es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Ir al canal en Telegram
1 328
Suscriptores
+224 horas
+87 días
+9530 días
Archivo de publicaciones
በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ስር የሚገኘው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የአሰልጣኝ ልማትና ተቋማት ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት የኮሌጆችን አቅም ለማሳደግና የአሰልጣኝ መምህራንን የክህሎት ክፍተት መሙላት የሚያስችል ተከታታይነት ያለው ስራ በመስራት ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡ በኢትዮጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አሰልጣኝ መምህራን የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠናን ዲጂታላይዝ ለማድረግ የሚያስችሉ ስራዎችን በአይ ሲ ቲ ትምህርትና ስልጠና ክፍል ተግባራዊ ተደረገ፤ ይህም አሰልጣኝ መምህራኑ እርስ በእርስ የክህሎት ሽግግር በማድረግ በተቋሙ የሚሰጡ ስልጠናዎችን በኢ-ለርኒንግ ለመስጠት የሚያስችሉ ግብዓቶችን በራስ አቅም በመስጠት SSD RAM Upgrade  በማድረግና ወርክሾፖችን በማደራጀትና በቀጣይ የሶፍትዌር በተለይም ፎቶሾፕ ስልጠናዎችን ሊያሰጡ የሚችሉ ስራዎች ተሰርቷል፡፡ በዚህም የኮሌጁን አሰልጣኝ መምህራንን አቅም ከመገንባቱ ባሻገር እና በወጪ አንጻር ኮሌጁ ሊያወጣ የሚችለውን ከፍተኛ በጀት የቀነሰ ሆኗል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ጥር 22/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

ለሥራ ፈላጊዎች የማይንድ ሴት ስልጠና ተሠጠ። ስልጠናው የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የሥራ ዕድል ፈጠራና አንድ ማዕከልማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ሥራ ፈላጊዎች ተቀጥሮ መስራት ላይ ብቻ ሳይሆን በግልም ሆነ ተደራጅተው ሥራ እንዲፈጥሩ በሚያነሳሳ መልኩ ቀርቧል። በዚህም ተሳታፊ የሆኑ ከአስተዳደሩ ወረዳዎች የተወጣጡ ሥራ ፈላጊዎች ከዚህ በፊት ተቀጥሮ ለመስራት ብቻ ይጠብቁ የነበሩ ከስልጠናው ባገኙት ግንዛቤ በግልም ሆነ ተደራጅቶ ለመስራት መነሳሳት እንደተፈጠረባቸው ገልጸዋል። ቢሮው በአስተዳደሩ ትኩረት  የተሰጠውን የስራ አጥ ቁጥር ለመቀነስ የተጀመሩ የተለያዩ ስራዎችን በተለይም በኮሪደር ልማቱ እና ከኢንዱስትሪዎች ጋር ግንኙነት በመፍጠርና ሥራ ፈላጊዎች ተደራጅተው ወደ ሰራ እንዲሰማሩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ በመስራት ላይ ይገኛል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ጥር 22/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

#በመካከላችን “አንድ  በቁጥር፤ ብዙ በግብር!” ተወልዶ ያደገው እዚሁ በተወዳጇ ድሬዳዋ ሲሆን ከልጅነቱ በተለያዩ የጥበብ ስራዎች ዝንባሌ ትኩረት በመስጠትና ደስ ስለሚያሰኘው እየሞከረ እንዳደገ ይናገራል፤ እራሱን ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ በውስጡ የሚብላላ ቁጭት እንዳለው ይህም ድሬዳዋ የብዙ ጠቢባን መፍለቂያና መናኸሪያ የመሆኗን ቅርስነት ቅብብሎሽ አንጸባራቂ ሆኖ መመልከት አካልም መሆን መሻቱና ናፍቆቱ መሆኑን ይገልጻል፡፡ ዛሬ ልናስተዋውቃችሁና አብልጠን ልናበረታታው ይዘን የቀረብነው የሥራና ክህሎት ቤተሰብ አሰልጣኝ መምህር ዳንኤል በላይ ይባላል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክሎህት ቢሮ ስር በሚገኘው የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የአይ ሲ ቲ ትምህርትና ስልጠና ክፍል ውስጥ በአሰልጣኝ መምህርነት ዜጎችን እያበቃ የሚገኝ ግን በቃ የማያውቀው የባለ ብዙ ሞያዎችና ተሰጥኦ ባለቤት ድንቅ ቤተሰብ ነው፡፡ እናም ጥበበኛው በቁጥር አንድ ሰው ነው ግና በክህሎትና ግብር ብዙ ሆኖ አሰልጣኝ መምህር ነው ስትሉት ሰዓሊ ሆኖ ታገኙታላችሁ እኛ ለማበረታታትና ለመደገፍ ቅንነታችንን አብዝተን እንግለጥ እንጂ ከሙዚቃው መንደር ብትሄዱ እርሱ በዚያም ይገኛል መቼ በዚህ ብቻ ተገድቦ የተለያዩ የቅርጻቅርጽ ስራዎችን ሲሰራ ከተፈጥሮ ውበት ጋር አፍቃሪየ መናኝ ሆኖ በንመለከተው አንታዘበው እናበረታታው ነገ ብዙ ክህሎት ላላቸውና ለሚሰሩ አዕምሮዎችና እጆች አርዓያ ይሆናል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ጥር 21/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+4

photo content
+9

የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኤጀንሲ በ2017 በጀት ዓመት በመጀመሪያው ግማሽ ዓመት የደረሱበትን የዕቅድ አፈፃፀም ደረጃ በመገምገም የታዩ ጠንካራ ጎኖችን ለማስቀጠል እንዲሁም በአፈፃፀም ላይ ውስንነት የታየባቸውን ተግባራት ለይቶ አፋጣኝ መፍትሄዎችን ለማስቀመጥና የዓመታዊ ዕቅድ አፈፃፀም ውጤትን በላቀ ደረጃ መፈጸም የሚያስችል አቅም ለመፍጠር በቢሮው እና በስሩ ከሚገኙ ኮሌጆች አመራርና ባለሞያዎች ጋር ውይይት አካሄደ፡፡ በአጠቃላይ በሪፖርቱ ከተመላከቱ ስራዎች መካከል በ3 የመንግስት እና በ5 የግል ኮሌጆች የቅበላ መጠን ስንመለከት የአዲስ ሰልጣኞች ቅበላ ወንድ 2319 ሴት 2662 በድምሩ 4981 የአዳዲስ ሰልጣኞች ቅበላ የተከናወን ሲሆን በዚህም በእቅድ ከተያዘው 4924 የቅበላ መጠን አንፃር 4981 የተንነ ሆን የ101.2 በመቶ አፈፃፀም ያለው ሲሆን የነባር ሰልጣኞች ቅበላ ወንድ 2087 ሴት 3164 በድምሩ 5251 የነባር ሰልጣኞች ቅበላ ተከናውኗል ይህም በእቅድ ከተያዘው 5380 የቅበላ መጠን አንፃር የ97.6 በመቶ አፈፃፀም ሲኖረው በገበያ ተኮር አጫጭር ስልጠናዎችን 2689 ገበያ ተኮር አጫጭር ስልጠናዎችን ለማከናወን ታቅዶ 1201 ወንድ 1456 ሴት ጠቅላላ 2657 ስልጠናን ማከናወን የተቻለ ሲሆን ይህም ከግማሽ ዓመቱ ዕቅድ አንፃር የ98.8 በመቶ አፈፃፀም መድረስ ተችሏል፡፡ ቢሮው ከከሌጆች ጋር ዕቅዱን በመናበብ የመከለስ፣ የድጋፍና ክትትል ስራውን ማጠናከር፣ የመደበኛ ሰልጣኝ ማብቃት ላይ ኢንስፔክሽን በየጊዜው በማድረግ ዞኒንግ እና ዲፈረንሼሽን ላይ በዚህ በጀት አመት በተዘጋጀው መውጫ ዕቅድ ወደ ተግባር በመግባት፤ የከተማዋን ነዋሪ ችግር የሚፈቱ ከዚህ ቀደም ተሰርተው የተቀመጡትን በማሻሻል መጠቀም እንዲሁም ትምህርትና ስልጠናውን በተሻለ መልኩ ለመምራት የሚያስችሉ መመሪያዎችን በማዘጋጀት ወደ ስራ ማስገባትና ዲጂታላይዜሽን ላይ የተጀመሩ ስራዎችን በማጠናከር ወደ ልህቀት ማሳደግ ላይ በቀጣይ ስድስት ወራት ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ የቢሮው ም/ኃላፊ እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ገልጸዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ጥር 20/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

በሶማሌ ኢሳ ማህበረሰብ ዘንድ ሰላምን በማስፈን እና አብሮነትን ለማጠናከር ለበርካታ መቶ ዓመታት የቆየው ”ሔር ኢሴ “ ቃላዊ ህግና የዳኝነት ስርዓት በዩኔስኮ በወካይ የማይዳሰስ የሰው ልጆች ቅርስነት
+7
በሶማሌ ኢሳ ማህበረሰብ ዘንድ ሰላምን በማስፈን እና አብሮነትን ለማጠናከር ለበርካታ መቶ ዓመታት የቆየው ”ሔር ኢሴ “ ቃላዊ ህግና የዳኝነት ስርዓት በዩኔስኮ በወካይ የማይዳሰስ የሰው ልጆች ቅርስነት መመዝገቡን ተከትሎ በድሬዳዋ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል በድሬዳዋ አለማቀፍ ስቴዲየም በሺዎች የሚቆጠሩ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ባህላዊ አልባሳትን በመልበስ እየታደሙበት የሚገኘው የእውቅና መርሃ-ግብር መካሄድ ጀምሯል። በዝግጅቱ ከጅቡቲ ፣ ከሱማሊያ ፣ ከሱማሌ ብሔራዊ ክልል መንግስት የመጡ ልኡካን ቡድኖች እና ተጋባዠ እንግዶች እየታደሙ ነው ። በትዕግስት ቶሎሳ ፎቶ፦ አገኘሁ ሸዋረጋ

#ዜና በሶማሌ ኢሳ ማህበረሰብ ዘንድ ሰላምን በማስፈን እና አብሮነትን ለማጠናከር ለበርካታ መቶ ዓመታት  የቆየው ”ሔር ኢሴ “ ቃላዊ ህግና የዳኝነት ስርዓት በዩኔስኮ በወካይ የማይዳሰስ የሰው ልጆች ቅርስነት መመዝገቡን ተከትሎ በድሬዳዋ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል። ዛሬ ከሰዓት በኋላ በድሬዳዋ ወጣቶች አካዳሚ የኢሳ እናቶች ያዘጋጁዋቸው የማህበረሰቡ ባህላዊ ምግቦች ቅምሻን ለመታደም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በስፍራው ተገኝተዋል ፡፡ የማህበረሰቡን አኗኗርና ባህል እና የአመጋገብ ስርዓት ጭምር እንዲያጸባርቅ ተደርጎ በተዘጋጀው የባህላዊ ምግቦች ትርኢትና ቅምሻ ላይ ከጅቡቲ ፣ ከሱማሊያ እና ከሱማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትና የመጡ እንግዶች እና ልኡካን ቡድን አባላት የታደሙ ሲሆን ለህዝቦች የእርስ በእርስ ከቀራረብ  ሚናው ከፍተኛ ከመሆኑም በላይ ወጣቶች ባህልና ወጋቸውን እንዲማሩም አስተዋጾው የጎላ መሆኑም ተወስቷል ፡፡ ይህ ዝግጅት ነገ ቅዳሜም በድሬዳዋ አለማቀፍ ስቴዲየም በሺዎች የሚቆጠሩ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ባህላዊ አልባሳትን በመልበስ የሚታደሙበት የእውቅና መርሃግብር እንደሚካሔድ እና ምሽት ላይ በወጣቶች አካዳሚ በሚዘጋጅ ደማቅ የሙዚቃ ኮንሰርት ማጠቃለያ እንደሚደረግ ከወጣው መርሐ ግብር መረዳት ተችሏል፡፡

photo content
+9

"ሔር ኢሴ" በተባበሩት መንግስታት የትምህርትና የባህል ተቋም /ዩኔስኮ/የዓለም ቅርስ ሆኖ መመዝገቡን ምክንያት በማድረግ  ከዛሬ ጀምሮ በድሬዳዋ  በዓሉ በተለያዩ መርሀ ግብሮች እየተከበረ ይገኛል ። የሶማሌ ኢሳ ማህበረሰብ ፍትሃዊ ያልተጻፈ መተዳደሪያ ሕግ “ሔር ኢሴ” በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የሰው ልጆች ወካይ ዓለም አቀፍ የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርሶች ዝርዝር ውስጥ መመዝገቡን ምክንያት በማድረግ በዛሬው ዕለትም የፓናል ውይይት ተካሂዷል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የበጀት፣ ኢኮኖሚ ንግድና ኢንድስትሪ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ የድሬዳዋ አስተዳደር  ሥራና ክህሎት ቢሮን የ2017 በጀት አመት የመጀመሪያው 6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም  ግምገማ  እና የመውጫ ውይይት አካሄደ ። ========================== የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች በስራቸው የተደለደሉትን  የአስተዳደሩ ተቋማት ዕቅድ አፈፃፀም ለመገምገም ያለመ  የመስክ ምልከታ  ሲያደርጉ የቆዩ  ሲሆኑ በዛሬው ዕለትም የድሬዳዋ  አስተዳደር ምክር ቤት የበጀት፣ ኢኮኖሚ፣ ንግድ ና ኢንዱስትሪ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ  ክትትልና ቁጥጥር ከሚያደርግባቸው   የአስተዳደሩ ተቋማት መካከል አንዱ የሆነውን የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ በመገኘት  የ2017 በጀት አመት የመጀመሪያውን የ6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማና የመውጫ ውይይት አድርጓል። ቋሚ ኮሚቴው  በቢሮው ስር ያሉ ተጠሪ ተቋማትና ፕሮጀክቶች ከክህሎት ልማትና ስራ ዕድል ፈጠራ ጋር ተያያዝነት ያላቸውን  ተግባራት አፈፃፀም ያሉበትን ደረጃ  ባለፉት ቀናት የመስክ ምልከታ ሲያደርጉ ቆይቶ በዛሬው ዕለትም ከቢሮው ማኔጅመንት አባላት ጋር በተቋሙ የግማሽ አመት ዕቅድ አፈፃፀም ዙሪያ ሰፋ ያለ ውይይት በማድረግ በአፈፃጸም ሂደት የታዩ ጠንካራ ጎኖች ተጠናክረው  እንዲቀጥሉና በውስንነት የተለዩ ጉዳዮች መታረም እንዳለባቸው  የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ የመውጫ ግብረ መልስ ተሰጥቷል። በዚህም የቢሮው ም/ኃላፊና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ለቋሚ ኮሚቴው በክህሎት ልማት በመደበኛና አጫጭር ስልጠናዎች፣ በከተማ እና ገጠር ስራ ዕድል ፈጠራ፣  በኢንተርፕራይዝ ልማት ፣ በአሰሪና ሰራተኛው ዘርፍ እንዲሁም የካፒታል ፕሮጀክቶች አፊፃፀም ባለፉት ስድስት ወራት የተሰሩ ስራዎችን እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እንዲሁም በቀጣይ የታሰቡ ጉዳዮችን ጠቅሰው ማብራሪያ ሰጥተዋል። በአጠቃላይ ቢሮው በ2017 ዓ.ም የ6 ወር ዕቅድ  አበረታች አፈፃፀሞች መታየቱንና በዘርፉ በውስንነት የተለዩትን እንዲታረሙ በማድረግ በቀጣይ በተለይ የሥራና ክህሎት ምክር ቤትን በመጠቀም ሁሉም የዘርፉ ባለድርሻ አካላት  የተጀመረውን ቅንጅታዊ አሰራር አጠናክሮ በማስቀጠል በስፋትና በጥራት የክህሎት ልማትና የከተማና የገጠር ስራ ዕድል ፈጠራ ላይ ትኩረት ሰጥተው መስራት  እንዳለባቸው የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ አይናለም ተዘራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል ። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ጥር 15/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በሚሰጠው የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው የውጭ ሀገር ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ዝርዝር። ህጋዊ አማራጮችን ብቻ በመጠቀም ደህንነቱ የተረጋገጠ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ተጠቃሚ ይሁኑ! ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ፡ ጥቅምት 16፤ 2017 በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE ቴሌግራም፦ https://t.me/fdre_mols ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official ሊንክዲን፡- https://www.linkedin.com/.../ministry-of-labor-skill-fdre/

የበጀት፣ ኢኮኖሚ ንግድና የኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኮሌጁን መደበኛ ፣ በኮሌጁ በሚገኙ ፕሮጀክቶች የ2017 በጀት ዓመት የ6 ወር የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አከናወነ፡፡ የኮሌጁን መደበኛ ፣በኮሌጁ በሚገኙ ፕሮጀክቶች የ2017 በጀት ዓመት የ6ወር የእቅድ አፈጻጸም ከዝግጅት ምእራፍ አንስቶ እስከ ግማሽ በጀት አመቱ ማጠቃለያ ድረስ በከፍተኛ ትጋትና የሁሉም ተሳትፎ በጋራ በማካተት እየሰራን እንገኛለን ፡፡ ያሉት የቋሚ ኮሚቴውን ልኡክ ቡድን የተቀበሉትና የኮሌጁን ሁኔታ ለልኡክ ቡድኑ ያብራሩት የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሃዲን አብዱልሃሚድ ሲሆኑ የእቅዱን አፈጻጸም በአብዛኛው ፐርሰንት ያሳካንበት የ6ወር አፈጻጸም ነው ብለዋል፡፡ በተጨማሪም ኮሌጁ በ ቴክኒክና ሙያ አዲሱ እሳቤ አንጻር ከእቅዱ ጋር በማስተሳሰር እየሠራን እንገኛለን ብለዋል። አያይዘውም የከተማው አስተዳደሩ እየሠጠን ያለውን ሃላፊነት ተቀብለን ያለምንም እንከን እየሰራን እንገኛለን ብለዋል። የቋሚ ኮሚቴውን ልኡክ ቡድን የመሩት ወ/ሮ አይናለም ተዘራ እንዳሉት ኮሌጁ በመደበኛ እንዲሁም በኮሌጁ ባሉ ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ከእቅዱ አንጻር አመርቂ ውጤት የታየበት ነው ያሉ ሲሆን አያይዘውም ተቋሙን ሞዴል እንዲሆን የሚሰራው ስራ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት የተገኙ ልምዶችና ውጤቶች ለሌሎች ተቋማት የማካፈል ስራዎች ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡በመጨረሻም ልኡክ ቡድኑ በኮሌጁ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን የመስክ ምልከታውንና ሪፖርቱን መሰረት በማድረግ የተለያዩ ገንቢ አስተያየቶችን ሰጥተዋል፡፡ የኮሌጁ ኮምኒኬሽን ጥር 12/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ