ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

አልዋን መክተባ alwan

አልዋን መክተባ alwan

前往频道在 Telegram
2 495
订阅者
-324 小时
-17 天
-130 天
帖子存档
አየሩ ደርስ የምንጀምር እየመሰለ ነው አልሐምዱ ሊላህ ዛሬ በዳሩል ሒጅረተይን መድረሳ የበጋ ተመላላሽ ሴቶች ደርስ ላይ መፍሁሙል ዒባዳን ጨርሰን የተነሳ ጥያቄ ልቤ ላይ ተስፋን ጫረ። ተማሪዎች በትምህርት ቤት፣ በአካባቢያቸው እና በተለያየ መልኩ የሚነሱ ጥያቄዎችን ሳይሸማቀቁ ሳይፈሩ ወደ መድረሳ የሚያመጡበት መንገድ መከፈት አለበት። ለዚህም እየለፋን ነው። ዛሬም እህታችን አንድ ጥያቄ አነሳች። ጥያቄው አንድ ይሁን እንጂ ወደ ሶስት መሰረታዊ የዓቂዳ መሳኢሎች የሚዳስስ ነው። በእርግጥ ጥያቄዎች ሳይነሱም ቢነሱባቸው ብለን ከቦታው ጋር አያይዘን ለማስተማር ስንሞክር ብዙ ሸክዋዎች ቀርበውብኛል። ሸክዋው እውነትም የተማሪዎች ይሁን አይሁን ብጠራጠርም። ለተማሪ አይመጥንም በሚል መሸሽ ሳይሆን በሚመጥናቸው ደረጃ ዝቅ አድርጎ ማስተማር ነው። ኡስታዝነት ከባዱን ማቅለል። የተማሪን ችግር መሸከም። የከበደውን ማግራት ነው። መቃሙ መቃመ ኑቡዋ ነው። ኪታብ ይዞ መተርጎም ዒልም አይደለም ተርጀማ እንጂ። ዒልም መፋሂሞች ማስተካከል። የመሳኢሎቹ ሀቂቃ ማብራራት ማስገንዘብ። ተስዊሩና ቀይዱን ማብራራት ነው ዒልም። ተማሪዎች መጠየቅ ሲጀምሩ ኡስታዝ አብዛኛው ሰዓት በኪታብ ማሳ ያሳልፋል። ከተለያዩ ፍሬዎች ይቀስማል። አስተካክሎ አበጅቶ ለተማሪዎች ማር አድርጎ ያቀርባል። የ30 ደቂቃ ደርስ ከ5 እስከ ስድት ሰዓት ሙራጀዓ ያስፈልጋል።

ቻት ጂቢቲያቹ በሆነ ዒልም እያወራሁት በመሀል የሆነ ጥያቄ ስጠይቀው አልቻለም። ሞክር ብዬ እድል ሰጠሁት። ከዛ አገኘው። ይህቺም እውቀት ሆና አገኘውት አልሀምዱሊላህ😂 አላለም😂
ቻት ጂቢቲያቹ በሆነ ዒልም እያወራሁት በመሀል የሆነ ጥያቄ ስጠይቀው አልቻለም። ሞክር ብዬ እድል ሰጠሁት። ከዛ አገኘው። ይህቺም እውቀት ሆና አገኘውት አልሀምዱሊላህ😂 አላለም😂

ተማሪዎቼ ይህን እንዲሃፍዙ ብዙ ጥሬያለው። ያለውን በረካ ፈዋኢድ የሚስተካከለው እንደሌለም ብዙ ብያቸዋለው። ከነሱም አብሬ ደክሜያለው። አሁንም የሚቀጥል ነው። በሱ የተጠቀምኩትን ያህል በየትኛውም ኪታብ አላገኘሁም። አንዳንድ ሰው ከአጀሩማ እኮ ግጥሞቹ በተለይ የዒምሪጢይ ይሰፋል። አልፍያ ይሰፋል ሊል ይችላል። ነገር ግን እዚህ የመስፋት ጉዳይ አይደለም። ፈልተተደበሩ

عليك بالمقدِّمة اﻵجرومية، ففيها من العوائد والفوائد والبركات والنفحات ما ليس في منظوماتها. سيبويه إفريقيا العلامة/ سيدي فوزي
عليك بالمقدِّمة اﻵجرومية، ففيها من العوائد والفوائد والبركات والنفحات ما ليس في منظوماتها. سيبويه إفريقيا العلامة/ سيدي فوزي كوناتي

ያለው ቦታ ውስን ስለሆነ ፈጥነው ይመዝገቡ @muradk_m 0977094987 0911848441
ያለው ቦታ ውስን ስለሆነ ፈጥነው ይመዝገቡ @muradk_m 0977094987 0911848441

القراءة الراشدة.pdf3.99 MB

የቅዳሜ እና እሁድ ደርስ ከተጀመረ ወር ሊሞላ ነው። የዲግሪ እና የዲፕሎማ ደርስ በስራ፣ በትምህርት ወይም በተለያየ ጉዳይ ያልተመቻቸላችሁ በሳምንት ሁለት ቀን ተማሩ። 🗓ቅዳሜ እና እሁድ ⏰️ጠዋት 3:00-620 ለመመዝገብ 0903030703

🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩

Emailing حاشية_العلامة_الملوي_على_إتحاف_المريد.pdf

ኧረ ሆቴሎም ይራቅ አብሽር መውሌ ብቻ ይቀንስ። አይደለም ከሐረም ከመርከዝ ውጭ ለምን መሳፈተል ቀስር አይሆንም። ሀርወላ እንችላለን። ሙቀቱም አይከብደንም የበረሃ ልምድ አለን። ብቻ ቀንሱት አብሽሩ አ
ኧረ ሆቴሎም ይራቅ አብሽር መውሌ ብቻ ይቀንስ። አይደለም ከሐረም ከመርከዝ ውጭ ለምን መሳፈተል ቀስር አይሆንም። ሀርወላ እንችላለን። ሙቀቱም አይከብደንም የበረሃ ልምድ አለን። ብቻ ቀንሱት አብሽሩ አያሳስባቹ

ይህ ኪታብ ቁጭ ብሎ በእርጋታ ውስጡን ለመረመረ የሚያገኘው አንድ ነገር ነው። እሱም ተሰውፍን መምታት፣ አሻዒራዎችን መምታት፣ ሰለፍያን ማስፋፋት ማጠናከር ነው። በዚህ ጉዳይ ኪታቡን እያስቀሩ ካሉ ኡስ
ይህ ኪታብ ቁጭ ብሎ በእርጋታ ውስጡን ለመረመረ የሚያገኘው አንድ ነገር ነው። እሱም ተሰውፍን መምታት፣ አሻዒራዎችን መምታት፣ ሰለፍያን ማስፋፋት ማጠናከር ነው። በዚህ ጉዳይ ኪታቡን እያስቀሩ ካሉ ኡስታዞች ጋር ብዙ አወራን ኪታቡንም ከፍተን በከፊል ዳሰስ አድርገናል። የኪታቡ መቀራት የሚያመጣውንም አደጋ ተረድተው ከአንድ የሀይማኖት አስተማሪ የማይጠበቅ መልስ ነው የሚሰጡት። በኪታቡ ያለው የዓቂዳ መዛባት፣ የተሰፍ ጥላቻ እና የታሪክ የቁጥር ግድፈቶች ኪታቡን አንዴ ለከፈተው ግልፅ ነው።