en
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

Open in Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

Show more
The country is not specifiedThe category is not specified
4 330
Subscribers
-924 hours
-407 days
-8130 days
Posts Archive
🇺🇦🇷🇺⚡️ ጭስ፣ ከሞስኮ ቅዱስ ባሲል ካቴድራል ሲወጣ ታይቷል። የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች በቦታው ናቸው፣ እሳቱን ለአሁን የተቆጣጠሩት ይመስላል። *-*-* መቱት እንዴ እነ አጭሬ? አሁን አሁን እኮ ምንም ነገር አይታመንም። "ድንገት" ነው የተፈጠረው፣ የሚባል ነገር ቀርቷል።

+3
🇺🇦🇷🇺⚡️ኪየቭ፣ በአሁኑ ሰዓት በከባድ የሩሲያ ጥቃት ሥር ትገኛለች። ፍንዳታዎቹ "ጆሮ የሚበጥሱ" ናቸው። በመላው ኪየቭ መብራት ሄዷል።

🇺🇸🇮🇷⚡️አሜሪካ በኢራን ላይ ለቀናት የሚቆይ አዲስ የጥቃት ዙር ልትጀምር ተዘጋጅታለች — WSJ ግብ፦ ቴህራንን እጅ እንድትሰጥ ማስገደድ።

🇮🇷🇺🇸🇮🇱 AXIOS: አሜሪካ የኢራንን መሠረተ ልማቶቿን ለማውደም ዝግጅቷን እያደረገች ነው፣ እስራኤልም በድብደባው ልትሳተፍ ትችላለች።

🇺🇸🇮🇷⚡️- አስቸኳይ ዜና፦ Wall Street Journal እንደዘገበው፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕ የኢራን መንግሥት እንዲሸነፍ ለማስገደድ በማሰብ፣ አዲስ ጥቃት እንዲደረግ አዝዘዋል። ጥቃቶቹ፣ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ላይ ሊጀምሩ ይችላሉ እና ለብዙ ቀናት ይቆያሉ ተብሎ ይጠበቃል። ባለሥልጣናት እንደሚሉት፣ በቅርብ ሳምንታት ውስጥ፣ ትራምፕ የጊዜያዊ ሰላም ስምምነቱ ትርጉም የለሽ እንደሆነ ለታማኝ ሰዎቹ ቅሬታውን አሰምቷል፣ እንዲሁም እሱ የማይሠራ መሆኑን ሁልጊዜ ያውቅ እንደነበር  ጨምሮ ተናግሯል።

🇺🇸🇮🇷⚡️- አስቸኳይ ዜና፦ Wall Street Journal እንደዘገበው፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕ የኢራን መንግሥት እንዲሸነፍ ለማስገደድ በማሰብ፣ አዲስ ጥቃት እንዲደረግ አዝዘዋል። ጥቃቶቹ፣ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ላይ ሊጀምሩ ይችላሉ እና ለብዙ ቀናት ይቆያሉ ተብሎ ይጠበቃል። ባለሥልጣናት እንደሚሉት፣ በቅርብ ሳምንታት ውስጥ፣ ትራምፕ የጊዜያዊ ሰላም ስምምነቱ ትርጉም የለሽ እንደሆነ ለታማኝ ሰዎቹ ቅሬታውን አሰምቷል፣ እንዲሁም እሱ የማይሠራ መሆኑን ሁልጊዜ ያውቅ እንደነበር ጨምሮ ተናግሯል።

⚽️⚡️- በኒውዮርክ ፖስት ዘገባ መሠረት፣ ፊፋ፣ በዓለም አቀፍ ተቃውሞ እና በUEFA ከፊፋ ለመውጣት በመወሰኑ ምክኒያት፣ በዓለም ዋንጫ ላይ ለግል ባለሀብቶች አክሲዮኖችን ለመሸጥ ያቀደውን እቅድ፣ ሰርዞታል።

⚽️⚡️- በኒውዮርክ ፖስት ዘገባ መሠረት፣ ፊፋ፣ በዓለም አቀፍ ተቃውሞ እና በUEFA ከፊፋ ለመውጣት በመወሰኑ ምክኒያት፣ በዓለም ዋንጫ ላይ ለግል ባለሀብቶች አክሲዮኖችን ለመሸጥ ያቀደውን እቅድ፣ ሰርዞታል።

🇮🇱 የብዙዎች መላ ምት በአሁኑ ሰዓት።

ስፔን ትችታለች ፈረንሳይ ትችታለች ቱርክ ትችታለች
+3
ስፔን ትችታለች ፈረንሳይ ትችታለች ቱርክ ትችታለች

+2
🇪🇸🇫🇷🇹🇷🇮🇱 የስፔን የደን እሳት የአቮካዶ እርሻን አወድሟል፣ ለዓመታት ምርትን አደጋ ላይ ጥሏል የወይን ጠጅ አምራቾች በፈረንሳይ ውስጥ ያሉ የእሳት አደጋ ሰራተኞችን ለመርዳት 'የተቻላቸውን ሁሉ' ያደርጋሉ። የቦዲካም ካሜራ ቪዲዮ በቱርክ የደን እሳት ላይ የፊት መስመር ውጊያን ያሳያል። እነዚህ ሦስቱ ከእሳት በላይ የሚጋሩት ነገር አለ... *-*-*-* አንዳንድ ሰዎች ነጥቦችን ለማገናኘት መሞከር ጥሩ ነው ይላሉ።

🇪🇸🇲🇦 ከ50,000 ስደተኞች 48,300 የሚሆኑት ወደ ሴውታ ከገቡ በኋላ ወደ ሞሮኮ ተመልሰዋል፣ እና ቢያንስ 57 ሰዎች ሲሻገሩ ሞተዋል፣ - EL PAÍS *-*-*- የገቡት በሙሉ ወደ ሞሮኮ
+2
🇪🇸🇲🇦 ከ50,000 ስደተኞች 48,300 የሚሆኑት ወደ ሴውታ ከገቡ በኋላ ወደ ሞሮኮ ተመልሰዋል፣ እና ቢያንስ 57 ሰዎች ሲሻገሩ ሞተዋል፣ - EL PAÍS *-*-*- የገቡት በሙሉ ወደ ሞሮኮ ተመልሰዋል፣ NewYork Timesም እንደዘገበው። የተመለሱበት ምክኒያት የሚገርማችሁ፣ በከተሞቹ የሚበላ ምግብ በማጣታቸው ነው። ሁሉም በሩን ዘጋ እና መንገድ ላይ ቀሩ። ሆዳቸውን ሲሞረሙራቸው ተመለሱ። የስፔንን ስም ለማጥፋት ከባድ ሴራ ተጎንጉኗል። ይሄ ዝም ብሎ በባዶ የሆነ አይደለም። መቶ ሺህ ሕዝብ አደራጅቶ ማነው በወረራ መልክ የላከባት? ማነው ድንበር ድረስ ጭኖ ያመጣቸው? ማነውስ ሂዱ ውረሩ ያላቸው? ከኋላቸው ያለው ማነው? ስፔን፣ እንደሚታወቀው በአውሮፓ ለእስራኤል እሾክ የሆነች ሀገር ናት፣ የጋዛን ጦርነት በመቃወም አንደኛ ናት፣ የእርዳታ መርከቦችን እያደራጀች ወደ ፍልስጤሞች በየጊዜው በመላክ እገታውን ለመስበር የምትጥር ናት። ስፔን፣ በአጭሩ የእስራኤል መንግሥት እና ፖሊሲዎች ግንባር ቀደም ነቃፊ ናት። እስራኤል አደራጅታቸው ይሆን? ለዚያ ማስረጃ ቢሆን የኔታንያሁ ልጅ በ2019 "አረብና ሙስሊሞች" ስፔንን እንዲወሩ በትዊተር ያደረገው ቅስቀሳ ከጽሑፉ ጋር ተያይዟል። በሌላ በኩል፣ በኢራን ጦርነት፣ ስፔን ለአሜሪካ ጦር ሀገሬን አላስጠቅምም ማለቷ አሜሪካንን ክፉኛ አስቆጥቶ ነበር። የአሜሪካዎች ንዴት እስካሁን አልበረደም። NewYork Times በዛሬው ሌላ ዘገባው፣ የሞሮኮ መንግሥት ወራሪዎቹ ስፔንን እንዲወሩ መመሪያ ሲሰጥ ነበር ብሏል። ማንነው እነዚህን በአጥንታቸው የቀሩና የተጎሳቆሉ አረቦችን አደራጅቶ ወደ ስፔን ለወረራ የላካቸው?

—❗️🇺🇸/🇮🇶/🇮🇷 ይሄንንም በላይኛው ዘገባ ላይ ጨምሩበት። ሰበር ዜና ነው። አሜሪካ፣ ጦር ኃይሏን ከኢራቅ ልታስወጣ መሆኑ ታወቀ። ከሰሜን ኢራቅም (ኢርቢል ኩርድ)፣ የነበሯትን 6 ፔትርዮት
—❗️🇺🇸/🇮🇶/🇮🇷 ይሄንንም በላይኛው ዘገባ ላይ ጨምሩበት። ሰበር ዜና ነው። አሜሪካ፣ ጦር ኃይሏን ከኢራቅ ልታስወጣ መሆኑ ታወቀ። ከሰሜን ኢራቅም (ኢርቢል ኩርድ)፣ የነበሯትን 6 ፔትርዮት አየር መቃወሚያ ሲስተሞችን ለማውጣት፣ እየነቃቀለች ትገኛለች። አሜሪካ ቀድሞውኑ በርካታ የፔትሪዮት ባትሪዎችን ከኢርቢል አውጥታለች፣ እና ቀሪ ወታደራዊ ኃይሎቿን በሙሉ እስከ ሴፕቴምበር 30፣ 2026 ድረስ፣ ከኢራቅ ኩርዲስታን ታወጣለች። ይህ እርምጃ የተወሰደው፣ ኢራን በአካባቢው በሚገኙ የአሜሪካ ኢላማዎች ላይ ተደጋጋሚ የድሮን እና የሚሳይል ጥቃቶችን ከፈጸመች በኋላ ነው። እነዚህን ጥቃቶች ለመከላከል ከጊዜ ወደ ጊዜ አስቸጋሪ እየሆኑ መጥተዋል። ከ2003 ጀምሮ፣ ከ23 ዓመታት በላይ ከተያዘ በኋላ፣ ከአሜሪካ ወታደራዊ መኖር ነፃ የሆነች ኢራቅ ለመጀመሪያ ጊዜ እውን ይሆናል። – Al Monitor

—❗️🇺🇸/🇮🇶/🇮🇷 ይሄንንም በላይኛው ዘገባ ላይ ጨምሩበት። ሰበር ዜና ነው። አሜሪካ ኃይሏን ከኢራቅ ልታስወጣ ነው፣ ከሰሜን ኢራቅ (ኢርቢል ኩርድ) የነበሯትን 6 ፔትርዮት አየር መቃወሚያ
—❗️🇺🇸/🇮🇶/🇮🇷 ይሄንንም በላይኛው ዘገባ ላይ ጨምሩበት። ሰበር ዜና ነው። አሜሪካ ኃይሏን ከኢራቅ ልታስወጣ ነው፣ ከሰሜን ኢራቅ (ኢርቢል ኩርድ) የነበሯትን 6 ፔትርዮት አየር መቃወሚያ ሲስተሞችን ለማውጣት እየነቃቀለች ነው። አሜሪካ ቀድሞውኑ በርካታ የፔትሪዮት ባትሪዎችን ከኢርቢል አውጥታለች፣ እና ቀሪ ወታደራዊ ኃይሎቿን በሙሉ እስከ ሴፕቴምበር 30፣ 2026 ድረስ፣ ከኢራቅ ኩርዲስታን ታወጣለች። ይህ እርምጃ የተወሰደው፣ ኢራን በአካባቢው በሚገኙ የአሜሪካ ኢላማዎች ላይ ተደጋጋሚ የድሮን እና የሚሳይል ጥቃቶችን ከፈጸመች በኋላ ነው። እነዚህን ጥቃቶች ለመከላከል ከጊዜ ወደ ጊዜ አስቸጋሪ እየሆኑ መጥተዋል። ከ2003 ጀምሮ፣ ከ23 ዓመታት በላይ ከተያዘ በኋላ፣ ከአሜሪካ ወታደራዊ መኖር ነፃ የሆነች ኢራቅ ለመጀመሪያ ጊዜ እውን ይሆናል። – Al Monitor

🇺🇸🇰🇼🇮🇷⚡️— አሜሪካ ኩዌትን ነፃ አውጥታለች፣ አሁን ግን ከኢራን ጥቃት ለመጠበቅ እየተንገዳገደች ነው -- Wall Street Journal ከኢራን ጋር የተካሄደው ጦርነት በኩዌት በሚገኙ
🇺🇸🇰🇼🇮🇷⚡️— አሜሪካ ኩዌትን ነፃ አውጥታለች፣ አሁን ግን ከኢራን ጥቃት ለመጠበቅ እየተንገዳገደች ነው -- Wall Street Journal ከኢራን ጋር የተካሄደው ጦርነት በኩዌት በሚገኙ የአሜሪካ ተቋማት ላይ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን ስላስከተለ፣ አሜሪካ በኩዌት ያላትን ወታደራዊ ቁጥር ከግማሽ በላይ ለመቀነስ እንደገና እየገመገመች ነው፣ ሲል WSJ ዘግቧል። ➡️ ፔንታገን ከኢራን ጋር ጦርነት ከመጀመሩ በፊት በኩዌት ውስጥ ያለውን የወታደር ሕልውና ለመቀነስ አስቀድሞ እያሰበ ነበር። ➡️ በአሜሪካ ማእከላት ላይ ከተካሄዱት የኢራን ጥቃቶች በኋላ፣ ፔንታገን በአሜሪካ ሰራተኞች ላይ የሚደርሰውን አደጋ ለመቀነስ በማሰብ በኤሚሬት ውስጥ ያለውን የወታደራዊ አሻራ የበለጠ እንደቀነሰ ይታወቃል። *-*-*- ከሳዑዲ ጋር በተያያዘ ቀደም ብሎ ያልኳችሁ ነገር ነበር፡ አሜሪካ አረቦችን መጠበቅ ደክሟታል።

+4
🇺🇦 ይህ በዚህ እንዳለ በኪየቭ... ፌዶሮቭ ወደ መከላከያ ሚኒስቴር እንዲመለስ የሚጠይቅ ሌላ ተቃውሞ እየተካሄደ ነው። ዛሬ ቀደም ብሎ ዘለንስኪ ፌዶሮቭን ከብሔራዊ ደህንነት እና መከላከያ ምክር ቤትም አስወጥቶታል። *-*-* ፌዶሮቭ ማለት የዛሬ 15 ቀን ዘለንስኪ ያባረረው የዩክሬን ተወዳጅ የመከላከያ ሚኒስቴር ነው። ከጥቂት ቀናት በኋላ ደግሞ፣ የጦሩን ዋና አዛዥንም ማባረሩ ይታወሳል። ሰልፎቹ ሰላማዊ ናቸው እስካሁን። እንደምታዩትም የሞልቃቆች ሰልፍ ይመስላል። ሩሲያዎች ሰልፎቹን 'የካርቶን አብዮት' ሲሉ ይጠሩታል፣ በውስጣቸው ሰልፉ መልኩን ቀይሮ በዩክሬን ዘለንስኪ ላይ ፖለቲካዊ ውጥንቅንጥ እንዲያመጣ ቢመኙም።

⚽️ የአውሮፓ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ራሱን ከፊፋ አገለለ፣ ከአሁን በኋላም ከተቋሙ ወጥቻለሁ ብሏል። አውሮፓ፣ የዓለም ዋንጫን የግል ለማድረግ በኩሽነር በተደገፈው እቅድ ላይ ተቃውሞውን በማሰማት ከፊፋ ራሱን ማግለሉን አስታውቋል። የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበራት ህብረት (UEFA) በዓለም ዋንጫ እና በሌሎች የፊፋ ውድድሮች ላይ ላለመሳተፍ እና ከተቋሙ ለመውጣት በአንድ ድምጽ ዛሬ ባደረገው ስብሰባ መወሰኑን አስታውቋል። ኩሽነርና እና ኢንቬስተሮቹ፣ የፊፋን 20 በመቶ የባለቤትነት ድርሻ ለግላቸው ለማዘዋወር ከፊፋ ጋር ምስጢራዊ ስብሰባዎችን ካደረጉ በኋላ፣ ለመወሰን ጫፍ ደርሰዋል፣ ብሏል የአውሮፓ እግር ኳስ ፌዴሬሽን። “የአውሮፓ አቋም ግልጽ ነው። ለዚህ ሞዴል በፍጹም ህጋዊነት አንሰጥም። ለሚቀጥለው ትውልድ በአደራ የያዙትን ለመሸጥ ማንም ሰው ሥነ ምግባራዊ ስልጣን የለውም።”  UEFA, ሁሉም 55 አባል ማህበራት የፊፋ በዓለም ዋንጫ እና በሌሎች የፊፋ ውድድሮች ላይ ያለውን የባለቤትነት ድርሻ ለግል ባለሀብቶች ለመሸጥ ያቀደውን እቅድ ውድቅ እንዳደረጉ በመግለጽ፣ የዓለም ዋንጫ ከትውልድ ወደ ትውልድ የተገነባ የሕዝብ የስፖርት ትሩፋት እንጂ የግል ባለሃብቶች እንዲሆን አንፈቅድም፣ በመሆኑም ከፊፋ ሕብረቱ ወጥቷል ብሏል።

⚽️  አውሮፓ፣ የዓለም ዋንጫን የግል ለማድረግ በኩሽነር በተደገፈው እቅድ ላይ ተቃውሞውን በማሰማት ከፊፋ ራሱን ማግለሉን አስታውቋል። የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበራት ህብረት (UEFA) በዓለም ዋንጫ እና በሌሎች የፊፋ ውድድሮች ላይ ላለመሳተፍ እና ከተቋሙ ለመውጣት በአንድ ድምጽ ዛሬ ባደረገው ስብሰባ መወሰኑን አስታውቋል። ኩሽነርና እና ኢንቬስተሮቹ፣ የፊፋን 20 በመቶ የባለቤትነት ድርሻ ለግላቸው ለማዘዋወር ከፊፋ ጋር ምስጢራዊ ስብሰባዎችን ካደረጉ በኋላ፣ ለመወሰን ጫፍ ደርሰዋል፣ ብሏል የአውሮፓ እግር ኳስ ፌዴሬሽን። “የአውሮፓ አቋም ግልጽ ነው። ለዚህ ሞዴል በፍጹም ህጋዊነት አንሰጥም። ለሚቀጥለው ትውልድ በአደራ የያዙትን ለመሸጥ ማንም ሰው ሥነ ምግባራዊ ስልጣን የለውም።”  UEFA, ሁሉም 55 አባል ማህበራት የፊፋ በዓለም ዋንጫ እና በሌሎች የፊፋ ውድድሮች ላይ ያለውን የባለቤትነት ድርሻ ለግል ባለሀብቶች ለመሸጥ ያቀደውን እቅድ ውድቅ እንዳደረጉ በመግለጽ፣ የዓለም ዋንጫ ከትውልድ ወደ ትውልድ የተገነባ የሕዝብ የስፖርት ትሩፋት እንጂ የግል ባለሃብቶች እንዲሆን አንፈቅድም፣ በመሆኑም ከፊፋ ሕብረቱ ወጥቷል ብሏል።

+7
🇺🇦🇷🇺⚡️በሩሲያ ግዛቶች ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ዒላማዎች፣ ሌሊቱን እና እስከ አሁንም በቀጠሉ የዩክሬን ጥቃቶች፣ ተመትተው እየነደዱ ናቸው። ከባባድ ኢንዱስትሪዎች፣ ሎጀስቲክ ሴንተሮች (በተለይ Wild Berries) እና 'ወታደራዊ' የተባሉ ዒላማዎች፣ እስከ ዳጊስታን ግዛት ድረስ፣ በዘለቁ ጥቃቶች ተመትተዋል። አስደናቂ እሳቶች እና ጭሶች የከተማዎች ሰማይ ላይ አንዣበው ታይተዋል። *-*-*- አንድ ነገር ልበል፣ በፊት በፊት በነዋሪዎች የሚቀረፁ በዩክሬን ላይ የሚደርሱ የጥቃት ቪዲዮዎችን፣ በቴሌግራም እንደልብ ማግኘት ይቻል ነበር። ሰው ፖስት ያደርጋል ታያለህ። ዛሬ ከዩክሬን የሚወጡ ቪዲዮዎች ከሞላ ጎደል የሉም። ዩክሬን እንደ ሕግ፣ የጥቃት ቪዲዮዎችን ቀርጾ የሚለጥፍን እንደምትቀጣ ከዓመት በፊት በሕግ አውጃለች። ይህን የሚያደርግ ዩክሬናዊ ወየውለት፣ ከጠላት እኩል ይታያል፣ ወገናችሁን ቀርጻችሁ ለጠላት አታጋልጡ፣ ዩክሬንን እንታደግ እና የተለያዩ ማባባያ እና ማስፈራሪያ ነገሮችን ከተናገሩ/ካወጁ በኋላ ሕዝቡ ተቀብሏል። እናም በዜጎች የሚቀረጹ እና የሚለጠፉ ቪዲዮዎች ሙሉ በሙሉ ቀርተዋል። ያሉም ካሉ በጣም ቪዥ ያሉ የደበዘዙና እና የማይታዩ ናቸው። ሩሲያ በሌላ በኩል፣ ተመሳሳይ እገዳዎችን አውጥታለች። የሚሰማ እና ተቀብሎ ተግባራዊ ያደረገ ሩሲያዊ ግን የለም። ሁሉም ያሻውን ይቀርፃል፣ ሁሉም ይለጥፋል። የሰፈር ንትርክ፣ ድብድብ፣ ለቅሶ፣ ንጭንጭ፣ እሳት፣ ጭስ፣… አይቀራቸውም። HD የሆነ ቪዲዮ እኮ ነው ደግሞ። ይሄ የሩሲያን ገጽታ በክፉ ጎድቶታል። ዛሬ ዩክሬንን አጥቂ፣ አሸናፊ፣ አንበሳ፣ ሩሲያን ድመት፣ ደካማ፣ ተሸናፊ አስመስሏቸዋል። እውነቱም እንደዛ ይሆን እንዴ?

🇸🇦🇾🇪— ሳውዲ ዓረቢያ፣ 'ከፍተኛ' የተባለ ወታደራዊ ጥቃት፣ በሁቲ ኃይሎች ላይ፣ በየብስም በባሕርም ለመክፈት በዝግጅት ላይ መሆኗ ተነገረ። የጦር ኃይሏን በአሁኑ ሰዓትም እያሰባሰበች ትገኛለች
🇸🇦🇾🇪— ሳውዲ ዓረቢያ፣ 'ከፍተኛ' የተባለ ወታደራዊ ጥቃት፣ በሁቲ ኃይሎች ላይ፣ በየብስም በባሕርም ለመክፈት በዝግጅት ላይ መሆኗ ተነገረ። የጦር ኃይሏን በአሁኑ ሰዓትም እያሰባሰበች ትገኛለች። ሳዑዲ፣ በሁቲ ኃይሎች በቀይ ባሕር፣ በባበል ማንደብ መተላለፊያ ላይ፣ የተጣለባትን እገታ ለመስበር የበርካታ ሀገራት ወታደራዊ ጥምረት መመስረቷን ያወጀችው ትናንት ነበር— The Guardian *-*-*- ጦርነት ውድ ነው፣ ለሳዑዲም ቢሆን። አንዴ ከተገባበትም በቀላሉ የሚወጣበት ነገር አይደለም። ሳዑዲ ብትጠነቀቅ ይሻላል። በሌላ በኩል ደግም፣ መተላለፊያ መስመሮቿ እና የእለት እንጀራ የምታገኝበት መውጫና መግቢያዎቿ ተዘግተውባት እና እገዳ ተጥሎባት፣ ዝም ብላ ትቀመጥ ማለትም አያስኬድም። ስለዚህ ባለ በሌለ ኃይሏ፣ የመጣው ይምጣ፣ እያየሁ አልራብም፣ ብላ ልትገባበት ትችላለች። ሳዑዲዎች በሕልማቸውም በውናቸውም አስበው የማያውቁት አጣብቂኝ ውስጥ ነው የገቡት። በዚህ ሁሉ ለእኔየ አሜሪካ ነገር ገርሞኛል። በቀጠናው የነበራት ኃይል ክፉኛ ደቋል ማለት ነው በኢራን። ወይንም፣ እጅግ በጣም ደክሟት ዝላለች። ይሄን ያልኩት፣ በሌላ ጊዜ ቢሆን፣ ሳዑዲን ከእንዲህ ያሉ ችግሮች የመጠበቅ ኃይል ነበራት። ቀላል ነበር። ዛሬ ታሪክ ተቀይሯል መሰለኝ፣ የቻለች አይመስልም። ሳዑዲዎች ለአሜሪካ ጥበቃ ከሚከፍሉት የገንዘብ መጠን አንጣር ይሄ በትንሹ ከአሜሪካ የሚጠብቁት አገልግሎት ነበር። 'እራስሽን በራስሽ ታደጊ' ያለቻት ይመስላል አሜሪካ ሳዑዲን።