en
Feedback
BiT SU Official Information Channel

BiT SU Official Information Channel

Open in Telegram

➤➤➤ This channel has been created to provide students with timely and relevant information from the Student Union and management offices. bitstudentunion4@gmail.com

Show more
The country is not specifiedThe category is not specified
1 219
Subscribers
+2624 hours
+1347 days
+13930 days
Posts Archive
Business Incubation and Techno-Entrepreneurship Center (BiTec) of the Bahir Dar Institute of Technology (BiT), Bahir Dar Univ
Business Incubation and Techno-Entrepreneurship Center (BiTec) of the Bahir Dar Institute of Technology (BiT), Bahir Dar University, is pleased to announce a Call for Applications for intensive hands-on training programs in the following cutting-edge technology areas: $ Robotics $ Internet of Things (IoT) $ Potential unlocking training $ 3D Modeling and 3D Printing This practical training is designed to equip participants with industry-relevant technical skills, foster innovation, and enhance entrepreneurial capacity in emerging technologies. Apply now and take the next step toward becoming a future technology innovator. https://forms.gle/Ns3z7ZfpMfNcxUPh8

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ እና ቦይንግ የአቪዬሽን ፈጠራ ማዕከል ለማቋቋም ታሪካዊ የረጅም ጊዜ የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ (ሐምሌ 1/2018 ዓ.ም) — ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ እና የዓለም አቀፉ የቦይንግ (NYSE:BA) ኩባንያ በፍጥነት እያደገ የሚገኘውን የአቪዬሽን ዘርፍ ይበልጥ ለማጠናከር፣ በኤሮስፔስ ምህንድስና ትምህርት ፈጠራን ለማበረታታት እንዲሁም ብቁ የሰው ኃይል ለማፍራት የሚያስችል የረጅም ጊዜ የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል። ይህ ስምምነት በባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (BiT) ውስጥ "የአቪዬሽን ፈጠራ ማዕከል" (Aviation Innovation Center) ለመገንባት የሚያስችል ሲሆን፣ ማዕከሉ በተግባር ላይ የተመሰረተ ትምህርት፣ ምርምር፣ ፈጠራ እንዲሁም ለጀማሪ የቴክኖሎጂ እና የፈጠራ ሥራዎች የድጋፍና የማብቃት (Incubation) አገልግሎት የሚሰጥ ይሆናል። የፊርማ ሥነ ሥርዓቱን የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር መንገሻ አየነ እጅጉ እና የቦይንግ አፍሪካ ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሄኖክ ተፈራ ሻውል ያከናወኑት ሲሆን፣ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶክተር ምትኩ ዳምጤ ስለ ተቋሙ አጠቃላይ ገለጻ አድርገዋል። የቦይንግ አፍሪካ ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሄኖክ ተፈራ እንደገለጹት፣ በሚቀጥሉት ሁለት አስርት ዓመታት የአፍሪካ አየር መንገዶች ከ1,200 በላይ አዳዲስ አውሮፕላኖችን እና ከ74,000 የሚበልጡ አዲስ የአቪዬሽን ባለሙያዎችን ይፈልጋሉ። ኢትዮጵያ በዘርፉ ከአፍሪካ ግንባር ቀደም መሆኗንና ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ደግሞ አንጋፋ የኢንጂነሪንግ ተቋም መሆኑን ጠቅሰው፣ ትብብሩ ተሰጥኦ ላላቸው ወጣቶች የሙያ ዕድገት ከመፍጠሩም በላይ እየተስፋፋ የመጣውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አገልግሎት፣ የአየር ማረፊያ መሠረተ ልማት እና የኤሮስፔስ አካላት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ዕድገትን ይደግፋል። የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር መንገሻ አየነ በበኩላቸው ትብብሩን "ታሪካዊ ምዕራፍ" በማለት የገለጹት ሲሆን፣ በኤሮስፔስ ትምህርት፣ ምርምርና የቴክኖሎጂ ሽግግር በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ ማዕከል ለመገንባት በጋራ እንደሚሠሩ አረጋግጠዋል። ይህ ማዕከል የብቁ ሰው ኃይል ልማትንና የቴክኖሎጂ ንግድን በመደገፍ ለሀገራዊ ኢንዱስትሪ ሽግግር አስተዋፅኦ የሚያበረክት ሲሆን፣ ቦይንግ ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ውስጥ በሂሳብና ሳይንስ (STEM) ትምህርት የጀመረውንና ባለፉት አምስት ዓመታት ከ14,700 በላይ ወጣቶችን ተጠቃሚ ያደረገውን ተግባር ይበልጥ ያጠናክረዋል።

🚀 Metacodz BiT 🤝 IS Hub AAU Summer Bootcamp Great news for the BiT community! 🎉 Metacodz BiT is excited to collaborate wit
🚀 Metacodz BiT 🤝 IS Hub AAU Summer Bootcamp Great news for the BiT community! 🎉 Metacodz BiT is excited to collaborate with IS Hub at Addis Ababa University to provide exclusive priority opportunities for BiT students in the FREE, fully virtual Summer Bootcamp. 💻 Choose one of four tracks: • AI • Frontend Development • Backend Development • Mobile App Development ⚠️ Limited seats. This opportunity is for students who are fully committed to completing the entire bootcamp. How to Apply ➊ Register here, ➋ After registering, contact @Famir3 on Telegram to be added to the Metacodz BiT priority list for our acceptance recommendation. Don't miss this opportunity to gain practical skills, build real-world projects, and strengthen your portfolio this summer. Join us for more updates: 📱 Telegram | LinkedIn: #MetacodzBiT #ISHub #SummerBootcamp #BiTTech #BDU

🚀 Metacodz BiT 🤝 IS Hub AAU Summer Bootcamp Great news for the BiT community! 🎉 Metacodz BiT is excited to collaborate wit
🚀 Metacodz BiT 🤝 IS Hub AAU Summer Bootcamp Great news for the BiT community! 🎉 Metacodz BiT is excited to collaborate with IS Hub at Addis Ababa University to provide exclusive priority opportunities for BiT students in the FREE, fully virtual Summer Bootcamp. 💻 Choose one of four tracks: • AI • Frontend Development • Backend Development • Mobile App Development ⚠️ Limited seats. This opportunity is for students who are fully committed to completing the entire bootcamp. How to Apply ➊ Register here, ➋ After registering, contact @Famir3 on Telegram to be added to the Metacodz BiT priority list for our acceptance recommendation. Don't miss this opportunity to gain practical skills, build real-world projects, and strengthen your portfolio this summer. Join us for more updates: 📱 Telegram | LinkedIn: #MetacodzBiT #ISHub #SummerBootcamp #BiTTech #BDU

እባካችሁ በ ክፍል ተወካይ በኩል ሰብስባችሁ ላኩ ለብቻ ስትልኩ ተቀባይነት የለውም…::

​📢 አስቸኳይ ማስታወቂያ ለአመታዊ መጽሄት ፎቶ ላልመረጣችሁ ተማሪዎች በሙሉ! ​በአሁኑ ሰዓት በግቢ ውስጥ የሌላችሁ እና የመጽሄት ፎቶ ያላስመረጣችሁ ተማሪዎች፣ ሂደቱን ለማፋጠን ሲባል በእናንተ ምትክ እኛ አመሳስለን እንድንመርጥላችሁ እያንዳንዳችሁ አንድ ጥሩ ፎቶ በተወካይችሁ በኩል(አንድ ላይ) በአስቸኳይ እንድትልኩልን እንጠይቃለን። ​📩 ፎቶ የምትልኩበት አካውንት፦ @halelujah143 ​⚠️ ማሳሰቢያ፦ ፎቶ ያላከ ተማሪ ከመጽሄቱ የሚወጣ መሆኑን በጥብቅ እናሳውቃለን!

​📢 አስቸኳይ ማስታወቂያ ለአመታዊ መጽሄት ፎቶ ላልመረጣችሁ ተማሪዎች በሙሉ! ​በአሁኑ ሰዓት በግቢ ውስጥ የሌላችሁ እና የመጽሄት ፎቶ ያላስመረጣችሁ ተማሪዎች፣ ሂደቱን ለማፋጠን ሲባል በእናንተ ምትክ እኛ አመሳስለን እንድንመርጥላችሁ እናንተነታችሁን የምንለይበት እያንዳንዳችሁ አንድ ፎቶ በአስቸኳይ እንድትልኩልን እንጠይቃለን። ​📩 ፎቶ የምትልኩበት አካውንት፦ @halelujah143 ​⚠️ ማሳሰቢያ፦ ፎቶ ያላከ ተማሪ ከመጽሄቱ የሚወጣ መሆኑን በጥብቅ እናሳውቃለን!

በቀጣይ በBiT ግቢአችን ውስጥ ሊስተካከል ወይም መሻሻል አለበት የምትሉት፣ በህብረቱ አቅም ሊፈታ የሚችል ምን ችግር አለ? ​ይሄ ነገር ቢሰራበት/ቢስተካከል መልካም ነው" የምትሉትን ማንኛውንም ገንቢ ሃሳብ በኮመንት (Comment) አጋሩን! የእናንተ ድምፅ ለተሻለ ለውጥ መነሻ ነውና ሃሳባችሁን ለመስማት ዝግጁ ነን። 👇

​ውድ ተማሪዎቻችን፣ የዕረፍት ጊዜያችሁን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ ተጨማሪ ምርጥ እና ጠቃሚ የኦንላይን መማሪያ ገጾችን (Platforms) ይዘንላችሁ ቀርበናል፦ ​1. ለቴክኖሎጂ፣ ዲዛይን እና ለፈጠራ ስራዎች (Tech & Creative Skills) ​Scrimba: የዌብ ዲዛይን እና ኮዲንግ (Frontend Development) በተለየ ሁኔታ ኮዱን እያዩና አብረው እየጻፉ (Interactive) በነፃ መማሪያ ድንቅ ገጽ 👉 scrimba.com ​Cognitive Class (by IBM): በዳታ ሳይንስ (Data Science)፣ በ-AI (Artificial Intelligence) እና በብሎክቼይን ላይ በርካታ ነፃ ኮርሶችን እና ዲጂታል ባጆችን (Badges) የሚሰጥ 👉 cognitiveclass.ai ​UX Design Institute (Free Courses): ስለ ዩዘር ኤክስፒሪያንስ (UX/UI Design) እና ስለ አፕሊኬሽን ዲዛይን መሰረታዊ እውቀት በነፃ የሚሰጥበት 👉 uxdesigninstitute.com ​2. ከታዋቂ ዩኒቨርሲቲዎች በነፃ ለመማር (Top Universities) ​MIT OpenCourseWare: የአለማችን ቁጥር አንድ የቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (MIT) ሙሉ የኮምፒውተር ሳይንስ እና የኢንጂነሪንግ ማስተማሪያ ቁሳቁሶችን እና ሌክቸሮችን በነፃ ያጋራበት ገጽ 👉 ocw.mit.edu ​Khan Academy: በተለይ ለሂሳብ (Math)፣ ለሳይንስ እና ለኮምፒውተር ፕሮግራሚንግ መሰረታዊ እውቀቶች ፍጹም ነፃ እና ግልጽ የሆኑ ቪዲዮዎችን የሚያቀርብ 👉 khanacademy.org ​3. ለአለም አቀፍ እድሎች፣ ውድድሮች እና ስኮላርሺፖች (Opportunities & Hackathons) ​Opportunity Desk: በአለም ዙሪያ ያሉ ነፃ የክረምት ስልጠናዎችን፣ የወጣቶች ኮንፈረንሶችን፣ የገንዘብ ሽልማት ያላቸው ውድድሮችን እና ስኮላርሺፖችን ሰብስቦ የሚይዝ ገጽ 👉 opportunitydesk.org ​Devpost: በቴክኖሎጂ እና በሶፍትዌር ዙሪያ የሚዘጋጁ አለም አቀፍ የሃካቶን (Hackathon) ውድድሮችን የሚያገኙበት እና ከተለያዩ ሀገራት ተማሪዎች ጋር በጋራ መስራት የሚችሉበት 👉 devpost.com ​💡 የህብረቱ ምክር፦ ትልቅ ስኬት የሚጀምረው በትንሽ እርምጃ ነው። ከላይ ከተጠቀሱት ውስጥ አንዱን መርጣችሁ በቀን 30 ደቂቃ ብቻ በመመደብ እረፍታችሁን ፍሬያማ አድርጉ!

ውድ ተማሪዎቻችን፣ የዕረፍት ጊዜያችሁን ፍሬያማ ለማድረግ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያላቸውንና በነፃ ሰርተፊኬት የሚሰጡ ድንቅ የኦንላይን መማሪያ ገጾችን (Platforms) ሊንክ ይዘንላችሁ ቀርበናል፦ ​1. ለቴክኖሎጂ እና ለሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ (Tech & Coding)freeCodeCamp: ሙሉ በሙሉ ነፃ የሆነ፣ ከዌብ ዲዛይን (HTML/CSS/JS) እስከ Python እና AI ድረስ በፕራክቲካል ፕሮጀክቶች የሚያስተምር 👉 freecodecamp.orgHarvard's CS50 (via edX): የሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ታዋቂው የኮምፒውተር ሳይንስ መግቢያ ኮርስ በነፃ የሚሰጥበት 👉 edx.org/course/cs50s-introduction-to-computer-scienceCoursera (Financial Aid): እንደ Google እና IBM ካሉ ታዋቂ ተቋማት ሰርተፊኬት ለማግኘት "Financial Aid Available" የሚለውን በመጫን በነፃ መማር ይቻላል 👉 coursera.orgKaggle Learn: በዳታ ሳይንስ (Data Science) እና ማሽን ለርኒንግ (Machine Learning) ላይ ፍላጎት ላላቸው አጫጭርና ተግባራዊ ኮርሶች 👉 kaggle.com/learn2. ለአመራር ብቃት፣ ለቢዝነስ እና ለዲጂታል ማርኬቲንግ (Leadership & Marketing)Atingi Platform: በተለይ ለአፍሪካውያን የተዘጋጀ፣ በአመራር ብቃት (Leadership)፣ በስራ ፈጠራ እና በዲጂታል ማርኬቲንግ ላይ በርካታ ነፃ ኮርሶችን ከነሰርተፊኬቱ የሚሰጥ 👉 atingi.orgGoogle Digital Garage: የዲጂታል ማርኬቲንግ መሰረታዊ እውቀቶችን በነፃ ተምረው ማረጋገጫ ሰርተፊኬት የሚያገኙበት 👉 skillshop.exceedlms.com/student/catalog/list?category_ids=2844-google-digital-garageGreat Learning Academy: በሶፍትዌር፣ በዳታ ሳይንስና በቢዝነስ ዘርፎች ሰፋ ያሉ ነፃ አጫጭር ኮርሶችን የሚያቀርብ 👉 mygreatlearning.com/academy

ይህ የዕረፍት ጊዜ ከአእምሮ እረፍት ባሻገር፣ ራሳችንን የምናበለጽግበትና አዳዲስ ክህሎቶችን (Skills) የምናዳብርበት ጥሩ አጋጣሚ ነው። ​በሚቀጥሉት ቀናት ለሙያችን እና ለግል እድገታችን የሚጠቅሙ Online ስልጠናዎችን፣ ኮርሶችን እና ጠቃሚ እድሎችን እዚህ ግሩፕ ላይ የምናጋራችሁ ይሆናል። እናንተስ ይህንን እረፍት በምን ለማሳለፍ አቅዳችኋል? ሀሳባችሁን ኮሜንት ላይ አጋሩን እስኪ ለጓደኞቻችሁ ምክር ስጡ!

ውድ የጊቢያችን ተማሪዎች የዘንድሮውን የትምህርት ዘመን በብዙ ልፋት እና ጥረት በስኬት አጠናቀን ወደየቤተሰቦቻችን ተመልሰናል። ግቢው ያለ እናንተ ድምቅታ ባዶነቱ ቢያስታውቅም፣ ሁላችሁም አድካሚውን ጊዜ አሳልፋችሁ አሁን ጥሩ እረፍት እንደምታደርጉ ተስፋ አደርጋለሁ። ​በነበረን ቆይታ ለነበረው ትብብር ሁላችሁንም እያመሰገንኩ፣ ከቤተሰብ ጋር መልካም እና ፍሬያማ የዕረፍት ጊዜ እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ! 🙏

ውድ አንባቢያን ዛሬ ይዘንላችሁ የቀረብነው በሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በ2018 ዓ.ም ከተመረቁ ተማሪዎች መካከል አብላጫ ውጤት ያስመዘገበውን ተመራቂ ሲሆን በትምህርት ቆይታው ስኬታማ የሆነበትን እና የህይወት ተሞክሮውን ልናካፍላችሁ ወደናል መልካም ንባብ፡፡ በመጀመሪያ ለቃለ ምልልሱ ፈቃደኛ ስለሆንህ እናመሰግላለን! ISC:- እስኪ እንተዋወቅ ሙሉ ስም እና የትውልድ ቦታህን ብትገልጽልን? ስሜ ብሩክ ተመስገን እባላለሁ። ተወልጀ ያደኩት ከዚሁ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፔዳ ግቢ ውስጥ ነው። ISC:- የልጅነት አስተዳደግህና የትምህርት አቀባበልህ ምን እንደሚመስል ብታብራራ? ​​ተማሪ ብሩክ ፡- የልጅነት ህይወቴ በወላጆቼ ፍቅር፣ ትጋትና ያልተቆጠበ ድጋፍ የታነጸ ነበር። በቤተሰቤ ውስጥ የበኩር ልጅ እንደመሆኔ መጠን የተጣለብኝ ኃላፊነት የነበረ ቢሆንም፣ በወቅቱ እንደማንኛውም ህጻን ወደ ጨዋታ የማደላበት ጊዜ ይበዛ ነበር። ነገር ግን ከ9ኛ ክፍል ጀምሮ በትምህርቴ ላይ ከፍተኛ ትኩረትና ጥረት ማድረግ ጀመርኩ። በሂደትም የነበረኝን የትምህርት አቀባበልና ውጤት በከፍተኛ ደረጃ በማሻሻል ዛሬ ለደረስኩበት የላቀ የትምህርት ደረጃ ለመብቃት ችያለሁ። ISC;- የምን ትምህርት ክፍል ተማሪ ነህ፤ ያስመዘገብኽው ውጤት፤ በባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ቆይታህ የነበረህ የትምህርት አቀባበል ሁኔታ ምን እንደሚመስል ብትነግረን? ​ተማሪ ብሩክ ፡- በባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ (Software Engineering) ተማሪ ነኝ። ያስመዘገብሁት ውጤትም CGPA 3.97 ነው፡፡ በዩኒቨርሲቲ ቆይታዬ የንድፈ-ሃሳብ ክፍለ-ጊዜዎችን (Lectures) በአግባቡ ለመከታተል እተጋ ነበር። ከመምህራን የሚሰጡ እውቀቶችንና ልምዶችን በትኩረት ከመቅሰም ባሻገር፣ ያልተረዱኝን ነጥቦች በግልፅ በመጠየቅ አጠናክራለሁ። በተጨማሪም በክፍል ትምህርት ብቻ ሳልወሰን፣ የዘርፉን ወቅታዊ እድገቶች ለመከታተል የበየነ-መረብ (Internet) ግብዓቶችን በስፋት በመጠቀም እውቀቴን ሳበለጽግ ቆይቻለሁ። ISC:- በዩኒቨርሲተው ቆይታህ የነበረህ አስደሳች ወይም አሳዛኝ ገጠመኝ፤ የፍቅር ታሪክም ካለህ ባጭሩ ብትገልጽ? ​​ተማሪ ብሩክ ፡- የፍቅር ታሪክ ጉዳዩን ለጊዜው ብናልፈው ይሻላል (ከፈገግታ ---- ጋር) ። ከአስደሳች ገጠመኞቼ መካከከል ግን ከክፍሌ ተማሪዎች ጋር አብረን የምናሳልፋቸው የመዝናኛ ጊዜያትና ጨዋታዎች ተጠቃሽ ናቸው። እነዚህ አጋጣሚዎች ራሴን ከከባዱ የትምህርት ጫና ለቀቅ አድርጌ ጊዜውን በጥሩ ሁኔታ እንድደሰትበትና አእምሮዬ እንዲታደስ ረድተውኛል። አሳዛኝ ገጠመኞች ባይጠፉም፣ ሁልጊዜም መልካሙንና አስደሳቹን ገጽታ መያዝን እመርጣለሁ። ISC:-  ከመምህራንና ከጓደኞችህ ጋር የነበረህ ቆይታና ግንኙነት ምን ይመስላል? ​​​ተማሪ ብሩክ ፡- የጓደኝነት ግንኙነቴን በሁለት መልኩ ማየት እችላለሁ፤ የጀመሪያው በማህበራዊ ህይወት በኩል አብሮ ከመኖርና ከመማር የሚመጣ ሲሆን፣ በተለያዩ ሁነቶች (Events) እና ስነ-ስርዓቶች ላይ በመሳተፍ የዳበረ ነው። በእነዚህ ጊዜያት ውስጥ አስደሳች፣ ፈታኝና ትምህርት ሰጪ የሆኑ በርካታ አጋጣሚዎችን አብረን አሳልፈናል። ሁለተኛው በትምህርት ሂደት ውስጥ ያለው ግንኙነት ሲሆን፣ ይህም የቡድን ስራዎችን (Group Projects) ፣ የማሰልጠኛ መድረኮችንና የኢንተርንሺፕ (Internship) ስራዎችን ያጠቃልላል። እነዚህ ተግባራት በተማሪዎች መካከል መልካም ተግባቦት እንዲኖር፣ ስራን በኃላፊነት ተከፋፍሎ የመስራት፣ በተናጠል የተሰሩ ክፍሎችን የማቀናጀት እና ቡድንን የመምራት ክህሎቶቻችንን እንድናዳብር ትልቅ እድል ሰጥተውናል። ​ከኢንስቲትዩቱ መምህራን ጋር የነበረኝ ግንኙነትም እጅግ መልካም ነበር። በማንኛውም ጊዜ ጥያቄ ሲኖረኝ በአክብሮትና በአግባቡ ያስተናግዱኝ የነበረ ሲሆን፣ ምክር በምሻበት ወቅትም አስፈላጊውን እገዛ አድርገውልኛል። ከአንዳንዶቹ ጋርማ ከመምህርነት ባለፈ እንደ ጓደኛ በቅርበት የምንግባባበት የሙያ ትስስር ፈጥረናል። ISC:-  እንደ አርዓያ የምትቆጥራቸው ግለሰቦች ወይም መምህራን ካሉ ብትነግረን? ​​​ተማሪ ብሩክ ፡-  የናቪዲያ (Nvidia) ተባባሪ መስራችና ዋና ስራ አስፈፃሚ ጄንሰን ሁዋንግ (Jensen Huang)፣ የሙያ ልቅናን ከረጅም ጊዜ አርቆ አሳቢነት ጋር አቀናጅቶ የሚጓዝ መሪ በመሆኑ ለእኔ ቀዳሚ የአርአያነት ተምሳሌት ነው። በልጅነቴ ለቪዲዮ ጌሞች (Video Games) ከነበረኝ ፍቅር የተነሳ በግራፊክስ ካርዶች (Graphics Cards) በኩል መጀመሪያ ባውቀውም፣ እያደግኩ ስመጣ ግን ለዘመናዊው AI መሰረት በሆነው ቴክኖሎጂ ላይ የነበረው የፅናት ጉዞ በጥልቀት ማርኮኛል። እኔም በሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ ትምህርቴ የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ የምተጋ ተማሪ እንደመሆኔ፣ የእሱ ታሪክ በንድፈ-ሃሳብ ብቻ ሳልወሰን ማህበረሰባዊ ተፅዕኖ ያላቸውን ተጨባጭ የቴክኖሎጂ መፍትሄዎች በተግባር እንድገነባ ያተጋኛል፤ ይህም በፈታኝ ሁኔታዎች ውስጥ ሳይቀር የረጅም ጊዜ እሴት ባላቸው የምርምርና የልማት ስራዎች ላይ በትኩረት እንድሰራ ስንቅ ሆኖኛል። ISC:- በቀጣይ ከምረቃ በኋላ ለመስራት ያሰብካቸው ስራዎች ምንድን ናቸው? ​​​ተማሪ ብሩክ ፡- በትምህርቴና በግል ጥረቴ ያገኘሁትን የሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ እውቀትና ክህሎት በመጠቀም፣ በንድፈ-ሃሳብ ብቻ ያልተገደቡና በተግባር በሰዎች ህይወት ላይ ተጨባጭ ለውጥ የሚያመጡ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን መገንባት በቀጣይ ትልቁ ትኩረቴ ነው። ከምረቃ በኋላ እውቀቴን ይበልጥ ለማስፋት የድህረ-ምረቃ ስኮላርሺፖችን (Scholarships) ማግኘት እና ትኩረቴን በ-AI Engineering ላይ ማድረግ ዋነኛ እቅዴ ነው። በተለይም እንደ አማርኛ ላሉ ውስን ግብዓት ያላቸው ቋንቋዎች (Low-resource languages) የላቁ የ-website፣ የ-AI እና የ-NLP (Natural Language Processing) መፍትሄዎችን በማልማት፣ ውስብስብ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ማህበረሰባዊ እሴት እንዲፈጥሩና የብዙዎችን የዕለት ተዕለት ህይወት እንዲያቃልሉ ማድረግ የህይወት ትልቁ አላማዬ ነው።  ISC:- ማስተላለፍና ማመስገን የምትፈልፈው መልእክት ካለ? ​​​ተማሪ ብሩክ ፡- በዚህ የስኬት ጉዞዬ ውስጥ ዘወትር ያልተለየኝንና የህይወቴ ብርሃን የሆነውን ሁሉን ቻይ እግዚአብሔርን፣ እንዲሁም የላሰለሰ ድጋፍና ማበረታቻ በማድረግ ሁልጊዜም ከጎኔ ያልተለዩትን ውድ ቤተሰቦቼንና ጓደኞቼን በላቀ ክብርና ምስጋና ማመስገን እወዳለሁ። ​ተጨማሪ ማስተላለፍ የምፈልገው መልእክት ቢኖር፡ ማንኛውም ሰው ጉዞውን ሲጀምር ፍጹም (Perfect) ሆኖ እንዳልሆነ በመረዳት፣ በአዕምሯችን ውስጥ ያለን ትልቅ እቅድ ወደ ተግባር ለመለወጥ መጀመሪያ መሞከርና መጀመር እንዳለብን ነው። ማንም ሰው ሲጀምር ባለሙያ ሆኖ አይነሳም፤ ነገር ግን በፅናት መሞከርና መለማመድ ወደ ላቀ ጥበብና ስኬት የሚያደርስ ብቸኛው መንገድ ነው። ለነበረን ቆይታ እናመሰግናለን !!

3.75 እና ከዛ በላይ ያመጣችሁ ሴት ተመራቂ ተማሪዎች እንኳን ለዚህ ታላቅ ክብር አበቃችሁ እያልን ስካርፍ(ሪቫን) ያልወሰዳችሁ ካላችሁ የዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ተቀዳሚ ዳይሬክተር ቢሮ ቁጥር 309(ዊዝደም) መጣችሁ እንድትወስዱ እናሳስባለን።

ስፖርት ማስተር ተከፍቷል

ላይብራሪ ያላስፈረማችሁ ተመራቂ ተማሪዎች አሁን እስከ ሰባት ሰአት ባለው ብቻ ኮርያ ህንጻ ቁጥር 9 እየሄዳችሁ እንድታስፈረሙ ይሁን

Dear Fellow Graduates, Today we celebrate not only our graduation but also the incredible journey that brought us here. Together, we faced challenges, overcame obstacles, and created memories that will last a lifetime. Every late-night study session, every project, and every achievement has shaped us into the graduates we are today. It has been an honor to serve as your Graduation Class President and to share this remarkable journey with each of you. I extend my heartfelt gratitude to our families, instructors, and friends for their unwavering support and encouragement throughout our university years. As we step into a new chapter of our lives, let us carry forward the knowledge, friendships, and values we have gained. May we continue to strive for excellence, embrace new opportunities, and make a positive impact wherever life takes us. Congratulations, Class of 2026! The future is ours to shape. I wish each of you success, happiness, and fulfillment in everything you do. Once a Tiger, Always a Tiger. Go Tigers! Yohanees Graduation Class President