የቀጠናው ተመልካች
Open in Telegram
በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።
Show moreThe country is not specifiedThe category is not specified
4 330
Subscribers
-924 hours
-407 days
-8130 days
Posts Archive
4 330
+4
🇺🇸⚡️🇮🇷 ከሰሞኑ አይቼ የደነገጥኩበት ፎቶ ይሄ ነው። ይሄ USS Abraham Lincoln ነው፣ ግዙፉ የአሜሪካ የጦር መርከብ። በኢራን ጦርነት የነበረውን ግዳጁን ጨርሶ ወደ ታይላንድ ለእረፍት በዚህ እንደደረሰ የተነሳ ፎቶ ነው።
ፎቶው በአሜሪካ መነጋገሪያ ሆኖ ላለፉት ጥቂት ቀናት አለ። ተመልከቱት! በስብሷል እኮ፣ ተንኮታኩቷል። ሞራሉ የደቀቀ አዛውንት ነው የመሰለው፣ ግርማ ሞገሱ እና ሃይባው እርቆታል። ዝሏል፣ ተስፋ የቆረጠም ይመስላል። አንዳንዱ የመርከቡ ክፍል በማንኛውም ሰዓት ተገንጥሎ ሊወድቅ የደረሰ እኮ ነው የመሰለው። ብቻ ያን የመሰለ የኃይል እና የበላይነት ማረጋገጫ መርከብ በዚህ ሁኔታ ማየት ቅስመ- ሰቢሮ ነው።
በዚህ መርከብ፣ አሜሪካ በኢራን ጦርነት እየከፈለችው ወይም እያስከፈላት ያለውን ዋጋ ማየት ይቻል ይሆናል።
4 330
🇺🇸🇸🇾⚡️ — ፕሬዝዳንት ትራምፕ፦
ይህ በጣም ጥሩ ነገር ነው! ሶሪያ እራሷን ለሆርሙዝ የባሕር መተላለፊያ አማራጭ አድርጋ እያቀረበች ነው።ትራምፕ ያያያዘውን እና ይህ ዜና የወጣበትን የትናንቱን የWashington Post ትናንት አንብቤዋለሁ። ሊንኩን ከታች አያይዝላችኋለሁ፣ ማንበብ የምትፈልጉ ከሆነ። ሶሪያ በየብስ ለሆርሙዝ አማራጭ መተላለፊያ ልሆን እችላለው ብላ እራሷን እያቀረበች እንዳለ ነው ጽሑፉ የሚያትተው። ሓሳቡ የተወለደው የኢራቅ ነጋዴዎች በሆርሙዝ ሲዘጋባቸው በሶሪያ ድንበር በመኪና ነዳጅ መሸጥ ከመጀመራቸው ነው። አሁን ላይ ከኢራቅ በቀን 5ሺ ተሳቢ መኪኖች ወደ ግማሽ ሚሊዮን በርሚል ነዳጅ በሶሪያ በኩል ያመላልሳሉ። ችግሩ ይሄ ሁሉ ተሳቢ የሚጭነውን አንድ መርከብ በግማሽ የመጫን አቅሙ የሚጭነውን ነው። በሆርሙዝ በኩል በቀን እስከ መቶ ሠላሳ መርከቦች ከ14-20 ሚሊዮን በርሚል ነዳጅ ያስተላልፋሉ። የሆርሙዝ አቅም አይደረስበትም። ነዳጅ ብቻም አይተላለፍበትም ወሽመጡ፣ ሙሉ የአካባቢው ሀገራት ሸቀጦች የሚያልፉትም በዚህ ነው። ስለዚህ የብሱ ከሆርሙዝ ጋር ሲስተያይ አባይን ያላየ ምንጭ ያደንቃል ዓይነት ነገር ነው። አሁን ደግሞ እነዚህ ሀገሮች ወደ ሌላ ሓሳብ ተሻግረዋል። ምናልባት ከኢራቅ፣ ከኩዌት፣ ከኤሜሬት እና ከሳዑዲ በሶሪያ በኩል ባንቧ ዘርግተን ነዳጅ ብናስተላልፍ እያሉ ናቸው። ሶሪያ ለዚህ ዓይነት ሥራ ሊያገለግሉ የሚችሉ ቁልፍ የሆኑ በርካታ ወደቦች አሏት። የሆነው ሆኖ፣ ይሄም ሓሳብ ብዙ ቢሊዮን ብሮችን የሚያስወጣና ብዙ ዓመታትን የሚወስድ ፕሮጀክት ነው። ይሰራ ይባል፣ ኢራን ታሰራለች? መንገድ እየፈለገች አታሰናክለውም? እነዚህ ሁሉ ጭንቀት የወለዳቸው አማራጫዊ ሓሳቦች ናቸው።

ሰላም፣ ሰላም የቀጠናው ተመልካች አድማጭ ተመልካቾቻችን። እንደምን ከረማችሁ? ከቀጠናው ጉብኝት በሰላም ተመልሻለሁ።
በኢራን ዋሻ ሁለት ቀን አያቶላው ጋር ራት የመብላት ዕድል አጋጥሞኛል። አንዱን ቀን በግ አርዶ ነው የጋበዘኝ። አያቶላ ደህና ነው ጤናውን እኔ እንዳየሁት። ትንሽ ቀኝ እጁ አካባቢ በእሳት ከመቃጠሉ ውጭ፣ ምንም ችግር አላየሁበትም። ንቁ እና ምጡቅ ነው።
የመጣሁት ከአቢሲኒያ፣ ከሐበሻ ምድር ነው ስለው፣ በጣም ነው አቅፎ የሳመኝ።
አቢሲኒያ ነቢያችን ወዳጆቻቸውን ያሸሹባት ሀገር አይደለችም እንዴ? አለኝ። አዎን፣ ነች! ስለው፣ ወዲያው፣ ለውጥ ያስፈልጋታል፣ ነው ያለኝ። ምን ታይቶት እንደዛ እንዳለ አልገባኝም። የአቢሲኒያ ሐበሾች ለለውጥ ትግል መጀመራቸውን እዚህ ዋሻ ውስጥ ማን ሊነግረው ይችላል? ነው ያልኩት ለራሴ። ብቻ ከመለያየታችን በፊት፣ አታስቡ ጤናዬን ደህና ነኝ በልልኝ ብሎኛል፣ ተመልካቾቻችንን።
ሀገሩ ደህና ናት፣ ኢራን በሰላም ወጥተህ በሰላም የምትገባባት ሀገር ናት። እንደ ኢትዮጵያ ሰላም አላጣችም። እንደ ኢትዮጵያ፣ የገበሬዎች፣ የሹፌሮች፣ የነጋዴዎች፣ የሕፃናቶች፣ የሴቶች፣ በአጠቃላይ የሲቪሊያኖች ጅምላ ግድያ የለባትም። ሁሉም በሚባል ደረጃም ጠግቦ የሚያድርባት ሀገር ናት። ሐኪሞች እና አስተማሪዎች አይራቡባትም። በዚህ ጦርነት ሀገሩ አጥቂ በመሆኗ እና ቁጭ ብላ ለመጠቃት ባለመፍቀዷም፣ ውስጧን አስከብራ አለች።
ከኢራን በቀጣይ ወደ ሳዑዲ ነበር ያቀናሁት። ሳዑዲ በጣም ትልቅ ሀገር ናት። በዚያም MBSን ለማግኘት ሞክሬያለሁ፣ አልተሳካም። የእናቱ አጎት አባት ስላረፉ በረሃ ለቅሶ ሄዶ ነው ብለውኛል፣ እናም አልተገናኘሁትም።
ሳዑዲ፣ ከሞላ ጎደል ደህና ናት፣ ሰላምም ናት። ትሞቃለች። እንደ ኢትዮጵያ በገዢዎቿ አልተጨማለቀችም። ሰላም አላት። እንደ ኢትዮጵያ ገዢዎች፣ ገዢዎቻቸው ሕዝባቸውን አይገድሉም። ወጥቶ፣ ሠርቶ መግባት በደንብ ይቻላል። ሳዑዲ፣ ጦርነቱ በአፋጣኝ እንዲቆምላት ትፈልጋለች። ብዙውን ከነዳጅ ጋር የተያያዘ ምርቶቿን እንደ ድሮው፣ እንደፈለገች፣ በባሕር ላይ እየተንሸራሸረች መሸጥ ስላልቻለች፣ ጠሃዩም መሰለኝ፣ ብቻ ጠቆርቆር ብላብኛለች። ይሄ ደግሞ እጅግ የጎዳት ይመስለኛል፣ እንዲሁ ስጀርባቸው ይሄን አስተውዬባቸዋለሁ። ፍሉስ እያጠረ ነው።
የሚገርማችሁ፣ ሳዑዲን ጠለቅ ስትሉባት፣ በጣም ብዙ ደሃዎችን እና ችግረኞችን ታያላችሁ፣ ለማኞችን ታያላችሁ፣ የተበጫጨቁ ልብሶችን ያደረጉ ባለ ባዶ እግር ሕፃናቶችን በፈራረሱ እና በአንድ ላይ እጭቅጭቅ ባሉ ቤቶችና ሰፈሮች ልታዩ ትችላላችሁ። ምናልባት የኮሪደር ልማት አዋሳ ልምዷን ብታካፍላት …
ሳዑዲን አካልዬ ወዲያው አጭሬን፣ (ዘለንስኪን) ለማየት ያቀናሁት ወደ ዩክሬን ነበር። ትንሽ ሰዓት ስለነበረኝ፣ አጭሬን ስለ ሰላም አንስቼባት ነበር። አሁን ባለው ሁኔታ አልፈልግም፣ እያሸነፍን ስለሆነ ግፋ በለው ነው ያለችኝ በግልጡ። ይሄንን ግን ለማንም እንዳትናገር፣ convince እና confuse በሚባለው መርህ አውሮፓንም አሜሪካንንም እያጇበኩኝ መዋጋት ይዣለሁ፣ ያ ደግሞ ተመችቶኛል ነው ያለችኝ። አጭሬን እኔ በበኩሌ እንዳየኋት፣ በተለይ አሜሪካ ብር መስጠቷን እስከቀጠለች ድረስ፣ ሩሲያን እየጎመጀች ጦርነቱን እንደምትቀጥል ነው። አሜሪካ ስታቆም ብቻ ታቆማለች፣ ወይም ሙሉ በሙሉ በሩሲያ ጦር ከተደመሰሰች ብቻ ታቆማለች። ከዚያ ውጭ ማንኛውም ምድራዊ ኃይል አያስቆማትም።
ሩሲያ በበኩሏ ቀስ በቀስ ነገረ ዓለሙን እያጋለችው የመጣች ይመስላል። በኪየቭ በነበረኝ ቆይታ እንቅልፍ የሚባል በዓይኔ አልዞረም። የፍንዳታው ድምፅ ጫት ቅመህ እንዳደርክ ዓይኖችህን 60ሻማ ቦጌ አንፖል እንዳደረገ ይነጋል። ሩሲያ ከሰሞኑ በደንብ ይዛለች፣ ዩክሬንም የዋዛ አልሆነችም፣ መጪውን ውጤት በጋራ የምናየው ይሆናል።
የተከበራችሁ የቀጠናው አድማጭ ተመልካቾቻችን፣ እንኳን በደህና ቆያችሁኝ!

የተከበራችሁ የቀጠናው አድማጭ ተመልካቾቻችን፣ እንኳን በደህና ቆያችሁኝ።
እንኳን በደህና ቆያችሁኝ!
4 330
የዚህ ገጽ አድማጭ ተመልካቾች፡ ላልተወሰኑ ቀናቶች የምሄድበት ቦታ ስላለ እና በዚያም፣ ይህን ፔጅ ማስኬድ የማልችል በመሆኑ፣ አዳዲስ መረጃዎች አይለጠፉም።
ትናንት እንዳነበባችሁት፣ ሲአይኤ እና ሞሳድ የአያቶላውን ዱካ ማግኘት አልቻሉም። ቢፈጉም ቢጥሩም፣ ምንም ፍንጭ የለም። ሰውዬው መንፈስ ነው ብዬ ነበር።
ከዚያም በኋላ፣ ባልታሰበ ሁኔታ፣ ከራሱ ከፈረሱ አፍ፣ በውስጥ መስመር "ና!" የሚል መልዕክት ደርሶኛል፣ እናም በቀጠናው (ለሰውዬው ደህንነት ሲባል በማልጠቅሰው ቦታ) ወደምትገኝ ሥፍራ ለማቅናት ወስኛለሁ ፡)
በዚህም ምክኒያት ከዚህ ፔጅ የምጠፋ ይሆናል።
የሆነው ሆኖ፣ ስለተከታተላችሁኝ እና ስላነበባችሁልኝ እጅግ በጣም አመሰግናለሁ። እስከምመለስም ድረስ፣ ለወዳጅ ዘመዶቻችሁ ገጢቷን ሼር እያደረጋችሁ ጠብቁኝ እላለሁ።
4 330
🇮🇷🇺🇸⚡️በኢራን ላይ የሚደረገው ጥቃት መታገዱ የመጣው ምክትል ፕሬዝዳንት JD Vance እና የአሜሪካ ጦር ሰራዊት የጦር አዛዥ፣ ትራምፕን ከጥቃቱ ለማሳገድ ካደረጉት ጥረቶች በኋላ ነው።
በኢራን ላይ የሚደረገውን ጥቃት ለማቆም ትራምፕ በወሰነው ውሳኔ የሚሳኤል ክምችት እጥረትም ቁልፍ ሚና ነበረው።
4 330
🇮🇷🇺🇸⚡️ሰበር ዜና፡ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በኢራን ላይ አሜሪካ ልትወስድ የነበረውን "ዘመቻ ድለዛ"፣ እንደተወው አስታወቀ።
በቀጠናው ያሉ ሀገሮች "እባክህ ትራምፕ፣ ጦርነት ከተጀመረ በመጀመሪያ የምንጠፋው እኛ ነን ስላሉኝ እና ስለለመኑኝ፣ ለእነሱ ስል ትቼዋለሁ" ብሏል።
ኢራንም የድርድር ሂደቶችን ዳግም ለማንቀሳቀስ እና በሕይወት ለመኖር ጥኑ ፍላጎት በማሳየቷ፣ እሷም እንድትበለጥግ ሐሳቤ በመሆኑ፣ እንዲሁም ለዓለም ሠላም እና መረጋጋት ስል፣ አቅደነው የነበረውን ጠረጋ ሰርዘነዋል" ሲልም ተናግሯል።
"ሁሉም አካላት ወደ ሥራ መሥራት እንዲንቀሳቀሱ" አሳስቧል።
*-*-*-
ትራምፕ እጅግ በጣም አርቆ አስተዋይ ሰው ነው፣ ሆሆ እያሉ በጦርነቱ ቢያስገቡት፣ በረጅም ሂደት ምን ሊፈጠር እንደሚችል ተገንዝቧል። በደንብ ተገንዝቧል። አሜሪካ በዚህ አሁን ጉዳዩ ባለበት ዝግመተ ሂደት፣ በረጅም ጊዜ ብትሸነፍ ወይም በአካባቢው ተጽእኖዋን ብታጣ እንኳ፣ ቢያንስ ሕልውናዋን አስጠብቃ፣ በሕይወት ኖራ ነው።
በሕይወት ኖሮ ማጣት እና ከሕይወት ጠፍቶ ማጣት፣ የተለያዩ ነገሮች ናቸው።
4 330
🇮🇷🇺🇸 በFOX NEWS የትራምፕ አስተዳደር ከኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ጋር አዲስ ጦርነት ከመጀመሩ በፊት የአሜሪካ ሚሳይሎችን የምርት ክምችት አቅርቦት አውጥቷል።
ይታያችሁ እስኪ፣ "የቀረኝ ሚሳዬል ትንሽ ነው" የሚል ዘገባ፣ በዋዜማው።
4 330
🇮🇷🇺🇸🇮🇱⚡️በአሜሪካ የመከላከያ መምሪያ ውስጥ ያለ ምንጭ ለፎክስ ኒውስ፦
“በኢራን ላይ ለሚደረግ ትልቅ የጦርነት ዝግጅት ተዘጋጅተናል። ባለፉት ጥቂት ሰዓታት ውስጥ፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በእስላማዊ አብዮታዊ ጥበቃ ኮርፕስ አሸባሪ ኃይሎች ላይ በርካታ ገዳይ እና አደገኛ ጥቃቶችን አጽድቀዋል።"
4 330
🇮🇷🇺🇸🇮🇱⚡️ሙሐመድ ሜራንዲ፦
ትራምፕ ዛሬ ማታ ጥቃት ቢሰነዝር፣ የኢራን ምላሽ ከመጠን በላይ እና ፈጣን ይሆናል።
ሁሉም ሕዝብ፣ በአረቢያ ባሕረ ሰላጤ የወንጀለኛ፣ በቤተሰብ የሚመሩ አምባገነንነቶች ያሉባቸውን ሀገራት ለመልቀቅ ወዲያውኑ መዘጋጀት አለባቸው።
4 330
🚨🇺🇸🇮🇷📺‼️CBS፣ የአሜሪካ ባለስልጣንን በመጥቀስ፦ አሜሪካ በመላው ቴህራን የኤሌክትሪክ ኃይል ሙሉ በሙሉ ለማቋረጥ እያቀደች ነው።
⚠የማስታወሻ፦ እቅዱን ለመፈጸም ምንም የመጨረሻ ውሳኔ በፕሬዝዳንቱም ሆነ በቃል አቀባዩ በይፋ አልተደረገም።
4 330
🇮🇷⚡️🇺🇸🇮🇱 The NewYork Times፦
አጋሮች እንደሚሉት፣ በኢራን ዩናይትድ ስቴትስ ወደ ስትራቴጂካዊ ሽንፈት እየተጓዘች ነው። የፕሬዝዳንት ትራምፕ ዓላማዎች ሁሉ አልተሳኩም፣ የሆርሙዝ ባሕር መተላለፊያም ሊከፈት አልቻለም።
የአሜሪካ አጋሮች፣ የተባባሰ ጦርነት አሜሪካን እንደሚጎዳ፣ ወደ መስተጓጎል እንደሚወስድ እና አቋሟን እንደሚያዳክም ያምናሉ።
ጦርነቱ ሊባባስ ይችላል፣ ነገር ግን እስካሁን ያለው ውጤት፣ "ስትራቴጂካዊ ኪሳራ እና ሽንፈት" ነው።
4 330
🇺🇸🇬🇧🇦🇺🇩🇪 የአሜሪካ ኤምባሲ፣ እንግሊዝ፣ አውስትራሊያ እና ጀርመን፣ ዜጎቻቸው ከሚከተሉት ሀገሮች በፍጥነት መውጣትን እንዲያስቡ ጠይቀዋል፦
🇧🇭 ባህሬን
🇪🇬 ግብፅ
🇮🇶 ኢራቅ
🇮🇱 እስራኤል
🇯🇴 ዮርዳኖስ
🇰🇼 ኩዌት
🇱🇧 ሊባኖስ
🇴🇲 ኦማን
🇶🇦 ኳታር
🇸🇦 ሳዑዲ አረቢያ
🇦🇪 የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ
*-*-*-
ከባድ የሰብዓዊ ቀውስ ሱናሚ በቀጠናው እየመጣ ነው።
4 330
🇮🇷❌🇺🇸🇮🇱 — የኢራን ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን፦
ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ፣ በኢራን ሕዝብ ጫንቃ ላይ የተጫኑ ጦርነቶች፣ ዓመታት የዘለቁ ማዕቀቦች፣ ዘርፈ ብዙ ጫናዎች እና ተደጋጋሚ የጠላትነት ድርጊቶች፣ ተፈጽመዋል።
በእነዚህ አስቸጋሪ ቀናት ሁሉ፣ እውነተኛዎቹ ጀግኖች ሕዝቡ ነበር። የኢራን የወደፊት እጣ ፈንታ በኢራን ሕዝብ ይወሰናል!
4 330
⚽️— UEFA ለፊፋ ፕሬዝዳንት፡ በገዛ ፍቃድህ ሥልጣንህን ልቀቅ ወይም እናባራሃለን።
ፊፋ፣ 20 ፐርሰንት የተቋሙን ድርሻ ለትራምፕ አማች ለመሸጥ ሲያደርገው የነበረው የውስጥ ለውስጥ ድርድር ከታወቀ በኋላ የተነሳው እሳት፣ አልበረደም።
በዚህም ምክኒያት፣ የአውሮፓ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ ዛሬ፣ የፊፋ ፕሬዝዳንት፣ ጂያኒ ኢንፋንቲኖ፣ ከሥራ እንዲለቅ ወይም የአስቸኳይ ጊዜ የአመኔታ ማጣት ምርጫ እንዲገጥመው፣ UEFA አስገድዶ እንደጠየቀ፣ The Telegraph ዘግቧል።
➡️ ሁሉም 55ቱ UEFA አባል ማህበራት የአመኔታ መጉደል እንቅስቃሴን ለመደገፍ ዝግጁ ሲሆኑ፣ ሂደቱን ለማስጀመር 43 ድምጾች ብቻ ያስፈልጋሉ።
4 330
🇺🇸🇮🇱🇮🇷መንፈስን ማሳደድ ➖➖➖➖➖➖➖➖➖
🔴 ሞሳድ እና ሲአይኤ፣ የኢራንን ታላቅ መሪ፣ አያቶላ ሙጅተባ ኻሜኒን፣ መገኛ ቦታ ለማግኘት በንቃት እየሞከሩ ቢሆንም፣ እስካሁን አልተሳካላቸውም።
ሰውዬውን በመፈለግ ላይ ምንም አይነት ፍንጮች አልተገኙም። የተጠለፉ የደህንነት ካሜራዎች እንዲሁም ልዩ ልዩ የስፓይዌር ሶፍትዌሮች ጥቅም ላይ ቢውሉም፣ አልተጠቀሙም።