1 327
订阅者
-124 小时
+67 天
+8830 天
帖子存档
ኢ-መደበኛ አንቀሳቃሾችን ወደ መደበኛ ኢንተርፕራይዝ እንዲሸጋገሩ ከአበዳሪ ተቋማት ጋር በመተባበር በቀጣይም ብድር የሚያገኙበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የሚያስችል የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ፤
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የኢንተርፕራይዞች ልማት ዳይሬክቶሬት ይህን የስልጠና መድረክ ለኢ-መደበኛ አንቀሳቃሾች ሲያዘጋጅ የሥራን ጠቀሜታ በመረዳትና ለሥራ ያላቸውን ተነሳሽነት በመጨመር የራሳቸውንና የቤተሰቦቻቸውን ህይወት እንዲለውጡ አስፈላጊና ጠቃሚ የሆኑ መሠረታዊ የንግድ ክህሎቶች እንዲጨብጡ ታሳቢ ያደረገ ነው፤
የኢንተርፕራይዞች ልማት ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ የሆኑት ወ/ሮ መቅደስ ከፈለኝ እንደገለጹት አንቀሳቃሾቹ ይህን ስልጠና ከወሰዱ በኋላ በሥራ ፈጠራና ሥራ ፈጣሪነት ላይ ግንዛቤያቸውን የሚጨምር ሲሆን በንግዱ ሙያ ውስጥ ውጤታማ ሊያደርጉ የሚያስችላቸውን ባህሪ በመላበስና ብቃቶችን እንዲያዳብሩ የሚያግዛቸው እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ጥር 23/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
በድሬዳዋ ነጻ ንግድ ቀጠና ውስጥ አጫጫር የሙያ ስልጠና ለመስጠት የተደራጀው የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ የእሳትና ድንገተኛ አደጋ መከላከል እና መቆጣጠር እንዲሁም የመጀመሪያ የህክምና እርዳታ አሰጣጥ ስልጠና በአዲሱ የሙያ ደረጃ መሰረት አጫጭር የቴክኒክና ሙያ ስልጠና እንዲሰጥ የእውቅና እድሳት ለማድረግ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ ምልከታ ተደረገ።
በአጠቃላይ ለስልጠናው አስፈላጊ የሆኑ የሰው ሃይልና የማሰልጠኛ መሣሪያዎች ስለመሟላታቸው እንዲሁም የስልጠና አሰጣጥ አቅምን በምልከታ ለማረጋገጥ በባለሞያዎች የተዋቀረ ቡድን ማሰልጠኛውን ከሚመሩ እና ከሚያስተባብሩ ባለሙያዎች ጋር ውይይት የተካሄደ ሲሆን በቀጣይ ማሰልጠኛው ለአንድ አመት የተሰጠውን የምዝገባ ፈቃድ አፈጻጸም ጥሩ መሆኑ መመልከት የተቻለ ሲሆን የቀጣይ ሶስት አመታት የስልጠና የእውቅና ፈቃድም በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ በኩል የሚያገኝ ይሆናል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ጥር 23/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ስር የሚገኘው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የአሰልጣኝ ልማትና ተቋማት ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት የኮሌጆችን አቅም ለማሳደግና የአሰልጣኝ መምህራንን የክህሎት ክፍተት መሙላት የሚያስችል ተከታታይነት ያለው ስራ በመስራት ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡
በኢትዮጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አሰልጣኝ መምህራን የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠናን ዲጂታላይዝ ለማድረግ የሚያስችሉ ስራዎችን በአይ ሲ ቲ ትምህርትና ስልጠና ክፍል ተግባራዊ ተደረገ፤ ይህም አሰልጣኝ መምህራኑ እርስ በእርስ የክህሎት ሽግግር በማድረግ በተቋሙ የሚሰጡ ስልጠናዎችን በኢ-ለርኒንግ ለመስጠት የሚያስችሉ ግብዓቶችን በራስ አቅም በመስጠት SSD RAM Upgrade በማድረግና ወርክሾፖችን በማደራጀትና በቀጣይ የሶፍትዌር በተለይም ፎቶሾፕ ስልጠናዎችን ሊያሰጡ የሚችሉ ስራዎች ተሰርቷል፡፡
በዚህም የኮሌጁን አሰልጣኝ መምህራንን አቅም ከመገንባቱ ባሻገር እና በወጪ አንጻር ኮሌጁ ሊያወጣ የሚችለውን ከፍተኛ በጀት የቀነሰ ሆኗል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ጥር 22/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
ለሥራ ፈላጊዎች የማይንድ ሴት ስልጠና ተሠጠ።
ስልጠናው የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የሥራ ዕድል ፈጠራና አንድ ማዕከልማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ሥራ ፈላጊዎች ተቀጥሮ መስራት ላይ ብቻ ሳይሆን በግልም ሆነ ተደራጅተው ሥራ እንዲፈጥሩ በሚያነሳሳ መልኩ ቀርቧል።
በዚህም ተሳታፊ የሆኑ ከአስተዳደሩ ወረዳዎች የተወጣጡ ሥራ ፈላጊዎች ከዚህ በፊት ተቀጥሮ ለመስራት ብቻ ይጠብቁ የነበሩ ከስልጠናው ባገኙት ግንዛቤ በግልም ሆነ ተደራጅቶ ለመስራት መነሳሳት እንደተፈጠረባቸው ገልጸዋል።
ቢሮው በአስተዳደሩ ትኩረት የተሰጠውን የስራ አጥ ቁጥር ለመቀነስ የተጀመሩ የተለያዩ ስራዎችን በተለይም በኮሪደር ልማቱ እና ከኢንዱስትሪዎች ጋር ግንኙነት በመፍጠርና ሥራ ፈላጊዎች ተደራጅተው ወደ ሰራ እንዲሰማሩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ በመስራት ላይ ይገኛል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ጥር 22/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
#በመካከላችን
“አንድ በቁጥር፤ ብዙ በግብር!”
ተወልዶ ያደገው እዚሁ በተወዳጇ ድሬዳዋ ሲሆን ከልጅነቱ በተለያዩ የጥበብ ስራዎች ዝንባሌ ትኩረት በመስጠትና ደስ ስለሚያሰኘው እየሞከረ እንዳደገ ይናገራል፤ እራሱን ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ በውስጡ የሚብላላ ቁጭት እንዳለው ይህም ድሬዳዋ የብዙ ጠቢባን መፍለቂያና መናኸሪያ የመሆኗን ቅርስነት ቅብብሎሽ አንጸባራቂ ሆኖ መመልከት አካልም መሆን መሻቱና ናፍቆቱ መሆኑን ይገልጻል፡፡
ዛሬ ልናስተዋውቃችሁና አብልጠን ልናበረታታው ይዘን የቀረብነው የሥራና ክህሎት ቤተሰብ አሰልጣኝ መምህር ዳንኤል በላይ ይባላል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክሎህት ቢሮ ስር በሚገኘው የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የአይ ሲ ቲ ትምህርትና ስልጠና ክፍል ውስጥ በአሰልጣኝ መምህርነት ዜጎችን እያበቃ የሚገኝ ግን በቃ የማያውቀው የባለ ብዙ ሞያዎችና ተሰጥኦ ባለቤት ድንቅ ቤተሰብ ነው፡፡
እናም ጥበበኛው በቁጥር አንድ ሰው ነው ግና በክህሎትና ግብር ብዙ ሆኖ አሰልጣኝ መምህር ነው ስትሉት ሰዓሊ ሆኖ ታገኙታላችሁ እኛ ለማበረታታትና ለመደገፍ ቅንነታችንን አብዝተን እንግለጥ እንጂ ከሙዚቃው መንደር ብትሄዱ እርሱ በዚያም ይገኛል መቼ በዚህ ብቻ ተገድቦ የተለያዩ የቅርጻቅርጽ ስራዎችን ሲሰራ ከተፈጥሮ ውበት ጋር አፍቃሪየ መናኝ ሆኖ በንመለከተው አንታዘበው እናበረታታው ነገ ብዙ ክህሎት ላላቸውና ለሚሰሩ አዕምሮዎችና እጆች አርዓያ ይሆናል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ጥር 21/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኤጀንሲ በ2017 በጀት ዓመት በመጀመሪያው ግማሽ ዓመት የደረሱበትን የዕቅድ አፈፃፀም ደረጃ በመገምገም የታዩ ጠንካራ ጎኖችን ለማስቀጠል እንዲሁም በአፈፃፀም ላይ ውስንነት የታየባቸውን ተግባራት ለይቶ አፋጣኝ መፍትሄዎችን ለማስቀመጥና የዓመታዊ ዕቅድ አፈፃፀም ውጤትን በላቀ ደረጃ መፈጸም የሚያስችል አቅም ለመፍጠር በቢሮው እና በስሩ ከሚገኙ ኮሌጆች አመራርና ባለሞያዎች ጋር ውይይት አካሄደ፡፡
በአጠቃላይ በሪፖርቱ ከተመላከቱ ስራዎች መካከል በ3 የመንግስት እና በ5 የግል ኮሌጆች የቅበላ መጠን ስንመለከት የአዲስ ሰልጣኞች ቅበላ ወንድ 2319 ሴት 2662 በድምሩ 4981 የአዳዲስ ሰልጣኞች ቅበላ የተከናወን ሲሆን በዚህም በእቅድ ከተያዘው 4924 የቅበላ መጠን አንፃር 4981 የተንነ ሆን የ101.2 በመቶ አፈፃፀም ያለው ሲሆን የነባር ሰልጣኞች ቅበላ ወንድ 2087 ሴት 3164 በድምሩ 5251 የነባር ሰልጣኞች ቅበላ ተከናውኗል ይህም በእቅድ ከተያዘው 5380 የቅበላ መጠን አንፃር የ97.6 በመቶ አፈፃፀም ሲኖረው በገበያ ተኮር አጫጭር ስልጠናዎችን 2689 ገበያ ተኮር አጫጭር ስልጠናዎችን ለማከናወን ታቅዶ 1201 ወንድ 1456 ሴት ጠቅላላ 2657 ስልጠናን ማከናወን የተቻለ ሲሆን ይህም ከግማሽ ዓመቱ ዕቅድ አንፃር የ98.8 በመቶ አፈፃፀም መድረስ ተችሏል፡፡
ቢሮው ከከሌጆች ጋር ዕቅዱን በመናበብ የመከለስ፣ የድጋፍና ክትትል ስራውን ማጠናከር፣ የመደበኛ ሰልጣኝ ማብቃት ላይ ኢንስፔክሽን በየጊዜው በማድረግ ዞኒንግ እና ዲፈረንሼሽን ላይ በዚህ በጀት አመት በተዘጋጀው መውጫ ዕቅድ ወደ ተግባር በመግባት፤ የከተማዋን ነዋሪ ችግር የሚፈቱ ከዚህ ቀደም ተሰርተው የተቀመጡትን በማሻሻል መጠቀም እንዲሁም ትምህርትና ስልጠናውን በተሻለ መልኩ ለመምራት የሚያስችሉ መመሪያዎችን በማዘጋጀት ወደ ስራ ማስገባትና ዲጂታላይዜሽን ላይ የተጀመሩ ስራዎችን በማጠናከር ወደ ልህቀት ማሳደግ ላይ በቀጣይ ስድስት ወራት ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ የቢሮው ም/ኃላፊ እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ገልጸዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ጥር 20/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
+7
በሶማሌ ኢሳ ማህበረሰብ ዘንድ ሰላምን በማስፈን እና አብሮነትን ለማጠናከር ለበርካታ መቶ ዓመታት የቆየው ”ሔር ኢሴ “ ቃላዊ ህግና የዳኝነት ስርዓት በዩኔስኮ በወካይ የማይዳሰስ የሰው ልጆች ቅርስነት መመዝገቡን ተከትሎ በድሬዳዋ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል
በድሬዳዋ አለማቀፍ ስቴዲየም በሺዎች የሚቆጠሩ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ባህላዊ አልባሳትን በመልበስ እየታደሙበት የሚገኘው የእውቅና መርሃ-ግብር መካሄድ ጀምሯል።
በዝግጅቱ ከጅቡቲ ፣ ከሱማሊያ ፣ ከሱማሌ ብሔራዊ ክልል መንግስት የመጡ ልኡካን ቡድኖች እና ተጋባዠ እንግዶች እየታደሙ ነው ።
በትዕግስት ቶሎሳ
ፎቶ፦ አገኘሁ ሸዋረጋ
#ዜና በሶማሌ ኢሳ ማህበረሰብ ዘንድ ሰላምን በማስፈን እና አብሮነትን ለማጠናከር ለበርካታ መቶ ዓመታት የቆየው ”ሔር ኢሴ “ ቃላዊ ህግና የዳኝነት ስርዓት በዩኔስኮ በወካይ የማይዳሰስ የሰው ልጆች ቅርስነት መመዝገቡን ተከትሎ በድሬዳዋ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል።
ዛሬ ከሰዓት በኋላ በድሬዳዋ ወጣቶች አካዳሚ የኢሳ እናቶች ያዘጋጁዋቸው የማህበረሰቡ ባህላዊ ምግቦች ቅምሻን ለመታደም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በስፍራው ተገኝተዋል ፡፡
የማህበረሰቡን አኗኗርና ባህል እና የአመጋገብ ስርዓት ጭምር እንዲያጸባርቅ ተደርጎ በተዘጋጀው የባህላዊ ምግቦች ትርኢትና ቅምሻ ላይ ከጅቡቲ ፣ ከሱማሊያ እና ከሱማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትና የመጡ እንግዶች እና ልኡካን ቡድን አባላት የታደሙ ሲሆን ለህዝቦች የእርስ በእርስ ከቀራረብ ሚናው ከፍተኛ ከመሆኑም በላይ ወጣቶች ባህልና ወጋቸውን እንዲማሩም አስተዋጾው የጎላ መሆኑም ተወስቷል ፡፡
ይህ ዝግጅት ነገ ቅዳሜም በድሬዳዋ አለማቀፍ ስቴዲየም በሺዎች የሚቆጠሩ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ባህላዊ አልባሳትን በመልበስ የሚታደሙበት የእውቅና መርሃግብር እንደሚካሔድ እና ምሽት ላይ በወጣቶች አካዳሚ በሚዘጋጅ ደማቅ የሙዚቃ ኮንሰርት ማጠቃለያ እንደሚደረግ ከወጣው መርሐ ግብር መረዳት ተችሏል፡፡
"ሔር ኢሴ" በተባበሩት መንግስታት የትምህርትና የባህል ተቋም /ዩኔስኮ/የዓለም ቅርስ ሆኖ መመዝገቡን ምክንያት በማድረግ ከዛሬ ጀምሮ በድሬዳዋ በዓሉ በተለያዩ መርሀ ግብሮች እየተከበረ ይገኛል ።
የሶማሌ ኢሳ ማህበረሰብ ፍትሃዊ ያልተጻፈ መተዳደሪያ ሕግ “ሔር ኢሴ” በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የሰው ልጆች ወካይ ዓለም አቀፍ የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርሶች ዝርዝር ውስጥ መመዝገቡን ምክንያት በማድረግ በዛሬው ዕለትም የፓናል ውይይት ተካሂዷል።
