fa
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

رفتن به کانال در Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
4 301
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-137 روز
-8030 روز
آرشیو پست ها
🇾🇪🇸🇦🇮🇷🇺🇸 የመን፣ ሊከፈትባት ላለው ዘመቻ እራሷን እያዘጋጀች ነው፣ እንደ እኔ ከጠየቃችሁኝ፣ በአሜሪካ ሰዓት አቆጣጠር ሌሊቱን፣ እኩለ ሌሊት አካባቢ፣ በየመን አቆጣጠር ሊነጋጋ ሲል፣ ትደበደባለች! ሳዐዲ በበኩሏ፣ በአሁኑ ሰዓት አሜሪካ ሓሳቧን እንዳትለውጥ ቆማ እየጠለየች ነው። እንዲህም ሆኖ፣ የሚገርማችሁ ነገር፣ አሁን በዚህ ሰዓት የመን ሚሳኤሎችን ወደ ሳኡዲ አስወንጭፋለች።

❗️🇺🇸/🇾🇪 የመን፣ ትደብደብ ተብላ ሳይፈረድባት አይቀርም፣ እንደ CNN ዘገባ። ፕሬዝዳንቱ፣ ሊደረጉ የሚችሉ ጥቃቶን ገምግሟል። አሜሪካ በመላው ቀጠና የአደጋ ጊዜ ያወጀችው፣ ኢራን ወይም የመን
❗️🇺🇸/🇾🇪 የመን፣ ትደብደብ ተብላ ሳይፈረድባት አይቀርም፣ እንደ CNN ዘገባ። ፕሬዝዳንቱ፣ ሊደረጉ የሚችሉ ጥቃቶን ገምግሟል። አሜሪካ በመላው ቀጠና የአደጋ ጊዜ ያወጀችው፣ ኢራን ወይም የመን በምላሹ ሊወስዱ የሚችሉትን አፀፋዊ እርምጃ በመፍራት ነው።

⚡️🇺🇸 ትራምፕ ወደ ዋይት ሃውስ አሁን ተመልሷል።

⚡️❗️በአሁኑ ሰዓት በመላ ቀጠናው አየሩ ከብዷል፣ የሆነ ነገር እዚም እዚያም እየተወጠወጠ እንደሆነ ያስታውቃል። በማን ላይ እና በምን ላይ እንደሆነ፣ ይሄ ነው ብሎ መናገር አይቻልም። የምናውቀው ግን፡ ከፍተኛ የሆነ የአሜሪካ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ይስተዋላል። መላው ቀጠና አደገኛ ማስጠንቀቂያ ውስጥ ገብቷል። ኢራን ሰራዊቷን በከፍተኛ ሁኔታ እና በተጠንቀቅ አቁማ ትገኛለች። ከዚህም በተጨማሪ፣ መሰረተ-ልማቶቿን በልዩ ሁኔታ እየጠበቀች ነው። የመን፣ ኢራቅ እና ሳዑዲ፣ ሽር-ጉድ ላይ ናቸው። ሰራዊቶቻቸው በየፊናቸው ለመንቀሳቀስ እየሞከሩ ነው። ሶሪያ የአየር መቃወሚያ ሲስተሞቿን ለኩሳ ተዘጋጅታለች። እስራኤል ከአሜሪካ ጋር የሆነ ነገር ለመጀመር ዝግጅቷን እንዳጠናቀቀች ይወራል። ሁሉም ዛሬ ሌሊቱን … ማዕበል እየመጣ ነው? አፍጥጠን እናድራለን። በቀጠናው ያለው ጉዳይ ደስ የሚል አይመስልም፣ ተፋፍሞ ሊባባስ ቋፍ ላይ ነው።

🇺🇸❗️ፕሬዝዳንት ትራምፕ፣ የያዛቸውን ፕሮግራሞቹን ሰርዞ፣ በአስቸኋይ ወደ ዋይት ሃውስ አሁን የሚመለስ ይሆናል።
🇺🇸❗️ፕሬዝዳንት ትራምፕ፣ የያዛቸውን ፕሮግራሞቹን ሰርዞ፣ በአስቸኋይ ወደ ዋይት ሃውስ አሁን የሚመለስ ይሆናል።

🇮🇷🇺🇸⚡️❗️ኢራን፣ ጦር ሠራዊቷ በያለበት በተጠንቀቅ እንዲቆም እና የዝግጅቱን ደረጃ ከፍ እንዲያደርግ አዛለች።

🇮🇷🇺🇸⚡️❗️ኢራን፣ ጦር ሠራዊቷ በያለበት በተጠንቀቅ እንዲቆም እና የዝግጅቱን ደረጃ ከፍ እንዲያደርግ አዛለች

🇺🇸🇾🇪🇸🇦⚡️- ሰበር ዜና፡ "በሳውዲ ዓረቢያ እና በኢራን በሚደገፉ ሁቲዎች መካከል ያለው ግጭት ሊባባስ የሚችልበት እድል ሰፊ ነው፣ የደህንነት ተቋሞቻችን እንደገመገሙት።" - የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

🇺🇸⚡️የአሜሪካ ስቴት ዲፖርትመንት (ውጭ ጉዳይ)፣ በመካከለኛው ምሥራቅ ቀጠና "ውጥረት እየጨመረ ስለሚሄድ" ዜጎቹ ወደ አካባቢው እንዳይጓዙ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል። የአደጋውን ከፍተኝነት ወደ 4 ነጥብ አሳድጎታል። *-*-*- ከፍተኛው 5 ነው።

🇮🇹🇸🇦⚡️- ጣሊያን ዜጎቿ በሳውዲ ዓረቢያ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እና ወደ ጃዛን፣ ከሚስ ሙሻይት እና ናጅራን ከመጓዝ እንዲቆጠቡ ማስጠንቀቂያ ሰጠች። ጣሊያን ይህን ያለችው፣ ባሳለፍነው ሳምንት አለመረጋጋትን እና በታጣቂዎች ሊደርስ የሚችል አደጋን እንደ ምክኒያት በመጥቀስ፣ አሜሪካ ዜጎቿ ወደ ሳዑዲ ከመጓዛቸው በፊት ጉዟቸውን ደግመው "እንዲያጤኑ" ዜጎቿን ካስጠነቀቀች በኋላ ነው። *-*- እኔ አምልጫለኋ ታዲያ፣ በጊዜው መጣሁላችሁ ለቀጠናዎች

🇮🇹🇸🇦⚡️- ጣሊያን ዜጎቿ በሳውዲ ዓረቢያ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እና ወደ ጃዛን፣ ከሚስ ሙሻይት እና ናጅራን ከመጓዝ እንዲቆጠቡ ማስጠንቀቂያ ሰጠች። ጣሊያን ይህን ያለችው፣ ባሳለፍነው ሳምንት አለመረጋጋትን እና በታጣቂዎች ሊደርስ የሚችል አደጋን እንደ ምክኒያት በመጥቀስ፣ አሜሪካ ዜጎቿ ወደ ሳዑዲ ከመጓዛቸው በፊት ጉዟቸውን ደግመው "እንዲያጤኑ" ዜጎቿን ካስጠነቀቀች በኋላ ነው።

🇸🇦🇾🇪✈️ የሳዑዲ አረቢያ ተዋጊ አውሮፕላኖች፣ ጣዒፍ ከሚገኘው የንጉሥ ፋህድ አየር ኃይል ጣቢያ በመነሳት፣ በምስራቅ የመን ግንባር የሚገኙ የአንሷረላህ (ሁቲ) ኢላማዎች ላይ ጥቃት እያካሄዱ ናቸው።

🇾🇪❌🇸🇦 — የሁቲ (አንሷሩላህ) የፖለቲካ ቢሮ አባል ሐዚም አል አሳድ በቅርቡ በሪያድ ላይ ስለደረሰው ጥቃት፡- የሚመጣው ከእስካሁኑ ትልቅ ይሆናል በአላህ ፍቃድ። ገና አላዩም። ጠላት ሳዑዲ በ
🇾🇪❌🇸🇦 — የሁቲ (አንሷሩላህ) የፖለቲካ ቢሮ አባል ሐዚም አል አሳድ በቅርቡ በሪያድ ላይ ስለደረሰው ጥቃት፡-
የሚመጣው ከእስካሁኑ ትልቅ ይሆናል በአላህ ፍቃድ። ገና አላዩም። ጠላት ሳዑዲ በየመን ሕዝብ ላይ በእሳት በመጫወት በጣም ሩቅ ሄዷል። እገታ፣ ጥቃት፣ ግድያ፣ ስም ማጥፋት፣ እና የአይስስ ዓይነት ጽንፈኝነት (በየመን ያደረሱት ግፍ ነው።)

🇸🇦🇾🇪⚡️ ሮይተርስ : በሪያድ ንጉሥ ኻሊድ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ አካባቢ የእሳት ነበልባል እና ከፍተኛ ጥቁር ጭስ ታይቷል። አየር ማረፊያው፣ በአሁኑ ጊዜ ማንኛውንም የበረራ አገልግሎት መስጠት አቁሟል።

⚡️🇺🇸🇮🇱🇸🇦 — በእስራኤል የአሜሪካ አምባሳደር ማይክ ሃከቤ፡
እስራኤላውያን ከሳውዲዎች ጋር የጸጥታ ስምምነት ቢኖራቸው ደስ ይላቸዋል። ሳውዲዎች የአብርሃም ጎጆ አካል ቢሆኑ ደስ ይለኛል፣ ይመጣሉ። በእርግጠኝነት፣ በእስራኤል ውስጥ በዚህ ጉዳይ የማመንታት ነገር አይታይም። ማመንታቱ በሳዑዲ ውስጥ ነው። የሐሳብ ፍጭቶች እንደሚኖሩ ተስፋ ማድረግ አለብን። አሁን ላይ ጥሩ ወታደራዊ-ለወታደራዊ፣ ጥሩ መረጃ-ለመረጃ ልውውጥ አለ ማለት እችላለሁ።
*-*-* ሳዑዲ የምትፈልገው ወሬ አይደለም፣ እባካችሁ ተጨባጭ እርዳታ ትፈልጋለች፣ እርዷት ሳዑዲን። እስራኤል እርጃት፣ እባክሽ፣ እየለመነችሽ።

⚡️🇸🇦🇾🇪 በሪያድ የሚገኘው የአርማኮ ነዳጅ ማከማቻ፣ በአሁኑ ሰዓት እየነደደ ይታያል። የዋና ከተማው ሰማይ በአብዛኛው በጥቁር ጭስ መሸፈኑን መረጃዎች ያሳያሉ።

🇸🇦🇾🇪⚡️በአሁኑ ሰዓት የሪያድ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ፣ እሳት እየነደደበት ይታያል።
+1
🇸🇦🇾🇪⚡️በአሁኑ ሰዓት የሪያድ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ፣ እሳት እየነደደበት ይታያል።

🇮🇱🇮🇷 የእስራኤል የፀጥታ ተቋማት፣ በኢራን ጦርነት ወቅት ለኢራን ሰፊ የስለላ ሥራ ሲሠሩ የነበሩ ያሏቸው የእስራኤል ወታደራዊ ክፍሎች ላይ፣ ምርመራ እያካሄዱ እንደሆነ አስታወቁ። ዝርዝር ከመግለፅ የታቀቡት የፀጥታ ባለስልጣናቱ፣ በIDF ውስጥ ለኢራን በስፋት የስለላ ሥራ ሲሰሩ የነበሩ የጦሩ አባላት እንዳሉ ተናግረው፣ ሁሉንም ነገር ምርመራው ሲያልቅ ግልጽ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል - Jeruselam Post

🇺🇦🇺🇸⚡️🇷🇺 ሰላም የሚገኘው በኃይል ነው። ኃይል ደግሞ በጽናት ነው። አሜሪካ፣ አመሰግናለሁ! ዘለንስኪ። ኪየቭ ዋሽንግተንን፣ የፀረ-ሩሲያ ማዕቀቦችን በማውጣቷ አመስግናለች።
🇺🇦🇺🇸⚡️🇷🇺 ሰላም የሚገኘው በኃይል ነው። ኃይል ደግሞ በጽናት ነው። አሜሪካ፣ አመሰግናለሁ! ዘለንስኪ። ኪየቭ ዋሽንግተንን፣ የፀረ-ሩሲያ ማዕቀቦችን በማውጣቷ አመስግናለች።

+2
🇸🇦🇾🇪⚡️🇾🇪❌🇸🇦 — በሪያድ፣ የሚሳዬል ጥቃቶች እና የአደጋ ጊዜ ደውሎች አሁን ድረስ ከተማውን እየናጡ ይገኛሉ። የአንሷረላህ (ሁቲ) ባለስቲክ ሚሳኤሎች፣ የአሜሪካ ጦር/የሮያል ሳዑዲ አየር መቃወሚያ ሚሳዬሎችን አልፈው ሲወርዱ እንዳዩም፣ የዓይን እማኞች ከቦታው እየዘገቡ ናቸው።