1 327
订阅者
-124 小时
+67 天
+8830 天
帖子存档
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የበጀት፣ ኢኮኖሚ ንግድና ኢንድስትሪ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮን የ2017 በጀት አመት የመጀመሪያው 6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የመውጫ ውይይት አካሄደ ።
==========================
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች በስራቸው የተደለደሉትን የአስተዳደሩ ተቋማት ዕቅድ አፈፃፀም ለመገምገም ያለመ የመስክ ምልከታ ሲያደርጉ የቆዩ ሲሆኑ በዛሬው ዕለትም የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የበጀት፣ ኢኮኖሚ፣ ንግድ ና ኢንዱስትሪ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ክትትልና ቁጥጥር ከሚያደርግባቸው የአስተዳደሩ ተቋማት መካከል አንዱ የሆነውን የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ በመገኘት የ2017 በጀት አመት የመጀመሪያውን የ6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማና የመውጫ ውይይት አድርጓል።
ቋሚ ኮሚቴው በቢሮው ስር ያሉ ተጠሪ ተቋማትና ፕሮጀክቶች ከክህሎት ልማትና ስራ ዕድል ፈጠራ ጋር ተያያዝነት ያላቸውን ተግባራት አፈፃፀም ያሉበትን ደረጃ ባለፉት ቀናት የመስክ ምልከታ ሲያደርጉ ቆይቶ በዛሬው ዕለትም ከቢሮው ማኔጅመንት አባላት ጋር በተቋሙ የግማሽ አመት ዕቅድ አፈፃፀም ዙሪያ ሰፋ ያለ ውይይት በማድረግ በአፈፃጸም ሂደት የታዩ ጠንካራ ጎኖች ተጠናክረው እንዲቀጥሉና በውስንነት የተለዩ ጉዳዮች መታረም እንዳለባቸው የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ የመውጫ ግብረ መልስ ተሰጥቷል።
በዚህም የቢሮው ም/ኃላፊና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ለቋሚ ኮሚቴው በክህሎት ልማት በመደበኛና አጫጭር ስልጠናዎች፣ በከተማ እና ገጠር ስራ ዕድል ፈጠራ፣ በኢንተርፕራይዝ ልማት ፣ በአሰሪና ሰራተኛው ዘርፍ እንዲሁም የካፒታል ፕሮጀክቶች አፊፃፀም ባለፉት ስድስት ወራት የተሰሩ ስራዎችን እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እንዲሁም በቀጣይ የታሰቡ ጉዳዮችን ጠቅሰው ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በአጠቃላይ ቢሮው በ2017 ዓ.ም የ6 ወር ዕቅድ አበረታች አፈፃፀሞች መታየቱንና በዘርፉ በውስንነት የተለዩትን እንዲታረሙ በማድረግ በቀጣይ በተለይ የሥራና ክህሎት ምክር ቤትን በመጠቀም ሁሉም የዘርፉ ባለድርሻ አካላት የተጀመረውን ቅንጅታዊ አሰራር አጠናክሮ በማስቀጠል በስፋትና በጥራት የክህሎት ልማትና የከተማና የገጠር ስራ ዕድል ፈጠራ ላይ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንዳለባቸው የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ አይናለም ተዘራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል ።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ጥር 15/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
Repost from Ministry of Labor and Skills - Ethiopia
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በሚሰጠው የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው የውጭ ሀገር ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ዝርዝር።
ህጋዊ አማራጮችን ብቻ በመጠቀም ደህንነቱ የተረጋገጠ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ተጠቃሚ ይሁኑ!
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ፡
ጥቅምት 16፤ 2017
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols
ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official
ሊንክዲን፡- https://www.linkedin.com/.../ministry-of-labor-skill-fdre/
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
የበጀት፣ ኢኮኖሚ ንግድና የኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኮሌጁን መደበኛ ፣ በኮሌጁ በሚገኙ ፕሮጀክቶች የ2017 በጀት ዓመት የ6 ወር የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አከናወነ፡፡
የኮሌጁን መደበኛ ፣በኮሌጁ በሚገኙ ፕሮጀክቶች የ2017 በጀት ዓመት የ6ወር የእቅድ አፈጻጸም ከዝግጅት ምእራፍ አንስቶ እስከ ግማሽ በጀት አመቱ ማጠቃለያ ድረስ በከፍተኛ ትጋትና የሁሉም ተሳትፎ በጋራ በማካተት እየሰራን እንገኛለን ፡፡ ያሉት የቋሚ ኮሚቴውን ልኡክ ቡድን የተቀበሉትና የኮሌጁን ሁኔታ ለልኡክ ቡድኑ ያብራሩት የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሃዲን አብዱልሃሚድ ሲሆኑ የእቅዱን አፈጻጸም በአብዛኛው ፐርሰንት ያሳካንበት የ6ወር አፈጻጸም ነው ብለዋል፡፡ በተጨማሪም ኮሌጁ በ ቴክኒክና ሙያ አዲሱ እሳቤ አንጻር ከእቅዱ ጋር በማስተሳሰር እየሠራን እንገኛለን ብለዋል። አያይዘውም የከተማው አስተዳደሩ እየሠጠን ያለውን ሃላፊነት ተቀብለን ያለምንም እንከን እየሰራን እንገኛለን ብለዋል።
የቋሚ ኮሚቴውን ልኡክ ቡድን የመሩት ወ/ሮ አይናለም ተዘራ እንዳሉት ኮሌጁ በመደበኛ እንዲሁም በኮሌጁ ባሉ ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ከእቅዱ አንጻር አመርቂ ውጤት የታየበት ነው ያሉ ሲሆን አያይዘውም ተቋሙን ሞዴል እንዲሆን የሚሰራው ስራ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት የተገኙ ልምዶችና ውጤቶች ለሌሎች ተቋማት የማካፈል ስራዎች ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡በመጨረሻም ልኡክ ቡድኑ በኮሌጁ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን የመስክ ምልከታውንና ሪፖርቱን መሰረት በማድረግ የተለያዩ ገንቢ አስተያየቶችን ሰጥተዋል፡፡
የኮሌጁ ኮምኒኬሽን
ጥር 12/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ
+1
አቶ ሮቤል ጌታቸው የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ለከተራና ለጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።
የተከበራችሁ የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።
ከጥምቀት በዓል በዋናነት ትህትናን፣ ይቅርታን እና ታዛዥነት እንማራለን። ስለዚህ በዓሉን ስናከብር ሆነ ከበዓሉ በኋላ እነዚህን ሦስት ነገሮችን በተሰማራንበት መስክ ሁሉ ማሰብና መተግበር ይጠበቅብናል።
በዓሉ ከኃይማኖታዊ በዓልነቱ ባሻገር የአብሮነታችን መገለጫ ከመሆኑም በተጨማሪ የሀገርና የህዝብ ሃብት እንዲሁም የዓለም ቅርስ ሆኖ በዩኔስኮ የተመዘገበ ስለሆነ በዓሉን ስናከብር ሀገራዊ ገፅታን በሚያሳድግ መልኩ ማክብር ይገባናል።
ህዝበ ክርስቲያኑም በዓሉን ሲያከብር የተቸገሩ ወገኖቻችንን በማብላት በማጠጣት እንዲሁም ከሁሉም ህብረተሰብ ጋር ሠላምና አብሮነትን በሚያጎለብት መልኩ ማክበር ያስፈልጋል።
በድጋሚ እንኳን ለከተራና ለጥምቀት በዓል በሠላም አደረሳችሁ። አደረሰን መልካም በዓል።
አቶ ሮቤል ጌታቸው
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ
በ2017 ዓ.ም በአስተዳደሩ ለሚደረገው የቴክኖሎጂና የፈጠራ ስራ ውድድር ከተቋምና ከአጠቃላይ ትምህርት ቤቶች ለውድድሩ የተመለመሉ ተወዳዳሪ አሰልጣኝ መምህራኖች፣ ሰልጣኞች፣ ኢንተርፕራይዞችና ለአጠቃላይ ትምህርት ቤት ተማሪዎችና መምህራን ስለ ውድድሩ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተዘጋጀ፡፡
በዚህም ውድድሩ በዘርፉ ያለውን ችግር ለመቅረፍ መንግስት ባወጣው ፖሊሲና ስትራቴጂ መሰረት ለአሰልጣኞችና ሰልጣኞች፤ ለመምህራንና ተማሪዎች እንዲሁም የኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾችን በአስተዳደሩና በአገር አቀፍ ደረጃ በየአመቱ በማወዳደር ለማበረታታትና ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን በመተካት ረገድ ያለው ፋይዳ ላቅ ያለ ነው፡፡
በተጨማሪ በአስተዳደሩ ያለውን የቴክኖሎጂ እድገት ለህብረተሰቡ በማስተዋወቅ የተያዘውን የቴክኖሎጂ መቅዳትና ማሸጋገር ሂደት ለማቀላጠፍ እንዲያስችል የቴክኒክና ሙያ መር የገበያ ትስስር የሚፈጥር ሲሆን በድሬዳዋ አስተዳደር ደረጃ የካቲት እንዲሁም በአገር አቀፍ ደረጃ መጋቢት ላይ ውድድሩ የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ጥር 10/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
ከጋንቤላ አፔኖ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ እና ከደቡብ ምዕራብ ቴፒ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የተወጣጣ ልኡካን ቡድን በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ልምድ ልውውጥ አደረገ፡፡
ኮሌጆቹ በነበራቸው የልምድ ልውውጥ ጉብኝት መርሃ-ግብር ወቅት የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ በEASE ፕሮጀክት ያለውን የላቀ አፈፃፀም ሂደት በዝርዝር የተመለከቱ ሲሆን በተጨማሪም ኮሌጁ በተለያዩ ተግባራት እያከናወናቸው የሚገኙ ስራዎችም በኮሌጁ ዲኖች አማካኝነት ሰፋ ያለ ገልፃ ተደርጎላቸዋል::
ልኡካን ቡድኑ በኮሌጁ ባደረጉት ምልከታና የተደረገላቸው ገለፃን መነሻ በማድረግ በተካሄደው የጋራ ውይይት ወቅትም የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጁ እያደረገው ያለው እንቅስቃሴ አስደናቂ መሆኑን ገልፀው በተለይም ኮሌጁ በEASE ፕሮጀክት አተገባበር ላይ እያሳየ ያለው የላቀ አፈፃፀም ለሌሎች አቻ ተቋማትም ምሳሌ መሆን የሚችልበት የአፈፃፀም ደረጃ ላይ እንደሚገኝም በውይይታቸው ወቅት አንስተዋል::
በተጨማሪም ልኡካን ቡድኑ በኮሌጁ የሚገኙ የተለያዩ የትምህርትና ስልጠና ክፍሎች እንዲሁም ዎርክ ሾፖችን ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን እዚህ በኮሌጁ ያገኙትን በርካታ ልምዶችንም ቀምረው በመጡባቸው ኮሌጆች ውስጥ ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚሰሩም ገልፀዋል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
ጥር 9/2017 ዓ.ም
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
+5
የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2017 በጀት አመት መደበኛ ስራ የ6ወር አፈጻጸምና የEASTRIP ፕሮጀክት እንዲሁም የSIFA ፕሮጀክት አፈጻጸም ለኮሌጁ የቦርድ አባላት በዛሬው እለት ቀረበ፡፡
የኮሌጁን ሪፖርት ያቀረቡት የኮሌጁ ዲን በአቶ ሰለሃዲን አብዱልሃሚድ ሲሆኑ የኮሌጁ ከዝግጅ ት ምእራፍ እሰከ ትግበራ ምእራፍ ድረስ የተሰሩ ስራዎችንና የተገኙ ውጤቶችን የገለጹ ሲሆን አያይዘውም የቴክኒክና ሙያ አዲሱን እሳቤ ከተቋሙ አሁናዊ ሁኔታ ጋር ያለበትን ሁኔታ ያስረዱ ሲሆን በቀጣይም የሚሰሩ ስራዎችን ለቦርድ አባላት አቅርበዋል፡፡በመቀጠልም የEASTRIP ፕሮጀክት እንዲሁም የSIFA ፕሮጀክት አፈጻጸም በፕሮጀክቶ M&E specialist በአቶ መሳይ ጥላሁን ቀርቧል፡፡
ከሪፖርቶቹ በኋላም በቀረበው የእቅድ አፈጻጸም ላይ የቦርድ አባላቶች የተለያዩ ገንቢ አስተያየቶችን የሰጡ ሲሆን በመጨረሻም በቦርዱ ሰብሳቢ ክቡር አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ የብልጽግና ፓርቲ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ እና የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ቦርድ ሰብሳቢ በኮሌጁ እንዲሁም በፕሮጀክቱ የስራ አፈጻጸም ላይ ማጠቃለያ እንዲሁም የስራ መመሪያ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡
የኮሌጁ ኮምኒኬሽን
ጥር 9/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ እና በድሬዳዋ አስተዳደር ከሚገኘው የስራ አመራር ኢንቲትዩት ጋር በትብብር ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከ ኢንቲትዩቱ ጋር በመተባበር እየሰራቸው ከሚገኙ ተግባራቶች በተጨማሪ ዘላቂነት ባለው መልኩ ውጤታማ ስራዎችን ለማከናወን እንዲረዳ ሁለቱ ተቋማት የመግባቢያ ስምምነቱን ተፈራርመዋል::
የመግባቢያ ስምምነቱን የፈረሙት የኮሌጁ ዲን እቶ ታደለ አሰፋ እንዲሁም የስራ አመራር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አወቀ ለገሰ ሲሆኑ ስምምነቱም በአቅም ግንባታ ስልጠናዎች፣በጥናቶች እንዲሁም በማማከር ዙሪያ በትብብር ለመስራት ያለመ ሲሆን በቀጣይ በመግባቢያ ስምምነቱ መሰረት በማድረግ ወደ ትግበራ እንደሚገባም ትግልፇል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
ጥር 9/2017 ዓ.ም
በኮሌጅ ለሚገኙ አሰልጣኝ መምህራን የተቄም ውስጥ ምዘና አዘገጃጀት ላይ ስልጠና በመሰጠት ተገለጸ በማድረግ ለማዘጋጀት የተሰጠ ግንዛቤ ሲሆን ፤
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴ/ሙ/ት/ስ ዘርፍ የሰልጣኝ ልማትና ተቋማት አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት የ2017 የስልጠና ዘመን በፌደራል ደረጃ በማዕከል በሁሉም ሙያዎች ለተሰሩ የሥርዓተ ትምህርቶች እና የማሰልጠኛ መርጃ መሳሪያዎች በማዘጋጀት የትምህርትና ስልጠናውን ጥራት ለማሻሻል ከሚያስችሉትና ሚያግዙት የተለያዩ ሰነዶችን በማዘጋጀትና በማሰልጠን ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል፡፡
በመሆኑም ሃያ የስልጠና ፕሮግራሞች ላይ ከየትምህርት ክፍሉ ለተውጣጡ አሰልጣኞችና አዘጋጅ አሰልጣኞች የተቋም ውስጥ ምዘና መሳሪያዎችን ለማዘገጀት ከሁለቱ የመንግስት ኮሌጆች የስልጠና አስተባባሪዎች እና ከግል ኮሌጆች ለተውጣጡ አሰልጣኞች የምዘና መሳሪያዎች አዘገጃጀት ስልጠና በመስጠት በማዘጋጀት ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ጥር 9/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የ2016 ዓ.ም ቅድመ ሞዴል የ2017 ዓ.ም ለሞዴል ኢንተርፕራይዞች በኢንተርፕርነርሽፕ እና በቢዝነስ ዴቨሎፕመንት ላይ ከድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ በተጋበዙ መምህራን ሰልጠና ተሰጠ።
በዚህም ስልጠና የኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾችን ባገኙት ዕውቀትና ክህሎት ምርትና ምርታማነታቸውን ለማሳደግና ያላቸውን ልምድ እርስ በእርሳቸው እንዲለዋወጡ ለቀጣይም የዕድገት ደረጃ ለማብቃት አቅማቸውን የሚገነባ ይሆናል።
በመሆኑም ኢንተርፕራይዞቹ በቀጣይ በሞዴል መመዘኛ መሰረት ተመዝነው ከዛ ውስጥ የተሻለ የሚባሉትን ምርጥ ተሞክሮ የሚቀመር ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ታዳጊ መካከለኛ በየአመቱ የሚሸጋገሩትን በመስፈርቱ መሰረት የመለየት ስራ በቀጣይ ተጠናክሮ ይሰራል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ጥር 8/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
በግብርና ዘርፍ በከተማ ግብርና ዶሮ ዕርባታ ስራ ላይ የተሰማሩ የከተማና የገጠር ኢንተርፕራይዞች በጋራ በማቀናጀት ልምዳቸውን እንዲለዋወጡና ስለ ዘርፉ ሞያዊ የሆነ ስልጠና ተሰጠ።
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የኢንተርፕራይዞች ልማት ዳይሬክቶሬት በአስተዳደሩ በከተማና በገጠር ተደራጅተው በስራ ላይ ለሚገኙ ኢንተርፕራይዞች የተለያዩ መንግስታዊ ድጋፎች ይሰጣል ከነዚህም ውስጥ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት የመስሪያና የመሸጫ ቦታ ምችችት፣ የብድር ምችችት እና አቅም የሚገነቡ ስልጠናዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡
በዚህም በአስተዳደሩ ለሚገኙ በዶሮ ዕርባታ ስራ ላይ ለተሰማሩ በከተማም በገጠርም ለተሰማሩ የኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ሞያዊ ስልጠና እንዲያገኙ ተደርጓል በቀጣይም ደግሞ የገበያ ትስስር ለመፍጠርና ሌሎች ያጋጠሟቸው ችግሮች ላይ በመወያየት መፍታት የሚቻልበት አግባብ ላይ መግባባት ተፈጥሯል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ጥር 7/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
