምናምን እያሉ።
ሳዑዲን በምታክል ሀገር ላይ እነዚህን ሲቢሮ የላከ ፈጣሪ …
4 321
🇸🇦⚡️🇾🇪 ሳዑዲ ዓረቢያ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን እና በሺዎች የሚቆጠሩ ተዋጊዎችን በአል-ዋዳህ ድንበር በኩል ወደ የመን ለማስገባት እየተዘጋጀች ነው።
4 321
🇸🇦🇺🇸❌🇾🇪一 የሳዑዲው ልዑል መሐመድ ቢን ሰልማን፣ በትንትናው ዕለት ለትራምፕ ሁለት የስልክ ጥሪዎችን በማድረግ፣ አንሳረላህ (ሁቲ) ወደ ባብ አል-መንደብ የባሕር ወሽመጥ እየገሰገሱ በመሆኑ በአሜሪካ በኩል ጥቃቶችን እንዲያደርግ አሳስቦት ነበር፤ ይሁን እንጂ ትራምፕ እምቢ ብሏል።
በሌላ በኩል ደግሞ፣ ዋሽንግተን ለሪያድ ዒላማዎችን ለመለየት የሚያስችሉ መረጃዎችን እና ዳታዎችን እንደምትሰጥ Axios ዘግቧል።
አሁን አልአንሳር ወሽመጡን ተቆጣጥሯል።
